Friday, January 31, 2014

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ አካባቢ ጥቃት ፈፀመ

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የአገራችን ኢትዮጵያን ዳር ድንባር ለሱዳን ለማስረከብ ሽር ጉድ እያለ የሚገኘውን የወያኔን አገዛዝ ጸረ-አገርና ጸረ-ህዝብ እንቅስቃሴ በመቃወም በመተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ዘባጭ ባህር በተባለ ቦታ ከወያኔው 24ኛ ክፍለ- ጦር ጋር በጥር 21- 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሠዓት ላይ ባደረገው ውጊያ 14(አስራ አራት) ገድሎ 12(አስራ ሁለት) አቁስሏል።Ethiopian freedom fighters
በመተማና አካባቢው በተደጋጋሚ በአርበኛው ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የወያኔው ቅጥረኛ ሠራዊት ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው እየፈረጠጠ መሆኑ ሲታወቅ በደረሰበትም ጉዳት ማካካሻ ይሆነው ዘንድ ሰላማዊውን ነዋሪ በእናንተ ምሽግነት ነው እየተመታን ያለነው በሚል እንግልት እያደረሱበት መሆኑ ታውቋል።
በተያያዘ ዜና በጭልጋ ወረዳ ጫቁ የተባለ አካባቢ ነዋሪዎች ከብት፣በግና ፍየል በአካባቢው የወያኔ ታጣቂዎች እየታረደ እየተበላባቸው መሆኑ ታውቋል።
በዚሁ አካባቢና አጎራባች ወረዳዎች የወያኔው ተላላኪዎች ተደጋጋሚ ንብረትን የመዝረፍ ሂደት የተቆጣው ነዋሪ ለምንድን ነው ንብረታችንን የምትዘረፉት ምን አደረግናችሁ ብለው ሲጠይቁ እናንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ፣መንገድ መሪዎች እንዲሁም ስንቅ አቀባዮች ናችሁ የሚል ምክንያት የሰጧቸው መሆኑ ታውቋል።
ሕዝቡም እኛ የአርበኛው አባልም ደጋፊም አይደለንም ከፈለጋችሁ እነሱን ተከታትላችሁ መዋጋት ትችላላችሁ እኛን ምን አድርጉ ነው የምትሉ? ሲሉ ምሬታቸውን ቢገልፁም እንግልቱ እንዳላበራ ዘጋቢያችን ካደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።
ዘጋቢያችን አክሎ እንደገለፀው የወያኔው ተላላኪዎች በሕዝቡ ላይ እያደረሱ ያለው እንግልት ያስቆጣቸው ብዛት ያላቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኛች ግንባር ሠራዊትን እየተቀላቀሉ መሆኑን አስታውቋል።
በሌላ ዜና የአማራ ክልል ፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆነው ሙሉጌታ ወርቁ የተባለው ግለሰብ በክልላችን ቢሮዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰዎች ተሰግስገዋል በሚል ምክንያት ሰሞኑን በየወረዳው ፅ/ቤት የማፅዳት ዘመቻ በሚል ከፍተኛ ስብሰባ እያደረገ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተደጋጋሚ ጥቃት እያሰጋው የመጣው ሆድ አደሩ የአማራው ክልል ባልስልጣናት ሕዝቡን በተለያየ ምክንያት ማሰቃየቱ ሳያንሰው የራሱ ታማኝ የሆኑ ቅጥረኞቹ ላይ እምነት በማጣት የሚያደርገውም የጠፋበት መሆኑ ግልፅ እየሆነ መምጣቱን አመላካች እንደሆነ የዚሁ ችግር ሰለባ ልንሆን እንችላለን ያሉ ወገኖች ጠቁመዋል።
በይበልጥ አማራዉን በማይወክሉት የወያኔ አገልጋዮች እየተሰቃየው ያለው ሕዝቡ ሲሆን ፣ እነሱም ሕዝቡ ከጎናችው አለመኖሩን በመረዳታቸው የተፈጠረው ክፍተት በፈጠረባቸው ጭንቀት የመንግስት ሠራተኛውንም ሆነ ነጋዴውን ማመሱን እንደቀጠሉበት ለማወቅ ተችሏል።

በጎንደር ክ/ሃገር ሳንጃ ወረዳና አካባቢው ሕዝብን ሲያሰቃይ የነበረው የልዩ ሃይል አዛዥ ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ተገደለ

ግለሰቡ የተገደለው በጥር 21-2006 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች ማሰሮ ደንብ የተባለ ቦታ በጥይት ተደብድቦ ቆስሎ ወዲያውኑ ወደ ጎንደር ቸቸላ ሆስፒታል ቢወሰድም በማግስቱ ማለትም በጥር 22-2006 ዓ,ም ህይወቱ አልፏል።
ይህ ግለሰብ በወረዳው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የአርበኞች ደጋፊ ናችሁ በሚል ሲያሰቃይ የነበረ ሲሆን፣ ብዙ ንፁሃን ግለሰቦችን በድርጅቱ ደጋፊነት ስም እየፈረጀ እንደገደለ ፣ እንዳሰረና እንዲሰደዱ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ። ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ግለሰቡ ከድርጊቱ ታቅቦ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር ካልሆነ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድበት የፅሁፍ መልዕክት የደረሰው ቢሆንም ሊታረም ባለመቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰርጎ ገቦች እርምጃ እንዲወስዱበት ተደርጓል።
በጎንደር አካባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ እርምጃ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ሲወሰድ የአካባቢውን ሕዝብ ማንገላታቱ የተለመደ ቢሆንም ሻለቃ ቀለሙ ክብረት ከሞተበት ከትናንት ጀምሮ ግን በህዝቡ ከፍተኛ ስቃይ እያደረሰበትና ገዳዮቹን ታውቃላችሁ እናንተ ናችሁ እየደበቃችሁና ቀለብ እየሰፈራችሁ የምታስጨርሱን በሚል ብዙ ሰዎች እንደታሰሩ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ በበኩሉ ወደፊትም ቢሆን ወያኔና ተላላኪዎቹን ከዚህም በከፋ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ አስታውቆ ሕዝቡም ከመሬቱና ከንብረቱ እየተፈናቀለ መኖሩ ያበቃ ዘንድ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ይህን አፋኝ ስርዓት ለመገርሰስ የበኩሉን አስተዋፅዖ ማበርከት እንዳለበት ጥሪውን አስተላልፏል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር
 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10873/

Saturday, January 25, 2014

በሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ገፅታ አሁን ደግሞ ተባብሷል ይለናል Human Right Watch በ2014


በሰብአዊ መብት አያያዝ አደጋ ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ገፅታ አሁን ደግሞ ተባብሷል ይለናል Human Right Watch በ2014 የዓለም የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ፡-ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም. መሞታቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ የተተካው አዲሱ አመራር ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች እንደሚያደርግ ተጥሎ የነበረው ተስፋ ተዳፍኗል፤ በ2013 ዓ.ም ተጨባጭ የሆነ የፖሊሲ ለውጥ አልታየም፡፡ ይልቁንም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሃሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት እና በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ላይ የጣሉትን ጥብቅ ገደብ ማስፈጸማቸውን የቀጠሉበት ሲሆን የሲቪል ማህበራትን እና ነጻ መገናኛ ብዙሃንን እንቅስቃሴ ለማዳከም አፋኝ ሕጎችን ይጠቀማሉ፤ግለሰቦችንም ፖለቲካዊ መነሾ ያላቸውን ክሶች በመመስረት የጥቃት ዒላማ ያደርጋሉ። መንግስት በሃይማኖታዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ መግባቱን የተቃወሙ ሙስሊሞች ዓመቱን ሙሉ በጸጥታ ሃይሎች የዘፈቀደ እስር፣ እገታ፣ ድብደባ እና ሌሎች ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በሐምሌ ወር 2012 ዓ.ም. የታሰሩት 29ኙ የተቃውሞው መሪዎች የፍርድ ሂደት ከጥር ወር 2013 ጀምሮ ለህዝብ፣ ለመገናኛ ብዙሃን፣ እና ለቤተሰብ አባላት ዝግ ተደርጓል፡፡ እጅግ አወዛጋቢና መሠረታዊ ግድፈት ያለባቸውን ድንጋጌዎች በያዘው የሃገሪቱ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ መሰረት ጥፋተኛ የተባሉ የተቃዋሚ መሪዎች እንዲሁም አራት ጋዜጠኞች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከሃገር ውስጥ በሚገኝ ገቢ እና ከውጭ በሚመጣ እርዳታ በሚደገፉ ስፋት ያላቸው የልማት ፕሮግራሞች አፈጻጸም ምክንያት የአንዳንድ ማህበረሰብ ተወላጅ ነዋሪዎች ያለበቂ ምክክር ወይም ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ከመኖርያቸው እንዲፈናቀሉ ይደረጋል፡፡ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው አንስተው ወደ ሌላ ቦታ ለማስፈር ሃይል፣ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይፈጸማሉ፤ ለምሳሌ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚገኙ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት የኖሩበት መሬት መንግስት ለሚያካሂደው የስኳር መስኖ ልማት ይፈለጋል በሚል መፈናቀላቸው እንደቀጠለ ነው። በሰላም የመሰብሰብ ነጻነት ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ህዝብ ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆነውን ቁጥር የሚይዙት የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላት ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ አድርገዋል፡፡ የተቃውሞው መነሻ ምክንያት መንግስት በእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ውስጥ እና በአዲስ አበባ በሚገኘው የአወሊያ መስጊድ ላይ ይፈጽማል የተባለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ነው፡፡ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎቹን ለመግታት መንግስት ሃይል ተጠቅሟል፤ የዘፈቀደ እስር እና ድብደባ በተቃዋሚዎቹ ላይ ፈጽሟል፤ እነዚህ ሕገ ወጥ ተግባራት በሀምሌ 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው በጥቅምት 2012ዓ.ም በጸረ ሽብርተኝነት አዋጁ መሰረት ክስ በተመሰረተባቸው 29 ታዋቂ የተቃውሞ እንቅስቃሴው መሪዎች ላይም ተፈጽመዋል፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደቱን መገናኛ ብዙሃንን፣ ዲፕሎማቶችን እና የቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ህዝብ እንዳይከታተለው ከጥር ወር ጀምሮ ዝግ አድርጎታል፡፡ አንዳንዶቹ ተከሳሾች በእስር ላይ እያሉ ተገቢ ያልሆነ አያያዝ እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል። እንዲሁም እንዳንዶቹ ተከሳሾች ለሁለት ወራት ያህል የሕግ አማካሪ ወይም ጠበቃ ያላገኙበት ሁኔታና ከቤተዘመድ ጋር ለመገናኘት የነበረውን ችግር ጨምሮ የፍርድ ሂደቱ በሕግ በተቀመጡ ስርዓቶች አግባብ መካሄዱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ በርካታ ግድፈቶች ተፈጽመዋል።
በተከሳሾቹ ላይ በመንግስት ቴሌቪዥን ውንጀላ እና ክስ ያለበት መረጃ በማስተላለፍ መንግስት ተከሳሾቹ ከፍርድ ውሳኔ በፊት ነጻ ሆነው የመገመት መብታቸውን የሚጋፋ ድርጊት ፈጽሟል። መንግስታዊ በሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) ጃሃዳዊ ሃረካት የሚል ርዕስ ያለው ፕሮግራም በጥር ውስጥ የተላለፈ ሲሆን ፊልሙ ከተከሳሾቹ ውስጥ አምስቱ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት በቁጥጥር ስር እያሉ የተቀረጸ ክፍል አካቷል። ፕሮግራሙ የተቃውሞው መሪዎችን እንደ አሸባሪዎች በመቁጠር የሙስሊሞቹን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከአክራሪ የእስልምና ሃይሎች ጋር አነጻጽሯል፡፡ እስሩ እንዳለ ቢሆንም በ2013ም ተቃውሞው ቀጥሏል፡፡ በነሃሴ ወር መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የረመዳን ወር መጨረሻ የሆነው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሚከበርበት ዕለት የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የአይን እማኞች በአዲስ አበባ በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች ተሰማርተው እንደነበረ የገለጹ ሲሆን ታማኝ ምንጮች ደግሞ ሰልፈኞቹን ለመበተን ፖሊስ ከተገቢው በላይ ሃይል እንደተጠቀመ እና ለጊዜውም ቢሆንም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳትፎ አዲስ መጭ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር ሰላማዊ ሰልፍ አካሂዷል፤ ሰልፉ በስምንት ዓመት ጊዜ ውስጥ በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው፡፡ የጸጥታ ሃይሎች የሰማያዊ ፓርቲን ጽህፈት ቤት ጥሰው በመግባት በርካታ ሰዎችን በማሰራቸውና የፓርቲውን ንብረቶች በመውረሳቸው ምክንያት ፓርቲው በነሀሴ ወር ሊያካሂድ አቅዶ የነበረው ሰልፍ ተሰርዟል። ሰማያዊ ፓርቲ ቀደም ብሎ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ ለመንግስት አቅርቦ የነበረው ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ነበር። የዘፈቀደ እስር እና ጎጂ አያያዝ የዘፈቀደ እስር እና በእስር ቤቶች የሚደረግ ጎጂ አያያዝ ከፍተኛ ችግር መሆኑን ቀጥሏል፡፡ ተማሪዎች፣ የተቃዋሚ ጎራ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች እና ሌሎችም የመሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት መብታቸውን መግለጽ የሚፈልጉ ሰዎች በየጊዜው በዘፈቀደ ይታሰራሉ፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካ ምክንያት የሚያዙ ሰዎች ላይ በተለይም እነዚህ ሰዎች ከክስ ወይም ከፍርድ ሂደት በፊት በሚታሰሩበት እና ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው አዲስ አበባ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል ጎጂ አያያዝ ይፈጸማል፡፡ በሃይል በማስገደድ ከእስረኞች መረጃ፣ የእምነት ቃል እና ሃሳብ ለማውጣጣት እስከ ማሰቃየት የሚደርስ ጥቃት እና ሌሎች ጎጂ አያያዞች የሚፈጸሙባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው። የተያዙ ሰዎች በተለይ ክስ ከመመስረቱ በፊት ብዙ ጊዜ የህግ አማካሪ እንዳያገኙ ይደረጋል፡፡ ያልተገባ አያያዝ የተፈጸመባቸው እስረኞች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከፍርድ ቤቶች የሚያገኙት መፍትሄ እጅጉን ውሱን ነው፤ አንዲሁም እስር ቤቶች እና ሌሎች የማቆያ ቦታዎች በገለልተኛ መርማሪዎች በመደበኛነት እንዲጎበኙ አይፈቀድም፡፡ ከመንግስት ጋር ቀረቤታ ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የተወሰኑ እስረኞችን እና እስር ቤቶችን የጎበኘ ቢሆንም በማንኛውም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ወይም ሌላ ድርጅት መደበኛነት ያለው የክትትልና የምርምራ ስራ አይሰራም። በሃምሌ ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የአውሮፓ ፓርላማ የልዑካን ቡድን አባላት አስቀድሞ ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የነበረ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚገኘውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይጎበኙ በባለስልጣናት ተከልክለዋል።
ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በ2009 ዓ.ም የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ ከወጡ በኋላ በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በከፍተኛ ደረጃ ተገድቧል፡፡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጁ በዓለም ላይ ካሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ከወጡ በጣም አፋኝ ህጎች አንዱ ነው፡፡ በሰብዓዊ መብቶች፣ መልካም አስተዳደር፣ ግጭት አፈታት፣ እና የሴቶች፣ የህጻናት እና አካል ጉዳተኛ ሰዎች መብቶች ዙሪያ አድቮኬሲ የሚሰሩ ድርጅቶች ከጠቅላላ ገቢያቸው 10 በመቶ በላይ እርዳታ ከውጭ ምንጮች መቀበል እንደማይችሉ ይደነግጋል፡፡ በዚህ ሕግ ሳቢያ እጅግ መልካም ስም የነበራቸው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ይሰሩ የነበረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የቀነሱ ሲሆን ሌሎቹም ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ስራዎችን መስራት ጭራሹኑ አቁመዋል። በርካታ ታዋቂ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች በተፈጠረባቸው ስጋት ምክንያት ሃገሪቱን ለቀው ተሰደዋል፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በከፍተኛ የመንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፤ እንዲሁም በርካታ ጋዜጠኞች ራሳቸው ላይ ቅድመ ምርመራ ያካሂዳሉ፡፡ መንግስትን በፅኑ የሚተቹ ድረ ገጾች እና ጦማሮች በመደበኛነት ይዘጋሉ እንዲሁም የውጭ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች በተደጋጋሚ ይታፈናሉ። ለነጻ የሃገር ውስጥ ጋዜጦች የሚሰሩ ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ተከታታይ ጥቃት እና ማስፈራራያ እንደቀጠለ ነው።
የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ የፖለቲካ ተፎካካሪዎችን ለማጥቃት፣ ነጻ ሃሳብን ለማፈን፣ እንዲሁም ጋዜጠኞችን ዝም ለማሰኘት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በሐምሌ ወር 2012ዓ.ም የሽብር ጥቃት ለመፈጸም በማሴር እና አሸባሪ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ በሚል በተከሰሰው ጋዜጠኛ እና ብሎገር እስክንድር ነጋ ፈንታ ላይ የተሰጠውን የ 18 ዓመት የእስር ቅጣት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በግንቦት ወር 2013 እንዲጸና ወስኗል። እስክንድር ‘የፔን’ የመጻፍ ነጻነት ሽልማትን በ2012 ተሸልሟል፡፡ የፍትህ ጋዜጣ ጋዜጠኛ የሆነችው ርዕዮት ዓለሙ ገቤቦ በጻፈችው ጽሁፍ ምክንያት በጸረ ሽብር ህጉ በተጠቀሱ ሶስት ክሶች ተከሳ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባታል፡፡ በመጀመርያ ተፈርዶባት የነበረው 14 ዓመት በይግባኝ ወደ 5 ዓመት የተቀነሰላት ቢሆንም የቀረው የአምስት ዓመት ፍርድ ላይ ያቀረበችው ይግባኝ በጥር ወር ውድቅ ተደርጎባታል፡፡ ርዕዮት ከፍተኛ ዝና ያለውን የ2013 የዩኔስኮ ጉሌርሞ ካኖ የዓለም ፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸልማለች፡፡ የሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚያካሂዳቸውን የተቃውሞ ሰልፎችን ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል እንዲሁም በዘፈቀደ ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከህትመት ውጭ የሆነው የሙስሊሞች ጉዳይ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ሰለሞን ከበደ በጥር ወር የታሰረ ሲሆን የጸረ-ሽብር ህጉን አዋጅ በመጣስ ክስ ተመስርቶበታል፡፡ የጋዜጣው የቀድሞ ዋና አዘጋጅ ዩሱፍ ጌታቸው በ2012 በተመሳሳይ ህግ ተከሷል፡፡ ሌሎች በርካታ ጋዜጠኞች በ2013 ከኢትዮጵያ ተሰደዋል፤ ይህም ሃገሪቱን በስደት ላይ ባሉ ጋዜጠኞች ብዛት ከዓለም ሶስተኛ ሃገር አድርጓታል፡፡
ከልማት ፕሮግራሞች ትግበራ ጋር በተያያዘ የሚፈጸም በሃይል ማፈናቀል የኢትዮጵያ መንግስት ከሚያካሂደው የሰፈራ መርሃ ግብር ጋር በተያያዘ አንደሚፈፀሙ የሚገለጸውን በደሎች መንግስትም ሆነ የለጋሽ ማህበረሰብ አባላት በበቂ ሁኔታ መመርመር አልቻሉም፡፡ የመሰረታዊ አገልግሎቶችን አቅርቦት ለማሟላት በሚል ምክንያት በዚህ መርሃ-ግብር 1.5 ሚሊዮን የገጠር አካባቢ ነዋሪዎች ከመኖርያ አካባቢያቸው ተነስተው በሌሎች ቦታዎች እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ ይሁንና መርሃ ግብሩ ተግባራዊ በተደረገበት በመጀመሪያው ዓመት በጋምቤላ ክልል አንዳንድ ቦታዎች የተካሄደው ሰፈራ በሃይል የተደረገ ሲሆን ድብደባ እና የዘፈቀደ እስር የተፈጸሙባቸው አጋጣሚዎችም ነበሩ። ከዚህም ሌላ የማስፈሩ ስራ የተካሄደው ከተነሺዎቹ ጋር በቂ ምክክር ሳይደረግ እና በቂ የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም ነው። የዓለም ባንክን የአሰራር ተጠያቂነት የሚከታተለውና ከባንኩ ነፃ የሆነው የቁጥጥር ቡድን በስደት ላይ የሚገኙ የአኙዋክ ብሔረሰብ አባላት ባንኩ ጋምቤላ ውስጥ የራሱን የአሰራር ሁኔታዎች ጥሷል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ በማለት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ የዓለም ባንክ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ቦርድ በሐምሌ 2013 ተቀብሎታል። ይህ ሪፖርት በሚዘጋጅበት ወቅት ምርመራው በመካሄድ ላይ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ሸለቆ የሚኖሩ 200 ሺህ ተወላጅ ነዋሪዎችን ከመሬታቸው ላይ በማስለቀቅ በ245 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የስኳር ልማት ስራ ማከናወኗን ቀጥላለች። እነዚህ በጥምር ግብርና እና ከብት እርባታ የሚተዳደሩ ተወላጅ ነዋሪዎች ለዘመናት ከኖሩበት መሬት ተፈናቅለው በሰፈራ መርሃ ግብር አማካኝነት በቋሚ መንደሮች እንዲሰፍሩ ተደርጓል።
ዋና ዋና ዓለምአቀፍ አካላት ኢትዮጵያ ከውጭ ለጋሾች እና ከአብዛኞቹ የቀጠናው ጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት አላት፡፡ ይህ ጠንካራ ግንኙነት የተመሰረተው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በምታደርገው አስተዋጽኦ፣ ከምዕራብ ሃገራት ጋር በጸጥታ ጉዳይ ላይ ባላት ትብብር እና የተወሰኑ የሚሊኒየም የልማት ግቦችን በማሳከት ረገድ ባስመዘገበችው እድገት ምክንያት ነው፡፡ ሃገሪቷ ያላት ይህ ጠንካራ ግንኙነት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በዝምታ እንዲያልፍ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ በ2013ም ኢትዮጵያ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያላትን የአደራረዳሪነት ሚና የቀጠለች ሲሆን ወታደሮቿም በአወዛጋቢው አቢዬ ግዛት የሰፈነውን አስተማማኝ ያልሆነ ጸጥታ በማስጠበቅ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደሶማልያ ዘልቀው መግባታቸውን የቀጠሉ ቢሆንም ወታደሮቹ በዚያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል አካል አይደሉም። ኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው ድጋፍ ከለጋሾች ማግኘቷን የቀጠለች ሲሆን በ2013 ያገኘችው ድጋፍ 4 ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል፡፡ የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች አንደመሆናቸው መጠን ለጋሽ ሃገራት እጅግ አስከፊ ሆነውን የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ አስመልክቶ ግን ዝምታን መርጠዋል። ከልማት መርሃ ግብሮች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ተፈጽመዋል የተባሉ በደሎችን አስመልከቶ የሚቀርቡ ክሶችን ለመመርመር የሚወስዱት እርምጃም እጅግ ውሱን ነው።
ግብጻዊያን ኢትዮጵያ በምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት ከናይል ወንዝ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወደ ግድቡ ይቀየሳል የሚል ስጋት ስለገባቸው በ2013 ዓ.ም. የኢትዮጵያ እና የግብጽ ግንኙነት የበለጠ ሻክሯል። 85 በመቶ የሚገመተው የናይል ወንዝ ውሃ ምንጭ ኢትዮጵያ ስትሆን ግብጽ ደግሞ ለሚያስፈልጋት ማንኛውም የውሃ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በናይል ወንዝ ላይ ጥገኛ ነች፡፡ ግድቡ 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ከአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ይሆናል፡፡ የግድቡ ግንባታ የተጀመረው በ2012 ሲሆን በ2018 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከምዕራባዊያን ለጋሽ ሀገራት በተጨማሪ ቻይና፣ ህንድ እና ብራዚል የተለያዩ ከፍተኛ መጠን ላላቸው የልማት ስራዎች የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል። ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ የግል ኢንቨስትመንት እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን በ2013 የግብርና ንግድ፣ ሃይድሮኤሌክትሪክ፣ ማዕድን ማውጣት እና ነዳጅ ፍለጋ ኢንቨስትመንት ስራዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ነው።የግብርና ንግድ ኢንቨስትመንት በዋናነት ከህንድ፣ ከመካካለኛው ምስራቅ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመጡ ሲሆን የመሬት ዋጋው ዝቅተኛ መሆን እና ለጉልበት የሚከፈለው ዋጋ አነስተኛነት ባለሃብቶቹን የሚስብ ሆኗል። እንደ ሌሎቹ በርካታ ትልልቅ የኢትዮጵያ የልማት ፕሮጀክቶች ሁሉ እነዚህ መርሃ ግብሮች ሲተገበሩ ሰዎችን ከመሬታቸው በሃይል የማፈናቀል ተግባር ሊፈጸም ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ።
 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2014/01/21/422-2/

አልበሺር እና የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ጥረት


የሱዳኑ ፕሬዚደንት ኦማር ሀሰን አልበሺር በኤርትራ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት ከማጎልበት ጎንለጎን በአካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገለጸ። ኣልበሺር ከኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት የሶስት ቀናት ቆይታ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ
በተለይም የኢትዮ ኤርትራን የሰላም ንግግር ስመልክቶ መነጋገራቸውን ምንጮች ኣመልክቷል።
የኣሁኑ ውይይት በሁለቱ ተደራዳሪ ኣገሮች በኩል ሊቀርቡ በሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነበርም ተብሏል።
የሱዳኑ መሪ ኦመር ሓሰን ኣልበሺር፣ ባለፈው ሳምንት በኤርትራ ያደረጉት የሶስት ቀናት ጉብኝት፤ የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ኬርቲ ለዜና ወኪሎች እንዳስረዱት፤ የሁለቱን ኣጎራባች ኣገሮች ግንኙነት በማጎልበት ላይ ያተኮረ ነበር። የኣልበሺር ጉብኝት ባለፈው ህዳር ወር የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የተደረገ መሆኑን የጠቀሱት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኬርቲ በዚህ ግንኙነት ሁለቱ መሪዎች ከዚህ ቀደም የተፈረሙ የውል ስምምነቶች ሊተገበሩ ስለሚችሉባቸው ዝርዝር ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ኣስረድቷል።
ባለፈው ማክሰኞ ኤርትራ ሲገቡ ደማቅ ኣቀባበል የተደረገላቸው ኣልበሺር ከኣስመራ ውጪ ያሉ ኣንዳንድ ከተሞችንም የጎበኙ ሲሆን በኤርትራ 21ኛ ዓመት የነጻነት በዓል ላይም ተገኝተው ነበር። ሁለቱ መሪዎች፣ ኣልበሺር እና ኢሳያስ፣ የዔርትራው ገዢ ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች የበላይ፣ የማነ ገ/ዓብ፣ ለዜና ምንጮች እንደገለጹት፣ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታን ጨምሮ በበርካታ አካባቢያዊ እና ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ ኣንዱና ዋናው የመሪዎቹ አጀንዳ የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ንግግር ነው ተብሏል።
በኖርዌይ ኣገር፣ ስታቫንገር ዩኑቨርሲቲ፣ የፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ዶ/ር ግሩም ዘለቀ እንደሚሉትም የኣልበሺር የኣስመራ ጉብኝት የሰላም ንግግሩ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን በሁለቱ ወገኖች በኩል ሊቀርቡ በሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
እርቀ ሰላም መውረዱ ለሁለቱም ኣገሮች በተለይ ም ደግሞ ዶ/ር ግሩም እንደሚሉት ለኤርትራ ከፍተኛ ጠቀሜታ ነው ያለው።
ከኤርትራ በኩል በጉዳዩ ላይ እስከ ኣሁን ይፋ የሆነ መግለጫ ባይኖርም በኢትዮጵያ በኩል ግን፤ የጠ/ሚኒስትሩ ቃ/አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ እንደሚሉት፣ ቀደም ሲል የተቀመጡት ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ለመደራደር ግን መንግስት ዝግጁ ነው።
በዚህ የሰላም ንግግር፤ ከተሳካ ማለት ነው፤ ተጠቃሚዎቹ በዋናነት ሁለቱ ኣገሮች ቢሆኑም ዶ/ር ግሩም ዘለቀ እንደሚሉት ደግሞ ኣልበሺርም ቢሆኑ በግልም ጭምር ተጠቃሚ መሆናቸው መዘንጋት የለበትም።
ከተገንጣዩዋ የደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር ካለባቸው የግዛት ይገባኛል ውዝግብ በተጨማሪም የዳርፉር ቀውስን ጨምሮ በሰሜን ኩርዱፋን እና በብሉ ናይል ግዛቶችም በውስጥ ችግሮች ተጠምደው የሚገኙት ኣልበሺር ምንም እንኳን ከኣፍሪካ ህብረት በኩል አንጻራዊ ተቀባይነት ቢኖራቸውም በምዕራባውያኑ ዘንድ እንደ ወንጀለኛ መፈረጃቸው ይታወቃል። በዚሁ የተነሳም ዓለም ዓቀፉ ፍ/ቤት ICC የእስር ማዘዣ እንደቆረጠባቸው ይገኛሉ።
ጃፈር ዓሊ
ኂሩት መለሰ
dw.de

ግራና ቀኝ ጠፋን! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡
Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam
በአደባባይ የሚጽፉ ሰዎች ሁለት ነገሮችን ለይተው መገንዘብና ለሌሎችም ሲየያስተላልፉ ለይተው ማስተላለፍ አለባቸው፤ አንዱ የሆነና የተረጋገጠ ሁነት ነው፤ይህንን ሳይበርዙና ሳይከልሱ እንዳለና እንደተገኘ ማስተላለፍ ግዴታ ነው፤ ሁለተኛው የራስ አስተያየት ነው፤ የጠራውንና የነጣውን አውነት ከጎደፈ የግል አስተያየት ጋር አጋብቶ ማቅረብ ወይ አለማወቅ ነው፤ አውቀው ከሆነም ለማታለል ከመሞከር የሚቆጠር ነው፤ በአለንበት ዘመን አብዛኛውን ጊዜ የምናየው ፊደሎቹን ማወቅ እንደሙሉ እውቀት ይቆጠራል፤ ወይም በሌላ አነጋገር ፊደልን ማወቅ የመጻፍ ችሎታን ይሆናል፤ ይህ ትልቅ ስሕተት ነው፤ ፊደሎችን ማወቅ ትልቅና መሠረታዊ የእውቀት ጎዳና ላይ መግባት ነው፤ ጎዳናው ግን በጣም ረጅም ነው፤ በእውቀት ጎዳና ላይ መግባት የእውቀት ባለቤት ከመሆን ጋር እንዳይደባለቅ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ በአገራችን ፊደልን ማወቅ ሌላም አደጋ አለው፤ ፊደልን ማወቅ ከሥልጣን ጋር ሲጋባ የሚያስከትለውን ውድቀት ከአንዴም ሁለቴ አይተናል፤ እያየንም ነው፤ ስለዚህም ፊደል ኃላፊነትን ያመጣል፤ አለዚያ በአለፉት ሠላሳ ዓመታት ያየነው ውድቀት እየተከበረ ይቀጥላል፡፡
መጻፍ እንደመናገር ሊቆጠር ይቻላል፤ሆኖም በመጻፍና በመናገር መሀከል ትልቅ ልዩነት አለ፤ በንግግር ላይ ከሰዎች በሚቀርበው ጥያቄም ሆነ ተቃውሞ እንዲህ ማለቴ ነው ብሎ የተናገሩትን እዚያው ለማረምና ለማስተካከል ይቻላል፤ በተጻፈ ነገር ላይ እንዲህ ዓይነቱ ወዲያው የመታረም ዕድል የለም፤ ስለዚህም ለመጻፍ በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው፤ ከላይ እንደተገለጸው ፊደልና ሥልጣን ሲጋቡ ሰንደቅ ዓላማው ጨርቅ ነው ከማለትም ሊያልፍ ይችላል፤ ለምሳሌ የደርግን የትርፍ ቤቶች አዋጅ ብንመለከተው ‹‹ትርፍ ቤት›› ሲል ትርፍን እንተወውና ‹‹ቤት›› ለሚለው ትክክለኛ ትርጉም አልሰጠም፤ ስለዚህም በጭራሮ የተያያዘ ምንም ‹‹ቤት›› የሚያሰኘው (መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት፣ መታጠቢያ ቤት፣ … የሌለው) በሃምሳ ሳንቲም የሚከራይ ነገር ‹‹ቤት›› ተብሎ በሺህ ብር ከሚከራይ ቤት ጋር ተወረሰ! ያፈረ የለም እንጂ አሳፋሪ ነው!
እንዲህ ዓይነቱ ችግር ከየት የሚመጣ ነው? አንድ አጠቃላይ የአስተሳሰብ ችግር አለ፤ ለየት ያለውን ከጅምላው፣ ግዙፉን ከረቂቁ፣ አንዱን ከብዙው ያለጥንቃቄ ማደባለቅ በአማርኛ በጣም የተለመደ እየሆነ ነው፤ የአስተሳሰብ ችግር ነው፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ (አበሻና ሆድ የሚለው ጽሑፍ ባሕር ተሻግሮ የአበሻን ነገር-ዓለም ትቶ የተጠበሰ ውሻ (ሆት ዶግ) የሚበላውንም አስቀየመውና ሌሎች ስለአበሻ የጻፍኋቸውን ተውኩት እንጂ አበሻና መናገር የሚለው በተለይ ለባሕር ማዶው ዘሎ-ጥልቅ ተስማሚው ነበር፤) በማናቸውም ነገር ላይ ለመቀባጠር በጣም ኃይለኛ ምኞት አለው፤ አንዱ ያስተሳሰብ ችግር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፤ ሳያስቡና ሳይጨነቁ አፍ እንዳመጣ ከመናገር ልማድ ጋር የተያያዘ ነው፤ አሁን ደግሞ የጎሠኛነት ሥርዓት ካመጣብን ጣጣ ዋኖቹ የአስተሳሰብ ችግሮች እነዚህ ናቸው፤  የቡድን መብትን መሠረታዊ አድርጎ የግለሰብን መብት ጨፍልቆ የተነሣው የወያኔ የጎሣ ሥርዓት ከሃያ ዓመታት በኋላ በስንት ጥረት የደረሰበት አሁንም የተዛባ ድምዳሜ የቡድን መብትንና የግለሰብ መብትን ጎን ለጎን አቁሞ እኩል ናቸው ማለትን ነው፤ ለውጡ የተጣራ ባይሆንም ሃያ ዓመታት መፍጀቱ የወያኔን የመማር ፍጥነት የሚያመለክት ነው፤ የሥልጣን ጉልበትና የሥልጣን ምኞት ተጽእኖ እንደአንድነት ያለውንም የፖሊቲካ ፓርቲ ፐሮግራሙን እንዲለውጥና የግለሰቦችንና የቡድን መብቶች በአንድ ደረጃ ላይ እንዲያስቀምጥ ተደርጎአል፤ ከቡድን ውስጥ ግለሰቦች ሁሉ ሙልጭ ብለው ሲወጡ ስለቡድን መብት የሚያወራ ምን እንደሚባል እንጃ! ከቀኝ ወደግራ የዞረ? ወይስ ከግራ ወደቀኝ? ወይስ … ቀኝ ፖሊቲካ ባዶ ከረጢት ይዞ ይቀራል።
በተደጋጋሚ እንዳየሁት ለግለሰብ መብቶች የቆመ ቀኝ-ዘመም፣ ለቡድን መብቶች የቆመ ግራ-ዘመም የሚባል ይመስላል ይህ ስሕተት ነው።
ቀደም ሲል የታወቀው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እኔን ቀኝ-ዘመም እያለ ጽፎ ሳይ ይህ ሰው በአውነት አንድ መዝገበ ቃላት ማየት አቅቶት ነው? ወይስ እኔን በተለየ ዓይን ለማየት ከመፈለግ የተነሣ ነው? ወይስ የሲአይኤውን መልክተኛ ፖል ሄንዜን ሰምቶ ነው? የሱ ጎሣ አባል መሆንንና አለመሆንን እኔ የምመርጠውና የምወስነው አይደለም፤ ታምራት በኢትዮጵያዊነት ወይም በዜግነት ዓይን ሊመለከተኝ አለመቻሉም የእኔ ጥፋት አይደለም፤ ሁሉም ቢቀር በሰውነት ደረጃ ሊያየኝ ይችል ነበር፤ ይህንንም አልቻለም፤ እንግዲህ ወይ እኔ ሰው አልሆንኩለትም፤ ወይ እሱ ወደሰውነት ደረጃ አልደረሰም፤ በታምራት ነገራ ቀኝ-ግራ መጋባት እንደኔው ጥርጣሬ ውስጥ ገብቶ የነበረው ክፍሉ ሁሴን ወደጥናት ተመልሶ የታምራትን ስሕተት አረጋገጠ፤ እኔም እንዲሁ አደረግሁና የታምራት ነገራን ግራ መጋባት አረጋገጥሁ፤ ታምራት ነገራ የጎሣ ቀኝ ገብቶት ግራ ፖሊቲካ ቀኝ ሆኖበታል! ቀኝ-ግራ ፖሊቲካ በጎሣ አባልነት የሚገኝ ወይም የሚታጣ ይመስለዋል፤ ዘር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ሀብትና ሌላ ማናቸውንም ነገር ከቁም-ነገር ሳይቆጥሩ ለማንም ሰው በሰውነቱ ብቻ ማግኘት የሚገባውን መብት እንዲያገኝ ቆሞ መከራከር ለታምራት እንግዳ ነገር ይመስለኛል፤ ገና እሱ ሳይወለድ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቲያትር በተደረገ ስብሰባ ላይ ለምን የኢትዮጵያ ራድዮ በኦሮምኛ አይናገርም? በማለት ጌታቸው ኃይሌ ጋር ሆነን የማስታወቂያ ሚኒስቴር ሰዎችን ሞግተን  ነበር፤ ይህ ለታምራት የቀኝ ፖሊቲካ ነው፤ የሱ ጎሣ-ዘመም ፖሊቲካ ግራ መሆኑ ነው! ጎሠኛነት ምን ጊዜም የትም ቦታ እንደግራ ፖሊቲካ ተፈርጆ አያውቅም።
አሁን ደግሞ ሰሎሞን አብርሃም ይህንኑ የታምራት ነገራን ስሕተት ለመድገም የዳዳው ስለመሰለኝ በዝምታ ለማለፍ አልፈለግሁም፤ ሰሎሞን (liberalism) የሚለውን የአንግሊዝኛ ቃል በባሕርዩ የሌለበትን ትርጉም ሊሰጠው ይዳዳዋል፤ ሰሎሞን አብርሃም ሊጽፍበት የተነሣው ጉዳይ በእኔ ግምት በጣም ወቅታዊና አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን የግል ስሜትን ከሁነት ጋር፣ ያልተጣራ የተውሶ ሀሳብን (‹‹ፊዩዳሊዝም፣ ሊበራሊዝም››…) ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር በማያያዝ አስተሳሰቡን ያጎደፈው ይመስለኛል፤ ያነሣው ጉዳይ በተለይም እንደሱ ላለ ፖሊቲከኛ ከስሜተኛነትና ከወገንተኛነት የጸዳ ቢያደርገው (‹‹ወግ አጥባቂ፣ቀኝ አክራሪ›› ..)፣ወይም ደግሞ ያልተጣራ (‹‹የሊበራል ዴሞክራሲን ርዕዮተ ዓለም የሚከተሉ ይመስላሉ፤›› እያለ በጎን ከሚጎሽም የጸዳውን እውነት ፊት ለፊት እያቀረበ ድካማቸውን ቢተነትን የሚጠቅም ይሆን ነበር።
ግራና ቀኝ ፖሊቲካ የሚባለውን ከጎሣ ፖሊቲካ ጋር ለማገናኘት የሚፈልጉ ሰዎች ወጣቶችን ወደአስከፊ ስሕተት እንዳይመሩ መጠንቀቅ ያለባቸው ይመስለኛል፤ የጎሣ ሥርዓትን የሚቃወሙትን ወገኖች በሌላ መንገድ ለመቋቋም ቢሞክሩ የተሻለ ነው፤ በጎሣ ክፍፍል ማመን ሌላው ቀርቶ በሰውነት ደረጃ ለመሰለፍም ያስቸግራል፤ ለማናቸውም የጎሣ ፖሊቲካን ከግራ ፖሊቲካ ማዛመዱ እሳትና ውሀ ነው።


 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10757/

የኢዜአ ማደናገሪያ ዜና – አንድ ተጨባጭ ምሳሌ

ታደሰ ብሩ
በቅድሚያ የሚከተለውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን (ኢዜአ) ዜና አጣጥሙልኝ።
…
ጎባ ጥር 10/2006
በባሌ ዞን   ከእርሻ ስራ በተጓዳኝ በንብ ማነብ ፓኬጅ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘታቸውን የዞኑ የእንስሳት ሀብት ልማትና ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የእቅድና ግምገማ በለሙያ አቶ ታዬ ኣጋ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለፉት ስድስት ወራት የማር ምርቱን ለአካባቢው ገበያ ያቀረቡት ከ89ሺ 200 የሚበልጡ አርሶ አደሮች ናቸው ።
የማር ምርቱን ለአካባቢያቸውና ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ ከሆኑት አርሶ አደሮች መካከል ከ21 ሺህ 699 የሚበልጡት ሴቶች መሆናቸውንም አብራርተዋል ።
በዞኑ ዘጠኝ ደጋማ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች የማር ምርቱን የሰበሰቡት ከ100ሺ ከሚበልጡ ባህላዊ፣ የሽግግርና ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች በመጠቀም እንደሆነ አብራርተዋል ።
በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት ለገበያ የቀረበው የማር ምርት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ1ሺህ ኪሎ ግራም ብልጫ ያለው እንደሆነም አስታውቀዋል ።
ጽህፈት ቤቱም የዞኑን አርሶ አደሮች የማር ምርትና ምርታማነት በሁለት እጥፍ ለማሳደግ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን ለአርሶ አደሮቹ በማሰራጨት ላይ እንደሆነም ጠቁመዋል ።
…
ይህንን ዜና  እዚህ ያገኙታል።
ዜናውን በጥንቃቄ ያላነበበ ሰው የተለመደ ልማታዊ ዜና በመሆኑ ምንም የሚያስደንቅ ነገር አያገኝበትም። ሆኖም ትንሽ ስሌት ብጤ እንጨምርበት።
ሀ.  ከሽያጭ የተገኘው ገንዘብ 53.7 ሚሊዮን:   ብር 53, 700, 000
ለ.  የአምራቾቹ ብዛት:                          89, 200 ገበሬዎች
ሐ.  የፈጀባቸው ጊዜ:                           6 ወር
ከዚህ በመነሳት የሚከተለውን ማስላት ይቻላል።
የአንድ አምራች አማካይ የሽያጭ ገቢ:           53, 700, 000  ÷ 89, 200 = ብር 602.02
የአንድ አምራች አማካይ ወርሃዊ የሽያጭ ገቢ:    602.02/ 6 = ብር 100.34
በዚህ “ድንቅ ስኬታማ ፓኬጅ” አንድ ገበሬ በወር በአማካይ የሚያገኘው የሽያጭ ገቢ ብር 100.34 ነው። በአማካይ ማለት ደግሞ ከዚህም በታች የሚያገኙ ብዙ አሉ ማለት ነው። በተለይ አንድ ብርቱ “ልማታዊ” ገበሬ ካለ የሌሎቹ ሰብስቦ ነው የሚወስደው። ለማንኛውም ግን የገበሬዎች ምርታነት እኩል ነው ብለን እናስብና ስሌታችንን በአማካይ እንቀጥል።
አንባቢ እንደሚያውቀው የሽያጭ ገቢ የተጣራ ገቢ (ወይም ትርፍ) አይደለም። ገበሬዎች ከዚህ ፓኬጅ ምን ያህል እንደተጠቀሙ ለማስላት ወጪያቸው መሰላትአለበት። ከዜናው በመነሳት በአዕምሮዓችን የሚመጡ ወጪዎች የሚከተሉት ናቸው።
  1. እያንዳንዱ ገበሬ በአማካይ በወር ምን ያህል ሰዓታት በዚህ ሥራ ላይ አዋለ?
  2. “ከ100ሺ ከሚበልጡ ባህላዊ፣ የሽግግርና ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች” በሥራ ላይ ውለዋል። የእነዚህ ቀፎዎች የእልቀት ዋጋ (depreciation) በወር  ምን ያህል ነው?
(በነገራችን ላይ ይኼ ራሱ ሌላ ዜና የሚወጣው ነገር ነው። በአገሪቱ ትልቁ የዜና አገልግሎት በትላልቅ ፎንት ዜና የሠራለት “ፓኬጅ” ለአንድ ገበሬ በአማካይ ሁለት ቀፎ እንኳን ሳያቀርብ ነው።  ለ 89,200 ሰው 100, 000 ማለትም በአማካይ ለአንድ ገበሬ 1.12 ቀፎ ነው!)
  1. ማሩ በምን ታሸገ? (ስልቻም ከሆነ የስልቻው ዋጋ)
  2. ማሩ በምን ተጓጉዞ ገበያ ደረሰ?
የገበሬን ድካም ለሚያውቅ ወጪዎቹ እነዚህ ብቻ እንደማይሆኑ ይረዳል፤ ግን ይብቃኝ።
ይህንን ሁሉ ስናስብ ነው ዜናው እጅግ አስገራሚ የሚሆነው።  የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዜና አቀራረብ ጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን አንባቢን ያሳፍራል። ይህንን ዜና ሳነብ የተሰማን ስሜት እፍረት ነው። ይህ ነው የኢዜአ ልማታዊ ጋዜጠኝነት!!!
የኢዜአ ስኬትን የማጋነን ፍላጎት፤ ማለትም የተገኘው ገንዘብ እና በፓኬጁ የተሳተፉ ገበሬዎችን ብዙ አድርጎ የማቅረብ ፍላጎት፣ ብዙ ሲካፈል ብዙ ትንሽ የሚሆን መሆኑ ያስረሳው ይመስለኛል።
ጥር 11 ቀን 2006 ዓ.ም
ፀሐፊውን ለማግኘት tkersmo@gmail.com

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10757/

“ወደው አይስቁ” (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል።  የሚናገሩትን አያውቁትም።  የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ።  እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣  የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም።  “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል።  ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል።  እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም።  እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ።  የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው።  ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው።  “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።
አጼ ምኒሊክ አምስት ሚሊዮን ጡት ቆርጠዋል ሲሉን ግን፤ ስሌቱ ላይ የቤት ስራቸውን በደንብ የሰሩት አይመስልም። በአጼ ምኒሊክ ዘመን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ቁጥሩ ስምንት ሚሊዮን ነበር።  የአምስቱ ሚሊየን ህዝብ ጡት ከተቆረጠ፣ በዘመኑ ወንዶቹም ጡት እንደነበራቸው ያመላክታል። ግን ያንን ሁሉ ጡት እንዴት ሊቆርጡት እንደቻሉ ተናጋሪው አላብራሩም።  ስልጣኔን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት አጼ ምኒሊክ በመጀመሪያ ያደረጉት የጡት መቁረጫ ማሽን ማስገባት መሆኑን ከጉግል ላይ በቅርቡ ሊገኝ ይችላል።
ጉግል፣ ጉግል፣ጉግል፣ጉግል፣…… እያለ መነጋገርያውን ለቆ ወረደ -  የምኒሊክን አዲስ ታሪክ የሚያስተምረው።
“ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል።… ይህንንም በቅርቡ ይፋ በሚሆነው ጥናት ታገኙታላችሁ… ።”  የሚል ሌላ ተናጋሪ መድረኩን ይዞ ሲናገር ከማርስ የመጣ ፍጡር ነበር የመሰለን።
ጨርቁን ጥሎ እርቃኑን መንገድ ለመንገድ የሚሄድ፤ ወይንም ደግሞ እጅና እግሩ በሰንሰለት የታሰሩ ሰው ስናይ፤  በተለምዶ ይህ ሰው አብዷል እንላለን – ውጭውን ብቻ አይተን። ጥሩ ልብስ ለብሰው በስነልቦና እና በአእምሮ መታወክ የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ እብዶች እንዳሉ ብዙውን ግዜ እንዘነጋለን።  እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች በቀን ቅዠት የሚሰቃዩ፣ የስነምግባርና የሞራል እስረኞች በመሆናቸው አእምሯቸው ይታወካል። በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የአጼ ምኒሊክ ጣእረ ሞት እየመጣ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነው።
ፓልቶክን ከሰባት አመታት በኋላ መስማቴ ነው።  ይህን ትልቅ መድረክ፣  አንዳንዶች ታሪክ ሰርተውበታል። ሌሎች ታሪክ ሲያወሩበት ሰንብተዋል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ታሪክ የሚያጎድፉ ጉዶች ይዘውታል። ከሰባት አመታት በኋላ የኛ ፓልቶክ ሽቅብ ሳይሆን ቁልቁል አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ቢገርመኝም፤ በአንጻሩ ግን እንደ አዝናኝም እየሆነ መምጣቱን አልጠላሁትም።
እንደሰማነው የፓልቶክ ርእሱ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አልተቀየረም። የዛሬውም መነጋገርያ ርእስ ዳግማዊ ምኒሊክ ናቸው። እኚህ መሪ ካለፉ እነሆ መቶ አመት ሆናቸው። “የሞኝ ለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ!”  እንዲሉ አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ስለ አጼ ምኒሊክ አውርተው ሌሊቱንም ይመለሱበታል። ዛሬ ግን ወሬውም፣ ስድቡም ያለቀባቸው ይመስላል። ዛሬ ስለጀኖሳይድ እያወሩ አይደለም። ይልቁንም ጀኖሳይድ እያወሩ ነበር። ወንጀሉን ራሳቸው በቃል እየፈጸሙት…።
ሌላኛው ተናጋሪ ተራውን ጠብቆ መነጋገርያውን ያዘ። የተለመደውን የአጼ ምኒሊክን አጽም ከመቃብር እየጠራ ካወገዘ በኋላ፤ እንዲህ ሲል ተናገረ። “…አበበ ቢቂላን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ አድርገው ታላቅ በደል ፈጽመውበታል።”
መቼም ወደው አይስቁ።  እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች  እንኳ አይፈረድባቸውም። ገና ሃገር ሲለቅቁ የለቀቁ ስለሆኑ ለክርክርም አይመቹም።  ”አበበ ቢቂላ በሮም እና በቶክዮ ላይ የሮጠው በአጼ ምኒሊክ ዘመን ነው።” ብሎ ከሚከራከር ሰው ጋር ሙግት መግጠም እብደት ይሆናል።
“የቁቤ ትውልድ ነን።” የሚል ሌላ ታናጋሪ ደግሞ መጣ።  ይሄኛው ደግሞ የቆሪጥ መንፈስ የሰፈረበት ሳይሆን አይቀርም። የሚያወራው ሁሉ ስለ መቁረጥ ብቻ ነው። ሚኒሊክ ጡት፣ እጅ፣ ቆለጥ፣ እግር፣ ጥፍር… ቆርጠዋል አለን። እንደታናጋሪው ከሆነ እኚህ መሪ ያልቆረጡት ብልት የለም። ሃገር ማስተዳደሩን ትተው አስራ ሁለቱንም የሰውነት አካል ሲበልቱ ኖሯል!
አርፍደው የሚገቡት ተሳዳቢዎች ከአፋቸው የሚወጣውን ጸያፍ ስድብ ለመድገም ይዘገንናል።  በ”ምሁሮቻቸው” ገለጻ መሃል እንደ አዝማች ጣልቃ እየገቡ በአማራው ህዝብ ላይ ይወርዱበታል።  በዚህ ሁሉ መሃል ትንሽ የገረመኝ አንድ ክስተት ነበር።  የክፍሉ መሪ በስድድቡ መሃል ገብቶ በኦሮምኛ እንዲህ ሲል ተናገረ።
“ጀሪን ወል አኛተኑ። ማይኪ ኢቲ ኬኒ። ኑ ሂንደጌኛ”።
ወደ አማርኛው በግርድፉ ሲመለስ፣  ”ማይኩን ስጣቸው። እነሱ እርስበርስ ይባሉ። እኛ እንሰማለን።” እንደማለት ነው።  ዋናው ጨዋታ እዚህ ላይ ኖሯል። ምክንያቱም ይህንን ውግዘት እና ውርጅብኝ ሜንጫዎቹ ያለምክንያት በዚህ ሰዓት አላነሱትም። ነብሳቸውን ይማርና  አፄ ምኒሊክ ካረፉ 100 አመት አለፈ። የሙት አመታቸው መከበር ከጀመረ ደግሞ 70 አመት ሆነው። ይህንን ወቅት ጠብቆ በአማራ እና በክርስትና እምነት ላይ ለመዝመት የሚደረገው ሙከራ፣ ግብታዊ ሳይሆን በጥናት የተደረገ ስለመሆኑ ያመላክተናል። ግርግር በመፍጠር እና ዜጎችን እርስበርስ በማባላት፣ ትንሽ የፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚፈጸም የፖለቲካ ዝሙት መሆኑ ነው።
ልብ በሉ! የዚህ የሜንጫ ዘመቻ መሪዎች ኦሮሞዎች አይደሉም። አብዛኞቹ በግማሽ ከሌላ ዘር የሚወለዱ ናቸው። በእምነታቸውም ሆነ በዘራቸው የተቀላቀሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ።
ስድስት ሚሊየን አይሁዶችን የፈጀው አዶልፍ ሂትለር ግማሽ አይሁድ እንደነበር አንዘንጋ።

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/10748/