Showing posts with label ቁምነገር በዋዛ. Show all posts
Showing posts with label ቁምነገር በዋዛ. Show all posts

Thursday, November 28, 2013

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆኑት መቸ ነው?!!!


 
du_pm_haile_mar_desነፍሳቸውን ይማረውና(ድንገት ነፍስ ካላቸው፣መንፈስ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ነው)የቀድሞውና ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሞት ካረፉና ካረፍናቸው ጀምሮ ታላቋ ኢትዮጵያ ያለ ሀገረ ገዥ የቀረች ይመስላል፡፡ሆደ ቡቡነታቸውን ለመለስ ዜናዊ ሲነፋረቁ ያረጋገጥንላቸው ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ወንበሩ ላይ ቢቀመጡም እንደ ሁለት ወር ህጻን ከተጎለቱበት አላንቀሳቅስ ያላቸውን እርኩስ መንፈስ ሁለት ሰባት ቢታዘዝለት መልካም ነበር፣ነገር ግን ሰውየው በኢየሱሴ የዳኑ ናቸውና ጸበልን ከዚያው በጸበልህ የሚሉ መሆናቸው እኛ የእርሳቸውን ታማኞች መፍትሄ እንዳናዘጋጅ አድርጎናል፡፡ከሰሞኑ ደግሞ ይህ እርኩስ መንፈስ ምንም አላናግራቸው በማለቱ ጭንቀታችን የከፋ አድርጎታል፣መላ ያለህ ሁሉ ወዲ በል፡፡እርስዎስ ቢሆኑ በዚህ ቀውጢ ሰኣት ያልነገሱ መቸ ሊነግሱ ነው፡፡እኔ እንደው የእርስወ ነገር አያስችለኝምና ትንሽ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግለዎት፣የ2007 ምርጫ ደርሶ ሱናሜው ሳይጠርግዎት ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቢሞክሯት መልካም ነው እላለው፡፡አይተ በረከት ስሞንስ እስከመቸ ነው የስሁል ሚካኤልን መንበር ተረክበው ሲሽሩና ሲሾሙ ምን አለበት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚንስትር ቢያደርጓቸው፡፡(ስሁል ሚካኤል በጎንደር የነገስታት ዘመን ከትግራይ የመጡ መስፍን ሲሆኑ ከኋላ ሆነው ሲሾሙና ሲሽሩ የነበሩ ጉልበታም ናቸው)፡፡በመጨረሻም ለሃይለማሪያም ደሳለኝ የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፣ታሪክዎ ሲጻፍ ቤተ መንግስቱን ከሚጠብቁት ወታደሮች የተለየ አይሆንምና በጊዜ መላ ቢያበጁ፣ባይሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎት ከጠፋብዎ አኔን ያማክሩኝ፡፡የሚሰማን የለምእንጅ ባለ ራዕይውንም መክረናቸው ነበር፡፡ምን ያደርጋል ምክራችን ይዘውት ሽል አሉ እንጅ፡፡

Thursday, October 31, 2013

ኢትዮጲያኖች እንደንስር! የንስር አሞራ ዳግም ልደት



gn
ንስር አሞራ ከአዋፋት ዘር ለ70 ዓመት የህወት ዘመን መቆየት የሚችል ነዉ። ንስር አሞራ70 አመት እድሜዉን ለመኖር ወይም ለመጠበቅ በ40ኛ አመቱ ላይ ከፍተኘ መስዋትነት የሚጠይቅ ዉሳኔ ይወስናል። የንስር አሞራ የእግር ጥፍር በአግባቡ መስራት የሚችለዉ ለ40 አመት ብቻ ነዉ።
ንስር አሞራ ከተፈለፈለ ጀምሮ 40 ዓመት ከኖረ በዃላ በሰዉነት ክፍሉ ላይ በሚታየዉ ለዉጥ የተነሳ ፤ የአፍ መንቁሩ፤የእግሩ ጥፍር ና ላባዉ እንደበፊቱ ሊያገለግሉት አይችሉም። የእግሩ ጥፍሩ ደካማ በመሆን አደኑን አይዝለትም ፤ረጅምና ስል መንቁሩ ይታጠፋል ፤ ላባዉ በሰዉነቱ ይለጠፍና ክብደት ስለሚፈጥር ፤እንደልቡ አይበርም ። በዚህ ወቅት ንስር አሞራ ፡ በሁለት ዉሳኔዎች ላይ ይወድቃል ፤ ዝምብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ወይም 5 ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መሰዋትነትን በመክፈል ቀሪ 30 አመቱን እንደ ወጣት ንስር መኖር።
ሰላሳ ተጨማሪ ዓመት ለመኖር የአምስት ወር መሰዋትነት መክፈል፤
ንስር አሞራ ቀሪ 30 ዓመቱን ለመቀጠል ከፍተኛ ተራራላይ በመዉጣት ጎጆ ይቀልሳል።ንስር በተራራዉ ላይ ጎጆ ከቀለሰ በዃላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በመፋቅ ነቅሎ መጣል ነዉ ይህም ከፍተኛ ህመምና ስቃይ አለዉ ይሁን እንጂ አዲስ መንቁር ለማዉጣት ይህንን ማድረግ የግድ ነዉ ፤ ከዚያም አዲስ መንቁር ከወጣላት ወይም ከበቀለለት በዃላ በአዲሱ መንቁር የእግሩን አሮጌ ጥፍር ነቅሎ ይጥለዋል ። አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በዃላ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደመሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቀዉን ጥቅጥቅ ያለዉን ላባ ነቃቅሎ ጥሎ አዲስ ላባ እንዲበቅል ያደርጋል። ይህ ህመምና መከራ ያለዉ ድርጊት ነዉ ። ከዚያም የ 5 ወር የማገገሚያ ጊዜ ካጠነቃቀቀ በዃላ እንደገና ራስን የመዉለድ የትግል ሂደት ይጠናቀቅና ፡ተጨማሪ 30 ዓመቱን በሰማይ ላይ እየበረረ ና እያደነ በደስታ ይኖራል።
እኛ ኢትዮጲያኖች እንደንስሩ መሆን ያቅተን ይሆን?
በህወታችን ዉስጥ የምንፈልጋቸዉ ለዉጦች አንዳንድ ግዜ በአስቸጋሪና መራራ ሁኔታዎች ዉስጥ እንድናልፍ ግድ ይሉናል የሰዉ ልጅ በህይወቱ መከራ ሲገጥመዉ ከዚህ አስቸጋሪ ህወት ለመዉጣትና ለመለወጥ ፤ ብሎም ደስተኛ ለመሆን የህይወት ልምዱን መለወጥ ፤አሮጌ ልምዱን ፤ትዝታዎቹን፤ የእለት ተእለት ኑሮዉን አሽቀንጥሮ መጣል ግድ ይለዋል ፤ እነዚህ አሽቀንጥረን የምንጥላቸዉ ነገሮች ግን ለማስወገድ ከፍተኛ መሰዋትነት ይጠበቅብናል ፤ ይህንን መስዋትነት ከከፈልን ልክ እንደንስር አሞራዉ ቀሪህወታችንን በደስታ ልንኖር እንችላለን።
እኛ ኢትዮጲያኖች በአሁን ጊዜ ከመቸዉም ጊዜና ዘመን በከፋ መልኩ በሀገራችንም ሆነ በስደት ተሰቃይተን ተዋርደን የምንኖርበት ዘመን ሆኖ ሳለ ረዥሙን ዘመናችንን ለመኖር ትንሽ መሰዋትነት በመክፈል አሮጌ ልምዳችንንና ትዝታዎቻችንን፤አሽቀንጥሮ መጣል ተቸግረን ፤ የራሳችንን ቀሪ ህወት ብቻ ሳይሆን የዚችህን ለዘመናት በደም መሰዋትነት የኖረች ሀገር እድሜ ለማስቀጠል ፤ተስማምቶና ተባብሮ መስራት አቅቶን ፤ሀገራችን እላይዋላይ በተጣበቁ መዥገሮች ወዳለመኖር እየወረደች እያየን ፤ዝምብለን እንገኛለን አልያም ባላስፈላጊ ነገሮች ላይ አተካሮ ይዘን በአሮጌ ልምዶቻችን ተተብትበን እንገኛለን።
በኢትዮጲያ ታሪክ ዉስጥ በየዘመኑ የነበሩ ገዢዎች ጊዜያቸዉን ጨርሰዉ ሲወገዱ/ሲሄዱ/ አንጻራዊ ጠንካራ ወይም ደካማ ኢትዮጲያን ትተዉ ነዉ የሚሄዱት፤ወይም ኢትዮጲያ የምትባል ሀገር አትጠፋም።አሁን ኢትዮጲያ ባለችበት ሁኔታ የምትቀጥል ከሆነ ይህ ይኖራል ወይስ ይቀጥላል? በፍጹም። የወያኔ አገዛዝ በዚህ ከቀጠለ ወይም ጊዜ በጨመረ ቁጥር ተገዶም ሆነ በራሱ ጊዜም ቢሄድ ኢትዮጲያ የምትባል ሀገር ልናገኛት አንችልም ወይም አሁን ያለዉን የኢትዮጲያ ግዛት ማግኘት ዘበት ነዉ የሚሆነዉ።ምክንያቱም የገዥዉ አካል ኢትዮጲያን የማጥፋትና የማፍረስ እቅድ ይዞ የተነሳና ለዚሁም ሀያአራት ሰአት የሚሰራ ሲሆን በአንጻሩ ያለንዉ ደግሞ ፤ኢትዮጲያ ኢትዮጲያ ከማለት ዉጭ መሬት የወረደ ስራ መስራት አቅቶን ሃያሁለት አመት አስቆጥረን በተቃራኒዉ ለጥፋቱ ሃይል ምቹ ሆነናል።
እንደሀገር ካሰብን ጊዜዉ አሁንም አልረፈደም እንደ ንስሩ ከፍ ያለ ተራራላይ እንዉጣ ዝቅ አንበል ከፍባልን ቁጥር ጥሩ እይታ ይኖረናል ጥሩ እይታ ታጋሽ፣አስተዋይ ፣ቻይ ያደርገናል፤ከዛ በዃላ አሮጌ አስተሳሰባችንን ፣የማያስማሙንን፣ እኔ ብቻ የሚለዉን ስሜታችንን ፣የሚያለያዩንን፣ መንቁራችንን ፣ጥፍራችንን ወደዚያ ነቅለን ጥለን ፤ በሚያስማሙንን ፣በሚያቻችሉን ፣እንተካቸዉ። ይህንን ስናደርግ ወያኔን ታሪክ አድርገን ኢትዬጲያን እንታደጋታለን።
ሞት ለወያኔ !
ትንሳኤ ለኢትዮጲያ !
Amha Alemu
Norway
ይገባናል – we deserve !

zehabesha

Tuesday, October 22, 2013

ሴት ልጅ እንዳፈቀረችህ ማረጋገጥ የምትችልባቸው 10 መንገዶች


ሊሊ ሞገስ ከአፕል ቫሊ
(ይህ ጽሁፍ በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 56 ታትሞ የወጣ ነው)
APNM0T
APNM1T
የቅርብ ጊዜ የስነ ልቦና ጥናታዊ ሪፖርቶች… ሴት ልጅ ለአንተ ልዩ ፍቅርና መውደድ እንዳላትና እንደሌላት አዕምሮዋን በአካላዊ እንቅስቃሴዎቿ በኩል በቀላሉ እንድታነብ ያስችሉሃል!!
አካላዊ እንቅስቃሴዎች ዋነኛዎቹ የመግባቢያ መንገዶች ናቸው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴና ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴ ይባላሉ፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴዎች በራሳቸው ቋንቋ በመሆን ከንግግርም በላይ በሆነ መልኩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲህ አይነት ተግባቦት በአብዛኛው በተቃራ ፆታ ግንኙነት ውስጥ በተለይም በሴቶች ላይ ይስተዋላሉ፡፡
ግልፅ አካላዊ እንቅስቃሴ
አንድ ጊዜ ከሴት ጋር አይን ለአይን ከተገጣጠምክ ፊቷን ካዞረች በኋላ ያላትንም እንቅስቃሴዎች አስተውል፡፡ አይናች በመጋጨቱ አፍረት ወይም መጨናነቅ ነገር ከታየበት ተመችተሃታል ወይም ወዳሃለች ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ፀጉሯን እንደማፍተልተል፣ ልብሷን ወይም ጌጣጌጧን ማስተካከል ወይም ደግሞ እጇ ላይ ባለው ነገር መጫወት ከጀመረች እነዚህ ግልፅ የሆኑ ማረጋገጫዎችህ ናቸው፡፡
- ውስጥ እጇን አንብብላት፡- በአጋጣሚዎች እና አንድ ላይ በምትሆኑባቸው ሁኔታዎች ውስጥ እጇን ብትመለከት እሷም አሳልፋ ውስጥ እጇንና የእጇን አንጓ እንድትነካ ከፈቀደችልህ ሌላው ያንተ እሷን የመመቸት የአዕምሮ ፍቃድ ማሳያ አንዱ መንገድ ነው፡፡ ይህም ሁኔታ ‹‹ከፈለከኝ ያንተው ነኝ›› እንደማለት ነው፡፡
- ማጎንበስ፡- በምታጎነብስበት ጊዜ ትከሻዋን ወደ አንተ በመስበቅ ካጎነበሰች ዕድል በእጅህ ገብታለች ማለት ነው፡፡
- እግሮቿን ከፍታ በምትቀመጥባቸው አጋጣሚዎች ካሉ አንተ ጋር በመሆኗ ምቾት ተሰምቷታል ማለት ነው፡፡
- አንድ ሴት አንድን ሰው በምታይበት ጊዜ የአይን ብሌኗ ከሰፋ ያንን ሰው እንደምትወደው በተቃራኒው ደግሞ የአይን ብሌኗን ካጠበበች ለዛ ሰው ጥሩ ስሜት እንደሌላት አንድ መገለጫ ነው፡፡ አይን ለአይን በምትጋጩበት ጊዜ ፈገግታን ከቸረችህ ወደ እሷ ሂድና አነጋግራት፡፡ ሌላው እንደ መልካም ነገር መገለጫ የሚወሰደው አንተ በምታወራበት ጊዜ ለረባ ባልረባው ፈገግ የምትል ወይም ሳቅ የምታበዛ ከሆነ በእርግጠኝነት በደንብ ተመችተሃታል ይሄ ደግሞ የበለጠ የተሻለ ነው፡፡
- በምታወሩበት ጊዜ ሁሉ በተለይ ደግሞ እሷ ስታወራ አንተን በተለያዩ አጋጣሚዎች የምትነካህ ከሆነ መልካም ነገር አለ ማለት ነው፡፡ አይኖቻችሁ በሚጋጠሙበት ጊዜም ምቾት የማይሰጥ ቢሆን እንኳን እንደተፋጠጣችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላይ መርሳት የሌለብህ ነገር ቢኖር ፊትህን ከማዞርህ በፊት ፈገግ ማለትን ነው፡፡
ይህ ሁኔታ ታዲያ የአንተ እሷን መውደድና መልካም ሰውነት ያሳያል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም በአንዳንድ አጋጣሚዎች እየሰረቀቸፍ ስታይህ ልታጋጥምህ ትችላለች፡፡ ከሁለተኛውና ከሶስተኛው መገጣጠም በኋላ እንድታናግራት መፈለጓን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡
እንደ መልካም ተጫዋችነትህ የጨዋታውን ህግ በማክበር የፈለገችውን ነገር ማሟላት ግድ ይልሃል፡፡
መሽከርከር፡- አንድ ሴት ፀጉሯን አየር ላይ ወርውራ ወዲያው ዞራ ካየችህ አንተ እንድታያት ለማድረግ እየጣረች መሆኑን ማመን ትችላለህ፡፡
ዝግ አካላዊ እንቅስቃሴዎች
በማንኛውም ሁኔታ ስትመለከታት አይኗን ውስጡን የምታሽከረክረው ከሆነ በአንተ አቀራረብ ማፈሯንና እንዲሁም በአንተ ደስተኛ አለመሆኗን ለሰዎች ለማሳየት እየጣረች መሆኑን ማወቅ አለብህ፡፡ ይህ ነገር ከተፈጠረ እሷን የማግኘት እድልህ ትንሽ በመሆኑ ማድረግ ያለብህ ፊትህን አዙሮ መሄድ ነው፡፡
- በምታወሩበት ጊዜ እጇን ካጣመረች መጨናነቋን ወይም በሁኔታው ምቾት እንዳልተሰማትአመላካች በመሆኑ እስትራቴጂህን ወይም ስልትህን በፍጥነት መቀየር ይኖርብሃል፡፡ ሌላው ከዚሁ ከማጣመር ጎን የሚያያዘው የእግር ማጣመር ነው፡፡ እግር ማጣመር ልክ እጅን የማታመር ያህል መጥፎ ሲሆን ይህን አጋጣሚ የበለጠ መጥፎ የሚያደርገው ደግሞ አንድ ጊዜ እግሯን ካጣመረች እጇንም የማጣመር ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ ይሁንና እግሯን አጣምራም ቢሆን ጉልበቶቿ ወደ አንተ ከዞሩ ትንሽ ከመጨነቋ ውጪ ከአንተ ላይ ፍላጎት እንዳላት ያመላክታል፡፡ ተቃራኒው ሆኖ ጉልበቷ በሌላ አቅጣጫ ከዞረ ግን ችግር ውስጥ ነህ ማለት ነው፡፡
ወደኋላ መሸሽ ወይም መለጠጥ፡- ወንበር ላይ ከአንተ ራቅ ብላ ወይም ተለጥጣ የምትቀመጥ ከመሆን በደንብ የሚስተዋል አንተን ያለመሻቷ መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ምክር የሚሆነው የዚህ አይነት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በምታይበት አጋጣሚ ጨዋታውን ጥሎ መውጣት ብቻ ነው መፍትሄ የሚሆነው በእንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሴቷን የራሳቸው ማድረግ የሚችሉት ልምዱ ያላቸው ብቻ ናቸው፡፡
የአካላዊ እንቅስቃሴ ማታለያዎች
አንድ ሴት አንተን እየተከታተለችህ መሆኑንና ያለመሆኑን ለማወቅ አንድ የሚያስቅና የሚሰራ ማታለያ ልንገርህ፡፡ እሷ አንተን በምታይበት ሁኔታ ላይ ሆነህ ሰዓትህን እያየህ በዝግታ ከ1-3 ቁጠርና ቀና ብለህ እያት፡፡ እሷም ሰዓቷን እያየች ከሆነ አንተን ስታይህ እንደነበር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ የሆነ አንተን የሚወድ ሰው ባህሪ ነው፡፡ ልክ አንተ ሰዓትህን ማየት ስትጀምር እሷም ምን እየጠበክ እንደሆነ በማሰብ ሰዓቷን ታያለች፡፡
ተጨማሪ የአካላዊ እንቅስቃሴ መረጃዎች 1. ፀጉር ማፍተልተል
አብዛኛውን ጊዜ ፀጉሯን የምታስተካክል ወይም የምታፍተለትል ሴት የወንዶችን አይን ለመማረክ የምትሞክረው ናት፡፡ ፀጉር ማፍተልተሏንም ሆነ መነካካቷን በደቂቃ ውስጥ ሶስት ጊዜ የምታደርገው ከሆነ መያዝም ሆነ መታየትን የምትፈልግ መሆኑን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ፡፡ ሌላው ደግሞ ፀጉሯንየምትነካበት መንገድም የራሱ የሆነ መልዕክት እንዳለው መዘንጋት የለብህም፡፡ ይህም ፀጉሯን በቀስታ የምትነካካ ከሆነ የፍቅር ጥበብ እንዳላት ማወቅ የምትችል ሲሆን ከፈጠነች ደግሞ ማፈሯንና ትዕግስት አልባ መሆኗን ማየት ትችላለህ፡፡
2. የብርጭቆ ጠርዝ ላይ እጅን ማሽከርከር
በሲግመንድ ፎርይድ ቲዎሪ መሰረት ይህ ምልክት ለወሲብ የመጋበዝ ያህል ነው፡፡ ይህ አባባል ታዲያ በብዙ ሴቶች ተደግፏል፡፡ ይህን ጊዜ ታዲያ የጣቶቿን እንቅስቃሴ ልብ ማለት አለብህ፡፡ በዝግታ ጣቶቿን የምታሽከረክር ወይም የምታንቀሳቅስ ከሆነ ጥልቅ የሆነ እርጋታን፣ እራስ መቆጣጠርንና ጥበቃን አመላካች ስለሆነ ከጎኗ ልትቀመጥ ትችላለህ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በጥፍሯ ብርጭቆውን መምታት ከጀመረች ለነገሮች ትዕግስት ማጣቷንና መቸኮልን ወይም በሌላ መልኩ በወንድ ጓደኛዋ መናደዷን አመላካች ነው፡፡
3. በክንዷ ስትደገፍ
አሪስቶትል እንዳለው ከሆነ የሴት እጅ ብዙ ነገር ያወራል፡፡ በአካል እንቅስቃሴ ላይ ጥናት አድራጊዎች ደግሞ ሴቶች በእንቅስቃሴያቸው የበለጠ ነገሮችን እንደሚገልፁ ያብራራሉ፡፡ በክንዷ ደገፍ ብላ እጇን አገጯ ስር በማስቀመጥ አይኗ በሀሳብ ከዋለለ ተመስጣብኛለች ብለህ በማሰብ እንዳትሳሳት እንደውም በዛ ሰዓት ላይ እራሷን በመጠየቅ ላይ ስለምትገኝ ትንሽ ታገሳት፡፡ እሷም በዛ ሰዓት እያሰበች ከምትሆናቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ለዚህ ሰው እገባዋለሁ?›› ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሴቶች ብዙ ጊዜ ለጥያቄዎቻቸው መልስ የሚፈልጉት በዚህ መልኩ ስለሆነ ነው፡፡ መልሱ ምን እንደሆነ አንተ ታውቀዋለህ፡፡ ስለዚህ በተሳካ ሁኔታ እረጋ በማለትና በቀልድ በማዋዛት ውሳኔዋን ልታስቀይራት ትችላለህ፡፡
4. እጇን በማጣመር ተደግፋ ስትቀመጥ
ይህ አጋጣሚ በጭፈራ ቤትም ሆነ በየትኛውም ቦታ ሴት በማደን ላይ ከሆንክና ካጋጠመህ ዕድለኛ አይደለህም ማለት ነው፡፡ በዚህ አይነት አጋጣሚ ያለች ሴት ሁኔታህ አልተመቻትም ወይም አልተማመነችብህም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ታዲያ የተዘጋጀህበትም ቀልድም ሆነ ፈርጣማ ሰውነትህ ትርጉም ስለሌላቸው ባትለፋ ይሻላል፡፡ አይ ካልክ ደግሞ ቀለል ያለ የወሬ መጀመሪያ መንገድ ብትፈልግ ያዋጣሃል፡፡
5. ከንፈሯን ስታረጥብ
አንድ ሴት ከአንተ ጋር እያወራች በተደጋጋሚ ከንፈሯን የምታረጥብ ከሆነ ለፍቅር ያላትን ተነሳሽነት ይገልፃል፡፡ የስነ ባህል ተመራማሪዎች እንደሚሉት ከሆነ ሴቶች እንደዚህ አይነት ምልክት የሚሰጡት ከንፈራቸው ላይ ሌላ ነገር እንዲቀመጥ ሲፈልጉ ነው፡፡ ምን ሊፈልጉ እንደሚችሉ መቼም ላንተ መንገር የለብኝም፡፡
6. ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ
ሽፋሽፍቶቿን የምትነካካ ከሆነ ነፃነት ያላት ሴት መሆኗን መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ውስጥ መቀለድም ሆነ በትልቁ መሳቅ ላይጠበቅብህ ይችላል፡፡ ተነሳሽነቱን እሷ መውሰዷ ካልደበረህ በሁኔታዎቹ አብራችሁ ልትዝናኑ ትችላላችሁ፡፡
7. እግር ማወዛወዝ
እግር ማወዛወዝም ሆነ በፍጥነት ማጣጠፍ ሴቷ ለወሲብ ያላትን ተነሳሽነት ያሳያል፡፡ ይህን አጋጣሚ ደግሞ የበለጠ የሚያበረታታው እግሯን በማንቀሳቀስ ላይ እያለች ሳታስበው የምትከፍት ከሆነ ነው፡፡ በሲግመንድ ፎርይድ ክላሲካል ቲዮሪ መሰረት ይህ አጋጣሚ ለወሲብም ክፍት መሆኗን ጠቋሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሳይነሳ የማይታለፈው የምታደርገው የጫማ አይነት ነው፡፡ የጫማው አይነት ለማውለቅ የበለጠ ቀለል ያለ ከሆነ ለነገሮች ያላትም ተነሳሽነት ቀላል መሆኑን የበለጠ አመላካች ነው፡፡ ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በቤዚክ ኢንስትኒክት /Basic Instinct/ ፊልም ላይ የሻሮን ስቶን እግር አከፋፈት ነው፡፡
8. የጣቶች አይነት
አንድ ሴት ለእጇ ያላት አመለካከት የበለጠ ነገሮችንገላጭ ሲሆን በደንብ የተሰሩ ረጃጅም ጣቶች በጥንቃቄ የተቀለሙ ጥፍሮች መልካም የሆኑ አነቃቂ ነገሮች ናቸው፡፡ ይሁንና ሴቷ እጆቿን የምታንቀሳቅስበት መንገድ የበለጠ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባው ነው፡፡ ለረጅም ሰዓት እጆቿ ላይ በመፍጠጥ ከቆየች መናደዷን መረዳት ትችላለህ /ምናልባት ባንተ?/ ጠረጴዛውንም በጥፍሮቿ የምትመታ ከሆነ ተመሳሳይ መልዕክት ስለያዘ ብታስብበት ይሻላል፡፡
9. ከንፈሯን ከበላች
በመሳሳም ወቅት ከንፈርህን ከነከሰችህ ፍፁም አታቋርጣት፡፡ ምንም መጥፎ የሆነ ነገረ የለም፡፡ ግን እሷ በራሷ የራሷን የምትነክስ ከሆነ ለመጨናነቋ ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ለምን? ለሚለው መልስ ምናልባት በጥያቄ አይን አፍጥጠህባት ይሆን?
10. ነፍሷን አዳምጠው
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ መደበኛ ወንድና ሴት ግንኙነት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ በወሲብ ላይ ጤናማ የሆነ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህን መልዕክቶች አንብቦ መተርጎምና በእንቅስቃሴው ውስጥ የራስህን ድርሻ መውሰድ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ ሌላው ግን በደንብ እሷን መከታተልና ነፍስያዋ ማዳመጥ ዋናው ነገር ነው፡፡ አንድን ሴት አይተህ ከአንተ ምን እንደምትፈልግ ወሲብ፣ ፍቅር ወይስ ጥልቅ ቅርርብ የሚለውን ነገር ለማወቅ እነዚህን ከታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ማስተዋልና ነፍሷን ማወቅ ትችላለህ፡፡
ጮክ ብላ የምትስቅ ከሆነ፣ ከንፈሯን ካረጠበች፣ በጡቷ ወይም በዳሌዋ ከገፋችህ፣ በጥልቅ ካዳመጠችህ፣ በኩራት ከተራመደች፣ ዳሌዋን ካማታች፣ የአይን አሰባበሯ፣ እግሯን አጣምራ ወደኋላ ከገፋችው፣ ፊቷን ከሸፈነች፣ በጣቶቿ ፀጉሯን ካበጠረች፣ የማይነኩ የሰውነት ክፍሎችህ ውስጥ እጆቿን ከሰደደች፣ እስቶኪንጓን ካስተካከለች ወይም በሹራቧ ቁልፍ ስትጫወት፣ በጣም ከዘነጠች ከተኳኳለችና ሽቶ ከተጋነነ፣ በጆሮህ በተደጋጋሚ በመምጣት የምታንሾካሹክ ከሆነ ወይም ደግሞ ፍቅራዊ የሆነ ሌላ መንገድ ከተጠቀመች፣ በጥልቀት ካፈጠጠችብህ፣ እንዲሁም በአይኗ መዝናህ ካንተጋር የበለጠ ሰዓት ለማሳለፍ ከፈለገች በነገሮች ላይ እርግጠና ልትሆንና የራስህን ውሳኔና እንቅስቃሴ ልታሳልፍ ትችላለህ፡፡ 

zehabesha

Tuesday, October 15, 2013

ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ

ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ

በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው የሞኢ ኢብራሂም ሽልማት በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንዳልተገኘ ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።
8u7
ሞኢ ኢብራሂም የተባለው ድርጅት በመልካም አስተዳደር ለተመረጡ የአፍሪቃ መሪዎች ለሚሰጠው ሽልማት በዚህ ዓመት መስፈርቱን ያሟላ መሪ አለማግኘቱን አስታወቀ ። ድርጅቱ ዛሬ ለንደን ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በዚህ ዓመት ተሸላሚ እንደሌለ አስታውቋል ። ከ52 የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች መካከል የድርጅቱን መስፈርት ያሟላ መሪ አለመገኘቱ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር ። ድርጅቱ ለአፍሪቃ ሃገራት የሰጠው የመልካም አስተዳደር ደረጃም ዛሬ ይፋ ሆኗል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

dw.de

Thursday, September 12, 2013

ኮሎኔል ሃይማኖት ይፈቱ…!

ኮሎኔል ሃይማኖት ይፈቱ…! ርዮት አለሙም ትፈታ! (አቤ ቶኪቻው)

ኮሎኔል ሃይማኖት ይፈቱ…! ርዮት አለሙም ትፈታ!
ኮሎኔል ሃይማኖት የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት ናቸው፡፡ ከጫካ ታግለው መጥተው ሹመት በሹመት ሆነው “ሲሾም ያልበላ ሲሻር ምን ሊበላ ነው” ብለው ሲበሉ፣ ሲበሉ፣ ሲበሉ…”የተበሉ” ሴትዮ ናቸው፡፡Abe Tokichaw (Abebe Tolla) the Popular Ethiopian Political Satirist
አቶ ገብረውሃድ ማለት ደግሞ፤ “ስልጣናቸውን በመጠቀም ያከማቹት መሬት ቢሰበሰብ ኤርትራን የሚያክል ሀገር ይወጣዋል እና ትልቁ ስጋት ሰውዬው መሬቱን ለምን ወሰዱ… ሳይሆን ይሄንን መሬት ይዤ የራሴን እድል በራሴ ወስኛለሁ እና የመገንጠል መብቴ ይከበርልኝ እንዳይሉ ነው…” በሚል ሀገሬው ሲያማቸው የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡
እንግዲህ እኒህ ቱባ ባለስልጣን ቱባ ቱባ ዝርፊያ አድርገዋል ተብለው ሲታሰሩ ባለቤታቸው ኮሌኔል ሃይማኖት ደግሞ የራሳቸውንም የባለቤታቸውም ዝርፊያ ውጤት የሆነውን ንብረት “ለማንኛውም መደበቅ ነው የሚሻለው…” ብለው ሲያሸሹ ተገኝተው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡
ከላይ ያየነው ከመንግስት ሚዲያዎች እንደሰማነው እና በራሳችን ቋንቋ ተርጉምን እንደፃፍነው ነው፡፡
ይሄን ያክል ከተንደረደርን፤
ኮሎኔል ሃይማኖት አዲሱን አመት በእስር ቤታቸው ድል ያለ ድግስ ደግሰው ቤተሰቦቻቸው እዛው ቃሊቲ ድረስ ሄደውላቸው ያማራቸውን ለብሰው ያሰኛቸውን በልተው ደስ ያላቸውን ጠጥተው ስቀው ተጫውተው ነው ያሳለፉት፡፡
ከሁለት ቀን በፊት ከጋዜጠኛ ርዮት አለሙ ጋር ክፍል የተጋሩት ኮሎኔል ከጋዜጠኛይቱ ጋር ከተገናኙበት ቀን አንስቶ “ቀልባቸው አልወደዳትም” ይዝቱባታል፡፡ ይሰድቧታል፡፡ ያንጓጥጧታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የስጋ ዘመዳቸው ሆነቸው የቃሊቲ ሴት ዋርዲያዎች ሃላፊ አሚናዘር “እሰይ አበጀሽ የኛ ልጅ” ብላላቸዋለች፡፡
“ሙስና ይብቃ” ብላ ስትፅፍ ተገኝታ በቁጥጥር ስር የዋለችው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ፤ ከእናት እና ከአባቷ ውጪ ሌላ ሰው ማናገር አትችይም ተብላ ስትከለከል፤ ሙስና ይስፋ ብለው በሙስና የተዘረፈ ንብረቶችን ሲያሸሹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኮሎኔል ያለ የሌለ ሃይላቸውን ተጠቅመው ሊያበሳጯት እየተጉ ነው፡፡ ለዚህም አበል እንዲሆን በዓልን እስር ቤቱ መኖሪያ ቤታቸው እስኪመስል ድረስ አሸብርቀውበት ውለዋል፡፡
በተቃራኒው ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ በዓሉን በርሃብ አድማ አሳልፋለች፡፡ እንደ ኮለኔሏ እና እንደ ዋርዲያዎቹ ዛቻ ከሆነ ርዮት አለሙን በተለያየ ዘዴ ምግብ መመረዝን ጨምሮ ጥቃት ሊያደርሱባት እንደሚችሉ… ዝተውባታል፡፡
ኮሎኖል ሃይማኖትን ያሰራቸው አካል በጥፋታቸው እስር አስሯቸው ይሁን በስልጣናቸው ስራ እያሰራቸው ይሁን ግራ ተጋብተን እንገኛለን! ማሰሩ ከሆነ ግን፤ ይሄ እስር ሙስናን የሚዋጋ ሳይሆን ጭራሽ በሙስና የሚያስወጋ ነውና እና ዛሬውኑ ይፈቱልን! ጋዜጠኛ ርዮት አለሙም ትፈታልን! ሌላው ይቅር …ቢያንስ እስር ቤት ውስጥ ድጋሚ መታሰሯ ይቁም!

Thursday, September 5, 2013

ዜና በጨዋታ

ዜና በጨዋታ፤ አየር መንገዴ ሆነ እንዴ… መደዴ…!? (አቤ ቶኪቻው)

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ተደጋጋሚ ጉዳቶችን ሰምተንበት ደንግጠናል፡፡ ባለፈው ጊዜ በመላው ድሪም ላይነሮች ላይ የደረሰው የባትሪ መጋል የእኛንም አንድ ለእናቱ ድሪም ላይነር ስጋት ላይ የጣለ ነበር፡፡ ቀጠለ በለንደን ከተማ አንዱ አውሮፕላናችን ሲጨስ ታየ ተብሎ ትልቅ ወሬ ሆኖ እኛም ኤድያ…. አሁንስ አየር መንገዴ ቁጣ መጣበት እንዴ… ብለን አድነነ ከመዓቱ ብለን ፀሎት አደረግን፡፡ አሁን ደግሞ ከወደ ደቡብ አፍሪካ አንድ ወሬ ሰማን እቃ ጫኙ ካርጎ አየር መንገዳችን ሸክሙ ከብዶት እንደ ሮኬት ከአፍንጫው ወደላይ ተቀስሮ አየነው… አሁን ማንጎራጎር ጀመርን…Abe Tokichaw (Abebe Tolla) the Popular Ethiopian Political Satirist
ጥሩም አላወራም ሰው ሁሉ ባገሩ
ውድ አየር መንገዴ ምንድነው ነገሩ
መንሸራተት በዛ ቀረ እና መብረሩ
ካዋዋሉ ይሆን ወይ ካስተዳደሩ…
ብለን ሳናበቃ ከወደ አስተዳደሩ አንድ ዜና ሰማን፤ ይሄማ ካለ አዲስ መስመር አይሞከርም ይከተሉኝማ…
ከ9 ወር በፊት ወደ 1000 የሚጠጉ ሰራተኞች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተባረው ነበር፡፡ ሰራተኞቹን ለአየር መንገድ ያስቀጠራቸው ስባኮ (ስልጡን ባለሞያ ኩባንያ) የሚባል ድርጅት ነበር፡፡ ሰራተኞቹ የመባረራቸውን ምክንያት ሲጠይቁ ”ይሄ ”ስባኮ” የተባለ አስቀጣሪ ድርጅት ከአየር መንገድ ጋር ኮንትራቱን አቁሟል” ተባሉ፤ ጥቂት ምግባረ ሰናይ ተብለው ያልተባረሩ ሰራተኞችም በተባረሩት 1000 ሰራተኞች ምትክ አስቀጣሪ የሆነው “ማሊፎ” (ማህበራዊ ሊግ ፎረም) በተባለው ድርጅት እንዲታቀፉ ተደረገ፡፡ እነዚህ ያልተባረሩ ሰራተኞችም አዲስ ገቢዎቹን የማሊፎ ልጆች በቅጡ ስራውን እንዲያለምዷቸው ተመከሩ፡፡ በጄ… አሉ፡፡
በመሃል ላይ የቀድሞው “ስባኮ” ድርጅት ያስቀጠራቸው እና ያልተባረሩ ሰራተኞች አንድ ቅፅ ተላከላቸው ቅፁ “ከሊግ እና ከፎረም አባልነት እየመረጣችሁ ሙሉ” የሚል ነበር፡፡ እነርሱም “ስለ ሊግም ሆነ ስለ ፎረም በቂ እውቀት የለንም እኛ ስራችንን ብቻ ነው የምንሰራው… አትቁሙ… ” ብለው ሁለቱንም ቅጾች ሳይሞሉ መለሷቸው፡፡
ግዜው ሄደ ሄደ …አሁንም ሄደ…. “ማሊፎ” (ማህበራዊ ሊግ ፎረም) ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ከየቀበሌው የተሰባሰቡ የኢህአዴግ አባል ወጣቶችን ቀድሞ “ስልጡን ባለሞያ ኩባንያ” የተበላው ድርጅት ባስቀጠራቸው አንድ ሺህ ሰራተኞች ምትክ ካስቀጠረ 9 ወራት ተቆጠሩ፡፡ አሁን የማሊፎ ወጣቶች በስልጡን ባለሞያ ኩባንያ ልጆች በተሰጣቸው ስልጠና ስራውን ተላምደውታል፡፡ ”እሰይ እንኳን ተለመዱ” ይበሉና ይከተሉኝማ…
አሁንም ከትላንት በስትያ ወደ ሰባ አምስት የሚጠጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በፌደራል ፖሊስ እና በአየር መንገዱ ጥበቃ ሰራተኞች ከስራቸው ተባረዋል፡፡ እነዚህ ሰራተኞች ከቀበሌ የተላኩ አንድ ሺህ ሰራተኞችን ስራ እንዲያስለምዱ ከጓደኞቻቸው ተነጥለው “መልካም ስነምግባር አላችሁ” ተብለው ቀርተው የነበሩ ቢሆኑም፤ ”ከሊግ ከፎረም…” ምረጡ ሲባሉ “መልሱ የለም” ብለው ሁለቱንም አንሞላም ያሉ ናቸው፡፡
ማስታወሻ፤ ሊግም ፎረምም የኢህአዴግ መንትያ ልጆች ናቸው፡፡
የስራ መታወቂያቸውን ተቀምተው የተባረሩት እነዚህ ሰራተኞች ከስራ ሲሰናበቱ፤ ደሞዝ አልተሰጣቸውም፣ ደብዳቤ አልተሰጣቸውም፣ ማስጠንቀቂያ አልተሰጣቸውም፣ ትራንስፖርት እንኳን አልተሰጣቸውም፡፡ ስናጋንንም፤ ”ሰላም ወደቤታችሁ ግቡ” እንኳ አልተባሉም!
“ምን አጠፋን እና ከስራችን እንባረራለን” ብለው ቢጠይቁም “ድርጅቱ ጀርባቹን ሲያጠና ቆይቷል እናም አትሆኑንም” ብለዋቸዋል፡፡ ይሄንን የሚገልፅ ደብዳቤ ስጡን ብለው ጠይቀው ነበር…የሚሰማ አላገኙም፡፡
እናም አየር መንገዳችንን ትልቅ ቦታ ሰጥተነው የነበርን ሁላ… አየር መንገዴ ሆነ እንዴ… መደዴ….! ብለን እየተከዝን እንገኛለን! ገና ዛሬ… ብሎ የሽሙጥ ጥቄ መጠየቅ ይቻላል…!

abetokichaw

Saturday, August 31, 2013

የማለዳው ወግ … ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !

በሰላም አውሎ ላሳደረኝ ፈጣሪ ስተኛም ሆነ ስነሳ ” ተመስገን ፈጣሪየ! ” የምትለዋን ምስጋና ከማቅረብ ተቆጥቤ አላውቅም ። ቸርነቱ የማያልቅበት ፈጣሪ አምላኬ አጉድሎብኝ አያውቅም!  ጤና ስጠኝ ስለው ጤናውን ፣ ጥበብ  መላ ላጣሁለት መላ ስጠኝ ስለው መላ ብልሃቱን ፣ ጉልበቴን አበርታው ስለው ብርታቱን ፣ ቅን ልቦና ስጠኝ ስለው ርህራሔውን እና የፈለግኩትን ሁሉ አያጓድልብኝም!  እናም ዘወትር ተመስገን እለዋለሁ !
   ገና ከአልጋየ ሳልነሳ ከአፊ ውስጥ አንድ ቃል ይመላለሳል ፣ ቃሉ ወደ አረፍተ ነገር ሺር በሎ ተቀየረ ! በጨለማ የማያይ አይኔን ወደ ድቅድቁ ጨለማ የመኝታ ክፍል ጣራ አፍጥጦ በምናብ አነበንበዋለሁ … በጀርባየ ተኝቸ ወደ ጣራ ካፈጠጥኩበት ወደ ጎን ግልበጥ እልና  እጆቸን ጭንቅላቴ ስር ወሸቅ አድርጌ  ከአፊ የማወጣውን አረፍተ ነገር ደጋገምኩ  ” ተመስገን ተመስገን ተመስገን አልልም !”  …  እል ይዣለሁ!
የጋዜጠኛ ተመስገን ድብደባ  ሰሞነኛው መነጋገሪያ …
       ለምጀዋለሁና እንደቀሩት ቀናት በአርቡ የሳውዲ የእረፍት ቀን መዳረሻ በድቅድቁ ጨለማ ሌሊት ላይ ነቅቸ የሚነበብ የሚታይ ካለ ዳሰስ ዳሰስ አደረግኩ። የሚሞነጫጨር የማለዳ ወግ መነሻ የሚሆነኝ ጉዳይ ከአንድ የፊስ ቡክ ወዳጀ በኩል በውስጥ መልዕክት ደርሶኛል ። ይህው መልዕክት የደረሰኝ የኢቲቪ ዜና አንባቢ ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ በተባለ ቅጽበት ነበር ። መረጃው ሲሰራጭ እኔም በጅዳ ቆንስል ከድብደባ ያላነሰ ግፍ ተፈጽሞብኝ ነበር ።  በደል እየተፈጸማቸው ፡ እየታመሙና እያበዱ ስላሉ ወገኖቸ ጉዳይ መፍትሔ ፍለጋና ምክክር ስብሰባ “አትሰበሰብም ፣አትመክርም!” ተብየ የታገድኩበት አጋጣሚ ነበርና የሰማሁትም የሆነብኝም አበሳጭቶኝ አዘንኩ ! የቆንስሉን እገዳ መረጃ በጻፈ እጀ በተመስገን ላይ የተቃጣውን ድብደባ የተሰማኝን ስሜት ሳላንዛዛ በተሰራጨው መረጃ ስር አስተያየቴን እንዲህ በማለት አስቀመጥኩ  ” እርምጃው በማንም ይወሰድ በማን ፣ አላስደሰተኝም! ” በማለት …
     ይህ ከሆነ በኋላ በውስጥ መልዕክት መቀበያ ሳጥኔ ብዙ የተቃውሞና ድጋፍ መልዕክት ደረሰኝ!  የለመድኩት ነበርና ሁሉንም በጥንቃቄ እያነበብኩ አለፍኩት ። ከትናነት በስቲያ ከደረሱኝ መካከል ከላይ የጠቀስኩት መልዕክት እንዲህ ይላል” ሰላም ነብዩ በኢባሲ የደረሰብህ በጣም አሳዝኖኛል አሁን የሰማሁት መረጃክ ስለተመስገን መደብ እጅግ አዝኛለው አንተም ሀቅን እንናገር ስላልክ ከኢባሲክ ከተከለከልክ እደተመስገን አንዳያደርጉህ ተጠንቀቅ ” ይላል መልስ የሚያሻው አስተያየት!…  እርግጥ ነው ባለኝ ትርፍ ሰአት መረጃ በማቀበሌ እና ሃሳቤን ባንሸራሸርኩ ፣ ከተቃዋሚ ጽንፈኛ ተብየ እስከ መንግስት ጽንፈኛ ደጋፊዎች የሚሰነዘርብኝ የማስፈራሪያ የዛቻና የ”እንገድልሃለን !” ፉከራ እኔ ለምጀው ባልፍም ብዙዎቹን ያሳስባቸዋል! ከእኒህ ወዳጆቸ መካከል ምክር ለለገሱኝ ወዳጀ ምስጋና ካቀረብኩ በኋላ በሰጠሁት ምላሽ ከጋጠዎጦች ባልተናነሰ እኔንም ሆነ የዜጎች መብት መገፈፍ ያገባናል የምንልን ወገኖች መብት የማያከብሩ ፣ ሰላም የነሱን ፣ መብት ማስከበሩ ቀርቶ የሚገፉን የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ናቸው የሚል መልሴን ሰጠሁ … በዚህ ዙሪያና በተመስገን በምንም ሚዛን ተቀባይነት የሌለው ድብደባ ዙሪያ የማለዳ ወግ አምዴ ልሞነጫጭር ባስብም ድካም የመጻፍ ፍላጎቴን ጎድቶት እንቢ አለኝ !
ዛሬ ሌሊት ….
በድቅድቁ ጨለማ በነቃሁ ሰአት ይህንን እያሰላሰልኩ መረጃዎችን መፈተሽ ይዣለሁ … በኢቲቪ ጋዜጠኛ በተመስገን በየነ ላይ ደረሰበት የተባለውን ድብደባ ተከትሎ የቅርብ ወዳጆቹ ፣ አድናቂዎቹና  የኢቲቪ ጋዜጠኞች የሰጧቸው አስተያየቶች ተበራክተዋል ። ይህን ሁሉ ቃኝቸ ተመልሸ ገደም እንደልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ  !
በማለዳው ግን ተነሳሁ … እናም ሰሞነኛው ተመስገን አልለቀቀኝም  “ተመስገን አልልም ” እያስባለ ያሚያንሰላስለኝን ሃሳብ ከተጋደምኩበት ቀና ብየ መጻፍ ጀመርኩ  ! ግጥም ሆነ …
ተመስገን ማለቱ ክፉ ነው ባልልም
ስጋቱ ተገፎ ስላላየሁ ዛሬም
ተመስገን ተመስገን ተመስገን አልልም !
የቱ ነው እውነቱ የዝብርቅርቁ አለም ?
ሰው ያለ ሃጢያቱ ከቶ አይወነጀልም ?
ወህኒ አይወረወር አይደበደብም ?
ፍትህን ተነፍጎ ከቶ አይገደለም ?
ለዚህ የሚያስደስት ዛሬ መልስ የለኝም!
ስል በስሜት መነጫጨርሙ … ቀጠልኩ …
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ባልልም
ድብደባ ግድያን ፍጹም አልደግፍም !
…  አልኩና አንገቴን አቅንቸ በኩራት ተሞልቸ ተመስገን ተመስገን አልልም ስል የቅርብ ሩቁን ፣ ግራ ቀኙን የነፍስ ማጥፋት እኩይ ምግባር አጠየቅኩ … ምክርም መክሬ ፍላጎት ምኞቴን እንካችሁ አልኩ …
በጠራራ ጸሃይ በሚንቀለቀለው
“ኢትዮጵያዊ ክብሬ” ስላለ ቢከፋው
ቆፍጣናውን መምህር ያን አሰፋ ማሩን ከቶ ማን ገደለው ?
ያንን ጋዜጠኛ ተስፋየ ታደሰን ማነው ያጋደመው?
በምሽት ጨረቃ ድምቅ ፍንትው ባለው ?
ጀኔራል ሃየሎም ማነው የደፈረው ?
በጥይቱ ባሩድ ከእኛ የለያየው ?
ማለዳው ጸሃይ ጸጥ ረጭ ባለው
የደህንነቱን ሰው ክንፈን ገብረ ማን አጠፋው ?
አመት እንኳ ቀርቶ መንፈቅ ባልደፈነው
ወሎ ሰማይ ስር ረግቶ በሚታየው
በምሽት ጨረቃ ሸሁን በጭካኔ ማነው ገዳያቸው?
አልኩና ውጋት ህመም የምለውን ፣ ምክር ዝክር ይሆናል የምለውን ገጣጠምኩትን ! ከሙሉው ግጥም ግጥሜን በቀነጨብኳት ስንኝ ውጌን ልቋጭ …
ችግሩን ለማጥፋት ከሆነ የምናልም
ለድብደባ ፣ እስራት ፣ ለተበራከተው የሰው ልጅ ግድያም
መፍትሄ ፍለጋ ከሆነ ምንሻው እንዳይደጋገም
“ምንድነው ሰበቡ ” ብሎ ማጠየቁ ሳይጠቅም አይቀርም !
ህግ ባለበት ሃገር ግፉ ተበራክቶ ፣ ልዩነቱ ከሰፋ
ችግሩን እንመርምር ያለ መቁረጥ ተስፋ
ፍርድን አናዛባ ፣ ግፉንም አናብዛ ሰውን አናስከፋ
ሃገር አናሰድብ ሰሟን አናስጠፋ
ሰላምን አናውርድ ልዩነቱ ይጥበብ እንድንኖር በተስፋ
ይህን ሳናሟላ ፣ በልዩነት ሰበብ ሰውን አንበድለው
ሰው ከሃገሩ በምድሩ ክብሩን አናሳጣው
መብት በጠየቀ አሸባሪ አንበለው !
ይህን ካደረግ ሰውን ካከበርነው
ማግለልን ካቆምን በዘር በቀለሙ ብሎም በእሳቤው
ያኔ ነው ቀናችን ድብደባ ግድያ የሚጠፋውማ
ያኔ ነው ቀናችን ተመስገን መባያው
እልል የሚባለው ሰለም የሚኖረው!
ጥላቻን አጥፍተን ፣በእርቅ በይቅርታ ደምቀን ስንታይ ነው
ተመስገን  ፣ ተመስገን ፣ ተመስገን የምንለው !
ከእንቅልፍ አንቅቶ ያብተከተከኝን ሙሉ የስንኝ ቋጠሮ በወግ አሰናድቸ እስካቀርበው ለዛሬ የማለዳ ወግ ይህችን  ታክል ካወጋን አይከፋም !  ለእናንተ ለወዳጆቸ መልካም ቀንን ተመኝቸ  አንድየን አመስግኘ እንለያይ ! ፈጣሪ ሆይ አንተን አልፋና ኦሜጋ እናመሰግንሃለን  ! ተመስገን !
ሰላም
ነቢዩ  ሲራክ
ከወይና ደጋው ሳውዲ በአንዷ ከተማ

Wednesday, August 28, 2013

ጌሾና ጫት – በአውስትራልያ(daniel kibret)



ጌሾና ጫት – በአውስትራልያ(daniel kibret)



አሁን አብዛኛው አውስትራልያ የገባ ኢትዮጵያዊ በሚገኝባት የሜልበርን ከተማ ውስጥ አበሻው ሰብሰብ ብሎ በሚኖርባትና በሚሠራባት ፉትስክሬይ በተባለችው መንደር እንገኛለን፡፡ ይህች የሜልበርን ምዕራባዊ ቀበሌ የሆነች መንደር ጥንት የኤስያውያን መናኸርያ ነበረች ይባላል፡፡ ዛሬ ግን ዋናዋ የአፍሪካውያን ስደተኞች መሰባሰቢያ ናት፡፡ በዚህች ከ74000 ትንሽ ከፍ የሚል ሕዝብ በሚኖርባት መንደር ውስጥ ከ135 ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ይኖሩባታል፤ ከ85 ቋንቋ በላይ ይነገርባታል፡፡ እንዴው መርካቶ በሏት፡፡
በአውስትራልያ ታሪክ የመጀመሪያው የእንጀራ መሸጫ ሱቅ የተከፈተው እዚህ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እዚህ ሀገር እንጀራ በዋናነት ከስንዴ ወይም ከሩዝ ዱቄት ተቦክቶ የማሽላ ዱቄት ይቀላቀልበታል፡፡ የታደሉት ደግሞ ከሀገር ቤት የመጣ የጤፍ ዱቄት ለአመል ይጨምሩበታል፡፡ ስፋቱ የአገር ቤት እንጎቻ የሚያህል ሲሆን ውፍረቱ የሰንበት ቂጣ ታናሽ ወንድም ነው፡፡ ኮከብ የመሰለ ዓይን ባያገኝም፣ ሞጭሟጫ ከመባል ለጥቂት ይተርፋል፡፡ በብዛት የሚጋገረው ከብረት በተሠራ ምጣድ ነው፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከሀገር ቤት የሸክላ ምጣድ የሚያመጡ አሉ፡፡ ሳይሰበር ከደረሰላቸው፡፡
በፉት ስክሬይ ከደርዘን በላይ የኢትዮጵያውያን ሱቆች፣ ከአምስት በላይ ምግብ ቤቶች እንዳሉ ይነገራል፡፡ በአካባቢው ስትዘዋወሩ ቢያነጥሳችሁ ‹ይማርህ› የሚል አታጡም ይባላል፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ስለሚዘዋወሩበት፡፡ በርግጥ ወጣቶቹና ጎልማሶቹ እንዲህ ያለ ነገር አያውቁም፡፡ የሚገርማችሁ እንዲያውም እዚህ አካባቢ አበሻና አበሻ ሲገናኝ ቁጣ እንጂ ሰላምታ አይሰጣጥም፡፡ ሁለቱም ፊታቸውን ኮስተር አድርገው ነው የሚተላለፉት፡፡ እኔ እንዲያውም ‹እዚህ ሀገር የመጣው ያኮረፈው ተመርጦ ነው እንዴ› ብዬ ነበር፡፡
በፉት ስክሬይ የሚጠፋ ቅመማ ቅመም የለም፡፡ በተለይም ሕንድ ሱቅ ውስጥ በሀገራችን የጠፋው ቅመም ሁሉ ይገኛል፡፡ ሞያ በሜልበርን በሽ በሽ ነው፡፡ በርበሬ ከሀገር ቤት ለማስመጣት የአውስትራልያ የምግብ ሕግ ሲያስቸግር እዚሁ ሌላ በርበሬ ተፈጥሯል፡፡ ከሕንዶች ሱቅ የሚገዛ የሚያቃጥል ቀይ ቃሪያ አለ፡፡ እርሱን በኮረሪማ መፍጫ መፍጨት ነው፡፡ ከዚያ ደግሞ ቅመማ ቅመሙን ለብቻ ፈጭቶ መጨመር፡፡ በመጨረሻም አውስትራልያ ሠራሽ ምርጥ ድልህ ይሆንላችኋል፡፡
 አንድ ወዳጃችን ‹ሽሮ እኛን ስላሳደገች በክብር ጡረታ ወጥታ ትቀመጥ› ቢልም ከሀገር ሲወጡ አንዱ የሚናፍቀው ግን ሽሮ ነው፡፡ በአውስትራልያ ልዩ የሆነ የሽሮ አዘገጃጀት ተፈጥሯል፡፡ የባቄላው ዱቄት ከሕንድ ሱቅ ይገዛል፡፡ ከዚያም አመስ አመስ ይደረጋል፡፡ ለቅመማው አስፈላጊ የሆነውን ቅመምም ሕንዶቹ ያመጡታል፡፡ እርሱንም በቡና መፍጫ ፈጭቶ በመጠኑ ማመስ ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱን በባለሞያ እጅ ደባልቆ ምርጥ የውጭ ሀገር ሽሮ ማግኘት፡፡ ችግር ብልሃትን ይፈጥር የለ፡፡
   ለኢትዮጵያውያን እዚህ አንዱ ፈተና ከሀገር ቤት ባህላዊ ምግቦችን ማስመጣት ነው፡፡ የሀገሩ ሕግ ጥብቅ ስለሆነ፡፡ ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ ግን እንደ ካልዲ(የቡናን ፍሬ ያገኘው እረኛ) አዳዲስ ቅጠላ ቅጠሎችን የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን እዚህ ሞልተዋል፡፡ አንድ ቀን ነው አሉ፡፡ መቼም እኛ ታሪክን በጊዜና በሰዓት የመመዝገብ ችግር አለብን፡፡ (ተረቱም ታሪኩም ከዕለታት በአንድ ቀን ብሎ ነው የሚጀምረው) አንዲት የሀገሬ ሰው በግቢዋ ውስጥ ስትዘዋወር አንድ የምታውቀውን ቅጠል የሚመስል ነገር ታያለች፡፡ ጠጋ ብላ ቆረጠችውና መዳፏ ላይ አሸችው፡፡ ልክ ነው፤ እርሱ ነው፡፡ ወስዳ ለጓደኛዋ አሳየቻት፡፡ ሁለቱም ርግጠኞች ሆኑ፡፡ ጉዳዩን ወደ ልጅቱ እናት ‹ሪፈር› አደረጉት፡፡ እርሳቸውም እየተገረሙ ‹እርሱ ነው› አሉ፡፡ ለካስ ጌሾ ኖሯል፡፡ ጠላ ለመጥመቅ ችግር የነበረው ጌሾ በአውስትራልያ ምድር በቅሎ ተገኘ፡፡ ዛሬ በብዙ ኢትዮጵያውያን ግቢ ውስጥ ጌሾ በቅሎ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡
በዚህች ምድር በቅሎ የተገኘው ግን ጌሾ ብቻ አይደለም፡፡ መቼም አገር ደግ ነገር ብቻ አታበቅል፡፡ አንድ ወዳጃችን ሁል ጊዜ አንድ ቦታ እየሄደ ቅጠል ሸምጥጦ ሲወጣ ይታያል አሉ፡፡ መጀመሪያ አካባቢ ማንም ከቁም ነገር አልወሰደውም ነበር፡፡ በኋላ ግን ሸምጣጩ በዛ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም ግራ ገባቸው፡፡ በከተማዋ ውስጥም ወሬው ተባዛ፡፡ የሚሸመጠጥበት ቦታም በአንዳንድ ሰዎች መዘውተር ጀመረ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ከሥሩ እየነቀሉ ወስደው በጓሯቸው ተከሉት፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የአውስትራልያ ፖሊሶች ጉዳዩን ሰሙትና ክትትል አደረጉ፡፡ ለካስ ያ በወፍ ዘራሽ በቅሎ አገር እየተራኮተ የሚሸመጥጠው ጫት ኖሯል፡፡ ፖሊሶቹ እዚያ ቦታ የነበረውን መድምደው አጠፉት፡፡ ችግሩ ግን እነርሱ ሳይደርሱ በፊት በየግቢው ተዛምቷል፡፡ አንዳንድ ቤት ስትሄዱ ጫት በኩራት በቅሎ ታዩታላችሁ፡፡
ፉት ስክሬይ በአበሾች ዘንድ ከምትታወቅበት ሀብቷ አንዱ ምርጥ የሆነ ቁርጥ ሥጋ መሸጫ ስለሆነች ነው፡፡ መቼም ቁርጥ እየበላን ቁርጥ ነገር አለመቻላችን የሚገርም ቢሆንም የሀገሬ ሰው የትም ቦታ ቢሄድ፣ ምንም ዓይነት ትምህርት ቢማር ሊያጣው የማይፈልገው ነገር ቢኖር ቁርጥ ሥጋ ነው፡፡ ከነአባባሉም ‹የተማረ ሰውና የተሳለ ቢላዋ ሥጋ አያጣም› አይደል የሚባለው፡፡ እዚህ ከተማ በጥሬ ሥጋ ሻጭነታቸው የታወቁ ቤቶች አሉ፡፡ ነጭ፣ ቀይ፣ ጎድን፣ ዳቢት፣ ሻኛ፣ ለቁርጥ፣ ለወጥ እያሉ የሚያስተናግዱ፡፡ እነርሱ ጋ ገብቶ አለበለዚያም ደግሞ ሰፈር ይዞ መጥቶ ቁርጥ በኅብረት መብላት እዚህ የተለመደ ነው፡፡ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ አውስትራልያ ዘመድ ለመጠየቅም ሆነ ለመዝናናት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን በአውስትራልያ ቁርጥ ፍቅር ተነድፈው ነው የሚመለሱት፡፡ አንዳንድ የአውሮፓና የአሜሪካ ወዳጆቼ ጋር ስንጻጻፍ እንዲያውም ‹የአውስትራልያን ቁርጥ ሳትበላ እንዳትመጣ› ይሉኛል፡፡ እስቲ ቀምሼ እመሰክርለታለሁ፡፡
‹አይ እኔ ማን እንደነካው የማይታወቅ ሥጋ አልበላም› ለሚሉ አለያም ደግሞ ‹የተሸረፈ ጥርስ፣ ደልደል ያለም ላት አይቶ መርጦ ተከራክሮ መግዛት› ለሚያምራቸው ወደ ገጠሩ ክፍል ወጣ ማለት ነው፡፡ ከበግ አርቢ ገበሬዎች ጋር ምን የመሰለ የደብረ ብርሃን በግ ይገኛል፡፡ ማረዱን ባይፈቅዱላችሁም መባረኩን ይፈቅዱላችኋል፡፡ እነርሱ ደግሞ ገፍፈውና ቆራርጠው ይሰጧችኋል፡፡ ከዚያ በኋላማ ‹አቤት ባለፈው ለፋሲካ የገዛሁት ምን የመሰለ በግ› እያላችሁ ሾላ ገበያ የሄዳችሁ ማስመሰል ነው፡፡ 
ሜልበርን አውስትራልያ፡፡
 
ምንጭ  https://www.clickhabesh.com/~clickha1/?cat=185

ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በህንዳዊ ፕሮፌሰር ሲማሩ ነበር(ተመስገን ደሳለኝ)


“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡
እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!
ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…
በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤ ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ተመስገን ደሳለኝጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?
ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ..
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤
የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡
ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባትእንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?
በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን?…ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

 ምንጭ https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/08/27/123-5/

Monday, August 26, 2013

እኛና ስብሃት (የሞተው ማነው?)




… በጫጫታው መሀል ዝም ማለት … አድማጭ ያደርጋል፡፡ የሚደመጥ ነገር ሳይኖር ዝም የሚል ግን በህይወት አለመኖሩን እንዳረጋገጠልን ይቆጠራል። ህይወት እንዳልሞተች የምናረጋግጠው ህያው ነኝ ባይ ሲገልፃት ነው፡፡ የሞተው ሰውዬ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር መሆኑኑ ተማምነን ቀብረነው ነበር። አሁንም ግን መግለፁን ቀጥሏል፡፡ … አልሞተም ማለት ነው፡፡ ወይ እኛ ሞተናል፡፡
ስብሐት ሞቶም እያነጋገረን ነው፡፡ አንዳንድ ሙታንን ልንቀብራቸው አንችልም፡፡ አንደፍርም። ሞተው ቢመሩን እንመርጣለን፡፡ በህይወት ያለነው ከእነሱ ጋር አንመጥንማ! እነሱን በማሞገስ አልያም እነሱን በመርገም ብቻ ነው አለመሞታችንን የምናረጋግጠው፡፡ እረፍት ልንሰጣቸው አንችልም። እነሱን ሳንመረኮዝ ምን ላይ እንቆማለን? ከእነሱ መቃብር ጋር የእኛ ትንሳኤ ተሳስሯል፡፡ የኛ የትንንሾቹ ሰዎች፡፡ We stand on the shoulder of giants not to see further … በህይወት መኖራችን ራሱ ስለሚያጠራጥረን ነው፡፡
በጫጫታው መሀል ዝም ማለት አልቻልኩም። … ሚልኪ ባሻ ጀመረው፡፡ ሙታንን ቀስቅሶ ማናገሩን፡፡ ጠርጢዎስ መለሰለት፡፡ ጠርጢዎስ ከቫቲካን … ሁሌ መልስ ነው የሚሰጠው፡፡ መልሱ ላልተጠየቀበት ጥያቄ መሆኑ የለመድነው አባዜው ነው፡፡ … የሆነ ነገርን ሁሌ መመርኮዝ ያስፈልገዋል። “መንጠልጠል” ያለው የአለፈው ሳምንት ፀሀፊ ጠርጢዎስን በተለይ ይገልፀዋል፡፡ … ጠርጢዎስ፡- reacts on Issues before acting towards them … ከዚህ በፊት በሀይማኖት ክርክሮች ላይ አይተነዋል፡፡ በሰው ሀሳብ ላይ ከመመርኮዝ አልፎ … መገንደስ ይወዳል፡፡ “ጥሪዬ ነው” ብሎ ወደሚያምንበት ሀይማኖቱ አቅጣጫ ነው የሚገነደሰው፡፡ ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ እንደዛ አይነት ሰው ነው … It takes all kinds!
መጀመሪያ ሰላሳ ሰዎች ሆነን በሰውየው ትከሻ ላይ ወጣን፡፡ ሩቅ ለማየት ወይንም ስብሐትን ለመግለፅ ሳይሆን … ራሳችንን ለመግለፅ ወይንም ለማየት ብለን ነው፡፡ ሰውየው ሞቷል፡፡ እኛ ስናመሰግነውም ሆነ ስንሰድበው አይሰማውም። ስለዚህ፤ ምስጋናውም ሆነ ክብሩ … ጥቅሙም ሆነ ጉዳቱ … ለተንጠለጠልንበት ሀውልት ሳይሆን ለእኛው ነው፡፡
እሺ! … ሰላሳ ሰዎች የተንጠለጠሉበት መፅሐፍ በሰላሳ ሺ ሰዎች (ወይንም በላይ) እየተነበበ ሊሆን ይችላል አሁን፡፡ በሰላሳ ሺ አፎች ስለ መፅሐፉ ይወራል፡፡ የተወራው በሀምሳ እጥፍ ተባዝቶ ይራገባል፡፡ ይሄ ሁሉ ሰው ስለ ስብሐት ሲያወራ፤ የስብሐት መልክ እንደ አነበበው ተመልካች እይታ ብዙ ሆኖ ቢሆን “እሰየው” ነበር፡፡ “ስብሐት የሰውን ሁሉ መልክ ይመስላል፤ ወይንም ስብሐት ህይወትን በሙሉ የሚመስል ገፅታ አለው … ስብሐት ህይወት ነው፤” ብለን እንስማማ ነበር፡፡ አሁን ባልኩት ብዙ ገፅታ መስማማት ማለት፤ ህይው መሆን ማለት ነው፡፡ እኛም ሆነ ስብሐት በእኛ ውስጥ ወይንም አማካኝነት ህያው ሆነ ማለት ነበር፡፡
ለምሳሌ፤ የአጋፋሪ እንደሻሁ (ገፀ ባህሪ) በእርግጠኝነት የጥበብ (ውበት) ልኬት ናቸው፤ ካልን… የህይወትም ልክ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ጥበብ ህይወትን አጠቃሎ የሚወክል፣ የሚገልፅ፣ የሚተረጉም ነገር ስለሆነ ነው፡፡ በአጋፋሪ እንደሻው አማካኝነት ራሳችንን ማየት ካቃተን፣ ድርሰቱ ለህይወት፣ ከህይወት … ለህያዋን አይደለም፡፡ በአጋፋሪ እንደሻው ራሳችንን ማየት ቢያቅተን እንኳን … ቢያንስ ስብሐትን እንዳናይ መጠንቀቅ ነበረብን፡፡
“ሀምሌትን ስናይ ሼክስፒርን አየን” ከማለት አይተናነስም፡፡ ያሳዝናል … ያሳፍራል፡፡ ስብሐት ምን ያድርግ … ሌቱም አይነጋልኝ ላይ ስላለው የክንፈ ገፀ ባህሪ? የሌቱም አይነጋልኝ መፅሐፍን በዛሬው እለት ከገበያ ገዝቶ ቤቱ ገብቶ እሚያነብ ሰው ተጠያቂ የሚያደርገው ለንባቡ (አንብቦም ለመፀየፉ) … ያው የፈረደበትን ስብሐት ነው፡፡ ሰውየው እኮ ሞቷል፡፡ … ለኒዩክሊየር ጦር መሳሪያ ስጋት ኤንሪኮ ፈርሚ እና አንስታይን ምን ያድርጉ? … ጦር መሳሪያውን አሁን ያለ ሰው ነው ለክፉም ሆነ ደግ መርጦ የሚጠቀምበት … የቦንቡ መነሻና መድረሻ አሁን ያለ ሰው ራሱ ነው።
በ “ሌቱም አይነጋልኝም” ውስጥ ያለው ገፀ-ባህሪ ሳይሆን አሁን በማንበብ ላይ ያለ ሰው ነው ልክ ወይንም ስህተት፡፡ በሀምሌት ገፀ ባህሪ ውስጥ ሼክስፒርን ይቅርና … ሀምሌትንም ራሱን በማይቀያየር መልክ አናገኘውም፡፡ የኢትዮጵያዊው ሀምሌት ከእንግሊዛዊው ይለያል፡፡ እንደ ተዋናዩ የአተረጓጐም ብቃት … ገፀ ባህሪውን የመረዳት … ወይንም ወደ አካል ቋንቋ ቀይሮ የማቅረብ አቅም፡፡ የስብሐትም ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡
“If Hamlet has something of the definiteness of a work of art, he has also all the obscurity that belongs to life. There are as many Hamlets as there are melancholies.” (The critic as Artist)
“አምስት ስድስት ሰባት” ላይ ያለው ድህነት … የስብሐት አይደለም፡፡ በፅሁፍ ላይ የሰፈረው ገፀ-ባህሪ የኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው፡፡ የገፀ ባህሪውንም፤ ገፅ እና ባህሪ ደራሲው የሚስለው እኮ አንባቢው ልቦና ውስጥ ነው፡፡ … አንባቢ እኮ በፈጠራው ስራ ላይ ከግማሽ በላይ ባለቤት ነው፡፡ ደራሲው የሚፅፈው በሰዎች ልቦና ላይ ነው፡፡ “አምስት ስድስት ሰባት” ላይ ያለው ድህነት የእናንተ ነው፡፡ ስብሐት የሚባል ሰው ከእንግዲህ የለም … እረፉት!” ስብሐት አለ፤ ወንጀለኛ ወይንም ጠንቅ ነው… ብለን ስንወነጅለው እንኑር የምትሉ ከሆነ … እናንተ ናችሁ የሌላችሁት፡፡ የስብሐት ህይወት ላይ የምታነሱት የግብረ ገብ ጥያቄ … መቅረብ ያለበት … ለእናንተ ነው፤ ለእሱ አይደለም። “ቢግ ብራዘር አፍሪካ” ላይ ተደረገ ለተባለው ነውር ተጠያቂው ስብሐት ሊሆን አይችልማ፡፡ እናንተው ናችሁ ተጠያቂ፡፡ ቤቲም ልትጠየቅ አትችልም … ቤቲ ገፀ ባህሪን ተላብሳ ተወነች፡፡ እናንተ ገፀ ባህሪውን ተላብሳችሁ ተመለከታችኋት፡፡ ገፀ ባህሪውን ተላብሳችሁ ስብሐትን እንዲፅፋችሁ ወሰወሳችሁት። እሱ ለመፃፍ የተወሰወሰውን ያህል እናንተ ለማንበብ ተወስውሳችኋል፡፡ በሱ ውስጥ የምታነቡት ራሳችሁን ነዋ!
ስለዚህ ስብሐት ስንት መልክ አለው? ከተባለ … እኔ የምመልሰው “የእናንተን መልክ ብዛት” ብዬ ነው፡፡ ስብሐት ከስንት ብሔር መጣ? እናንተ ከመጣችሁበት የብሔር አማራጭ፡፡ ከስንት ማህፀን? እናንተን ካማጣችሁ የማህፀን ዥንጉርጉርነት … ወዘተ፡፡ ግን ተመልሼ ደግሞ ተጠራጠርኩ … ዥንጉርጉር ቢሆን ኖሮማ አመጣጣችሁ፤ ከሁለት አይነት የዕይታ አማራጭ ውጭ በተመለከታችሁ ነበር፡፡ ስብሐትን ወደ ልቅ ወሲብ አባትነት እና ልቅ የነፃነት ተሟጋች ከፍላችሁ ቁጭ አትሉም ነበር፡፡
… ከሁለት አማራጭ በላይ ያለ ለማስመሰል … በሁለት ድምፅ ደጋግሞ ለመዘመር … በየሳምንቱ ብዕር እና መርዝ እየቀላቀላችሁ የምታጠጡን ለምንድነው? … ብዕር በሽቶም ሆነ በመርዝ ቢሞላ ለስብሐት አይጠቅመውም፡፡ አይጐዳውም፡፡ ጉዳቱም ሆነ ጥቅሙ ለእናንተው ለራሳችሁ ነው፡፡ እንዲያውም ምን ጉዳት አለው? … ጥቅም ብቻ ነው። ግን ጥቅሙ “በስብሐት ላይ ተከራከርኩ!” ለማለት ያህል ብቻ ነው … በስብሐት ላይ ተከራከርኩ … ከሚሉት የበለጠ ደግሞ “አከራከርኳቸው!” የሚሉት የበለጠ ትርፍ ያገኛሉ፡፡ ስብሐት ቢወገዝም ሆነ ቢሞገስ የመፅሐፉ ሽያጭ ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡ “ሰላዩ ተያዘ” ወይንም “ሰላዩ አመለጠ” የሚለውን ዜና የሚያትሙ መፅሔቶች በሁለቱም ረገድ ብዙ ኮፒ ይሸጣሉ፡፡ “The spy catcher effect” እያሉ ይጠሩታል፡፡ win win situation…ነው፡፡
እንጂማ፤ ስብሐትን የሚከተሉ ሰዎች በህገ መንግስቱ የህግ ከለላ አይነፈጋቸውም፡፡ በቤተ ክርስቲያኑም ፍትሀት አይከለክላቸውም፡፡ የስነ ምግባር አስተሳሰባችን ከመሰረቱ በተነቃነቀበት የወቅቱ ትውልድ ላይ … ደራሲውን በስነ ምግባር ለመክሰስ መሞከር … ከራስ ጋር ፍልሚያ ውስጥ መግባት ነው፡፡
በራችንን ለውጭው አለም ተፅኖዎች ከፍተን፣ ግን ዘግተን ለመቀመጥ የምንሞክረው በር፤ ምንም አይነት የስነ-ልቦና መሀንዲስ (ለበሩ) ማጠፊያ… ለክርክራችሁ ደግሞ ማጣፊያ መፍትሔ ሊሰጣችሁ አይችልም፡፡ ስብሐት … በመስታወት የማይታየውን ማንነታችንን አውጥቶ … አሳየን፡፡ በተፈጥሮአዊነት የአፃፃፍ ዘዴ ተጨባጩን ሲያሳየን ወነጀልነው፡፡ … ተፈጥሮአዊነትን ትቶ የሀያ አንደኛውን ክፍለ ዘመን የአፃፃፍ ዘይቤዎች … ሱሪያሊዝምም … ሆነ ፋንተሲ … መጻፍ ሲጀምርም ወነጀልነው፡፡ በተፈጥሮአዊነት ተፈጥሮአችንን ስላሳየን ወነጀልነው፡፡ በምናባዊ የአፃፃፍ ዘይቤ ተፈጥሮአችንን “ሮማንቲሳይዝ” አድርጐ ሳያሳየን ሲቀርም ወንጀል ሆነ፡፡ “The nineteenth century dislike of Realism is the rage of caliban seeing his own face in the glass. The nineteenth century dislike of Romanticism is the rage of caliban not seeing his own face in a glass” (The Picture of DNIAN GRAY) ለምን ታሳየናለህ? … እና ለምን አላሳየኸንም? የሚለውን ግራ የተጋባ ጥያቄ መመለስ የሚችለው … ምን ማየት እና አለማየት እንደሚፈልግ የሚያውቅ ሰው ብቻ ነው፡፡ ይህንን መምረጥ የሚችል ሰው ደግሞ ራሱ ደራሲ ነው። ተራ አንባቢ የተሰጠውን መቀበል የተጣለበት ፍርጃ ነው፡፡ ተቀብሎ ሲያበቃ “አልቀበልም” የሚል ድንፋታ የትም አያደርስም … ጋዜጣ ላይ ስምን አትሞ ከማስነበብ በሚገኝ “በህይወት አለሁ ለካ!” የጉራ ባዶነት ውስጥ ከመሳከር በስተቀር፡፡
 ምንጭ addisadmas

Saturday, August 24, 2013

የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ

የአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ

2012-03-02t171851z_319859376_gm1e83303nh01_rtrmadp_3_kenyaየአቶ መለስ ሞት እና ጥቅማጥቅሞቹ፤ ስላቅ እና ሀቅ
ሰላም ወዳጄ… ተጠፋፍተናል ግዴለም እቅ….ፍ አድርጌ ሰላም ልበልዎት… እንዴት አሉልኝ.. እኔ የምለው አቶ መለስ ዜናዊ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞቱ እንደዋዛ አንድ አመት ሞላቸው አይደለም እንዴ… ወይ ጉድ ጊዜው እንዴት ይሮጣል ጃል… ምን እንደሚያመጣልን እንጃለቱ፤ አሯሯጡ ግን ወርቅ በወርቅ እንደሚያንበሻብሽ አትሌት ነው፡፡ ይሁና እኛ እንደሆነ “በርታ ግፋ” እያልን ከመደገፍ ወደ ኋላ አንልም… አረ እንደውም ጊዜ ሆይ፤ …ሩጥልኝ ልጄ አምልጠልኝ ልጄ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ለኔውም አልበጄ… ብለን እንደ ዶክተር ፈቃደ አዘዘ እንቀኛለን፤
እናልዎ ወዳጄ ዛሬ የመጣው ይምጣ ብዬ ሙት ወቃሽ አታድርገኝም ሳልል የአቶ መለስ መሞት ለሰፊው ህዝብም፣ ሰፊ መሆን ለተሳነው ኢህአዴግም፣ መጠን አልባ ለሆኑት ተቃዋሚዎችም በጣም ስንሳለቅ ደግሞ ለወይዘሮ ሀዜብ ሳይቀር በርካታ ጥቅማጥቅሞች አሉት ብዬ ልሟገትልዎ ነው…!
በ22 ዓመት ውስጥ ያየናቸው አቶ መለስ እንደው ዝም ብለው የእነ ስምሃል አባት እንደው ዝም ብለው የነ ወይዘሮ አዜብ ባለቤት እንደው ዝም ብለው የአቶ ዜናዊ አስረስ ልጅ ብቻ አልነበሩም፡፡ አቶ መለስ ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ኢህአዴግ ሊቀመንበር ከዛም ውስጥ ደግሞ እጅግ አደገኛ የሚባለው ህውሃት አባወራ የሀገሪቱ ጦር ሃይሎቹ አዛዥ (አሃ ለካስ ጦር ሃይሎች የድሮው ነው… እንደው የድሮ ስርዓት ናፋቂ የሆንኩ ሰውዬ… አሁን መከላከያ ነው ማለት ያለብን… በመከላከያው ውስጥ ጦር አለ ከተባለ እንኳ ጦሩ አቶ መለስ ነበሩ… ስለዚህ የጦር ሃይሎች አዛዥ ሳይሆኑ በመከላከያ ውስጥ ጦር የሆኑ ሰውዬ ነበሩ ብሎ አለመመስከር ጡር ነው… ) በጥቅሉ ሰውዬው የመላዋ ኢትዮጵያ ፈላጭ ቆራጭ ነበሩ፡፡
አሁን እኒህ ሰውዬ ሞተዋል… እስቲ ከተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ጋር አያይዘን የሞታቸውን ጥቅማ ጥቅሞች እንዘርዝር…
ለአባይ ግድብ ሲሉ አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
አባይን አቶ መለስ እንዴት እንዴት ይገደብ ብለው እንደጀመሩት ተነጋግረን ተነጋግረን መቼም ከስምምነት ላይ የደረስን መስለኛል፡፡ አባይዬ ድንገት ያለ ዕቅድ… ያቺ እነ ሙባረክን እንደ ሾላ ፍሬ ርግፍ ርግፍ ያደረገች አብዮት ወደ እኛም ትመጣ ይሆናል… በሚል ስጋት ነው ለማስቀየሻ ተብላ ነው የተጀመረችው፡፡
ለዚህ ዋና ማስረጃ በአምስት አመቱ ትራስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አለመፃፏ ሲሆን ሌላው ደግሞ የፕሮጀክቷ ስም አሁንም አሁንም መቀያየሩ ድሮውንም ቃሚዎች “በምርቃና” እንደሚሉት አይነት የታሰበች ድንገቴ ስራ መሆኗን ያሳብቃል፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ጭምር በተለይ ውጪ ሀገር የሚኖሩ “የኢህአዴግ ወጣት ክንፎች” የአባይን ግድብ “ሚሊንየም ዳም” ነው የሚሏት…! ህዳሴ መባሏን ከነጭርሹም አለሰሙም!
የሆነው ሆኖ አባይን አቶ መለስ ድንገት እንደጀመሯት ሁሉ ድነገት ያቋርጧታል የሚል ስጋት ሰቅዞ የያዛቸው ብዙዎች ነበሩ… (ብዙዎች ያልኩት አካብዶ ለማውራት እንዲመቸኝ ብዬ እንጂ… እንዲህ የሚያስቡት ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ስታስቲክስ አልሰራሁም፡፡ ነገር ግን ያናገርኳቸው ሁሉ የሰጡኝ ማብራሪያ አሳማኝ ነበር፡፡)  እንደሚታወቀው አባይን ለመገደብ የሚጠይቀው የገንዘብ አቅም ቀላል አይደለም፡፡ በየመስሪያቤቱ በጥፊም በርግጫም የሚደረገው መዋጮ አስከምን ድረስ እንደሚያስኬድ የሚያውቁት እርሳቸው ብቻ ነበሩ… እናም የሆነ ቀን የሆነ ቀን ማጣፊያው ያጠራቸው ቀን መለኛው መሌ በሆነ መላ ግንባታው እንዲቋረጥ ያደርጉ ነበር የሚለው ነገር ውሃ የሚያነሳ ሆኖ አግኝቼዋለሁ… ይህንን እያንሰላሰልን ታድያ ምን ይበጃል እያልን ስንጨነቅ አቶ መለስ ሞቱ… ለአባይ ሲባልስ እንኳን ሞቱ! ልክ እርሳቸው ሲሞቱ ሌጋሲን ማስቀጠል በሚለው መርህ ከዋናዎቹ አንዱ አባይ ግድብ አይቋረጥም የሚለው ሆነ፡፡ እሰይ እንኳንም አልተቋረጠ፡፡ እንኳንም ሞቱልን…!
ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
ተቃዋሚዎች በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግን ሲቃወሙ ከሁሉ በላይ የሚበረታባቸው የአቶ መለስ ግልምጫ ሽሙጥ እና እርምጃ ነበር፡፡ ሲያሻቸው ጣት እንቆርጣለን እያሉ ሲያሰኛቸው ሰብስበው እስርቤት እየላኩ አቶ መለስ ተቃዋሚዎች ላይ እንደሚጨክኑት ኢህአዴግ አይጨክንባቸውም፡፡ እውነቱን እንበለው ካልን ደግሞ መጨከን ብቻም ሳይሆን በፖለቲካው ቼዝም አቶ መለስን ተቃዋሚዎቹ አይችሏቸውም ነበር፡፡ ተቃዋሚዎቹ ፈረሳቸውን ቆስቁሰው ገና “ቼ…” ብለው ሮጥ ሮጥ ማለት ሲጀምሩ መለስ በወታደሮቻቸው ፈረሶቻቸውን እየሰነከሉ፤ ንግስታቸውን “ቼዝ” እያሉ ተቃዋሚዎቹን መላወሻ አሳጥተዋቸው ነበር፡፡
አሁን አቶ መለስ ሞተውላቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች መቼም ጨካኞች እንዳይባሉ ሰግተው በአቶ መለስ ሞት ሀዘናቸውን ሲገልፁ ቢሰማም ውስጥ ውስጡን ግን እሰይ ግልግል እንደሚሉ ማወቅ አያቅተንም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ተቃዋሚዎቹ ትንሽ ጠንከር ካሉ ኢህአዴግ ውስጥ ክፉኛ የሚገዳደራቸው አለ ብሎ ማመን ይቸግራል፡፡ ስለዚህም ለተቃዋሚዎች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
ለራሱ ለኢህአዴግ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
በተለይ ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመስለኛል ህውሃት ለሁለት ቃቃቃ…ቃ ብሎ ከተሰነጠቀ ጊዜ በኋላ የኢህአዴግ ስብዕና ኮስምኖ የአቶ መለስ ዜናዊ ስብዕና ደግሞ እጅግ በጣም የጎላበት ወቅት ነበር፡፡ አረ ከነጭርሹ መለስ ከልለውን ኢህአዴግን ማየት ተስኖን ነበር…! በዛ አያያዙ ጥቂት አመታት ቢገፉ ኖሮ ኢህአዴግዬ መለስ በተባለ ቅብ ተሸፍና እሰከመፈጠሯም እንረሳት ነበር፡፡
አሁን ግን መለስ ሞቱ ኢህአዴግ የሚባል ፓርቲም ምን አይነት ቅርጽ እና መልክ እንዳለው ሊታወቅ በቃ፡፡ ታድያ ለኢህአዴግ ሲባል ቅርፀ ግንባሯ እንዲታይ ሲባል፤ ያለ መለስ መኖር እንደምትችል ለማሳየት ሲባል፣ እንኳን መለስ ሞቱላት ብንል ምን ግፍ ተናገርን ይባላል፡፡
ወላ ለወይዘሮ አዜብ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
መጣች ስላቋ… ወይዘሮ አዜብ ቀላል ክብሮ ሆኑ እንዴ…! ክብሮ ማለት አራዶቹ ከበረ ከሚለው አማርኛ ቃል የወሰዷት ስትሆን የተከበረ ለሚባል ሰው የሚሰጥ ማዕረግ ነው፡፡ አዎ ወሮ አዜብ ክብሮ ሆነዋል፡፡ የመለስ ፋውንዴሽን ፕረዘዳንትነት አቶ  መለስ ባይሞቱ ኖሮ ከየት ይመጣ ነበር… አረ እንኳን ሞቱላቸው… (እዝችጋ እንኳ ጨክኛለሁ ይቅር ይበለኝ!) የምር ግን ወይዘሮ አዜብ እንደልቸው መልካም ገፅታቸውን እንዲገነቡ የአቶ መለስ ሞት ትልቅ እድል ሰጥቷቸዋል ብዬ አምናለሁ… ዝም ብለን ከመረመርን ወይዘሮ አዜብ በአቶ መለስ ሞት ጉዳት እንደገጠማቸው ሁላ በርካታ ትቅማጥቅሞችንም እንዳገኙ ግን መጠርጠር አያቅተንም!
ለችግኝ ተከላ ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ!
አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው እና በበትረ ስልጣናቸው ጊዜ ሰዎች አጥብቀው የሚያማርሯቸው በችግር ተከላ ነበር፡፡ አሁን ግን ሞቱ፣ አመትም ሞላቸው በስማቸውም በርካታ ችግኞች እየተተከሉላቸው ነው፡፡ በእውኑ ለእነዚህ ችግኞች ሲባል አቶ መለስ እንኳን ሞቱ ብንል ማነው እርኩስ የሚለን…! ማንም!
source... http://www.abetokichaw.com/

Wednesday, August 21, 2013

ደብዳቤ ከመለስ ዜናዊ (ይድረስ ለጓድ ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ)

ደብዳቤ ከመለስ ዜናዊ (ይድረስ ለጓድ ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ)

f44997cb312b542bbd55c895274ee230_XL220px-Meles_Zenawi_-_World_Economic_Forum_Annual_Meeting_2012
ካለሁበት ቦታ ጓዳዊ ሰላምታየ ይድረስህ። ከመጣሁ ጀምሮ ደብዳቤ ልጽፍልህ አስቤ ሳይሳካልኝ ስለቀረ እስከአሁን ቆየሁ። እዚህ ከመጣሁ ብዙ ነገር አጋጥሞኛል። በየጊዜው ብዙ ሰወች ስለሚመጡ፣ ስለናንተ ብዙ ነገር ይደርሰኛል።
እኔ ያለሁበት ቦታ በጣም የተለየ ቢሆንም፣ እዚህ ከመጣሁ በጣም ብዙ ሰው አግኝቻለሁ። ብዙወች ያውቁኛል። እኔም የማውቃቸው ብዙ ናቸው። ተሰባስበው ያነጋገሩኝ ብዙወቹ እኔ በተለያየ መንገድ ከምድር ወደዚህ የላኳቸው ናችው።
እንድሁም ታዋቂ የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞችም በቦታው ነበሩ። የኢትዮጵያዊያኖችን በይበልጥም የዘመዶቻቸውን ቁስል ላለመቀስቀስ ስል ስም አልጠራም። ዝርዝሩን ከፈለግክና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲናገር ከፈቀድክለት ይነግርሃል። የደህንነት መስሪያ ቤታችን ያረጋግጥልሃል።
በጣም ቁጥር ስፍር የሌላቸው፣ ትግራይን ለማስገንጠልና ኤርትራን ነፃ ለማውጣት ብለህ፣ ከኢትዮጵያ ጦር በኩል፣ ከህወሃት በኩል፣ ከሻብያ በኩል፣ ያስጨረስከን ነን ይሉኛል። በጣም የገረመኝ ሁሉም በአንድ ሆነውና ተስማምተው ነው
ያነጋገሩኝ። በተደጋጋሚ ያቀረቡልኝም ጥያቄ እኛን አስጨረሰህ ትግራይና ኤርትራ ምን የተሻለ ነገር አገኙ፤ ህዝቡ ከመለመን፣ ከመሰደድ፣ ከርሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከአምባገነን አገዛዝ ነፃ ወጣ ወይ የሚል ነበር። እንድሁም በትግራይ ተራራወች የጨፈጨፍናቸው የደርግን ግድያ ሸሽተው የነበረ የኢህአፓ ወጣቶች፣ በአዲስ አበባ ጎንደርና ሌሎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው በአጋዚ አነጣጣሪ ተኳሾች በኔ ትዛዝ ያስገደልኳቸው፤ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላና በደቡብ ህዝቦች በዘር ለያይተን ያጋደልናቸውና፣ በበደኖ፣ አርባጉጉ ከነህይወታቸው ገደል ያስጨመርናቸው፣ የብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል በማለት ቀስቅሰን በየጫካውና በየከተማው ኦነጎች ናችሁ እያልን የገደልናቸው የወለጋ፣ ባሌ፣ ጅማና ሃረር ወጣቶች፤ እንዲሁም ነፍጠኛ በማለት ፈርጀን እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ ያደረግናቸው ገበሬወች ነበሩ። በተጨማሪም በኤርትራ በየዋሻው ታስረው በርሃብና በግዳጅ ስራ ጠያቂ ሳይኖራቸው ያለቁ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ በተለያዩ ቦታወች እየተያዙ እንዲገደሉና እንዲሰወሩ ያደረግናቸው ኢትዮጵያዊያን በጣም ብዙ ነበሩ። እነዚህም ያናገሩኝ በአንድ ላይ ሆነው ነው። ሌሎቹ ቁጥራቸው የሚበዛው ከኢሳያስ ጋር በነበረን የግል አለመግባባት በባድሜ ስም ጦርነት ከፍተን ያስጨፈጨፍናቸው ነበሩ። ሁሉም እንዲወክላቸው የመረጡዋቸው፣ እቤታቸው በር ላይ በህወሃት ተኳሾቸ ያስገድልኩዋቸው መምህር አሰፋ ማሩ ነበሩ። ሁሉም ባንድ ቃልና በከፍተኛ ትዕግስት አናገሩኝ። አንተም ወደዚህ ትመጣለህን ብለው የተወሰኑት ቀለዱብኝ። ያሉበትን አለም የሚገዛው፣ እውነት፣ ሰባአዊነትና ትግስት ነው። ብዙወቹ ለአገር ሰማዕታት የሚሰጥ ልዩ የክብር ቦታ ተሰጥቷቸዋል።
የኔ መምጣት እንደተሰማ ካናገሩኝ ውስጥ ራስ አሉላ አባ ነጋ፣ አጼ ምኒሊክ፣ አጼ ዩሃንስ፣ ደጃችህ ገረሱ ዱኪ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ በላይ ዘለቀ፣ ሞገስ አስገዶም፣ አብርሃም ደቦጭ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ አርበኞች ነበሩ። ከሁሉም ግን ራስ
አሉላ በጣም ተበሳጭተዉና ደማቸው ፈልቶ፣ ይህን ከሃዲ አምጡልኝ በማለት፣ ምን ለማድረግ ነው ስንት ህዝብ መስዋዕት ሆኖ ያቆያትን አገር ለማፍረስ ይህን ሁሉ ያደረግከው በማለት ጠየቁኝ። እኔም በፀፀትና በፍርሃት መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። ከዚያም ከፊቴ ጥፋ ብለው አባረሩኝ። እኔም በሁለት እሳት መካከል ሆንኩ፣ አንዱ በስራዬ የተፈረደብኝ ሌላው ደግሞ የደረሰብኝ ፀፀት ነበር። ከዚያም ሃጢያቴን ለመናዘዝ አባታችን መምጣታቸውን ስለሰማሁ መፈለግ ጀመርኩ። እንደምንም አገኘኋቸው። እንደፊቱ የሚፈሩኝ መስሎኝ አባት ያሳልሙኝ ብዬ ጠጋ ስል፣ ክላ በማለት መቋሚያቸውን አንስተውና እኔንም አሳስተህ አስቀስፈኸኛል ብለው አባረሩኝ። ተስፋ ባለመቁረጥ ስፈልግ ሌላ አባት አገኘሁ። ቀረብ ብዬ አባት ሃጢያቴን መናዘዝ፣ ንስሃ መግባትና ካለሁበት እሳት መውጣት እፈልጋለሁ ስላቸው፣ ስለአንተ ቀድሜ ብዙ ሰምቻለሁ፣ መብርቅ መትቶህ በድንገት ነው እንዴ ወደዚህ የመጣህው አሉኝ። አይ አይደለም፣ ለረጂም ጊዜ ታምሜ ነበር አልኳቸው። እሳቸውም መልሰው ታዲያ የንስሃ እድሜ ተሰጥቶህ ይህን ሁሉ ጉድ ሃጥያት ተሸክመህ እንዴት ሳትናዘዝ ትመጣለህ ብለው በመገሰጽ ይቅርታ መጠየቅና ንስሃ መግባት ያለብኝ ግፍ በፈፀምኩበት በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት መሆኑን ነገሩኝ። በዚህም የተነሳ ይህን ደብዳቤ ፃፍኩልህ።
ጓድ ሃይለማርያም፣ በቅርብ የመጡ ብዙ ሰወች አገኘሁ። ከሁሉም የሰማሁት ተመሳሳይ ነው። አንተና የህወሃት ኢህአድግ ሰወች የመለስን “ሌጋሲ” (ውርስ) ሳይበረዝ ሳይከለስ እንቀጥላለን እያላችሁ ትፎክራላችሁ አሉ። ይህ የምትሰሩት
ስራ ሃጢያቴን እያባዘው ነው። አዜብ የመለስ ህይወት ታሪክ ሲነገር ገድሉ በአግባቡ አልተገለፀም አለች አሉ። ይህ ሁሉ ለኔ ምን ይጠቅመኛል? ያለሁበት ቦታ ውሸት፣ ከንቱ ውዳሴና ማሞካሸት የሚያስፈልገው አይደለም። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት የማይቀረው እየመጣ መሆኑን አውቄ እንኳ የሰረፀብኝን ትዕቢት ማሸነፍ፣ እውነቱን መቀበል፣ ያጠፋሁትን መናገርና ይቅርታ መጠየቅ አልፈለግኩም። እንዳውም እስከመጨረሻው ጊዜ ድረስ ከከፋፋይና ዘረኛ ስራየ አልተገታሁም።
አሁን ሌላ ሰው ነኝ፤ አልዋሽህም። ሃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ስክድና ሚልዮኖችን እንዳሸበርኩ ሁሉ፣ ጥላየን ስፈራ፣ ራሴን በከንቱ ስከላከል ኖሪያለሁ። እናንተም በፍርሃትና በጭንቀት ተሸፍናችሁ ማየት ያልቻላችሁትን እኔነቴን ልግለጽላችሁ። መሪ መሆን ማለት ከምንም ነገር ቅድሚያ ሃላፊነት መውሰድ ነው። ምንም እንኳ በስሬ የተሰለፉት እበላ ባዮች የተንኮል ተልዕኮየን ለማሳካት ቢረዱኝም፣ በአገሩ ጉዳይ ገለልተኛ ሁኖ፣ የተጫነውን ሁሉ ተሸክሞ የሚኖረው ብዙ ኢትዮጵያዊ ላደረግኩት በደል በዝምታው አስተዋፅዖ አድረጓል። እኔም ለማደርገው ሁሉ ሃላፊነት ሳይሰማኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳሰቃይና ስጨርስ ኖሪያለሁ። አንተ ደግሞ የኔን ስራ ያለምንም ለውጥ እደግማለሁ ብለህ መነሳትህ፣ ከምንም ነገር በላይ አሳሰበኝ።
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ የተጠናወተኝን አገር የመከፋፈልና ኤርትራን የማስገንጠል አባዜ ሳነበንብ በወንጀል ላይ ወንጀል ስሰራ ወደዚህ መጣሁ። ኢትዮጵያን ነፃ ለማወጣት ሳይሆን ትግራይን ለመገንጠል፣ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር
(ህወሃት) ብለን ተነስተን በብዙ ሺወች የሚቆጠሩ የትግራይን ወጣቶች በከንቱ አስጨረስን። ያአገር ድንበር ለማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንን በግፍ ጨፈጨፍን። በመሰሪና መርዝ በሆነ ቅስቀሳችን በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረውን ህዝብ አታለልን። ስውር ተልእኳችንን አሳካን።
ብዙ ኢትዮጵያዊያንና በለንደኑ ጉባኤ ያደራደሩን ፈረንጆች ሳይቀሩ የመከሩኝን ባለመስማት፣ ለኢሳያስ የገባሁትን ቃል ለመጠበቅና፣ ለአንድ አገር እድገት የባህር በር አያስፈልግም በማለትና የሃሰት ታሪክ በመፍጠር፣ ኤርትራን ከናት አገሯ
አስገንጥየ፣ ቀሪውን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠመንጃ ሃይል አፍኘ፣ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለት የተለየ ሃሳብ ያቀረቡትንና የተቃወሙትን ሁሉ ተራ በተራ አጠፋሁ። ኢትዮጵያን ያለባህር በር አስቀረሁ። ኤርትራን ከማስገንጠል አልፌ በአለም አቀፍ መድረክ የመጀመሪያውን እውቅና ለኤርትራ ሰጠሁ። በኢትዮጵያ ስም ተበድሬ ከፍተኛ ገንዘብ ለኤርትራ አስተላለፍኩ። ስራየ ሁሉ የኤርትራን ጥቅም ማስጠበቅ ሆነ።
የውጭ ጥቃት ይመጣል ተብሎ ሲሰጋ፣ አገሪቱን ከጥቃት ሊከላከል የሚችለውን የባህርና አየር ሃይል በተን። መውጫና መግቢያችን በትንሿ አገር ጂቡቲ መልካም ፈቃድ የሚወሰን ሆነ። ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላምና በአንድነቱ
እንዳይኖር፣ ጠባብ የዘር ፖለቲካ በመስበክና በህገመንግስቱ ዉስጥ የብሄረሰቦች መብት ያለገደብ እስከመገንጠል የሚለውን በማጽደቅ፣ አገሪቱን ጣሊያኖቹ ባሳዩን መንገድ በዘር ከፋፈልን፣ የአገሪቱን አንድነትና ደህንነት ለአደጋ ተጋልጦ እንዲኖር ህጋዊ መሰረት አስቀመጥን። ኢትዮጵያዊነትና የጋራ እሴት የሆነውን ሁሉ መግደል ዋናው ስራየ ሆነ። በአጭሩ በአዲስ አበባ የሚኖር የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባርን ዓላማ አስፈፃሚና የኢሳያስ አምባሳደር ሆንኩ። በጣም የሚያስገርመው የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የሚለውን ስማችንን እንኳ ሳንቀይር ኢትዮጵያን ይህን ያህል ዘመን መግዛታችን ነው።ይህን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ አለ ብየ ሳይሆን ነገርን ከስሩ በየ ነው። ለነገሩ እኛ መግዛት ከጀመርን የተወለዱትና የኛን ዘረኛ ቅስቀሳ እንደወተት እየጠጡ ላደጉት ወጣቶች ይህን ስራየን ባሳውቃቸው ምን ይከፋል።
የፈለግኩትን ሁሉ አፍርሸ እንደገና እገነባዋለሁ የሚል ከንቱ አመለካከት ነበረኝ። በዚህም መሰረት ያአገሪቱን ምሁራን አባርሬ ሌላ ምሁራንን በራሴ አምሳል እፈጥራለሁ በማለት፣ የተለየ ሃሳብ ያላቸውንና ይተቹኛል ብየ የፈራኋቸውን
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ችሎታ የላቸውም በማለት፣ ለአገር በሚጠቅሙበትና ብዙ ሊያስተምሩ በሚችሉበት እድሚያቸው፣ አባረርኩ። ያገሪቱን ምሁራን በማሳደድ ያለፍላጎታቸው የባዕድ አገር አገልጋይ እንዲሆኑና ብዙወችም
ተበሳጭተውና ተሰቃይተው እንዲሞቱ አደረግኩ። ለዚህ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ትልቅ ሚና ተጫውታልኛለች። በየመስርያ ቤቱ የኛን የዘር ፖለቲካ የማይቀበሉትን ሁሉ አባረርን። ምንም ችሎታው በሌላቸው ታጋዮች ተካን። ታማኞቻችንን በከፍተኛ ቦታ ለመመደብ ብዙው ሰው ድንጋይ መፈልፈያ እያለ በሚጠራው ሲቭል ሰርቪስ ኮሌጅ በማስገባት ዲግሪ አደልን። እንዲሁም ከአውሮጳ የተልዕኮ ዩኒቨርስቲወች “ድፕሎማ ሚልስ” በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ዲግሪ በመግዛት አደልን። ዛሬ እኔ ሳነጥስ አብረው ያነጥሱ የነበሩት በስሬ ያሰማራኋቸው አድርባዮች ሁሉ ባለ ማስተርስ ዲግሪ ተብለዋል። ለምን ያን ያህል የውጭ ምንዛሬ እንደአወጣሁና ትምህርት መርጃውን ራሴ እያተምኩ እንዳልሰጠኋቸው እስካሁን ለራሴም አልገባኝም። ታዲያ ነገሩ ሁሉ የኔን ቃላት እንደ ፀሎት መድገምና ድንቁርናን በአገሪቱ ማባዛት ሆነ።
ፈረንጆቹን ለማታለል፣ ከፍተኛ ብድር ለመበደርና ዕርዳታ ለማግኘት፣ የተጋነነና የውሸት መረጃ በመሰብሰብ፣ ለማስመሰል ያህል ህንጻ በመገተር ትምህርትን አስፋፋሁ አልኩ። ለህሊናቸው የሚገዙትንና የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ምሁራን
በስለላ ድርጅታችን ተብትበን በመያዝ አሽመደመድናቸዉ። ባጭሩ ተቋማቱ የካድሬ መፈልፈያና፣ እንደኮብል ድንጋይ ቀርጸው ካስቀመጡባቸው የማይንቀሳቀሱ፣ ሰምተውና አስበው የማይጠይቁ፣ አምባገነንን የሚያመልኩ በቀቀኖች ማምረቻ ሆኑ። በአገሪቱ እኔው ምሁር፣ እኔው ተመራማሪ፣ እኔው ህግ፣ እኔው ህግ አውጭ፣ እኔው ዳኛ፣ እኔው ፖሊስ፣ እኔው የጦር መሪ ሆኜ ኖርኩ።
በዘረኝነት መርሃችን የትግራይን ህዝብ እንዲጠላ ለማድረግና ምንጊዜም የኛ ደጋፊ ለማድረግ በሸርብነው ሴራ፣ ለሙን የጎንደርና፣ የወሎን መሬት ወደ ትግራይ ከለልን። ብዙ የዋህ ኢትዮጵያዊያን የትም ክልል ይሁን የኢትዮጵያ አካል
እስከሆነ ድረስ ብለው ተቀበሉት። የግል ደጋፊወቻችንን ሰፊና ዘመናዊ እርሻ እንዲኖራቸው በሁመራ ሰሊጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ በማድረግ የዛሬ ሃብታሞች የነገ አገር መሪዎችን ፈጠርንበት። ቀሪው ኢትዮጵያን የመግዛት ዘመናችን ካለቀ ግን፣ በጠባቡ አመለካከታችን ትግራይን ገንጥሎ ወደ ኤርትራ ለመቀላቀል የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጀን። ለዚህም እርዳታ እንድናገኝና ቀደም ብሎ በጫካ እያለን የተደረገልንን ውለታ ለመመለስ የጎንደርን ሰፊ ለም መሬት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያውቅ፣ ለሱዳን አሳልፈን ሰጠን። በተወሰነ የህውሃት መሪወች በተቆጣጠርነውና ከኢትዮጵያ ተዘርፎ፣ ከመንግስት ባንኮች ተውስዶ፣ በተቋቋመው፣ በግልጽ ባለቤትነቱ በማይታወቀው፣ የሂሳብ አያያዙ በማይመረመረው፣ ግብር በማይከፍለው፣ በትግራይ ልማት ድርጅት (ኤፈርት) ስም፣ ሌላ ባለሃብቶችን በማዳከም፣ ያአገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጠርን።
ሌላው ወንጀሌ የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት በማስመልከት የፈፅምኩት ነው። መሬት የመንግስት ነው ብለን ስንነሳ የረቀቀ የረጅም ጊዜ ዓላማ ይዘን የኢትዮጵያን መሬት ለመሽጥ፣ ለፈለግነው ደጋፊወቻችን ለመስጠት መሆኑን የተረዱ ብዙ
አልነበሩም። የኢትዮጵያን ህዝብ ከመመገብ አልፎ ለሌላ አገር ይተርፋል የተባለውን ቆላማ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች ለመሽጥ በነበረን የረጅም ጊዜ ዕቅድ መሰረት፣ መጀመሪያ ያደረግነው ህዝቡን በዘር መከፋፈልና ካአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ እንዳይሰራ ማድረግ ነበር። በዚህም ከበሽታና ከርሃብ ተርፈው የተቋቋሙትን ሰፋሪወች ከጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ባሌና ደቡብ ህዝቦች እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ አደረግኩ። የብዙ ህፃናትና ደካሞች ህይወት ሳይቀር አለፈ። ብዙ የመሃል አገር ሰወች በአርባጉጉ፣ በበደኖ እና ሌሎች ቦታወች ነፍጠኛ እየተባሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ብዙ የመንግስት ሰራተኞች ክልላችሁ አይደለም እየተባለ ተባረሩ። የኢትዮጵያ ባንድራ ተወረወረ። ኢትዮጵያዊነት እዲጠፋ፣ ጎሰኝነት እንድነግስ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘመቻ አደረግን። በዚህ ረገድ እነ ጓድ ታምራት ላይኔና አሰን አሊ በዘረኛ ቅስቀሳቸው ያደረጉት አስተዋጾዖ ከፍተኛ ነበር። ዛሬ ግን ታምራት እኔና ባለቤቴን እግዚአብሄር በተደጋጋሚ በገሃድ መጥቶ አናገረን እያለ ፈረንጆቹን ያታልላል አሉ። ድሮም ብልጣ ብልጥ ነበር። በዕውነት እግዚአብሄር ከቀረበው ቅድሚያ የኢትዮጵያን ህዝብ ነበር ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት። በዚህም መሬት ስሪትና ዘረኛ መርህ በሚስጥር በሚደረግ ስምምነት ሰፋፊ በአገር የሚተካከል መሬት ለነ ካራቱሪ፣ ሸህ አላሙዲንና ሌሎችም ሸጥን። በጋምቤላና ሌሎች ቦታዎች ብዙ ህዝብ ተገደለ፣ ተፈናቀለ፣ ሰፊና ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብቱ ተጨፈጨፈ። መሬቱ ሃላፊነት በጎደለው መንገድ በኬሚካል እንዲበከልና የአካባቢው ህዝብ በበሽታ እንዲለከፍ ተደረገ። እንዲሁም የከተማውን ቦታ ዋጋ ጣራ በማድረስ ከመንግስት የተጠጉና መሬት በተለያየ መንገድ በእጃቸው የገባ ደጋፊወቻችንን ሚሊዮነሮች እንድሆኑ አድርገናል። እኛን ያልደገፉትን ግን ኪራይ ሰብሳቢ በማለት በማሰር አሰቃይተናል።
ጓድ ሃይለማሪያም፣ ካደረግኩት ነገር ሁሉ አንተን ወደ ስልጣን ማስጠጋቴ የተሻለ ስራ የሰራሁ መስሎኝ ነበር። ምክንያቱም ፈርሃ-እግዚአብሄር አለህ ሲባል ሰምቸ ስለነበር ነው። እንዲሁም ደግሞ አንተ እንደ እኔ የሰው ህይወት እያጠፋህ፣ በሰው አካል ላይ እየተረማመድክ የመጣህ ጨካኝ ስላልሆንክ ነው። በተጨማሪም የተማርክ በመሆንህ የምታገናዝብና በራስህ የምትተማመን ትሆናለህ በየ ስለገመትኩ ነው። ምንም እንኳ ከስሬ ያላችሁትን ሁሉ ረግጬ በመያዝ፣ በኔ አዕምሮ እንድታስቡ ባደርጋችሁና የህወሃት ሰወች አላሰራም ቢሉህም፣ በምድር ሳልኖር ግን ይህን ያክል እኔን የምትፈራበትና፣ እኔን ለመሆን የምትጥርበት ጉዳይ አልገባኝም። ይህን ስራህን ያዩ ኢትዮጵያዊያን “the cloned” መለስ
እያሉ እንደሚጠሩህ ሰማሁ። “ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ” ማለትህንም ሰማሁ። እንዴት ብትፈራኝ ነው? በዕውነት ይህ ለኔ ይገባልን? ደግሞ መለስ “የሚማሩበት፣ የሚመራመሩበትና በርካታ ለመጪው ትውልድ አመራር አባላት በቂ የመነሻ ሃሳብ የሚያገኙበት በጥቅሉ ለጥልቅ ጥናትና ምርምር አንጡራ ሀብት ነው” ብለህ ማለትህ አሽሙር መናገርህ ነው። ጥሩ ብልሃል። የሰራሁት ወንጀል በዕውነትና በአግባቡ ተጠንቶና በመረጃ ተደግፎ ተጠናቅሮ ይቀመጥ ማለትህ ከሆነ ጥሩ ብለሃል። በትክክል እውነቱ ከወጣና ከተጠና የኔን ወንጀል ባለመድገም ከኔ የምትማሩት ብዙ ነገር አለ። አንተ ባትነግራቸውም ግን ብዙ ኢትዮጵያዊያን መረጃቸውን ሰብስበው ቀን እየጠበቁ መሆኑን አውቃለሁ። የትም ማምለጥ
አይቻልም፤ ወዮላችሁ።
ሰው እድሜው ሲጨምር ይበልጥ ራሱን ይሆናል ይባላል። አንተ ግን በየዕለቱ እኔን ለመሆን እየጣርክ ነው። ምነው አዕምሮህን ለኔ ባሪያ የምታደርገው? አንተ እኔ በየድንጋዩ ስር ስደበቅ፣ ስትማር፣ ስትመራመርና ስታስተምር ነበር።
እኔ በኮሚንስት አመለካከቴ እግዚአብሄርን ሳልፈራ እንዴት የሰውን ህይወት እደማጠፋ ሴራ ሳውጠነጥን ብዙውችን ስረሽን ሳስረሽን፣ አንተ የእግዚአብሄርን ቃል ስታነብ ነበር። ራስህን ሁን እንጂ ጓድ ጠቅላይ ሚንስተር። እኔን ሁነህ በጠባብ ህወሃቶች ከምትወደድ፣ ራስህን ሆነህ፣ ለህሊናህ ተገዝተህ ብትጠላ አይሻልምን?
ሌጋሲ ሌጋሲ የምትሉትና ባስለመድኳችሁ ጥራዝነጠቅ ቃላት የምታደናግሩት፣ ህዝቡ አይገባውም ብላችሁ ይሆን? እኔ ከዚህም ከዛም የባዕዳን ቃላትና ቁንጽል ሃሳብ በመቦጨቅ አንድ ጊዜ ትራንስፎርሜሽን፣ ሌላ ጊዜ ኪራይ ሰብሳቢ
ልማታዊ ባለሃብት እያልኩ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳደናግርና ሳሳስት ኖሪያለሁ። አሁንማ ሰዉ ሲሰክር ሁሉ የሚሰዳደበው ኪራይ ሰብሳቢ እያለ ነው አሉ። እኔ ኪራይ ሰብሳቢ (ሬንት ሲከር) የሚለውን ሃረግ ስዋስ ያደረግኩት መርሁን ላጥላላ በተቃራኒው ግን ከህወሃት የተጠጉትን የስልጣን ባለቤት ብቻ ሳይሆን፣ በኪራይ ሰብሳቢነት መርህ፣ ማለትም መንግስት የሚያደርገውን ቁጥጥር፣ እገዳና አዋጅ በመጠቀምና፣ አዲስ ምርት ወይም አዲስ ሃብት በመፍጠር ሳይሆን፣ የነበረውን በመሰብሰብ፣የመንግስት የሆነውን መሬትና ንብረት በመሸጥ፣መንግስት የሚያወጣውን ጨረታ በአቋራጭ በመውሰድ፣ እንዲበለጽጉ በማድረግ፣ ሚሊዮነሮች እንድሆኑ ነው። በዚህም፣ በቅርቡ አቦይ ስብሃት እንደገለጠላችሁ፣ የኔ ዋናው ዓላማ የአሁኑን ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሃብታቸው ተጽኖ ኢትዮጵያን ሲገዙ የሚኖሩ የአገሪቱን ሃብት የሚቆጣጠሩ፣ የህወሃት የገዢ መደብ መፍጠር ነው። ብዙ ሰው ሊረዳ ያልቻለውና የኔ ውስብስቡ አላማ ከጊዚያዊ ስልጣን መያዝ አልፎ ለመጭወቹ ምእተ ዓመታት የሚቆይ ገዥን መፍጠር ነው። ለዛም ነው የኔን ልጅ እንግሊዝ አገር ሳስተምር፣ አቦይ እንደነገራችሁ የሱን ልጆች ጣሊያንና ቻይና በመላክ፣ እንዲሁም የሌሎች ጓዶቻችንን ልጆች አሜሪካ አውሮፓ ልከን በማስተማርና ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተሻለ አዋቂ በማስመሰል ለቀጣይ ገዥነት እያዘጋጀን ያለነው። በአገር ውስጥ ግን ከመቀሌ በስተቀር ህንጻ ገተርን እንጅ ሌላውን ኢትዮጵያው ማደንቆር፣ ማዳከምና የትምህርት ጥራት እንዲወድቅ ነው ያደረግነው። በተጫማሪም ወጣቱን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለን፣ የጋራ መግባቢያ እንዳይኖረው፣ ካንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ፣ ከጎሳው ውጭ ለአገር እንዳያስብ አድርገነዋል።
በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ማለትህን ሰማሁ። ታዲያ እስር ቤቱን ሁሉ ያጣበቡት የኦሮሞ ወጣቶች፣ ነፃ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪወችና የሙያ ማህበር መሪወች ከኔ ጋር በምን ተጣልተው መሰለህ። እኛ ያገባናል ብለን
በጠመንጃ ሃይል፣ የሺዎችን ህይዎት አጥፍተን፣ ስልጣን ስንይዝ፣የፈለግነውን ሁሉ ያለገደብ ስናደርግ፣ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ግን ሰው የዘር ሃረጉ እየተቆጠረ አይገደል፣ አይፈናቀል፣ የመናገር መብቱ አይታፈን፣ መሰረታዊ ሰበአዊ መብት ይከበር፣ ስላሉና በሰላም በበዕራቸው ስለታገሉ ስንቶቹን በእስር፣ በድብደባ፣ አሰቃየን። ስንቶቹን ገደልን። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት ስላሉ፣ የሰው ልጅ በቋንቋው ተለይቶ መገደል የለበትም ስላሉ አስቃይተን የገደልናቸውና የብዙ ኢትዮጵያዊን ህይወት ያተርፉ የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ሰምቻቸው ቢሆን ኖሮ፣ የብዙ ኑፁሃንን ህይወት ማዳንና የግፍ ግድያን ማስቆም፣ ብቻ ሳይሆን ወንጀለኞች እንኳ ፍትህ የሚያገኙባት ኢትዮጵያን በፈጠርን ነበር። ስህተታችንን ሊጠቁሙ የሚችሉትንና የህዝብ አይን፣ ጆሮና አንደበት የሆኑትን የግል ጋዜጠኞችን አሰርን፣ ብዙወች አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ አደርግን። ዛሬ የመንግስትን ሃብት የሚዘርፉትን ባለስልጣናት የሚያጋልጥ ነፃ ጋዜጠኛ በመታፈኑ፣ ትንሹን ሌባ የሚያጋልጠው፣ ትልቁ ዘራፊ ሆኗል። ስንንቃቸው፣ ስናዋርዳቸውን ስናሳድዳቸው የነበሩ ጋዜጠኞች ናቸው አሉ፣ በአገር ውስጥ እውነቱን የሚናገር ጋዜጠኛ በጠፋበት ጊዜ፣ በተሰደዱበት አገር ሁነው የኔን ዜና ዕረፍት እንኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያሰሙት። ዛሬ ለህይወታቸው ሳይፈሩ የህዝብ መብት ይከበር ብለው በሰላም ስለጠየቁ፣ የኔና አገዛዝ ብልሹ አሰራር ስለተቹ፣ አስረን የምናሰቃያቸው እነ እስክንድር ነጋ፣ ብርሃኑ አራጌ፣ የኦሮሞና የኦጋዴን ወጣቶች፣ንጹሃን የፖለቲካ እስረኞች ካልሆኑ ምን ሊሆኑ ነው።
በህዝቡ መካክል ልዩነትን መፍጠርን የነበረም ልዩነት ካለ ማባባስ ዋናው የመግዣ ስልቴ ነበር። በዘር መካካል የማይታረቅ ልዩነት እንዲኖር መርዛማ የሃሰት ታሪክ በመፍጠርና የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው ብሎ በመቀስቀስ
ብዙዎችን ማሳሳትና በጠባብ የዘር ፖለቲካ እንዲጠመዱ አድርገናል። በሃይማኖት መካከልና ልዩነት መኖሩ የስልጣን እድሜየን ለማራዘምና የኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊዎችን ያዳክምልኛል ብየ በማሰብ፣ ልዩነቱ እየሰፋ ሲሄድ ዝም ብየ
ከመመልከትም አልፌ ልዩነቱን ለማስፋት የሚረዱኝን ግለሰቦች ስልጣን ላይ እንዲወጡና ነገሩን እንዲያባብሱ አድርጊያለሁ። ይህ ሁኔታ ደግሞ በቅርብ ጊዜ የምዕራባዊያንን ቀልብ ለመሳብ ረድቶኛል። በተጨማሪም የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘትና ተቃዋሚዎችን ለማፈን፣ እንደ ሶማሊያ ያለውንም አለመረጋጋት ተጠቅሜበታለሁ።
አኔና ህወሃት በደርግ ጊዜ የነበረዉን ጊዚያዊ ችግርን በዘላቂ በሽታ ተካን። ለመጭው ትውልድ ያተርፍንለት በቀላሉ የማይነቀል የዘረኝነት በሽታ ነው። የጎሰኝነት መጨረሻው ምን እንደሆነ ከሶማሊያ የበለጠ ሊያስተምረን የሚችል
ምን ነገር ይኖራል? በቅርብ ጊዚያት በግብፅ፣ ሶሪያ፣ቱኒሲያና ሊቢያ የተከሰተው ነገር ባግባቡ ላስተዋለው ትልቅ ትምህርት ነው። ከምንም ነገር በላይ የታፈነ ህዝብ በድንገት ተነስቶ ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ አሳይቶናል። የአምባገነኖች
መጨረሻቸው ምን እደሆነ ታይቷል:: ዛሬ አድናቆታቸው ያልተለየህ ሃያላን ቀን ሲጥልህ ከጎንህ እንደማይቆሙ ከሆስኒ ሙባረክ ሁኔታ የተማርክ ይመስለኛል። ብዙወቻችሁ የኔ እድል ላያጋጥማችሁና ባቋራጭ ወደዚህ አትመጡ ይሆናል። ዘመኑ የመረጃ ጊዜ በመሆኑና ከህዝብ የተደበቀ ነገር ሊኖር ባለመቻሉ ለፍርድ በምትቆሙበት ጊዜ የሚከላከልላችሁ ነገር ካለ የራሳችሁ ስራ ብቻ ነው። አስተውሉ። ጥሩ መሪ ችግር ድንገተኛ አደጋ ሁኖ ከመምጣቱ በፊት ያስተውላል ሲባል
አልሰማህምን?
ጨካኝ መሪን ባያሳድገውም ብዙ ጊዜ የሚወልደው አምባገነን መሪ ነው። የኔ ትልቁ ፍራቻ፣ ከኔ የባሰ ጨካኝ መሪ ኢትዮጵያን እንዳይቆጣጠራት ነው። ደርግ አገሪቱን ለኛ እንዳስረከበው፣ እኔና እኔ የፈጠርኩት አምባገነን ስርዓት ደግሞ አገር ሊመሩና ለኢትዮጵያ ሊያስቡ የሚችሉትን ሁሉ ተራ በተራ በማጥፋት፣ የአገሪቱን አንድነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ለሚችሉና በድንገት ስልጣን ላይ ለሚወጡ ክፉ አምባገነኖች ኢትዮጵያን አመቻቸናት። ላንተ ያወርስኩህ ኢትዮጵያ ይህች ናት። ስለዚህ የኔ ዋናው መለዕክት የመለስ ሌጋሲ፣ የመለስ ሌጋሲ የምትለውን ትተህ ራስህን ሁን። እኔም ልረፍበት። የአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መሪ ሁን። ከኔ መጥፎና ዘረኛ አገዛዝ ተማር። ዛሬ በመካድ የነገን ተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም። እኔ የፈጸምኩትን ስህተታት አትድገም። ይህን መልዕክት ደግሞ በስርህ ለተሰለፉት ባለስጣኖችህና ኢትይጵያዊያን አስተላልፍልኝ። ለኢትዮጵያ መልካም ነገር ታደርግ ዘንድ እግዚአብሄር ብርታቱን፣ ጥበቡንና ድፍረቱን
ይስጥህ።
ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን
መለስ ዜናዊ
ከላይኛው ቤት

የመለስ ነፍስም በቀጥታ ከሲኦል ወደ አዲስ አበባ ገባች::

የመለስ ነፍስም በቀጥታ ከሲኦል ወደ አዲስ አበባ ገባች::

መለስ ከሞተ ዓመት ሊሞላዉ ነው አይደል? ይገርማል እኮ አምና ይህን ጊዜ መለስ ታመመ ፣ መለስ ሞተ ተብሎ ሲወራ አቶ በረከት ብቅ እያሉ ምንም አልሆነም በቅርቡ ይመጣል እያለ ሲያታለለን ፣ በእኛ እና “ባለራዩን መሪያችንም” ሲያላግጥ ነበር … ወይ ግሩም! እስኪ ዛሬ ደግሞ እኛም በተራችን በ “ባለ ራዕዩ መሪያችን” ትንሽ እናላግጥ::
አቶ መለስ ነፍሳቸው ከስጋቸው ብትለይም ወዳጃቸዉም ጠላታቸዉም በሆነ ባልሆነው ስማቸዉን እየጠራ እረፍት ስለነሳቸው ለሁሉም ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ስለፈለጉ ለአንድ አፍታ ነፍሳቸው ምድርን ትጎበኝ ዘንድ እንዲፈቅድላት ፈጣሪን ከሲኦል በደብዳቤ ፈቃድ ጠየቁት ፤መቸም ሰው የገደለ እና ያስገደለ ሰው ገነት እንደማይገባ ሁላችሁም ታዉቃላችሁ ብዬ ነዉ ከሲኦል ያልኩት:: የለመኑትን የማይነሳ ፈጣሪም “ ወደቀደመ ክፉ ስራህ እንዳትመለስ” የምትለዉን አምላካዊ ቃል ነግሮ ለነፍሳቸው ፈቃድ ሰጣት::
የመለስ ነፍስም በቀጥታ ከሲኦል ወደ አዲስ አበባ ገባች:: ነፍሳቸው አዲስ አበባ እንደገባችም በሕይወት ዘመናቸው አይተዉት በማያውቁት መልኩ በየቀበሌው የሃዘን ድንኩአን ተጥሏል፣ ፎቶአቸዉ በየቦታዉ ተሰቅሏል ፤ ከፎቶአቸዉ ስርም “ ባለራዩ መሪያችን” የሚል ፅሁፍ አዩና ድርጅታቸው ኢህአዴግ እሳቸው ቢሞቱም ስም ለማዉጣት እንዳልሰነፈ ስለተረዱ ትንሽ ፈገግ አሉ:: በመቀጠልም ነፍሳቸው ወደ አንዱ የቀበሌ የሃዘን ድንኩአን በመግባት ሰው ምን እንደሚል ለመስማት ወሰነች:: በድንኩአኑ ዉስጥ የተሰበሰቡት ሁሉ የቀበሌዉን ሊቀመንበር “ አይዞህ ባገር የመጣ ነው” እያሉ ሲያፅናኑት ነፍሳቸው አይታ ትንሽ ግራ ተጋባች፤ ከተወሰኑ ደቂቃወች በሁአላ ሊቀመንበሩ ስልክ ስለተደወለለት ከድንኩአኑ ወጥቶ ስለሄደ በድንኩአኑ የተሰበሰቡት ሰወች እርስ በእርስ በነፃነት ማዉራት ጀመሩ:: ምንም እንኩአን በሳቸው ሞት ያዘኑ ሰወች ቢኖሩም በድንኩአኑ ዉስጥ የተሰበሰበዉ አብዛኛዉ ሰው እንዲህ እያለ ሲያማርራቸዉ ነፍሳቸዉ ሰማች “ ይህ የተረገመ ሰዉዬ ቁሞም ሙቶም ያስለቅሰናል አይደል” ፤ ነፍሳቸውም እጅግ ተበሳጨች እና እንደዚህ የሚሉትን ሰወች “እጣት ለመቁረጥ” ፈለገች ግን “ወደቀደመ ኃጢያትህ አትመለስ” የምትለዉ የአምላካቸዉን ትእዛዝ አስታወሰችና ዝም አለች::
ከዚህ ቀጥሎ ነፍሳቸው በቴሌቪዥን ምን እንደሚባል ለማወቅ ስለፈለገች ሰተት ብላ ኢቲቪ የተከፈተበት አንድ መዝናኛ ቦታ ገባች:: እጣታቸዉን ቀስረው መቼ እንደተነሱት ትዝ ያላላት ፎቶ ከጋዜጠኛዉ ጀርባ ተሰቅሏል:: የሃዘን ጥቁር ልብስ የለበሱ የተለያዩ ሰወች በሳቸው ሞት የተሰማቸዉን ሃዘን ይገልፃሉ፣ ሁሉንም በጥሞና ስትከታተል የነበረችዉ ነፍሳቸው የጎዳና ተዳዳሪወች “እኛ እሳቸዉን አምነነ ነው ጎዳና የወጣነው ከእንግዲህ ማን ይጠብቀናል” ሲሉ ስለሰማች በጣም ተከዘች:: ቀጥሎ በሠራዊት ፍቅሬ የሚመራዉ የአርቲስቶች ቡድን የሃዘን መግለጫ ሲያስተላልፍ ነፍሳቸው ሰራዊትን አየችና ተበሳጨች ፣ “አይ አጅሬ በኔ ሞትም ቢዝነስ ይሰራል አይደል” ይገርማል እኮ ብላ ተናዳ ሳትጨርስ ትግስት ወይሶ እንባዋን ሞከ ሞክ እያደረገች “እሳቸው እኮ ምን ልበልህ አንዳንዴ ቀበቶአቸው ተፈትቶ ታየዋለህ ፣ ሌላ ጊዜ ፀጉራቸው ተንጨብሮ ሳያበጥሩት ታያቸውለህ … እሕ ሕ ሕ ሕ” ስትል ነፍሳቸዉ ስለሰማች በጣም ተገርማ “ መለስ የሚንጨባረር ፀጉር ለመሆኑ ነበራቸው እንዴ? ቀበቶየንስ መቼ ነው ያየችዉ ?” ብላ እራሷን ጠየቀች፣ በኢቲቪም በጣም ተናደደች:: በተለይ በማስታወቂያ ሚንስተሩ በበረከት ስምዖን ላይ እንዲህ ተናገረች “ ይሄ የማይረባ ቢያንስ ስለፀጉሬና ቀበቶዬ የተባለዉን እንኩአን ምናለ ቆርጠዉ እንዲያወጡት ቢያስደርግ” ፤ ገና ሙቷል ተብሎ እንዲህ በለመደ ዉሸታም ቴሌቪዥን ጣቢያዉ የሀገር መሳቂያ ያድርገኝ! ብላ “ድሮስ ከ ኢቲቪ ምን ይጠበቃል” ልትል ስትል ኢቲቪን እራሳቸው መለስ ዉሸት እንዳስተማሩት ስላወቀች ተፀፀተች ::
በመቀጠልም ነፍሳቸው ስለሳቸው በጋዜጣ ምን እንደሚባል ለማወቅ ስለፈለገች ጋዜጣ ገዝታ ማንበብ ቀጠለች:: ገቢያ ላይ ያገኘችዉ በመንግስት የሚታተሙትን ጋዜጦች ብቻ ነበር ፤ ሌላዉ ቀርቶ እሳቸው በሕይወት እያሉ እንድምትታተም ያውቁአት የነበሩት “ፍትህ” ጋዜጣ መዘጋቷን ሰወች ሲያወሩ ሰማች:: የመንግስት ጋዜጦች ላይ ከኢቲቪ የተለየ ነገር ማግኘት ስላልቻለች በጣም ተናደደች ፤ መለስ የግል ጋዜጦችን በጅምላ የዘጉበትንም ቀን እረገመች ::
በጋዜጣዉ ብዙም ያልረካችዉ ነፍስ ከመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) የተሻለ ነገር አይጠፋም ብላ አንድ ኮምፒተር ላይ ተጣደች:: በሕይወት እያሉ አዘዉትረው የሚጎበኙትን “አይጋ ፎረም” እና “ትግራይ ኦን ላይን” ላይ ሰላሳቸው ሞት የፃፉትን ስታነብ ከቆየች በሁአላ ከስር ስለአባይ ግድብ የተፃፈ ነገር አየች:: “ትግራይ ኦን ላይን” ላይ የሳቸው ደጋፊወች ግድቡ ሲጠናቀቅ “ መለስ ግድብ” መባል አለበት ብለዉ የፃፉትን አይታ ትንሽ ደስ አላት:: ነገር ግን ከስር ለግድቡ ማሰሪያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በአዉሮፓ እና በአሜሪካ የተጠሩ ስብሰባወች “በአሸባርወችና ፀረ ልማቶች ” ሴራ ተበተኑ የሚል ዜና ስላየች እንደገና ተበሳጨች:: ቀጥሎም የተቃዋሚወችን ድህረ ገፅ ማየት ስትጀምር “ አቶ መለስ ባለማችን ሁለተኛዉ ሃብታም ጠቅላይ ሚኒስቴር ነበሩ” የሚል ዜና አየች በዝርዝሩም ይህ ገንዘብ ለአባይ ግድብ ከሚያስፈልገው ጠቅላላ መጠን ሶስት አራተኛዉን መሸፈን ይችላል ማለት ነው ይላል፤ ነፍሳቸው በጣም ስለተበሳጨች ለእናንተ እልክስ ይህን ገንዘብ ለግድቡ አዋጥቸው በሞትኩ ኑሮና ግድቡም አልቆ በስሜ በተሰየመ ብላ ጮኽች ::
ነፍሳቸው ከኢንተርኔት ላይ ከመነሳቷ በፊት ሚስጥራዊ የፌስ ቡክ አካዉንታቸዉን ከፈተች:: ፌስ ቡክ ላይ ቀደም ሲል በየመንገዱ ተሰቅለዉ ያየቻቸዉን ፎቶወች ደጋፊወቻችዉ ግድግዳቸው ላይ ለጥፈው “ባለራዕዩ መሪያችን” እያሉ ስያሞካሹአቸው አይታ ፈገግ ከማለቷ አንዱ የማይወዳቸው ልክ ሲኦል ዉስጥ ባየቻቸው እና ጧት ማታ በሚገርፏት ሰይጣናት አምሳያ የሳቸዉን ፎቶ “ቫምፓየር” አስመስሎ የፌስ ቡክ ግድግዳዉ ላይ ለጥፎ ስላየች እጅግ በጣም ተበሳጨች ፤ ከሁሉም ያበሳጫት ደግሞ ያ ምስል ብዙ “ላይክ” ማግኘቱ ነበር፤ “ይህንስ እንኩአን ጣቱን አንገቱንም ብቆርጠው አልረካ” አለችና ለራሷ ተናገረች::
ነፍሳቸው ምድርን ተሰናብታ ወደሲኦል ከመመለሷ በፊት እጅግ ይወዱት የነበረዉን የደህንነት መስሪያ ቤቱን መጎብኘት ፈለገች እና እሳቸዉ እና የቅርብ ሰወች በሚያውቁት ሚስጥራዊ የበር መክፈቻ ቁጥር በሩን ከፍታ ገባች:: እሳቸው ከሞቱ በሁአላ መስሪያ ቤቱ የሰበሰባቸውን መርጃወች ሰታሥስ እሳቸዉ በሌሉበት በቅርቡ ባህርዳር የተካሄደውን የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የሚያሳይ ቪዲዮ አገኘች:: በጉባዔው ላይ የፎቶአቸው ቁጥር ከተሰብሳቢዉ ሳይበልጥ እንደማይቀር ስታስተዉል በኢህአዴግ አፈረች ፤ በዛ ላይ እሳቸዉን የተኩት ሰዉዬ አሁንም አሁንም “ባለራዩ መሪያችን” ሲል ስትሰማ እንደለመደችዉ “ የሞኝ ዘፈን ሁልግዜ አበባዬ” ብላ ተረተችበት:: ማጠቃለያ ላይ ባለቤታቸው አዜብ “ በዚህ ዓለም ላይ በ 4000 ብር ደሞዝ ሀገር የሚመራ መለስ ብቻ ነበር”ስትል ነፍሳቸዉ ሰማችና አይይ ይ “ዉሸት ለኔም አልጠቀመ እንዴት በጋህነም እሳት እንደምቃጠል ብታይ አትዋሽም ነበር” ብላ አዘነች፤ ሀዘኗን ሳትጨርስ ቀጥሎ ባየችዉ ቪዲዮ በጣም ደነገጠች:: ቪድዮዉ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር:: ሕዝብ ተሰብስቦ ተቃዉሞዉን ያሰማል ፣ ሁኔታው ከምንም በላይ አስቆጣት እና እንዲህ አለች “ ገና ከሞትኩ ዓመት እንኩአን ሳይሞላኝ አዳሜ ተሰብስቦ ቀዩን መስመር ተላለፈ?”፤ “እነዚህ ጣቶች የሚቆርጣቸው አጡ ማለት ነው?” “መንጋ አሸባሪ!”:: ይህን ብላ ወደመቃብሯ ስታመራ መንፈሷ በጣም ስለታወከ እንዲህ አለች “ ይህን ሁሉ ጉድ የሚያሳዩኝ ከዚህ ጨርቅ ህዝብ ማህል አዲስ አበባ ስለቀበሩኝ ነው እንጅ ይህን ጊዜ ወርቁ ሕዝቤ በሚኖርበት ቦታ ቢቀብሩኝ ኑሮ በሰላም አንቀላፋ ነበር”::
Mstewal Dessalew
source..freedom4ethiopian

Saturday, August 17, 2013

አጭር ጨዋታ

አጭር ጨዋታ፤ ሆያ ሆዬ እና ኢቲቪ!

ህፃናቶቹ የቡሄን በዓል ለማክበር ተሰባስበዋል። በየ ቤቱ እንደ ሁኔታው የተለያየ ግጥም እያሰናዱ በየደጃፉ ይጨፍሩ ነበር። በዚህ ሁኔታ ሲሄዱ ሲሄዱ አንድ የኢህአዴግ ዋና ካድሬ ቤት ደረሱ። “ይህ ሰው ድርጅቱን ካላቆላመጡለት ጠብ አይለውም፤ ጭራሽ ለፀብ ይጋበዛል እንጂ…” በሚለው ጨፋሪዎቹ ህፃናት ተስማምተዋል። ስለዚህም በራዲዮ እንደሚሰሙት ኢህአዴግን “አውራው ፓርቲ” እያሉ እየጠሩ አሞካሽተው ሳንቲማቸውን ገቢ ለማድረግ ተነጋገሩ… በተኮላተፈ የልጅ አንደበት ጀመሩ…
“መጣና መጣና ደጅ ልንጠና…
እዚህ ቤቶች አንደምን ናችሁ
ባመት አንድ ቀን መጣንላቹ….
“እዛ ማዶ አንድ ፊኛ
እዚህ ማዶ አንድ ፊኛ
አውሪው ፓርቲ አደገኛ”
ብሎ ዘፈን አወጣ  ሌላው ህፃን ቀስ ብሎ ማስተካከያ ተናገረ። “አውራው ፓርቲ ነው የሚባለው!” አለው። ስለዚህ ድጋሚ አስተካክሎ ለመጨፈር ደገመው፤
“እዛ  ማዶ አንድ ፊኛ
እዚህ ማዶ አንድ ፊኛ
አውሬው ፓርቲ አደገኛ”
አሁንም ተሳሳተ። ይሄን ጊዜ ሊሸልሙ የተዘጋጀው አባወራ ካድሬ ከስልክ ከፍ ከራዲዮ ዝቅ ያለ አንዳች መነጋገሪያ አወጣ። ተነጋገረም። ልጆቹ ደነገጡ ዱላቸውን እና ፊታቸውን አዙረው ወደ መጡበት ሮጡ! እግሬ አውጪኝ አሉ። እግራቸው ግን አላወጣቻቸውም አካባቢው ከመቅስፈት በአድማ በታኝ ፖሊሶች ተሞላ። ሁሉም ልጆች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ማታ ላይም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲህ የሚል ዜና ቀረበ።
“ሆያ ሆዬን ሽፋን በማድረግ በማድረግ ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ሲያራምዱ የነበሩ ፈልፈላ ግለሰቦችን የፌደራል ፖሊስ እና የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።
ግለሰቦቹ ከሻቢያ፣ ግንቦት ሰባት እና ኦነግ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንደነበራቸው የተደረሰበት ሲሆን አንዳንዶቹም ኤርትራ ድረስ በመሄድ መንግስትን የሚያጥላላ የቡሄ ግጥም ሲለማመዱ እንደነበር ተደርሶበታል” የሚል ዜና ቀረበ!
abetokichaw...........

Thursday, August 15, 2013

ምስራቅ ሐረርጌ በርካታ ሰዎችን በመንከሱ እንዲገደል የተፈረደበት ዝንጀሮ ተይዞ የፍርድ ውሳኔው ተፈፀመበት

ምስራቅ ሐረርጌ በርካታ ሰዎችን በመንከሱ እንዲገደል የተፈረደበት ዝንጀሮ ተይዞ የፍርድ ውሳኔው ተፈፀመበት Baboon in Ethiopia sentenced to be killed

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ጨለንቆ ከተማ ቀበሌ 01 20 ሠዎችን ነክሶ ጉዳት አድርሷል የተባለው ዝንጀሮ በሞት እንዲቀጣ ፍርድ ቤት እንደወሰነበት ይታወሳል ።
በወቅቱ ዘገባችን ላይ እንደተመለከተውም የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ደቻሳ አብዲ አብራሽ በ19997 ዓ.ም ጀምሮ ዝንጀሮውን አሳድገውታል ።
ዝንጀሮው የ7 ዓመት ከ7 ወር ዕድሜ እስኪደርስ ከቤት እንሰሳም ጋር ሆነ ከሰው ጋር ሰላማዊ ህይወትን ይኖር ነበር።
ከግዜ በኋላ ግን ባህሪው ተለወጧል።
የባህሪው ለውጥ አመላካች የሆነው ሰዎችን መተናኮልና መናከስ መጀመሩ ነው ፤ በመሆኑም ዝንጀሮውን ማሰር በባለቤቶቹ የተወሰደ እርምጃ ነበር።
መታሰሩን ያልፈቀደው ዝንጀሮው የታሰረበትን በመበጠስ ሰተት ብሎ ወደ ጨለንቆ ከተማ ይገባል።
በከተማዋ እየተዘዋወረም 20 ሰዎችን በመንከስ ጉዳት ያደርስባቸዋል።
ከዚህ በኋላ የሜታ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ዝንጀሮውን በጣቢያው ያስረዋል።
ነገር ግን ሐምሌ 21 ቀን 2005 ከፖሊስ ጣቢያው የታሰረበትን ገመድ በጥሶ በመውጣቱ ምክንያት የወረዳው ፖሊስ ዝንገሮውን ለመያዝ የፖሊስ አባላትን ያሰማራል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ባሳለፍነው ሰኞ በፍርድ ቤት በመሰባሰብ አቤት ይላሉ።
ፍርድ ቤቱም የነዋሪውን ስጋት ከግምት በማስገባት ዝንጀሮው በተገኘበት ይገደል ሲል ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ፖሊስም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለመፈፀም ዝንጀሮውን በማደን ላይ የነበረ ሲሆን ፥ የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ስዩም ደገፉ እንደተናገሩት ዝንጀሮው ከትናንት በስቲያ በቁጥጥር ስር ውሎ የፍርድ ውሳኔው ተፈፅሞበታል።

Wednesday, August 7, 2013

እነሱ እና እኛ! (ቴዲ - አትላንታ)

እነሱ እና እኛ!
(ቴዲ - አትላንታ)

መቼም የተሻለ እስክናይ ድረስ ያለንን ማድነቃችን የሚጠበቅ ነው። የተሻለ ስናይ ደግሞ የኛም እንደዚያ እንዲሻል ስለምንፈልግ፣ የተሻለውን ካልተሻለው እያነጻጸርን መፍትሄ መጠቆማችን እንዲሁ የሚጠበቅ ነው። ሁሉ ለበጎ ነውና በዚህ ሂሳብ መሰረት እስቲ ትንሽ እንጨዋወት።

ቢዮንሴ ኖውልስ የታወቀች አርቲስት ነች። በዓለም ላይ በዝናም ይሁን በሃብት፣ በውበትም ቢሆን ከሚጠሩ እንስት አርቲስቶች መካከል ከቁንጮዎቹ ተርታ የማትጠፋ ነች። በፌስ ቡክ ገጿ 48 ሚሊዮን የሚሆኑ ተከታዮች አሏት። ይህች አርቲስት በቅርቡ እዚህ አትላንታ አንድ የሙዚቃ ዝግጅት አቅርባ ነበር።

ዝግጅቱን ካየሁ በኋላ የመንጠራራት መብቴን በመጠቀም፣ የኛን ኮንሰርቶች በጥቂቱ ማነጻጸር ፈለግኩ። ጥሩ ፍርደኛ እንድሆን ያተኮርኩት ማስተካከል በምንችላቸው ነገሮች ላይ ብቻ እንጂ፣ የማንችላቸው ነገሮች ላይ አይደለም። እኛ ኢትዮጵያውያን ጥሩ ነገር አይወድልንም ያለው ማነው?! ከሰአት ማክበር ልጀምር።

ሰአት ማክበር
የቢዮንሴ ዝግጅት ልክ ከምሽቱ 2 ሰአት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ( 8ፒ ኤም ውጭ አገር) ይጀመራል ተባለ። ልክ በሰአቱ የአዳራሹ የመግቢያ ሙዚቃ ጀምሮ ነበር። ከ 15 ሺ የማያንሰው ተመልካች ወደ አዳራሹ ሲገባ ፣ ኮሽታና ግርግር ፣ ሰልፍና ግፊያ አልነበረም። በቂ አስተናጋጆች፣ በቂ የመግቢያ በሮች ነበሩ። ሁሉም እንደደረጃው - እንደከፈለው መጠን - በተለያዩ በሮች ገባ - አለቀ። በተባለው ሰአት የመድረኩ ሙዚቃ ተለቀቀ። የቢዮንሴን የሙዚቃ ትርዒት የሚያሳዩ ፊልሞች በትልቅ እስክሪን በሙዚቃው ታጅበው ቀረቡ። እሷ ሳትታይ ፣ ያለች ያህል ስሜት ፈጠረ። ልክ 8፡ 30 ሲል ቢዮንሴ ወጣች። አወጣጧ ራሱ ትልቅ ዝግጅት የተደረገበትና ልብን ቀጥ እንዲያደርግ የተለፋበት እንደነበር ያስታወቃል። አጨራረሱ ራሱ ታሪክ ስላለው መጨረሻ ላይ አነሳዋለሁ።

የኛ ኮንሰርትና ሰአት
እዚህ አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ኮንሰርት ሲደረግ ከምሽቱ 4 ሰአት (10 ፒ ኤም) ይጀምራል ቢባል፣ ቢያንስ 3 ሰአታት ያህል መጠበቅ ግድ ነው። አንዳንድ ጊዜ ሁለትና ሶስት ዘፋኞች እንኳን እያሉ ከሌሊቱ 7 ሰአት ( 1 ኤ ኤም) ካልሆነ በቀር ወደ መድረክ ብቅ አይሉም። በር ላይ ለመግባት ስልፍ ግዴታ ነው፣ አንዳንዴም አውቀው (ቢዚ ለመምሰል) ያስልፋሉ ይባላል። የገባውም ሰው ቆሞ ቆሞ ከደከመውና ኸረ ጀምሩ ብሎ ከጮኸ በኋላ ነው አርቲስቱ ብቅ የሚለው። በተባለው ሰአት መጀመርን መጠየቅ ቅንጦት አይደለም። አዳራሽ ገብተን ያለ ሥራ ሶስት ሰአት በመቆየት የምናባክነውን ጊዜ ማነው የሚከፍለን? .. .. ልቀጥል .. ከዚያ ዘፋኙ ይወጣል .. ሲወጣ በጣም ከጥቂቶች በቀር ዝም ብሎ መውጣት እንጂ ምንም አወጣጥን ማሳመር የለም። አወጣጤ እንዴት ቢሆን የበለጠ ይስባል? ብሎ የሚጨነቅ አርቲስት እስካሁን አልታየም።

ክፍያ
የቢዮንሴ ኮንስርት ክፍያ ከትንሽ እስከ ትልቅ - እንደደረጃው - የተለያየ ነው፣ ሰዉ በከፈለው ልክ መቀመጫም ሆነ መቆሚያ ያገኛል፣ በቂ የክፈለ አጠገቧ ይሆናል፣ .. በቂ ያልከፈለ ራቅ ብሎም ያያታል። ቁምነገሩ ክፍያው የታወቀና የማይለወጥ ነው - ትኬቱም መሸጥ የሚጀመረው ገና ዝግጅቱ 3 እና 4 ወር ሲቀረው ነው።

የኛ ክፍያ
እኛጋ ክፍያ እንደ አዲስ አበባ አየር በየደቂቃው ይለዋወጣል። ቀድሞ 40 ዶላር ይባልና፣ በሩ ላይ ሰልፍ በዛ ሲል .. 60 ሆኗል ይባላል ..፣ ቀድሞ የሚገዛ 30 ዶላር ነው ይባልና፣ በብዛት ሰው ቀድሞ መግዛት ሲጀምር፣ ትኬት ይነሳና አልቋል ይባላል.. [በር ላይ በበለጠ ዋጋ ለመሸጥ መሆኑ ነው) .. ... አንዱ አዘጋጅ በሩ ላይ 40 ዶላር እየተቀበለ ሲያስገባ፣ በሌላው በር 50 ካልሆነ አትገቡም የሚል አለ ...፣ በር ላይ ያለው ክርክር ሌላ ነው። ዋጋው 30ም ይሁን 100 .. ቀድሞ ማሳወቅ ይገባል። ዘፋኝ በመጣ ቁጥር የሚመጣው ተመሳሳይ ሰው ሆኖ ሳለ፣ ልክ በአንድ ቀን እንጨርሰው አይነት ስሜት ትክክል አይደለም። ካስፈለገ እኮ ሰው ለከፈለው ነገር ደረሰኝ መጠየቅም ይችላል። መስጠት ደግሞ - በህጉ ግዴታ ነው። ያ ማለት የሚታተመው የመግቢያ ትኬት ላይ ዋጋው በትክክል መጻፍ አለበት ማለት ነው። ካስፈለገ ደግሞ የተለያየ አይነት ደረጃ ያለው ዋጋ መተመን ሌላው አማራጭ ነው።

የጊዜ አጠቃቀም
ቢዮንሴ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ( 8ፒ ኤም) ሙዚቃዋን መጀመሯ ዕድሜያቸው ከ 18 በታች ግን ከ 13 በላይ የሆኑ አድናቂዎቿ ወጣቶች እንዲገቡ ከማስቻሉም በላይ በጊዜ መጀመሩ በጊዜ ኮንስርቱ እንዲያልቅ አድርጓል። 8 ጀመረች፣ 11፡45 (ለ እክለ ሌሊት ሩብ ጉዳይ) ጨረሰች። በማግስቱ ሥራ ያለው፣ ከመሸ በኋላም ሌላ ቦታ መሄድ ያለበት፣ ሌላው ቀርቶ የሌሊት ሥራ ያለበት እንኳን ቢሄድ ይደርሳል - ምንም የባከነ ጊዜ የለም።

የኛ ጊዜ አጠቃቀም
በኛ ኮንስርት ከ እኩለ ሌሊት በኋላ ይጀመራል። መጀመሪያ ነገር የኛ ኮንሰርት ያው "አዳር" እንደሆነ ስለሚታወቅ፣ ሰዉ ቀን ይተኛል ...፣ ከዚያ ሌሊቱን ሙሉ እዚያው አድሮ ሊነጋ ሲል ቤቱ ይሄዳል፣ ከዚያ እንደገና ቀኑን ይተኛል - ስለዚህ ለአንድ ኮንሰርት ሁለት ቀንና አንድ ሌሊት ባከነ ማለት ነው። አሁንም .. በጊዜ ጀምሮ ፣ በጊዜ መጨረስን መጠየቅ የቅንጦት ጥያቄ አይደለም - ማድረግ የሚቻል እንጂ። ቀን ብናደርገው ማን ይመጣል? የሚሉ አሉ .. መች ተሞክረ? ነው መልሱ።

እረፍት የለም
ቢዮንሴ መድረክ ላይ ለ 3 ሰአት ተኩል ያህል ስትጫወት እረፍት የሚባል ነገር አልወሰደችም። ገንዘቡን ለከፈለው ሰው ክብርና ዋጋ ስለሰጠች ያለማቋረጥ ነበር የተጫወተችው .. መድረክ ላይ ለጥቂት ደቂቃዎች የማትታየው ልብሷን ለመቀየር ስትገባ ብቻ ነው .. እሱም ከ 3 ደቂቃ አይበልጥም - እሱም ቢሆን ዳንሰኞቿ ዳንሳቸውን፣ ሙዚቀኞቹም ሙዚቃቸውን ሳያቆሙ ነው። በየት ገብታ በየት እንደወጣች ሳይታወቅ ልብሷን ቀይራ መድረክ ላይ ነች። "የዲጄ እረፍት" የሚባል ነገር የለም። የከፈልነው እሷን ለማየት ነው - ለገንዘባችን ዋጋ ሰጥታለች - እሷንም ያለረፍት አይተናታል።

የኛ እረፍት
አንድ ዘፋኝን ተዉትና ሁለትና ሶስት ዘፋኝ እንኳን ኖሮ፣ ለዚያውም ከ እኩለ ሌሊት በኋላ ዘፈኑ ተጀምሮ ፣ በየ 4 ዘፈኑ "ትንሽ ልረፍ" የሚለን አርቲስት ብዙ ነው። እንዲያውም ዘፋኙ ከሚጫወተው በላይ የዲጄው ሙዚቃ ቢቆጠር ይበልጣል። የከፈልነው ለዘፋኙ ነው ለዲጄው? የሚያሰኝ ነው። ሰዉ የከፈለው እኔን ለማየት ነው፣ ስለዚህ ላስደስተው ብሎ የሚያስብ አርቲስት እንፈልጋለን። እንዲያውም [ዲጄዎች ቅር እንዳይላችሁ እንጂ] ዲጄ መኖርም የለበትም። አንዳንዱ ኮንስርት የአርቲስቱ ነው ወይስ የዲጄ ኮንስርት? ያሰኛል እኮ! ረጅም ሰአት በመዝፈን ቢያንስ መሃሙድ አህመድን አደንቃለሁ - ሌሎቹማ በየ 20 ደቂቃው የ 20 ደቂቃ እረፍት ሲወስዱ ምንም ቅር አይላቸውም። በሰአት 7 ዶላር የሚከፈለው ሰው የሙሉ ቀን ክፍያውን ከፍሎ እንደገባ የሚያውቁ አይመስለኝም። ቢዮንሴ ሶስት ሰአት ያለማቋረጥ ከዘፈነች የኛ አርቲስቶች ምን ያቅታቸዋል? እንደሷ ስፖርት መስራት፣ ራስን መጠበቅ .. "ምናምኑን" መቀነስ ነው ... ለታዳሚው ክብር ሊሰጡ ግድ ነው። ይህም ጥያቄ ሊሆን የሚችል እንጂ የቅንጦት ጥያቄ አይደለም።

ማይክራፎንና ሳውንድ
ቢዮንሴ መድረኩ ተከፍቶ ብቅ ብላ "ሃሎ አትላንታ" ካለችበት ሰአት አንስቶ ፣ "ቀስ እያላችሁ ንዱ፣ መልካም መንገድ እወዳችኋለሁ" ብላ እስከተሰናበትችበት ደቂቃ ድረስ ጥርት ያለ ሙዚቃ፣ ቅልብጭ ያለ ድምጽ ነበር። ሁሉ ነገር ቀድሞ ሰው ሳይመጣ በፊት ምናልባትም ከአንድ ቀን በፊት ተስተካከሎና ተመጥኖ የተዘጋጀ ነበር። መጋረጃው ተከፈተ፣ ቀጥታ እሷና ባንዷ ሙዚቃ ጀመሩ .. ጨረሱ - በቃ!

የኛ ማይክራፎንና ሳውንድ
እኛ ጋ ስንመጣ ገና ሲጀመር "ሙከራ አንድ ሁለት ሶስት" የማይቀር ነው። አንዳንዴማ በሚያሳፍር መልክ እዚያው መድረክ ላይ ዘፋኙና ሳውንድ ማኑ ይከራከራሉ፣ ጊታሪስቱ ጊታሩን የሚሞክረው እዚያው ነው፣ ሰው 40 እና 50 ዶላር ከፍሎ ፣ ሁለትና ሶስት ሰአት ቆሞ ጠብቆ ገና ማይክራፎን ላዩ ላይ ነው የሚሞከረው። ይህ በቀላል ቋንቋ ንቀት ነው። አንድ አርቲስት እንዴት በራሱ ዝግጅት ላይ ቀድሞ መጥቶ ሁሉ ነገር መስተካከሉን አያረጋግጥም? አንዳንዶቹ ለስሙ ሳውንድ ለመሞከር ብለው ከዝግጅቱ በፊት ይመጣሉ፣ ምኑን እንደሚሞክሩት ግን አይታወቅም በኋላ ላይ ሰው ፊት በመብራቱና በድምጹ "ሲበሳጩና ችግርም ሲኖር በሳውንድ ማኑ" ሲያላክኩ ይታያሉ። የሚገርመው አንዳንዶቹ አርቲስቶች ሳውንድ ለመሞከር ሌላ ሁለተኛ ዘፋኝ ወይም ከባንዱ ተጫዋቾች እንዱን ነው የሚልኩት ይባላል። "የኔ ሾው ነው" ብሎ መጨነቅ አይታይባቸውም። ታዳሚ ቆሞ እየጠበቀ፣ እንዴት ሰው ላይ ማይክራፎን ይሞከራል? .. ቀድማችሁ በጊዜ ሁሉን ሞክሩ፣ እኛን አክብሩን.. ከመሬት የተገኘ ገንዘብ አይደለም የምንክፈለው ብንል ይህም የቅንጦት ጥያቄ አይደለም - ሊሆን የሚችል እንጂ!

ሙዚቃ ፣ መብራትና አለባበስ
የቢዮንሴ ሾው ራሱ ፊልም ነበር ማለት ይችላል። ለአድናቂዎቿ ክብር ከመስጠቷ የተነሳ ለዚያ የሶስት ሰአት ዝግጅት ራሱን የቻለ ሳውንድ ትራክ - ለዚያውም በፊልም የታጀበ - ቀድሞ ተዘጋጅቶለት ነበር።፡ በያንዳንዱ ዘፈን ላይ በደቂቃ ውስጥ ቀይራ የምትወጣው ልብስ ከያንዳንዱ ዘፈን ጋር አብሮ የሚሄድ ነበር። ምናልባት ለአንድ ኮንሰርት አራት ሻንጣ ልብስ ሳትይዝም አልቀረችም። ስለዚህ ሙዚቃው የተለየ ውበት ነበረው። ያን ያደረገችው ለዝግጅቷ ከመጨነቋ የተነሳ ነው። ይህች በመላው ዓለም የተደነቀች አርቲስት "ታዋቂ ነኝ" ብላ አትኮፈስም፣ እያንዳንዷ ጥቃቅን ነገር ሰዉን ለማስደስት የታለመ ነው። ስትደንስና ስትዘል በፍጹም ጉልበቷን አትቆጥብም። ስለዚህ ሶስት ሰአት ተኩሉ ጊዜ ምንም ሳይታወቅ ሰው በጥፍሩ እንደቆመ አለቀ።

የኛ አለባበስና አቀራረብ
የኛ አርቲስቶች የትም ከተማ፣ የትም መድረክ ላይ ቢሄዱ ያው አንድ ናቸው፣ ለዚያ ሾው፣ ለዚያች ቀን ብለው የሚዘጋጁበት የተለየ ነገር የለም። ከጥቂቶች በቀር ለአለባበሱ የሚጨነቅም የለም። አንድ ስታይል ካለ በቃ በዚያችው ይነጋል። አንዳንዴ በፒጃማ ይሁን በተቀደደ ጂንስ፣ በቲሸርትና በቱታ ... ወጥተው የሚዘፍኑም አሉ - [ስም እንጥራ እንዴ?] .. ይቅር .................. ግን ሰው ሰርግ ቤት እንኳን ሲሄድ ለሙሽሮች ክብር ይዘንጣል - ለቦታው የሚሆን ልብስ ይልብሳል። የኛ አርቲስቶች - ከጥቂቶች በቀር - ግድም የላቸው። ከ 10 እስከ 20ሺ ዶላር ይዘው ለሚሄዱበት ኮንሰርት ፣ ያንንም ለሚከፍላቸው ታዳሚ ቢጨንቁ ምን አለበት? በሙዚቃው ተመስጠው እኛንም ቢመስጡን፣ ለኛ እንደተጨነቁልን እንዲሰማን እንዲያደርጉ መጠየቅ .. ይህም የቅንጦት ጥያቄ አይደለም- ሊሆን የሚችል እንጂ።

ቅደም ተከትልና አጨራረስ
ቢዮንሴ ኖውልስ የሙዚቃዎቿ ቅደም ተከተል ቀድሞ በጥናት የተዘጋጀና የታወቀ ነው። እነዚያን ሰአታት እንደ እምቦሳ እየዘለለች ስትደንስና ስትዘፍን . አንዴም ወደ ሙዚቀኞቿ ዞር ብላ እንኳን አላየችም። እነሱም ሥራቸውን ያውቃሉ፣ እሷም ታውቃለች - ተግባብተዋል። ትኩረቷ ታዳሚው ላይ ስለሆነ ሰዉም ትኩረቱ እሷና ሙዚቃው ላይ ነው። ስሜት የሚሰርቅ ባዕድ ነገር የለም። አጨራረሷም ለየት ያለ በልዩ የሙዚቃ ቅንብርና መብራት የታጀበ፣ ምስጋናና ሙገሳ ያለበት፣ ልብ የሚያንጠለጥል አጨራረስ ነበር። ሁሉን አመስግና ፣ ሰዉ ቀስ ብሎ እንዲነዳ ነገራ፣ በሰላም እንድንገባ ምኞቷን ገልጻ (ንግግሯ ሁሉ በልዩ ሙዚቃ የታጀበ ነበር) ተሰናበተች።

የኛስ ሙዚቃ አካሄድ?
እኛ ጋ ስንመጣ፣ አርቲስቱ አንድ ዘፈን ዘፍኖ ፣ ሁለተኛው ገና ዞሮ ከባንዱ ጋር አውርቶ ነው የሚወስነው፣ እንዲያውም ጀምሩ ሁሉ ብሎ አስጀምሮ ነው ወደ ሰዉ የሚዞረው፣ ይህ በጣም አሳፋሪ ነው፣ ለሰው ጀርባ አይሰጥም። ሙዚቃ የሚመረጠውም መድረክ ላይ አይደለም። ይህ ቀድሞ አለመዘጋጀትን ነው የሚያሳየው። አንዳንዶቹማ (ታዋቂ የሚባሉት ጭምር) ሙዚቃው ተጀምሮ ሁሉ ያስቆማሉ. . እና "ልክ አይደለም - እንደገና" ሲሉ እዚያው ለባንዱ ትዛዝ ይሰጣሉ። አሳፋሪ ነው። እንኳን የተከፈለበት፣ የነጻ ዝግጅት እንኳን "ዝግጅት" ያስፈልገዋል። በአንድ ኮንሰርት ላይ ስንት ዘፈን፣ የትኛው ዘፈን እንደሚዘፈን ቀድሞ መዘጋጀት ምን ያቅታል? ለታዳሚው ክብር ከተሰጠ ይህ ቀላል ነው። .. እንደዚያም ሆኖ ዝግጅቱ የሆነ ሰአት ላይ አለቀ ይባላል ..፣ አንዳንዱ አርቲስት ደህና እደሩ ይላል .. አንዳንዱ ደግሞ እየዘፈነ በዚያው ወደውስጥ ይገባል እዚያው ይቀራል.. ሌላው ደግሞ "ትንሽ እረፍት" ብሎ ሄዶ በዚያው ይቀራል. .. የፈረደበት ዲጄ ይጨርሰዋል። ቀድማችሁ የምትዘፍኑትን አውቃችሁ ፣ ባንዱም አውቆና ተራ አስይዞ እንዲመጣ አድርጉ፣ አስሬ ጀርባችሁ እየሰጣችሁን ፣ ምን እንዝፈን እያላችሁ አትመካከሩብን ብንል ይህም የቅንጦት ጥያቄ አይደለም . በቀላሉ የሚሆን እንጂ።

ተጨማሪና ማጠቃለያ
በቢዮንሴ ኮንስርት አዳራሹ ውስጥ 15ሺ ያህል ሰው ሲኖር መጠጥ የሚሸጠው ከአዳራሹ ውጭ ነበር፣ እናም ሁሉም ያቅሙን (ሳያበዛ) ቀምሶ ይገባል፣ ሺሻ ወይም ሲጋራ የሚባል ጭስ አይፈቀድም። የፈለገ ውጭ ማጨስ ይችላል። ስለዚህ ያለ ጭስ ሽታ የተረጋጋ ግን ደስ የሚል ኮንስርት ነበር። በጊዜ የሚያልቅ መሆኑ በራሱ ሰው ለተጨማሪ መዝናናት (መጠጣትም ቢፈልግ) ስለሚችል ስክሮ የሚጋፋ .. ካልሰከርኩ መደነስ አፍራለሁ የሚል ሰው አልነበረም። እኛ ጋ ስንመጣ መድረኩና የመጠጥ መሸጫው ምንም ያህል አይራራቅም፣ አንዳንዱም (አሁን ወደኛ ስመጣ) ካልሰከረ (ች) መደነስ የሚችሉ የማይመስላቸው ብዙ አሉ። ስለዚህ በሙዚቃ መካከል ስክሮ የሚጋፋ፣ ሴቱን የሚጎትት .. በሞቅታ መድረክ ላይ ካልወጣሁ የምትል ...አሉ። አሁን አሁን ሺሻ የሌለበት ማምሻም ሆነ ኮንስርት እንዳይኖር የተባለ ይመስል፣ የሚያጨስም የማያጨስም በጭስ መታፈኑ ግድ ነው። ለመጨፈር ለኮንስርት የመጣ ሰው ቁጭ ብሎ ሺሻ የሚያጨስበት ምክንያት በግሌ አይገባኝም። አርቲስት ያለበት ኮንስርትና የዲጄ ኮንስርት የተደባለቀብን ይመስለኛል። ስለዚህ ጭስ የማይፈልጉ ሰዎች ከአበሻው ኮንስርት እያዘኑ ተሰናብተዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው አዘጋጆቹ በር ላይ ከሚገኘው በተጨማሪ በሺሻውም በመጠጡም ገንዘብ ማግኘት ስለሚፈልጉ ነው።

አንድ ምክር - ለዚህ ለዚህ እኮ .. የሙዚቃ ዝግጅቱ በጊዜ (እንደ ቢዮንሴ ሾው) ቢጀመር - በነገራችን ላይ አብዛኛው የአሜሪካውያን ትላልቅ ኮንስርት በጊዜ ተጀምሮ እኩለ ሌሊት ላይ የሚያበቃ ነው - ሰዉ በሙዚቃው ተደስቶ እኩለ ሌሊት ላይ ሲያልቅ፣ እዚያው በዲጄ መጠጡንም ጭሱንም ማስኬድ ይቻላል ... ያኔ የማይፈልገው ይሄዳል .. ሌላውም በነጻነት ይቆያል። ሁለት ዓይነት ገቢ ተገኘም ማለት ነው። የሚጨስ ነገር ከሌለና በጊዜ ከተጀመረ ሰው ከነወጣት ልጆቹ ፣ እቤት ያሉ ካገር ቤት የመጡ አባትና እናትን ጭምር ይዞ ሊመጣ ይችላል። ታዳሚው ይበዛል ማለት ነው። በማግስቱ ግዴታ ሥራ መግባት ያለበትም ሰው እንዲሁ በጊዜ ስለሆነ ይመጣል .. ጥቅሙ ብዙ ነውና ይታሰብበት።

ስለዚህ .. የባሰ አታምጣ እያልን ወደታች ሳይሆን የተሻለ አምጣ እያልን ወደላይ ልናይ ያስፈልጋል። ለኛ ኮንስርት የሚከፈለው ለቢዮንሴም ሾው የሚከፈለው ነው። እኛ ክብርና ጥሩ ነገር ፣ ጥራትና ንጹህ የሆነ ነገር፣ የተጠና እና የተቀናጀ ነገር አይወድልንም ያለው ማነው? በርግጥ ይወድልናል - ማግኘትም መብታችን ነው። ሁላችሁም ይህን ነገር ለምታውቋቸው ብታስተላለፉ ጥሩ ነው። የተሻለ ማግኘት እየቻልን በትንሽ ነገር የምንቀረው ስለማንናገር ነው። ቢዮንሴ ኖውልስ ያን ሁሉ አድናቂ ያፈራችው በ ዕድል አይደለም - እንዲህ ተጨንቃ ለፍታና አክብራ ነው።

"Don't settle for less, when you can get more" ይላሉ ፈረንጆች።
source...www.facebook.com/dinqmagazine