Showing posts with label ሙስና. Show all posts
Showing posts with label ሙስና. Show all posts

Tuesday, December 17, 2013

“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ


ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡
aregash adane 2
ከሕወሐት ክፍፍል በኋላ አረና ሲደራጅ፣ ለአገራችን የታገልንለት ዓላማ ሙሉ በሙሉ ስላልተሣካ፣ ያልተሣካው እንዲስተካከል አለያም የተሻለ ለማድረግ የራሣችንን ጫና ማሣደር አለብን ብለን ነው አቋም የያዝነው፡፡ ስንደራጅ ሀገራዊ ፓርቲ የመመስረት ዓላማም ፍላጐትም ነበረን፡፡ ነገር ግን በነበርንበት ሁኔታ አገራዊ ድርጅት መመስረት ቀላል አልነበረም፡፡ ጠንካራ ርዕዮተ ዓለም፣ በጣም ወሣኝ አባላት ያሉት አገራዊ ድርጅት መመስረት አሁንም ቢሆን አስቸጋሪ ነው፡፡ ሀገራዊ ድርጅት የመመስረት ፍላጐት ቢኖረንም የነበርንበት ተጨባጭ ሁኔታ አልፈቀደልንም፡፡ በተግባር ስንመለከተው የብሔረሰቦች መብት ሙሉ ለሙሉ ባይከበሩም፣ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት ሁኔታዎች እስኪፈቅዱልን ድረስ ብለን አረናን መሰረትን፡፡
ይህን ካደረግን በኋላ አረናን ይዘን ቁጭ አላልንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ ካልተመሠረተ የትግራይም ይሁን የሌላው ብሔር ብሔረሰቦች ችግር ይፈታል ብለን አናምንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ የሚመሠረትበትን ሁኔታ መፍጠር አለብን ብለን ከሌሎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ እውቅና ካላቸውና በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር በአጭር ጊዜ ውይይት ጀመርን፡፡ መድረክ በሚባለው ድርጅትም የገባነው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
ሎሚ፡- ከክፍፍሉ በኋላ ተዘጋጅቶ የነበረው “ሕዝባዊ” የተባለ ጋዜጣ በምርጫ 97 በጋዜጣው ርዕሰ አንቀፅ ከገዢው ፓርቲ ይልቅ ቅንጅት ላይ ጠንካራ ትችት ታቀርቡ ነበር ይባላል፤ እንዲያ ተደርጎ ከሆነ ትኩረታችሁን ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ ያነጣጠራችሁበት ምክንያቱ ምንነበር;
አረጋሽ፡- ከኢህአዴግ ይልቅ ወደ ቅንጅት ያተኮረ ነበር የሚለው አስተያየት ለኔ ትክክል አይመስለኝም፡፡ ጋዜጣውን በትክክል አንብቦ ተረድቶ የተሰጠ አስተያየት አይመስለኝም፡፡ ያኔ ኢህአዴግን ነበር የምንታገለው፡፡ ከዴሞክራሲ አንፃር፣ ከህግ ልዕልና አንፃር፣ ከመናገርና መደራጀት አንፃር፣ ከፕሬስ ነፃነት አንፃር… እነዚህን እና ሌሎች ተጨባጭ ሁኔታዎችን መነሻ እያደረግን በጋዜጣችን ጠንከር ጠንከር ያሉ አስተያየቶችን እንሰጥ ነበር፡፡ የ97 እንቅስቃሴ ሲመጣም ኢህአዴግ “ዴሞክራሲያዊ፣ ግልፅ እና ነፃ ምርጫ ይመጣል” ብሎ ከጀመረ በኋላ ኃይሉ ሲዛባበት፣ ስልጣኑ እየተንገዳገደ መሆኑን ሲረዳ ቀድሞ የገባውን ቃል ማጠፍ ጀመረ፡፡ እንዲያውም የመሸነፍ አዝማሚያ ሲያይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን በመቅረብ “ኢህአዴግ አሸንፏል” ነበር ያለው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ፀረ-ዴሞክራሲ የሆኑ አዋጆችን አውጇል፡፡
ከዚህ በመነሣት ተገቢ አለመሆኑን በሚመለከት በርካታ ነገሮች ፅፈናል፡፡ “ይሄ የዴሞክራሲውን አካሄድ ማጥበብ እንደሆነ፣ ገና ቆጠራው ሣይጠናቀቅ እኛ አሸንፈናል ብሎ መናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነናዊነት እንደሆነ፣ ተቃዋሚዎቹም ቢሆኑ በህጉና በአግባቡ መያዝ እንዳለባቸው፣ የሕዝብ ድምፅ በአግባቡ ሊቆጠርና ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባው፣ መሸነፉን አምኖ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መቀበል እንዳለበት በሚመለከት ደጋግመን ፅፈናል፡፡ ከዚህ አንፃር ካየነው ቅንጅትን የሚያጠቃ አቋም ነበራችሁ የሚለው አስተያየት አሳማኝ አይደለም፡፡ ቅንጅት ላይ ጫና ወይም ትኩረት ማድረግ ሳይሆን፣ ቅንጅቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የጠቆምንበት ሁኔታ ነበር፡፡
ሎሚ፡- ፓርቲያችሁ አረና በ2006 ዓ.ም. ምን ዓይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው;
aregash adane 1አረጋሽ፡- አረና ጳጉሜ ውስጥ ሦስተኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ አንዳንድ ሕገ ደንቦቹን አስተካክሏል፤ የሚሻሻሉ ነገሮችን አሻሽሏል፡፡ አዳዲስ አመራሮችን መርጧል፤ ለምሣሌ የቀድሞው የፓርቲው ሊቀ-መንበር በአዲስ እንዲተኩ አድርገናል፡፡ ወጣቶችን ወደ አመራር አምጥተናል፡፡ ለውጥና የማሸጋሸግ ስራ ተሰርቷል፡፡ ወጣቱ ወደ ፖለቲካው መድረክ ቢመጣ የትግል ሂደቱን እየተላመደና እየተማረበት ይሔዳል በሚል ነው፡፡ እኛ የወደፊት መሪዎች አይደለንም፤ የወደፊት መሪዎቹ ወጣቶቹ ናቸው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ የዕቅድ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፡፡ በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረግንም ነው፡፡ በእውነቱ ይህ በእኛ ፍላጐት ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ የሌሎቹም ፍላጐት ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁም ሀገሪቱ የወጣት ምሁራን የተሻለ አመራር እንድታገኝ የማድረግ ኃላፊነት አለብን የሚሉ ግለሰቦችን የማሰባሰብ አቅም ያስፈልጋል፡፡ እኛ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠርና እንዲመቻች ካሉት ፓርቲዎች ጋር በፕሮግራሞቻችን ተስማምተን ሀገራዊ ፓርቲ እንዲመሠረት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ንዑስ ኮሚቴ ከኛም ከሌሎችም ድርጅቶች ተውጣጥቶ እየተንቀሣቀሰ ነው፡፡ የአረና ጉባኤ አንደኛው ማጠንጠኛም ይሔ ነው፡፡ ሌላው የጉባኤው አጀንዳ ፓርቲው በተጠናከረ መልኩ ከሕዝቡ ጋር መገናኘት፣ እስከ ገጠር የዘለቀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለብን የሚያሳስብ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህን ነገሮች እንዳናደርግ የሚያግዱን ችግሮች አሉ፡፡ አንዱ የገንዘብ አቅም ነው፡፡ ህዝቡ ከስጋትና ከፍራቻ አልወጣም፡፡ ቢሆንም ባለን አቅምና ችሎታ በትናንሽ ከተማዎች ስብሰባ በማድረግ እንቅስቃሴያችንን ጀምረናል፡፡ እንዲሁም ከመድረክ ጋር በመሆን በናዝሬት፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡
ሎሚ- ፓርቲያችሁ ባደረገው ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ “ውህድ ፓርቲ” እንደሚያስፈልግ ደጋግሞ ገልጿል፡፡ ወደዚህ አቋም የመጣችሁበትን አቋም ቢያብራሩልን;
አረጋሽ፡- ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ሀገራዊ ድርጅት ቁልፍ ሚና አለው፡፡ በተበታተነ መንገድ በክልሎች ብቻ ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ያሉት ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔ ካልተቀመጠላቸው በስተቀር በክልል ደረጃ ብቻ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የምንፈልገውን ለውጥ አናመጣም፡፡ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል፡፡ ሀገር የሚቀይር ኃይል ያስፈልጋል፡፡ ሀገር እንዲቀየር ከተፈለገ ሀገራዊ ፓርቲ መኖር አለበት፡፡ ይሕም ማለት ውህደት መፍጠር ማለቴ ነው፡፡ ውህደት ሲኖር ነው በሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ ያለውን ችግር አብሮ መፍታት የሚቻለው፡፡ በግንባር ደረጃ ብቻ አብሮ መታገል መንግስትን ላይፈትነው ይችላል፡፡ ተገቢውን ጫና አሳድሮ መንግስት ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ እንዲያደርግ ሊያስገድደው አይችልም፡፡ ስለዚህ ሀገራዊ ፓርቲ ተፈጥሮ፣ ሀገራዊ አመራር ካልተመሠረተ ለየብቻ በሚደረግ ትግል የሚመጣ ለውጥ የትም አያደርስም በሚል ነው ለውህደት የተነሳነው፡፡
ሎሚ፡- የህወሓት መመስረቻና መቀመጫ በሆነው ትግራይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ወጣቶች በማህበራዊ ድረ ገፆችና በሌሎች ሚዲያዎችም በገዢው ፓርቲ ላይ ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው፡፡ ይሔ ምንን ተከትሎ የመጣ ይመስልዎታል;… በአንፃሩ የሴቶች እንቅስቃሴ የማይንፀባረቀውስ ለምንድን ነው;
አረጋሽ፡- የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ እየሄደ ነው፡፡ መሠረታዊ መነሻውም ትግራይ ውስጥ ያለው ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት አካሄድ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቱ ላይ ተንፀባርቋል፡፡ ሕዝቡ ደጋግሞ የታገለ ሕዝብ ነው፡፡ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ነው፡፡ መስዋዕትነት የከፈለው ደግሞ የዲሞክራሲ፣ የኑሮ፣ የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ነው፡፡ ሕዝቡ ከዚህ በኋላ የምንበደልበት ስርዓት አይኖርም ብሎ ነው ሦስትና አራት ልጆቹን ከአንድ ቤት ልኮ ያታገለው፡፡ ያንን እምነት ይዞ የታገለ ሕዝብ፣ መልሶ ለዚህ ዓላማ ነው የታገልኩት የሚለው ድርጅት (ህወሓት) ሲጨቁነው ምሬት ሊሰማው የማይችልበት ምክንያት የለም፡፡
አስተዳደሩ ሕዝቡን ከሌሎች ክልሎች በበለጠ ተቆጣጥሮና ወጥሮ ይዞታል፡፡ በትግራይ ውስጥ ሁሉንም ሕዝብ በወጣት፣ በሴቶች፣ በተለያዩ ማህበሮች አደራጅቶ ከህወሓት ትዕዛዝ ውጭ እንዳይመራ እየተደረገ ነው፡፡ የወገንተኝነት፣ የዝምድና ሥራ፣ የሙስናም ጉዳይ አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ችግሬ እየተሰማ አይደለም የሚል ስሜትም አለ፡፡ ይህንን መሠል እሮሮዎች እየወጡ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የተማረው ክፍል በተወሰነ መልኩም ቢሆን የነፃነት ስሜት ስላለው ያንን ማስተጋባት ጀምሯል፡፡ ተቃውሞው ከዚህ የመነጨ ይመስለኛል፡፡ ሌላኛው የሕወሓት ሥጋት ተጨማሪ ኃይል እየፈጠረ ያለው የአረና እንቅስቃሴ ነው፡፡ የአረና እንቅስቃሴ ወጣቶችን እያደራጀ ነው፤ ወጣቶችን ወደ አመራርነት እያመጣ ነው፡፡ ዓላማውን እየገለፁ ነው፤ ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር አብሮ እየተወያየበትና እየመከረበት ነው፡፡ ይሔ ደግሞ የበለጠ እንዲነቃቃ አድርጐታል፡፡ በተለይ እኛ የቀድሞ የህወሓት አባላት ለሕዝብ ችግር መታገል አለብን ብለን መንቀሳቀሳችን ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር፣ የሕዝቡ ምሬት፣ የእኛ እንቅስቃሴ ተዳምሮ ወጣቱን እንዲነሳሳ እያደረገው ነው፡፡
የሴቶች ተሳትፎን በሚመለከት… አረና ከተመሰረተ ገና አምስት ዓመቱ ነው፡፡ እንቅስቃሴያችን ደግሞ ውሱን ነበር፡፡ ሴቶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በማህበር ተደራጅተዋል፤ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሳይቀር በሊግ (በአንድ ለአምስት) ተጠርንፈዋል፡፡ ይሕም ሆኖ የአረና አባላት የሆኑ ሴቶች አሉ፡፡ በአመራር ደረጃም የተወሰኑ አሉ፡፡ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴያችን እየጠነከረ ሲሄድ ሴቶቹ የመምጣታቸው ነገር ይጨምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢህአዴግ ዋነኛ ኃይሎቹ ሴቶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በልማት፣ በማህበር አደራጅቶ እንዲንቀሣቀሱ ያደረገው ሴቶችን ነው፡፡ ይህም ጥቅም ፈጥሮለታል፡፡ እኛ ይህን አዝማሚያ መስበር አለብን፡፡ ግን በሂደት ለውጦች ተፈጥረው የሴቶች እንቅስቃሴም እየጐላ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች እንቅስቃሴ በማይታይበት ሁኔታ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳና፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ያሉ ሴቶች እስከ መታሰር የሚከፍሉትን መስዕዋትነት እንዴት ይመለከቱታል;
አረጋሽ፡- የእነሱ ወደ እስር ቤት መሄድ በተናጠል የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስልጣኑን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መልቀቅ የማይፈልግ ድርጅት ስለሆነ፣ ለይስሙላ ዴሞክራሲ አለ፣ ነጻ ምርጫ እናደርጋለን እያለ በሚዲያ ቢያስተጋባም በተግባር ግን ዜሮ ነው፡፡ በሕዝብ ድምፅ ተሸንፎ ሥልጣኑን ለማስረከብ የተዘጋጀ ድርጅት አይደለም፡፡ ከስልጣን የመውረድ ስጋትና ፍራቻ ስላለው፣ ዴሞክራቲክ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን አይፈልግም፡፡ ኃይል ያለው ሀሳብን፣ ኃይል ያለው ፅሁፍን ይፈራል፡፡
የሕዝብ ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶች… እንዲጠናከሩ፣ እንዲያብቡ ወደ መድረክ እንዲመጡ አይፈልግም፡፡ ብዙኃኑን ሕዝብ ያንቀሳቅሳሉ ያላቸውን ሰዎች በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ ለይቶ ያዳክማቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሀሣባቸው ወይም የሚያነሱት ጥያቄ የራሣቸው “የግል” አይደለም ብሎ ስለሚያስብና ሕዝብ ጋ ከደረሰ ችግር ይፈጥራል ብሎ ስለሚሰጋ በአጭሩ የመቅጨት ስራ ይሰራል፡፡
የብርቱካንም ይሁን የርዕዮት እንዲሁም የሌሎች የፖለቲካ ታሳሪዎች ሁኔታ ከኢህአዴግ ስጋት የመነጨ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ሀሣብ እንዲስተጋባና እንዲሰማ አይፈልግም፡፡ አዲስ ሀሣብ ሕዝቡ ጋር ደርሶ ኃይል እንዲፈጥር አይፈልግም፡፡ በሽብር እና በሌሎች ምክንያቶች በማሳበብ ሊወጡበት የማይችሉበት ቦታ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ከማሰር ጐን ለጐን የማሳቀቅና ከመንገዳቸው የማስወጣት ሥራዎችም ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ በብዙ መንገድ ይኮረኩማል፡፡ ኢህአዴግ ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ አካሂዶ ሲሸነፍ ሊወርድ፣ ካልተሸነፈ ሊቆይ የተዘጋጀ ፓርቲ አይደለም፡፡ ለዘላለም እኔ ነኝ መግዛት ያለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ ይሔንን አስተሳሰቡን የሚፃረረውን ድርጅትም ይሁን ግለሰብ ማጥፋት የለመደ ፓርቲ ስለሆነ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ከዚህ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
ሎሚ፡- ህወሓት “የአዲስ አበባ እና የመቀሌ” በሚል ቡድን ለሁለት መከፈሉ ይነገራል፤ የኢህአዴግ “አስኳል” ነው የሚባለው ህወሓት ውስጥ መከፋፈል መከሰቱ የሚፈጥረው አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት ይኖራል;
አረጋሽ፡- በህወሓት ውስጥ ክፍፍል አለ፤ ለሁለት ተከፍሏል የሚባለውን ነገር ላውቀው አልቻልኩም፡፡ ክፍፍል አለ ብዬ ለመውሰድ ትክክለኛ መረጃ የለኝም፡፡ “ተከፋፍለዋል” የሚል እምነት የለኝም፤ አንድ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳን ተከፋፍለው አንድ ሆነውም ለመዝለቅ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው የሚለው ጥያቄ ቢነሣ ነው የሚሻለው፡፡
aregash adane 3በአጠቃላይ ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ሁልጊዜም ደጋግመው “የጠ/ሚ መለስን ራዕይ እናስተገብራለን” ነው የሚሉት፡፡ ራዕይ ለተወሰነ ጊዜ ትቶላቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁኔታዎች ግን በየጊዜው ነው የሚቀያየሩት፡፡ ከሁኔታውና ከጊዜው ጋር የሚሄድ “ራዕይ” ካልያዙ የያዙት እምነት የሚገድላቸው ይመስለኛል፡፡ አዳዲስ ሀሣቦችን፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር እያስተሳሰሩ መሔድ ካልቻሉ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ሕዝብ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ የሚያስገባ ራዕይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሕዝቡ ተበደልን ሲል፣ ዴሞክራሲ የለም ሲል የህግ ልዕልና የለም ሲል፣ ፍትህ የለም ሲል፣ ጉቦና ወገንተኝነት እየተስፋፋ ነው ሲል፣ መፍትሄ አምጡልን ሲል፣ “ሀገሪቱ በእድገት ላይ ነች፤ አንዳንድ ችግሮች ብቻ ነው፤ እነሱንም በሂደት እንፈታቸዋለን” የሚል ምላሽ እየሰጡ መዝለቅ አይችሉም፡፡ ተከፋፍለዋል የሚለው ግን እኔ የተከፋፈሉበትን ሁኔታ ስላላየሁ ስለሱ አስተያየት ለመስጠት ይከብደኛል፡፡
ሎሚ፡- የትግራይ ሕዝብና የህወሓት ግንኙነትስ ምን ይመስላል;
አረጋሽ፡- ህወሓት ከትግራይ ሕዝብ ጋር የተሳሰረ ታሪክ አለው፡፡ 17 ዓመት ሙሉ ሕዝቡ ታግሏል፡፡ አመራሩ ተለወጠ እንጂ አሁንም ሕዝቡ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡ ያንን ሁሉ ትግል ያደረገው ደግሞ ደህና ስርዓት ይመጣል ብሎ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ በመኖር ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ስርአት ይመጣል ብሎ ነው መስዕዋትነት የከፈለው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደግሞ ህወሓት ይሔንን እንዳይቀጥል እያጠፋ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሃዊ እየሆነ፣ አፋኝ እየሆነ ነው ያለው፡፡ ከዚህ አንፃር የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ እየተማረረ ነው፡፡ መፍትሄ ስጡን እያለ ነው፡፡ ስብሰባ በተደረገ ቁጥር ችግሩን በስፋት ይገልፃል፡፡ እንዲሰሙትም እየጠየቀ ነው፡፡ ይሁንና ተደጋግሞ ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሄ ግን አላገኘም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅሬታ እየተፈጠረ ነው፡፡ ጠንካራ የሆነ ድርጅት ከተፈጠረ የትግራይ ሕዝብ አብሮ ከመታገል ወደኋላ አይልም፡፡ አሁን ግን የእኛ አቅም ነው የሚወስነው፡፡ ሀገራዊ በምንለውና ይፈጠራል በምንለው ፓርቲ ዙሪያ የሚወሰን ነው፡፡ ለትግልም ሆነ ለመብቱ በሰላማዊ መንገድ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመታገል የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ ነው፡፡ እኛ ጋ ድረሱ፤ ከተማ ብቻ ቁጭ አትበሉ እያለ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አለን ትላላችሁ፤ ሌላ ጊዜ ትጠፋላችሁ የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው፡፡ የህወሓትና የትግራይ ሕዝብ ሁኔታም እየሻከረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ ነው፡፡
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

Tuesday, October 29, 2013

የጤና ጥበቃን ሙስና ማን አቤት ይበለው?


Demesew Desta E-mail address dtydmx@gmail.com

Demesew Desta

Demesew Desta
የፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ የተካሄደን የሙስና ምዝበራ በሪፖርቱ መጠቀስ ያለበትን ሳይጠቀስ ማለፉ አግራሞትን አጭሮብኛል። ነገሩ እንዲህ ነው ለረጅም አመት በመድሀኒት ዘርፍ የኢትዮጵያ መድሀኒትና የህክምና መገልገያ እቃዎች በማስመጣት ለመላው ሀገሪቱ በማከፋፈል (ፋ.ር.ሚ.ድ) በመባል የሚታወቀው ድርጅት ጉለሌ ጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት የሚገኝ መስሪያ ቤት ሲሆን በሀገሪቱ በሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ቅርንጫፎች ያሉትና በጣም ጥሩ አገልግሎት ለህብረተሰቡ የሚሰጥ ተወዳዳሪ የሌለው መስሪያ ቤት ነበር።
ሆኖም ህወሀት መራሹ መንግስት ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ጥሩ በሚባል መልኩ ስራውን ሲሰራ የቆየ ቢሆንም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ2001 የመስሪያ ቤቱ ስም እንዲቀየርና ተጠሪነቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስር ሆኖ የሀገሪቱ የእርዳታም ሆነ በግዢ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለተለያዪ ለጤና ተቋማት መድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በማቅረብ ስሙም የመድሀኒት አቅርቦትና ፈንድ ኤጀንሲ (መ.አ.ፈ.ኤ) ሆኖ ከዚህ ቀደመም የመንግስት የልማት ድርጅት ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ሙሉ በሙሉ ወደ መንግስት ድርጅት እንዲቀየር ተደርጓል።

የዚህ ጽሁፍ አላማ የመስሪያ ቤቱ አወቃቀርና ስለሚሰጠው አገልግሎት ለማስቃኘት ሳይሆን በመድሀኒት አቅርቦትና ፈንድ ኤጀንሲ ተቋም ውስጥ የተፈጸመን የሙስና ተግባር የጸረ ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት መንግስታዊ የሆኑ ድርጅቶች በተለያየ ምክንያት መመዝበራቸውን ሪፖርቱ አንድን ብቻ የሀዋሳ ቅርንጫፍ የመ.አ.ፈ.ኤ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊየን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሀኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ በሪፖርቱ ገልጿል።
ሆኖም ይህ የጸረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ የሀዋሳን ቅርንጫፍ ነጥሎ ቢጠቅስም ነገር ግን በሀላፊነት የተጠየቀ አለመኖሩ እራሱ አነጋጋሪ ነው። የሚገርመው ደግሞ የአዲስ አበባው ዋናው መስሪያ ቤት እና የጅማው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት በባሰ ሁናቴ መመዝበሩ የተለያዩ መረጃዎች ስላሉኝ ቀጥሎ በዝርዝር እሄድበታለው።
የዚህ የሙስና ተግባር ባለቤቶች በመጀመሪያ ፋ.ር.ሚ.ድን ወደ መ.አ..ፈ.ኤ ለመቀየር ከመብቃቱ በፊት በሁሉም ክልል ያሉት የመድሀኒት ማስቀመጫ መጋዘኖች በጣም በጥሩ ሁናቴ የተያዙ እንዲሁም በሚገባ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው እኔው እራሴ ምስክር ነኝ ምክንያቱም በአንድ ወቅት እዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ እሰራ ነበር።
ሆኖም ይህ ዘረፋ በሶስቱም መስሪያ ቤት የተካሄደ ቢሆንም  የሀዋሳውን ብቻ ጸረ ሙስና ኮሚሽን በሪፖርቱ መጥቀሱ የሚገርም ነው። ምክንያቱም አንድ አይነት በሚመስል ሁኔታና በተቀነባበረ መልኩ በዋናው መስሪያ ቤት አዲስ አበባ በሚገኘው እና በቅርንጫፍ ጅማና ሀዋሳ ዘረፋ ተካሂዶባቸዋል።

ነገሩ እንዲህ ነው በወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የነበሩት ዶክተር ቴውድሮስ አድሀኖም ጨምሮ በተለያዪ የጤና ዘርፍ ላይ ያሉ ሀላፊዎች ፊርማቸውን ያኖሩበት ደብዳቤ ለዘረፋው የመንግስት ተገን ያላቸው ግለሰቦች ይህንን ደብዳቤ በመያዝ ወደ መ.አ.ፈ.ኤ ድርጅት ለዘረፋው የሚተባበሯቸው የስራ ሀላፊዎች እነሱም፤

1, አቶ ሀይለስላሴ ቢሆን (የመ.አ.ፈ.ኤ ዋና ዳይሬክተር)
2, አቶ የማነ ብርሀን ታደሰ (የመ.አ.ፈ.ኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር)
3, ወ/ሮ ዝናብ ተክሊት (የጉለሌ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ)
4, ወ/ሮ ሶፋኒት (የምግብና የመድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ሀላፊ)
ጋር በመሆን በብዙ ሚሊየን ብር የሚገመት የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች መዝብረዋል።
እነኚ ዘራፊዎች ፊርማቸውን ያኖሩበት ደብዳቤና የመድሀኒቱ ይዘትና መጠን የሰፈረበት ሰነድ በእጄ ላይ ይገኛል ሆኖም ይህንን መረጃ ላቀበሉኝ ሰዎች ደህንነት ስል ላልተወሰነ ጊዜ ከማውጣት ተቆጥቤአለው።

እስቲ ስለ ዶክተር ቴውድሮስ አድሀኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስተር በነበረበት ወቅት ያሳይ የነበረው ታይታ (showing) ጥቂት ነገር ልበላቹ። ወቅቱ ገና ተሹሞ እንደመጣ በሀገራችን ላይም የሞባይል ስልክ አገልግሎት ጥቅም ላይ ውሎ ነበር እናም ይህ ሚኒስቴር ያንን ወቅት በመጠቀም ማንኛውም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የጤና ሰራተኛ ቅሬታ ወይም ችግር ካለ በሞባይል ስልኩ ደውሎ ቅሬታውን እንዲያቀርብ ፍቃድ ቢሰጥም ስልኩ ግን ለታይታ እንጂ የእውነት አገልግሎት ለመስጠት የቀረበ አልነበረም።
ለምሳሌ በዛህ ወቅት የጳውሎስ ሆስፒታል ዶክተሮች አንድ የወያኔ ካድሬ ተነስቶ የሰአት ፊርማ ካልፈረማቹ በሚል አስገዳጅ ሁኔታ አስቀምጦባቸው ዶክተሮቹም ቅድሚያ ህሙማንን መጐብኘት ይቀድማል ወይስ ፊርማ ጋር መሰለፍ በሚል ትልቅ አለመግባባት ተከስቶ ነበር። ይህን ጉዳይ ወደ ሚኒስቴሩ ጋር ቅሬታቸውን ለማሰማት በተቀመጠላቸው ስልክ ቢደውሉ እንዲሁም በአካል ቢሄድም መልስ ሳያገኙ ቀርተዋል።

ሌላው ደግሞ ሚኒስቴሩ የዳቦ ስሞች በማውጣት ለምሳሌ ከዚህ ቀደም ጤና ጥበቃ ሲሰራበት የነበሩትን ስሞች ፕራይመሪ ሀልዝ ኬርን ወደ ጤና ኤክስቴንሽን፤ ጤና ረዳትን ወደ ጤና ሰራዊት የመሳሰሉት በማለት ስም ቀያየረ እንጂ በፊትም የነበረ ፕሮግራም ነው። አሁን ደግሞ በቲወተር ተያይዞታል። ይህ ሁሉ የታይታ ምልክት ዶክተሩ የራሱን ስም ከመገንባት ውጪ በጤናው ዘርፍ ላይ ምንም ያመጣው ለውጥ  የለም።

በእርግጥ ለህወሀት ትልቅ ስራ ሰርቶላቸዋል ይህም በጤና ጥበቃ ስም የሚመጣውን ማንኛውም የእርዳታ ገንዘብና መድሀኒቶች ወደ ህወሀት ድርጅቶች ካዝና እንዲገባ አድርጏል፣የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ባለቤት ወ\ሮ አዜብ መስፍን በኤች.አይ.ቪ ዙሪያ ላይ የሚመደበውን ከፍተኛ የውጭ በጀት እንድትመዘብር ሁናቴዎችን አመቻችቶላታል፣ የጤና ጥበቃ ሰራተኞችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በአስገዳጅ ሁናቴ የወያኔ አባል የማድረግ ስራ ሰርቷል እና በዙሪያው ከአንድ ዘር በተውጣጡ ግለሰቦች በጤና ጥበቃ ሀላፊነት ላይ አስቀምጧል።

በመቀጠል በዋናነት ስለተነሳሁበት የሙስና ዋና ተዋናይ ስለሆነው አቶ ሀይለስላሴ ቢሆን ላስቃኛቹ። ለ20 አመታት ያህል ይህ ግለሰብ በመድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት ውስጥ በሀላፊነት የቆየ ሲሆን በተለያየ ጊዜ ከህወሀት ድርጅቶች ጋር መድሀኒትና የህክምና መሳሪያዎች በህገ ወጥ መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ደጎስ ያለ ገንዘብ ሲመዘብር የቆየ ነባር የህወሀት ታጋይ ነው።

ይሁንና የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ በዚህ ይብቃህ ብሎ ሳይከሰው አሁንም በሀላፊነት መ.አ.ፈ.ኤ በዋና ዳይሬክተርነት በመምራት ለህወሀት ድርጅቶች ለሆኑ የመድሀኒት አስመጪዎችና የመድሀኒት ፋብሪካዎች በህገ ወጥ የጨረታ አሰራር መድሀኒቶችን በግዢ መልክ ለ መ.አ.ፈ.ኤ እንዲያቀርብና ያለማንም ከልካይነት የመስሪያ ቤቱን ገንዘብ ያለ አግባብ በመጠቀም ላይ ይገኛል።

ይህ ግለሰብ በአንድ ወቅት እንደሰማነው እራሱ ዶክተር ቴድሮዎስን እንደሚያዝ እና የፓለቲካ ስውር እጅ ያለው በጤናው ዘርፍ ያሉትን ከፍተኛ የሙስና ተግባራት በመሪ ተዋናይነት የሚመራ ነው። ይህንን ትልቅ ዘረፋ የሚፈጽመው ግለሰብ የሚያስቆምም ሆነ ወደ ህግ የሚያቀርበው አለመኖሩ ምን ያህል ሀገራችን ብልሹ አሰራርና የመልካም አስተዳደር እጦት ውስጥ እንዳለች ማሳያ ነው።

ቁም ነገሩ ተጠቃሎ ሲታይ የህዝብና የመንግስት ንብረት ያለ አግባብ ተመዝብሯል ተሰርቋል ስለዚህ ለፓለቲካና ለተለያዪ ማህበራዊ ጉዳዮች በጋራ እንደምንቆመው ሁሉ ያለአግባብ የሚመዘበሩ የሀገሪቱ የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ዘረፋ ትኩረት መሰጠት እንዳለበትና እንዲሁም በያለንበት ሙሰኞችን ማጋለጥ የዜግነት ግዴታ ነው። ቸር እንሰንብት።

zehabesha

“ቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝም ይውደም!!!” የሃገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያሳስበናል::




አገር ትልቅ ለውጥ ላይ ናት፤ ከፍተኛ የትራንስፎርሜሽን ሂደት ላይ ነን እየተባለ፤ በጐን የዝርፊያ የኮንትሮባንድ እና “በአንድ ጀንበር ፎቅ ሠርቼ ልደር” ዓይነት ዘመናዊ ምዝበራ ይታያል፡፡የጥፋት ድርጊት የሚፈጽሙ ወገኖች ለሀገር እንደቆሙ፤ የህዝብ ልጆች እንደሆኑ አድርገው መጮሃቸውና ሀቀኛ መምሰላቸው፤ ሌላው እንዳይናገር በር ይዘጋል፡፡ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንከኖቻችን ጥቅል ውጤት ማስጨነቁና ማሳሰቡ የሀገርና የህዝብ ስሜት ላለው ሁሉ አይቀሬ ነው፡፡ በተለይም ዱሮ የእጅ - እላፊ ይባል የነበረው የምዝበራና አገርን የማራቆት ተግባር፣ (ዛሬ ሙስና የተባለውን)፤ “ባንዱ ያለማ ባንዱ ያደለማ” ሆኗል፡፡ “በአንዴ ዘጋ/ዘጋች” ዛሬ የተለመደ ቋንቋ ነው፡፡ እንደነናይጄሪያና እንደነናይሮቢ (“ናይሮበሪ” እንደተባለው) ዐይን - ያወጣ የቀን ተቀን ዘረፋ የሚመጣው ከላይ እስከታች እየተወሳሰበ ያለው ሙስና ፍፁም ወደፈጠጠ ደረጃ ሲደርስ ነው፡፡

አንድም ሙስናው በየአቅጣጫው መሆኑ፤ አንድም ደግሞ ቢሮክራሲያዊ መጠቅለያ መኖሩ እጅግ ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ (ዱሮ “ቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝም ይውደም” የሚል መፈክር ነበር፤ ነብሱን ይማረው!) በዚህ ላይ የግለሰቦች አሻጥር ሲጨመርበት፣ ከቁጥጥር ውጪ ወደሆነ ደረጃ ይሸጋገራል፡፡ የመሬት አሰቃቂ አወሳሰድ፣ ከፍተኛ የኮሚሽንና የድለላ ሥራ፣ አደገኛ ወገናዊ አሠራር…በአስደንጋጭ የድህነት መቀመቅ ውስጥ ለገባች አገር ከምትሸከመው በላይ ትከሻ አጉብጥ ሸክም ይሆንባታል፡፡ የባሰ ዘግናኝ የሚሆነው ደግሞ ከዕለት ወደ ዕለት በምዝበራ ምክንያት መታሰር ራሱ እየተለመደና ቀላል እየመሰለ መምጣቱ ነው፡፡ “እገሌ ታሠረኮ” ሲባል፤ “ተወው በልቷል - የሚበቃውን ቀለብ አከማችቷል” ማለት እንደሰላምታ የሚነገር መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡

ዱሮ “በሥራው አጋጣሚ በእጁ የገባውን የመንግሥት ገንዘብ ለግል ጥቅሙ በማዋሉ” የሚለው ሐረግ ነበር ሬዲዮንና ቴሌቪዥን ያጣበበው፡፡ ዛሬ ዳር እስከዳር በየሰው አፍ የሚወራ ነገር ሆኗል፡፡ ዝርፊያው ዓይነት በዓይነት ሆኗል፡፡ ተወርቶም በቀላሉ ይረሳል፡፡ በተለይ ለህብረተሰብ ቀጥተኛ መጥፊያ የሚሆኑ እንደመድሃኒት ያሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ባመቸው መንገድ ሁሉ ተበርዘው ከተባዙ፣ ምን ያህል አሰቃቂ የሆነ ዕልቂት እንደሚያስከትሉ መገመት አያዳግትም፡፡ የሚያስገኙት ገንዘብ የትየለሌ፣ የሚፈጁት ህዝብ የትየለሌ!!

ማናቸውንም የጥፋት ድርጊት የሚፈጽሙ ወገኖች ለሀገር እንደቆሙ፤ የህዝብ ልጆች እንደሆኑ አድርገው መጮሃቸውና ሀቀኛ መምሰላቸው፤ ሌላው እንዳይናገር በር ይዘጋል፡፡ They shout at most against the vices they themselves are guilty of እንደሚሉት ነው ፈረንጆቹ - ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮህ እንደማለት ነው፡፡ ጩኸቱ በቅጡ ለገባው አገር - ወዳድ ሰው ግን፤ “ቤቱን አቃጥሎ እንዴት ብሩህ ቀን እንደሆነ ተመልከቱ” አለ እንደተባለው ነው፡፡ ልዩነቱ ያኛው ለግሉ እየተጠቀመ፤ ይሄኛው የገዛ ንብረቱን ጭምር እያወደመ የሚጃጃል መሆኑ ነው፡፡ ሁለቱንም መዋጋት ተገቢ ነው!(አዲስ አድማስ)
 

Friday, October 25, 2013

የጌታነህ ትሬዲንግ ባለቤት ራሳቸውን በሽጉጥ ገድለው እንዲሞቱ የተደረገበት ምስጢር ከ4 ዓመት በኋላ ወጣ


(አራጣ አበዳሪው ከተማ ከበደ እኚህ ናቸው)
(አራጣ አበዳሪው ከተማ ከበደ እኚህ ናቸው)
(ዘ-ሐበሻ) አንድ ሰሞን በአዲስ አበባ በዋጋ ቅናሽ የሆኑ ልብሶችን በማስመጣትና ትላልቅ ሱቆችን “ጌታነህ ትሬዲንግ” በሚል ከፍተው እየሰሩ ከፍተኛ ታዋቂነትን እና ተወዳጅነትን ካተረፉ በኋላ ወዲያውኑ ራሳቸውን አጠፉ ተብሎ በ2009 ዓ.ም ተነግሮላቸው የነበሩት የዚህ ትልቅ ድርጅት ባለቤት አቶ ዮሐንስ ጌታነህ ከ4 ዓመት በኋላ የአሟሟታቸው ምክንያት ይፋ ሆነ።
“አቶ ዮሐንስ ጌታነህ የጌታነህ ትሬዲንግ ባለቤት ሲሆኑ፣ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ራሳቸውን በሽጉጥ ገድለው ተገኝተዋል።” በሚል በወቅቱ አሟሟታቸው ተሸንፎ የነበሩት እኚሁ ግለሰብ ለሞት ያበቋቸው አሁን በነ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ በሙስና ተከሰው የሚገኙት 10ኛው ተከሳሽ  አቶ ከተማ ከበደ አስገልጥ መሆናቸውን አቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ላይ መረዳት ተችሏል።
አቶ ዮሐንስ ጌታነህ ኢትዮጵያ ውስጥ በከፈቱት ፋብሪካ የተለያዩ ልብሶችን በአነስተኛ ዋጋ እያመረቱ ለገበያ ያቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ለተለያየ ምርት የሚያገለግሉ ጥሬ ዕቃዎችንም ያቀርቡ ነበር አቶ ዮሐንስ ሕይወታቸውን ካጠፉ 4 ዓመት ያለፋቸው ቢሆንም መንግስት ለሞታቸው የነበረውን ምክንያት እያወቀ በአቶ ከተማ ከበደ ላይ አሁን ክስ መመስረቱን አንዳንድ ሰዎች በፖለቲካ አለመስማማት የተፈጠረ ነው ይሉታል። እነዚህ አስተያየት ሰጪዎች ታዋቂው አራጣ አበዳሪ አቶ ከተማ ከበደ ከመንግስት ጋር ባይጣሉ ኖሮ እንዲህ ያለ የተደበቀ ምስጢር አይወጣም ነበር ይላሉ።
በአቶ ከተማ ከበደ ላይ የተመሰረተው ክስ የሚከተለው ነው፦
23ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የገንዘብና የባንክ አዋጅ ቁጥር 83/1986 አንቀጽ 59(1) (ሸ) ስር የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ አሜሪካ አገር ከምትኖረው ትእግስት ከተማ ከበደ ከተባለች ልጁ ውክልና በመውሰድ ጌታነህ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ዮሐንስ ጌታነህ ካሳ ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ስምምነት ብር 40,000,000 (አርባ ሚሊዮን ብር) ብድር በመስጠት ለባንኮችና መሰል የፋይናንስ ተቋማት ብቻ የተፈቀደውን የባንክ ስራ በህገወጥ መንገድ እንደ ንግድ ስራ ሲሰራ በመገኘቱ በፈፀመው ወንጀል ተከሷል።
24ኛ ክስ
በ10ኛ ተከሳሽ ላይ ብቻ
ወንጀሉ
በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 715(ሀ) እና (ሐ) ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ፣
የወንጀሉ ዝርዝር
ተከሳሹ አቶ ዮሀንስ ጌታነህ ካሳ የተባሉ የግል ተበዳይን የገንዘብ ችግር መሰረት በማድረግ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክስዮን ማህበር ጣና ቅርንጫፍ እና ከአቢሲኒያ ባንክ ነጋድራስ ቅርንጫፍ ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከግል ተበዳይ ድርጅት በተለያዩ ቀናት በተፃፉ የተለያ ቼኮች በልጁ ትእግስት ከተማ ከበደ፣ በእራሱ በተከሳሹ እና ኬኬ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በተባለ በእራሱ ድርጅት በህግ ከተፈቀደው ወለድ በላይ ብር 111,705,397.83 (አንድ መቶ አስራ አንድሚሊዮን ሰባት መቶ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ብር 83/100 ሳንቲም) አራጣ በማስከፈል በግል ተበዳይ ላይ የሀብት መራቆት እንዲደርስበትና እራሱን እንዲያጠፉ በማድረጉ በከባድ ሁኔታ አራጣ ማበደር ወንጀል ተከሷል።

zehabesha

Wednesday, October 16, 2013

የአስተዳደሩ ምርመራና ክስ ኤክስፐርት በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ

-በቦሌ ጉምሩክ ኃላፊና በአንድ ባለሀብት ላይ የተዘጋጀው ክስ ሳይነበብ ቀረ
በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሥልጣን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው፣ በማረሚያ ቤት በሚገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት
አስተዳደርና ግንባታ ፈቃድ ባለሥልጣን በነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ መዝገብ፣ በሌሉበት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት፣ የአስተዳደሩ ፍትሕ ቢሮ የምርመራና ክስ ኤክስፐርት አቶ ተስፋዬ ዘመድኩን በቁጥጥር ሥር ውለው ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ቃሲም ፊጤ፣ አቶ ተስፋዬ ዘመድኩን፣ የሊዝ አሰባሰብ ክትትል ኦፊሰር አቶ ገብረየሱስ ኪዳኔና የመሬት አቅርቦት አፈጻጸም ንዑስ የሥራ ሒደት አቶ በቀለ ገብሬ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ሦስቱ ተከሳሾች ሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. የተጻፈ ክስ ቀርቦባቸውና ተነቦላቸው የዋስትና መብታቸው በመከልከሉ፣ ማረሚያ ቤት ቆይተው ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ 
ከሦስቱ ተከሳሾች በተጨማሪ በሌሉበት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት አቶ ተስፋዬ አብረው በመቅረባቸው ቀደም ብሎ የተመሠረተው ክስ ተነቦላቸዋል፡፡ የዋስትና መብታቸውም ታልፎ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ በጽሕፈት ቤት በኩል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ከአቶ ተስፋዬ በስተቀር ሦስቱ ተከሳሾች ለጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ተቀጥረው የነበሩት የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ የቅድመ ክስ መግለጫ እንዲያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ አቶ ተስፋዬ ተይዘው በመቅረባቸው ክሱ እንደ አዲስ ተነቦላቸው በሁሉም ላይ የቅድመ ክስ መግለጫ ለማቅረብና ተከሳሾች በጠየቁት የዋስትና መብት ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
ሌላው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና ነጋዴዎች ጋር በቁጥጥር ሥር ውለው በነበሩት በባለሥልጣኑ ቀድሞ የቦሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ አዳዩና በተለያዩ ንግድ ሥራዎች ላይ የተሰማሩት አቶ ማሞ ኪሮስ ላይ የኮሚሽኑ ዓቃቤ ሕግ ክስ አዘጋጅቶ የመጣ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በእድሳት ላይ በመሆኑ ዳኞች ቀድሞ ይሠሩበት ከነበረው ችሎት ወደ ሌላ ችሎት በመቀያየራቸውና ሳይሟሉ በመቅረታቸው ሳይነበብ ቀርቷል፡፡ 
አቶ ማሞ ኪሮስ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተሳትፈዋል በሚል መጠርጠራቸውንና አቶ ዮሴፍ አዳዩ በሥልጣን ያላግባብ መገልገል፣ ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘትና በሌሎችም ወንጀሎች መጠርጠራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ 
ethiopian reporter

Tuesday, September 17, 2013

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃላፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ

ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል። 
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ 94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል። 
ከአራዳ ክ/ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ህገወጥ የካሳ ክፍያ በመፈጸሙ ሦስት የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው በ2004 ዓ.ም ክስ ቢመሰረትም የቅጣት ውሳኔ አላገኝም። 
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የ12 ሚሊዮን ብር እና የ34 ሚሊዮን ብር ህገወጥ ብድርን እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት በቂ የሰነድ ማስረጃ እንደተገኘባቸው ቢገለጽም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቱዋል፡፡ 
በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከመመሪያና አሰራር ውጪ ለግለሰቦች የስልክ መስመር እንዲዘረጋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ስልክ በማስደወል በመስሪያ ቤቱ ላይ 14 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱን የተመለከተ ሁለት ምርመራዎች ተጠናቀው በክስ ሂደት ላይ ሲሆኑ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በሚፈጥሩት ጫና ክሱ እየተጓተተ ነው። 
በትግራይ ክልል የሚገኘው በሼባ የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ መብራት ሀይል ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ 65 ሚሊዮን 300 ሺ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጣርቶ ለወሳኝ አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል። 
በተመሳሳይ በኦሮምያ ክልል በደብረዘይት የሚገኝ የግል የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረሱ ምርመራው አጣርቶ የፀረ ሙስና ኮሚሺን ቢልክም የፍትህ መጓተት ታይቶበታል። 
በመብራት ሀይል አላግባብ በ 248 ሚሊዮን 900 ሺ ብር የተፈጸመ የ4 ሺ4 መቶ 70 ትራንስፎርመሮች አለም አቀፍ ግዢ በሁለት የምርመራ መዝገቦች የተጣራ ቢሆንም ውሳኔ አልተሰጠበትም። 
ንብረቱ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኑፋክቸሪንግ ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ የሆነ ግምቱ 4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ የብርና የነሃስ ሜዳልያ ከግምጃ ቤት በመጥፋቱ ተመርምሮ የተረጋገጠ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም። 
በተንዳሆ ፕሮጀክት ከግብር ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጠናቆ ክስ ተመስርቷል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሊዝ እንዲስተናገድ የተወሰነለትን የመኖሪያ ቤት ኅ/ሥ/ማ ያለ ሊዝ በማስተናገድ የተሰጠ 30 ሺ 3 መቶ 32 ካ/ሜ ቦታ ምርመራ ተጠናቆ ክስ የተመሰረተ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም። 
ለብሄራዊ ባንክ በሽያጭ ከሚቀርብ ወርቅ ጋር በተያያዘ የባንኩ ሰራተኞችና ነጋዴዎች በመመሳጠር 63 ሚሊዮን ብር በመመዝበር አስቀድሞ ተከሰው የነበሩ አሁን ጥፋተኛ ተብለው ጉዳዩ ለቅጣት ውሳኔ ተቀጥሯል። 
በቂርቆስ ክ/ከተማ በልማት ተነሺዎች ስም ከመመሪያ ውጪ ግምቱ 13 ሚሊዮን 3 መቶ ሺ የሆነ 2, ሺ 1 መቶ 45 ካ/ሜትር ትርፍ መሬት አላግባብ በተሰጣቸው እና ከካሳ ክፍያም ጋር በተያያዘ 5 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ብር በትርፍ የተከፈላቸው ግለሰቦች ጉዳይ፤ በኢትዮጵያ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሀዋሳ ቅርንጫፍ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሃኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተደረገ የ100 ሚሊዮን የእህል ግዢ ጨረታ ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጨረታውን ያሸነፉ መሆኑ በተደረገው ምርመራ በመረጋገጡ ጨረታው እንዲሰረዝና በግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት የተደረገባቸው በጥቅሉ ከህዝብ በግብር የተሰበሰበ በርካታ ገንዘብ በአንድም በሌላ መልኩ በከፍተኛ አመራሮች ተጽእኖ በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ተጣርቶ ለፍርድ ሰጭው አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ቀርተዋል፡፡ 
ከ 7 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የመዘበሩ የስራ ሃፊዎች አልተቀጡም ሲል ከፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ አሀዙ በ2005 የተፈጸመውን ሙስና አላካተተም። 
ባለፉት 22 የኢህአዴግ የአገዛዝ አመታት የተፈጸሙና በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተጣራ በሙስና የተዘረፈ ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ይገመታል።

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/09/17/632-2/

Thursday, September 12, 2013

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አቃቤ ህግ ጉቦ ሲቀበል ተያዘ::

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አቃቤ ህግ የነበረው ግለሰብ ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን የፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
ግለሰቡ ጳጉሜን 4 ቀን 2005 ዓ.ም 30 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል በኮሚሽኑ የክትትል ሠራተኞች እጅ ከፍንጅ ተይዟል።
ግለሰቡ የወንጀል ድርጊቱን ሊፈጽም የቻለው ከታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምርመራውን አጠናቆ ክስ እንዲመሰረት ለአቃቤ ህጉ ካስተላለፈው የአንዲት ግለሰብ የክስ መዝገብ ጋር ተያይዞ ነው።
ግለሰቡ መሥሪያ ቤቱ ከአቃቤ ህግ እንዲከታተለው የተሰጠውን የክስ መዝገብ ከተቀበለ በኋላ ለግለሰቧ  በመደወል የክስ መዝገቡ እሱ ጋር መሆኑን በመናገር ፤ ጉዳዩን አይልሻለሁ በማለት የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት ገንዘብ እንድትሰጠው መጠየቁን ኮሚሽኑ አመልክቷል።
በዚሁ መሠረት መጀመሪያ 5 ሺህ ብር ጉቦ ከተቀበለ በኋላ ተጨማሪ 30 ሺህ ብር እንዲሰጠው ግለሰቧን ጠይቋታል።
ይህ ጥቆማ የደረሰው ኮሚሽኑ ተገቢውን ክትትል በማድረግ አቃቤ ህጉን በዕለቱ ካዛንቺስ አካባቢ ከግለሰቧ እጅ 30 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ሊይዘው ችሏል።
ኮሚሽኑ በግለሰቡ ላይ ተጨማሪ የምርመራ ማስረጃ አሰባስቦ ፍርድ ቤት ለማቅረብ በሂደት ላይ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/09/11/324-6/

Saturday, August 31, 2013

የሀገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥር ስር ዋሉ።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለ አግባብ መጠቀም ፥ ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል  ተጠርጥረው ነው።
ከፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው  ፥ ተጠርጣሪው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።
ኮሚሽኑ ግለሰቡ ፈጽመውታል ከተባሉ የሙስና ተግባራት ጋር በተያያዘ ሌሎች ተያያዥ ምርመራዎችን እያካሄደ ይገኛል።
የዛሬ አመት ገደማ ኮሚሽኑ በአቶ ወልደስላሴ  ወንበር ላይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ አቶ አይቼው ተፈታን በተመሳሳይ ወንጀል ከሷቸው በአሁን ጊዜ  ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው  ።
አቶ አይቼው ከገቢ በላይ ምንጩ ያልታቀ ሃብት አፍርተዋል የተባሉባቸው ሆቴሎች እና ሌሎች ንብረቶች በአሁን ጊዜ መታገዳቸው ይታወቃል።


ምንጭ ፡-(ኤፍቢሲ)

Sunday, August 4, 2013

ጉቦ እየተቀበለ የፈተና ውጤት የጨመረ መምህር በሙስና ተከሰሰ

ጉቦ እየተቀበለ የፈተና ውጤት የጨመረ መምህር በሙስና ተከሰሰ Teacher sued for accepting bribe and inflating test result

Written by አለማየሁ አንበሴ, AddisAdmassNews.com
ከ10 ዓመት በላይ እስር ሊያስቀጣ ይችላል በአየር ጤና ሁለተኛና መሰናዶ ት/ቤት ለ11 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ጉቦ እየተቀበለ የፈተና ውጤት በመጨመር ከክፍል ወደ ክፍል እንዲዘዋወሩ አድርጓል የተባለው የባዮሎጂ መምህሩ አቶ ፈቃዱ ቢጀጋ በሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተበት፡፡ የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ፣ የክስ ዝርዝር እንደሚያስረዳው፤ በመምህሩ ላይ ሁለት ክሶች የቀረቡበት ሲሆን በአንደኛው ክስ በ2005 የትምህርት አመት የ9ኛC ክፍል የክፍል ሃላፊ ሆኖ የተመደበበትን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም፣ ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ለአስራ አንድ ተማሪዎች ዘጠኝ የሚደርሱ የትምህርት አይነቶች ላይ ለእያንዳንዱ የትምህርት አይነት መምህራን ሳያውቁ እስከ 91 ነጥብ በመጨመር ከክፍል ወደ ክፍል ማለፍ የማይገባቸው ተማሪዎች እንዲያልፉ ለማድረግ በማሰብ፣ ከስልጣኑ በላይ በሆነ አሠራር በመንግስት የትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ፣ በፈፀመው በስልጣን ያለአግባብ መጠቀም የሙስና ወንጀል እንደተከሰሰ ተመልክቷል፡፡ በሁለተኛነት በቀረበው ክስ ላይም ሃላፊነቱን ያለአግባብ በመጠቀም የግል ተበዳይ የሆነ አንድ ተማሪ ካርድ እንዲሰጠው ሲጠይቀው “ውጤትህ የተሟላ አይደለም፤ የተሟላ ውጤትህን የያዘ ካርድህን እንድሰጥህ ከፈለግህ ገንዘብ አምጣ” በማለት ጠይቆ፣ ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰአት ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ አንድ ግሮሰሪ ውስጥ ከግል ተበዳይ 200 ብር ተቀብሎ “ካርድህን እልክልሃለሁ፤ ገንዘብ ግን ስለሚያንስ ትጨምራለህ” በማለት በነጋታው ከምሽቱ 12 ሰዓት ሲሆን ተጨማሪ 150 ብር ከዚሁ ተበዳይ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ በመያዙ በሙስና ጉቦ በመቀበል ወንጀል ተከሷል፡፡ ክሱ እንደደረሰው ለፍ/ቤቱ ያረጋገጠው ተከሳሽም፣ በችሎቱ በተገኙና ሊረዱት በፈለጉ ጠበቆች አማካይነት የተከሰሰበት የህግ አንቀጽ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ፣ “ፍ/ቤቱ ጉዳዬን በዋስ ሆኜ እንድከታተል ይፍቀድልኝ” ሲል የጠየቀ ሲሆን አቃቤ ህግም በዋስትና ጥያቄው ላይ ተቃውሞ እንደሌለው አመልክቷል፡፡ ይሁን እንጂ ተከሳሹ ከ10 አመት በላይ በሚያስቀጣ ወንጀል የተከሰሰ በመሆኑ የዋስትና ጥያቄውን ባለመቀበል፣ መዝገቡን ለነሐሴ 3 ቀን 2005 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡

sodere...........

Saturday, August 3, 2013

ከትራንስፎርመሮች ግዥ ጋር በተያያዘ መንግስትን ከፍተኛ ገንዘብ ያሳጡ 9 የኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች ተከሰሱ

ከትራንስፎርመሮች ግዥ ጋር በተያያዘ መንግስትን ከፍተኛ ገንዘብ ያሳጡ 9 የኮርፖሬሽኑ የስራ ሃላፊዎች ተከሰሱ


አዲስ አበባ ፣ሀምሌ 26 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ)  ከትራንስፎርመሮች ግዥ ጋር  በተያያዘ  መንግስት 25 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንዲያጣ አድርገዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 9 የኢትዮጵያ ኤለሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው።
ሁለት ስራ አስፈጻሚዎች በሚገኙባቸው በእነዚህ መዝቦች ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 2ኛ የወንጅል ችሎት ለሁለተኛ ጊዜ የጊዜ ቀጠሮ ከፈቀደ  በኋላ ነው፤ የፈደራሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን  አቃቤ ህግ ዛሬ የምርመራ ቡድኑ  ስራውን በማጠናቀቁ ክስ ለመመሰረት የበቃው።
አቃቤ ህግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የዲስትሪቢዩሽን ሲስተም ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ብርሃኔ ፣ የሲስተምና የደንበኞች አገልግሎት ድጋፍ ክፍል ሃላፊ አቶ ሞገስ በላቸው ፣ የቴክኒክ ክፍል ቡድን መሪው አቶ መኮንን ብርሃኔ ፣ ሚስተር ጂሰስ ባራሶይን የኮብራ ኢንስታሌሽን ዋይ ሰርቪሽየስ ኢንዲያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዳይሬክተር እና የጉድ ላክ እስቲል ቲዩብስ ሊሚትድ ኩባንያ  ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ናሬሽ ቻንድራን በአንደኛው መዝገብ ሲከሰሱ ፤
በሁለተኛው መዝገብ  ደግሞ በአትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የሃገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም ስራ እሰፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ ፣ የኢንጂነሪንግ ክፍል ሃላፊው  አቶ ሚሊዮን ማቱሳላ ፣ የሰፕላይ ቼን ሃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ዳንኤል ገብረስላሴ ፣ የኢንጂነሪንግ ፕሮሰስ  የስራ ሂደት ተወካዩ አቶ ሰመረ አሳቤ እና  የጨረታ ገምጋሚዎቹ አቶ አሸናፊ ዮሃንስ ፣ አቶ ፋሪስ አደም ፣ ብሩክ ተገኝ ፣ ጌታቸው አዳነ እና ሁለቱ የውጭ ሃገር ኩባንያ ስራ አስኪያጆች ናቸው።
የኮብራና ጉድላክ ኩባንያዎች  ሁለቱንም መዝገቦች የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በሁለት መዝገቦች የተጠቀሱ ተጠርጣሪዎችን በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 1ኛ እና 15ኛ የወንጀል ችሎቶች ነው ክስ የመሰረተባቸው።
እነ አቶ መስፍን  በተጠቀሱበት የክስ መዝገብ  አቶ መስፍንን ጨምሮ  አቶ ሞገስ በላቸው እና አቶ መኮንን ብርሃኔ  ሃላፊነታቸውን ተጠቅመው  ራሳቸውን እንዲሁም በመዝገቡ የተጠቀሱ ሁለቱን የውጭ ሃገር ኩባንያዎችን በመጥቀም መንግስትን ጎድተዋል በሚል ወንጀል ነው የተጠረጠሩት።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችን በሰፕላየርስ ክሬዲት ለመግዛት ከዛሬ አራት አመት በፊት ባወጣው ጨረታ ፥ ጉድላክ ቲዩብስ የተሰኘው የህንድ ኩባንያ ጨረታውን በማሸነፍ 3520 ትራንስፎርመሮችን ከ17 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሆነ ዋጋ ለማቅረብ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ይስማማል።
ኮርፖሬሽኑ ጉድላከ ስቲል ቲዩብስ የትንስፎርመር አቅራቢ ፣ ኮብራ ኢንስታሌሽንስ ግዥውን  በገንዘብ እንዲደግፍ እና ኮርፖሬሽኑ ደግሞ የትራንስፎርመሮቹ ገዥ በመሆን ወደ ስራ ለመግባት የውል ስምምነቱ ተጠናቋል።
ጉድላክ ከወራት በኋላ እኔ አቅሙ ስለሌለኝ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ውለታ የገባው ኮብራ ኩባንያ ደርቦ ሁለቱንም ስራ ያከናውን በማለት ያመለከተ ሲሆን ፥ ኮርፖሬሽኑ በወቅቱ ጉድላክ  ከስምምነቱ እንዳይወጣ በማለት ደብዳቤ መጻፉም በክሰ መዝገቡ ተመልክቷል።
አቶ መስፍን ግን ያለኮርፖሬሽኑ እውቅና የሶስትዮሹን ስምምነት ወደ ሁለትዮሽ ዝቅ በማድረግ ፥ ሁለቱ የውጭ ሃገር ኩባንያዎች ያዘጋጁትን ውል  ያለምንም ማገናዘቢያ  በመቀበል ማጽደቃቸው በክስ መዝገቡ ተመልክቷል።
ከዚያም ተከሳሹ የገንዘብ ምንጭ ለሆነው ለሪዘርቭ ባንክ ኦፍ ኢንዲያ በጻፈው ደብዳቤ ለውሉ ተቀባይነት ማረጋገጫ ሰጥቷል ይላል ክሱ።
ከአቶ መስፍን ጋር በመዝገቡ የተጠቀሱ ሁለቱ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ትብብር በማድረጋቸው ከእነዚህ የውጭ ኩባንያዎች ጋር ህገ ወጥ ስምምነት በመደረጉ መንግስት ከ17 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካን ላር በላይ ማጣቱም በመዝገቡ ተጠቅሷል።
አዳዲስ ትራንስፎርመሮች ወደ ሃገር ቤት መጥተው ከትራንስፎርመር ጋር በተያያዘ የሚፈጠረው የሃይል አቅርቦት ችግር ይፈታል ተብሎ ሲጠበቅ  ያገለገሉ እና የቅርብ ስሪት ሆነው ተገኝተዋል።
በክሱ 4ኛ እና 5ኛ ተራ ቁጥር ላይ የተጠቀሱ የውጭ ሃገር ኩባንያዎች  ከአቶ መስፍን ጋር በመመሳጠር ችግሩ እንዲከሰት ማድረጋቸውንም ክሱ ያስረዳል።
እነ አቶ ሽፈራው ተሊላ የሚገኙበት የክስ መዝገብም በተመሳሳይ መልኩ  ባደረጉት የውል ስምምነት ያገለገሉ 1950 ትራንስፎርመሮች ወደ ሃገር ቤት ገብተዋል።
አስሩም ተከሳሾች ፈፅመውታል በተባለው የሙስና ወንጀል ዛሬ የተከሰሱ ሲሆን ፥ ተከሳሾቹ የፊታችን ሰኞ በሁለቱም ፍርድ ቤቶች የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ትጠበቃል።

በጥላሁን ካሳ





Friday, August 2, 2013

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው አቶ ቃሲም የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል መሠረት በማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ኮሚሽኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ብሎ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ምክር ቤቱም የግለሰቡ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የቀረበለትን የሰነድና የውሳኔ ሐሳብ ከመረመረና የአሠራር ሒደቶችን ግንዛቤ ውስጥ ካስገባ በኃላ ሰኔ 28/2005  ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል፡፡
የተጠርጣሪው ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ምክር ቤቱ የደረሰበትን ውሳኔ ተከትሎ ኮሚሽኑ አቶ ቃሲምን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን ፥ የተጠርጣሪነት ቃላቸውን በመቀበል አስፈላጊው ሕጋዊ ሥራ ማከናወኑንም ነው ያመለከተው ፡፡
ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም ከሀገር ወጥተዋል  በሚል  ሲወራ  እንደነበር የሚታወስ  ቢሆንም ፥ ዛሬ ማምሻውን በቁጥጥር  ስር የዋሉት በቢሯቸው  እንዳሉ  መሆኑን ነው ኮሚሽኑ  ያስታወቀው ።
ግለሰቡ ቀደም ብለው ከሀገር የወጡትም ለስልጠና እንደነበር ነው የተመለከተው ።
ነገ  በፌደራሉ ከፍተኛ  ፍርድ ቤትም ቀርበው  ቀጠሮ ይጠየቅባቸዋል  ተብሎ  ይጠበቃል ።
source....fababc.com 



Tuesday, July 30, 2013

ፍርድ ቤቱ በእነ መላኩ ፈንታና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መዝገቦች በተጠረጠሩ 19 ግለሰቦች ላይ ለ8ኛ ጊዜ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት በእነ መላኩ ፈንታ እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መዝገቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ 19 ግለሰቦች ላይ ለ8ኛ ጊዜ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ።
የፈዴራሉ ስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን የምርመራ ቡድን በመዝገቦቹ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ 19 ግለሰቦች ላይ የካሄደውን የምርመራ ሂደት ለፍርድ ቤቱ ዛሬ አቅርቧል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች የፌደራሉ ስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በየጊዜው የሚያቀርበው የምርመራ ሂደት ተመሳሳይነት ያለው ነው ሲሉ ፥ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ መዝገቡን በመመርመር ሂደቱ በየጊዜው መሻሻል እያሳየ ነው ብሏል።

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች በሁለት መዝገብ የተካተቱ 19 ግለሰቦች ሲሆኑ ፥ የቀድሞው የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ በእርሳቸው በተሰየመው መዝገብ የተጠቀሱት አቶ እሸቱ ወልደሰማያት ፣ አቶ ማርክነህ አለማየሁ ፣ አቶ አስመላሽ ወልደማርያም ፣ አቶ ከተማ ከበደ ፣ አቶ ስማቸው ከበደ ፣ ዶክተር ፍቅሩ መሃሩ እና የአቶ ማርክነህ እህት ወይዘሮ ትእግስት አለማየሁ ናቸው ።

አቶ መላኩ በሚሌ ፍተሻ ጣቢያ ህገ ወጥ በሆነ ትእዛዝ ሳይፈተሹ ያለፉና ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ እቃዎችን አስመልክቶ እጃቸው ነበረበት በሚል በተጠረጠሩበት ወንጀል ፥ እየተካሄደ ባለው ምርመራ ሂደቱ ወደፊት እየተጓዘ መሆኑን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል ።

ቡድኑ ያከናወናቸው ተግባራት

በመዝገቡ ከተካተቱ ስምንት ተጠርጣሪዎች መካከል ከአቶ ከተማ ከበደ ፣ አቶ ስማቸው ከበደ እና ወይዘሮ ትእግስት አለማየሁ ውጪ ፥ የተቀሩት በህገ ወጥ መንገድ በጅምላ የተቋረጡ መዝገቦች እና ያአግባብ የታክስ ኦዲት በመከለስ ተግባር የመንግስት ገቢ ዝቅ እንዲል ማድረግ የሚለው ሌላው የምርመራ ቡደኑ እድገት ያሳየ ምርመራ ካካሄደባቸው ወንጀሎች ተጠቃሽ ነው።

መላኩ ፈንታን ጨምሮ በመዝገቡ ተካተው የነበሩ የመንግስት ሰራተኞች ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አካብተዋል በሚል በየተረጠሩበት ወንጀል ፥ የምርመራ ቡድኑ በተሰጠው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የሃብት ጥናት መረጃ ማሰባሰቡንም አስታውቋል።

ቡድኑ ተያያዥነት ያላቸው የምርመራ ስራዎችን ማከናወኑን እና ለቀሪ ምርመራ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት የጠየቀ ሲሆን ፥ የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላችው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄው በዝቷል፤ ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢለቀቁ የነበራቸው ሃላፊነት አሁን ከእነርሱ ጋር ስለሌለ እንደተባለው ምስክሮችን አያስፈራሩም፣ ማስረጃም አያጠፉም፤ የሚሉና ሌሎችንም አቅርበዋል።

ከተጠርጣሪዎች አቶ ማርክነህ ጠበቃቸው ሳይመጡ በመቅረታቸው በግላቸው በጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ ምንም የማቀርበው የመከራከሪያ ነጥብ የለኝም ፍርድቤቱ ራሱ የመሰለውን ትእዛዝ ይስጥ ፤ ነገር ግን የዋስትና መብቴ ይከበርልኝ ሲሉ አመልከተዋል።

የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን በበኩሉ ከተጠርጣሪዎች እና ከጠበቆቻቸው ዘንድ በዋስትና ጥያቄው ላይና የተነሳው የተቃውሞ ሃሳብ ፥ የወንጀሉ ውስብስብነት እና ከባድነት ካልሆነ በስተቀር፤ ቡድኑ በየጊዜው በልዩ ትኩረት በትጋት እየሰራ መሆኑንና ተጓተተ ለተባለው  የሁለት ኩባንያዎች የኦዲት ስራም እንዲሁም መስክ የሄደው የምርመራ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ የምርመራ ስራ ማካሄዱን በምሳሌነት አንስቷል።

ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ቡድኑ ቀሪ የምርመራ ስራዎች እንዳሉት በመገንዘብ የተጨማሪ 10 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዶ የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቀ ለነሃሴ 2, 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በሌላኛው እና በአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ስም በሚጠራው መዝገብ ደግሞ የምርመራ ቡድኑ በኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በነበሩት አቶ ገብረዋህድ አቶ በላቸው በየነ እና አቶ ጥሩነህ በርታ ፥ በህገ ወጥ መንገድ በጅምላ አቋርጠውታል በሚል በተጠረጠሩበት ወንጀል ላይ በተፈቀደው 10 የምርመራ ቀን ውስጥ የሁለት ምስክሮችን ቃል መቀበል እና የሰነድ ማስረጃ የማሰባሰብ ስራዎችን አከናውኛለሁ ብሏል ።

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በመመሳጠር የመንግስት ቀረጥና ታከስ እንዳይሰበሰብ በማድረግ ያለአግባብ ተጠቅመዋል በተባለው የሙስና ወንጀል ላይ ፥ በተመሳሳይ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰብሰቡን አስረድቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንግስት ሲሚንቶ ያለቀረጥ በአስመጪዎቸ መጥቶ ለታለመለት ስራ እንዲውል ፍቃድ የሚሰጥ ሲሆን ፥ አቶ ነጋ ያለቀረጥ እንዲገባ የተደረገውን ሲሚንቶ ከአስመጪው ኮንትራት በመውሰድ አሁን ኮሚሽኑ እየደረስኩበት ነው ባለው የምርመራ ሂደት አቶ ነጋ ከባለሰልጣኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ሲሚንቶውን እያጓጓዙ በተለያዩ ሱቆች አራግፈዋል ብሏል።

ቡድኑ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ወደ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት በማምራት ስሚንቶው ለታለመለት አላማ መዋል አለመዋሉን የተመለከተ መረጃ ኮፒ አድርጎ መውሰዱን ያመለከተ ሲሆን ፥ ለቤቶች ልማት ይገባል ተብሎ በየሱቆች ለገባው ሲሚንቶ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ ከባለስልጣኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተወልደ ብስራት እና አሞኘ ታገለ ተጠያቂ ተደርገዋል።

ቡድኑ በዚህ መዝገብ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እና አቶ ጥሩነህ በርታ ላይ የመንግስት ግብር የሚሰውሩ ግብር ከፋዮችን ማጋለጥ ይቻል ዘንድ በተዘረጋው ስርአት መሰረት ፥ ለጠቋሚዎች የሚከፈል አበል ጠቋሚ ሳይኖር ጠቋሚ እንዳለ ተደርጎ ለግል ጥቅማቸው አውለውታል በተባለው ከፍተኛ ገንዘብ ምዝበራ ዙሪያ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማሰባሰቡን አስታውቋል።

በአጠቀላይ በዚህ መዝገብ የምርመራ ቡድኑ ከ27 የሚልቁ የምስክሮችን ቃል ሲቀበል ፥ 26 የሚሆኑ ምስክሮች ይቀሩኛል ብሏል።

ቀሪ ተግባራትን ለማከናወንም ቡድኑ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ያስፈልገኛል በማለት ሲጠይቅ ፥ የግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ቀሪ የምርመራ ስራዎች እንዳሉ ተገነዘቢያለው በማለት  የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ ለ8ኛ ግዜ በመፍቀድ ፥ የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 2 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።



በጥላሁን ካሳ



source...http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=4776%3A---------19---8----&catid=102%3Aslide


Monday, July 29, 2013

114 ኪሎ ሜትር የሐዲድ መስመር ለመዘርጋት ለባከነው 60 ሚሊዮን ዩሮ ተጠያቂው ማነው?

በአገራችን ለትራንስፖርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ ሲሰጡ ከነበሩ አንጋፋና ታላላቅ ድርጅቶች መካከል የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት አንዱና በሁለት እህትማማቾች አገሮችና (በኢትዮጵያና በጂቡቲ) ሕዝቦች መካከል ዲፕሎማሲያዊ ትስስሩ የማይበጠስ የጋራ መገናኛ ድርጅት እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡
ድርጅቱ ከዚህም ባሻገር ከአገራችን የሚወጡና ወደ አገራችን የሚገቡ ከፍተኛ ክብደት ያላቸውንና መጠነ ብዙ ለአገር ግንባታ የሚውሉ የፋብሪካ፣ የግብርና ወዘተ. ግባቶችን የሚያመላልስ ጠቃሚ የትራንስፖርት አካል ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የመሀልና የዳር አገር ሕዝቦችም የኢኮኖሚ ጥምረት እንዲኖራቸው ያገዘና በርካታ ቤተሰቦችም እንዲተዳደሩበት ያደረገ እናት ድርጅት ነበር፡፡
ይሁንና ይህ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው ድርጅት በማርጀት፣ በጦርነት፣ በተፈጥሮና በአስተዳደራዊ ችግሮች ወዘተ. እንደቀድሞው ሊቀጥል ባለመቻሉ አንዳንድ ችግሮችን በተለይም በእርጅና የተበላሹ ሐዲዶችን (መስመሮች) መቀየር እንዲችል ከአውሮፓ ሕብረት (EU) የ60 ሚሊዮን ዩሮ ዕርዳታ ተሰጥቶት የ114 ኪሎ ሜትር መንገድ እድሳት እንዲደረግ ኮንስታ ጆይንት ቬንቸር ከተባለ የጣሊያን ድርጅት ጋር ውል ተደርጐ ሥራው ከአምስት ዓመታት በፊት እንዲጀመር መደረጉ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ይህ የተባለው የኢጣሊያ ኩባንያ ከጅምሩ ለሥራው ብቁ እንዳልነበረ እየታወቀና በተለያዩ ጊዜያት ኃላፊነት ያለባቸው የምድር ባቡር የማኔጅመንት አባላት፣ የፋይናንስ ሚኒስቴር ተወካይ፣ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ተወካይ እንደዚሁም ኮንሰልታንት የነበረው ኢኔኮ የተባለው ስፔናዊ ተቆጣጣሪ ድርጅት ጭምር ባልሳሳት በየጊዜው የተሠራውንና የተደረሰበትን ለመገምገም ድሬዳዋ እየተገናኙ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ሆኖም ጠብ ያለ ሥራ ሳይሠራና 30 ኪሎ ሜትር ያህል እንኳን ሐዲድ ሳይዘረጋ ጠያቂም ተጠያቂም ሳይኖር ድርጅቱ (ኮንስታ) ከ1/3ኛ በላይ የሆነ ገንዘብ ካባከነ በኋላ የተጀመረው ሥራ እንዲቆም ተደርጓል፡፡
የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ ምንም እንዳልተሠራና የመስመርና የድልድይ ሐዲዶች ተነስተው ለባሰ ኪሣራና ውድመት ድርጅቱ መዳረጉ እየታወቀ፣ ሕዝብና መንግሥትን ለማታለል መስመሩ እንደተሠራና እንዳለቀ ተቆጥሮ ባለፈው አምስት ወር ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ድል ያለ ድግስ ተደግሶ ምረቃ መደረጉ ነው፡፡ ለኮንስታም ድርጅት ሽልማት መስጠቱ እንደዚሁም በድርጅቱ ኃላፊዎችም የትራንስፖርት ሥራው ተጀምሮ በሳምንት አምስት ጊዜ ባቡር እየተመላለሰና ሥራው እንደተጀመረ መግለጫ መሰጠቱ አነጋጋሪ ነው፡፡
በያዝነው ወር ደግሞ የ114ቱ ኪሎ ሜትር 60 ሚሊዮን ዩሮና ለድግሱ ወጪ ብክነት ተጠያቂው ማን እንደሆነ ሳይለይ፣ ከድሬዳዋ ጂቡቲ መስመር ለማስቀጠል የድርጅቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የሐዲድ መስመሩን ለመጠጋገን ዘመቻ ጀምረዋል (በቅርቡ አይሻ ላሠራውና ጐርፍ ወስዶት ተጠገነ የተባለውን 2,000,000 ብር ወጪ የሆነውን ሳይጨምር)፡፡ ሆኖም ግን ይሳካላቸው አይሳካላቸው ፈጣሪ የሚያውቀው ቢሆንም፣ ከ30 ዓመታት በላይ ድርጅቱን ሲመሩ የነበሩና ፈጽሞ ለኪሣራ የዳረጉ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ በሐዲድ ሥራ ላይ (በባቡር ቴክኖሎጂ) ምንም ዓይነት ዕውቀት የሌላቸውና በሙስና የተጨመላለቁ የማኔጅመንት አባላት፣ ትላንት ድርጅቱ አነስተኛ ቢሆንም ለባቡሮችና ለጋሪዎች እንደዚሁም ለመስመር ሥራው ሐዲዶችና መለዋወጫዎች እያሉት ማስተዳደር ያልቻሉ፣ በቂ ባለሙያ በሌለበትና ሥራውን ለቆ በሄደበት ሁኔታ ዛሬ ከዜሮ ተነስቶ ምንም ሳይኖር ከድሬዳዋ ጂቡቲ ባቡር እንዲቀጥል እናደርጋለን ብሎ በድፍረት መነሳሳት፣ አገርን ለከፍተኛ ወጪ ሕዝብን ደግሞ ለአደጋ የሚዳርግ ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ መቀለድ ስለሆነ ሊታሰብበት እንደሚገባ ከወዲሁ መጠቆም እወዳለሁ፡፡
(ሜንታ ነኝ፣ ከድሬዳዋ) ************
የ15 ከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ወቅታዊ ሁኔታ
የ15 ከተሞች መጠጥ ውኃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክና በአውሮፓ ኅብረት ብድርና ዕርዳታ በመካሄድ ላይ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ሦስት አካላት ያሉት ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 36.2 ሚሊዮን ዩሮ ነው፡፡ ይህም 16.5 ሚሊዮን ዩሮ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በብድር፣ 16.5 ሚሊዮን ዩሮ ከአውሮፓ ኅብረት በዕርዳታ የተገኘ ሲሆን፣ የተቀረውን ማለትም 3.2 ሚሊዮን ዩሮ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን ነው፡፡
ነገር ግን በጨረታ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋ በመናሩ ምክንያት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ 50 ሚሊዮን ዩሮ በላይ እንደሚያስፈልግ ይገመታል፡፡ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 23 ቀን በ2010 በተደረገው የጨረታ ሒደት የግንባታ ጨረታው ኮንስታ ስፓ ይመራው ከነበረው የሦስት ድርጅቶች ጥምረት ወይም ሽርክና ማቲዮሊ ጆይንት ቬንቸር በመባል ይጠሩ ከነበሩ የኮንትራክተር ስብስቦች ጋር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን ውል በመፈራረም፣ ግንባታው እ.ኤ.አ. ጥር 20 ቀን በ2011 በይፋ ተጀምሮ ነበር፡፡
ሆኖም ኮንትራክተሩ በገባው ውል መሠረት ሥራ እንዲያጠናቅቅ የተሰጠውን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች፣ ትዕዛዞችና ማስጠንቀቂያዎች ላይ ትኩረት ባለመሰጠቱ ከድርጅቱ ጋር የነበሩንን ውሎች አስመልክቶ ከአበዳሪ፣ ከለጋሽ ድርጅቶቹና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር መወሰድ የሚገባውን ዕርምጃ አስመልክቶ ተደጋጋሚ ውይይቶችና ምክክሮች ከተደረጉ በኋላ፣ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 12 ቀን 2013 ጀምሮ የግንባታ ውሉ እንዲቋረጥ ሆኗል፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አቋም መሠረት ይህ የውል መቋረጥ ቀደም ሲል መደረግ የነበረበት ቢሆንም፣ ከአውሮፓ ኅብረት የተገኘውን ዕርዳታ ላለማጣት ሲባል እንዲዘገይ ተደርጓል፡፡
ስለዚህ በቅርቡ የተከሰተው መቋረጥ የግንባታ ውሎቹ መቋረጥ ብቻ እንጂ ፕሮጀክቱ አለመቋረጡ ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ወቅት ከሁለቱ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች ጋር ያሉንን የብድርና ዕርዳታ ስምምነቶች ለማራዘም ከመግባባት ተደርሶ ጉዳዩ በሒደት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከሁለቱ አበዳሪና ለጋሽ ድርጅቶች በተደረገው ስምምነት መሠረት የተቀሩት ሥራዎችን ለማስጨረስ የጨረታ ሒደቱ እንዴት መሆን እንዳለበትና በምን መልኩ ሒደቱን ማሳጠር እንደሚቻል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተወያይቶ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
በመሆኑም በቅርቡ በተቋረጡት ኮንትራክቶች ያልተቆፈሩ የውኃ ጉድጓዶች ለማስቆፈር ከአንድ ኢትዮጵያ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት የተፈጸመ ሲሆን፣ የቧንቧና መገጣጠሚያዎች ግዢን ለማከናወን የጨረታ ሰነድ ዝግጅቱ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም የቧንቧና መገጣጠሚያዎች ግዢ ጨረታ በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚወጣ ይጠበቃል፡፡ የተቀሩት የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዢና ተከላ የጨረታ ሰነዶች ዝግጅት በቅርቡ እንደሚጠናቀቅና አየር ላይ እንደሚውል እናረጋግጣለን፡፡ በሌላ ወገን የፕሮጀክቱ አካል የሆነው የአቅም ግንባታ ሥራ ውል ተፈጽሞ በአሁኑ ወቅት በተመረጡ ስምንት ከተሞች ሥራው ተጀምሯል፡፡
(የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር)
የጥቂት ዳያስፖራዎችን ሕገወጥ ተግባር የሚመለከት ጥቆማ 
የኢትዮጵያ መንግሥት ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ጀምሮ አሁን በሥልጣን ላይ እስከሚገኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ድረስ አገራችንን የበለፀገችና ለዜጎች ምቹ የሆነች አገር ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ እኛም በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሆነን በተለያየ አጋጣሚ የሌላ አገር ዜግነት ያለን ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ባለን ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት የበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ ምቹ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ወደተግባር እንድንገባ ላደረጉትና እያደረጉት ላሉት በጎ ነገር ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
አሁን ግን ይህን የመንግሥትና የሕዝብ ጥሪ እንደ ልዩ አጋጣሚ በመጠቀም በተለያዩ ተቀባይነት በሌላቸው ሥራዎች ላይ በመሳተፍ አገር እየጎዱ፣ የመንግሥትን ገቢ እያሳጡ እንዲሁም የብዙውን አገር ወዳድ ዳያስፖራ ልፋት መና እያስቀሩ በአቋራጭ ለመክበር የሚሯሯጡ ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ዳያስፖራዎችን በቅርበት እየተመለከትን ነው፡፡
እነዚህ ዳያስፖራዎች ሕገወጥ ሥራዎችን በሕጋዊነት መጋረጃ በመጋረድ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከሚፈጽሙትም ሕገወጥ ተግባሮች መካከል በውጭ አገር ያፈሩትን ጥቂት ሀብት የተለያዩ ውስብስብ መንገዶችን በመጠቀም አራጣ በማበደር በአጭር ጊዜ ለመክበር የሚያደርጉት ጥረት አንዱ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በተደጋጋሚ ከአገር ሲወጡና ተመልሰው ሲመጡ የግል መገልገያዎች በማስመሰል የተለያዩ ቁሳቁሶችን (በተለይ ኮምፒውተሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና የተለያዩ መድኃኒቶችን) አስፈላጊውን የመንግሥት ቀረጥ ሳይከፍሉ ይዘው በመግባት፣ ንግድ ፍቃድ ሳያወጡም ሆነ አስፈላጊውን መንገድ ሳይከተሉ ለገበያ እያቀረቡ ሕጋዊ ነጋዴውን እየጎዱ ይገኛሉ፡፡
በዚህ አጋጣሚ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ፍቃድና መታወቂያ እንዲሰጥ ኃላፊነት የተሰጠው የመንግሥት አካል፣ አዲስ ፈቃድ ሲሰጥም ሆነ የነበረውን ሲያድስ አገር ውስጥ በምን ሥራ ላይ ለመሳተፍ እንዳሰቡና እየተሳተፉ እንደሚገኙ የማጣራት ሥራ ቢሠራ መልካም ነው፡፡ እንዲሁም የፍትሕ አካላትና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አስፈላጊውን ክትትል ቢያደርጉ፣ ይህንን ሕገወጥ ተግባር ሥር ከመስደዱ በፊት ለመግታታት እንደሚቻል አምናለሁ፡፡
ከሁሉ ሁሉ በላይ ግን የአገራችን ልማት የሚናፍቀን ኢትዮጵያውያን ሆንን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እነዚህን ጥቂት ሕገወጦች ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ በቃችሁ በማለት ከመምከር ጀምሮ አስፈላጊውን ጥቆማ ለተገቢው አካል መስጠት ይገባል፡፡ ይህንንም ከማድረግ እነዚህ ግለሰቦች ከሕገወጥ ተግባራቸው ተገትተው ራሳቸውንም ሆነ አገርን በሚጠቅም ተግባር እንዲሳተፉ በማድረግ ለተነሳንለት ራዕይ የበኩላችንን ኃላፊነት እንድንወጣ እጠይቃለሁ፡፡
(የአገርን ጥቅም ከሚያስቀድሙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አንዱ)
ethiopian reporter
source.... justfreedomnow.blogspot.no/2013/07/114-60.html

ተጠርጣሪ ባለሥልጣናት ባለድርሻ የሆኑበት ‹‹ልማት በዕድገት›› የሚባል ድርጅት መገኘቱ ተጠቆመ

ተጠርጣሪ ባለሥልጣናት ባለድርሻ የሆኑበት ‹‹ልማት በዕድገት›› የሚባል ድርጅት መገኘቱ ተጠቆመ


በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከሚገኙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኃላፊዎችና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጋር በተጠረጠሩበት ወንጀል ታስረው የሚገኙት የትራንዚት ሠራተኛ በነበሩት አቶ ማሞ ኪሮስ ስም የተቋቋመና የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊዎች ባለድርሻ የሆኑበት ‹‹ልማት በዕድገት›› የሚባል ድርጅት መገኘቱን፣ የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ሐምሌ 18 ቀን 2005 ዓ.ም. የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ኃላፊ በነበሩት እነ አቶ ዳዊት ኢትዮጵያ የምርመራ መዝገብ በተፈቀደለት አሥር ቀናት ውስጥ ያከናወናቸውን የምርመራ ሒደቶች ለችሎቱ እንዳስረዳው፣ አቶ ማሞ ኪሮስ የትራንዚት ሠራተኛ ሆነው ሳለ ‹‹ያለቀረጥ በነፃ ያስገቧቸው›› በሚል የተጠረጠሩ 22 ኮንቴይነሮች ሞጆ ደረቅ ወደብ ላይ ተይዘዋል፡፡ ተጠርጣሪውና በሌላ ምርመራ መዝገብ የተካተቱ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ባለድርሻ የሆኑበት፣ ‹‹ልማት በዕድገት›› በሚል ስያሜ አክሲዮን ማኅበር አቋቁመው መገኘቱን መርማሪ ቡድኑ አስረድቷል፡፡
አዲስ የተቋቋመውን ድርጅት አቶ ማሞ በሥራ አስኪያጅነት በሚመሩበት ጊዜ ‹‹ለድርጅቱ›› እየተባለ የተለያዩ ዕቃዎች ያለቀረጥ መግባታቸውን የሚያሳይ ፍንጭ ማግኘቱንም መርማሪ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ድርጅቱን የሚገመግምና የሚመረምር ቡድን አቋቁሞ እየሠራ መሆኑንም ቡድኑ አክሏል፡፡
የምስክሮችን ቃል መቀበሉን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ አዳማ፣ አዋሽና ሚሌ የተጓዘው መርማሪ ቡድንም በአጠቃላይ የ18 ምስክሮችን ቃል መቀበሉን አስታውቋል፡፡
ሁሉም ተጠርጣሪዎች ያከማቹትን ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን በሚመለከት ባለሙያዎችን በማሰማራት እየሠራ መሆኑንም ቡድኑ ገልጿል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ዳዊት ኢትዮጵያ፣ ማሞ አብዲ፣ አሸብር ተሰማ፣ ፍፁም ገብረ መድኅን፣ ማሞ ኪሮስ፣ አበበልኝ ተስፋዬና ኮነ ምህረቱ (በዋስ ተለቀዋል) ሲሆኑ፣ ሁሉም በግላቸውና በጠበቆቻቸው አማካይነት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸውና በውጭ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡
ሌላው ፍርድ ቤቱ የተመለከተው በእነ አምባው ሰገድ አብርሃ (የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሕግ ማስከበር ኃላፊ)፣ አቶ ተክለአብ ዘርአብሩክ፣ ያዴሳ ሚደቅሳ፣ እሸቱ ግረፍ፣ ጌታሁን ቱጂ፣ መላኩ ግርማ፣ አስፋው ሥዩም፣ ጌታነህ ግደይ፣ ዮሴፍ አዳዊ፣ በእግዚአብሔር አለበልና ዘለቀ ልየውን የምርመራ መዝገብ ነው፡፡
ኮሚሽኑ በተሰጠው አሥር የምርመራ ቀናት ለጠቋሚዎች ይከፈል የነበረን አበል፣ ቀረጥ ያልተከፈለባቸውና በሕገወጥ ጥቅም መመሳጠር የገቡ ዕቃዎችን፣ ታክስ ዝቅ የማድረግ ሥራን በሚመለከት ሰነድ መሰብሰቡንና ምስክሮችን መቀበሉን አስረድቷል፡፡
በሁሉም ተጠርጣሪዎች ማለትም በዕለቱ በቀረቡት 18 ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ ምርመራ እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ተጨማሪ የ14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
እነ አምባው ሰገድ በራሳቸውና በጠበቆቻቸው አማካይነት የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ፣ የተጠርጣሪዎችን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ለኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን አሥር ቀናት በመፍቀድ ለሐምሌ 29 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ethiopian reporter

Thursday, July 11, 2013

እነመላኩ ፈንታ እና በእነ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገቦች ላይ ለ5ኛ ጊዜ የምርመራ ቀጠሮ ተፈቀደ


በአሸናፊ ደምሴ
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምርመራ እያካሄደባቸው በሚገኙት በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የቀድሞ አመራሮችና ነጋዴዎች ተቀዳሚ ሁለት መዝገቦች ስር ባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የመርማሪ ቡድኑ ስራዬን አላጠናቀኩም በማለቱ ለ5ኛ ጊዜ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፍ/ቤት ፈቀደ።በትናንትናው ዕለት በእነመላኩ ፈንታ መዝገብ ላይ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የስራ ክንውናቸውን ለችሎቱ ሪፖርት ያደረጉት የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን አባላት እንደገለፁት፤ 1ኛ፣ 2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተጠርጣሪዎችን ጠቅሶ ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ የተከለከለን ስሚንቶ በህገ ወጥ መንገድ እንዲገባ በማድረጋቸው ክስ የተመሰረተባቸውን ግለሰቦች የክስ ሂደት ማቋረጥን በተመለከተ ሰነዶች መሰብሰባቸውን ከሶስት ሰዎችም የምስክርነት ቃል መቀበላቸውን አስረድተዋል። በተለያዩ የጉምሩክ ህጎች ጥሰት ሳቢያ የተመሰረተ የጅምላ ክሶች ማቋረጥን በተመለከተ በ1ኛ፣ በ2ኛ፣ በ3ኛ፣ በ4ኛ እና በ7ኛ ተጠርጣሪዎች ላይ 20 የሚደርሱ መዝገቦች መሰብሰባቸውና የምስክሮችን ቃል ስለመቀበላቸው አትቷል። የመርማሪ ቡድኑ አክሎም ከተገቢ በላይ ሀብት ማካበትን አስመልክቶ ከተለያዩ ባንኮችና ግንኙነት ካላቸው ተቋማት ማስረጃዎችን ስለመሰብሰቡ ጠቁሟል። አክሎም በተጠርጣሪዎች ላይ የምስክሮችን ቃል መቀበልና ሰነድ ማሰባሰብን እንዲሁም የኦዲት ሪፖርቶችንና የባለሙያ አስተያየቶችን እየሰበሰበ መሆኑን በመጥቀስ የምርመራ መዝገቡን በማደራጀት ስራ ላይ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል። ክንውኑን በዝርዝር ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ይቀረኛል ያላቸውን ስራዎችም ዘርዝሯል። በዚህም መሰረት ከቀረጥ ነፃ የገቡ ዕቃዎች ለታለመላቸው አላማ ስለማዋል ወይም አለመዋላቸው ማጣራት እያደረኩ ነው፤ በህገ-ወጥ መንገድ ወደሀገር ውስጥ የገባ ስሚንቶዎችን በተመለከተ የስድስት ምስክሮችን ቃል መቀበል፤ በናዝሬት በሚሌና በድሬዳዋ ያሉ ሰነዶችንና የሰው ምስክሮችን ቃል መቀበል ቀጣይ የቡድኑ ስራ ስለመሆኑ ተቀምጧል። በሌላም በኩል በቦሌ ኤርፖርት አድርገው ወደሀገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎችን በተመለከተ የተቋረጡ ክሶች ላይ የሶስት ምስክሮችን ቃል መቀበል እና ምንጩ ያልታወቀ የሀብት ክምችትን በተመለከተ የምስክሮችን ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ እንደሚቀረው ጠቁሟል። በዚህም ፍ/ቤቱ ተጨማሪ የ14 ቀናት ተጨማሪ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።ከዚህም ባሻገር መርማሪ ቡድኑ በእነመላኩ ፈንታ መዝገብ ሶስተኛኛ ተጠርጣሪ ሆነው የቀረቡት የገቢዎችና ጉምሩክ ከፍተኛ አቃቤ ህግ ምክትል ዳይሬክተር የአቶ መርክነህ አለማየሁ እህት እንደሆኑ የተነገረላቸውን ወ/ሮ ትዕግስት አለማየሁ በመዝገቡ 10ኛ ተጠርጣሪ አድርጎ አቅርቧል። ግለሰቧ ከወንድማቸው ጋር በመመሳጠር በሀዋሳ የተንጣለለ ቪላ ቤት ከመገንባታቸውም በተጨማሪ በባንክ ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ አኑረዋል ሲል ያትታል። በዚህም ሳቢያ ወንድማቸው በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ከባንክ አውጥተው ለማሸሽ ሲሞክሩ ደርሼባቸዋለሁ ሲል ያትታል። በተያያዘም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ጉዳያቸው በመታየት ላይ በሚገኘው በእነአቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ያከናወናቸውን እና የሚቀሩትን ተግባራት ለፍርድ ቤቱ አስረድቶ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜን የጠየቀ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ ግን የ10 ቀናት ቀጠሮን ሰጥቷል። በዚህም መዝገብ ውስጥ ሁለት አዳዲስ ተጠርጣሪዎች ተካተው ቀርበዋል። በዚህም መሰረት የአዳማ ቅርንጫፍ ሰራተኛ የሆኑት አቶ ያለው ዋቆ እና እንጀራ እናቱ ናቸው የተባሉት ወ/ሮ ሽቱ ነጋሽ ተካተውበታል። ይህም አጠቃላይ የተጠርጣሪዎቹን ቁጥር 63 ያደርሰዋል።በመሆኑም በእነገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ መዝገብ ስር ቀሪ የምስክሮቹን ቃል ለመቀበል እና መዝገቦችን ለማሰባስብ እንዲሁም በአዳማና በሚሌ ፣ በድሬዳዋ የሚደረጉ ምርመራዎችን ለማጠናቀቅ የ14ቀን ተጨማሪ ጊዜን ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ግን 10 ቀናትን በመፍቀድ ለሐምሌ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።በአንፃሩ ደግሞ በእነመላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ስር ለተዘረዘሩት ስምንት ተጠርጣሪዎች የ10 ቀናት ተለዋጭ የምርምራ ጊዜን በመፍቀድ ለሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም ቀጥሯል።

source........sendek 

Thursday, July 4, 2013

ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ?

south_president-1
July 4, 2013
ትምህርት ሚኒስቴርነት፤ በማማረር ወይስ በማባረር…! ?
መንጌ የነገረኝ ቀልድ ትቅደም፤
መንጌ ማለት አሉኝ ከምላቸው ጓደኞቼ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እሳት የላሰ የአራዳ ልጅ ነው፡፡ “ካራዳ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ፤ ባይበሉም ባይጠጡ ስንቅ ይሆናል ቀልዱ” የተባለለት ጨዋታ አዋቂ!
አንድ ሙዝ ነጋዴ ነበር አለኝ መንጌ…
እሺ…
ሙዙ ገበያ ሲያጣ ምን ያደርጋል መሰለህ…
እ…
የተሰቀለውን ያወርደዋል፡፡ መሬት የነበረውን መስቀያው ላይ ያንጠለጥለዋል፡፡ እንደርሱ ብቻ አይደለም፤ “ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ…” ሲልም ያበረታታዋል… አለኝ፡፡
እኔ ፋራው የምጠይቀው ጥያቄ ነው እንጂ የሚገርመው… ከዛስ… አልሸጥ ያለው ሙዝ ይሻጣል…. ወይስ ይንቀሳቀሳል…?
መንጌ ይስቃል… እርስዎም ይሳቁ፡፡
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሙዙ ነጋዴ ናቸው፡፡ የሱቁ ባለቤቶች “እስቲ ደግሞ ለአኬር፤ ሙዝ አትፍዘዝ ተንቀሳቀስ” ይበሉ … ብለዋችው ይሁን; በራሳቸው ተነሳሽነት እንጃ ሞዛዞቻቸውን ቦታ አቀያይረዋቸዋል፡፡ (ሙዛ ሙዞቻቸውን ማለቴ ነው….)
አቶ ሬድዋን የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር… ተደርገዋል፡፡ የምርም ስለ ኢህአዴግዬ ዋይ ዋይ ለማለት እርሳቸው ሳይሻሏት አይቀሩም፡፡ ምክንያቱም አቶ በረከት ስምዖን ቻርጅ እንዳለቃቸው በጣም ያስታውቃሉ፡፡ (ጢን… ጢን.. ማለት ከጀመሩ ቆይተዋል) ስለዚህ ነጋ ጠባ ስለ ድርጅታቸው በየአደባባዩ እየተከሰቱ “በላውድ ስፒከር” ሊጮሁላት አይቻላቸውም፡፡ እናም፤ ባትሪ ፉሉ አቶ ሬድዋን መተካታቸው ለዚህ ቦታ ትክክል ይመስለኛል፡፡
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስቴር… ይሄኛው ያስቃል፡፡ የሰውዬው የስራ ልምድ እኮ አስተኳሽነት ነው፡፡ እንግዲህ በዚህ የስራ ልምዳቸው እንደ ጥይት የሚተኳኮስ የትራንስፖርት ስርዓት ይዘረጉልናል፡፡ ብለን ተስፋ እናድርግ እንዴ…!
በእውነቱ ቀልድ በብዛት የሆነበት ፓርላማ ነውኮ ያለን! ለአስፋልቱ የተሸለ ስርዓት ዝርጋታ “የሰው ያለህ” በሚለው የትራንስፖርት ችግር ላይ፤ የሰው ልጅን አስፋልት ላይ በጥይት ሲዘረጉ የነበሩ ሰውዬ ሲሾሙ አስደናቂ ታሪክ ላይ መመዝገብ ያለበት ታሪክ ነው!
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የማፈናቀል ጥበባቸውን ለምን እንደተፈለገ እንጃ ይዘውት ወደ ትምህርት ሚኒስቴርነት ከች ብለዋል፡፡ ይቺ ስልጣን ከአቶ ደመቀ በምን ምክንያት “መንጩ” እንደተደረገች እንጃ… አቶ ደመቀ ስራ በዝቶባቸው ይሆናል እንዳንል… እርሳቸው ለራሳቸው አንድ ሶስተኛ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው፡፡ እንኳንስ ለአንድ ሶስተኛ ምክትልነት እና ያኔ አቶ ሃይሌ ብቻቸውን ሙሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው እየሰሩ፤ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነቱንም “ቀጥ” አድርገው ይዘውት ነበር፡፡ ታድያ አንድ ሶስተኛ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነትና የትምህርት ሚኒስቴርነት ምን አላት…
የሆነ ሆኖ የትምህርት ሚኒስቴርነቱን ቦታ አቶ ሃይሌ ለአቶ ሽፈራው ሽጉጤ እነሆ በረከት ብለዋቸዋል፡፡ እኛም እየጠየቅን እንገኛለን፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለፈው በክልላቸው ያማረሯቸውን እና ከክልላቸው ያባረሯቸውን ሰዎች እያስታወስን፤
የትምህርት ሚኒስቴርነት ብቃት የሚለካው በማማረር ወይስ በማባረር… ! ? እንላለን፡፡
ችግሩ መንግስታችን የፈለገ ጥያቄ ቢጠየቅ መልስ መስጠት መልስ የመጥራት ያክል ይከብደዋል እና መልሱ “መ” ነው፡፡ መ- መልሱ የለም፡፡
አረ እረስቼያቸው እኒያ ፍትህ ሚኒስቴርም በምን እንደወረዱ ሳይነገረን ሌላ በምን እንደመጡ የማናቃቸው ሰውዬ ተሸሙብን አይደል!
ለማንኛውም ሹመኞቹ ቢቀያየሩም ባይቀያየሩም ዋናው የድርጅታችን ልብ መግዛት ነው እና ድርጅታችን ኢህአዴግ እኛን ቦንድ ግዙ እንደምትለን ሁሉ፤ እኛም እባክሽ ልብ ግዢ እንላታለን! ቦንዱ ለራሳችሁ ብዬ ነው እንደምትለንም ሁሉም፤ እኛም ልብ ግዢ ማለታችን ለራስሽ ብለን ነው እንላታለን!

source ...http://www.abetokichaw.com/2013/07/04/