Friday, August 2, 2013

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ሀምሌ 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ቃሲም ፊጤ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡
ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው አቶ ቃሲም የተጠረጠሩበትን የሙስና ወንጀል መሠረት በማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ኮሚሽኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀደም ብሎ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ምክር ቤቱም የግለሰቡ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የቀረበለትን የሰነድና የውሳኔ ሐሳብ ከመረመረና የአሠራር ሒደቶችን ግንዛቤ ውስጥ ካስገባ በኃላ ሰኔ 28/2005  ያለመከሰስ መብታቸውን ያነሳ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል፡፡
የተጠርጣሪው ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ምክር ቤቱ የደረሰበትን ውሳኔ ተከትሎ ኮሚሽኑ አቶ ቃሲምን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን ፥ የተጠርጣሪነት ቃላቸውን በመቀበል አስፈላጊው ሕጋዊ ሥራ ማከናወኑንም ነው ያመለከተው ፡፡
ተጠርጣሪው ከዚህ ቀደም ከሀገር ወጥተዋል  በሚል  ሲወራ  እንደነበር የሚታወስ  ቢሆንም ፥ ዛሬ ማምሻውን በቁጥጥር  ስር የዋሉት በቢሯቸው  እንዳሉ  መሆኑን ነው ኮሚሽኑ  ያስታወቀው ።
ግለሰቡ ቀደም ብለው ከሀገር የወጡትም ለስልጠና እንደነበር ነው የተመለከተው ።
ነገ  በፌደራሉ ከፍተኛ  ፍርድ ቤትም ቀርበው  ቀጠሮ ይጠየቅባቸዋል  ተብሎ  ይጠበቃል ።
source....fababc.com 



No comments:

Post a Comment