Friday, August 23, 2013

መሰረት በዳይምንድ ሊግ የዓመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝግብ አሸነፈች

በ5ሺ ሜትር የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮና አሸናፊ መሰረት ደፋር በሲዊዲን ስቶኮልም ትናንት በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ 3ሺ ሜትር ውድድር 8፡30፡29 በሆነ ሰዓት በመግባት በርቀቱ የዓመቱን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች፡፡
በሞስኮው ሻምፒዮና 5ሺ ሜትር መሰረትን በመከተል የገባችው ኬኒያዊቷ መርሲ ችርኖ በዚህ ውድድር ላይ 8፡31፡23 በሆነ የግሏ ምርጥ ሰዓት ሁለተኛ ሆናለች፡፡
ሌላዋ ኢትዮጵያዊት  ሲፋን ሀሰን ውድድሯን  8፡32፡53  በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ሶስተኛ ስትሆን ገንዘቤ ዲባባ 8ኛ ወጥታለች፡፡
ከሞስኮው ሻምፒዮና ከጥቂት ቀናት በኋላ ማሸነፍ በመቻሌ ደስ ብሎኛል፣በጥሩ ብቃት እንደምገኝ ይሰማኛል ስትል መሰረት አሸናፊ ከሆነች በኋላ ተናግራለች፡፡
በ1ሺ 5 መቶ ሜትር መኮነን ገብረ መድህን  ውድድሩን 9ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል፡፡በዚህ ውድድር  የጅቡቲው አትሌት አያንለህ  ሱለይማን  የኬኒያውን የርቀቱ  አሸናፊ አሰቤል ኪፕሮፕን በመቅድም አሸንፏል፡፡
በ8 መቶ ሜትር ሴቶች ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አበባ አረጋዊ በሲዊዲን በደጋፊዋ ፊት ተሸንፋለች፡፡አበባ አረጋዊ በ1ሺ 5 መቶ ሜትር በሞስኮ ሻምፒዮና ለሀገሯ ወርቅ ብታበረክትም በዚህ ውድድር 6ኛ በመሆን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ኬኒያዊቷ ኤኑስ ሳም ናት በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆነችው፡፡
erta

No comments:

Post a Comment