Friday, August 16, 2013

የኢትዮጵያ አንድነትና ሕልወና ከባድ አደጋ ተደቅኖበታል። ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ማምራቱ አይቀሬ ነው።

የኢትዮጵያ አንድነትና ሕልወና ከባድ አደጋ ተደቅኖበታል። ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ማምራቱ አይቀሬ ነው።

በመካከላችን አንድነት የሚኖረው መቼ ነው?
መተሳሰብ የሚሰፍነው መቼ ነው?
ለየራሳችን ፍላጎት መተሳሰቡን (‹‹የመረዳዳት ባህላችንን››) እናቆየውና የራሳችን የሁላችን ስለምንላት ሀገራችን የጋራ አስተሳሰብ አለን?
አይመስለኝም፡፡ ብዙዎቻችን ከራሳችን ውጭ ማንም ያለ አይመስለንም፡፡ ሀገሪቱም ከእኛ ውጭ አሳቢ እንደሌላት እንድመድማለን፡፡ አለዚያም ሀገሪቱን ረግጠን እና በሀገሪቱ አላግጠን ለማለፍ መለኮታዊ ቅባት እንደተቸረን ይሰማናል፡፡ ይህማ ባይሆን እኩልነታቸውን አስከብረናል በምንልበት ሀገር ዘለፋን አፈናጥረን በተውን !
ህውሃት/ወያኔ በገነቡት ሥርዓት ውስጥ በደለ፣ግፎች ፣ችግሮችና እንከኖች የትዬ ሌሌ እንደነበሩ 22 አመታት ቢያንስ ከተቃዋሚዎች አንደበት ነጋ ጠባ እንሰማለን፡፡
አንዳንዶቹን ጆሮ ዳባ ልበስ ካላልን በደንብ እናውቃቸዋለን፡፡ እነሱም ፓርቲያቸውም አይክደውም፡፡ በየቀበሌውና በየወረዳው እንዲሁም በየክልሉ እንደ “ማፍያ” መደራጀት የቀራቸው “የመንግስት ሌቦች” እና በዝባዦች መኖራቸውን ማንም አይክድም ፡፡
ልማታችንን የጎተቱት እነማን ሆኑና?
ዛሬም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ብሔር ተኮር ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከቀበሌ ጀምሮ ያሉት የስልጣን እርከኖች በአንድ ብሔር አባላት የተያዙ እንደሆኑ ሀሜት ይናፈሳል ብቻ ሳይሆን እውነትም ጭምር ነው፡፡
ከደቡብ ኢትዮጵያ የተፈናቀሉት አማሮች መጠጊያ ማጣታቸው እስካሁንም እያነጋገረ ይገኛል፣ ኦጋዴን ውስጥ ያልተፈታ ችግር አለ፣ ኦሮምያ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ችግር አለ።የኑሮ ውድነት ዜጎችን አስጨንቆ ይዟል፣ ከተሞች በምእራባዊያን ባሕል ተወረዋል ፣ የትምህርት ጥራት ችግር አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል፣ ሥራ አጦች በርክተዋል ፣ ካድሬ መሆን የመኖርያ ፈቃድ ከመሰለ ቆይቷል፣ የመኖርያ ቤት እጥረት አሳሳቢ ነው፣ ሃይማኖታዊ አክራሪነት መንግስት እዲፈጠር ይጎተጉታል ፣ የፕሬስ ነጻነት የለም ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ተባብሷል፣ ውሸት በተደጋጋሚ ይስተጋባል፣ ቋንቋን፣ መሬትን፣ ባሕልን ወዘተ የተመለከቱ ጥያቄዎች ዘወትር ይነሣሉ፡፡ ለእነዚህ እና መሠል ጉምጉምታዎች ቀጥተኛ እና ቀና የሆኑ መልሶችን መስጠት የሚቻለው አስተዳደር ቢመጣለት ሕዝቡ ደስታውን አይችለውም፡፡
የዚህ ሁሉ ምንጩ ቢያንስ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሀገሪቱን የጋራ አድርገን አገራዊ መግባባት ላይ መድረስ ስላቃተን ይመስለኛል፡፡ (ቢንላደን ለሁሉም አሜሪካዊያን እንጅ ለቡሽ አሊያም ለኦባማ ብቻ ጠላት እንዳይደለ ልብ ይሏል)
በርካታ ህውሃት/ኢህአዴግ ኀዘንተኞች በህዝቡ ላይ ሲያላግጡ “የመለስን ራዕይ እናሳካለን፣ የጀመሩትን እናስጨርሳለን” የሚሉ ትላልቅ መፈክሮችን ሲያስተጋቡ መስማት በመንግስትና በካድሬዎች የተለመደ ሆኗል፡፡
ሕዝብ ሲያጉረመርምባቸው የነበሩ ጉዳዮች በእርጋታ ሊጤኑ እንደሚገባቸው መረዳት መልካም ነው፡፡ በየጊዜው የሀገር ውስጥና የውጪ ሚዲያዎች የጩኸት ሰበብ የሆኑ የተለያዩ አዋጆች፣ ደንቦች፣ ክልከላዎች፣ አፈናዎች ወዘተ—በአዲሱ ተተኪ አስተዳዳሪ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል ብል የተሳሳትን አይመስለኝም፡፡
እውነት እቺ አገር የማን ናት?
የተቃዋሚዎች ወይስ የኢህአዴግ? የእኛ የዜጎች ሁሉ ወይስ የጥቂት ባለጊዜዎች?በደንብ አስበን በደንብ መክረን በደንብ አገናዝበን ለራሳችን መልስ ልንሰጥበት የሚገባ ሁነኛ ጥያቄ ነው፡፡
ያኔ ብቻ ነው “እቺ አገር የአንድ ፓርቲ እዳ ናት ወይስ የሁላችን እዳ?” ለሚለው ትክክለኛ ድምዳሜ ላይ መድረስ የምንችለው፡፡
የኢትዮጵያ አንድነትና ሕልወና ከባድ አደጋ ተደቅኖበታል። ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ማምራቱ አይቀሬ ነው።
አምላክ አገራችን ይጠብቃት!
መልካሙን ያምጣልን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!
ከሰብዓዊ
source...freedom4ethiopia

No comments:

Post a Comment