Thursday, September 18, 2014

“ክልክል ነው”

“ክልክል ነው”

(በእውቀቱ ስዩም)
not allowed
ማጨስ ክልክል ነው
ማፍዋጨት ክልክል ነው
መሽናት ክልክል ነው
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል?
ትንሽ ግድግዳና ትንሽ ኃይል ባደለኝ
“መከልከል ክልክል ነው”፤ የሚል ትዕዛዝ አለኝ፡፡
(በእውቀቱ ስዩም፣ የ፣ሣት ዳር ሐሳቦች፣ 2000)

በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል

በጎደሬ ወረዳ የዘር ግጭት ተነሳ፤ መከላከያ ገብቷል

የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ከነቤተሰቦቻቸው ተገደሉ
gode-rie
በጋምቤላ ዞን በጎደሬ ወረዳ ነጋዴዎችና ሰፋሪዎች ከአካባቢው ተወላጅ የመዠንገር ጎሳ አባላት ጋር ተጋጩ። በግጭቱ ከ17 ሰባት በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በግጭቱ የመዠንገር ዞን አስተዳዳሪና የጎደሬ ወረዳ ዳኛ ከነቤተሰቦቻቸው የግጭቱ ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። ግጭቱን ለማብረድ የመከላከያ ሠራዊት የገባ ሲሆን፣ የጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ በጉዞ ላይ እንዳለ በተሰጠ መመሪያ እንዲመለስ ተደርጓል
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ለጎልጉል እንደገለጹት በወረዳው በመሬት ባለቤትነትና በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ከመሀል አገር በመጡ ሰፋሪዎችና ነጋዴዎች መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ ዓመታትን አስቆጥሯል። የፌዴራል አገዛዙም ሆነ የክልሉ አመራሮች ችግሩ ሳይሰፋ ሰላማዊ መፍትሄ ባለማፈላለጋቸው ችግሩ ሊካረር ችሏል። ኢህአዴግ የሚከተለው በዘር ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲ ለችግሩ መባባስ በዋንኛነት ተጠቃሽ ነው።
ባለፈው ሃሙስ በአንድ የመሃል አገር ሰፋሪና የአካባቢው ተወላጅ በሆነ አርሶ አደር መካከል ድንገተኛ ጸብ ተነስቶ ነበር። በጸቡ የመዠንግር ጎሳ አባል የሆነው አርሶ አደር ህይወት አለፈ። በጎሳ አባላቸው መገደል የተበሳጩ ዘመዶች ውሎ ሳያድር በወሰዱት የበቀል ርምጃ አንድ ሰፋሪ የመሃል አገር ሰው ህይወት አለፈ። እንደ ዜናው አቀባዮች ከሆነ በዚሁ በመሬት ጉዳይ በተከሰተው የሁለት ግለሰቦች ህልፈት ተከትሎ ችግሩ ተካረረ።
በተመሳሳይ ቀን ማምሻው ላይ ከመሃል አገር የመጡት ሰፋሪዎች የዞኑን አስተዳዳሪ፣ ባለቤታቸውንና ሁለት ልጆቻቸውን መኖሪያ ቤታቸው በመሄድ በስለት ገደሉ። በተመሳሳይ አንድ የጎደሬ ወረዳ አስተዳዳሪ ከባለቤታቸውና ከልጃቸው ጋር ተገደሉ። በደቦ የተጀመረው የስለት ግድያ እየሰፋ የሟቾችን ቁጥር 17 እንዳደረሰውና በስለት የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር ከ40 በላይ መሆኑን በስልክ የገለጹት ያካባቢው ነዋሪዎች “አሁን ፍርሃቻ አለ። ቤት ለቤት የተካሄደው ግድያ የት ጋር ያቆማል? የመከላከያ ሠራዊት ሚናም ግልጽ አይደለም” ብለዋል።
goderieየጋምቤላ ዞን ልዩ ኃይል ግጭቱን ለማብረድ እየገሰገሰ ባለበት ወቅት ከአዲስ አበባ በተሰጠ ትዕዛዝ ወደ ጋምቤላ እንዲመለሱ መደረጉን ያመለከቱት እኚሁ ክፍሎች፣ “የጋምቤላ ልዩ ኃይል ግጭቱ ያለበት ቦታ ሲደርስ በራሱ ክልል ሰዎች ላይ መጤዎች ጉዳት ማድረሳቸውን ሲመለከት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ግጭት ሊፈጠር ይችላል” በሚል ስጋት የልዩ ኃይሉ ወደ ጋምቤላ የተመለሰበትን ምክንያት ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በገጀራና በተለያዩ የስለት መሳሪያዎች የተካሄደው ግድያ የሚዘገንን እንደነበር፣ ቀን ጠብቆ ተጎጂው አካል ከመበቀል ወደኋላ እንደማይል፣ በስለታማ ቁሶች የሚከናወነው ግድያ ሊሰፋ እንደሚችል ስጋታቸውን አክለው የገለጹት ነዋሪዎች ኢህአዴግ ሰላማዊ መፍትሄ ሊፈልግ እንደሚገባ ከወዲሁ ጠይቀዋል። በጋምቤላ ክልል በሳንቲም የሚቸበቸበውና የተፈጥሮ ደን እያወደመ ያለው ኢንቨስትመንት የተወሳሰበ ችግር ማስከተሉ አይዘነጋም። በዚሁ ሳቢያ በርካታ ንጹሃን ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው። ክልሉን ከላይ ሆነው የሚመሩት አቶ አዲሱ ለገሰ መሆናቸው ይታወቃል።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን አስመልክቶ ከኦስሎ ለጎልጉል አስተያየት ሲሰጡ “ባሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የሰላም ረፍት ይሁን፣ ፍትህ በልጅ ልጆቻችሁ ትፈርድላችኋለች፣ ፍትህ ሩቅ አይሆንም” በማለት ነበር የጀመሩት። አያይዘውም “ምንም እንኳ ባል ፖለቲከኛ ቢሆን ሚስትና ልጆች ምን አደረጉ? ህጻናትና ሴቶች በማያውቁት ጉዳይ ለምን ሰላባ ይሆናሉ? ቀደም ሲል አብረው የሚኖሩ ሰዎች ዛሬ ለምን ይጋጫሉ?” ሲሉ ችግሩ ሁሉ የሚመነጨው ኢህአዴግ ከሚከተለው ጎሳን መሰረት ያደረገ የከፋፍለህ ግዛው መርህ አንደሆነ ገልጸዋል።
“መመሪያ ሰጪው፣ ገዳዩ፣ አስገዳዩ፣ ቆሞ ተመልካቹ፣ … ሁሉም ከፍትህ አደባባይ አያመልጡም” ያሉት አቶ ኦባንግ “ዘርን እየለየ የሚከናወን ግድያ “ጄኖሳይድ” ነው። አኙዋኮች ላይ በጅምላ ከተከናወነው ጭፍጨፋ ለይተን አናየውም” ሲሉ በጉዳዩ ክፉኛ ማዘናቸውን አመልክተዋል።
የሚመሩት ድርጅት ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለና አስፈላጊ ነው የሚለውን ስራ እያከናወነ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ ሁሉም ያካባቢው ነዋሪዎች ሰፋሪም ሆነ የቀዬው ተወላጆች እንደቀድሞ በፍቅር ሊኖሩ የሚያስችላቸውን እሴቶች እንዲጠብቁ መክረዋል። በተለያዩ ያገሪቱ ክፍሎች ጎሳን እየለየ የሚካሄደው ግድያና ማፈናቀል እየሰፋ እንጂ እየቀነሰ ባለመሆኑ ስጋቱ ከፍተኛ እንደሆነም ገልጸዋል። በዚህ ከቀጠለና ህወሃት የቀበራቸው የጎሳ ፈንጂዎች ሲነዱ እሳቱ ሁሉንም ስለማይምር ሁሉም ዜጎች ጥንቃቄ እንዲወስዱ አሳስበዋል። ኢህአዴግም ችግሮችን ከማስፋት ይልቅ የሚቃለሉበትን አግባብ ለራሱ ሲል ሊከተል እንደሚገባ ጠቁመዋል። ጎልጉል የዞኑንና የወረዳውን አስተዳደር ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይሁን እንጂ የክልሉ ፖሊስ ዝርዝር መግለጫ ባይሰጥም የተባለው ቀውስ ስለመፈጠሩ አልካደም።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Friday, September 12, 2014

ሰሞኑን ኢትዮጵያዊው መምህር ግርማ ወንድሙን ለማግኘት ከመላው አውሮፓ እና አሜሪካ ወደ ስዊትዘርላንድ የመጡት ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ቁጥር ከተጠበቀው ከ5 እስከ 6 እጥፍ ሆኖ በመገኘቱ ለፀጥታ ያሰጋል በማለት ፖሊስ ስነ ስርአቱን እንዲቋረጥ አድርጓል።

 Ethiopian healer causes chaos in Altstetten, Switzerland


A miracle healer from Ethiopia has attracted over 5000 visitors in Zurich complex 457 – where 300 to 700 were expected. For security reasons the police cleared the building.
If you were driving through the Hohlstrasse in Altstetten on Saturday afternoon, you probably stuck in a traffic jam. Thousands of people were running, according to a reader-reporter on the street. VBZ-employees had to regulate the traffic so that an even greater chaos wouldn’t materialize. “Hundreds of strollers were parked outside the complex 457″, says the reader reporter.
Responsible for the onslaught was the Ethiopian priest Memehir Girma Wondimu. “He can mentally and physically heal the sick,” says Mistre Haile Selassie, OK Member of the healer events in the complex. He had expected around 1,000 visitors. “But there were five or six times more.” People had traveled from all over Europe and even the United States. “Most of them came originally from Ethiopia and Eritrea.”
sw6 sw5 sw4 sw3 sw2
“Security was no longer guaranteed»
According to Marco Cortesi, media director of the Zurich city police, the organizers had announced 300 and 700 visitors: “Ultimately, however, it was around 2500 in the complex – and additional crowd of 2000 to 3000 were waiting outside.” Since security was no longer guaranteed, the police had to intervene at 2 clock. “The evacuation went smoothly – the priest was very cooperative,” says Cortesi.
Organizer Haile Selassie does understand the situation. But he is sad the priest couldn’t stay until Sunday as planned. “Many visitors traveled in vain.” But still, Wondimu has healed a paralytic in Zurich, among other things, says Haile Selassie.

ethiotube.....

Monday, July 7, 2014

ስለምንደግፈው ወይም ስለምንቃወመው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት የራሳችን አእምሮ ምን ያህል ፍትሀዊ ነው? የሐሳብ ልዩነት እርስ በእርስ ለመተናነፅ እንጂ ለቂመኝነትና በቀለኝነት አይዳርገን!



ብዙ ጊዜ የምንደግፋቸውና የምንቃወማቸው ነገሮች ምክነያታዊና ከማስተዋል ሳይሆን በደረቅ ስሜተኝነት ሲሆን ለምንደግፈው ከስኬት ይልቅ ውድቀት ለምንቃወመው ደግሞ ከምክነት ይልቅ ብርታት ይሆናል፡፡ የሰው ልጆች በስሜተኝነት መደገፍና መቃወም በሁሉም ማህበረሰብ የሚታይ ሲሆን በአንዳንድ ማህበረሰብ ግን ገዝፎ ይታያል፡፡ በስሜተኝነት የመደገፍና የመቃወም ባሕሪ ግን በዘር የሚተላለፍ ተፈጥሮአዊ ለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ይልቁንም ለዚህ ባሕሪያችን ትልቅ አስተዋፅዖ አለው ብዬ የምገምተው ከተወለድን በኋላ የሚገጥሙን የሕይወት ልምዶቻችንና ከባቢያዊ ተፅእኖዎች ናቸው፡፡ ያደግንበት ማሕበረሰብ አስተሳሰብ፣ በግላችን የገጠሙን የሕይወት ተሞክሮዎች፣ የኑሮ አለመረጋጋትና አልፎም ተስፋ የቆረጠ አኗኗርና የመሳሰሉት ይመስለኛል፡፡ እንዚህ ስሜታዊ የሆኑ አመለካከቶቻችን ከሚንጸባረቁባቸው ጉዳዮች አንዱ ደግሞ የፖለቲካ ደጋፊነትና ተቃዋሚነት ነው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ደጋፊነትና ተቃዋሚነት ስመጣ ከብዙ አገሮች እምብዛም የተለየ ነው ብዬ ባላምንም በውጭ በሚኖሩ (ዲያስፖራ) ኢትዮጵያውያንና ተማርን በሚሉ ዜጎች ያለው ምክነያታዊ ያልሆነው ደጋፊነት ወይም ተቃዋሚነት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖረው ብዙ ሕዝብ የከፋ ነው፡፡ ይህ ልዩነት በተለይ አሁን አሁን በአገር አመለካከትም ላይ በውጭ በሚኖሩትና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩት መካከል ክፍተት እየፈጠረ መጥቷል፡፡  በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ስሜታዊነት ከፖለትካ አመለካከት ብቻም ሳይሆን ፍጹም የሕሊና መታመንን በሚጠይቀው ሀይማኖታዊ ጉዳዮችም ላይ በአገሩ ከሚኖረው የከፋ ሳይሆን አልቀረም፡፡  በዚህም የተነሳ ብዙ ጊዜ የአገርና ሕዝብን ትክክለኛ ጥቅሞችንና ደህንነቶችን ሳይቀር ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ለራሳቸው ስሜታዊ ተቃዋሚነት ወይም ደጋፊነት መጠቀሚያ ሲያደርጓቸው ይታያል፡፡ ቀጥሎ ተማርን በሚሉ ብዙ ሰዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኛ ነን በሚሉ ሰዎችም እንዲሁ ተመሳሳይ ኃላፊነትን የዘነጋ አገርንና ሕዝብን ያላማከለ ስሜት ወለደ አልፎም ሴራዊ የሆኑ አካሂዶች ይስተዋላሉ፡፡ በተለይም የፖልቲካ ፓርት መሪዎችና ጋዜጠኞች ብዙ ሕዝብም ለማሳተፍ ከሚያስችላቸው ስሜታቸውን የማጋራት ዕድል ጋር በተያያዘ የሚያደርሱት ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡

ይሄው ተጽኗቸው በሚያመጣው ስጋት ታዲያ በስልጣን ላይ ያለ አካል የእንዚህን አካላት አመለካከትና አካሄድ የሚመለከተው በአትኩሮት ነው፡፡ ሥጋቱ ሲጨምርም እንዚህን አካላት እንቅስቃሴያቸውን ያስጠነቅቃል ሰበብ ፈጥሮም ያስራል ይቀጣል፡፡ ይህ የሁሉም አገራት ሂደት ነው፡፡ ሴሜታዊ እርምጃው ግን ስልጣን ላይ ያለው አካልም ጭምር ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እርምጃዎች ሌሎች በስሜት እየተነዱ አልፎ አልፎም በልዩ ሴራዊ በሆነ አካሄድ የሚያጠፉን የፖለቲካ መሪዎችንም ሆነ ጋዜጠኞችን  ኃላፊነት የሚሰማቸው ዜጎች ከማድረግ ይልቅ የቅጣትና የበቀለኝነት እርምጃ ሲወሰድ ይታያል፡፡ እንዲህ ያለው እርምጃ ደግሞ በስሜትና በልዩ ሴራ የተጠነሰሱ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ልዩ ግዝፈት እየሰጣቸው ተራ የሆኑ ሰዎችን ሳይቀር ወደ ትልቅ ታዋቂነት፣ ጥቃቅን አለመገባባቶች ወደ ትልቅ አገራዊና አህጉራዊ ብሎም አለም ዓቀፋዊ ጠቦች ያደርሳቸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችንና አንዳንደ የፖለቲካ አመለካከት የላቸውን ሰዎች አስሯል በሚል  በሰፊው በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሳይቀር ይወቀሳል፡፡ የታሰሩት ጋዜጠኞችም ሆኑ ፖለቲከኞች ግን ለእስር ያበቃቸውን ነገር በውል የሚያውቁት አሳሪዎቹና ታሳሪዎቹ ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ መንግስት በሕዝብና በአገር ደህንነት ላይ ችግር ፈጥረዋል ባይ ነው፡፡ ታሳሪዎቹ ደግሞ አሁን ያለው መንግስት የፕሬስ ነጻነትና ዲሞክራሲያዊ ፖለቲካን ስለማይቀበል በነጻ አስተሳሰብ አራማጆች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው ባዮች ናቸው፡፡ ችግሩ ግን ሁለቱም አካላት (አሳሪውም ታሳሪውም) ጋር ከስሜተኝነት የመጣ ድርጊቶች ይነበባሉ ባይ ነኝ፡፡ በመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ባለስልጣኖች በእልህና በቀጭነት መንፈስ የሚወስዱት እርምጃ ብዙ የችግሩ ግዝፈት ምክነያት እንደሆነም ይሰማኛል፡፡ ዜጎችን በአስተማሪነትና በአስተዋይነት ዘለቄታ ያለውን ኃላፊነት በመስጠት በስሜት ብቻ ተቃዋሚ የነበሩትን ለሕዝብና አገር ጠቀሜታ ያለውን የበኩላቸውን ድርሻ ከሚቃወሙት መንግስት ጎን ሳይቀር በመሰለፍ ሊያበረክቱ በቻሉ ነበር፡፡  በእኔ እምነት ብልህ መሪ ለሚቃወመው አካል ኃላፊነት ሰጥቶ ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ ተቃውሞን ወደ ደጋፊነት ሊዘውር የሚችል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እርግጥ ይህ የሚሆንበት ደረጃ አለው፡፡ በተቃዋሚነት ወንጀል ጭምር የሰሩ ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑና ነጻ ይሁኑ ማለት ፍትሀዊ አይደለምና፡፡ ገና ለገና ግን ይሄ ችግር ይፈጥርብኛል በሚል ስጋት የሚቃወመንን ስልጣንና ጉልበት ስላለን ብቻ ማሰርና ማስወገድ ስህተት ነው፡፡ ይልቁንም ሌላ ግዙፍ ጫጫታ መፍጠር ነው፡፡ ሌላ አገርንና ሕዝብንም የሚያውክ ግዙፍ አለመገባባት ሲብስም ወደ እርስበርስ ጦርነት የሚያመራ ነው፡፡

ወደ ታሰሩ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጉዳይ አትኩሮቴን ላድርግና፤ በእኔ እምነት መንግስት አሰራቸው የተባሉት ጋዜጠኞችም ሆኑ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደተባለው ልዩ ወንጀል እውንም ሰርተው ካልሆነ ለሌላ የበለጠ ራሱ መንግስት ሊጠቀምበት የሚችልበት ሚና ተሳታፊ ሊያደርጋቸው የሚችልበት እድሉ ሰፊ ነበር፡፡ ልዩ ወንጀልም ሠርተዋል ከተባለ የሠሩት ወንጀል ካለማወቅና፣ አንዳንዴም ከስሜተኝነት የተነሳ ከሆነ አሁንም ስሜተኝነታቸውን እንዲያስተውሉትና አስተማሪ በሆነ እርምት ሀላፊነትን በማሸከም ምህረት ቢያደርግ የመልካም አስተዳደር ልዩ መገለጫ እርምጃ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ሆኖም ከስሜተኝነትና ከአለማወቅ በዘለለ በልዩ ሴራ ወንጀል ለፈጸሙ አካላት ይህ ምህረት ተገቢ ነው ብዬ አላንም፡፡ ምክነያቱም በልዩ ሴራ የተሰማራ አካል መቼም ቢሆን የተለከፈበትን ሴራውን ለመቀጠል ይችላልና ነው፡፡ ከነዚህ ልዩ ሴራ ከሚያራምዱት ውጭ ግን በአለማወቅና በስሜተኝነት የመጡ ጥፋቶችን ይቅር ማለት ለአጥፊዎቹ አስተማሪ በመሆን ለሌላ በቀል አዘል እልኸኝነት እንዳይነሳሱ ከማድረጉም በላይ ፍትሀዊነትንም ለሕዝብ በማሳየት ሌላ ጊዜ አጥፊዎች ሲታሰሩና ሲቀጡ በጭፍኑ ከሕዝብና ከሌሎች ያገባናል ከሚሉ ሰዎች ወቀሳን ጫጫታን ለማስወገድ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ፡፡ ካልሆነ ግን ይቅርታ የማይገባውን የተረጋገጠውንም ወንጀለኛ መንግስት ሲቀጣ ይህ የሆነው ወንጀለኛ ሆኖ ሳይሆን መንግስት ኢ-ፍትሃዊ ስለሆነ ነው የሚሉ ጫጫታ ፈጣሪዎችን ማብዛት ይመስለኛል፡፡

በእንዲህ ያለ ግርግር ወንጀለኞች ከሌሎች አካላት እንደ ልዩ የፍትህ ወይም የነጻነት ታጋይ ተቆጥረው ሊሸለሙ ሊወደሱ ይችላሉ፡፡ ሸላሚዎቹ ደግሞ ወይ በውል ውስጡን የማይረዱ ስሜትን ብቻ ተከትለው የሚበይኑ ናቸው ወይ ደግሞ ውስጡን በውል የሚያውቁ ግን የወንጀሉ ሁነኛ ደጋፊዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ ሂደት ደግሞ የአገርንና ሕዝብን የጠራ ደህንነት ሊጋፋ ይችላል፡፡ ታሳሪዎች ወንጀለኛ ባይሆኑምና እውንም ለሕዝብና ፍትህ በመታገላቸው ታስረው እንኳን ቢሆን እስር ቤት እያሉ መሸለም ጥሩ አካሄድ እንዳልሆነ አስባለሁ፡፡ እንዲህ ያለው ሽልማት ከበጎ ጎኑ ጥፋቱ የበለጠ ይሆናልና፡፡ ሂደቶችንም በእልኸኝነትና ጥላቻ ከፍትሀዊ አመለካከት አስወጥቶ አሳሪዎችን ለበለጠ መጨከን ታሳሪዎችን ለበለጠ እንግልት ሊዳርግ ይችላልና፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ግን አሳሪንም ታሳሪንም በተግሳጽም ሆነ በማግባባት አሳሪዎች ፍትሀዊ አመለካከታቸው የሚዳብርበትን ታሳሪዎችም ፍትሀዊ በሆነ መልክ ከእስር የሚፈቱበትን ተጽዕኖ መፍጠር ታላቅነት ነው፡፡ በተመሳሳይ በውጭ ኃይሎች የሚደረግ ግፊትና ውግዘት አዘል መግለጫዎችም ብዙ መዘዞች አሏቸው፡፡ በወዳጀነት ከሚሆን ተግሳጽና በማገባባት የሚመጡ መፍትሔዎች ግን ዘላቂም አስተማማኝም ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ብዙ አገራትም ይሁኑ ሌሎች አለም አቀፍ ይመለከተናል የሚሉ አካሎች ደግሞ በአብዛኛው ጉልበተኝነታቸውን የሚያሳዩባቸውን የውግዘትና የማስፈራራት ቃላቶችን አሳሪ ወይም እነሱ አጥፊ ብለው በሚያቧቸው መወርወር በተቃራኒው ታሳሪዎችን ወይም እነሱ መበታቸው ነው ብለው ለሚያሰቧቸው ውዳሴንና አዞህ ባይ ቃላቶችን ባዶ ተሰፋ ይሰጣሉ

ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ጋር በተያያዘ ብዙ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ወሕኒ እንዲገቡ መደረጉን ሁላችንም የምናስታውሰው ነው፡፡ ብዙዎቻችን እንደምናስታውሰው በዚህ ወቅት ከወትሮው ለየት ያለና ኢትዮጵያዊነትንና የሕዝቦቿን ባህላዊ እሴት የሚያንጸባርቅ መንግስትንና ታሳሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ለማደራደርና በመጨረሻም የታሰሩ ወገኖችን ከእስር እንዲፈቱ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያበረከተ የሽምግልና ቡድን ታይቶ ነበር፡፡ ይህ ቡድን በቀጣይነትም መሰል ችግሮቻችንን በማስወገድ ሁሉም ወገን በመግባባትና ኃላፊነት በተሞላው ሁኔታ ለአገርና ለሕዝብ ጠቃሚ በሚሆኑ ጉዳዮች ለመሥራት ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፡፡ የዚህ ቡድን ዋነኛው ተዋናይና የትልልቅ ራዕዮች አመንጪ የነበሩትም ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ ቃል ገብተውልን የነበረውም እንደዛው ነበር፡፡ ሆኖም ይህ በብዙዎቻችን በጥሩ እይታ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው አገር በቀል የሽምግልና ቡድን ብዙም በዘላቂነት ልናየው አልቻልንም፡፡ ምክነያቶቹ ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከምክነያቶቹ አንዱ ይሆናል ብዬ የማስበው ግን ቡድኑን ከመንግስት ጋር የሚወግን፣ ለግል ጥቅም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች አድርጎ ማሰብ ነው፡፡ እንዲህ ያለው አስተሳሰብ ደግሞ በእውንም በቅንነትና በበጎ አሳቢነት ለአገርና ለሕዝብ በአለን ተጽኖ ፈጣሪነታችን እናገልግል ብው የተነሱ ግለሰቦችን ከማሳዘኑና ጥረታቸውንም ዋጋ ቢስ እንደሆነ ከማሳሰቡም በላይ እናቀራርባቸዋለን የሚሉትን ተቃራኒ ቡድኖችን ለማግባባት ትልቅ ዕንቅፋት ነው፡፡

በእኔ አስተሳሰብ የእነፕሮፌሰር ኤፍሬም አገርኛው የሽምግልና ቡድን ከየትኛውም ዲፕሎማሳዊና ሌላ ተጽዕኖ ፈጣሪ አካል የተሻለ ለዘለቄታውም ተቃራኒ የነበሩ ቡድኖች ወደ አንድ መጥተው በወንድማማችና እህትማማች መንፈስ የሀሳብ ልዩነታቸውን የበለጠ የአገርና የሕዝብ ጉልበት እንዲሆን ለማድረግ ትልቅ አቅም ሊኖረው የሚችል ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደነበር እረዳለሁ፡፡ እኔ ፕሮፌሰር ኤፍፌምንና አጋሮቻቸውን ተረድቻቸው የነበረው ፍጹም በሆነ የእኔነት መንፈስ ነው፡፡ በእርግጥም የፕሮፌሰሩ ፍልስፍና እኔ ከማስበው ጋር በጣም የተጣጣመ ነበር፡፡ በወቅቱ ለሕዝብ ይፋ እንዳደረጉት እሳቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ ሌሎች ጣልቃ እንዲገቡ አይፈልጉም፡፡ ከብዙዎቻችን በተሻለ እናደራድር በሚል የሚያመጡትን መዘዝ ጠንቅቀው ያውቁታልና፡፡  በእርግጥም ከእኛ በላይ ለእኛ ሊያስብልን የሚችል የለም፡፡ እኛ ደግሞ ከሌሎች የአለም አገራት በተለየ ሁኔታ ብዙ ጊዜ በዲፕሎማሳዊ ድርድር ሰበብ የተካድንና ለልዩ ሴረኞች ሰለባ የሆንን ሕዝብ ነን፡፡ በተለይ አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባውያኑ በምንም መልኩ አመኔታ ሊሰጣቸው የሚችሉ አደራዳሪዎች አይደሉም፡፡ ለሌላው ሕዝብ ቅንጣት ደንታ የሌላቸው በዲሞክራሲና ፍትሕ ሥም የአገራትን ሕዝቦች እርስ በእርስ በማፋጀት ኑሮአቸውን በሰው ልጆች ደም የሚገነቡ ናቸውና፡፡ እናስተውል ዛሬ በአረቡ ምድር እያደረጉ ያሉትን፡፡ በተለይም ደግሞ የሰሜን አፍሪካ አገራትን ልብ እንበል፡፡ ሊቢያ ዛሬ ካላት ሠላምና ፍትህ ምዕራባዊያኑ አምባ ገነን ባሏቸው ጋዳፊ ዘመን ፍትሕና ሰላም ነበራት፡፡ ግብፅም፣ ቱኒዚያም እንደዚያው፡፡ ሳዳም ሁሴን ለኢራቅ ዛሬ ካሉት በብዙ እጥፍ በተሻለ ጥሩ መሪ እንደነበሩ እናስተውል፡፡  የሶሪያው አልአሳድ ለሶርያውያን አምባገነን ሆነው አይደለም እስካሁንም አገራቸው ጦርነት ውስጥ ያለችው፡፡ ሌላ ልዩ ማስተዋል በአሁኑ ወቅት የአልአሳድ መንግስት ጉልበት እያገኘና ተቃዋሚዎቹንም እያሸነፈ ለሕዝብም መረጋጋትና ሠላም እያመጣበት ባለበት ሁኔታ የአሜሪካው መሪ ኦባማ ተቃዋሚዎችን ለማጠናከር የ500ሚሊዮን ዶላር ፍቃድ ኮነግረሳቸውን ጠይቀዋል፡፡ በጣም አስገራሚው ነገር ደግሞ አሜሪካ ራሷ አሸባሪ ባለችውና ዛሬ የኢራቅ ራስምታት የሆነውን አይሲስን ቡድን የአላሳድ መንግስት በሶሪያና ኢራቅ ድንበር በአየር ማጥቃቱን ተከትሎ ነው ኦባማ ኮነግረንሳቸውን ተቃዋሚዎችን ለማጠናከር በሚል የገንዘብ ድጋፍ የጠየቁት፡፡ ጉዳዩ ሶርያ ውስጥ ሰላምና ዲሞክራሲ ለማስፈን ሳይሆን በዘላቂ ብጥብጥ ሕዝብን ለእልቂት መዳረግ ነው፡፡ ምዕራባውያኑ የሰው ደም የሚገብሩለት ሰይጣን ግብሩን ቢያቆሙበት ሊያጠፋን ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ አገራቱን የሚመሩት የልዩ ሚስጢራዊ ማሕበረሰብ እምነት ነው፡፡

እንግዲህ እንዲህ ያሉትን ሴረኞች እያመንን ነው ዲፖሎማሲ ዲሞክራሲ ምናምን እያልን ለዘመናት የተጃጃልነው፡፡ የእኛዎቹና አገሪኛዎቹ አደራዳሪዎች ግን ቢያንስ የሕሊና ክስ ስለሚገጠማቸው በአገርና ሕዝብ ላይ አንዳች ሴራ ለመወጠን እድላቸው የጠበበ ነው፡፡ በእርግጥም በወቅቱ በአገርበቀሉ የሽምግልና ቡድን የነበሩት ግለሰቦች ስብስብ ጥሩ ሥምና ስብዕና የነበራቸው እንደነበር እናስታውሳልን፡፡ የቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ከአርባ ዓመት በላይ ኑሯቸው በአሜሪካ ቢሆንም ብዙዎች ኢትዮጵያዊነትን ክደው አሜሪካዊ ለመሆን አለ የተባለ ድንጋይ ሲፈነቅሉ እሳቸው ለዚህ ሁሉ ዘመን ዜግነታቸውን ጠብቀው ከዚያም በላይ በባዕድ አገር ማንነታቸውን በጉልህ ለማሳየት በኢትዮጵያዊ የባህል ልብሳቸው ደምቀው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊነታቸውን ከምንም በላይ የሚኮሩበት ዜጋ ናቸው፡፡ ሌሎቹም የቡድኑ ስብስቦች እንደዚያው፡፡     

ብዙ ጊዜ ሰዎች ስለታሰሩ ብቻ እንደ ልዩ የነጻነት ታጋይ ተቆጥረው ሊወደሱ አይገባቸውም፡፡ አሳሪዎችም ተራ በሆነ በግል ቂመኝነት ወይም ሕዝብንና አገርን ታሳቢ ባላደረገ መሠሪነት ዜጎችን ማሰር የለባቸውም፡፡ ብዙ እውነትም መታሰር የነበረባቸውና ፍትሀዊ ፍርድ ሊበየንባቸው የሚገባ ታሳሪዎች በግርግር ሲወደሱና እንደ ነጻነት አርበኛ ተደርገው ሲሸለሙ ጭምር እናያለን፡፡ አሳሪዎችም ብዙ ጊዜ ፍትሃዊ ባልሆነ ሁኔታ ዜጎችን እንደሚያስሩ እናያለን፡፡ ከዚህም በላይ አሳሪዎች እንደመሪ ጥፋት እንኳን ቢኖር በትዕግስትና በማስተዋል ጥፋተኞችን ወደ መልካም ስነምግባር በሚላበሱበት ሁኔታ ለማረም ብዙ እድል እያላቸው በተራ ስሜተኝነትና አልፎም በቂመኝነት ታሳሪዎችን በቀለኛ በሚሆኑበት ሁኔታ ሲያስሩና ሲቀጡ እናያለን፡፡ ይህም እንደ ልዩ ባሕል በትውልድ መካከል እየቀጠለ ለዘመናት የአንድ አገር ልጆች ለዘመናት በባላንጣነት እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡  የገዛ ወንድሙን ለመበቀል ከጠላቶቹ ሳይቀር ይወግናል፡፡  ዛሬ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ባለአንጣ ከሆኑ ቡድኖች  በመተባበር በኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ላይ እያሴሩ ናቸው የሚባለው በስልጣን ላይ ባሉት መሪዎችና ተቃዋሚ በሚባሉት መካከል ያለውን አለመግባባት በማርገብ ፋንታ ወደ ከረረ የመበቃቀል እልኸኝነት መንፈስ እንዲያመሩ ባደረጉ ስሜታዊ እርምጃዎች ነው እንጂ ከመጀመሪያው አሁን ያሉ ባለአንጣነትና በቀለኝነት በሁለቱም ወገን ኖሮ አይመስለኝም፡፡   

መንግስት እንደመንግስት ቻይነቱ ይብዛ ኃላፊነትም ስላለበት አጥፊዎችን (ከልዩ ወንጀለኞች በስተቀር) ወደ ጥሩ እርምት በማምጣት መልካም ዜጎች እንዲሆኑ ሆደ ሰፊ መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡ አጥፊዎችም ጥፋታቸውን ማመን መቻል አለባቸው፡፡ ጥፋታቸውን ማመን እስካልቻሉ ድረስ ለወደፊትም አይታረሙምና፡፡ ዛሬ ብዙዎች እንደሚያናፍሱት ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይሁን ነጸ አስተሳሰብ በሚል በሚጽፉ የመንግስትም ሆን የግል ጋዜጦችና ሌሎች የመገናኛ ብዙሀን ያን ያህል ትኩረት ሊሰጥ አይፈልግም፡፡ ምክነያቱ ደግሞ ብዙ ጊዜ ተዋሽቷል ብዙ ጊዜም ተክዷል፡፡ በቃ በሠላም መኖርንና ብልፅግናን ብቻ ይፈልጋል፡፡ ዲሞክራሲ ምናምን እየተባለ ራሳቸው ፍትህና ዲሞክራሲ ባልገባቸው ስሜተኞችና አልፎም ሴረኞች መወናበድ አይፈልግም፡፡ ዲሞክራሲም ከሆነ የአሜሪካና የአውሮፓ የተባለው አይነት በአፍንጫችን ይውጣ፡፡ ዜጎቿን እስከዛሬም በቀለም ለይታ ፍትሕን በዜጎች መካከል ያላሟላች አሜሪካ በምን መስፈርት ለእኛ እንደ ምሳሌ ትጠቀሳለች፡፡ አለማስተዋላችን እንጂ ይቺ አገር (ኢትየጵያ) ብዙ ለሌሎች ሳይቀር ምሳሌ የሚሆን ታሪካውና ባህላዊ ፍትሀዊ አስተሳሰቦች ያሏት አገር ናት፡፡ አስተውሉ ይህች አገር በኋላ በመጣንው ትውልዶች የተበከለ ሥምና ታሪክ እንዲኖራት ሆነ እንጂ ከመሠረቱ እጅግ አስደናቂ በሆኑ የጥበብ ፈላስፎች ትመራ እንደነበር እናያለን፡፡ በዚች አገር ሀይማኖት፣ ቀለም፣ ዘር ሳይሆኑ ስብዕና ብቻ ፍትህን የሚያሰጥባት አገር ነበረች፡፡ የነብዩ መሀመድ ተከታዮች ወደ ክርስቲያኑ መሪ ለመጠለል ሲመጡ ሀይማኖታቸው ሌላ መሆኑ ሰብዓዊ የመኖር መብታቸውን አልከለከለውም፡፡ ይልቁንም በእንግድነት በክብር አቀባበል ተደረገላቸው እንጂ፡፡ ዛሬ ግን ለብዙዎቻችን ስብዕና ሳይሆን በሀይማኖት፣በዘር፣ በቀዬ፣ ወዘተ መመሳሰላችን ነው ትልቅ ድርሻ ያለው፡፡ በዙ ሙስሊም ዜጎቻችን ከአገራቸው ይልቅ የአረቡ አለምን የሚያስቀድሙ ናቸው፡፡ ከአውሮፓ በመጡ እምነቶች ጥላ ሥር ያሉም ብዙዎች  ከአገራቸው ይልቅ የምዕራቡ አለም ናፋቂዎች ናቸው፡፡  የግብፅና ኢትዮጵያ እግር ኳስ ሲካሄድ ለግብፅ ከስሜት የደገፉ ዜጎቻችን በአባይ ጉዳይ ግብጽና ኢትዮጵያ ቢጣሉ የግብጽ ባንዳ ላለመኆናቸው ዋስትና የለንም፡፡ እንኳንስ ይህን ያህል አረብን ናፋቂነት ስሜቱ እያለ ቀድሞም ብዙም ፈረንጅ ናፋቂ ባልሆኑት ዜጎቻችን ዘመን በጥቅም ታውረው ለጣሊያን ባንዳ የነበሩ ዜጎቻችን ቁጥር ቀላል አልነበረም፡፡ ከራሱ አገር ይልቅ ሌሎችን የሚናፍቅ ትውልድ ደግሞ ይህ የእኛው ዘመን ትውልድ ነው፡፡ ይህ ትውልድ በራሱን ማንነት የሚያፍር የባሪያ አመለካከት ስላለው የራሱ የሆኑ ታሪካዊና ባህላዊ በጎ እሴቶቹ አይታዩትም፡፡ ሴቶችን እንደ ዕቃ ይቆጥሩ የነበሩት የምዕራባውያንና የአረቡ (ዛሬም ያው ነው) አገራት ዛሬ ለእኛ ለሴቶች ልዩ ክብር ከጥንት ጀምሮ ይሰጥ የነበረው ባህል ባለቤቶች ስለሴቶች መብት ሊያስተምሩን ይሞክራሉ፡፡ እኛም የራሳችንን ትተን ልክ አዲስ እንደነገሩን እነሱን ሰማን፡፡ በኢትዮጵያ ብዙ ሕዝቦች ባህል ሴት ንጉስም፣ ጀግናም ትወልዳለች እየተባለ ልዩ ክብር ይሰጣት እንደነበር ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ ክፉኛ በተጣሉ ሁለት የሚደባደቡ ሰዎች መካከል ሴት ለግልግል ብትገባ በመሀል ስለገባችው ሴት የቱንም ያህል የከረረ ጥል ቢሆን ጠበኞቹ ሰይፋቸውን ወደሰገባው የሚመልሱበት ማሕበረሰብ እንደነበረን ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡  እነዚህ ሁሉ እውነቶች ግን በኋላ በመጣው ትውልድ ነቀዘው የሌላ ናፋቂዎች ሆንን፡፡

አሁንም እላለሁ እኛ አገርንና ሕዝብን ካስቀደምን ጠባችን ቢሆን ለአገሬና ሕዝቤ በዚህ መልኩ እንጂ ይሄኛው አይጠቅምም የሚል የሐሳብ ልዩነት ካልሆነ የበቀለኝነት አይሆንም፡፡ ጠባችን ግን እኔ ልብላ እኔ ልብላ ከሆነ አገርና ሕዝብ እዚህ ጋር ወደጎን ተገፍትረዋልና እርግማኑ በራሱ መጥፊያችን ይሆናል፡፡  አገርንና ሕዝብን ካልን ደግሞ የራሳችንን ገመና ለሌሎች አውጥተን አንሰጥም፡፡ ከጠላት ጋርም አንወግንም፡፡ ሞት ቢኖር ወንድሜ ይግደለኝ እንጂ አገሬን አልከዳምና፡፡ ለአንድ አገርና ዜጎቿ ከሆነ ጭንቀታችን የሁላችንንም ልብ የሚረዱት የእኛው ወገንና አካል የሆኑ አገር ወዳድ ሽማግሌዎቻችን እንዲዳኙን ፍቃደኞች ነን፡፡ ተግሳጻቸውንም ለመቀበል ለባችን በቂም አይመረዝም፡፡ አእምሮአችን በአወቀ ቁጥር በማስተዋል ፈንታ በስሜት የሚነዳም ከሆነ እወቀታችን መካን ነው፡፡ ጥበባኛና ለአገርና ሕዝብ አሳቢ ከመሆን ፈንታ በቀለኛ ከሆንም ሰይጣንን እንወክላለን፡፡ የአገሬ ልጆች ወደ ራሳችን እንመለስ፡፡ የአገሬ ሽማግሌዎች በተኳረፉ ልጆቻችሁ መሀከል ቁም፡፡ አንተም ተው አንም ተው በሉ! ባዕድ በመካከላችን አይግባ! ጓዳችንን ለጠላት አናሳይ! ስሜታችንን  እንግታ አካሂዳችን ሁሉ በማስተዋል ይሁን! እኛ እርስ በእርስ ጠላቶች አይደለንም! ካልተግባባን ሽማግሌርዎቻችን ይዳኙን!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ አገራችንን ይባርክ! አሜን!

የታላቋ ቀን ልጅ ሰኔ 30 2006ዓ.ም

         


    

Tuesday, May 27, 2014

አጠፉም አለሙም የታላቁ ምኒሊክ ታሪክ የኦሮሞም ሕዝብ ታርክ ጭምር ነው



በሰከነ አእምሮ ማሰብ ካልቻልን ሁሌም አደጋ ላይ ነን፡፡ ለሰከነ አእምሮ ደግሞ ሁል ጊዜ ስለሕሊና መኖርን ይጠይቃል፡፡ ሕሊናውን የሚክድ ግን ለእውነት ሳይሆን በውሸት፣ በአድርባይነት ወይም በሴረኝነት አልፎም በአረመኔነት ይኖራል፡፡ ሰው ባለወቀው ነገር ቢሳሳት ሕሊናው ነጻ እስከሆነ ድረስ ላጠፋው ጥፋት ካሳም ይሁን ይቅርታ ለማድረግ አልጎደፈም፡፡ ሳያውቅ በማትፋቱ ቢያዝንም አንዴ ካወቀ በኋላ ጥፋቱን ባለመድገም ጥፋቱን ይበቀለዋል፡፡ ለሕሊናውም እርካታና ካሳ ይሆንለታል፡፡ እውነትን አውቀው ግን የካዷት ሕሊናቸው አንዴ ስለጎደፈ በጎ ነገርን ለማሰብ አእምሮአቸው አይቻለውም፡፡ ሁሌም ክፉ የሆኑ መንገዶችን ሲገነባ ይኖራል፡፡ ውለታ፣ ሕዝብ፣ አገር፣ የመሳሰሉት ሁሉ ሕሊናቸው በበጎ ላልታነጸ ሰዎች ምናቸውም አይደለም፡፡ ለግል ለሚሉት ጥቅማቸው መሳካት ሲሉ በሚሊዮን ሕዝብ ቢያልቅ አገር ቢፈርስ ታሪክና ማህበረሰብ ደብዛው ቢጠፋ ጉዳያቸው አይደለም፡፡ ሰዎች በበጎ ሕሊና የሠሩት ታሪክ ለእነዚህ ሕሊናቸው ለመረቀዙት አደገኛ ወጥመድ ስለሚሆንባቸው የበጎ አሳቢዎቹን ታሪክ ማርከስና ማውደም ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ጥሩ ጉልበት የሚሆናቸው የሰዎች እውነትን መዘንጋትና በሌሎች ስብከት ስሜታዊ መሆን ነው፡፡  መሠሪዎች የሰዎችን ልጆች ለመሠሪ ዓላማቸው መሣካት የሞት ዕራት የሚጠቀሙበት ዋነኛው አጋጣሚ የራሳቸው የሰዎች ልጆች ስሜተኝነትና እውነታን ለማየት አለመቻል ነው፡፡

ሰሞኑን አኖሌ በተባለ ቦታ ከመቶ ዓመት በፊት በታላቁ ምኒሊክ አገርን አንድ የማድረግ ሂደት በነበረ ጦርነት የጡትና እጅ መቁረጥ ግፍ በምኒሊክ ዘመቻ ተፈጽሟል በሚል አንደ መታሰቢያ የተባለ ሐውልት በመቆሙ ምክነያት ብዙዎች እየተነጋገሩበት ይገኛል፡፡ የተባለው ግፍ በዚያ ዘመን ሊሆኑ ከሚችሉ ክስተቶች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ከመገመት ያለፈ ግን የተጨበጠ መረጃ ሊገኝለት የቻለ አይመስልም፡፡ ሐውልቱም ሲቆም አፈታሪክን መሠረት አድርጎ እንጂ ተጨባጭ መረጃን መሠረት አድርጎ አይደለም፡፡ ሐውልቱን ያቆሙት መታሰቢያና አስተማሪ ቢሉትም ብዙዎች በተቃራኒው በሕዝብ መካከል ጥላቻን ለመፈጠር የቆመ ሐውልት ነው ሲሉ ይተቹታል፡፡ ይበልጠውን ደግሞ ድርጊቱ ተፈጸመ ከተባለ ከመቶ ዓመት በኋላና የተረጋገጠም መረጃ ባልተገኘበት ሁኔታ መሆኑ በእርግጥም ዓላማው ከበጎ ሕሊና የመጣ እንዳልሆነና ይህን ትውልድ ለመመረዝ የታሰበ እንደሆነ ተፈርጇል፡፡ እኔም ይህን ሐውልት የማየው የጥላቻ ምልክት እንጂ አስተማሪና መታሰቢያ እንደሆነ አይደለም፡፡

በአንድ የራሴን አስተያየት ባስተላለፍኩበት ጽሑፌ ኦሮሞ ነኝ የሚለው ብዙው ሕዝብ በታላቁ ኢትዮጵያዊ ሚንሊክ ላይ ያለው ጥላቻ ከምን የመጣ ነው? ሐውልቱን ጨምሮ ብዙ ነጥቦችን አንስቼ ነበር፡፡ በዚህ ጽሑፍ ኦሮሞ ነኝ የሚለው ሕዝብ (ይቅርታ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ በብዙዎቻችን የአስተሳሰብ እንጂ የዘር ጉዳይ እንዳለሆን ላሳስብ እፈልጋለሁ) በምኒሊክ ታሪክ የነበረውን ድርሻ ጠቆም ማድረጌን እያስታወስኩ ለዛሬ በተሸለ  ላቀርበው ወደድኩ፡፡

ታላቁ ምኒሊክ ጥፋትም ይሁን ልማት ሠሩ ያለ ኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ አልሠሩትም፡፡ በአገር መገንባቱም ይሁን አገርን ከጠላት ወረራ ለመከላከል በተደረጉ ጦርነቶችም ሆኑ ሌሎች የታላቁ ምኒሊክ ታሪኮች ኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ በላይ ድርሻ አለኝ የሚል ሕዝብ እንዳለ አላውቀም፡፡ የታላቁ ሰው የታሪክ ዘመን ደግሞ ዛሬ ከየትኛው አገሪቱ ካለፈችበት ዘመናት ሁሉ ትውልድና ሕዝብን የሚያኮራ ተግባራት የተሠሩበት ዘመን ለመሆኑ ልንክደው የምንችለው አይደለም፡፡  ይህ ታሪክ ግን እውነትን ለማይወዱ ሕሊናቸውን ለካዱ የግል ጥማቸውን ለማርካት ብቻ ለሚኖሩ ታላቅ ጋሬጣ ስለሆነባቸው  ይህን ለዜጎች ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝብ ሁሉ አልፎም የሌሎች የግፍ አገዛዝ በተጫናቸው የአለም ሕዝብ ሁሉ እንደ ተምሳሌት የሚታየውን ታሪክ ማራከስ ከተቻለ ማጥፋት ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው፡፡

ምኒሊክ አማራ ከተባለው ሕዝብ እንደሆኑ ቢታመንም አማራ የተባለው ሕዝብ በምኒሊክ ታሪክ የነበረው ድርሻ ከኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ ጋር ሊወዳደር የሚችል አይመስለኝም፡፡ አኖሌም በሉት፣ ችለንቆ ወይም ወላየታ፣ ወይም ለአላም ሳይቀር አድስ ምዕራፍን በማሳየት የሚታወቀው አድዋ በምኒሊክ በኩለ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ በበላይነት የተሳተፈባቸው ጦርነቶች እንደሆኑ እረዳለሁ፡፡ በእርግጥም የምኒሊክ የጦር መሪዎች በብዛት ኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ እንደሆኑ ታሪክም መዝግቦት የሚገን እውነት ነው፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በጦርነቶቹ የነበሩ ድሎችም ሆኑ ጥፋቶች ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ በበላይነት የተሳተፈባቸው ናቸው፡፡ ኦሮሞ በተባለው አርሲ ሕዝብ አኖሌ ላይ ዛሬ ሐውልት የቆመለት ግፍ ደረሰ ከተባለ ደግሞ ተጠያቂው በበላይነት ኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ የነበረው የምኒሊክ ሠራዊት ነው፡፡ ያ ማለት ደግሞ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ ሌላ ቦታ ያለ ኦሮሞ በተባለ ወንደሙ ላይ የፈጸመው ግፍ ነው፡፡ ሆኖም ከሆነ የገደለው ባሌ የሞተው ወንድሜ ብለን ከማዘን በቀር የበቀል ሐውልት ልናቆምለት ባልተገባን ነበር፡፡

ምኒሊክ ጦርነቶችን ሁሉ ተገደው እንጂ ወደው በማን አለብኝነት የደሩባቸው ጊዜ አልነበረም፡፡ አገርን አንድ በማድረግ ሒደት ብዙዎችን ያለጦርነት ወደ አንድነት ያመጡ ሲሆን አልፎ አልፎ በነበሩ የአካባቢ መሪዎች ለሠላም እምቢ ማለት ወደ ጦርነት አምርቷቸዋል፡፡ አኖሌ፣ ጨለንቆና ወላይታ ጉልተው በታሪክ የተጠቀሱት ናቸው፡፡ ምኒሊክ በጦርነቶቹ ሁሉ ድል አድራጊ ቢሆኑም በጦርነቶቹ በነበሩ ጥፋቶች ይልቁንም የሰዎች ሕወት መጥፋት እጅግ ያዝኑ እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡ በጦርነት ምክነያት ሕዝቡ በመጎዳቱ ካዘኑባቸው ጦርነቶች አንዱ ደግሞ የአርሲው አኖሌ ጦርነት እንደነበር በታሪክ ተጠቅሷል፡፡ በወቅቱ በነበሩ ልማዶች አሸንፎ የገባ ጦር (ወታደር) የተሸነፋን ሕዝቡና ንብረቱን መማረክ እና ለራሱ እንደሎሌ ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ይህን ግን በአርሲ ሕዝብ ላይ ወታደራቸው እንዳያደርገው እንዲህ ሲሉ ነበር ያስጠነቀቁት "ወንድምህ የአርሲ ሕዝብ በአላወቀው ነገር በዚህ ጦርነት እጅጉን ተጎዳ አሁን ግን ወንድምህን የአርሲን ሕዝብ እንደሎሌህ ልታደርገው አልተፈቀደልህም" ነበር ያሉት፡፡  

ዛሬ እየተነሳ ያለው ሐርካ ሙራ እና ሐርማ ሙራ እንደ አንድ የጦርነት ክፉ ውጤት ተከስቶ ሊሆን ይችላል፡፡ ከሆነም ደግሞ ከምኒሊክ እውቅና ውጭ በአንዳንድ ወታደሮች የተደረገ ግፍ እንጂ በምኒሊክ ትዕዛዝ እንዳልሆነ እረዳለሁ፡፡ ምኒሊክ በባሕሪያቸው እንኳንስ የሴትን ልጅ ጡት መቁረጥ ቀርቶ በየትኛው መልኩ ሰው እንዲጎዳ የሚፈልጉ ሰው አይደሉም፡፡ ጦርነቶቻቸውም የዓላማ እንጂ የትኛውንም ሕዝብ ይሁን ግለሰብ ለመጉዳት ታስቦ አልነበረም፡፡ ከውጊያ ድል በኋላም በተዋጓቸው ላይ የበቀል ሳይሆን የፍቀር አቀባበል ነበር ያደርጉላቸው የነበረው፡፡ ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ምኒሊክ የጀግና  ትክክለኛ ባሕሪ ያላቸው ናቸው፡፡ ጀግና የዓላማ እንጂ የግል ጠላት የለውም፡፡ በአኖሌም ለሕዝቡ ያደረጉት ይህንኑ ነው፡፡ ጀግና በጀግንነት እንደ ጠላት የተዋጋውን ያደንቃል፣ ያከብራልም፡፡ ድል ቢያደርገው እንኳን ክብሩን አይነፍገውም፡፡ ድል ሲያደርግ ስለ አላማው መሳካት ይደሰታል እንጂ ስለጠላት ሞት ደስ አይለውም፡፡ እንዲህ ያለ ጀግና ደግሞ በጦርነት ድልን እንጂ ሽንፈትን የማየት ዕድሉ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ይህ የምኒሊክ ልዩ መገለጫ ነበር፡፡

እንግዲህ ምኒሊክ እንዲህ ባለ የጀግንነት ባሕሪያቸው ለባሕሪያቸውና ለዓላማቸው ከተስማሟቸው ጀግኖች ሠራዊታቸው ጋር በዘመናቸው ያተቀዳጇቸውን ሁሉ ድሎች ለታሪክ አስመዝግበዋል፡፡ ምኒሊክ በስኬታማነታቸው አንድ ሰው በእድሜው ሊሰራው ከሚችለው በላይ እንደሆነ አረዳለሁ፡፡ ማንም አይደለም በኢትዮጵያ በዓለም ላይ እንኳን በአለፉት 500ና ከዚይም በሚበልጥ ዘመናት እንደምኒሊክ ውጤታማ የሆነ መሪ አለ ብዬ አላምንም፡፡ ካለ የታሪክ ምሁራን አከሌ የሚባል የዚህ አገር መሪ ቢሉ በአስመዘገቧቸው ውጤቶች ልናወዳደራቸው እንችላለን፡፡ ምኒሊክ የደሀ አገር መሪ ባይሆኑ ኖሮ በተባበሩት መንግስታት ሳይቀር መታሰቢያ የሚቆምላቸው ሰው ናቸው፡፡ ተምሳሌትነታቸው ለሕዝብ ሁሉ ነበርና፡፡ በተለይም የቀኝ የቀኝ ገዥዎችን አይነኬነትና አይበገሬተን ባመከነው ድላቸው ብቻ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለአለም ምሳሌ የሚሆኑ ታላቅ ሰው ናቸው፡፡ ይህ ሁሉ ታሪክና ክብር ደግሞ ኦሮሞ በተባለው ሕዝብ የበላይነት የተከናወነ ነው፡፡ እኔ ጎደሬና ጎጃሜ ምኒሊክ ዘመን ጉልህ ድርሻ ነበራቸው የሚል ታሪክ አላውቅም፡፡ አማራ የተባለው ሕዝብ ድርሻ በምኒሊክ ታሪክ ትልቅ ነበር ከተባለ ደግሞ በየትኛውም መሥፈርት ኦሮሞ የተባለውን ያህል ድርሻ የለውም፡፡

ችግሩ የሚጀምረውና ዛሬም ያለው ብዙው ትውልድ የታላቁን ሰው ታሪክ ሊያንኳስ የሚሞክረው የምኒሊክ ታሪክ በአብዛኛው የሸዋ ሕዝብ የበላይነት መሆኑ ነው፡፡ የምኒሊክ አጋር የነበረ ኦሮሞም በሉት አማራ በብዛት ከሸዋ መሆኑ ዛሬ ስልጣን ላይ ላሉት ወለጋም በሉት አርሲ፣ ጎጃሜም በሉት ጎንደሬ እንዲሁም ትግሬ እንደራስ ታሪክ ሊታይ አልቻለም፡፡ ትግሬው አጼ ዮሐንስን እንጂ ምኒሊክን ታላቅ ማድረግ አይፈልግም፡፡ ሁለቱም ለእኔ የኢትዮጵያ መሪዎች ናቸው አከብራቸዋለሁ፡፡ ምኒሊክን ግን እኔ በታሪክ ከማውቃቸው ሁሉ የላቀ አደርጋለሁ፡፡ ጎጃሜና ጎንደሬውም ለሸዋ ነጋሲያን የእኔ ለማለት ቅር ይለዋል፣ ወለጋና አርሲው የአማራ ነጉስ በማለት እራሱን ከታሪክ ባለቤትነት ለማራቅ ጎራ ይፈጥራል፡፡ ሸዋ ዛሬ አንገት ደፊ ሆኗል፡፡ ኦሮሞ ሸዌው የጀግናው የጎበና ዳጬ ሥም በክብር ፋንታ ስድብ ሆኖበት አፍሯል፡፡ ተሳዳቢዎቹ ታሪክን ጥላሸት በመቀባት በትውልድ የራስ መተማመን እንዳይኖር እንቅልፍ አጥተው ነው የሚሰሩት፡፡ አማራው ሸዌ እንደዛው ለአገር ያበረከተው አሰተዋጽዖ ከስድብ ተቆጥሮበት ነፍጠኛ ጨቋኝ እየተባለ ተገፍቷል፡፡ እውነታው ግን የሸዋ ሕዝብ (ኦሮሞም በሉት አማራ) ዛሬ ላለችው ኢትዮጵያ አጥንትና ደሙን ገበረላት እንጂ ትምህርት እንኳን አዲስ አበባ ዙሪያ ሰፍሮ እንደሌሎች አልደረሰውም፡፡ ይህ ሕዝብ ግን የሚኖረበት ቦታ በፈጠረለት አጋጣሚም ሊሆን ይችላል ከሌሎቹ በተሻለ ከዘረኝነት ልክፍት ነጻ ነው፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ ለታሪክ ብክለትም ሆነ መስተካካል ዋነውን ሚና የሚጫወቱት ምሁራንና ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ሕዝብ የራሱን ታሪክ የሎሎች ነው ተብሎ በምሁራንና በፖለተከኞች ስለሚሰበከው ለራሱ ታሪክ ባለቤት አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የታወቀ ታሪክ አለው ተብሎ ቢነገር እንደ አገው ሕዝብ ታሪክ ያለው ሕዝብ ለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ ዛሬ አክሱም፣ ላልበላና ብዙ የሰሜን ኢትዮጵያ የሰውልጅ ጥንታዊ ጥበቦችን የሚያሳዩ ስነ ሕንጻዎች አማራ ወይም ትግሬ የተባለው ሕዝብ የገነባቸው ሳይሆኑ ጥንታዊያኖቹ አገዎች ያበረከቷቸው ናቸው፡፡ ዛሬ ግን ይህ ህዝብ የእነዚህ ድንቅ  ሥራዎች ባለቤት እንደሆነ ምን ያህል እንደሚያውቅ አላውቅም፡፡ ይልቁንም እነዚህ ሥራዎች ለልሎች ወንድሞቹ ይበልጠውን ንብረት ሆነዋል፡፡  አገሪቱንም ወክለው የአገር ኩራትና ድምቀቶች ሆነው እናያቸዋለን፡፡ በተመሳሳይ የአገር ክብርና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታና የብልጽግናም ፈር ቀዳጅ የነበረው የምኒሊክ ዘመን ታሪክ ኦሮሞ ከተባለው ሕዝብ በላይ የተሳተፈበት ባይኖርም ታሪኩ ግን መሪው አማራ ነው ተብሎ ስለታመነ የአማራ ተብዬው እንጂ የኦሮሞ ታሪክ እንደሆነ ለማሰብ ብዙዎቻችን እድሉን አጥተናል፡፡ ይልቁንም ይህን ታሪክ ኦሮሞ በተባለው ሕዝብ እንደ አንድ የታሪክ ኪሳራ ተደርጎ እንዲታይ ተደርጓል፡፡ በአገርን አንድ ማድረግ የነበረው ተሳትፎ ቢዘነጋ እንኳን በቀጭ ግዛት ለነበሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ነጋሪትን ያስተጋባው አደዋ እውነታ ከየትኛውም ሕዝብ በላይ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ የፈመው ታሪካዊ ገድል እንጂ  አደዋ ትግራይ ስለሆነ የትግራይ ሕዝብ የበላይነቱን ሚና የተጫወተበት አይደለም፡፡ ለዚህ የራሱ ለሆነው ታሪክ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ ባይተዋርነት ሲሰማውና ብዙዎችም በጥላቻ ሳይቀር ሲመለከቱት ሌሎች የእኔ ብለው በየአመቱ ያከብሩታል፡፡

ለዚህ ሁሉ ደግሞ ኦሮሞ የተባለውን ሕዝብ ከኢትዮጵያነቱና ከታሪክ ባለድርሻነቱ ነጥለው ለራሳቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉት በሚፈልጉ በእርግጥም እያደረጉትም ባሉ የዚሁ ሕዝብ ነን ብለው የኦሮሞ ታሪክ አዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ነን ባዮች የጥቅም ጥመኞች የረጩት መርዝ ዋነኛ ምክነያት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ ኦሮሞ የተባለውን ሕዝብ በቀድሞ መንግስታት ተበዳይ ነህና ነጻ እናወጣሀለን በሚል ሁሉም መሞከሪያ ሲያደርገው እናያለን፡፡ አሳዛኙ ግን ሆሉም ሕዝቡን በተበከለ ታሪክ እየመረዙ ከሌሎች ጋር በሠላም እንዳይኖር ከማድረጋቸውም በላይ ሁል ጊዜ አመጽ አነሳሽ እያደረጉ ለጥይትና ለብዙ እንግልት ዳርገውታል፡፡ ሁላችንም ገሀድ የምናውቀው ሀቅ በመጀመሪያዎቹ የኢሕዴግ አመታት ኦሮሞ የተባለውን እወክላለሁ የሚለው ኦነግ የተባለው ድርጅት መሪዎች በቦሌ በኩል በሠላም የተሻለ ኑሮ የኖሩበታል ተብሎ ወደታመነ አገር ሲሸኙ ደሀው ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ ልጅ ኦነግ ነህ እየተባለ ሲገደልና ሲማቅቅ ኖረ፡፡ ዛሬም ድረስ ይህ ችግር አለ፡፡  መሪዎቹ የነበሩት ግን አሁንም የውጪው አገር ሲበቃቸው በሠላም ወደ አገራቸው ተመልሰው በመረጡት ቦታ እየኖሩ ነው፡፡ እስኪ ይህ እውነት አይደለም? በሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ ልጆች ግን ኦነግ ተብለው የት እንደገቡ እንኳን አይታወቅም፡፡ ኦነግ ተብዬውም ዓላማው ሕዝብን ነጻ ማውጣት ሳይሆን እንዲህ የሕዝብን ልጆች በሌላው ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩ ነበር፡፡ በዚህ ሂደት የመመጣው ጥፋት ለመሪ ተብዬዎቹ ምናቸውም አልነበረም፡፡ እነሱ ከጅምሩ የግል ጥቅም እንጂ የሕዝብ ነገር መቼ ገዷቸው፡፡

ኦነግ ከተባለውም ውጭ ያሉት ዛሬ ኦሮሚያ የተባለውን ክልል የሚያስተዳደረወን መሪዎች ጨምሮ ኦሮሞ ለተባለው ሕዝብ ምንም ራዕይ ያላቸው አደሉም፡፡ ሕዝቡን ከሌላው ሕዝብ ጋር በሠላም እንዳየኖር በተፈጠረውም ባልተፈጠረውም ታሪክ ይበክሉታል፡፡ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ የቱንም ያህል በአገሪቱ ትልቁን ቁጥር የያዘ ቢሆንም በአገር ውስጥ በሚኖረው ተጽዕኖ ውሱን እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በልማቱም ቢሆን ከሌሎች ወደኋላ የቀረ ነው፡፡ ሕዝቡ ስለ ልማትና ዕድገት እንዲያስብ ሳይሆን አሁን ያለው ትውልድ በልተወለደበት ዘመን ስለተፈጠሩም ስላልተፈጠሩም ታሪክና ተረቶች እየተሰበከ ከሌሎች ጋር በሠላም እንደይኖር ሆኗል፡፡ ሀያ ምናምን አመት ስለ አማራ የተባለው ሕዝብ ጨቋኝነት ተነገረው፡፡ ግን ዛሬ እንመረዋለን የሚሉት የሰጡትን ነጻነት አላየንም፡፡ ይልቁንም ከሌሎች በሠላም እንዳይኖር ሌላ የተመረዘ በጥላቻ ያደገ አዲስ ትውልድ በመፈጠሩ ዛሬ በየ ዩኒቨርሲቲውና በየትምህርት ተቋሙ የብሔረሰብ ጠብ አንሽ ሆኖ እናየዋለን፡፡

በአዲስ አድማስ ስለአኖሌ አስተያየታቸውን ከሰጡት የኦሮሞ ሕዝብ ተወላጅ ነን የሚሉት ምሁራን በአብዛኞቹቹ የአኖሌን ሐውልት መቆም እንደ መታሰቢያና አስተማሪ የሚያዩት ናቸው፡፡ ታሪኩ ነበር ወይ ተብለው ሲጠየቁ ግን የሰጡት ምላሽ አሳዛኝ ነበር፡፡ አገሪቱን በርዕሰ ብሔርነት የመሩት ዶ/ር ነጋሶ በሐውልቱ መቆም ተስማምተው ስለታሪኩ እውነታነት ግን ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው ይመክራሉ፡፡ እንደሳቸው አባባል አፈታሪክም ከታሪክ መረጃዎች አንዱ ስለሆነ የቱንም ያህል ተጨማሪ የማረጋገጫ ጥናት ቢያስፈልገውም 20 ሚሊየን ብር ያወጣ ሐውልት ማቆም ተገቢ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ሐውልቱን በአስተማሪነቱም በሉት በመታሰቢያነቱ እንውሰደው የደረግ በሚሉት ተጨማሪ ጥናት ይህ ታሪክ ውሸት ሆኖስ ቢገኝ ምን ለማስተማር ወይም ማንን ለማሰብ ቆመ፡፡ ሌላኛው የኦፌዴን መሪ እንደነበሩ የምናውቃቸው በአለፉት መንግስታት ጉልህ ሚና የነበራቸው አቶ ቡልቻ ደግሞ ሌላ ከምሁር የማይጠበቅ አስተያየት ሲሰጡ ተነበዋል፡፡ ለእሳቸው ታሪኩ እውነት መሆኑ ማረጋገጫቸው አንድ የዩኒቨርሲቲ የነበረ ሰው ስለነገራቸው ነው፡፡ ምን ማለት ነው? የታሪክ ማረጋገጫ ማለት ዛሬስ ብሎ ብሎ እከሌ አለኝ እከሌ አላለም ሆነ እንዴ? ይልቁንም እሳቸው በእድሜያቸው ለዚህ ታሪክ ቅርብ ስለሚሆኑ ከወላጆቻቸው በቀጥታ ሊሰሙት በቻሉ የተሻለ መረጃ በሆነ፡፡ አቶ ቡልቻ በአለፉት ሁለት መንግስታት ሊያውም ትልልቅ በተባለ ቦታ ማገልገላቸውና በእድሜያቸውም የገኙት ልምድ ለሕዝብ የሚበጅ ጥሩ ዕድል ነው ብዬ ባምንም ብዙ ጊዜ እሳቸው ለራሳቸው ተደማጭ እሆናለሁ ብለው የሚያስቡትን እንጂ የሕሊናቸውን የሚናገሩ አይመስሉኝም፡፡ በአለፉት መንግስታት ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ ተበድሏል ሲሉም ምን ማለታቸው እንደሆነ አይገባኝም፡፡ ልብ በሉ እኔ አልተበደለም የሚል መከራከሪያ ለማቅረብ ሳይሆን የሰውዬውን አካሄድ እክል ለመጠቆም ነው፡፡ አቶ ቡልቻ የሚያምርባቸው ዛሬ እንደ ድልድይ ሆነው የኦሮሞ የተባለውን ሕዝብ ከሌላው ጋር አንድ የሚሆንበት እድል ማመቻቸትና በሠላም እንዲኖር ማድረግ፣ ታሪክ የሚበክሉትንም በገሰጽ ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ኦሮሞ የተባለውን ሕዝብ መጠቀሚያ ለማድረግ እንጂ ለሕዝቡ ተቆርቋሪ የሆኑ ምሁራንና ፖለቲከኞች ልናይ አልቻልንም፡፡ ይልቁንም ሕዝቡን ከራሱ ታሪክና ከሌሎች እየለያዩት ማንነቱን እንዲምታታበት፣ ሌሎችንም እንዲጠላና ጽንፈኛ እንዲሆን ብዙ መከሩት፡፡

በመጨረሻ ሕዝቡን የራሱን ታሪክ የሌሎች እንደሆነ አድርጋችሁ ባዶ አታስቀሩት፡፡ የምኒሊክ ታሪክ ከሌሎች በጎላ ኦሮሞ የተባለውን ሕዝብ ያሳተፈ ቢሆንም አነሰም በዛም በሌሎች የታሪክ ሂደቶች ሁሉ ይህ ሕዝብ በክፉውም በበጎውም ተሳታፊ ነበር፡፡ ሁሉም ያስብበት እውን የምኒሊክ ታሪክ የማን ነው?!

አመሰግናለሁ

የታላቋ ቀን ልጅ ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.   
    

Sunday, May 11, 2014

ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው”



Imageወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።
ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።
በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።
ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉምሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።
ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!
ክፋት እንደእሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደዓምድ ይወጣል፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤… ኢሳይያስ 9/18-21

ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።

ዓባይ እንደዋዛ–“ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” ክፍል ሶስት (ከአክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)


Dr. Aklog Birara

Dr. Aklog Birara

ክፍል ሁለት ዓባይና ኢትዮጵያ አንድና የተያያዙ መሆናቸውን ያሳያል። አንድና የተያያዙ ናቸው የሚለውን ሃሳብ ከተቀበልን ዓባይ
መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እስካገለገለና ኑሮውን እስካሻሻለ ድረስ የኢትዮጵያን ይገባኛልነትና የሚሰሩ መሰረተ ልማቶች መቀበል
የኢትዮጵያውያን ግዴታ ነው። ዓባይ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥሪት መሆኑን አምናለሁ። ጎሳዊ ወይንም ክልላዊ ሃብት አይደለም።
ስለሆነም፤ ዓባይን የምንታደገው “ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” ብለን እንጂ በጎሳ መታወቂያችን አይደለም። ከዚህ ጋር
አያይዠ ለማሳሰብ የምፈልጋቸው ብዙ ትችቶች አሉኝ፤ ጥቂቶቹ። አንድ፤ የህወሓት መንግሥት ጎሳዎች እርስ በርሳቸው እንዲጨፋጨፉ
ዋና ቀስቃሽ መሆኑ፤ ጭፍጨፋዎችና ዛቻዎች ሲካሄዱ ችላ ማለቱ ኢትዮጵያን ወደ አደገኛ ስርዓት ሰራሽ የእልቂት ጎዳና እየመራት ነው።
አንዳንድ የውጭ መንግሥታት ለዚህ የእርስ በርስ ግጭት መጋቢ ሆነዋል። ሁለት፤ ዶር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል
ጉዞና የሕይወቴ ትዝትዎች” በተባለው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊያነቡት ይገባል ብየ በምገምተው መጽሃፉ ያቀረበው ትችት ከፊታችን
የተደቀነውን አስኳል የፖለቲካ ኃይሎች አሰላለፍ መጠላለፍ በግልፅ ያሳያል። ይኼም፤ ህወሓት ሆነ ብሎ ያገለላቸው አብዛኛውን
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚወክሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥቃቅንና ከለውጥ በኋላ ሕዝብ ተወያይቶ ሊፈታቸው የሚችለውን ልዩነቶች
ወደጎን ትተው ሰብሳቢ ወደሚሆነው ወደ ማህል የሚስብ ዲሞራሳዊ አጀንዳ አለመቅረጻቸው ነው። አብዛኛውን ሕዝብ የሚወክለው
“የኦሮሞና የአማራ ልሂቃን ፖለቲካ በዋናነት በሁለቱ ጫፎች ላይ ቆሞ ገመድ ከመጎተት ወደ መሃል መጥቶ የጋራ ዲሞክራቲክ አጀንዳ
መቅረጽ አልተቻለውም። ብዙዎቹ ሂሳብ የመወራረድ ፖለቲካን የዛሬ 30 እና 40 ዓመታት ብቻ ሳይሆን፤ የዛሬ 130እን 140 ዓመታት
በፊት የነበረውም ጭምር እንተሳሰብ የሚሉ ይመስሉኛል። የኦሮሞ ልሂቃን ዋናው ችግራቸው የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ለመቅረፅ
ከመጣር ይልቅ ለብቻ የሚደረገው ትግልን የመንግስተ-ሰማያት አስተማማኝ መንገድ አድርግው ማምለካቸው ነው። የአማራው ልሂቃን
በሽታው በዋናነት በአማራ ልሂቅ የተፈጠረች የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደዛው እንድትቀጥል ነው። እምነታቸው መቀጠል ትችላለች ነው።”
ከዶር መረራ ትችት ዋና ትምሕርት ነው ብየ የተቀበልኩት የኦሮሞን ልሂቃን የመገንጠል አምልኮ፤ ወይንም የአማራን ልሂቃን
ኢትዮጵያን ወደ ነበረችበት ንጉሳዊ ወይንም ደርጋዊ ስርዓት የመመለስ ተልእኮ ሳይሆን የሁለቱ አንጋፋ ሕብረተሰብ ክፍሎች ልሂቃን
ኢትዮጵያን ከመገነጣጠልና ከእልቂት አደጋ ለመታደግናን ሕዝቧን ዘላቂና ፍትሃዊ ወዳለው የእድገት መሰላል ለማመቻቸት እየተነጋገሩና
እየተወያዩ የጋራ ዲሞክራሳዊ አጀንዳ ለመቅረፅ አለመቻላቸውን ነው። ይኼን ባለማድረጋቸው የውጭ ኃያላን መንግሥታት፤ በተለይ
አሜሪካ በተናጥል ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍና ጠበቃነት ዋጋ አልሰጡትም። ወደፊትም ዋጋ የሚሰጡት አይመስለኝም።
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጣ ውረድ በጥልቀትና በቀጥታ የሚያውቀው ዶር መረራ እንዲህ ይላል። “…ለታሪክም ለሕዝብም አስቀምጨ
ማብቃት የምፈልገው መሰረታዊ ነጥብ፤ አብዛኛው የትግራይ ልሂቃን “ስልጣን ወይም ሞት” ብለው ሥልጣን ላይ የሙጥኝ እስካሉ
ድረስ፤ አብዛኛው የአማራ ልሂቃን በአፄዎች ዘመን የንበረውን የበላይነት መልሼ አገኛለሁ ብሎ የሚገፋውን የሕልም ፖለቲካ
እስካልተወ ድረስ፤ ብዙሃኑ የኦሮሞም ልሂቅ ኦሮሚያን ለብቻ የማውጣቱን ሕልም እስካልተወ ድረስ ሃገራችን ከአደጋ ቀጠናና ቀውስ
የምትወጣ አይመስለኝም።” እኔም የማሳስበው ተመሳሳይ ነው። የሶስቱም (የትግራይ፤ የአማራና የኦሮሞ) ልሂቃን አገሪቱ ብትፈራርስና
እልቂት ቢፈጸም በታሪክ፤ በአብዝኛው የኢትዮጵያ ሕዝብና በተከታታይ ትውልድ ተጠያቂዎች ናቸው። “ጂብ ከሄደ ውሻ ጮኸ”
የሚለው እንዳይከሰት እፈራለሁ። ኢትዮጵያ “ከአደጋ ቀጠና”፤ ሕዝቧን ከእልቂት ለማዳንና ዓባይን ከግብጾች አደጋ ወዘተ ለመታደግ
ፍላጎት ካለ– ያለ ይመስለኛ–የፖለቲካው አደረጃጀት፤ ውይይትና ድርድር ከጎሳ ፖለቲካ ወደ ኢትዮጵያውያን ፖለቲካ መሸጋገር
አለበት። የኦሮሞ፤ የአማራና በህወሓት “ስልጣን ወይም ሞት” ውጭ የተሰለፉ የትግራይ ልሂቃን ለኢትዮጵያና ለመላው ሕዝቧ ባለ
አደራ ሆነው አብረው የሚሰበሰቡበት ወሳኝ ወቅት አሁን ነው። አገሪቱ ከፈራረስችና እልቂት ከተካሄደ በኋላ የምናደርገው ጭኸት
ለማንም አይበጅም። አሁንም የዘገየን ይመስለኛል። ለዚህ ነው፤ የጉራጌ ሆነ የአማራ፤ የኦሮሞ ሆነ የትግሬ፤ የሶማሌ ሆነ የአኟክ ወዘተ
መፈክር “ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” ብለን ለሁሉም ዜድጎች ዲሞክራሳዊና ሰብዓዊ መብት መነሳት አለብን የሚል
አደራ ያቀረብኩት። የኢትዮጵያ ሕዝብ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ድምፁን አሰምቶ የፈለገውን የመንግሥት ስር ዓት የመመስረት መብት
አለው። ለፍትህ የሚቆረቆሩ ልሂቃን፤ ጎሳና ኃይማኖት ሳይለዩ የዲሞራሳዊ ማእከል አጀንዳ የማመቻቸት የሞራል ግዴታ አለባቸው።
ሶስተኛ፤ በአብዛኛው፤ ስርዓቱን የምንቃወም ግለሰቦችና ስብስቦች በሙስና የተበከለው የህወሓት መንግሥት፤ ከሕግ ውጭ በዓመት
ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ከድሃው ሕብረተሰብ ተሰርቆ ወደ ውጭ እንዲጎርፍ ያመቻቸ ራሱን አገልጋይ የመንግሥት ስርዓት መሆኑን
ነው። የዛሬው ስርዓት ሙስና ተወዳዳሪ እንደሌለው አምናለሁ። እነደ ተሃድሶ ግድብ ግዙፍና የማይንቀሳቅሱ የመሰረተ ልማት ምሰሶዎች
ሲሰሩ፤ ቢያንስ እንኳን ለሃገርና ለሕዝብ ይጠቅማሉ። በኔ ግምት ሊባክን የሚችለው ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመተው የውጭ
ምንዛሬና የብር ኢንቬስትሜንቱ የተሃድሶን ግድብ ለመገንባት፤ ለኢትዮጵያውያን የስራ እድል ለመፍጠር መዋሉ ተቀባይነት ያለውና
የሚደገፈ የዘመናዊነት መለኪያ ነው። ይህ የኢትዮጵያ የዓባይ ይገባኛልነት ትችት ሕብረተሰቡን፤ በተለይ ዲያስፖራውን በይፋ ከማነጋገሩ
ቀደም ሲል፤ “Ethiopia: the deal of the century (የመሬት ነጠቃና ቅርሚት) በተባለው መጽሃፌ ስለ ዓባይ ኢትዮጵያዊነት፤ ስለ
ተሃድሶ ግድብ ብሄራዊና ማህበራዊ ጥቅም፤ የተያያዙ ጥያቄዎችና መሰረታው የፖሊሲ ሃሳቦች ባጭሩ አቀርባለሁ። 1. ማንኛውም ዘመናዊነትን ለመቀዳጀት የሚፈልግ አገር ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው ሕብረተሰቡን የሚያቆራኝ የልማት መሰረት
ለመጣል ለመሰረተ ልማት ቅድሚያ መስጠት ግዴታው ነው። መንገዶች፤ ድልድዮች፤ ግድቦች፤ የሃዲድ መረቦች፤ የአየር
መጓጓዣዎች፤ ትምሕርት ቤቶች፤ የጤና ጣቢያዎች፤ መፀዳጃዎች፤ የንፁህ ውሃ ጉድጓዶችና ቧምባዎች ወዘተ ማልማት ወሳኝ
ነው። የኢህአዴግ መንግሥት በእነዚህ ዘርፎች ዙሪያ ያደረገው የመዋእለ ንዋይ ፈሰስ የሚያስመሰግን ነው። አከራካሪውና
እስካሁን ያልታየው መሰረተ ልማት ከምርት ኃይሎችና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር አለመያያዙ እና ጎሳዊ መሆኑ ነው።
2. የተሃድሶና ሌሎች ግዙፍ የመብራት ኃይልና የመስኖ ግድቦች ከዚህ አስፈላጊ ከሆነ መሰረተ ልማት አይለዩም። ሆኖም፤
ግድቦች ሲሰሩ ሁለገብ ጥናትና ምርምር ማድረግ፤ አካባቢው ለተከታታይ ትውልድ እንዲያገለግል ማመቻቸት ፤ ነዋሪዎች
እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ማድረግ እና አማራጮችን ማቅረብ፤ መላው ሕብረተሰብ የሚጠቀምበትን እቅድ ማውጣት ግዴታ ነው።
3. በተለይ ለመስኖ የሚያገለግሉ ግድቦች በስፋት መሰራት ቁጥሩ እየጨመረ የሄደውንና የሚሄደውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የምግብ
ፍላጎትና ዋስትና ለማሟላት ያስችላሉ። እንዲያውም፤ የእድገቱ ዋና ትኩረት መጀመሪያ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና
እንዲኖራት ማድረግ ነው። ዛሬ ብዙ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የሚመኩት ለጋስ አገሮች፤ በተለይ አሜሪካ በሚለግሰው
የምግብ እርዳታ ነው። ይህች አገር ዘላለም የምግብ ጥገኛ ሆና ከቆየች አስደናቂ እድገት አለ ለማለት አይቻልም። ዓባይን
ያህል ለመስኖ የሚያገለግል ወንዝ ይዞ ጥገኛ መሆን የአገዛዝ ድክመትን ያሳያል። የምግብ ራስን መቻልና የምግብ ዋስትና
ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ለም መሬትን ለውጭ ኢንቬስተሮች በመቸርቸር አለመሆኑን ከላይ በተጠቀሰው በማስረጃ
በተደገፈ መፅሃፍ በሰፊው ያሳያል። የደርግ መንግሥትና የግራው ክፍል ዋናና ሲጠቀስ የሚኖረው ዲሞክራሳዊ አስተዋፆ
መሬትን ላራሹ ማድረጉ ነው። ለእያንዳንዱ ከተመኛ ድሃ ሆነ ሃብትም ቤተሰብ ለራሱ መኖሪያ አምስት መቶ ካሪ ሜትር
መሬት ሰጥቶ በሕግ እንዲከበር ማድረግ ዲሞክራሳዊ ውሳኔ ነበር። ህወሓት ይኼን የሰው ህይዎት የተከፈለበት የአብዮት
ውጤት የፖለቲካና የግል ትርፍ መጠቀሚያ ማድረጉ በታሪክ ያስጠይቀዋል። ወጣቱ ትውልድ ለዚህ ዲሞክራሳዊ መብት
መታገል ይኖርበታል። በገጠር ሆነ በከተማ፤ የመሬት ባላቤትነት እውቅና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነት ጋር የተያያዘ ነው።
4. ከውሃ የሚገኝ የመብራት ኃይል ለአገር ወለድ ኢንዱስትሪ ልማት መስፋፋት ቁልፍ ነው። የአየሩ ሁኔታ ከፈቀደ ከሌላ ነዳጂ
በበለጠ ደረጃ ተከታታይና ራሱን የሚያድስ ጥቅም ይሰጣል። ለአካባቢ እውቅና ሰጥቶ ይኼን የተፈጥሮ ሃብት መንከባከብ
ለተከታታይ ትውልድ ዋስትና ያለው የውሃና ከውሃ የሚገኝ መብራት፤ የመስኖ እርሻና የመሳሰሉ ጥቅሞች ይሰጣል።
ኢትዮጵያ የእርሻ ሰብሎች፤ የእንስሳት ወዘተ ኃብታም አገር ናት። ይህ የተፈጥሮ ኃብት ለኢንዱስትሪ መጋቢ ነው። የአገሪቱን
የጨርቃጨርቅ፤ መጫሚያ፤ የምግብ ውጤትና ሌሎች የፍጆት እቃዎች ለማምረትና ፍላጎትን ለማሟላትና ለውጭ ገበያ
ከእርሻና ከእርሻ ጋር የተያያዙ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ያለው እድል ሰፊ ነው። ትኩረቱ ግን የአገር
ውስጥ ፍላጎትን በተቻለ መጠን ማሟላት ነው የሚል ሃሳብ እሰነዝራለሁ። ተራው ኢትዮጵያዊ የመግዛት አቅሙ
የሚፈቅደውን ማቅረብ የእድገት መለኪያ መሆን አለበት። ኢትዮጵያውያን በአገራቸው የሚመረቱትን የኢንዱስትሪ ውጤቶች
የመግዛት ባህልን ልምድ ማድረግ ዘላቂነት ላለው እድገት ወሳኝ ነው። እድገት “ስልጣን ወይም ሞት” ለሚል ቡድን አገልጋይ
መሆኑ ማቆም አለበት። የሚያቆመው ለዲሞክራሳዊ ስርዓት የቆመ የአንድነት ኃይል ነው እላለሁ።
5. የዓባይ ወንዝ ኢትዮጵያዊነት እውቅናና የተሃድሶ ግድብ መገንባት በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተደገፈ ነው። ሕዝቡ
ቀደም ሲል ቅኝ ገዢዎች፤ በተከታታይ የግብጽና ሌሎች የአረብ መንግሥታት ሆነ ብለው ጠብ እየጫሩ ኢትዮጵያ በዚህ
ግዙፍ የተፈጥሮ ሃብቷ እንዳትጠቀምና ከድህነት ነጻ እንዳትወጣ ማድረጋቸውን ያውቃል።
6. የኢትዮጵያ ሕዝብ እንግሊዞች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በወቅቱ በጥቁር አፍሪካ ብቸኛ የነጻነት “ደሴት” እና እውቅና የነበራትን
ኢትዮጵያን እንደሌለች አድርገው ወደጎን ትተው በ1929 እና በ1959 ዓባይን ለግብፆችና ለሱዳኒሶች አውርሰው መሄዳቸውን
ያውቃል። ሆኖም፤ እነዚህን የተዛቡ ውሎች ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት አልተቀበሉም። አዲሱና ለሁሉም የተፋሰስ
አገሮች የሚጠቅም፤ የNile Basin Initiative የተባለው መመሪያ የተባበሩት መንግሥት የልማት ድርጅት፤ ዓለም ባንክ፤
የካናዳ ተራድዖ ድርጅትና ሌሎች የደገፉት መርህ የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች በሙሉ ደግፈውታል። ከጣና በለስ
ፕሮጀክት ጀምሮ፤ የዓለም ባንክ አመራር ኢትዮጵያ ድህነትን ለመቀነስ የምትችለው የዓባይ ወንዟን ለመስኖ እርሻና
ለኢንዱስትሪ ልማት ስትጠቀም ነው የሚል መሰረታዊ የልማት ዓመራር እንደነበረው አውቃለሁ። ሆኖም፤ ይህ ድርጅት
ለኃይል ማመንጫ ግድቦች የሚሰጠው ብድር ከአገር ወደ አገር ይለያያል። የፖለቲካ ውሳኔ አለበት ማለት ነው። ቁም ነገሩ
ግን፤ ዓለም ባንክ የናየል መርህን ከተቀብለ በኋላ ከመወላወል ወደ እርግጠኛነት ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያን የይገባኛል አቋም
በቀጥታም ባይሆን ውስጥ ለውስጥ ይደግፋል። በአፄ ኃይለ ሥላሴና በደርግ ዘመኖች ታላቁን የዓባይ ግድብ በሚመለከት
የዚህ አይነት ጥራት ያለው አቋም አልነበረውም። ዓለም ባንክ የሚወስዳቸው አቋሞች በአብዛኛው የሚያሳዩት የአሜሪካ
ድጋፍ እንዳለ ነው። ግብጾች ከጅምሩ የዓባይ ግድብ የትም እንዳይደርስ ሞክረዋል። የማያከራክረው፤ የዓለም ሁኔታ በፍጥነት
ተለውጧል። ይህ ለውጥ ኢትዮጵያ የተሃድሶን ግድብ ለመገንባት ሙሉ መብት እንዳላት ያመለክታል።
7. ይህን በሚመለከት የአፄ ኃይለ ሥላሴ፤ የደርግንና የኢህአዴግ መንግሥታት ተመሳሳይ አቋም ይዘው ይገኛሉ። የግድቡን
ቅድመ ሁኔታ ያመቻቹት የቀድሞዎቹ መንግሥታት ሲሆኑ፤ ህልሙንና ራእዩን ወደ ተግባር የተረጎመው የአሁኑ መንግሥት
ነው። ስርዓቱን ስለምንቃወም ብቻ ለሃገር የሚጠቅሙ፤ ማንም የማያንቀሳቅሳቸው ሃውልት የሚመስሉ ግድቦች ሲሰሩ
መደገፍ ገዢውን ፓርቲ መደገፍ አይደለም። በበኩሌ፤ ስርዓቱንና የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም እለያለሁ። ያለፈውን
የኢትዮጵያን ዘመናዊ አገዛዝ አመሰራረት ውጣ ውረድ ስናይ፤ በሃገር ማእከላውዊነት፤ በሃገር ታሪክ ተከታታይነትና የወደፊት
አብሮ መኖር፤ አብሮ ማደግ፤ አብሮ ሃገርን መታደግ የሚያምን መንግሥት መደገፍ አግባብ አለው። የመንግሥቱ የበላዮች
ቢለወጡ የአገር ዘላቂ ጥቅም አይለወጥም። የአገር ዘላቂ ጥቅምና ደህንነት እንደ ሸቀጥ አይሸጥም፤ አይለወጥም። ዓባያና
በዓባይ ላይ የሚሰራ መሰረተ ልማት አይሸጥም፤ አይለወጥም። የዓባይ ግድብ ከዚህ ያለፈ የኢትዮጵያ የማይሸጥ፤ የማይለወጥ
የማንነት ታሪክ ጋር ተመሳሳይነት አለው እላለሁ።
8. በማህበረሰብ ህይዎት አንጻር ሲታይ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተራበ፤ እየተሰደደ ሰማንያ ሶስት በመቶ የሚሆነው በኩራዝ
መብራት እየተጠቀመ ወዘተ ዓባይ አይገደብ ብሎ መበየን በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ መፍረድ ነው። የዚህ አይነቱ
አቋም የሚጠቅመው ግብፃችን ይሆናል። ይኼን ስል ሁለተኛውንና ዋናውን የዲሚክራሳዊ ስርዓት አስፈላጊነት እንዳንረሳ
አሳስባለሁ።
9. የግድቡ ጥቅም የመብራት ኃይል ብቻ አይደለም። አስዋን፤ የቪክቶሪያ ፏፏቴና ግድብ፤ ኢዋዙ ፏፏቴና ሌሎች ለሽርሽር
(ቱሪዝም) በየዓመቱ የሚስቡት የሰው ብዛት፤ የሚያስገኙት ገቢ፤ የሚቀጥሩት የሰራተኛ ብዛት ከፍተኛ ነው። የተሃድሶ
ግድብም ይኼን የመሰለ ጥቅም እንደሚስገኝ ለማሰብ አያዳግትም። አክሱምን፤ ጎንደርን፤ ላሊበላን ወዘተ ለማየት የሚመጣው
አገር ጎብኝ ተጨማሪ ሃውልት አገኘ ማለት ነው። የዘላለም የተፈጥሮ ሃብት የዘላለም የኢኮኖሚ መንቀሳቀሻ ይሆናል።
10. የተሃድሶ ግድብ እቅድ በድንገት የተፀነሰ አለመሆኑን ባለፈው ሃምሌና ነሃሴ በተከታታይ በእንግሊዝኛ ባቀርብኳቸውና በክፍል
አንድ በአማርኛ ባቀርብኩት መጻጽፍት አሳይቻለሁ። በግብፅ የተካሄደው የሕዝብ አመጽ የግብፆችን ትኩረት ለጊዜውም
ቢሆን በአገሪቱ እርጋታ ላይ እንዲያተኩር አድርጎታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ክፍተት መጠቀሙ አግባብ አለው።
በተጨማሪ፤ የአፍሪካ የተፋሰስ አገሮች መብታችን ይከበር እያሉ ነው። ሆኖም፤ ይህ ጊዜአዊ የሆነ የግብፅ ድክመት በመለወጥ
ላይ ነው። የግብፅ የመንግሥት ዓመራር ፍጹም ብሄርተኛ (ultra Egyptian Nationalist) ወደ ነበረው የናስርና ሞባርከ
አይነት ወታደራዊ አገዝዛ እየተሸጋገረ ነው። ይህ ወታደራዊና አምባገነናዊ ይዘት ያለው አገዛዝ በተሃድሶ ግድብ ላይ ኢላማ
ያደርጋል የሚሉ ብዙ ናቸው። ባለፈው ዓመት መጨረሻ ዶሃ በተደረገው የዓረቦችና የአፍሪካውያን ልሂቃን ስብሰባ አንድ
የታወቀ ግብጻዊ ያቀረበው ትንተናና ድምዳሜ አመልካች ነው።
11. “በአፍሪካ የሚካሄደው ግዙፍ የሆኑ የመብራት ኃይል አቅርቦት ግድቦች ስራ አዲስ የወንዝ ውሃ ኃያላን መንግሥታት
እየፈጠረ ነው (New Hydropoewer Hegemony).” ይህ ኃያልነት ከማን ላይ እንዳተኮረ ግልፅ ነው። ግብፅን የሚመለከት
ግዙፍ ግድብ የሚሰራው በዓባይ ወንዝ ላይ ነው። አዲስ ወይንም መጤ የወንዝ ውሃ መብራት ኃያል አገር ተብላ
የምትጠራው ኢትዮጵያ ናት። ምሁሩን “የዓባይን (ናየል) ወንዝ ለጋራ አገልግሎት ለማዋል የተጀመረው የኢትዮጵያና የሌሎች
የአፍሪካ ተፋሰስ አገሮች መብት ነው። ድሃና ኋላ ቀር የሆኑት አገሮቻቸው የማልማት መብት አላቸው። የዓለም ሕግ
ይፈቅድላቸዋል። ይህ መብት በስራ መተርጎሙ የማይቀር ነው። የሚጠቅመው የጥቁር አፍሪካ አገሮችን እየለያዩ “አዲስ
ኃያል” ማለት ሳይሆን በጋራ በሚሰሩ የአባይ ሁለ-ገብ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ነው” ወዘተ በማለት ለማግባባት ያደረግሁት
ጥረት የትም የደረሰ አይመስለኝም። ግብፃዊው የሚለው ይህ አዲስ ክስተት ተቀባይነት የለውም ነው። እኔ ደግሞ የምለው
ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የሚጋሩትን ታላቅ ወንዝ ለራሳቸው ሕዝብ አገልጎሎትና ለሃገራቸው ልማት ለማዋል
መብታቸው ነው። ማንም ኃይል ሊያቆማቸው አይችልም የሚል ነው። ሚዛናዊ የሆኑ የግብፅ ልሂቃን ዓባይን ሚዛናዊ በሆነ
መንገድ መጠቀም አግባብ አለው ይላሉ።
12. ምንም እንኳን “ሃይድሮ ፖወር ሄጀሞኒ፤ የውሃ ኃይል የበላይነት” ሆነ ተብሎ የአፍሪካ አገሮች እንደ ኃያላን መንግሥታት
እየሆኑ ሂደዋል፤ “ደቡብ አፍሪካና ናይጀሪያ” አዲስ የጥቁር አገሮች የበላይ ጡንቻ ያሳያሉ” ወዘተ የሚል አፍሪካውያንን
የሚከፋፍል ሃሳብ ቢያሽከረክርም፤ አባባሉ አያዋጣም። አንድ አገር የተፈጥሮ ሃብቱን ተጠቅሞ ድህነትን ለመቀነስ፤ ቢቻል
ለማጥፋት ሲጀምር የዚህ አይነት ቅፅል ስም መስጠቱ አግባብ የለውም። ሰላም አይፈጥርም። የገልፍ አገሮችና ሳውዲ አረቢያ
የነዳጅ ኃብታቸውን አልምተው ሃብታም ስለሆኑ አዲስ ኃያላን ያላቸው የለም። ናይጀሪያ አዲስ ኃያል አገር ብትሆን ኑሮ
ሺብርተኞችን ለማደን የአሜርካ እርዳታ አያስፈልጋትም ነበር። ኃያል ስትሆን ደግሞ ማንም ሊኮንናት አይችልም።
ኢትዮጵያውያን ካወቅንበት ኢትዮጵያም ተገቢውን አህጉራዊ ኃያልነት ትቀዳጃለች የሚል እምነት አለኝ። ይህ በብልሃት፤
ሁሉን በሚያስትፍ ዲሞክራሳዊ ስርዓት ስኬታማ ይሆናል። አገሪቱ ከተበታተነችና እልቂት ከተካሄደ ይህም ህልም ይሆናል።
13. የዓባይን ግድብ ለማፍረስ የሚሞከረው የግብፆች የጦርነት “አለንጋ” አያስፈራኝም። የሚያስፈራኝ ህወሓት የፈጠረው
የሕብረተሰብ መከፋፈልና የሰብዓዊ መብቶች ሁሉ መገፈፍ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሃገሩ ቀና ነው። ብሄር፤ ብሄረሰብ፤ ሃይማኖት፤ ሃብት፤ ጾታ፤ ስደተኛ፤ አገር ውስጥ ኗሪ የሚል ሳይለየው በአንድ ላይ፤ ለአንድ ብሄራዊ ዓላማና ለእውነተኛ
የሁሉም ዜጎች እኩልነት ከቆመ ማንም የሚያጠቃው ኃይል እንደማይኖር ሙሉ እምነት አለኝ። ደጋግሜ እንዳሳሰብኩት፤
ግብፆች በፖለቲካና በኃይማኖት የተለያዩ ዘርፎች አሏቸው። የሚዳኛቸው ግን ማንነታቸውን ማወቃቸው ነው። “ግብፅ
አገራችን ናት። እኛ ግብጻውያን ነን” የሚለው እውቅና በያንዳንዱ የግብፅ ዜጋ ደም ስር የገባ መሆኑን ተመላልሸ
ካነጋገርኳቸው ግብጻውያን ተምሬያለሁ። ግብጾች በአስተሳሰብና በኃይማኖት ከአንድ ፋብሪካ የወጡ አይመስሉም። በዓባይ
ጥያቄ ግን አንድ ወጥ ናችው ለማለት ይቻላል።
ግብጾች “ግብፅ ሃገሬ ናት፤ እኔም ግብጻዊ ነኝ” የሚሉት ለኢትዮጵያውያን አዲስ ክስተት አይደለም። ተስፋ የሚሰጠኝ እሴት እኛ
ኢትዮጵያውያን ከማንም ባላነሰ ደረጃ “አገሬ ኢትዮጵያ፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ” እያልን አድገናል። ባህላችንና መታወቂያችን ይኼው
ነበር። ለኢትዮጵያ ነጻነት፤ ለሁሉም ሕዝቧ ክብር ሲሉ ተዋግተው የሞቱት ኦሮሞዎች፤ ጉራጌዎች፤ ደቡቦች፤ ትግራዮች፤ ኤርትራዉያን፤
አፋሮች፤ አማራዎች፤ ሶማሌዎች፤ ክርስትያኖች፤ ሙስለሞች ወዘተ ለዚህ የሚያኮራ እውቅና አብቅተውናል። እንደዛሬው አይሁን እንጅ
በእኔ ትውልድ ያየሁት የፓስፖርት መታወቂያ፤ ከግንባሬ ላይ የተለጠፈ ጎሳየ አልነበረም። በተማሪው እንቅስቃሴ የማውቃቸው ከዚህ
ዓለም ያለፉና አሁንም በህይወት ያሉ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከየት መንደርና ጎሳ እንደመጣን ተነጋግረን አናውቅም። አናስብውም
ነበር። አነጋጋሪያችን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚበጅ ፍትሃዊና ዲሞክራሳዊ ስርዓት እንዴት እናራምድ የሚል ነበር። በሃገር ቤትና
ከሃገር ውጭ ያለው ወጣት ትውልድ–ተማሪው፤ አስተማሪው፤ የቢሮ ሰራተኛው ወዘተ ቀና አመለካከት፤ ከራሱ ጥቅም በላይ ለሃገሩና
ለወገኑ የሚቆረቆር፤ ለነገው ትውልድ የሚያስብና የሚታገል ለመሆኑ የአይን ምስክር ነኝ። የዚህ ሰብሳቢ መልእክትና ማሳሰቢያ አንድ
ነው። “አገሬ ኢትዮጵያ፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ።” ይኼን እንደ አሮጌ ጨርቅ አውልቀን ጥለን ዓባይን ሆነ ሌላውን የኢትዮጵያ የተፈጥሮ
ሃብት ለመታደግና ለመላው ሕዝብ ጥቅም ለማዋል አንችልም። ዲሞክራሳዊ አማራጭም ለመመስረት የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብት
መገፈፍ የራሴ መብት መገፈፍ ነው ወደሚል ሰብሳቢ ፖለቲካ ከሸጋገር መቻል አለብን።
አንዱ የወቅቱ ጥያቄ አገር ቤትና ውጭ ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች፤ የገዢው ፓርቲ አባላትና ሌሎች በዓባይ ይገባኛልነት
የሚያምኑ ሁሉ “አገሬ ኢትዮጵያ፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ” ብለው የመሰብሰብና ለአንድ ዓላማ የመቆም ግዴታቸውን ከተወጡ ግብፆች
ኢትዮጵያን ለማጥቃት አይችሉም እላለሁ። ይህን የምልበት ዋና ምክንያት ከኢትዮጵያውያ አስደናቂ ታሪክ፤ ከጀግኖⶩ ጀብዱ ልምድ
የተማርኩትን ምርኩዝ በማድረግ ነው። አፄ ምኒልክ የአድዋን ድል ለኢትዮጵያና ለዓለም ጥቁር ሕዝቦች ያበረከቱት ዘመናዊ መሳሪያ
ስለነበራቸው አይደለም። ክሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰቦችና እምነቶች የተወጣጡ አርበኞቿ በአንድ ላይ፤ “አገሬ ኢትዮጵያ፤ ዜግነቴ
ኢትዮጵያዊ” ብለው በአንድ ላይ ስለተዋጉና ስለሞቷላት ነው። የፋሺስቶችን ወረራ አንቀበልም ብለው ለአምሥት ዓመታት በዱር
በገደሉ የተዋጉላትም አርበኞቿ ይኼን የተቀደሰ አርማ ተከትለው ነው። ስለሆነም፤ ከግብፅ የመሳሪያ የበላይነት የበለጠ አስተማማኝ
የሚሆነው ወሳኝ ኃይል የኢትዮጵያውያን ወንድማማችነት፤ እትማማችነትና አንድነት ነው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ከሕዝቧ
አንድነትና እውነተኛ እኩልነት ሊለይ አይችልም። ብሄራዊ አንድነቷን ለመጠበቅ የምትፈልገውና የምትችለው ኢትዮጵያ፤ የተባበረና
በሕግ ፊት እኩል የሆነ ሕዝብን ትጠይቃለች። የተባበረና መብቱ የተከበረ ሕዝብ መሳሪያ የማይተካው ኃይል ነው።
ለስልጣን ብቻ የቆመው ህወሓት ለዚህ ኃይል መበታተን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ነው። በአንድ ቦታ፤ “እኔ ከሌለሁ አማራውን ኦሮሞው
ሊነሳብህና ሊጨፈጭፍህ ነው፤ ተጠንቀቅ” ብሎ ይቀሰቅሳል። በሌላ ቦታ፤ ኦሮሞውን “የአማራ ነፍጠኞችና የኢሰፓ አምባገነኖች
እንደገና ሊመጡብህ ነው። የዱሮውን መንግሥት ለመመለስ እየተዘጋጁ መሆናቸውን እናውቃለን።” በሌላ በኩል ደግሞ ለትግራይ
ሕዝብ “የሸዋ አማራ አሁንም እየዶለተብህ ነው።” በደቡብና ሌሎች ክልሎች “የራስክን ጥቅምና ማንነት ካላስከበርክ፤ አማራውና
ኦሮሞው ይጨፈጭፍሃል” ወዘተ እያለ ሕዝብን ከሕዝብ ሲለያይ ቆይቷል። ይህ የቅኝ ገዢዎች “ከፋፍለህ ግዛው” አይነት የውሸት
ዓመራር ግብፇችንና ሌሎች ኃያላንን ለመቋቋም ማነቆ ሆኗል። ሕዝቡ እውነቱን ከውሸቱ ለይቶ ለመብቱ በአንድ ላይ እንዳይነሳ
አድርጎታል። ለዚህ መልሱ የህወሓት የስልጣን መቆያ የሆነውን የመለያየት ዘዴ አውቆ በአንድ ላይ አገር አቀፍ በሆነ የሕዝብ ዓመጽ
መነሳት ብቻ ነው። መረዳት ያለብን ህወሓት ራሱን መርምሮ ወደ ፍትሃዊ ስርዓት ካላመራ አገሪቱን አጥፍቶ ራሱንም ያጠፋል።
ለስልጣኑ ቆይታ ያደረገው ስሌትና ስልት በተለይ ኦሮሞውና አማራው እርስ በርሱ ቢተላለቅ ደንታ የሌለው አመራር ነው። ወጣቱ
ትውልድ ከዚህ ባሻገር ማሰብ አለበት። እልቂት ለማንም አጥፊ ነው። መከላከል የሁላችንም ሃላፊነት ነው። ለጥላቻው መጋቢ የሆን
ሁሉ በታሪክ ተጠያቂዎች እንደምሆን አያከራክርም።
ያለው የከፋፍለህ ግዛው ችግር እንዳለ ሆኖ (ይኼን ለመፍታት አብሮ ከመታገል ውጭ አማራጭ ያለ አይመስለኝም)፤ ይህ ግዙፍ ግድብ
የኢትዮጵያውያን መታወቂያ ሃውልት መሆኑን ግን መካድ አደገኛ ነው። ሌሎች የኢትዮጵያ መንግሥታት ሊገነቡት የፈለጉትንና አቅም
ስለሌላቸውና ሁኔታዎች ስላልፈቀዱ ስኬታማ ያላደረጉትን የአሁኑ መንግሥት መስራቱ አያስነቅፍም። ደጋግሜ ለማስታወስ የምፈልገው
አስኳል ጉዳይ የኢትዮጵያ የዓባይ ይገባኛልነት ከሶስት ሽህ ዓመታት በላይ ከሚገመተው ተከታታይ የኢትዮጵያ ታሪኳ ጋር የተቆራኘ
ነው የሚል የፀና እምነት አለኝ። ይህ ዓለም ያደነቀውና አንድ የመፃሕፍት ቤት የሚሞላው የኢትዮጵያ ተከታታይነት ታሪክ ከጥያቄ
በላይ አልፏል። ይህ አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ አልባ ክስተት በስልጣን ስሜት፤ ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት በህወሓት መሪዎች ጥላቻ
የተሽከረከረ እልቂት ያስከተለና ወደፊትም የሚያስከትል ሂደት ነው። የዓባይ ይገባኛልነት ጥያቄ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ከኢትዮጵያ
ህልውና ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑን ህወሓት መቀበል ግዴታ ሆኖበታል። ተወዳጅንት ለማግኘት መሆኑ አያከራክርም፡፡ ኢትዮጵያ
በረዢም ታሪኳ ይገባኛል ብላ ባትከራከርና የብዙ ዜጎቿን ህይዎት መስዋት ባታደርግ ኖሮ፤ ገዢው ፓርቲ የተሃድሶን ግድብ ለመስራትአይችልም ነበር። በአንፃሩም ግብጾች የሚሉት ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ይገባኛልነት አግባብ ይኖረው ነበር። ለህወሓት መሪዎችና
ለኢህአዴግ አባላት ለማሳሰብ የምፈልገው ታሪኩን የካደ ሕዝብ በዓባይ ላይ ታሪካዊ መብት አለኝ ለማለት የሞራል ብቃት እንደሌለ
ነው። ዛሬ የማይካደው ክስተት የኢትዮጵያን ታሪክ የለም የሚለው ህወሓት ካልፈለገውና ካላሰበው የታሪክ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብቷል።
ታሪክን አፈራርሶና ሰርዞ የታሪክ ጨለማን መፍጠር ለጊዜው የበላይነት ጥቅም ቢሸምትም ዙሮ ዙሮ ሁሉንም እንደሚያጠፋ እሰጋለሁ።
ስርዓቱ ሆነ ብሎ የፈጠርው ጎሳዊ ፖለቲካ የህልውና ጉዳይ ሆኗል። ጎሳዊው የፖለቲካ ዓመራር ህወሓት ለራሱ የስልጣን የበላይነትና
ቆይታ ሲል ለተባባሪ የጎሰኞች ቡድኖች (ethnic elites) ፤ በማስፈራራት፤ በመደለል፤ ጉርሻ በመስጠት ወዘተ በናንተ ተወካይነት
“ጭቁን ሕዝቦች” ለመጀመሪያ ጊዜ እፎይ ብለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት አግኝተዋል በሚል ከእውነቱ የራቀ ስሌት
የኢትዮጵያን ታሪክ፤ አንድነትና የኢትዮጵያን ሕዝብ የቆየ ጠንካራ ግንኙነት፤ ሏዓላዊነት አወቃቀር ከስሩ ንዶታል። ባጭሩ፤ ቢቀበልም
ባይቀበልም፤ ቢያውቅም ባያውቅም፤ የህወሓት ዓመራር የተከተለውና የሚከተለው የአገር ዘመናዊነት ዓመራር “ከተሃድሶ ግድብ”
ኢትዮጵያዊነት ጋር ሊጣጣም አልቻለም። ኢትዮጵያ “ከመቶ ዓመታት በላይ የሚሰላ ታሪክ የላትም። የዛሬይቷ ኢትዮጵያ በኃይልና
በጭፍጨፋ የተፈጠረች ናት። ከፈለጉ ብሄር/ብሄረሰቦች የመገንጠል መብት አላቸው” ወዘተ ከተባለ ኢትዮጵያውያን ከሚጋሯቸው
ይልቅ የሚለዩአቸው ያይላሉ ማለት ነው። ዓባይን ሆነ ሌላ የተፈትሮ ኃብት፤ የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና ደህንነት አብሮና ተባብሮ
ለመከላከል ያስቸግራል ማለት ነው። የህወሓትን አፍራሽ አመራር ከተቀበሉና ስኬታማ ለማድረግ ከፈለጉ የሁሉም ክልሎች ነዋሪዎች
“ዓባይ የኢትዮጵያ ነው። የአሁኑ መንግሥት የሚሰራው ግድብ አግባብ አለው። የግብፆችን የጦር ዛቻ አንቀበልም” የማለት ግዴታ
የለባቸውም። የጎሳዊውን አቀራረጽ ከተቀበልን ( የተገኙ ዲሞክራሳዊ ድሎችን፤ ለምሳሌ የመሬት ላራሹን፤ የባህል፤ ቋንቋ፤ ታሪክ
እኩልነትን ወዘተ ተቀብለን)፤ ዛሬ ወሳኙ ክልልና ጎሳዊ ማንነት እንጂ ኢትዮጱያና ኢትዮጵያዊነት አይደሉም። ሌላው ቀርቶ፤ በነጻና
በድሎት በምእራብ አገሮች የምንኖረው ስደተኞች በኃይማኖት፤ በፀሎት ቤቶች፤ በሞያዎች፤ በምግብ ቤቶች ወዘተ የተሰበሰብነውና
የምንሰበሰበው ጎሳዊና መንደራዊ በሆነ አወቃቀር ነው። አንዱ ከሌላው ጋር የመወያየት፤ አንዱ ከሌላው የመማር፤ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች
ዙሪያ ከብሄር፤ ብሄረሰብና ኃይማኖት ባሻገር በጋራ የመወያየትና ገንቢ ዓማራጮች የማቅረብ ልምድ ጠፍተዋል። ህወሓትና ተባባሪዎቹ
ከስራ ላይ ያዋሉት መርህ የምንጋራው ታሪክ፤ ልምድና ባህል የለም የሚል መልእክት የሚሰጥ ክስተት ነው። ከላይ እንዳሳየሁት፤
ዓባይን ለመታደግ ጭምር፤ የጋራ ታሪክ፤ ባህልና ልምድ ለኢትዮጵያና ለሕብረተሰቧ የወደፊት ታላቅነት ወሳኝ ነው።
የኢትዮጵያ ተከታታይ የሆነ የማይካድ ታሪክ የአንድ ብሄር ወይንም ኃይማኖት ትግል ውጤት አይደለም። በተለያዩ ቀውጢ ወቅቶች
ማንም ሳይስገድዳቸው፤ ለሃገራቸውና ለራሳቸው ክብር ሲሉ የሞቱላት ቁጥር በሚሊዮኖች ይታሰባል። ከሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰቦችና
እምነቶች የተወጣጡ ጀግኖች መስዋእት እንደሆኑላት የኢትዮጵያና የውጭ አገር የታሪክ በላሞያዎች በማስረጃ አቅርበውታል። ጥቂቶቹን
በክፍል ሁለት አቅርቤአለሁ። የጎሰኞች የታሪክ ብረዛ ለሁሉም አደገኛ ደረጃ ይዞ ወጣቱን ትውልድ የተያያዘ ታሪክ እንደሌለውና እርስ
በርሱ ‘እንዲፋጭ’ ከመጋበዙና ከማመቻቸቱ በፊት ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚወክሏቸው ተቋሞችና ጀግኖች ከሚለያዩአቸው ያይሉ
ነበር። አገር ወዳዱና ለሃቅ የሚሟገተው አኩሪ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የአባቶች ስንብት” በሚል ወቅታዊ አርእስትና
ትንተና ላሰበበትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ለሚጨነቅ አግባብ አለው። እንዳሳሰብኩት፤ ዛሬ ታላቅ፤ ሃብታምና ዘመናዊ ናቸው ብለን
የተሰደድንባቸውና ወጣቱ ትውልድ የሚሰደድባቸው አገሮች ኢትዮጵያ የሄደችበትን ውጣ ውረድ መንገድ ሂደውበታል። እነዚህ አገሮች
ከኢትዮጵያ ያላነሰ እልቂት ተካሂዶባቸዋል። መሪዎቻቸው ያተኮሩት በእርስ በርስ መወነጃጀልና ለእልቂት በሚዳርግ መወነጃጀል
አልነበረም። ይህ ቢሆን ኑሮ የምናደንቃት አሜሪካ የዓለም ኢኮኖሚና የጦር ኃይል መሪ አትሆንም ነበር። በብዙ የእርስ በርስ ጦርነት
ያለፈችውና ዛሬም ከፍተኛ ውጥረት የገጠማት ናይጀሪያ ደቡብ አፍሪካን ቀድማ (በጠቅላላ ገቢ ሲመነዘር) የአፍሪካ የኢኮኖሚ መሪ
ሆናለች ባልተባለችም ነበር። ሁለቱም አገሮች ታሪካችውን አልበረዙም። ታሪክ የሌለው ሕዝብ የሚጎዳው የተከታታይ ትውልድን የጋራ
ደህንነትና ብልፅግና መሆኑን ተገንዝበዋል። የማሳስበው ከእነዚህም ልምድ እንድንማር ነው።
“በርካታ አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች እና የማንነት ጭፍለቃዎች የማንክደው የታሪካችን አካል ቢሆንም፤ ሃገር በመታደግ ዘመቻው በመሰለፍ
ዛሬ ኢትዮጵያንን-ኢትዮጵያ ያደረጉት፤ (እኛን “ዜግነታችን ኢትዮጵያዊ” ነው ለማለት ያበቁን፤ የኒ ጭማሬ) ከራስ አሉላ አባነጋ እስከ
ራስ ጎበና ዳጩ፤ ከፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ እስከ ፊታውራሪ ገበየሁ፤ ከራስ መኮንን እስከ አሚር አብዱላሂ፤ ከደጃዝማች
ባልቻ ሰፎ እስከ ራስ መንገሻ ዮኃንስ…በአድዋ የፈጸሙት አኩሪ ጀብዱ ነው። በአናቱም እነዚህን ጀግና አባቶች ለአንድ ዓላማ አንድ
ግንባር ያዋላቸው ሃገራዊ አጀንዳ እንጂ፤ ንጉሳዊ ፍቅር ወይንም አድርባይነት አለመሆኑ ከማናችንም ባይሰወርም፤ በህወሓት የኑፋቄ
ስብከት ተነድተን በአንድነት የሚያቆሙንን መስተጋብሮች አፍርሰን፤ የተናጥል ማንነት የምንሻ ከሆነ፤ አባቶቻችንን አሰናብተን፤ አዲስ
ማንነት ፈጥረን ወደ ገደሉ አፋፍ መገፋታችን የጊዜ ጉዳይ ከመሆን የሚታደገው አለመኖሩን ማስታወስ እወዳለሁ” በማለት ከፊታችን
የምናየውን ለሁሉም አደጋ ፈጣሪና ኢትዮጵያን እንዳልነበረች የሚበታትን ሁኔት በግልፅ አስቀምጦታል። ይህ እንደ ግብፅ ላሉ
የኢትዮጵያን ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት፤ የመላው ሕዝቧን በሕግ የተረጋገጠ እኩልነት ለማይፈልጉ ኃይሎች ሁሉ ሳይዋጉ በረከት
ይሰጣቸዋል የሚል ግምት አለኝ። በኤርትራ እንደታየው፤ የኢትዮጵያውያን የእርስ በርስ ግጭት ስኬታማ ሲሆን የሚጎዳው ማን
ይሆናል ብለን ብንጠይቅ መልሱ ቀላል ነው። የሚጎዳው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። ለምሳሌ፤ ህወሓት የፈጠረው ስርዓት የእርስ በርስ
ጦርነት ቢያስከትል የማይረሳና የማይቆም ግጭት ይፈጥራል። ዛሬ በዩክሬን የምናየው በኢትዮጵያም እንደሚሆን አልጠራጠርም።
ስለዚህ፤ መፍትሄውን የምንፈልግበት ወቅት ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም እላለሁ። የዲሞክራሲ ማእከል አጀንዳ መቅረፅ ከሚመጣ ችግር
ሊያድነን ይችላል የሚል ግምት አለኝ። የዲሞክራሳዊ ስርዓት አማራጭ ትግል የሁሉም ትግል መሆን አለበት እላለሁ። እሁሉም በላይ የሚጎዳው ከሁሉም ብሄር፤ ብሄረሰብና ኃይማኖት የተወጣጣው ከስድሳ በመቶ በላይ የሚገመተው በደርግ ጊዜና ከደርግ
በኋላ የተወለደው ወጣቱ ትውልድ ይሆናል። ዛሬ ከሃገሩና ከቤተሰቡ ተለይቶ በበረሃ፤ በውቅያኖስና በአረብ አገሮች የሚሰቃየው፤
የሚሞተው ለመስራት፤ ለመፍጠር፤ ለማምረት የሚችለው አማራ፤ አፋር፤ ኦሮሞ፤ ጉራጌ፤ ሶማሌ፤ ትግሬ ወዘተ ትውልድ ነው።
በማፈንና በስደት ስሌት ሲታይ ስርዓቱ ጎሳ፤ ፆታ፤ እድሜና ኃይማኖት አይለይም። ወጣቱ ትውልድ እውቀት አለው። ስርዓቱ
“በፈጠረልን የጥላቻ ወጥመድ ገብተን እርስ በርሳችን እንጨራረስ የሚል ጤነኛ ሰው ያለ አይመስለኝም። ብንሰደድም ምንም አይደል፤
የቀረው ያልፍለታል” የሚል ግለሰብ ያለ አይመስለኝም። እርስ በርሱ የመወያየት እድል ቢኖረው ወጣቱ ትውልድ በራሱ ላይ
አይፈርድም የሚል እምነት አለኝ። እየቆየ የሚከሰተው ሃቅ ወጣቱ ትውልድ እርስ በርሱ እንዳይተማመን፤ እርስ በርሱ ተደጋግፎ
ፍትሃዊና ዲሞክራሳዊ መንግሥት እንዳይመሰርት የፈረዱበትና ለአደጋ ያመቻቹት የህወሓትና ጥገኛ የጎሳ መሪዎች ናቸው። ሆኖም፤ ቀስ
በቀስ ወጣቱ ትውልድ የጎሳ ክፍፍልንና የማይታረቁ ልዩነቶችን አጋነው ለስልጣንና ለግል ኃብት ማካበቻ እንዲሆኑ ያደረጉና የሚያደርጉ
ከፋፋይና በታኝ ኃይሎች መሆናቸውን እየተገነዘበ ሄዷል። ወጣቱ ትውልድ እንዲገነዘበው የምመኘው የፍትሓዊ ለውጥ ኃይሎች ሁሉ
ኢላማቸው መብታችውን ከገፈፈው ፓርቲና ከስርዓቱ ላይ እንዲሆን ነው። የስርዓቱን እድሜ ያራዘመው የኢህአዴግ ፍትሃዊ አገዛዝ
አይደለም። የሌሎቻችን መበታተን፤ አለመተማመን፤ አለመከባበርና አለመደጋገፍ ነው። ህወሓት ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የበለጠ
የመበታተን፤ ሰርጎ የመግባት፤ የመደለል፤ የማስፈራራት እውቀትና ሃብት አለው። ይህ ጥንካሬ ከሕዝቡ ጥንካሬና ኃይል አይበልጥም።
የጋምቤላ፤ የኦጋዴን፤ የኦሞ ሸለቆ፤ የአማራ፤ የአፋር፤ የኦሮሞ ወዘተ ሕዝብ በተናጠል ሲጨፈጨፍ “ነግ በኔ” ብለን ለማውገዝ
አልቻልንም። ተራችን የምንጠብቅ እንመስላለን። ህወሓት እኛን እርስ በርሳችን አባልቶ ይገዛል፤ ራሱን እንድንመስል አድሮጎናል። ጠብ
ጫሪው ሌላ ነው እያለ ራሱን ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚል ቡድን ነው። ሌላው ቀርቶ፤ የመንፈሳዊ ተቋሞችን የፖለቲካ ስልጣን መጠቀሚያ
አድርጓቸዋል። የመንፈሳዊ አባቶች እርስ በርሳቸው ጠላትነት ሲፈጥሩና ምእመናንን ጎጠኛና መንደረኛ ሲያደርጉ የሞራል ድክመት የት
እንደደረሰ ለመገንዘብ ቀላል ነው። በተመስገን ደሳለኝ አባባል፤ “ኢህአዴግ ያለፉትን ሁለት አስርታት ያለመንገራገጭ ማለፍ የቻለው
በጠብ-መንጃ፤ እንደ አሸን በፈሉ ሰላዮች፤ እንዲሁም ከሊቅ እስከ ደቂቅ፤ ከኃይማኖታዊ እስከ ዓለማዊ ማሕበራት ውስጥ በዘረጋው
የካድሬ ጥርነፋ ብቻ ሳይሆን፤ ለርእዩተ ዓለሙ ሳጋና-ማገር ያደረገው የሃገሪቱን ታሪክ ከልሶ፤ ደልዞ እና ፈጠራ አክሎበት በመስበክም
ጭምር መሆኑ በግላጭ የሚታይ እውነት ነው።” ለመጨመር የምፈልገው ህወሓት ሆነ ብሎ ሥስታምነትን እንደመመሪያ መፍጠሩን፤
እኛ በኢትዮጵያዊነታችን ሳይሆን በጎሳዎቻችን እንድናምንና በተናጥል እንድንታገል ማድረጉን ነው። ወደማይፈለገው ዝቅተኛ የትግል
መሰብሰቢያ ደረጃ ወስዶናል ማለት ነው። የእኛ ሰብሳቢ መመሪያ ጎሰኛነት ከሆነ ከምንቃወመው ከህወሓት ዓመራር የሚለየን ምን
እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። በጎሰኛነት ፖለቲካ ወጥመድ ተይዞ የጎሰኛነት አገዛዝ ይውደም ሲባል አማራጩ ምን አይነት ስርዓት
እንደሚሆን ለማወቅ ልዩ ጥበበኛ መሆን ያስፈልግ ይመስለኛል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብትና ክብር አለው። ይህ መብት
አማራ፤ አፋር፤ ጉራጌ፤ ወላይታ፤ ኦሮም፤ ሶማሌ፤ አኟክ ወዘተ አይለይም። ካልለየ፤ አግባብና የሚያዋጣው፤ የዓለምና የኢትዮጵያ ሕዝብ
የሚቀበለው የትግል መንገድ በኢትዮጵያዊነታችን በአንድ ላይ ለፍትፍ-ርትአ፤ ለእውነተኛ እኩልነት፤ ለዲሞክራሲ በጋራ መታገል ብቻ
ነው። ይኼን ካላደረግን በራሳችንና እነወክለዋለን በምንለው ሕዝብ ላይ ፈረድን ማለት ነው። በቅርቡ የኦባማ መንግሥት ለአንድ
የታወቀ ኢትዮጵያዊ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የነገረው፤ “እናንት ኢትዮጵያን በአንድ ላይ፤ በአንድ ድምፅ ለመናገር እስካልቻላችሁ ድረስ
አዳማጭ የላችሁም” ነው። ይኼን መሳይ መልእክት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከአሜሪካ፤ ከካናዳ፤ ከአውሮፓ የጋራ ማህበር ወዘተ
ሰምተናል። እኛ ህወሓትን እንወቅሳለን እንጂ ችግሩም፤ መፍትሄውም በእኛው እጅ ነው።
የህወሓት ዓመራር ከፋፋይ ብቻ ሳይሆን የማባበል ችሎታ ያለው ነው። በቁሳቁስ ማባበል ታማኝነት የሚገዛ መሆኑን ስላወቀ፤
ስደተኛውን ጭምር አባብሎ የከተማ መሬት ፈቃድ ሰጥቶ ኪራይ ይሰበስባል። ገንዘብ ያለውን ስደተኛ በከተማ መሬት ብቻ ሳይሆን፤
በንግድና በቤት ግንባታ ፈቃድ አባብሎ ደጋፊው አድርጓል። የኢትዮጵያ እድገት አድናቂ ከሆኑት ተመልካቾች መካከል ስደተኛው
የመጀመሪያውን ደረጃ ይዟል። ከአገሪቱና ከአብዛኛው ወጣት ትውልድ ደህንነትና ውርደት የበለጠ የራሱና የቤተሰቡ ኑሮ መሻሻል
ይገዛዋል። ህወሓት ሰላዮችን በተቃዋሚው ስብስቦች ሰርጎ የማስገባት ችሎታ አለው። በውጭ አገሮች በሰላማዊ ሰልፎች፤ በፓልቶኮች፤
በመገናኛ ብዙሃን፤ በቤተክርስትያን፤ በመስጊድ ወዘተ ቀድመው ህወሓትን የሚያወግዙ የህወሓት ሰላዮች መሆናቸውን ብዙ ታዛቢዎች
ያውቃሉ። ሆኖም መንጥረው ለማጋለጥ አልቻሉም። ሌላው ቀርቶ የራሳችን ስብስቦች ለመቆጣጠር አለመቻላችን የሚያሳየው
የዲስፕሊን ጉድለትን ጭምር ነው። ተቃዋሚዎች ለዚህ ሰርጎ ገብነት መፍትሄ ማግኘት አለባቸው። ህወሓትን የሚደግፈው ክፍል
ከአምስት በመቶ በላይ የሚሆን አይመስለኝም። ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆነው የት ሔደ???
የተወሰኑ ስግብግቦችንና የጥቅም ሰዎችን፤ በተለይ ወጣቶችን፤ ማባበልና መግዛት እስከተወሰነ ደረጃና ወቅት ያገለግላል። በተመሳሳይ፤
እሰከተወሰነ ጊዜ ወጣቱን ትውልድ ሰላይ ማድረግ ሕብረተሰቡን ለመከፋፈልና ለማሳፈራራት ይረዳል። ሆኖም፤ ሁሉም ወጣቶች
ሰላይ፤ ካድሬና ሃብታም ሊሆኑ አይችሉም፤ አይደሉም። የዛሬ ሰላዮች የነገ የህብረተሰብ ወገኖች የማይሆኑበት ሕግ የለም። ሁሉም
ወጣቶች የኢትዮጵያን እውነተኛ ታሪክ፤ የብሄር/ብሄረሰቦችን ታሪክ የመዘገበው ትሥስር አያውቁም ለማለት አንችልም። እውቀትን
የሚፈልግ ወጣት የሃገሩን ታሪክ እንደማንም ፈልጎ ያውቃል። ህወሓት ወጣቱን ትውልድ የታሪክ ደንቆሮ አድርጎ ለመቆየት አይችልም።
ታሪክ ለመቅበር ዘላለማዊነት ያስፈልጋል። አገዛዝ ዘላለማዊ የሆነበት አገር የለም። መለወጡ አይቀርም። ከጎሳ በላይ በአንድነት
ለዲሞክራሳዊ ስርዓት መነሳት ቀስቃሽ እንደሚሆን አልጠራጠርም። የፖለቲካ ልሂቅን ሚናም ይኼው ይመስለኛል። ወጣቱ ትውልድ
ደንቆሮ አይደለም። ከፍርሃት ዓለም እየወጣ ነው። ለራሱ የወደፊት እድል እየተቆጨ እንደሚሄድ አምናለሁ። የሁሉም የፖለቲካ
ስብስቦች ልሂቃን ሃላፊነት ይኼ ትኩስ ወጣት ኃይል ገንቢና ሁሉን ኢትዮጵያውያን ወደሚያስተናግድ ዲሞክራሳዊ አማራጭ
እንዲያዘነብል ማበረታት ይመስለኛል። ቤተክርስቲያን ወይንም መስጊድ የሚያዘወትር ወጣት ከፀሎቱ ባሻገር ስለ እምነቱ ለማወቅ ይጣጣራል፤ እውቀቱ እየጠነከረ ይሄዳል።
እውቀት እንደ ተስቦ በሽታ ነው። አንዱ ወደ ሌላው ይመራል፤ ይዛመታል። በማውቀው ልቆጠብና ስለታቦት ምንንነት ባጭሩ ላቅርብ።
የታወቀው የኢትዮ-ኢዝራኤል የቆየ ግንኙነት ደራሲ “The Sign and the Seal—the quest for the Ark of the Covenant,”
ግራሃም ሃንኮክ የኢትዮጵያን ጥንታዊትነት፤ የክርስትና ኃይማኖት ጥንታዊ መንስኤ መሆንና የእስልምናን ኃይማኖት ማስተናገድ፤
የኢትዮጵያንና የኢዝራኤልን ግንኙነት ጥንታዊነት፤ የዓባይን ማእከላዊነት በማስረጃ አቅርቦታል። ቁም ነገሩ ኢትዮጵያ ጥንታዊ መሆኗን
ሲጠቅስ እንዲህ ብሏል። “ብሉይ ኪዳንም ሆነ አዲስ ኪዳንን ያስተናገደች ኢትዮጵያ ለአይሁዶች ሁለተኛ አገርና መጠጊያ” እንደነበረች
ነው። የኢዝራኤላውያን አባትና መሪ የነበረው ሙሴ “ኢትዮጵያዊት ሚስት አግብቶ በኢትዮጵያ መኖሩን አረጋግጧል። ከክርስቶስ በፊት በ
470 ዓም (የጣና ማርቆስ አባቶች በፃፉት መሰረት) የኢስራኤሎች መታወቂያ የሆነው “ታቦት/ጽላት ሙሴ” (Ark) ከኢየሩሳሌም ወጥቶ
ኢትዮጵያ እንደገባ ሃንኮክ ተዘዋውሮ ባገኘው መረጃ አረጋግጧል ይላል። ከዚህ የተማርኩት ትችት፤ በመፅሃፍ ቅዱስ፤ በኮራን፤ በጥናትና
በልምድ የተገኘ ሂደት በማያሻማ ሁኔታ የሚያረጋግጠው የኢትዮጵያን ታሪክ ተከታታይነትና የዓባይን ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ ተከታታይነት ሲባል አንድ ወጥ፤ ላይና ታች የሌለበትና የረጋ ሕብረተሰብ ማለት አይደለም። ኢስራኤላውያን ለሁለት ሽህ
ዓመታት ተበታትነው ነበር። ተስፋ ሳይቆርጡ ታግለውና በምእራብ አገሮች ተደግፈው አዲሲቱን ኢስራኤል መስርተዋል። ኢትዮጵያ
ጥንታዊ ብትሆንም አንድ ወጥ (homogeneous) ሕዝብ የላትም። አስደናቂ አገር አድርጎ የሚለያት ይኼ የሕብና የእመነት ስርጭት
ጭምር ነው። የኢትዮጵያ የሕዝብ ስርጭት፤ የባህል፤ የንግድ፤ የመንፈሳዊ፤ የጆግራፊና ሌሎች ግንኙነቶችን ያሳያል። የኦሮሞ ሕዝብ
የማህል አገሩን አቋርጦ ወደ ምእራብ፤ ወደ ሰመኔንና ወደ ምስራቅ እንደተስፋፋ ታሪክ ያስተምረናል። የትግራይ ሕዝብ ከአክሱም በኋላ
በመላው ኢትዮጵያ ተስራጭቷል። አማራውም እንደዚሁ። ማንኛውም ስብጥር ሕዝብ ከአንዱ ወደሌላው ክፍል ሲሄድ በአዲሱ ቦታ ካሉ
ሕዝቦች ጋር ይቀላቀላል። እኛ ስደተኞች ተሰደን እንደ ደሴት ለብቻችን አንኖርም። እንቀላቀላለን፤ መብት አለን። ጥልቀት ጥናት ያካሄዱ
ባለሞያዎች የሚያስተምሩን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደዛሬው “በክልል ከዚህ ወዲያ አታልፉም” ያላቸው እንዳልነበረ ነው።
ከህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት በፊት ኢትዮጵያውያን እንደፈለጉት በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል የመኖር መብት ነበራቸው።
“እትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ ኢትዮጵያዊ ነው” ይሉ ነበር ማለት ነው። የሃሳብ፤ የፖለቲካና የእምነት ልሂቃን ይኼን የሕዝብ ትሥስር
ለወጣቱ ትውልድ ማስተማር ግዴታችን ነው። እኛ ከማናውቀው ሕዝብ ጋር ለመኖር ከቻልን፤ ከምናውቃቸው ወገኖቻችን ጋር ለመኖር
እንችላለን የሚል እምነት አለኝ። ይኼን ፈረንጆች እስከሚነግሩን መቆየት አሳፋሪ ሆኖ አገኘዋለሁ።
አባይ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መመኪያና መጠቀሚያ መሆን አለበት የምለው ከዚህ የታሪክ ሂደት በመነሳት ጭምር ነው። እስራኤሎች
ኢትዮጵያ የልዩ ልዩ ብሄር/ብሄረሰቦችና ኃይማኖቶች አገር መሆኗን ይቀበላሉ። ጥናቶች የሚያሳዩት አብዛኛዎቹ እስራኤሎች ኢትዮጵያ
ዓባይን የመጠቀም መብት እንዳላት ያምናሉ። ስለሆነም፤ አንዳንድ ተመልካቾች ኢትዮጵያን የሚጠቅማት ከእስራኤል ጋር ያላትን
ተከታታይ ግንኙነት ማጠናከር ነው ይላሉ። ይኼን ብንቀበል፤ ባንቀበል ኢስራኤል እንደሌሎች አገሮች ለማስከበር የምትፈልገው የራሷን
ደህንነትና ጥቅም መሆኑን መርሳት የለብንም። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን መመካት ያለባቸው በራሳቸው ላይ ነው። ከተከፋፈሉ
አይችሉም። ከሁሉም በላይ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚጠቅመው ጎዳና የአሁኑ አፋኝና ክልላዊ (አግላይ) ስርዓት ሕዝብን በሚወክል፤
በሕግ የበላይነት በሚያምን፤ የሕዝብ ተሳትፎና እኩልነት በሚቀበል፤ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥቅምና አገልግሎችት ሙሉ በሙሉ
የሚቆም ዲሞክራሳዊ ስርዓት ሲተካ ብቻ ነው። የፈለገው የውጭ እርዳታና ድጋፍ ቢገኝ፤ የፈለገው በያመቱ እጥፍ እድገት አለ ቢባል፤
የፈለገው ዲያስፖራ ቤት ቢሰራና የውጭ ምንዛሬ ቢልክ (አብዛኛው ውጭ ባንኮች ይቀራል) የሕብረተሰብን መተባብር፤ ጥንክርናና
የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት ሊተካ አይችልም። በራስ መተማመን ወሳኝ ነው። በራስ ለመተማመን የትምሕርት አቀራረፅና አመራር ወሳኝ
መሆኑን በክፍል ሁለት አሳይቻለሁ። ፖለቲካዊ ትምሕርት በራስ መተማመንን ተቀዳሚ አያደርግም። ጥገኛነትን ያጠናክራል። የእስራኤል
ጥንክርና ከህብረተሰቡ አንድነትና ራስን የመቻል ጥረት ጋር የተቆራኘ ነው። እስራኤል በአረቦች የተከበበች አገር ብትሆንም፤ የራሷ
ጥንካሬና የምእራብ አገሮች ድጋፍ የማትደፈር አገር አድርጓታል። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን እንደ እስራኤልና ኢስራኤላውያን
አይደሉም። አስተማማኝ የሆነ የሚመኩበት አገር የለም። ባለፈው ታሪካቸው እንዳሳዩት ሁሉ በራሳቸው መመካት አስፈላጊ
ይመስለኛል። ታሪክን መቀበል ወሳኝ የሚሆነው ለዚህ ጭምር ነው።
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ተከታታይ የሆነ፤ ለህብረ-ብሄር ግንኙነት መሰረት የሚሆን
ሂደት አልነበረም ሲሉ የሚያንፀባርቁት የውጭ አገር ሊቃውንትንና የጎሰኛውን ህወሓት እሴት ነው። “የጥቁር አቴና” ደራሲው በርናል
“የግብፅ ስልጣኔ የአባይ ወንዝ ውጤት ብቻ አይደለም…..የኢትዮጵያውያንና የሌሎች ጥቁር አፍሪካውያን በረከት ጭምር መሆኑ በባህል፤
በኢኮኖሚ፤ በግዙፍ ስራዎች ወዘተ ይታያል” ብሏላ። ኢትዮጵያ ግብፅን ገዝታ ነበር። ኢትዮጵያ ከግብፅ ያላነሰ ታሪክና ስልጣኔ አላት።
ለግብፅ አበርክታለች። በአይኔ ያየሁት፤ አስዋን ግድብ ላይ የተሰራው ታላቅ ሙዚየም የጥቁር ሕዝቦች አስተዋፆ እንዳለበት ምስክር ነው።
ይኼን ሃቅ በጥናት ተደግፎ ያሰመረው በርናል እንዲህ ብሏል። “የአውሮፓውያንና የአረቦች ዘረኛነት መሰረታዊ ዓላማ እንዳለው
አያከራክርም…. አንድ አፍሪካዊ (ኢትዮጵያዊ) ንጉሥ ወታደሩን ከኢትዮጵያ ይዞ ወደ ግብፅ፤ ወደ መካከለኛው ምስራቅ (Asia Minor)
እና በግብፅና በመከካለኛው ምስራቅ አድርጎ ወደ አውሮፓ መሄዱ እየታወቀ ይኼን ታሪክ የመዘገበውን የጥቁር አፍሪካ አስተዋጾ ሃቅ
እንደሌለ ማቅረባቸው ለህሊናው ለሚገዛ ሰው የሚታሰብ ሆኖ አላገኘውም።” እርሱ አልተቀበለውም። እነዚህና ሌሎች አስተዋፆዎች
የኢትዮጵያ ታላቅነት መስታወቶች ናቸው። የታሪክ ታላቅነት ያለው አገርና ህብረተሰብ ራሱን አድሶ የዘመናዊ ኢኮኖሚ መስርቶ ታላቅ ማህበረሰብና ታላቅ አገር ለመገንባት እንደሚችል ምንም አልጠራጠርም። ይችላል። ቻይናዎች እያደረጉት ነው። ጃፓኒዎችና ኮሪያኖች
አድርገውታል ወዘተ። የኢትዮጵያ የትምሕርት ሂደት ለራሴና ለተከታታይ ትውልድ የራሳችን የሚኮራ ታሪክ፤ ባህልና ልምዶች እንድናውቅ
አላደረገም። ህወሓት ፈጽሞ አውድሞታል። ግብጾች በፖለቲካ ቢለያዩም የግብፅን ታሪክ፤ የግብፅን “የዓባይ ባለቤትነት፤ ማለትም
ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መብት)፤ የጥቁር አፍሪካን ኋላ ቀርነት ለተከታታይ ትውልድ አስተምረዋል። አሁንም ያምኑበታል። ያስተምራሉ።
ትምሕርት ለሕዝብ መተዋወቅና ግንኙነት ወሳኝ ነው። ለዚህ ነው ማንኛውም አገር በአብዛኛው ወሳኝ የሆኑ የትምሕርት ግብአቶችን
ብሄራዊ የሚያደርጉት። የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ የሕዝብ መቆራኘት ወሳኝነት አያምንም። ወጣቱን ትውልድ የሚያስተምረው ወደ
“ጎሳው ገብቶ” የጥላቻ ቀንበር እንዲሸከም ነው። በነጻነት የምንኖርና ነጻነትንና ፍትህን የምንፈልግ ሁሉ፤ “ኢትዮጵያ ሃገሬ ናት፤ ዜግነቴ
ኢትዮጵያዊ ነው” ለማለት እስካልደፈርንና አብረን እስካልተሰለፍን ድረስ በአምባገነናዊ አገዛዝ አዙሪኝ እንደምንሺከረከር ማጤን
አስፈላጊ ነው። ስርዓቱ የፈጠረውን የብሄር/ብሄረሰብ መለያዎች አወቃቀርና መፈክሮች አንግበን ዲሞክራሳዊ ስርዓት ለመመስረት
አንችልም። በልዩነተቻችን እስከተሰበሰን ድረስ ተጠቃሚው የህወሓት “ስልጣን ወይም ሞት” አርማና የአገዛዝ ስልት ሆኖ እንደሚቆይ
አያከራክርም። የዓባይ ግድብ መሪ ተጠቃሚ የሚሆነው ይኼው ቡድን ይሆናል ማለት ነው።
ማጠቃለያ
ኢትዮጵያ የዓባይን የተፈጥሮ ሃብቷን ለራሷ ሕዝብ ኑሮ ለመሻሻልና ድህነትን ለመቀነስ፤ የዘመናዊ ኢንዱስትሪን ለማስፋፋትና የምግብ
ዋስትናን ስኬታማ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት መደገፍ አግባብ እንዳለው በተከታታይ አሳስቢያለሁ። ይኼን ተከታታይ የኢትዮጵያ
መንግሥታት ስኬታማ ለማድረግ የሞከሩትን ግዙፍ የሆነውን የዓባይን የዘመናዊነት ልማት ፖሊሲ የግብፅ መንግሥትና ተባባሪዎች
እንዳይሳካ ለማድረግ እንደሚሞክሩ ይጠበቃል። በታሪኩ ደጋግሞ እንዳሳየው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱ ተከብሮ በአንድ ላይ የጋራ
ጥቅሙን ለማስከበር ከተነሳ ምንም ኃይል ሊያቆመውና ሊገታው እንደማይችል እምነት አለኝ። ይህ ሃሳብ መንታ መንገድ ነው ብየ
ከጀመርኩት ሁለተኛ ዘርፍ ይወስደኛል። ይኼም የስርዓቱ ጎሳ-ተከል ከፋፋይነት ጉዳትና፤ የዲሞክራሳዊ ስርዓት አስፈላጊነት ዓላም
የአመራር ክፍተት ነው።
ባለፉት ሃያ ሶስት ዓመታት ህወሓት በበላይነት ለመግዛት የቻለው “ለጭቁን ሕዝቦች” ፍትህ ስለቆመና በድርጊት ጥቅሞችን ስላሳየ
አይመስለኝም። እኛ ስለተከፋፈልን ነው። መንግሥት፤ በልማት ስም፤ የጋምቤላን፤ የኦሞ ሸለቆን፤ የኦሮሞን፤ የአፋርን ወዘተ ሕዝብ
ከመሬቱ እያባረረና እየጨፈጨፈ ለጭቁኖች ቁሜአለሁ ለማለት የማይችል መሆኑን ማስረጃዎች ተጠቅመን በአንድ ድምፅ ለማጋለጥና
ድምፃችን ለማሰማት አልቻልነም። የኦሮሞን ወጣት እየጨፈጨፈ ለጭቁኖች መብት ለመቆም አትችልም ብለን በአንድ ላይ ለማውገዝ
አልቻልነም። የአማራን ድሃ ገበሬ ሕዝብ ከቤቱና ከመሬቱ በቀጥታም ሆነ በተወካዮች አማካይነት እያባረረ፤ አማራውን በገደል
እየወረወረና እየረሸነ፤ የምትኖርበት “ክልልህ አይደለም” ሲል በአንድ ላይ ሆነን እነዚህ ወገኖችህ ናቸው ለማለት አልቻልነም።
የትግራይን ሕዝብ ዲሞክራሳዊ መብት እያፈነ ለዲሞክራሲ ቁሜአለሁ ሲል በአንድ ላይ ሆነን መብታቸውን በመደገፍ ድምጻችን
አላሰማነም። የአፋር፤ የቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ የኦሞ ሸለቆ፤ የኦጋዴን፤ የኦሮሚያ፤ የጋምቤላ ሕዝብ የተፈጥሮ ኃብት ለውጭና ለምርጥ
የውስጥ ለኢንቬስተሮች ሲቸረቸርና ነዋሪዎች ከቀያቸው ሲባረሩ በአንድ ድምፅ መብታቸው ይከበር አላልነም። የዓባይ ግድብ መገንባት
የኢትዮጵያ መብት መሆኑን ተቀብለን በአንድ ድምፅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ የሚፈልገው ግድቡን ብቻ አይደለም። በተመሳሳይ
ሳይሆን፤ በመጀመሪያ ደረጃ ሕዝቡ የሚፈልገው፤ ሰብአዊ መብቱ መከበሩን ነው። ተቀዳሚውና ዋናው የሕዝብ ጥያቄ ይኼው ነው
እያልን አልተሟገትነም። የአሜሪካ መንግሥትና ሌሎች እርዳታ አበርካቾች የሚከተሉት ፖሊሲ ከቀጠለ “ከሁሉም ያጣ ጎመን”
እንደሚሆኑ በጥናትና ምርምር ተደግፈን በአንድ ድምፅ አቤቱታችን ለማሰማት አልቻልነም። ለአምባገነናዊው ህወሓት እርዳታ ሰጥቶ
ለሰብአዊ መብቶች መገፈፍ አጋር መሆን እርጋታን ለማረጋገጥና ከሽብርተኛነት ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አያስችልም
የምንልበት ወቅት አሁን ነው። የሚያዋጣው ሁሉን አቀፍ፤ ፍትሃዊና ዲሞክራሳዊ ስርዓት እንዲፈጠር መደገፍ ነው ብለን በመተባበር
ከተነሳን አዳማጭ እንደምናገኝ አልጠራጠርም።
ባጭሩ፤ ዓባይን ለመታደግ፤ የግድቡን ፍሬ ለመካፈልና ስርዓቱን ለመለወጥ ከተፈለገ፤ በጎሳ፤ በኃይማኖት፤ በሃብት፤ በስልጣን ወዘተ
መከፋፈላችን ለምንፈልገው ዓላማ ማነቆ መሆኑን መቀበል አለብን። ስለሆነም፤ ግብፆችን “ኢትዮጵያን አትንኩ” ብለን ህወሓትን አፋኝ
አገዛዝክን ቀጥል ማለት ሃላፊነት የጎደለው ትችት ነው። “ሕዝብን እየከፋፈለህ የምትጨፈጭፍበት ወቅት ያቁም፤ መከፋፈልን
አንቀበልም” ብለን በአንድ ላይ ለሁሉም ኢትዮጱያውያን ፍትህ፤ ሰብአዊ መብት፤ ዲሞክራሳዊ መንግሥት የምንታገልበት ወቅት አሁን
ነው እላለሁ። በተናጥል ታግለን የትም አንደርስም። የግብፅ መንግሥትና ህወሓት የሚፈልጉት የእኛን በጎሳ፤ በኃይማኖትና በስልጣን
መከፋፈል፤ የእኛን እልቂት መሆኑን በተደጋጋሚ ለማሳየት ሞክሬያለሁ።
ይቀጥላል
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.