Showing posts with label ኢቲዮ ባሕል. Show all posts
Showing posts with label ኢቲዮ ባሕል. Show all posts

Saturday, January 18, 2014

ቴዲ አፍሮ የቅኔ ዕንቡጥ – ለእናቱ ልዩ ዓርማ ነው!


ከሥርጉተ ሥላሴ 16.01.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)
“የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል እግዚአብሄር፤ ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ (ምሳሌ ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 )
የሀገሬን ክብር አዝልቀህ – ልታደምቅ ታጥቀህ ተነስተኃል – አንተ የቅኝት ብርቅ፤ ራዕይ — አብነት። እማን ከፍ አድርገህ ልታሸልማተኝ ጌጥ ዕውቅናዋ ፈክቶ ዓለምን ልትመስጥ። ተግተህ ትሠራለህ – አንተ የቅኔ ዕንቡጥ፤ የነፃነት ቃና – የትውልዳችን – ፈርጥ!
ባልባለቀው መንፈሴ – ቴዴ አፍሮ የተስፋዬ ፀሐይ ነው። ማህተም አለበት! teddy afro
ዋና በር … ከሳቢያ ጥረት ምክንያታዊ፤ ከሳቢያ ተኮር ድካምም ምክንያታዊ ተግባራት የድል ዋዜማ ናቸው። ምክንያቱም የችግሩን ምንጭ ከሥሩ የሚያደርቀው በምክንያታዊና መሬት በረገጠ ተግባር ብቻ ጨለማው ነግቶ፤ የምሥራች ለነፃነት የመሸለም ስበታቸው ሆነ አስገዳጅነታቸው ጉልበታም ናቸው። የሚያስቀሩት ፍርፋሪ ስለማይኖርም ዘላቂ ድህነት ያስገኛሉ። የመፍትሄ መንገድ ጠራጊ የችግሩን ሳቢያ ማወቁ ሳይሆን ይልቁንም ምክንያቱን በሚገባ በልቶ ያማያዳግም መለስ ከመስጠቱ ላይ ነው። ምክንያት ተኮር የምርምር ተግባር በሸታውን ያገኛል። ህመሙን ከሥሩም ይነቅላል። ሳቢያ ተኮር እርጃዎች አቅመቢስ በመሆናቸው፤ ዋስትና የማይሰጡ ማስታገሻ ናቸው፤ አዘናጊ ልፈስፍስ ዝልቦ መንገዶች ናቸው!
ምልሰት፣ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008፤ በኢትዮ – አፍሪካዊው የቅኔው ልዑል በብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ሥም በሰዬምኩት ማህበራዊ ድህረ ገጽ፤ እንዲሁም በጸጋዬ ድምጽ ራድዮ ፕሮግራሜ ቃሊቲ ውስጥ ለነበረው ታናሼ „ሥምን መላዕክ ያወጣዋል“ በሚል አንድ መጣጥፍ መጻፌን ብቻ ሳይሆን በድምፄም ማቅረቤን አስታውሳለሁ። ልቤ ውስጥ የገባ የቅኔ ቀንበጥ ነበርና ቴዲ አፍሮ። ስለ ወጣቱ ከያኒ – ገጣሚ – ዜመኛ – ድምጽ ቃና፤ እንዲሁም የአቀራረብ ብቃት- በዛ ጹሑፌ ላይ ሥራዎቹ ተተርጓሚነታቸው (interpretable) እንዲሁም ተዋራራሽነታቸውን በስፋት ነበር የገለጽኩት።
የድርሻዬን ይባልለት – ስለ ይፈልቃል ገና!
ዛሬም ደግሞ ትንሽዬ የግል ዕይታዬን ለማለት ትክሻዬን ለሚወርደው ዱላ አስመችቼ ለመቀበል ቆረጥኩና እንዲህ ልል ነው። በዚህ ፈታኛ ወቅት መቆስቋሻ የሚያስፈልግበት ሳይሆን ገብቶ መርመጥመጥም ይጥማል። ፈተና ተፈልጎ የማይገኝ ከተገኘ ግን አንጥሮ የሚያሳምር ሜሮን ነው። አባቶቻችን ፈተናቸው ሲዘገይ ወይንም ፈተና ቸልም ብሎ ሲረሳቸው ሁለት ሶስት ሱባኤ ይይዛሉ። እኔው የእነሱ ህይውት ኑሮኝ በመንፈሳዊ ዘርፍ ብጣቂ ዘር ባይኖረኝም። በገኃዱ ዓለም ግን እኔም ፈተና ሥልጡን አድርጎ ቀርፆኛል። ተላምጄዋለሁ። ከጋሼ ጸጋዬ ፍቅር መንጭቶ በውሰድኩት የድህረ ገጽ ስያሜ ብርትዬም ታስራ በነበረችበት ውቅት ተግቼ በብዕር ብቻ ሳይሆን በተገኘው አጋጣሜ ሁሉ መፋለሜ፤ እኔን ቢደቁሰኝም፤ ክሱ ሀገር ምድሩን ቢያዳርስም እኔኑ ቢያደቃኝም፤ የወረደው ማዕት …. ግን ኃይልና ብርታት ሰጥቶት ከዛ በኋላ የተከደኑ ብዙ ሲሳዮችን እንድከውን አምላኬ ረዳኝ። ቀን ሲወጣ ታላቋ ኢትዮጵያ ትንቆጠቆጥበታለች። አዎን! እኔ በምኖርበት ሀገር ኢትዮጵያ የምትባል ታላቅ ሀገር ጸጋዬ የሚባል የኢትዮ አፍሪካዊ ፈላስፋ ዕውቅናቸው ሙሉዑ እንዲሆን ሆኗል። የኦነግን ተልዕኮ ለማሳካት ሆነ በቅዱስ ወንጌል ሰባኪ ተብዬ ክስ ተመስርቶብኝ ነበር። ለዛውም ለአንስት ባልተሰጠኝ ጸጋ ብከሰስም አሸነፍኩ። ተመስገን። እድሜ ለሚሹንግ ዩንቨርስቲ ታላቅ ሚዛናዊ ኢትዮጵያዊ ሙሑር። ብዕራቸው ከእሥር አስለቀቀን በጋራ ….. ሰላምም አሰፉን። ምስክርነታቸው አንጀት አርስ ነበርና። አለን ሚዲያዎቼ እና እኔ እንደ አመረብን። ፈቃዱን ለሰጠኝ ለራዲዮ ፕሮግራሙ ቲም የተሰጠው አጥጋቢ ጥሁፍም በእጄ ላይ ይገኛል።
እግዚአብሄር ይመስገን የ21ኛው ምዕተ ዓመት ታላቅ ሥራ የሆነውን የደራሲ አቶ ምስብእክ ወርቁን „ዴርቶ ጋዳን“ ረቂቅ ወጥ ሥራ ጭብጥ ሳስብ፤ የቴዲን በጋሼ ጸጋዬ ዙሪያ የሰራቸውን ድንቅ ጽጌረዳዊ ተግባር በመንፈሴ ደም ሳዘዋውር፤ የመንፈስ ቋሚ ትውፊታችን በዕድሜ ተከታዮቼ እንዲህ ፋፍቶ ሳልሞት ቆሜ በህይወት በማዬቴ እግዜአብሄር ይመስገን። አሜን! የኔ ታናሾችን እግዚአብሄር ያኑልርኝ። ደሜ ቋንቋ ቢኖረው የሚናገረው ቋንቋ ጸጋዬ በሆነ ነበር – ተግባባን?! እኔ ጋሼ ጸጋዬን እማውቀው ኢትዮጵያዊ ሆኖ እናቱን – ሰንደቁ ሲያደርግ ነው። ክብራችንም ነው። ጉልህ የቋንቋ ሊቅም።
አሁን ወደ ተነሳሁበት ወጣቱ የተወቀሰበትን „ጥቁሩን ሰው“ ለእኔ የሰጠኝን ንጹህ ትርጉም ለሌሎች ወገኖቼ ለምን አልሰጣቸውም ብዬ አላዝንም። ውበት እንደ አካባቢው ስለሚተረጎም። እኔ በሚታዬኝ፣ ለእኔ በሚሰማኝ ውስጥ እነሱ ላይኖሩ ይቻላሉ – ለእኔ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ሥጦታ ነው። ለትውልዱ በጣምራ ገለጻ አንገት ነው። ባለዜማዎችን ለዘመኑ ሊመራ የሚችል ምልክትም ነው። ይህ ወጣት የከወናቸውን ተግባራት በማስተዋል ሆነን ስናነባቸው አሱም ሆኑ ሥራዎቹም አርማችን ናቸው። ባለመታደል ሆኖ እንጂ። ከዚህ ሌላ እኔ የወጣቶች አደራጅ ስለነበርኩኝ ስሜታቸው በጣም ቅርቤ ነው። „የልጅ ነገር አንዱ ፍሬ አንዱ ጥሬ ሆኖ“ ነው እንጂ በዚህ ዙሪያ መሬት ዬያዘ ሰፊ ጥናት ከወጣቶቹ ጋር ሰርተን ነበር። ከእጄ ቢኖር እንዴት ወርቅ በነበረ። በሌላ በኩልም ወጣትነት ሁላችን ያለፍንበትም ነው።
ለማንኛውም ወጣት አትሁን ማለትም የፈጣሪን ታላቅ ተፈጥሮዊ ዶግማ ሆነ ሥልጣን መጋፋት ይመስለኛል። በዚህ አፍላ ዘመን ስንት ቦታ ይደረሳል። ወጣትነት ሳተናነት ነው ….. በእኔ ስሜት ማዕቀፍ ውስጥ ያለው የነፃነት ትርጉም፤ የማንነቴ ጣዝማ በመሆኑ የውስጤ ፍጹም ገዢ ነው። ነፃነት ማንነት ላለው እኔነቴ አንጎሉም ነውና። ማናቸውም የገኃዱ ዓለምን የኑሮ ስንክሳሮች የማያቸው ሆነ የምመዝናቸው እኔን ከሰጠኝ ብሄራዊ ነፃነት በታች እንጂ በላይ ከቶም ሊሆን አይችልምና። ከዚህ አንጻር ቴዲ አፍሮ ለትውልዱ ጥበብ ነው። አጀንዳዎቹ ኢትዮጵያና ነፃነቷ ስለሆነ – የሥርጉተም።
ስለሆነም „የጥቁሩ ሰው“ ፊልም በሙዚቃ የተቀነባበረ ብቻ ሳይሆን እኔ ሳዬው፤ እውነትም ለመናገር፤ ፊልሙ በዛ ዘመን የተሰራ ነው የመሰለኝ። ማለት ትዕይንቱ ጦርነቱ እዬተካሄደ የተቀረጸ ዓይነት ነው። ጭብጡና የጭብጡ ማዕከላዊ ተልኮዎ በሥርዓተ ተክሊል በፍጹም ሁኔታ በተፈጥሯዊ አኃታዊነት የተጋቡ ናቸው። በጣም የተዋጣለት ታላቅ ተግባር ሆኖ ነው ያዬሁት። ከዚህ ባለፈ ድሉ ሙሴውን – የህዝብ ስለመሆኑም አባወራ ጀግኖቻችን በነቂስ አውጥቶ ነው የተቃኘው ስለሆነ ይህ ወጣት በቀደመው፤ በዛሬው ወይንስ በሚመጣው በዬትኛው ዘመን የተፈጠረ ነው በማለት በልቤ ውስጥ ባለችው ሙዳይ ወስጥ እጅግ መስጥሬ አስቀመጥኩት። መብቴ ነው። እኔ እንደዚህ ላሉ ወጣት ጀግኖቼ አብዝቼ እሳሳላቸዋለሁ፤ ሰብስቤ በማህጸኔ ውስጥ ባስቀምጣቸውም እወዳለሁ፤ ዓለም ቀናተኛ ስለሆነች እንዳትነጠቀኝ ስለምሰጋ
teddy afroየወጣቱን ንጥር ተግባር ብቁ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ነገሮች ግጥሞቹ ጥልቅ መሆናቸው ነው። ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ በነብይነት ማያያዣ ፈጥሮ ያወራርሳቸዋል። ጥበብ ማለት ይህ ነው። ግጥምጥሞሽ ያልሆነ። እርግጥ ነው በግልብ ካዬናቸው ጊዜያዊ ደስታ ወይንም የማንደግፈው ከሆነም ጠብ አጫሪነ ስሜትን ቀስቅሶ ሊያበሳጨን ይችላል። አብሶ ከመልዕክቱና ሰብሉ ሊያለማ ከፈለገው ማዕከላዊ ማሳ ካልተነሳን እንደ መደዴ የቃላት ድርደር አድርገን ልንመከተው እንችላለን። የመልዕክቱ ውስጥ ንዑድ መንፈስ ነፃነት ነፃነት ነፃነት፤ ተፈሪነት ተፈሪነት፤ ገናናነት ገናናነት፤ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነት – አፍሪካዊነት ነው – የዓለም አብነት ኢትዮጵያ! ይህ ነው ውስጣችነን የወያኔ ሸፍጥ ካላሸፈተው …..
እያንዳንዱን ስንኝ በተን አድርገን በቁሙ ሳናነብ ውስጡን በቅንነትና በአዎንታዊነት ስንፈትሸው ቃሎችን ከስንኙ ሐረግ ነጥለን በመልካቸው ስናይ ደግሞ ቀለማችን አጉልቶ፤ እኛነታችን አብርቶ፤ ፍቅርን እንደ ታቦት ከብክቦ፤ ሩቅ ተጉዞ ሰላምን በናፍቆት ይጠራና ውስጣችን አስተቃቅፎ፤ ነገን በተስፋ ቀይሶ ይመከረናል፤ ያስተምረናል። ይፈትሸናል። ፍላጎታችን ኮትኩቶ የአቅጣጫውን ቅዬሳ ናሙና ከመንፈሳችን ሰርበዬር ውስጥ በሳቢነት ይቀርጸዋል። …..
እንዲሁም „ጥቁሩ ሰው“ በሀገራችን የነበረውን፤ አሁን ያለውን የሥነ ጥብብ እድገት ሥልጣኔም ቁልጭ አድርጎ ያሳዬናል። „ይህ የትውልድ ክፍተት አለበት፤ ወጥ ሥራዎች ተራቆቱ፤ የቀደሙት የሙዚቃ ስንኞች ቃናቸው ከዕውነተኛው ወይንም ከጋህዱ ዓለም ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ነበሩ። መሬት ያያዙ ነበሩ፤ ስለሆነም ወስጥን የመግዛት አቅም – ኃይልና – ስበት ነበራቸው። የዛሬዎቹ ግን ቤታቸው እንኳን አይመታም፤ ሥር አልሰደዱም“ … ወዘተ
… ለሚሉት ዕውነት ለመናገር የአርቲስት ቴዲ አፍሮ የመንፈስ ምርት ጥያቄያቸውን ሁሉ በአግባቡ የመለሰ ይመስለኛል። ደግሜም እላለሁ … እኔ አሁን ለተፈጠሩት ወጣቶች እጅግ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት አለኝ። በስለው ነው የተወለዱት ማለት እችላለሁ። መድረክ ሲያገኙ የማዬው ብቃት ከቶውንም ሊለካ የማይችል የመንፈስ ሐሴት ይሰጠኛል። ለዛውም በዚህ ሙጃ ሥርዓት፤ በዘመነ ወያኔ ተወልደውና አድገው … ሞት ያልተዋጀበት አንድም የኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ተቋም በሌለበት …. ይህን ጥሰው የወጡ የዘመኑ ጥቁር አንበሶች ናቸው – ለእኔ።
ንጽጽር፤
የብዙ ታዋቂ ዓለምዓቀፍ ባንዶችን ኮነሰርትን አብዝቼ እከታተላለሁ። የወጣቱ የፈጠራ ብቃት እኔ ነኝ ካለ ባንድ ጋር ሊመጥን የሚችል በቂ አቅም እንዳለው ነው ያዬሁበት። የቴዴ ሥራዎች መነሻ እሩቅ አይደለሙ። ከእናቱ ጓዳ፤ ከተጨባጩ ጭብጥ ስለሆነ፤ ስሜትን የመሳብ ችሎታው ብቻ ሳይሆን ስሜትን ተቆጣጥሮ የማቆዬት ጉልበቱም አንቱ ነው። ሁሉን ነገር፣ ሁሉን አካባቢ በቅኑና በትሁት መንፈስ ይዳስሳል። አንዱ የግጥም ዜማ በራሱ አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። ይህ ለኢትዮጵያ የሥነ – ግጥም ሆነ ሙዚቃ ነገ አዲስ አቅጣጫ ነው። ለማግሥትም ብቁ እርሾ!
ሌላው ቅኝቱ ራሱ መሰራቱ፤ ፍሬዘሩ ከውስጡ መፍለቁ፤ ከዚህም በላፈ የስንኙን ፍሰት ሳይጎዳ እንደ ራሱ ውስጠት አድርጎ፤ ጤናቸውን ጠብቆ፣ ሴላቸው ሆነ ደም ሥራቸው ሳይጎዳ፤ ኦርጋናቸው ሳይነደል እንደ ተፍጥሯቸው ስለሚቀርበው ይህ ደግሞ የወጣቱ ልዩ መለያ ጸጋው ነው። /ጀርመኖች አውስጌቦልሼ ታለንት/ ከሰው ዘር የተለዬ መክሊት እንደ ማለት። በዬሙያው እንዲህ ያሉ ሁለት አንጎል ያላቸው ይፈጠራሉና። በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊነት በጠላትነት ተፈርጆ፤ በፖሊሲ ደረጃ ወያኔ ተግቶ እዬሰራ፤ በዘመኑ ተፍጠሮ ግን፤ የወያኔን ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ፖሊሲ የቀደመ፤ የበለጠ ሥራ ነው። አንድ የፖለቲካ ድርጅት ረጅም ዓመት ከደከመበት የቴዲ ስንኞች የበለጠ ያፈሩና አርበኞች ናቸው። ለኢትዮጵያዊነትም ዘብ አደርም ናቸው። ሥነ ጥበብ ወተቱ የአድማጭ የሰላ እርምት ነውና ወጣቱ እርማቶችን በጸጋ ተቀብሎ ማስተናገድ ከቻለ አንድ ትውልድ የመፍጠር አቅሙ አንቱ እንደሚሆንም አልጠራጠርም።
የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ያን የመሰሉ ሥራዎቹን፤ ትውልድ የማይተካው ያ …. ዕንቁው ጋሼ ወጋዬሁ እሸቱ ነበር የሚተውንለት – የሚያነብለት። መዳህኒተዓለም አባታችን ንጉሥ ዳዊትን „እንደ ልቤ“ አለው ለጋሼ ጸጋዬም እንደ ልቤ ነበረው ጋሼ ወጋዬሁ። ዕድለኛ ነበር። እንደ ውስጡ ሆኖ፣ ከውስጡ የተቀመጠ ለእሱ ጸጋ ብሎ አምላኩ የመረቀለት ጋሼ ወጋዬሁ ነበር። ትውናው እንደ እራሱ ውስጥ አድርጎም ያቀርብለት ነበር። የጋሼ ጸጋዬ ስሜቱ መንትዮሽ በአህትዮሽ እንደ ነበር ይሰማኛል። መቼም እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ በሺ ዘመናት አንድ ጊዜ ወይንም ሁለት ጊዜ ነው የሚከሰተው። ከዚህ አንፃር ውስጡን ከእነተፈጥሮው ማቅረብ መቻሉ ለቴዴ ዕድለኛነቱን ድርብ ያደርገዋል። በስሜቱ የፍልጎት ልብ ውስጥ እሱ እራሱ በመንፈስም በአካልም አለና። ተቀድቶ የማያልቀው ውበቱም ይህ ነው። ወጣቱ ከያኒ የጻፈውን እራሱ ያቀርበዋል …. እራሱ አቀናብሮ እራሱ ያስጌጠዋል። አደራጅቶ፤ ውስጡን የሚገልጽለት ሌላ ሰው ቢያስፈልገው ኖሮ ከባድ ነበር። ግን እድሉና ምርቃቱ ወፍ አወጣቸው። ስለሆነም ተ — ጠ – በ – በ – በ – ት።
የሰማይ የላቀ ስጦታ!
እኔ የእግር ኳስ ፍቅረኛ ነኝ። እጅግ በጣም እግር ኳስን እወዳለሁ። አሁን ዬይድነቃቸው ልጆች ለእፍሪካ ዋንጫ በ2013 እ.ኤአ. ሲታደሙ ሰፊ የሆነ አትኩሮት ነበረኝ። ኢሮ ስፖርት ሀገራችን እንዴት ከፍ እዬደረገ ሲገልጸው እንደ ነበረ ማመን እስኪያቅት ድረስ እጅግ እጅግ ድንቅ ነበር። ያን ጊዜ አጋጣሚው ረድቶ ሀገሬ ኢትዮጵያ ከፍ አለች። ታሪኳ፤ የህዝቧ ባህል፤ ወግ ልምዷ፤ የነፃነት ገድሏ ሁሉ ተዘከረ። ኢትዮጵያን የኢሮ ስፖርት ፕሮግራም አቅራቢዎች ሆኑ አዘጋጆች ውስጣችን አሳምረው ነበር ኪናዊ አድርጎ ያነበቡን – ቀለማም አድርገው ነበር የኳሉን። ለእኔ ፈውስ ነበር። ዳንኩኝ!
መቼም ትውልዱ አዲሱ ማለቴ ነው በብዙ ፈታና ውስጥ ሆኖ፤ ግን ድንቅ ነገር ያሳዬናልና ከዓለም ዋንጫ ዝርዝር ውስጥ ዬኛዎቹ ሲገቡ ደስታዬ ወደር አልበረው። ታዲያ የመጨረሻ ማጣሪያው ከናይጀሪያ ጋር ሲሆን ግን አልተመቸኝም ነበር። አሳምሬ ናይጀሪያዎችን አውቃቸዋለሁና። የሆነ ሆኖ የኔዎቹ ማጣሪያ ሳያልፉ ሲቀሩ ዕንባ አውጥቼ ነበር ያለቀስኩት። የእውነት። እናት ሀገሬ፣ የመንፈስ ተክሊሌ፤ እምዬ ኢትዮጵያ – እንጀራዬ የመላ ዓለምን የእግር ኳስ ጨዋታን አለመገኘቷ አስከፋኝ። ልክ እንደ መጻፍ፤ መጸሐፍ ማንበብ ድንቡልቡሏንም ስለምወድ ብራዚል ላይ እመቤት ኢትዮጵያ ስትደምቅ ናፈቆኝ ግን ሳይሆን ሲቀር በጣም ተጎዳሁ። የኢትዮጵያ ጎል ጠበቂ ገና አልተወለደምና።
እግዚአብሄር ይመስገን … ሁልጊዜም የማምናበት ነገር፤ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና ዕንቡጡ ቅኔ አህጉርን ወክሎ በ2014 የዓለም ዋንጫ ብራዚል ላይ መገኘት በራሱ ክብር ነው። የሰማይ የላቀ ሥጦታ ነው። ልዩ ምርቃት ነው። የሥነ ጥበብ ቤተኛ ታዳሚዎች ሁሉ ልንደሰትብት የሚገባው መሪ ድል ነው። ቅኔኛው ቴዲ አፍሮ እንደ አባቶቹ እንደነ የቅኔው ልዑል ብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን መንገድ ተከትሎ፤ የአፍሪካ ነገር መስመሩ ነበርና፤ ፈልጎ የተነሳለት ድንቅ ራዕይ ከሀገሩ አልፎ አህጉሩንም ሊወክል ነው። እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው እንሆ አደረገለትም። ጉዞው አቅጣጫው እጅግ አጓጊ ነው።
ፅኑ ዕይታ!
እናት ሀገር ኢትዮጵያ ስትከብር፣ ስትደምቅ፤ ከፍ ስትል፣ ዜግነት ሲያበራ፣ እንደ ትናንቱ ኢትዮጵያ አፍሪካን በሥነ ጥበብ ጎራ ዳግም ልትመራ ስትመረጥ፤ ለመልካም ነገር ስትታጭ፤ ልዩ ፍጹም ልዩ ትርጉም ነው – ዕጹብ ድንቅ። ፍካታዊ ገጸ በረከት ነው። አበባዊ ረድኤት ነው። ለዚህ ተግባር ስኬታማነት እንደ ሰው የተገባን እናድርግ እንጂ፤ ትዕዛዙ ከመዳህኒተዓለም አባቴ ስለሆነ ሳንኩን ሁሉ አሸንፎ ሚሊዮን ፈን ያፈራል። አብሶ ጀርመኖች የሥነ – ጥበብ አክባሪና አፍቃሪ በመሆናቸው ለሽልማት ያጩታል። ጠብቁ። ቴዲን የቆዬ ሰው ይዬው። አፍሪካዊ ቪቫ ይሆናል። ዕውቅናውን አሳምረው ይሰጡታል። ሰፊ የሆነ በር ተክፍቶለታል። በሰውኛ ሥልጣን በሩን መዝጋት አይቻልም። „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል ጎንደሬ ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና!
ጀርመን በሥነ ጥበብ ጉዳይ 13ኛው ፕላኔት ነው – ለእኔ። ፍጹም የተለዩ ናቸው። በደንበር – በክልልል – በቀለም በምንም ነገር አይደለም የጥበብን ልዩ ጸጋ የሚለኩት፤ በመንፈስ ቅዱስ ንዑድ ስሜት እንጂ። የሰማይ ጸጋን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር ተስጥቷቸዋል። ይህ ቀን እኔ ስመኘው ነበር። አንድ ዝግጅት ለጀርመን ህዝብ ቢኖረው በማለት። የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ከጀርመን አልፎ ዓለም ሊታደምበት እንሆ ፈጣሪ አምላክ ወሰነ። ተመስገን!
እኔ በግሌ በፈጣሪዬ ስለማምን፤ ደግሞም የሥነ ጥብብ ሰውነት ሥጦታው የሰማይ ስለሆነ ጥበቃው ሰማያዊ ነው። በድንግልና ውስጡን ሆኖ ስለሚጫወተው ሥነ ጥበብን ያምርበታልና ሰጪው አጥር ቅጥር ይሆንለታል።
አዎን! ቀኑ እስኪደርስ ድረስ በጥንቃቄ፣ በፆም በጸሎት፣ ከብዙ ነገር ታቅቦ፣ ለዚህ ማዕረግ ካበቃው ከአምላኩ ጋር ቴዴ መሆን እንዳለበት እንደ ታላቅ እህታዊ አስተያየቴን አካፍለዋለሁ፤ ህይወቱ ያላችሁ ደግሞ እንደ ዕምነታችሁ በጸሎት ትደግፉት፣ ትረዱት ዘንድ በትሁት መንፈስ እጠይቃችኋለሁ። ከፀሎት በላይ ጠበቂ የለምና። ከጸሎት በላይ ዘበኛ የለምና። ምክንያቱም ያቺ መከራዋና ፍዳዋ የጠናባት ልዕልት ኢትዮጵያ፣ ልጆቿን አብልታ ማሳደር ያቃታት እናት ሀገር፤ ሚሊዮን የነገ ፍሬዎች ጉርሻ አጥተው በጠኔ የሚረግፉባት አምላኳ አረሳትምና እንሆ ከፍ ሊያደርጋት ማቀዱ ዬምልዓት ዕንባ ካሳ ነው። ለአምላካችንም ለቅዱስ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገውን ምስጋናችን ሳናቋርጥ እንግለጽለት። በዚህ ዘመን አንድ ታዊቂ፤ ተደማጭ ለዛውም ወጣት ማፍራት ነገን ያበራልና።
የአይቮሪው ዓለምዓቀፍ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫወች ዝሆኑ ድሮግባን፤ የዩክራይን ሁለት ወንድማማቹች የጀርመን ዓለም ዓቀፍ ቦክሰኞች ወስጥ ታናሹ ለዩክሬን ፍትኃዊ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሲገኝ የዓለም ሚዲያ እንዴት ያረብርባል መሰላችሁ፤ የኛ ግን ትዕቢተኛው የሳውዲ መንግሥት የታላቅ ሀገርን ክብር ጠቅጥቆ ልጇቿን እንደ እንሰሳ አስፓልት ላይ እንደዛ ሲያርድ አንድ ለዕንባችን ዕውቅና የሚያሰጥ ታዋቂ፤ ተደማጭ፤ ዓለም ጆሮውን የሰጠው ዋቢ አልነበረንም። ነገ ግን ይኖረናል ….. ለዚህ ፈታናውን ተጋርቶ መረባረብ የግንባር ተልዕኳችን ነው። ጦርነቱ ተክፍቷል በድል ማጠናቀቅ አለብን! ማቄን ጨርቄን የለም! ለተደራጀ መሬት ለያዘ ተግባር እያንዳንዳችን በግል ሁላችንም በጋራ እንትጋ! ኢትዮጵያ ናት ፊት ለፊት ቁማ እሳት ውስጥ እዬተርመጠመጠች ያለችው። በኪነጥበቡ ይህ ዕውቅና ሲመጣ ደግሞ ግንባር መሆን!
በተረፈ ትምክህት ጎርፍ ነው፤ አድማም ጤዛ ነው። በሥነ ጥበብ ላይ ተደራጅቶ ጦርነት መክፈትም ወስጥን መፋቅ ነው። ፍቅር ግን የጸደቀ ፍሬ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር ሳይሆን የሚያኮራ፣ ተለምኖም የማይገኝ ምርጥ ዘርነት ነው። ውስጣችን የነጠረ ወርቅ ነው። ድህነታችን፣ የህዝብ መበደል፣ መንገላታት ደግሞ የሥርዓታት እንጂ እናት አንዱን ልጅ የክት ሌላውን የዘወትር፤ አንዱን አብልታ ሌላውን አስርባ በፍጹም አታውቅም። የወተት ጡት ጋቶቻ ለሁላችንም እኩል ማጥባትን አዘውትረው ይሻሉ …. ህግጋቶቿ ናቸውና። እቅፏም ለሁላችን ሳይዛነፍ በእኩልንት ነው። ማዕዷም እኩል ለሁላችንም ነው። ስለሆነም በእናት ሀገራችን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሁሉ መቆስቆሻ ሳንፈልግ ሁላችንም እኩል መማገድ በእጅጉ ያስፈለገናል። ፈተና መጥቷል – ማለፍን ይጠይቃል_! እናት ኢትዮጵያ የበደለችው አንድም ሰው የለም!
ክወና! …
ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ምንጊዜም ስለማይረሳት እሷን ለማጠቃት የተነሱት ሁሉ የዶግ አመድ ይሆናሉ። በእኛ እድሜ እንኳን ሱማሌ፤ ኤርትራ፤ ግብጽ፤ አሁን ደግሞ ሱዳን ይታመሳሉ። አምላኳ ቀናተኛ ነውና። በ2012 እ.ኣ.አ. የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ እጬጌውን ከመንበራቸው፤ የጎጥ አፄውንም ደግሞ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ለኑዛዜ ሳያበቃ ነበር ያነሳቸው። ይህ ምርታማ መሬት፤ ለምለም አካባቢ፤ ሃብታምነት የሚባለውም ቢሆን አባታችን ከተከፋ ትል ከሰማይ ሊያዘንብበት ይችላል። እናስተዋል! —- ጉዳቱ ደግሞ የጋራ ነው እንደ ሰው ለምናስበው – ለእኛ።
እንኳንስ በተፈጥሮ ኤኪኖሚዋ ጥገኛ ለሆነ፤ ያልጠመጣጠነ ኤኮኖሚዊ ዕድገት ለሚገርፋት ኢትዮጵያ ቀርቶ የሰማይን ቁጣ እንጃፓን፣ ሱናሜም ማስቆም አልቻሉም። ይልቅ እንደ ሰው አስበን በዛ ቦታ ማን ይኖራል? ህፃናትን፣ አቅመ -ደካሞችን፤ ህሙማን፤ ነፍሰጡር ሴቶችን፤ እንሳሰት ሳይቀሩ ሊታስብላቸው ይገባል። ቀይ ቀበሮ እኔን ይገልጸኛል። ሶፍ ኡመር ዋሻ እኔን ያብራራኛል። ልዩ የሚባሉ አብዛኞቹ ሌላ ዓለም የማይገኙ አዕዋፋት ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚገኙት፤ ሁሉንም የሰማዩ ቁጣ ውስጣችን አብሮ እንዳያጭደው አደብ ገዝተን ወደ ፈጣሪያችን እንመለስ!
… ለሰው አይደለም። ወደ ፈጣሪያችን ቀልባችን መልሰን እራሳችን አዋርደን፤ ይቅርታ አምላካችን እንጠይቅ …. ኢትዮጵያ ሶስት አፄዎቿ ዓለም በቃኝ ብለው ገዳምን የመረጡ ንዑዳን የፈጠረች ቅድስት ሀገር ናት። ዘጠኙ ቅዱሳን ከተፈጠሩባት ሀገር አስበልጠው የመረጧት ሀገር ናት። ነብዩም ለጆቻቸው የተመኩባት ተምሳሌት ሀገር ናት።
የማከብራችሁ ወገኖቼ …. እጅግም የምናፍቃችሁ ደሞቼ … መንጠራራት መልካም ባይሆንም፤ ሰው ባላው ነገር ወይንም በቀጣይ ፍላጎቶቹ ዙሪያ አብዝቶ ሊንጠራራ ወይንም ሊመካ ይችላል። በተማመነበት ጉዳይ። በክርስቶ ወይንም በአላህ ሥልጣን መንጣራራት ግን ዕጣው ትውልድን ያሳርራል – ያርሳልም። ቅጣቱን የሚያቆም ምድራዊ ኃይልም አይኖርም፤ አባ ጳውሎስን አተረፈ ተዋህዶ? ወይንስ ቲፒ.ኤል.ኤፍ ሄሮድስ መለስን ታደገ? ገዳማት ታረሱ …. ቁጣውም ነደደ!
ፍቅር ተንበርክኮ እንሆ ይለምናል። አሁንም ህዝባችን በፍቅር ይጋባል፣ ይዋለዳል፣ አብልጅነት ይናሳል፣ ይጎራበታል፣ ጡት ይጣባል፤ ጓደኝነት ይገጥማል፣ ማህበሩን ዝክሩን አብሮ ይጠጣል፤ ሀዘን ተፍሰኃውን ፈቅዶና ደስ ብሎት ይጋራል፤ ይረዳዳል፤ ይህን የደም ግንኙት መበጠስ አይቻልም … ሰውኛ አይደለምና ….. በቁጭት ምክንያት ምላሽ ለመስጠት ፍላታችን ለማስታጋስ ስንል በምንሰነዝራቸው ቃሎች ከእልህና ከግብታዊነት ጸድተን እንስከን። ማስተማር የሚቻለው የሚወረወረውን ናዳ መልሶ በመልቀቅ ሳይሆን፤ ጨዋነታችን በለገሰን አርምሞ፤ በተደሞ፤ በትግሥትና በሆደ ሰፊነት ወያኔ ያዘጋጀውን ሴራ ማክሸፍ ስንችል ብቻ ይሆናል ብጡልነት። የዚህ ሁሉ ትርምስ ተዋናዩ ወያኔ ነው። ይህ አውሬ ያዘጋጀው መርዝ ወገኖቻችን አልተረዱትም። ዕውነተኛውን ነገር ወስጣችን ፈቅዶ ይቀበል ዘንድ እግዚአብሄር ይርዳን። ትጉኃን ቀጥሉ የሃቅ ምስክር መረጃዎችን በሚዛን ቀልቡን። አትናቁ ወይንም አቅልላችሁ አትዩትት። የተደራጀ ፈተና ነው። ፈተናው የሚረታው ደግሞ በበለጠ በተደራጀ ሥልጡንና ብልህ ተግባር ብቻ ነው።
ቀኑ እዬናፈቀኝ – የሰንደቄ ዜማ …
ህብር ስንኞችህ ማንነት ሊያለማ።
አፍሪካዊነቴ ሊደምቅም – ሊያበራ
በፈጠራ ዓውራ! ….
ዛሬ ለትናንቱ፤ ትናንትም ለነገ – አድዮ አጎመራ፤
ሉሲ ከፍ ትላላች በመንፈስ – በማማ
በፍውሰትህ – ጣዝማ …..።
እናት ታጌጣለች ….. በሞገስህ ግርማ፤
ታሪክ ይዘከራል – በወጣቱ ዓርማ!
ዓለም ይታደማል በመረዋ እማማ!
ህበረ – ቀለማቱ፤ — የቁንጅና ዋና!
አማንህ – ሊያዘመር ….
እሙ – ልትቀምር
የታጠቀ ዕውነት ብቃት ሊመሰክር፤
ያ …. የደግ ታሪክ ገር፤ መቅድምን ሊመራ
የዘማናት ሂደት …. ትውፊት ሊያነባብር
ዋዜማን – ሊያዘመር …. ብቃት አጎመራ!
ማሰሰቢያ።
• ግጥሞቹ 13.01.2014 00.17 (እ.ኤ.አ) ተጻፉ።
• ጎልተው የተጻፉት ፊደላት ጠብቀው እንዲነበቡ የሻትኳቸው ናቸው።
• የግጥሞቹ – ዕርእሶቹ ጎልተው የተጻፉት የተሰመረባቸው ቃሎች ናቸው። ነፃነት ታወጀላቸው ከፈለጉት ቦታ ላይ ሆኑ፤
• ፎቶው ከቴዲ አፍሮ የግል ድህረ ገጹ የተወሰደ ነው።
መፍቻ።
ዋና ሁለቱንም ትርጉም ይዞ ነው የታደመው። ለሁለተኛው ግጥሜ እርእስም ነው።
• ላልቶ ሲነበብ አብይ፣ ኣናት፣ አለቃ፣ መሪ፤ አስተዳደሪ፤ ሰብሳቢ፤ አዛዥ፤ ሙሴ፣ እረኛ፣ ተጠሪ፣ እርእሰ ጉዳይ እንደ ማለት … ሁሎችም እንደ አረፍተ- ነገሩ ፍሰት ይተረጉሙታል። ለእኔ ግጥም ሙሴ የሚለው ግጥሙ ነው።
• ሁለተኛው ጠብቆ ሲነበብ ደግሞ የአሳን ተፈጥሮዊ የኑሮ ልማድን የሚከተል ይሆናል። … የሰው ልጅ በእህልና በመጠጥ ብቻ አይኖርም። ህሊናው መስኖ ይፈልጋል። መስኖው ደግሞ ሥነ ጥበብ ነው። ሥነ ጥበብ ጥሩ ዋናተኛ ነው። ዋናው በውጭ ሳይሆን ውስጥን የሚቀድስ የሚፈውስ፤ የሚጠግን፤ የሚያጽናና፤ የሚያጸና፤ የውበት ውበት፤ የጌጥ ጌጥ ነው። ልዩነት በአንድነት አንድነት በልዩነት አኃቲነት በመፈቃቀድ የሚያበቅል – የሚያጸድቅም ነው … በዚህ ሂደት ህልም ህልም ነው ነገሩ የሚመስለው የዓለም ብቸኛ ፍቅረኛ በሆነው የእግር ኳስ ትንሳኤ የኢትዮጵያ ሥነ – ጥበብ በበትሩ አሳላፊ በውስጥነት ሊዋኝ ነው …. ያ … የዓለም ሚዲያ ሰልፉ፤ ያ … የዓለም ዕውቅ ሰዎች ታዳሚነት ውስተት እኛነት መስፍን ሆኖ ሊሰነቅ፤ እሰቡት ….. ውህድነት። በአንድ ለጋ ሊጋባ …. ይህ የምልዓት መንፈስ በሐሤት ኢትዮጵያን በዕዝነ – ህሊናን ሲዳስሳት … የቅዝፈቱን ቅኔ ዘጉባኤን የዳጎሰ ድምር ነው ዋና ያልኩት ….
• ጣዝማ …. ከተለመደው ውጪ የሚገኝ የተፈጥሮ የማይረጋ ማር። ለጤና እጅግ መዳህኒት የሆነ። አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው በቆላማ የሀገራችን ቦታዎች ነው። ቀለሙም ትንሽ ደመቅ ያለ ነው።
• አድዮ ማንም ሀገር ብሄራዊ አበባ የለውም። ኢትዮጵያ ግን አላት። መንገድ ጠራጊዋ የተስፋ አበባ አድዮ የአዲስ ዓመት ዋዜማ! የሰንደቅዓላማችን ማዕከላዊ ቀለም ከዚህ ተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ ይመስለኛል – በኪዳን። በ5ኛው መጸሐፌ ላይ „በፊደል“ የልጆች የግጥም መድብል የተሰራበት ነው፤ እንደዚህ ለዬት ያሉ ተፈጥሯችነን ከፊደል ላይ ዘርዘር አድርጌ ጽፌዋለሁ። በነገራችን ላይ የፊደል የፊት ሽፋን ከዓለም የሚለዬን፤ እንደ ውስጣችን የተፈጠረው ድንቁ የፊደል ገበታችን ሲሆን ከሌሎቹ መጸሐፍቶቼ በበለጠ በነጮች ተወዳጅም የሆነው እሱ ነው። ይወዱታል … በጣም። ቋንቋው አማርኛ ግን ተማረኩለት … ሌላ ቀን በዚህ ዙሪያ እመጣላሁ … አሁን ደግሞ የአፈሙዙ አቅጣጫ በእሱ ዙሪያ ስለሆነ ….
መንፈሶቼ – ታዳሚዎቼ! የፍቅር ማዕድ በመከባባር አብሮ አቆዬን ፤ለተሰጠኝ በቂ ጊዜ ምስጋናዬን በቅኑ ውስጠት – እንሆ!
ፈጣሪ አምላካችን የተበተነን ልቦናን ስበስቦ፤ እናታችን ከፍ ትል ዘንድ የጀመረውን ይጨርስ።
ልብ ይስጠን – ለሁላችን! የምንችለበትም ጽናትም! አሜን
ጨረስኩ — ንጹህ አዬርም አገኘሁ – ዱላውን የምችልበት!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

Monday, January 13, 2014

መሰረታዊ ግንዛቤ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ! (ዘነበ በቀለ)

   ዘነበ በቀለ
music-notesሙዚቃዊ ፍልስፍና እንቆቅልሹ የሚፈታው ህዝባዊ በሆነው መሰረታዊ ግንዛቤ ላይ ተመርኩዞ ነው። ህዝባዊ ግንዛቤ ስንል ደግሞ ሙዚቃው የሚሰጠውን ስሜትም ሆነ መልዕክት የገባውና አሰራሩን የተረዳው ክፍል ወሳኝ መሆኑን ለመጠቆም ነው።
የኢትዮጵያ ሙዚቃ ማለት በብዙ ዘመናት የህዝቡ አብሮ የመኖር ስልት መሰረትነት የተገነባ የጋራ ግንዛቤን የፈጠረ የባህሎችን ልዩነት አቀናብሮ የያዘ አንድ ወጥ ቅርስ የሆነ ማለት ነው። እነዚህን የቅርርብ ሁኔታዎች ለመገንዘብ ሶስት መሰረታዊ የሆኑ የዜማ መዋቅሮችን መመልከት የተገባ ነው። እነዚህም
1ኛ/ የዜማ ስልት
2ኛ/ ሪትም/ምት
3ኛ/ ቋንቋ
ሲሆኑ ከመመርመሪያቹ መንገዶች መሃል ዋነኞቹ ናቸው።

የዜማ ስልት ስንል ሙዚቃው የተገነባበትን መሰላል/ስኬል ማለታችን ነው።
ሪትሙ ደግሞ በየአካባቢው የአኗኗር ዘይቤ ላይ ተመርኩዞ በረገዳ፣ በዘፈን፣
በእስክስታ፣ በጭፈራ የሚተረጎም መሆኑን የሚገልፅ ነው።
ቋንቋውም ቢሆን እንደየአካባቢው የአነጋገር ፈሊጥ የሚታይ በመሆኑ ለምሳሌ ያህል – በጎንደር አማርኛና በጎጃም አማርኛ፣ በሸዋ አማርኛና በወሎ አማርኛ መሃል ልዩነት አለ። በኤርትራ ትግሪኛና በትግራይ ትግሪኛ መሀል ልዩነት አለ። ይህ ሁኔታ በዜማው ላይ ተፅዕኖ አለው’ የዜማው ስሪት ደግሞ ጭፈራውን ይወስነዋል።  ለምሳሌም የሸዋው ኦሮሞ ጎፈር አጥልቆ ረገዳ ሲጫወት ይስተዋላል። የወሎ ኦሮሞ ግን ጭፈራውን  በእስክስታ አጅቦ ነው የሚያቀርበው። የወለጋና የጂማ ኦሮሞ በጭፈራው ላይ እጅን ማርገብገቡ ተመሳሳይ ቢያደርጋቸውም ያርሲ ኦሮሞ አንገትን ማሽከርከር ይጠቀማል። በሁሉም ዘንድ የዜማ ባህሪያቸውና ሪትሙ የተለያየ ነው። ስለዚህም መለኪያው ሁሉንም ነጥቦች የዳሰሰ መሆን ይገባዋል እንጂ! የኦሮሞ ባህላዊ ሙዚቃ አንድ አይነት ነው ከማለት ይልቅ ኢትዮጵያዊ ትርጉም ያለው ለመሆኑ የበርካታ ባህሎችን ተመሳሳይ አሰራር መገምገም ያስፈልጋል።

የወያኔ ፖለቲካ የተቀነበበው በነገድ ማንነት ዙሪያ በመሆኑ ሙዚቃን በተለይም ኢትዮጵያዊ ፀባይ ያለውን ክፍል ለመተርጎም በርካታ ችግሮች ሲደነቀሩ ይስተዋላል። የሙዚቃን ምንነት በራሳቸው ፍላጎት ላይ ተመርኩዘው የሚተረጉሙ ግለሰቦች መኖራቸው ተገቢውን ግንዛቤ ያልጨበጡ አድማጮችን ለመፍጠር ምክንያት ሆኗል። በመሆኑም የሙዚቃ ግንዛቤ ፈሩን የለቀቀ ማንኛውንም ነገር በምርታማነት/ሽቀላ ስሌት ውስጥ ያስገባ በመሆኑ፣ የሙዚቃ ሰዎች በስራቸው ላይ ከጥራት ይልቅ ብዛትን እየመረጡ  በመምጣታቸው መካለስና መደለዝ፣ መደባለቅና መዋዋጥ፣ በተለይም በስታይል/ አሰራር ዘይቤው/ እንዲጨፈለቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆናቸው ይስተዋላል። በዚህም ምክንያት ከላይ የተጠቀሱትን ማገናዘቢያ ነጥቦች ያላሟሉ ሙዚቃዊ ስራዎችን በተናጠል በማቅረብ፣ በቋንቋ ላይ ብቻ የተመረኮዘ ግምገማን በመሰንዘር ይኸ ሙዚቃ የእከሌ ጎሳ/ነገድ ባህል ነው ብሎ መደምደም ፈሊጥ ሆኗል። ይሁን እንጂ! የየነገዱን አኗኗር ከቋንቋው ውጭ ተመልክቶ መገምገም አስፈላጊ ነው። ከሙዚቃው ጥበብ ባህርይ የወጣ ግምገማ ለሙዚቃው ምንነት ጠቃሚ አይሆንም።

የሙዚቃ አሰራር በተለያዩ መልኮች በህዝብ ውስጥ መተላለፉ ሀቅ ነው። በጉርብትና፣ ገበያ፣ ጦርነት፣ ራድዮ ማሰራጫ ወዘተ. ዋና ዋና የመተላለፊያ መንገዶቹ ናቸው። በመሆኑም
የኢትዮጵያ ህዝብ ባህል በነዚህ ሁሉ መልኮች የመተላለፍ ዕድል ስለገጠመው አንድ ወጥ የሆነ ሙዚቃዊ መሰረት ይዞ እንዲወጣ ዕድል አግኝቷል። ይህም የአምስት ድምፅ መሰላል ተከታይ መሆኑ አንዱና ዋናው ነው። በጣም ጥቂት የሆኑ ባህላዊ ሙዚቃዎች ከዚህ ባነሰ /ቶናል ሬንጅ/ ወይም የድምፅ ገደብ ውስጥ ያሉና በኦሮምኛ እንጉርጉሮ ሙዚቃ ውስጥ ከሚታየው ሄክሳቶኒክ/ ወይም ስድስት ድምፅ መሰላል እንዲሁም በአደሬ ክሮማቲክ ታይፕ/ የግማሽ ድምፅ ግንባታ ያለው ሙዚቃ መሰላል ውጭ፣ አብዛኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ማለትም የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የትግሬ፣ የወላይታ፣ የጉራጌ ወዘተ. የነገድ ሙዚቃዎች በአምስቱ መሰላል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በመሆኑም አንድ አይነት ሳይኮሎጂካል ሜክአፕ/ ፈጥረዋል።

የአምስቱ መሰላል ቶን የፈጠረው ሜላንኮሊክ ጠባይ የአድማጩን ሙዚቃዊ ግንዛቤ በመወሰኑና አንዳንድ ሁኔታዎችን ተመርኩዞ የሀዘን ስሜት የሚፈጥር በመሆኑ በተለይ እንዳሁኑ አይነት ህዝብ ያዘነበት የተከዘበት ዘመን ሲከሰት ለቅሶንና ሙሾን በመድረስ የሙዚቃውን አጠቃላይ ግንዛቤ ለውጦ እንባ አባሹ እንዲበራከት የሙዚቃው ይዘት  አንድወጥ ትርጉም ብቻ እንዲይዝ የሚያደርጉ ሙያተኞች ምክንያቶች ይሆናሉ። ሙዚቃ ደስታና ሀዘን የሚገለፁበት ጥበብ ብቻ አይደለም። ትምህርትንም ማስተላለፊያ እንደመሆኑ ሁሉ ፖለቲካም ጓዙን ጠቅልሎ በጥበቡ ታዛ ስር እንደሚጠለል ታሪክ መስክሮልናል።  ትክክለኛ ሁኔታዎች ከተለዋወጡ አጉል ቦታ የሚደነቀረው አሰራር ብዙ ትርጉሞችን ያዛባል። ለምሳሌ የቀረርቶ ዜማን  ያለቦታው መደባለቅ “ሳይገድሉ ጎፈሬ…” የሚሉት አይነት ትርጉምን የሚፈጥር ከመሆኑም በላይ ወቅታዊ የሆነ የመነሳሳት ስሜት ፈጣሪ የነበረውን የጦርነት ሙዚቃ ማዕረጉን ቀንሶ ለዳንስ እንዲውል ያደርገዋል።

የኢትዮጵያ ሙዚቃ በጊዜው ያልተዋዋጡ የተለያዩ የአካባቢ ባህሎችን ልዩ አሰራር የሚያከብርና በጋራ የሚታዩ ሙዚቃዊ እሴቶችንም አቅፎ የሚጓዝ የህዝብ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሙዚቃ በእንጉርጉሮና በዘፈን በመዝሙርና በመንፈሳዊ ዜማ መንገዶች መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ በመረዳት የሚጓዝ መሆኑ መታወቅ ይገባዋል።

ቸር ይግጠመን!!
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

Saturday, September 28, 2013

በእንቆቅልሽ ኖሮ በእንቆሽልሽ ያረፈው ድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ


መልካም ልደት ለሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሰሰ።
ከቅድስት አባተ
ጥላሁን ገሠሠ በህይወት ዘመኑ ከልጅነት እስከ እውቀት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ሆኖ በህዝብ አንቀልባ ላይ ያደገ ነው፡፡ ምክንያቱም ገና በ12 እና 13 ዓመት ዕድሜው ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ስለተቀጠረ እንደ ወላጅ ሆኖ ያሳደገው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ ግን ህዝቡ እንደ ወላጅነቱ ስለ ጥላሁን ገሠሠ ሁኔታ በተለይም እጅግ የከፋ አደጋ ሲደርስበት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ዘመናት እንደ ዋዛ እየከነፉ ነው፡፡
ተወዳጁ ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ከአፄ ኃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድረስ ማለትም በሶስት ስርዓቶች ውስጥ ልዩ ልዩ አደጋዎች ቢደርሱበትም በየትኛውም ዘመን ግን ይፋ የሆነ መረጃ ለህዝቡ አልተሰጠም፡፡ ከህግ አንፃርም የጥላሁን ገሠሠ አደጋዎች ፍትህ አላገኙም፡፡ ህግና ስርዓት ባለበት ሀገር ውስጥ የዚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ አደጋዎች እንዴት እንቆቅልሽ ይሆናሉ? ብለው የሚጠይቁ በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎች አድናቂዎቹም አሉ፡፡
ለምሳሌ በዘመነ አፄ ኃይለስላሴ ስርዓት ወቅት የጥላሁን ገሠሠ ወላጅ እናት በሰው እጅ በሽጉጥ ተገድለዋል፡፡ ይህን ወንጀለኛ ለማግኘት ጥላሁን ገሠሠ ብዙ ዋተተ፡፡ የናቱ ገዳይ ይገኝበታል ተብሎ የሚታሰብበት ስፍራ ሁሉ አሰሰ፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ጥላሁንም የህይወት ታሪኩን በሚገልፀው መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፡-
‹‹እናቴ የተቀበረችው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ነው፡፡ በእውነቱ የእናቴ በሰው እጅ መገደል እንደ እብድ አደረገኝ፡፡ የእናቴን ገዳይ ለማግኘት ሶስት አራት ዓመታትን ወስዶብኛል፡፡ እዚህ ቦታ (እዚህ ሰፈር) ታየ ሲባል እዚያ ሄጄ ሳደፍጥ፣ ከዚህ ተነስቶ ሄዷል ስባል ወደተባለበት ቦታ በመሄድ ስንከራተት ጠላቴን በጭራሽ ላገኘው አልቻልኩም›› (ገጽ 75)
ጥላሁን ገሠሠ የናቱን ገዳይ በመፈለግ ብዙ መከራ ደርሶበታል፡፡ ለፖሊሶቹ እንዲያፈላልጉት ገንዘቡን አውጥቷል፡፡ ገዳዩን በመፈለግ ሲባዝን በትዳሩ ውስጥ ክፍተት በመፈጠሩ የመጀመሪያ ባለቤቱ የሆነችዋንና በጣም ከሚወዳት ከወ/ሮ አስራት አለሙ ጋር የነበረው ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆኗል፡፡ የናቱን ገዳይ ይዞ ህግ ፊት የሚያቀርብለት አካል አጥቶ ጥላሁን ገሠሠ እንደ ተቆጨ አልፏል፡፡
የሚገርመው ነገር የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው ሰው እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መኖሩን አንዳንድ ምንጮች ይገልፃሉ፡፡ በ1980ዎቹ ውስጥ ይታተሙ የነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች እንደገለፁት ከሆነ ደግሞ፤ የጥላሁን ገሠሠን እናት ገድሏል ተብሎ የተጠረጠረ ሰው በንጉሱ ዘመን ተይዞ መታሰሩን ይገልፁና ደርግ ድንገት ወደ ስልጣን ሲመጣ ለእስረኞች ሙሉ ምህረት ሲያደርግ ይህም ተጠርጣሪ ከእስር ቤት መውጣቱን ፅፈዋል፡፡
ይህ ተጠርጣሪ በእርጅና ውስጥ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ መኖሩም ይነገራል፡፡ ግን በወቅቱ አስፈላጊውን ምርመራ ባለመደረጉ የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ ዓመታት አለፉ፡፡
ከዚህ በኋላ ደግሞ ጥላሁን ገሠሠ ላይ ከመጡት አደጋዎች በዋናነት የሚጠቀሰው የ1985 ዓ.ም አንገቱን በስለት ቆርጦ ለመግደል የተደረገው እጅግ ዘግናኝ ክስተት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የወንጀል ታሪክ ውስጥ እንቆቅልሽ ሆኖ እስከ ዛሬ ድረስ ተሸፋፍኖ የኖረ አደጋ ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠን ማነው አንገቱ ላይ በስለት የቆረጠው?
እንቆቅልሹ ይሄ ነው፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ራሱ መናገር አልፈለገም፡፡ ‹ሆድ ይፍጀው› ብሎት ለምን?
አንዳንድ ሰዎች በዚህ ላይ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ ጥላሁን ገሠሠ በህይወት እያለ አንገቱ ላይ በስለት ስለደረሰበት አደጋ እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ቢወጣ ደስ አይለውም፤ በዚህም ሳቢያ በጭንቀት እና በብሽቀት ይጎዳል፤ ስለዚህ ጉዳዩ ሆድ ይፍጀው ተብሎ ቢታለፍ ይቀላል፡፡ ምክንያቱም ጥላሁን እንዲገለፅበት ካልፈለገ ብንተባበረውስ የሚሉ አሉ፡፡
ይህን ከላይ የሰፈረውን ሀሳብ በቅንነት ካየነው ከጥሩ መንፈስ የመነጨ ስለሆነ ልንቀበለው እንችላለን፡፡ ግን እኮ የተፈፀመው ወንጀል ነፍስ የማጥፋት ሙከራ ነው፡፡ በየትኛው የህግ አግባብ እንዲህ አይነት ሙከራ ወንጀል ነው! ስለዚህ ይሄ ጉዳይ እስከ መቼ ነው ምስጢር ሆኖ የሚኖረው? የፖሊስ ሃይል ባለበት ሀገር እንዲህ አይነት ፍጥጥ ግጥጥ ያለ ድርጊት ላለፉት 19 ዓመታት በምን ምክንያት ነው ምስጢር ሆኖ የኖረው?
ይህ በጥላሁን ገሠሠ አንገት ላይ የደረሰው አደጋ ይፋ ባለመሆኑ ጉዳዩ ለብዙ ሃሜታዎች ክፍት ሆኖ ኖረ፡፡ ለምሳሌ አደጋውን የፈፀመው ራሱ ጥላሁን ገሠሠ ነው የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች መረጃዎች ደግሞ አንድ ሰው በራሱ ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሊፈፅም ፈጽሞ አይችልም በማለት ይገልፃሉ፡፡ ለምሳሌ የጥላሁን ገሠሠን የህይወት ታሪክ የሚያወሳው መጽሐፍ ‹መሰናዘሪያ› ጋዜጣን ጠቅሶ በተለይም አደጋው እንደደረሰ ጥላሁንን ሲያክሙት ከነበሩት ባለሙያዎች መካከል ዶ/ር ባዘዘው ባይለየኝ የተናገሩትን በሚከተለው መልኩ አቅርቧል፡፡
‹‹ጥላሁንን ከምሽቱ 12፡30 ላይ ሰዎች በአንቡላንስ ሆስፒታላችን ድረስ ይዘውት መጡ፡፡ በጆሮው አካባቢ ደም ይፈሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም በአየር ቧንቧው ማለትም ማንቁርቱ ላይ ተቆርጦ ደም ይፈሰው ስለነበር ባደረግንለት የመጀመሪያ እርዳታ ደሙን አቆምን፡፡ በጎን በኩል በስለቱ የደረሰው ጉዳት ጉበቱን አግኝቶታል፡፡ ግራ እጁ ላይ ያለው የደም ስር ከባድ ጉዳት ደርሶበት የነበረና በጠቅላላውም ሁለት ሰዓት የፈጀ የቀዶ ጥገና ህክምና ተደርጎለታል፡፡ በመተንፈሻ አካሉ በደሰበት ጉዳት ምክንያት ቁስሉ እስኪድን ድረስ ጊዜያዊ የመተንፈሻ መሳሪያ ተደርጎለት የሚተነፍሰው በዚያው ነበር፡፡ እንደ ማንኛውም ሰው መተንፈስ አይችልም፡፡ አንድ ሰው ራሱን አንድ ቦታ ላይ ሊወጋ ይችላል፡፡ ሶስት ቦታ ላይ ራሱን አቆሰለ ማለት ይከብዳል፡፡ ድፍረቱም አቅሙም አይኖረውም›› (ገጽ 105) በማለት ሀኪሙ ገልፀዋል፡፡
የህክምና ባለሙያው የሰጡት አስተያየትም አሳማኝ መንፈስ አለው፡፡ ስለዚህ አደጋውን ያደረሰው ሌላ አካል ነው ብለን እንድንጠረጥር ያደርገናል፡፡
ጥላሁን ገሠሠ አደጋው በደረሰበት ወቅት የታተሙ የነበሩት ጋዜጦችና መጽሔቶች ስለ ሁኔታው ያቀረቧቸውን መጣጥፎች በሙሉ መልሼ አይቻቸው ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ እጃቸው ላይ ትክክለኛው መረጃ ስለሌለ ከመላ ምትና ከተጠየቅ (Logic) በስተቀር የተደራጀ ማስረጃ አላቀረቡም፡፡ ዛሬ በህይወት የሌለው ታዋቂው የመድረክ አስተዋዋቂውና የጥላሁን ገሠሠ ጓደኛ የነበረው ስዩም ባሩዳ ተጠይቆ ሲመልስ፣ ‹‹እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ ጥላሁን ገሠሠ በቢላዋ አንገቱን ሊቆርጥ ቀርቶ፣ ጥፍሩን እንኳን በምላጭ ለመቁረጥ የሚፈራ ነው›› በማለት ገልፆታል፡፡ በወቅቱ የተጠየቁት የጥላሁን ገሠሠ ጓደኞች ሲናገሩ፣ ጥላሁን በራሱ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ እንደማይወስድ ጠቁመዋል፡፡ ታዲያ ማን ነው አደጋ ያደረሰበት?
tilahun
ዛሬ ጥላሁን በህይወት የለም፡፡ አንገቱ ላይ የደረሰበት አደጋ ‹‹በሆድ ይፍጀው›› ሰበብ ለዘመናት ምስጢር ሆኖ መኖር ያለበት አይመስለኝም፡፡ በወቅቱ ፖሊስ የተደራጀ ምርመራ ማድረጉ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ያ የምርመራ ውጤት ለፍርድ ቤት ይቅረብ ወይስ አይቅረብ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ጉዳዩንም በሐገሪቱ ውስጥ የተከሰተ አንድ ትልቅ ወንጀል አድርጎ የመመልከት አዝማሚያም አልተስተዋለም፡፡ ስለዚህ እኛ እንደ ጥላሁን ገሠሠ ‹‹ሆድ ይፍጀው›› ብለን ማለፍ ያለብን አይመስለኝም፡፡ እውነታውን ካላወቅን ሆዳችንን ይቆርጠናል፡፡ ከቶስ የማይክል ጃክሰንን አሟሟት በተመለከተ የነበረውን የፍርድ ቤት ሂደት ያየ፣ ጥላሁን ገሠሠን ሲያስታውስ ምን እንደሚል አላውቅም፡፡ የጥላሁን ገሠሠን እናት የገደለው አልታወቀ፡፡ ጥላሁን ገሠሠን አንገቱን በስለት የቆረጠው አልታወቀ፡፡ ምንድን ነው ጉዱ?
ሌላው አሰገራሚውና አሳዛኙ ጉዳይ የጥላሁን ገሠሠ ሞት ነው፡፡ ያንን የሚያክል የኢትዮጵያ የሙዚቃ ንጉስ እንደ ዋዛ ሞተ ሲባል በእጅጉ ያስደነግጣል፣ ይቆጫል፣ ያሳስባል፡፡
ሃሳብ አንድ
ድንገት ከአሜሪካን ሀገር ወደ ሐገሩ ኢትዮጵያ የመጣው ጥላሁን ገሠሠ ማታ በቤቱ ውስጥ ታመመ፡፡ ባለቤቱ እና ቤተሰባቸው በድንጋጤ ይዘውት ወደ አንድ የግል ሆስፒታል ሄዱ፡፡ እዚያም እንደደረሱ የኢትዮጵያው የሙዚቃ ንጉስ ተገቢውን ህክምና አለማግኘቱን ባለቤቱ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ በጥላሁን ገሠሠ የህይወት ታሪክ ውስጥ የሚከተለው ተጽፏል፡፡
‹‹ሰው ታሞብናል! እባካችሁ ዶክተር ጥሩልን›› አለቻቸው፣ እጅግ በተጣደፈ ሁኔታ፡፡ ድምፅ ሰምተው ከመጡት ሰዎች መካከል አንዱ ‹‹መጀመሪያ ካርድ አውጡና ነርሷ ትየው›› አለ በተረጋጋ ስሜት፡፡
‹‹እባካችሁ ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ በጣም አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል›› አለች ቶሎ እንዲረዱላት እተንሰፈሰፈች፡፡ ደንገጥ ብሎ ከልቡ የሚሰማት አጣች፡፡
‹‹ወ/ሮ ሮማን መላ ቅጡ ጠፍቶባት አይኖቿ ከወዲያ ወዲህ ሲዋትቱ ከወደ ጥግ በኩል የቆመ አንድ ዊልቸር አይታ ሄደች፡፡ እየገፋች ስታመጣው ያዩዋት ጥበቃ አብረው ወደ መኪናው አጋፏት››
‹‹ጥላሁንን ከመኪናው አውርደው ተሽከርካሪው ወንበር ላይ አስቀመጡት፡፡ ጥላሁንም ቁርጥ ቁርጥ ባለ ትንፋሽ፤ ‹‹እባክህ ዶክተርዬ ተንፍሼ ልሙት፣ የምተነፍስበት ነገር አድርግልኝ›› በማለት የመማፀኛ ቃል ወርወር ያደርጋል፡፡ ሐኪሙ በዝግታ መጥቶ አጠገባቸው ቆም አለና ጥላሁን የተቀመጠበትን ዊልቸር ከወ/ሮ ሮማን በመውሰድ እዚያው በዚያው በክሊኒኩ ኮሪደር ላይ ወደ ፊትና ወደኋላ እየገፋ በዝምታ ተመለከተው፡፡
‹‹ወ/ሮ ሮማን ስለ ህመሙ ስትነግረው በቀዘቀዘ ደንታቢስ ስሜት ያያታል፡፡ ያ ጎልቶ የሚታይ ድንጋጤዋ ስሜት፣ ፊት ለፊቱ ያለው የህመምተኛው ቅዝታ ቅንጣት ያህል ርህራሄ ያሳደረበት በማይመስል ስሜት፡፡
‹‹ስንት አይነት ልበ ደንዳና በየቦታው አለ!›› አለች ወ/ሮ ሮማን በውስጧ፡፡ ስለ ህክምና ስነ-ምግባር በአደባባይ የተገባው የሄፓክራተስ የቃል ኪዳን መሀላ እንደ ጤዛ ተኗል፡፡
‹‹ኧረ ባካችሁ አንድ ነገር አድርጉለት!! ምነው ዝም አላችሁ?›› አለች፡፡ ‹‹ኧረ እባካችሁ እርዱልኝ?›› አለችው፣ አጠገቧ የቆመውን ሐኪም፡፡
‹‹ዶክተርዬ መተንፈስ አቃተኝ፤ ትንሽ የምተነፍስበት ኦክስጂን አድርግልኝ? ተንፍሼ ልሙት›› እያለ ሲማፀን ሌላ ሐኪም ደርሶ ‹‹አስም አለበት እንዴ?›› አለ፡፡ ኋለኛውም እንደ ፊተኛው ሐኪም ርህራሄ ባጣ ስሜት፡፡ ከራሱ ከጥላሁን ይልቅ ስለ እሱ ልዩ ልዩ የህመም አይነቶችና ባሕሪይ በይበልጥ የምታውቀው ባለቤቱ ነች ማለት ይቻላል፡፡ ‹‹ባለሙያ ነኝ ማለት ባልችልም ስለ በሽታው በየጊዜው ከዶክተሮች ጋር የምነጋገረው እኔ በመሆኔ ብዙ ልምዶችና መረጃዎች አሉኝ›› ትላለች ወ/ሮ ሮማን፣ የአያሌ ዓመታት ግንዛቤዋን እያነፃፀረች፡፡
‹‹አስም ሳይሆን የልብ ህመም አለበት›› አለች ወ/ሮ ሮማን ፈጠን ብላ፡፡
‹‹እንግዲያው ጎተራ አካባቢ የልብ ህክምና የሚሰጥበት ኢንተርናሽናል ሆስፒታል ስላለ ወደዚያ ይዘሽው ሂጂ›› ብለዋት መልሷን ሳይጠብቁ ትተዋቸው ወደ ጉዳያቸው ተመለሱ፡፡ (ከገፅ 116-170 በከፊል የተወሰደ)
ይህ ከላይ የተፃፈው ታሪክ እውነት ከሆነ ለጥላሁን ገሠሠ ሞት አንዱ ምክንያት ሊሆን ነው፡፡ ሆስፒታል ደርሶ ህክምና አላገኘም፡፡ በስርዓት ተቀበለውም የህክምና ባለሙያ የለም ማለት ነው፡፡ እናም ይሄን የሚያክል ስህተትን በምንድን ነው የምናርመው? ስለ ጉዳዩስ የቤተዛታ ሆስፒታል አስተዳደር ምነው ዝም ይላል? መልስ የለውም? የሀኪሞች ማህበርስ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደ አጀንዳ አይነጋገርም? ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርስ? የህክምና ህጉስ የሄፓክራተስን የቃል ኪዳን መሐላ አላከበሩም ተብለው በሚተቹ ሀኪሞችና ተቋማት ላይ ምን ይላል? ይሄ የማይክል ጃክሰንን የአሟሟት ምስጢር የፈተሸ ችሎት የተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የጥላሁንን ገሠሠን ህልፈት ክፉኛ አስታወሰኝ፡፡
ሐሳብ ሁለት
የጥላሁን ገሠሠ ባለቤትና ቤተሰቦች፣ የልብ ህክምና የሚሰጥበትን ሆስፒታል ቢፈልጉ ያጡታል፡፡ ከዚያም ጎተራ አካባቢ ወዳለው ሰናይ ክሊኒክ ይደርሳሉ፡፡ እዚያም እንደ አንድ የህክምና ተቋም ተገቢውን እርዳታ እንዳላገኙ ተገልጿል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ኦክስጅን እያለ የፈለገውን ኦክስጅን ሳያገን ማለፉን በፅሑፍ ተገልጿል፡፡ እንደ ባለቤቱ ገለፃ በሁለተኛውም ሐኪም ቤት ውስጥ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ጥላሁን ገሠሠ አላገኘም፡፡ የባለቤቱ የወ/ሮ ሮማን በዙ በተደጋጋሚ ሐኪም ቤቶቹን እና የህክምና ባለሙያዎቹን እየጠቀሱ የሰሯቸውን ስህተቶች ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ በዚህ ጉዳይ ላይ ተገቢው ማጣሪያ ሳይደረግ የጥላሁን ገሠሠ ሞት ብቻ ይነገራል፡፡
አሁን ‹‹ሆድ ይፍጀው›› የሚል ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሐኪሞቹም ሆኑ የህክምና ተቋማቱ ሆድ ይፍጀው ብለው ተቀምጠው ከሆነ እኔ ሆዴን ቆርጦኛል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ ኦክስጂን አጥቶ ከሞተ እና ዝም ከተባለ ጥፋተኛው ራሱ ጥላሁን ነው ማለት ነው? ጊዜው የሆድ ይፍጀው አይመስለኝም፡፡
በአጠቃላይ ጥላሁን ገሠሠ የእናቱን ገዳይ አላወቀም፡፡ ህግም የናቱን ገዳይ አግኝቶ ተገቢውን ውሳኔ አልሰጠለትም፡፡ ከዚህ ሌላም አንገቱ ላይ በስለት የደረሰበት አደጋ እስከ ዛሬ ድረስ ምስጢር ሆኖ ኖሯል፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ ‹‹ዶክተርዬ! መተንፈስ አቃተኝ፤ ትንሽ የምተነፍስበት ኦክስጂን አድርግልኝ? ተንፍሼ ልሙት›› እያለ እጅግ በአሳዛኝ ተማፅኖ፣ እርዳታ ሳይደረግለት እንዳለፈ ይነገራል፡፡ በዚህም ጉዳይ ተጠያቂው ማን እንደሆነ የሚነገር ጉዳይ የለም፡፡ ሁሉም ነገር ዝም ነው፡፡ ውስብስብ የሆነው የማይክልጃክሰን አሟሟት ግን በግልፅ ችሎት ፍትህ አግኝቷል፡፡ የጥላሁን ገሠሠ አደጋዎችና ሞቱ ግን እንቆቅልሽ ሆኖ ይኖራል፡፡ እንቆቅልሹስ ሳይፈታ ለትውልድ እናስተላልፍ?S
ይህ ጽሁፍ በሚኒሶታ እየታተመ በሚወጣው መዲና ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነው።

zehabesha

Thursday, August 29, 2013

ሚካኤል ፀጋዬ

ፎቶ አንሽው ሚካኤል ፀጋዬ በተለያዩ አገሮች አውደ ርዕይ አሳይቷል። ከዚህ ባሻገር ፎቶዎቹ በታዋቂው ሳምንታዊ የጀርመን መፅሄት «ዴር ሽፒግል» ታትመው ወጥተዋል። ሮይተርስን እና ብሉምቤርግን የመሳሰሉ የመገናኛ ብዙኋንም በፎቶዎቹ ተጠቅመዋል።
የአንድን ሀገር ባህል ወይንም የአኗኗር ዘይቤ በመረጃ ጠብቆ ለማቆየት ቪዲዮ፣ ስዕል ወይንም ፎቶ ጥሩ ዘዴዎች ናቸው። የዛሬው የባህል መድረክ እንግዳችን ሚካኤል ፀጋዬ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በቀለም ቅብ ተመርቋል። ለአንድ ዓመት ያህል በቀለም ይስል ነበር በኋላ ግን ፎቶ አንሺነትን መርጧል።
የሚካኤል ፎቶዎች ሁለ ገብ ናቸው። ክረምት እና በጋ፤ ህፃናት እና አዛውንት፣ ሰዎች በስራ ወይንም በእንቅስቃሴ ላይ ሳሉ የሚያሳዩ ናቸው። ሚካኤል ለአውደ ርዕይ ካቀረባቸው ፎቶዎች መካከል፣ በብዛት የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አቀማመጥ፣ የህንፃ እና የመንገድ ገፅታዎች ይገኙበታል። « ታሪክን እንደመፃፍ ነው የማየው» ይላል ፎቶአንሽው። ሌላው ፎቶዎቹ መስታወታቸው የተሰበሩ መቃብር ላይ ያሉ ምስሎች ናቸው። እነዚህ ፎቶዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በአውደ ርዕይ ደረጃ አልቀረቡም። እስካሁን አንጎላ እና ፈረንሳይ ውስጥ ብቻ ሲሆን የታዩት ፤አብዛኞቹ ተመልካቾች የሰጡት አስተያየት ፎቶዎቹ ሁኔታውን በአግባቡ የሚያሳዩ ፤ነገር ግን የሚያሳዝኑ እና የሚረብሽ ስሜት የሚፈጥሩ መሆናቸውን ነግረውታል ። ሌሎቹ ሚካኤል ያነሳቸው ፎቶዎች በአዲስ አበባ የሚገኙትን የሴተኛ አዳሪዎችን አኗኗር ያሳያል።
ሚካኤል በፎቶው ማስተላለፍ ወይንም ማሳየት ስለሚፈልገው መልዕክት፣ በተለያዩ ሀገራት ለአውደ ርዕይ ስላበቃቸው ፎቶዎች እና ስለ ፎቶ አንሺነት ሙያ ሚካኤል ፀጋዬ ገልፆልናል። ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

Friday, August 9, 2013

ቢንያም ዳና እና « የኛ ስታይል»


ቢንያም ዳና እና « የኛ ስታይል»

ከአንድ አመት በፊት ነበር «ጋንግናም ስታይል» በገበያ ላይ የዋለው።ደቡብ ኮሪያዊው አቀንቃኝ ፕሳይ በዚህ አዝናኝ የዳንስ ቪዲዮ በአለም አቀፍ እውቅናን አገኘ። ቢንያም ዳና ደግሞ «የኛ እስታይል» ሲል ተጫውቶታል።
ትልቁ የኢንተርኔርት የቪዲዮ ማህደር YOU TUBE ላይ ብዙ « ላይክ» ወይንም ተወዳጅነት ያገኘ ቪዲዮ በመባል ጋንግናም ስታይል እኢአ በመስከረም ወር 2012 ዓ ም የጊነስ የዓለም ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ሰፍሯል። በታህሳስ ወርም ዮቲውብ ላይ  ቢሊዮን ጊዜ የታየ የመጀመሪያው ቪዲዮ ተብሏል። ዛሬ ገፁ ከ 1,7 ቢሊዮን በላይ ተጎብኝቷል። ቢንያም ዳና የተጫወተው « የኛ ስታይል» ደግሞ ይፋ ከሆነ ሁለት ወር ሊሆነው ነው ይላል። ወደ ኪነ ጥበብ ሙያ ከገባው 16 ዓመት ሊሞላኝ ነው ይላል ቢንያም።
እሱ እንደሚለው ይህንን ቪዲዮ አይተው ሰዎች የሰጡት አስተያየት ይበልጥ ሙዚቃ እንዲጫወት አበረታትቶታል። ቢንያም በደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የመድረክ መሪ ሆኖ ይሰራል። ሙዚቃ በትርፍ ጊዜ ነው የሚጫወተው።
በህዝብ ዘንድ « የኛ ስታይል» ምን አይነት አቀባለል አገኘ ? ይህንን ዘፈንስ ለመጫወት ምን አነሳሳው፤ ቢንያም አጫውቶናል።ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
ልደት አበበ
ሸዋዬ ለገሰ
dw.de

Thursday, August 8, 2013

አሳሳቢዉ የቅርስ ጥበቃ በኢትዮጵያ


አሳሳቢዉ የቅርስ ጥበቃ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ እድሜ ጠገብ ቅርሶች ላይ በተለያየ አቅጣጫ ጥፋት እየፈጸመ መሆኑን፤ በሕገ ወጥ ቅርስ አቀባዮች የሀገሪቱ የታሪክ ማህደር ወደ ዉጭ እየተጋዘ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ።
የሰዉ ልጅ መገኛ የሆነችዉ ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪክ የባህልና የቅርሶችም መገኛ ናት። የታሪክ ማህደር የሆነዉ ቅርስዋ የሚደረግለት ጥበቃ ምን ይመስላል? ህብረተሰቡስ ለቅርስ ያለዉ ግንዛቤ ምን ያህል ይሆን? በዕለቱ ቅንብራችን የምንዳስሰዉ ጉዳይ ነዉ።
ቅርስ ትናንት እያሳየ፤ ዛሬን እየኖረ፤ ነገን እያመላከተ ማለትም ሶስት ዘመናትን የሚያገኛኝ ድልድይ መሆኑ ይታመናል። ቅርስ ከጥንት ትዉልድ የሚወረስ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ሃብት መሆኑኑም ይገለጻል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ቅርስ የማንነት መገለጫ መሆኑ አያነጋግርም። ግን ለቅርሶቻችን ምን ያህል ክብካቤ እናደርጋለን? ዕዉቁ የታሪክ ምሁር ፕሮፊሰር ባሕሩ ዘዉዴ፤ በቂ ክብካቤ እንደማይደረግ ቢሆንም፤ አንዳንድ የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ገልጸዋል። ፕሮፊሰር ባሕሩ ዘዉዴ በመቀጠል  በተለይ በከተማ አካባቢዎች የሚታየዉ የግንባታ ሥራ  ቅርስን በሚያገናዝብ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል፤ ሲሉ አሳስበዋል። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ዉስጥ በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ተዘዋዉረዉ ጥናት ያደረጉትና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ክብካቤና ልማት ማሕበር መቋቋሙ በይፋ በተገለፀበት ዕለት ስዕላዊ መግለጫ ያቀረቡት፤ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሥነ-ጥበብ ታሪክ መምህር አቶ አበባዉ አያሌዉ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ቅርሶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
  በብሪታንያ ከተቋቋመ 14ኛ ዓመቱን የያዘዉ የኢትዮጵያ ቅርስ ማበልፀግያ ማሕበር፤ መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ  አቶ አለባቸዉ ደሳለኝ ማህበራቸዉ፤ ከኢትዮጵያ በስርቆት ወደ አዉሮጳ የተለያዩ ሀገሮች የተሻገሩ ቅርሶችን በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል። በሀገሪቱ የሚገኘዉ ቅርስ እንዲጠበቅ ተንቀሳቃሽ ቅርስም ከሀገር እንዳይወጣ እየሠራን ነዉ ያሉት በኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብና ዓለማቀፍ ግንኙነት ረዳት ሃላፊ አቶ ፋንታ በየነ በበኩላቸዉ፤ መስሪያ ቤታቸዉ እስከ ዛሪ በርግጥ በጥንካሪ አለመስራቱ ነገርግን በቀጣይ ቅርስን በመጠበቅ ሥራ ዕቅድ መያዙን ገልጸዋል።
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በ UNESCO  ስር ኢትዮጵያ ዘጠኝ ታሪካዊ ቅርሶችን በማስገዘብ ከአፍሪቃ የመጀመርያያዋ ሀገር መሆንዋ ይታወቃል። የማንነት መታወቅያ፤ የግል ታሪክ መግለጫ የሆነዉን ቅርስን መጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት ይመስለናል። ሙሉዉን ዝግጅት የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ!       
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ

DW.DE

ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ ከአመታት በኋላ መድረክ ላይ ተገናኙ

“ጥቁር ሰው” በድጋሚ ሲዘፈን ሌላ የሚያስጮህ ነገር እንደሚመጣ ያልጠበቀው የአውሮፓ ታዳሚ፤ ጉሮሮው እስኪነቃ እንደገና ጮኸ። ታዳሚው ከፊት ወንበር ላይ በVIP ላይ ታማኝ በየነ መቀመጡንም ሆነ፤ በስፍራው መገኘቱን አያውቅም። ቴዲ አፍሮም “ጥቁር ሰው”ን እንደገና ከማቀንቀን ውጪ፤ የድሮ ጓደኛው ወደ መድረክ ይመጣል ብሎ አልጠበቀም። የሆነው ግን እንዲህ ሆነ።

ሁለቱም ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የዘመኑ እውቅ አርቲስቶች ናቸው – ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ። ከአመታት
በፊት የነበረው ወዳጅነታቸውን ግን እንደድሮው ለማየት ያልታልን አድናቂዎቻቸው፤ በልባችን “ግን ለምን?” እያልን
መቆጨታችን አልቀረም። በተለይም ቴዲ አፍሮ ታስሮ በነበረበት ወቅት፤ ታማኝ በየነ “Free Teddy Afro” በሚል
ይሰራ የነበረውን አካል በማንቀሳቀስ ጉልህ ሚና መጫወቱ ይታወሳል። በዋሺንግተን ይደረጉ በነበሩ ሰላማዊ ሰልፎች
ላይ በመገኘት ጭምር ስለቴዲ ነጻ መሆን ቅስቀሳ አድርጓል።
ኢ.ኤም.ኤፍ. ባለው ሌላ የቪዲዮ መረጃ ታማኝ በየነ፤ “ጃ ያስተሰርያል” የሚለውን የቴዲን ዘፈን ግጥም በመቀየር፤ “ጃ
ቴዲ ይፈታ!” በማለት ሌሎቹንም ግጥሞች ጭምር፤ ቴዲ አፍሮ ነጻ መሆን እንደሚኖርበት በሚገልጽ መልኩ ሲዘፍን
ህዝቡም የለቅሶ ያህል፤ ታማኝን አጅበው ሲዘፍን የነበረው ሁኔታ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ሆኖም ከአመት በኋላ
ቴዲ አፍሮ ከተፈታ በኋላ ግን፤ በግልም በመድረክም ላይ ከነታማኝ በየነ ጋር ልናያቸው አልቻልንም። በመሃላቸው
ምንም አይነት መቀያየም ወይም መጠላላት ሳይኖር፤ እኛም እንደድሮው አንድ ላይ ሳናያቸው፤ አይናችንን ፍቅር
እንደራበው 2013 ገባ።
በዚህ አይነት ዝምታ ወራት አልፈው አመታት ተቆጠሩ። በአውሮፓ በሚደረገው አመታዊ የኳስ ጨዋታ ላይ፤
በመዝጊያው ምሽት ቴዲ አፍሮ ሊጫወት መጥቷል። ታማኝ በየነም ወደ አውሮፓ ሄዶ ነበርና የቴዲ አፍሮን የመዝጊያ
ዝግጅት ላይ፤ በክብር እንግድነት እንዲገኝ በነክንፉ በኩል ግብዣ ተደርጎለት በስፍራው ተገኝቷል። ዘፈን አልፎ ሌላ
ዘፈን ተተካ… “ጥቁር ሰው”ም ተዘፈነ።
“ጥቁር ሰው” ሲዘፈን ህዝቡ አብሮ ይዘፍናል… “ምኒልክ ጥቁር ሰው” እያለ ቴዲ አፍሮን ያጅበዋል። ዘፈኑ ካለቀ
በኋላ እንደገና እንዲዘፈን ህዝቡ ጥያቄ አቀረበ። ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሰውን እንደገና መጫወት ጀመረ። ህዝቡ ደስታውን
ገለጸ። በድጋሚው ሲዘፈን ሌላ የሚያስጮህ ነገር እንደሚመጣ ያልጠበቀው የአውሮፓ ታዳሚ፤ ጉሮሮው
እስኪነቃ እንደገና ጮኸ።
ታዳሚው ከፊት ወንበር ላይ በVIP ላይ ታማኝ በየነ መቀመጡንም ሆነ፤ በስፍራው መገኘቱን አያውቅም። ቴዲ አፍሮም
“ጥቁር ሰው”ን እንደገና ከማቀንቀን ውጪ፤ የድሮ ጓደኛው ወደ መድረክ ይመጣል ብሎ አልጠበቀም። የሆነው ግን
እንዲህ ሆነ።
ቴዲ አፍሮ “ምኒልክ ጥቁር ሰው”ን እያቀነቀነ ሳለ፤ ታማኝ በየነ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ይዞ ወደ መድረኩ ወጣ።
ህዝቡ ታማኝ በየነን ባልጠበቀው ጊዜና ቦታ ላይ ማየቱ ብቻ ሳይሆን፤ ጠቅላላ ሁኔታው በቁሙ አደነዘዘው… ብዙዎች
በደስታ ሲቃ ጮኹ፤ አንዳንዶች በደስታ አለቀሱ። ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮም እንደገና የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ፤
አንድ ላይ በአንድ መድረክ ላይ አውለበለቡ! የጽሁፍ ዘገባችን አበቃ። በቪዲዮ ለተቀረጸው ዝግጅት የስራ
ባልደረባዬ ክንፉ አሰፋን በመጋበዝ የኔ ዘገባ እዚህ ላይ ያበቃል።
(ዳዊት ከበደ ወየሳ – አትላንታ)
source...freedom4all

Saturday, July 27, 2013

11ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል

11ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል

በአዉሮጳ ኢትዮጵያዉያን የስፖርትና የባህል ፊዴሪሽን የዘንድሮዉን ዝግጅቱን በስዊዘርላንድ ጄኔቭ አጠገብ በምትገኘዉ ኒዮ ከተማ በደማቅ ዝግጅት አካሂድዋል።
ባለፈዉ ሳምንት ለአራት ቀናት በተካሄደዉ በዚህ ዝግጅት ላይ በሺዎችየሚቆጠሩ እድምተኞች እንደተገኙ ተነግሮአል።በኒዮ የስዊዘርላንድ ከተማ የተካሄደዉ 11ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ነበር የተጠናቀቀዉ። ከተለያዩ የአዉሮጳ ሀገራት፤ ከሰሜን አሜሪካ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የመጡ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያዉያን እና በተለይ የእስፖርት አፍቃሪዎች በዝግጅቱ ላይ መገኘታቸዉን እና እጅግ አስደሳች ግዜ እንደነበር የኢትዮ-ኮለኝ የእስፖርት ሊቀመንበር ወጣት ተስፋዪ አበበ ገልጾልናል። በእንጊሊዝ ነዋሪ የሆኑት እና በአዉሮጳ የኢትዮጵያዉያን የስፖርትና ባህል ፊዴሬሽን ዋና ተጠሪ አቶ ዩሃንስ መሰል በበኩላቸዉ እጅግ ብዙ ህዝብ እንደነበር፤ በተለይ ዘንድሮ ለህጻናት ልዩ ልዩ ዝግጅት እንደነበር ገልጸዋል።
Bild II
Titel Ethio Nürnberg Fußballmannschaft _Ethio - Europe Football Festival 2013 in Nyon, in der Nähe von Genf, Schweiz
Thema: Die 11th Annual Ethiopian Sport & Culture Festival in Europa fand in Nyon in der Nähe von Genf, Schweiz von 17.07 bis 20,0713
Autor/Copyright: Azeb Tadesse Hahn DW 250713
Schlagworte: Ethio Nürnberg Fußballmannschaft_ Ethio - Europe Football Festival 2013 in Nyon, in der Nähe von Genf, Schweiz
ኢትዮ- ኑረንበርግ የእግር ኳስ ቡድን
ልዩ ልዩ የህጻናት ባህላዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶችን ያካተተዉ ይህ ፊስቲቫል፤ በተለይ እግር ኳስ ሰፊዉን መድረክ ይዞት እንደነበር ታዉቋል። ከሰሜን አሜሪካ እና ከደቡብ አፍሪቃ የመጡ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድኖችእንዲሁም ከአዉሮጳ ወደ 24 የእግር ኳስ ቡድኖች ተሰባስበዉ ነበር። እዚህ በኑረንበርግ ነዋሪ የሆነዉና በአዉሮጳ የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የስፖርት ማህበር ዋና ፀሃፊ ፤ወጣት ካሱ ለገሰ፤ ኢትዮ- ኑረንበርጎች፤ በስዊዘርላንድ ሊዮ ከተማ ዝግጅት ላይ ተገኝተዉ እንደነበር ገልጾልናል። ሙሉ ዝግጅቱኑ ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ
source....http://www.dw.de

Friday, July 26, 2013

የኮርያ ዘማቾች ትዉስታ


የኮርያ ዘማቾች ትዉስታ

የኮርያ የዕርስ በርስ ጦርነት ካበቃ ዘንድሮ ስድሳ ዓመቱን ያዘ። በኮርያ የእርስ -በርስ ጦርነት ጊዜ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ በመሰለፍ ከደቡብ ኮርያዉያን ጋር የተሰለፉት ኢትዮጵያዉያን፤ የኮርያ ዘማቾች ማህበር በሚል ጥላ ስር ከተሰባሰቡ 20 ዓመት በላይ እንደሆናቸዉ ይናገራሉ።
የደቡብ ኮርያ መንግስት፤ በተመድ የኮርያ ዘማች ጦር ውስጥ ለተሰለፉ እና አሁን በህይወት ለሚገኙ ወደ 340 ለሚጠጉ አባት ዘማች ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ በማድረግ ላይ ሲሆን ለዘማች ልጆችና የልጅ ልጆችም ከአለፈዉ ዓመት ጀምሮ የነጻ ትምህርት እድል በመስጠት ላይ ይገኛል።
በ21 ዓመታቸዉ ወደ ኮርያ የዘመቱት እና የአሁኑ የኮርያ ዘማቾች ማህበር ሊቀመንበር ኮሎኔል መለሰ ተሰማ ስለማህበሩ እንዲህ ይገልጻሉ፤ በኮርያዉ ጦርነት ላይ ከዘመቱት መካከል ሻምበል ይልማ በላቸዉ ይገኙበታል፤ ሻንበል በላቸዉ፤ ከኢት ዮጵያ ተነስተን ኮርያ እስክንደርስ ወደ ሃያ ቀናት እንደፈጀባቸዉ ያስታዉሳሉ።
ከጅቡቲ ተነስተን በ22 ቀናችን ቱሳን ደረስን ያሉን ሻንበል ይልማ በላቸዉ ፤ ቱሳን የኮርያ ባህር በር መሆኑን አጫዉተዉናል። የኮርያ ዘማቾች ማህበር ሊቀመንበር ኮሎኔል መለሰ ተሰማ በበኩላቸዉ በኮርያ ደርሰን የመጀመርያዉ የኮርያ ገጠመኛችን ይላሉ በማስታወስ፤
በኮርያ ጦርነት ኢትዮጵያ ከ6ሺህ በላይ ወታደሮችን ማሳተፉዋን የገለጹልን ኮሎኔል መለሰ ተሰማ፤ በኮርያ የበጋ ልብስ እና የክረምት ልብስ መለያየቱን፤ ቀን በቀን የምንበላዉ እንጀራ በኮርያ አለመኖሩን አዉቀናል።
የኮርያዉያን ባህል ከኢትዮጵያዉያኑ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ አግንቸዋለሁ ያሉን ሻምበል ይልማ በላቸዉ ኮርያ ሳለን የእረፍት ግዜአችንን ጃፓን ድረስ እየሄድን እናሳልፍ ነበር ብለዉናል።
የማህበሩ ፕሬዝደንት እንደ ይልማ በላቸዉ ከደቡብ ኮርያ በተገኘዉ የነጻ ትምህርት እድል ባለፈው አመት 60 ተማሪዎች ወደ ኮርያ ሄደዉ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ 140 ተማሪዎችን ለመላክ ዝግጅቱን አጠናቀናል ብለዋል ። ከነዚህ መካከል የ 25 ዓመቱ ወጣት ሚኪያስ የኋላእሸት ይገኝበታል።
ለአንድ ዓመት የሞያ ስልጠና ወደ ኮርያ ለመሄድ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ የነገረን ወጣት ሚኪያስ የኋላ እሸት በወር ሶስት መቶ ዶላር እየተከፈለዉ ወደ አንድ ዓመት ተኩል ግድም የሞያ ትምህርቱን እንደሚከታተል አጫዉቶናል።
ከዛሬ 60 ዓመት በፊት በነበረው የኮርያ እርስ በርስ ጦርነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካይነት ወደዚያው ከዘመቱ አገራት መካከል ለኢትዮጵያዉያን ብቻ የመታሰብያ ሐዉልት ቆሞ ይገኛል፤ ያሉን የኮርያዉ ዘማች ኮሎኔል መለሰ፤ ትዝ የሚለኝን የኮርያ ዜማ ላዚምላችሁ ብለዉ አዚመዉልናል፤ ለቅንብሩ መሳካት ቃለ ልልስ የሰጡትን በሙሉ በዶቼ ቬለ ስም እናመሰግናለን።
ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

germen amharic radio....

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የት-መጣነት(origin) ጉዳይ ባደረጉት ጥናት ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ)

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የት-መጣነት(origin) ጉዳይ ባደረጉት ጥናት ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ)

”እኛ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሕዝብ ነን።እራሳችንን ዝቅ ማድረግ አይገባንም።ለምን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች አሁን? ይህ ማለት ኢትዮጵያን ያስጠሩ ሰዎች ቀድመው ነበሩ ማለት ነው።……ቀድሞ ‘ኢትዮጵ’ የሚባል ሰው ስለነበረ ነው።ለሀገር ሲሆን ‘ኢትዮጵያ’ አሰኛት እናም ከእርሱ ዘር የተወለድነው ሁሉ ኢትዮጵያውያን እንባላለን።እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ጃማይካ ነኝ ወዘተ ብልም ሃቁ እንዳፈጠጠ አለ።ይህ ሰው የኢትዮጵ ልጅ ስለሆንኩ እኔ ሁላችንም ብታምኑም ባታምኑም፣ብትክዱትም ባትክዱትም  ሁላችንም የእርሱ ልጅ ነን።እርሱ ከየት መጣ ለሚለው በሚወጣው መፅሐፌ ላይ ተዘርዝሯል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት እንደመጣን ከስር መሠረታችን የሚታወቅ እንጂ ሜዳ ላይ የተጠልን አይደለንም።ማንነታችን በትክክል የተመዘገበ እና የታወቀ ከማንም በላይ በእዚህ ምድር ላይ ከአይሁዳውያንም ቀዳሚ ነን።”
በመቀጠል ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለ ኩሽ፣ሴም፣ሰለሞናውያን ስርወ-መንግስት፣ስለ የኦሮሞ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግስና ታሪክም ሆነ የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ የነበረውን ታሪክ ሁሉ በሰፊው ተንትነዋል።”ለእዚህ ሁሉ ታሪክ ማስረጃ ምንድነው?” ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ መልሰዋል-
”ታሪኩ እስከ ዛሬ አንድ ሺህ አመት ድረስ  በደንብ ይታወቅ ነበር።ዮዲት ጉዲት ስትነሳ መፃህፍትን ሁሉ ስታጠፋ እና  የአክሱም መንግስት ሲፈርስ ‘አክሱማይ ሲራክ’  የተባለ ሰው  ፅሁፉን ይዞ ወደ ኑብያ(የአሁኗ ሱዳን) ተሰዶ እዝያው ሞተ።በኃላ ንጉስ ላሊበላ ከኢየሩሳሌም ስደት ሲመለስ መፅሐፉን ከኑብያ ወስዶ አፃፈው።በኃላ ግን የግብፅ ጳጳሳት ታሪኩን ለማስጠፋት ብዙ ሰሩ።አንዱ ምክንያታቸው መፅሐፉ ከጥንት የኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሮ እስከ ዮዲት መነሳት ጊዜ ብቻ የሚናገር ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ ማስተማር ሳይጀምር ለኢትዮጵያውያን ለሶስት አመት ያክል ቀ 22 ዓመቱ እስከ 25 አመቱ ድረስ ማስተማሩን በትክክል ይናገር ነበርና ነው።በእዚሁ መሳደድ ዳግም መፅሐፉን ይዘው አባቶች ወደ ኑብያ ተሰደዱ። ……መፅሐፉ የዛሬ 50 አመት ገደማ አንድ መነኩሴ ኑብያ ከፈራረሱ ህንፃዎች መካከል ሱዳናውያን የጥንት መፃህፍት መኖራቸውን ነገረዋቸው አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አመጡት።ከእዛ ወዲህ በተቆራረጠ መልክ መፅሐፉ ታትሟል።” ብለዋል።
የታሪክ ምርምር ቀጣይ ነው። ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በማስረጃ የተደገፈ የምርምር ውጤታቸውን አቅርበዋል።በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ እራሱን የቻለ መረር ያለ ምርምር ማስፈለጉን የሚያመላክት ነው።ቃለ ምልልሱ ሙሉውን በአንክሮ ሊሰሙት የሚገባ ነው።ያዳምጡት።
 የቀድሞው የኢቲቪ ዝነኛ ጋዜጠኛ ብዙ ወንድማገኘሁ  በፓልቶክ ስሟ (ሙያዬ) አወያይነት ይህ ዶ/ር ፍቅሬ ያደረጉት ቃለ መጠይቅ የተካሂደው  በኢትዮጵያ የመወያያ መድረክ ፓልቶክ (ECADF)  ነው።
freedom4ethiopian

Friday, July 19, 2013

ያሬዳዊ ዜማ በጀርመኑ መድረክ


ያሬዳዊ ዜማ በጀርመኑ መድረክ

ባለፈዉ ሳምንት የራድዮ ጣብያችን ባለበት ቦን ከተማ አቅራብያ በሚገኘዉ ኮለኝ ከተማ ባሉ የተለያዩ የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት፤ ከዓለም ሀገራት የተሰባሰቡ ከያንያን የአገሮቻቸዉን ጥንታዊ የሙዚቃ ስልቶችን አቅርበዋል።
በዚህ ዝግጅት ላይ ያሪዳዊ ዜማን ያቀረቡ ኢትዮጵያዉያንም ተካፋይ ነበሩ፤ በኮለኝ ከተማ ባለፈዉ ሳምንት ዓርብ በቀረበዉ ዝግጅትን ቃኝተን በዕለቱ መሰናዶአችን ልናካፍላችሁ ይዘናል፤

«የሮማዉ በጋ በኮሎኝ» የተሰኘዉ እና ከ25 ዓመት በፊት የጀመረዉ የሙዚቃ ድግስ በኮሎኝ ከተማ በሚገኙት 12 የሮማ ካቶሊካዊ አብያተ ክርስትያናት አቅርበዉ ነበር። አንጌሎስ/ ዲያቤሎስ --በጥሬ ትርጉሙ ፣ መላእክትና ዲያብሎስ በሚል ስያሜ የተካሄደዉ የሙዚቃ ምሽት ላይ በዓለም ዙሪያ ፣ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ የጥንታዊና ዘመናዊ ሙዚቃ አዋቂዎች፤ ተካፋይ ነበሩ። በመካከለኛዉ ዘመን እና ከዛም ለዘመናዊ ሥልጣኔ የመነቃቃት ሂደት በተጀመረበት ዘመን የተከሠተ የሙዚቃ ስልቶችን ማለት የባሮክ ሙዚቃ፤ የረቂቅ ሙዚቃ እና የጃዝ ሙዚቃ የመሳሰሉትን አቅርበዉ ተቀባይነትን አግኝተዉ እንደነበር ይታወሳል።
ባለፈዉ ዓርብ ምሽት በኮለኝ ማዕከል በሚገኘዉ ቅድስት ማሪያ የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተለያዩ መንፈሳዊና ፍልስፍና ይዘት ያላቸዉ ባህላዊ ሙዚቃዎች ቀርበዋል። በቅድስት ማርያ ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ የተካሄደዉ ዝግጅት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት እስከ ለሊቱ ስምንት ሰዓት የዘለቀ ነበር። የጀርመን፤ የቡልጋርያ ጥንታዊ የረቂቅ ሙዚቃ ቅላጺ በጥንታዊ እና ዘመናዊ ሙዚቃ ተቀናብረዉ የቀረቡበት መዘምራንን ያቀፈ ነበር። በዚሁ እስከ ሌሊቱ ስምንት ሰዓት በዘለቀዉ የሙዚቃ መድረክ ላይ የዳዊት ዝማሬን ያቀረቡ የያሬድ መዘምራን አባላት ተካፋይ ነበሩ።
ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ ሃገራት የተለያዩ ባህላዊ ሙዚቃ መሣርያን በሚጫወቱ በተለያዪ የዓለም ቋንቋዎች የሚያዜሙ ከያኒዎችን ወደ ጀርመን በመጋበዛቸዉ የሚታወቁት በጀርመን ታዋቂ የሆኑት ሙዚቀኛ ፒት ቡደ «የሮማዉ በጋ በኮለኝ» በተሰኘዉ የዓለም ጥንታዊ የረቂቅ ሙዚቃ ድግስ ላይ ተገኝተዋል። ፒት በዚህ ለሙዚቃ ድግስ አዘጋጆች ከኢትዮጵያ የጥንታዊዉን የያሬድን ዜማ ቢያስደምጡ ጥሩ መሆኑን ምክር ሰጥተዉ የያሬድ ዝማሪ እና የበገና ዜማ በድግሱ ላይ መቅረቡን ነግረዉናል ። ፒት ቡደ በገና አሉ ፤

«ለባህላዊ ሙዚቃ ከፍተኛ ፍቅር አለኝ። ያንን ስል የተለያዩ አገራት ባህላዊ ሙዚቃ ማለቴ ነዉ። አብዛኛዉን ግዜ ወደ ኢትዮጵያ በመሄዴ ብዙ ነገሮችን አይቻለሁ፤ እንደ አዲስም ተዋዉቄአለሁ። የዳዊት በገና ግን ልዩ ሆኖ ያገኘሁት፤ በጣም አስገራሚ የሆነ የሙዚቃ መሳርያ ነዉ። በገና የዘመናት ታሪክ መግለጫ ጥንታዊ መሳርያ ነዉ። የበገና ሙዚቃን ሲሰሙ፤ ራሱን መሳርያዉን ሲያዩ ሙዚቃ ከ2000 እና ከ 3000 ዓመት በፊት ምን አይነት ቅላጼ እንደነበረዉ መረዳት ይቻላል። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሌላዉ ዓለምም የሙዚቃ ዓይነቱ ምን እንደሚመስል ገላጭ ነዉ። ከበገና የሚደመጠዉ ዜማ፤ ጥንታዊና እጅግ ንጹህ ሙዚቃ ነዉ። የበገና ቅላጼ ከሚዜመዉ ዜማ ጋር ሲደመጥ፤ በተለይ ደግሞ በድሮ ግዜ በአዉሮጳ የነበረዉ አይነት ሙዚቃ በመሆኑ፤ በአሁኑ ዘመን ይህን አይነቱን ዜማ ማግኘትና ማድመጡ እጅግ አስደሳች ነዉ»
በአውሮጳ ሙዚቃ ገናና ስም ያላቸው የሙዚቃ ቀማሪውች ከመፈጠራቸው ከሺህ ዓመታት ቀደም ብሎ የተፈጠረዉ የሙዚቃ ሊቅ የቅዱስ ያሪድ ዜማን ከኢትዮጵያ የመጡት የቅዱስ ያሪድ መዘምራን እጅግ ሰፊና ረጅም ጣሪያ ባለዉ በኮለኙ የቅድስት ማርያ ካቶሊካዊ ቤተክርስትያን መድረክ ሲዜሙ እጅግ ዉበትን አግራሞትን አጎናጽፈዋል የሙዚቃ ድግሱን ለማድመጥ በቦታዉ ላይ የነበሩት እድምተኞችም ደስታና አግራሞታቸዉን በጭብጨባ ገልጸዋል፤ ያሪዳዊ ዜማን ያቀረቡት ደብተራዎች ሲሉም ነዉ ያወቋቸዉ፤

በአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምርያ ሃላፊ እንደሆኑ የነገሩን መምህር እንቁ ባህሪ ተከስተ፤ ያሪዳዊ ዜማን በአዉሮጳ ለማቅረብ አላማ አድርገን የመጣነዉ ቅዱስ ያሪድን ለማስተዋወቅና በዓለም ቅርስነት ለመያዝ ነዉ።
የቅዱስ ያሪድ ታሪክ በጀርመንኛ እና በእንጊሊዘኛ ጽሁፍ ታትሞ፤ የበገና ምንነት እና የኢትዮጵያ ታሪክ በጥቂቱ የሰፈረበት መግለጫ አነስ ያለች መጽሄት፤ ገና የሙዚቃ ድግሱ ሳይጀምር ተመልካቹ ወደ ቤተ-ክርስትያኑ ወደተዘጋጀለት ቦታ ሲገባ ይዞ ነበር የገባዉ፤ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ ለጀርመናዉያን አዲስ እንግዳ አልነበሩም፤ ገና በገናቸዉን ይዘዉ ወደ መድረኩ ሲቀርቡ ተመልካቹ በሞቀ ጭብጨባ ተቀበላቸዉ፤
ከዝያም የዜማቸዉን ፍቺ አጠር ባለ መልኩ በእንግሊዘኛ ተርጉመዉ በገና ድርደራቸዉን ቀጠሉ ፤
ጀርመናዉያኑ የበገና ድርደራዉን አይተዉ ሲደመሙ ሲደሰቱ ላየ፤ ለተለያየ ባህልን የማወቅ ጉጉታቸዉ፤ አልፎ ተርፎም መዉደዳቸዉን ማየቱ በራሱ የሚሰጠዉ ደስታ ለመግለጽ ትንሽ ያዳግታል፤ አሁንም በጭብጨባ ምስጋናቸዉን አቀረቡ አለሙ አጋም በገና ድርደራቸዉን
መጋቤ ስብሃት ዓለሙ አጋ በዚህ ዝግጅታችን ሲቀርቡ የመጀመሪያቸዉ ባይሆንም ስለ ስም
ማዕረጋቸዉ ግን አልጠየቅናቸዉም መጋቤ ስብሃት አሉ እዉቁ በገና ደርዳሪ አለሙ አጋ ፤ ምስጋናን በማቅረቤ ምስጋናን በመመገቤ ነዉ ሲሉ መልሰዉልናል። ያሪዳዊ ዜማን በኮለኙ ቅድስት ማርያ ካቶሊካዊ ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ በተዘጋጀዉ የጥንታዊ ፍልስፍናን የሚያንፀባርቅ ፤ የረቂቅ ሙዚቃና ባህላዊ የቤተ-ክርስትያን በቀረበበት መድረክ ላይ ካቀረቡት ቡድኖች መካከል ሊቀ ጠበብት ገብረ መስቀል ሙሉም ይገኙበታል። ዝማሜ አቋቋም ወረብ እና ሽብሸባን ዉብ የሆነዉን ባህላዊ አልባሳት አድርገዉ በኮለኝ ከተማ ለጀርመናዉያን ያቀረቡት፤ የቅዱስ ያሪድ መዘምራን፤ ወደ አገር ቤት ከመመለሳቸዉ በፊት፤ ለራድዮ ጣቢያችን አንድ መቋሚያ እና አንድ ጸናጽል አበርክተዋል፤ በምስጋና ተቀብለን፤ የዝግጅት ክፍላችን የመታሰብያ እቃ ማስቀመጫ ማህደር ዉስጥ አኑረናል፤ እናመሰግናለን። መጋቤ ስብሃት አለሙ አጋ ላደረጉልን ትብብርም ምሥጋናችን እናቀርባለን። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ