Wednesday, July 31, 2013

ጨው ጥቅሙና መዘዙ፣


ጨው ጥቅሙና መዘዙ፣

«ጨው ሲበዛ ያቅራል ፤ በርበሬ ሲበዛ ይመራል» ይባላል፣ ለሰውና እንስሳ ጠቀሚ ከሆኑ ማዕድናት መካከል አንዱ ጨው ነው፤ የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት(WHO) እንደሚመክረው ከሆነ እያንዳንዱ ሰው በየቀኑ መጠኑ ፣ከ 5 ግራም የማይበልጥ ጨው መመገብ
ይኖርበታል። ከዚህም ጋር ተያይዞ፤ ፖታሲየም በቀን 3,5 ግራም ጠቃሚ ነው ተብሎ እንደተመሠከረለት በዚህ በጀርመን ፤ ለህሙማን ጠቀሚ ምክርም ሆነ ትምህርት ያካፍላል ተብሎ የሚታመንበት ፣ የቤት ሀኪም(ሃውስ አርትዝት)የተሰኘው መጽሔት አስገንዝቦአል።
ጨው ይጠቅማል ብለን ስናወሳ፣ ምን ዓይነት የትኛውን ጨው ማለታችን እንደሆነ በቅድሚያ ግልጽ ማድረግ ሳይኖርብን አይቀርም።
ለምግብ ማጣፈጫ ሰዎች የሚጠቀሙበት የተለመደው ማዕድን ጨው ፣ በሥነ-ቅመማ ስሙ «ሶዲዮም ክሎራይድ» (NaCl)የተሰኘው ነው። ጨው፤ ሳይጣራ እንዲሁ የባህሩን ከውሃ ጋር የተቀላቀለውን በማቅረብ ባልተጣራ መልኩ ወይም አጣርቶ ማቅረብ ይቻላል። ለጤንነት ይበልጥ ተፋላጊ የሆነውና ሃኪሞች በሚያሳስቡት መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀው ፣ አዮዲን (አዮዳይን)የተሰኘው ሌላ ማዕድን የተቀላቀለበት ነው። ለአንስሳትና ሰዎች ህልውና እጅግ ጠቃሚ መሆኑ የሚነገርለት ጨው፤ ሲበዛ ለተጠቀሱት ክፍሎች ባቻ ሳይሆን ለዕጽዋትም ጎጂነቱ ከቶውንም አያጠራጥርም። የተመጠነ ጨው፤ ምግብን አጣፍቶ ለሰውነት ለአጥንትም ሆነ ለደም የሚጠቅም መሆኑ ብቻ ሳይሆን ምግብ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግም ፍቱንነቱ የሚያጠራጥር አይደለም።
ጨው ፣ በዓለም ህዝብ ታሪክ፣ ለምግብ ማጣፈጫነት የረጅም ዘመናት ታሪክ ነው ያለው። ሰው በቅድሚያ በሠፈረባቸውና ሥልጣኔ ባሥፋፋባቸው የዓለም ክፍሎች ብቻ ሳይሆን፤ በማዕከላዊው አውሮፓ በምትገኘው ጀርመን እንኳ፤ የ 3,100 ዓመታት ታሪክ ያለው መሆኑ ነው የተገለጠው። የጀርመን ዛኽሰን አንሃልት ፌደራል ክፍለ ሀገር፣ በቁፋሮ የጥንት የሥልጣኔ አሻራዎችን የሚያስሱ ጠበብት ባልደረባ የሆኑት ሃራልድ ሜለር ፤ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ጥንታዊውን የጨው ማዕድን ማውጫ ቦታ ለተመልካቾች በማሳየት እንደገለጡት ከሆነ፣ በሃለ ከተማና አካባቢዋ ይኖር የነበረው ህዝብ ፤ «ነጩ ወርቅ » የሚል ተቀጥላ ስም አግኝቶ በነበረው ጨው ሳቢያ ፣ ለሺ ዓመታት በተሻለ የኤኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመገኘት በቅቷል።
በኢትዮጵያ፣ በተለይ በአፋር በረሃ በዳሉልና አካባቢው የሚገኘው ጨው ፣ እየተጠረበ ፣ አሞሌ ጨው በመባል የታወቀው ጡብ መሰል ጥሬ ጨው፤ በነጋዴዎች አማካኝነት ለደጋው አገር ህዝብ ፣ ከዚያም አልፎ ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች እየተሸጠ፤ ለተጠቃሚዎቹ ተፈላጊ ምርት ፤ ለሻጮቹም ዋና ወረትም ሆነ ንብረት ሆኖ እስከዛሬ ድረስ የንግድ ልውውጡ እንደቀጠለ ነው። ይኸው የጨው ንግድ የ 30 ሺ ዓመታት ያህል ታሪክ እንዳለውም ነው የሚነገረው። የሰሃራ ምድረ በዳ በር ፤ የምሁራንም ዋና ማዕከል የነበረችው ቲምቡክቱ፣ የ 12ኛው ክፍለ ዘመን ነጋዴዎች፤ የጨውን ዋጋ ፣ ከመጽሐፍትና ወርቅ አሳንሰውት አያውቁም ነበር።
በጥንታውያን ግብጾች፤ ሜሶፖታማውያን፤ ቻይናውያን ግሪኮችና ሮማውያን ጨው፤ በተጨባጭነት ለምግብ ማጣፈጫ ብቻ ሳይሆን፤ በጥንታዊ እምነትና ልማድ፤እንዲሆም የተለያየ ሃይማኖች ልዩ ሥፍራ ሲሰጠው ኖሯል።

በጥንት ዕብራውያንና ግሪካውያን ዘንድ፤ መስዋዕት ሲቀርብ ፤ በሮማውያን አብያተ መቅደስም ፤ መስዋእቱ በጨው ታሽቶ ነበረ የሚቀርበው። በክርስትና ሃይማኖት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ፤ ደቀመዛሙትቱን፤ «እናንት የዓለም ጨው ናችሁ» ነው ያላቸው። ጨው ፣ ከመበላሸት ፤ኃጢአት ከሆነው ንቅዘት የሚከላከል ፤ የሚያጸዳ ኃይል እንዳለው ሆኖ ነው የሚታየው የሚተረጎመው ማለት ነው። በዘመነ ሐዲስ -ኪዳንም ፤ ጨው በምሳሌና በምልክት፣ የዕውቀት፣ ከንቅዘት ነጻ የመሆን ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል ያለ ዘለዓለማዊነትና ሥምረት ተምሳሌት ሆኖ ነው የተወሰደው።
መጽሐፍ ቅዱስ ፤ በአጠቃላይ ፣ ከ 30 በላይ ጨውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን አሥፍሯል። እ ጎ አ በ 1933 ዓ ም፤ የቲቤቱ ዳላይ ላማ ሲሞቱ፣ቀጥ ብሎ እንዲቆም በተደረገ ከጨው በተሠራ አልጋ ውስጥ ነበረ የተቀበሩት። በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ፣ በዛሬው ዘመንም ቢሆን የቆየ ልማድ እንዲጠበቅ በሚል ጭምር የሞተ ሰው ከመቀበሩ በፊት፣ ሬሣ- ሣጥኑ ውስጥ አንድ እፍኝ ጨው ይበተናል። ጨው፤ ከኃጢአት ነጻ የመሆን ፣ የዘለዓለማዊነት፣ ዲያብሎስንም ማበረሪያ ምልክት ሆኖ ነው የተወሰደው።
አስማተኞችና ርኩሳን መናፍስት እንዳያበላሹት በሚል ልማዳዊ እምነት እስኮትላንዳውያን በሚጠምቁት ቢራ ላይ ጨው ይጨምሩ ነበር። ለነገሩ የሚጠመቅ ቢራ ሳይበላሽ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆይ ፤ ጨው አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ፤ የሥነ ቅመማው ሳይንስ የሚያረጋግጠው ነው።
በመግቢያችን ላይ በጨረፍታ እንዳነሳነው፣ ለምግብነት የሚውል ጨው አዮዲን ማዕድን ሊኖረው ይገባል። አለበለዚያ ፣ ከአንገት ዕጢዎች (ታይሮይድ ግላንድ )የተባለው በማበጥ ወደ እንቅርት ይለወጣል። ኢትዮጵያ ፣ በያመቱ ከ 313,000 እስከ 399,000 ቶን ጨው እንደምትጠቀም ይታሰባል። በአዮዲን እጥረት በሚከሠት የጤና መቃወስ ሳቢያ ፣ አንዳንድ የዜና ምንጮች እንደሚጠቁሙት፤ በእርግዝና ወቅት፤ 50 ሺ ያህል ሰዎች ናቸው ህይወታቸው የሚያልፈው። በተለይ ህዝብ በርከት ብሎ በሚኖርባቸው በአገሪቱ ደጋማ አካባቢዎችም ሆኑ አምባዎች፤ የአዮዲንና አንዳንድ ጠቃሚ ማዕድናት እጥረት መኖሩ የታወቀ ነው።

በአሁኑ ዘመን ጨውን መጠን ባለፈ መልኩ፣ በተለያየ መንገድ ሰዎች እንደሚመገቡትና ይህም የደም ግፊትን ከፍ እንዲል በማድረግ በጤንነት ላይ ሳንክ እየፈጠረ ስለመሆኑ፣ የጤና ሳይንስ ባለሙያዎች ከማስመገንዘብ የቦዘኑበት ጊዜ የለም። ጨው፣ ድንገተኛ የልብ ድካምና ተመሳሳይ ህመም እንደሚያስከትል፣ ብርቲቱ የደም ግፊትም እንደሚያስከትል ነው የሚነገርለት። ከሞላ ጎደል የደም ግፊታቸው ከመደበኛው ትንሽም ቢሆን ከፍ የሚልባቸው ሰዎች የሚመገቡትን የጨው መጠን በአጅጉ መቀነስ ይኖርባቸዋል።
በምዕራቡ ዓለም ፤ በአሁኑ ጊዜ፤ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ፤ የምግብና መጠጥ አዘጋጂ ኩባንያዎች ወይም ታላላቅ የምግብ መደብሮች፣ በየጊዜው የሚቀርበውን ጤና-ነክ መመሪያ ልብ በማለት ፣ የሶዲዬም ፍጆታ መጠን እጅግ ዝቅ እንዲል እርምጃዎችን እስከመውሰድ መድረሳቸው ይነገርላቸዋ። ጨው በይበልጥ የሶዲየም ይዘት ተቀንሶ ፣ የፖታሲዮም ፍጆታ እንዲጨምርም ነው ምክር የሚሰጠው። ፖታሲየም ፤ በመሠረቱ፤ የባቄላ ዝርዮች ከሆኑ ጥራጥሬዎች፤ ከአተር፣ ከለውዝ ዓይነቶች ከ«እስፒናች»፤ ሙዝ ፓፓያና ቴምር ጭምር ይገኛል።
በብዙ አዳጊ አገሮች፤ እጅግ ተፈላጊ ከሆነው ኢምንት የምግብ ዓይነት ይበልጥ እጥረት የሚያጋጥመው ፣ የ «ቪታሚን ኤ»፣ አዮዲንና የብረት ማዕድናት ናቸው።
ጨው በሰውነት ውስጥ እንዴት እንደሚከማች፤ በልዩ ተልእኮ የተረጋገጠበት ሁኔታ አስገራሚም ተብሏል።

እ ጎ አ በ 1997 ዓ ም፣ ወደ ኅዋ ተጉዘው በነበሩት ጀርመናዊው ጠፈርተኛ ራይንሆልድ ኤባልድ ላይ የተከሠተው እንደ አንድ ማስረጃ ይጠቀሳል። አንዳች የስበት ኀይል በሌለበት ሰውም እንደ ላባ በሚንሣፈፍበት ኅዋ፣ በሰውነት ውስጥ የምግብ ዓይነቶች የሚያሳዩት ለውጥ ምን ይመስላል? ኤባልድ፤ ለ 2 ሳምንት ወደ ኅዋ በበረራ ላይ ሳሉና እንደተመለሱም፤ የሚመገቡትን በዝርዝር መጻፍ ነበረባቸው።
«በበረራው ወቅት፣ በአመጋገቤ፤ በምጠጣውም ጥብቅ ቁጥጥር ነበረ ያደረግሁና የመዘገብሁ። ታዲያ አስገራሚ ሁኔታ ነበረ የተከሠተው። እወስደው የነበረ ው የጨው መጠን ፤ መሬት ላይ ከሚወሰደው ወይም በህክምና መጽሔት ከምናውቀው የተለየ ነበር።»
ጠፈርተኛው የተመገቡት ፤ የጠጡትና የዕዳሪአቸውም ይዞታ በሚገባ ይመረመር ፣ ይመዘን ነበረና አስገራሚ ሆኖ የተገኘው፤ በኅዋው የበረራ ወቅት ብዙ ጨው ሰውነት ውስጥ መጠራቀሙ ነው። አንድ ጤነኛ ሰው፤ ሰውነቱ ውስጥ፣ በ 6 ሊትር ፈሳሽ ነገር ውስጥ ሊኖረው የሚገባ የጨው መጠን ነበረውና!
ተመራማሪዎቹ፣ ጨው በአጠቃላይ በኩላሊት በኩል ተጣርቶ ከሽንት ጋር መወገድ እንደሚኖርበት ቢታወቅም፤ የሰው አካላት ተግባራቸውን ፣ ሁሌ በተለመደው መልክ ብቻ እንደማያከናውኑ ነበረ ተመራማሪዎቹ የተገነዘቡት። ጨው በሰውነት ውስጥ የፈሳሽ ነጥረ ነገርን ዝውውር ማስተካከል ብቻ ሳይሆን፤ ደም ግፊት ላይ ተጽእኖ አለው። በሌላም በኩል፤ በአጥንት ግንባታም መሟሸሽም ረገድ አስተዋጽዖ ያደርጋል። በሽታን የመከላከል ሚናም አለው።ግራም ነፈሰ ቀኝ፤ ይህ ጠቃሚ ማዕድን፣ በሚያስፈልግ መጠኑ እንጂ ከሚገባው በላይ የሚወሰድ ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ጥንቃቄ ያሻል።
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ

ኢትዮጵያ በወሳኙ ጨዋታ ወሳኝ ተጨዋቾችን አታሰልፍም

ኢትዮጵያ በወሳኙ ጨዋታ ወሳኝ ተጨዋቾችን አታሰልፍም

  
ኢትዮጵያ ከመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ጋር በኮንጎ ብራዛቪል ላለባት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አይናለም ሀይሉን፣ አዲስ ህንጻንና ጀማል ጣሰውን እንደማታሰልፍ ፊፋ አሳወቀ፡፡

ተጨዋቾቹ የማይሰለፉት በማጣሪያ ጨዋታዎች ካርድ የተመለከቱ በመሆናቸው እንደሆነ ፊፋ  አስታዉቋል፡፡

በጨዋታው የማይስለፉ ተጨዋቾችን ለመተካት ለብሄራዊ ቡድኑ ከባድ ፈተና እንደሚሆን እየተነገረ ነው፡፡

መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ በሀገሯ ያለውን አለመረጋጋት ምክንያት በማድርግ ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገውን ጨዋታ በኮንጎ ብራዛቪል  እንዲሆን ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን /ፊፋ/ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

በዚህ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማሸነፍ ካልቻለ የተፈጠረውን ጥሩ አጋጣሚ  የሚያጣ ይሆናል፡፡

ደቡብ አፍሪካና ቦትስዋና በሚያደርጉት ጨዋታ አቻ ከተለያዩ በቀጥታ ኢትዮጵያ ማለፍ የምትችል ሲሆን ከሁለት አንዱ አሸንፈው ኢትዮጵያ ከተሸነፈች ወይንም አቻ ከወጣች ከውድድሩ የምትሰናበት ይሆናል፡፡

ኢሬቴድ፡- ስፖርት

ዓለም

ምርጫ በዝምባብዌ፣

የዝምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዛሬው ምርጫ የሚሸነፉ ከሆነ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ። አያሌ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት ሙጋቤ፣ ተፎካካሪአቸውን ጠ/ሚንስትር ሞርጋን ቻንጊራይን ለማሸነፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚተማመኑም ገልጸዋል። በሃራሬ
 የዶቸ  ቨለ ዘጋቢ ኮለምበስ ማቭሁንጋ የላከውን ዘገባ --ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ፣ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ፣ የዛሬው ምርጫ ለእርሳቸውና  ለ «ዛኑ-ፒ ኤፍ» ፓርቲያቸው ድልን የሚያጎናጽፍ እንደሚሆን ነው ያስረዱት። ከጠ/ሚንስትር ሞርጋን ቻንጊራይ ጋር  ሌላ ተጣማሪ አስተዳደር መሥረት የሚቻልበት አጋጣሚ ሁኔታ ይኖር እንደሁ ተጠይቀው ሲመልሱ፣---
«አይ፣ ያ አጋጣሚ በአሁኑ ጊዜ ይከሠታል ብለን አላከተትነውም ፤ ያለፈው ጊዜ ዓይነት  ሳይሆን የማያዳግም ዓይነት ውጤት እንደሚገኘው ነው የምንጠብቀው። ቀጥተኛ ውጤት ካላገኘን እንመክርበታለን። መተንበይ አንችልም። ተጨባጩን እውነታ እንደርስበታለን።  ይህ ተጨባጭ ሁኔታም ሆነ እውነታ  ደግሞ የሚወሰነው፣  ድምጽ በሚሰጡ መራጮች  ነው።»

እ ጎ አ  በ 2008 ዓ ም ምርጫ፣ ያሁኑ ጠ/ሚንስትር ሞርገና ቻንጊራይ፤ የተቃውሞው ወገን መሪ ነበሩ። በመጀመሪያው ዙር ምርጫ ፣ ሙጋቤን በነጥብ ቢበልጡም በሁለተኛው ዙር ፤ በሁለተኛው ዙር ወሳኝ ውድድር እ ጎ አ ከ 1980 ዓ ም አንስቶ በሥልጣን ኮርቻ ላይ የሚገኙትን በአፍሪቃ የረጅም ዘመን መሪ የሆኑትን አዛውንቱን ሙጋቤን ማፈናቀል አልተቻላቸውም። የአፍሪቃ መሪዎች የያኔውን ሁከት ያጀበውን ፣ ሙጋቤ ድል አድርጌአለሁ ሲሉ አዋጅ ያሰሙበትን የዳግም ምርጫ ውጤት አንቀበለውም  ነበረ ያሉት። ከዛሬው ምርጫ በፊት በመጨረሻው የምርቻ ዘመቻ  ንግግራቸው፣ ቻንጊራይ፤ ሥልጣኑን ከሙጋቤ መውሰዳቸው እንደማይቀር ነው የተናገሩት።
«በእኔ አስተዳደር ምሬታችሁ ይወገዳል። አዲሲቱን ዝምባብዊዌን በመገንባቱ ረገድ ተባበሩኝ። በመጀመሪያ በጠላትነት ዓይን እንተያይ ከነበረው ወገኖች ጋር ብስለትን በማሳየት፣  አዲሲቱን ዝምባብዌን  በመገንባቱ ረገድ እጅ ለእጅ  ተያይዘን ጉዞ እንቀጥል።ፕሬዚዳንት  ሙጋቤ፤ የጡረታ ዘመናቸውን ፤ በሰላምና ድሎት በትውልድ ሃገራቸው እንዲያሳልፉ ነው የምፈልገው።»

ሞርገን ቻንጊራይ፤ ሙጋቤ፤ የደቡባዊ አፍሪቃዊቷን ሀገር ኤኮኖሚ እንዲደቅ አድርገዋል በማለት ይወቅሳሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ሮበርት ሙጋቤ፣ ምርጫን የማያከብሩ አምባገነን እየተባሉ የሚሠነዘሩባቸውን አሉባልታዎች ዋጋቢስ አስተያየቶች ናቸው በማለት ለማጣጣል ሳይነሣሱ አልቀሩም ነው የተባለው። ሙጋቤ፣ የሚነቅፏቸው ወገኖች እንደሚሉት ምርጫዎችን እንደማያጭበረብሩ ነው የገለጡት።የዝምባብዌው ርእሰ ብሔር፣  በዛሬው ምርጫ ቢሸነፉ ከሥልጣን ይወርዱ እንደሁ ተጠይቀውም ሲመልሱ--
«ይህ መሆን ያለበት የተለመደ ጉዳይ ነው። ሁሉንም መሆን አትችልም ፣ ታሸንፋለህ ወይም ትሸነፋለህ። በምርጫው ካልቀናህ፤ ላሸነፉት እጅ መስጠት አለብህ። ካሸነፍህ፤ የተሸነፉት ወገኖች፣ ሽንፈትን   በጸጋ መቀበል ይኖርባቸዋል። ይህ ነው ፤ የምንደርገውም ይህንኑ ነው። ህጉ የሚለውን ተከትሎ መፈጸም!»
የ 89 ዓመቱ ጎምቱው የዝምባብዌ መሪ፤ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን፣ የምርጫውን ውጤት በተዓማኒነት የሚያቀርብ ገለልተኛ ተቋም ነው ሲሉም አስገንዝበዋል። የጠ/ሚንስትር ቻንጊራይ፤ ንቅናቄ ለዴሞክራቲክ ለውጥ(MDC) የምርጫ ኮሚሽኑ፤ በማጭበርበር የመራጮችን ድምጽ ፤ ለሙጋቤ «ዛኑ ፒ ኤፍ» ፓርቲ ይሰጣል በማለት መክሰሱ አልታበለም።  ከ 2 ሳምንታት በፊት፤ የዝምባብዌ መቅድማዊ ምርጫ በፀጥታ አስከባሪዎች ሲከናወን በህግ ከተፈቀደው በላይ ለ 3 ቀናት ተካሂዷል ነው ያለው-- MDC።

የዛሬው የዝምባባዌ ምርጫ፣ እ ጎ አ በ 2008 ዓ ም፤ ሁከት የተንጸባረቀበትና አነታራኪ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ፤ ሙጋቤና ቻንጊራይ ያቋቋሙት ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት፣ አሁን በይፋ ያከትምለታል። የትኛው ፓርቲ በተናጠል መምራት የሚያስችለውን ውጤት ያስመዘግብ ይሆን ? ከዛሬ ጀምሮ በሚከተሉት 5 ቀናት ውስጥ በይፋ ይታወቃል።
ዛሬ ምርጫው እንዴት እየተካሄደ እንደሆነ፣ አንድ ከደቡባዊው አፍሪቃ የልማት ማኅበረሰብ (SADC)የተወከሉ ታዛቢ እንዲህ ነበር ያሉት--
«እስካሁን አንዳች የማስፈራሪያ እርምጃም ሆነ ሁከት አልታየም የድምፅ አሰጣጡ ተግባር  በጥሩ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው። እርግጥ ገና በመሆኑ አጠቃሎ መናገር ያስቸግራል። በሌሎች የሀጋሪቱ ክፍሎች ምን እንዳለ አናውቅም። እስካሁን በሐራሬ ያየሁት ግን በጥሩ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን ነው።  
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

አስከፊው ስርዓት ከውስጥም ከውጭም ተወጥሯል።

አስከፊው ስርዓት ከውስጥም ከውጭም ተወጥሯል።

አበራ ሽፈራዉ /ከጀርመን/
የኢትዬጵያን ሕዝብ ሰብአዊና ቁሳዊ መብቶች በነፆነት ትግል ሰበብ ሕወሐት ለአለፉት 39 ዓመታት ሲረግጥ ቆይቷል።በመግቢያዬ ላይ ሀሳቤን በዚህ መልክ እንዳጠቃልል ያደረገኝ ደግሞ ባለፉት 39 ዓመታት የተከናወኑትን መለስ ብዬ ሳያቸው ከሰመሗቸው፣ካየሗቸውና ካነበብኳቸዉ እንደተረዳሁት በእርግጥም  ኢትዬጵያውያን በነዚህ ዓመታት በሕወሐት የለየለትና መሰሪ ተግባር  የተነሳ ሲገደሉ፣ሲታሰሩ፣ሰብዓዊ መብታችን ሲረገጥና፤በነፆነት ሥም ብዙዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሕወሐት ጥቅም አስፈፃሚነት ሲሞቱ አልያም የጥቅሙ ተቀናቃኞች በሙሉ ሕይወታቸዉን ሲያጡ ቆይተዋል፤አለፍም ካለ ደግሞ ያፈሩትን ንብረትና ሀብትም ለማጣት ተገደዋል፣ተዘርፈዋል፣ ተነጥቀዋል ፤እምቢ ካሉም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከዚህ አለም በጥይት ተገድለው በሞት ተለይተዋል ።
ከደርግ መንግስት ዉድቀት በኋላም ለ22 ዓመታት የታየው ተጨባጭ ሁኔታ በርግጥም እነዚህ ሕወሐቶች የኢትዬጵያ ቀንደኛ ጠላቶች መሆናቸውን አለምንም እፍረትና ይሉኝታ ሲያቅዱና ሲተገብሩ ቆይተዋል፤አሁንም ቀጥለዋል፤ተዉ ያለም የሚጠብቀው እስር፣ግርፋት፣መሰደድና ሞት መሆኑ ለሁሉም ኢትዬጵያውያን ብቻ ሳይሆን ዓለም እያወቀው ያለ ጒዳይ ሆኗል።
የውጭ ሀገራት የዲኘሎማሲና የውጭ ግንኙነቱም በተወሰኑ የጥቅም ግንኙነት ላይ ብቻ ባተኮረና የኢትዬጵያን ሕዝብ ጥቅም ወደጐን በተወ መልኩ የተከናወነ ሆኖ ቆይቷል፤በውጭ ሀገራት የዲኘሎማሲ ማህበረሰብ የሠብአዊና የፍትሕ ጥያቄ ሲቀርብ ግን እርሱ የእኔ ጒዳይ ነው ተዉት እያለ የሰው ልጆችን ከሰብዓዊነት ውጭ በመጨቆን በዚህ ዘመን የማይጠበቅ የጭቆናና የብዝበዛ ስርዓት በመሆን ቀጥሏል፤በየትኛውም የዓለም ሀገራት የማይፈፀም ግፍ ዛሬ በኢትዬጵያ ይፈፀማል።
የኢትዬጵያ ሕዝብ የሚያታግለው ስለአጣ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት ያካበተው ርህሩሕነት፣ቸርነት፣ቻይነት፣ይቅር ባይነት፣በመቻቻል አብሮ በጋራ መኖርንና መስማማትን ይዞ የኖረ ሕዝብ በመሆኑ ዛሬ ሕወሐት/ኢሕሐዴግ እነዚህን ጠቃሚ የማህበራዊ አኗኗር እሴቶች ለመጣል እየሞከረ ይገኛል፤ይሁንና በሕዝቡ ላይ ከልክ ያለፈ ግፍ በመፈፀሙና እነዚህን ለአገሪቷም ሆነ ለመሪዎቿ የሚጠቅሙ የማህበራዊ አኗኗር እሴቶችን ከሕዝቡ ላይ ለመሸርሸር በመሞከሩ ዛሬ ሕወሐት/ኢሕሐዴግን ለመጋፈጥ ብዙዎች ወደ ትግሉ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።
ሕወሐት/ኢሕሐዴግ ከለየለት ጥፋቱ ለመመለስ ባለመፈለጉና የሕዝብን ትግስት እንደፈሪ በመቁጠሩ ዛሬ ውጥረቱ
በራሱ በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ላይ ነግሷል፤ ወደደም ጠላም ተወጥሯል፤ሕዝቡ በድፍረት በሠላማዊ ሠልፍ ብቻ ለሕወሐት/ኢሕሐዴግ ጥላቻዉን እየገለፀ ይገኛል፤ይህም በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ሠፈር ትልቅ ድንጋጤን በመፍጠሩ የዉጥረቱን መጠን ለመቀነስ የሚደረጒ ልዩልዩ ስብሰባዎችም ቢሆኑ ሌላ ተጨማሪ ድንጋጤን በገዢዎቻችን ሠፈር እየፈጠሩ ይገኛሉ።
ሕወሐት/ኢሕሐዴግ የዲሞክራሲና የፍትህ ፅንሰ ሐሳቦች በፍፁም የማይገባዉና በ60ዎቹ የሶሻሊስት አስተሳሰቦች ተተብትቦ ፤በሰብአዊ ፍጥረት ላይ ባለዉ ንቀት የተነሳና ይኸዉ አሮጌ አስተሳሰቡ ዓለም ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አብረዉ ሊጓዙ የሚችሉ ወጣቶችን ለመሰብሰብ ባለመቻሉ፣የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ባለመፈለጉና በዚሁ አሮጌ አስተሳሰቦችና በጥላቻ ፖለቲካ በተመረዙ ሰዎች እየተመራ በመሆኑ ዛሬ ውጥረቱ በራሱ በድርጅቱ ዉስጥ እየሰፋ መምጣቱን ከራሱ ከድርጅቱ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ዛሬ ኢትዬጵያ ግልፅ ባልሆነ መልኩ በተደራጁ ማፍያዎች እንደምትመራ ኢትዬጵያን ብቻ ሳይሆኑ የአለም መሪዎች ጭምር እያወቁ የመጡ ይመስላል።
በቅርቡ እንኳን በዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ በጁን 20,2013 በኮንግረስ ማን የተከበሩ ስሚዝ ሰብሳቢነት በኢትዩጵያ ባለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ከመለስ በኋላ የምስክርነት ቃል መስማት በተከናወነበት ወቅት የተሰነዘሩት አስተየቶችና ለኢትዬጵያ መሪዎች ማነቆ የሚሆኑ ሕጐችን ለማውጣት ቃል መግባታቸዉን ስንመለከት አሜሪካ ከዚህ ስብሰባ በስተጀርባ በኢትዩጵያ ጉዳይ ላይ ያላትን ዕቅድ ለመተግበር መነሳቷን አልያም የሕወሐት/ኢሕሐዴግ መሪዎች አካሄድ እንዳላስደሰታቸው ያመለክታል።
ባለፈው ሰሞን የኢትዩጵያ የልማት ድጋፍ ስጪ አገሮች አምባሳደሮች የሰማያዊ ፖርቲ አመራርን ለማነጋገርና አንዳንድ መረጃ ለመለዋወጥ ማቀዳቸውና መተግበራቸው ከሕወሐት/ኢሕሐዴግ የይስሙላ ዴሞክራሲ ጋር ቅራኔ አንዳላቸውና በሕዝብ እንቅስቃሴም ዙሪያ የተለየ እይታ ይዘው መቅረባቸውን ፤እንዲሁም ለዘለቄታ ግንኙነታቸውና ጥቅሞቻቸው ሕዝብ ከጠላው ጋር መስራታቸው በታሪክ ሊያስጠይቃቸው እንደሚችል የገባቸውና ፤እነሱም ለውጥ ፈላጊ መሆናቸውን ማየት ይቻላል።
አውሮፓ ሕብረት የፖርላማ ተወካዬች በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ለመነጋገር በኢትዩጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ብንመለከት ደግሞ «ኑና እዪ»  የተባሉ ይመስል ሕዝቡ ላይ ያለዉን ችግር እራሳቸው በቅርበት ያዩትና እራሳቸውን ጭምር ያሳዘናቸው መሆኑና ፤የኢትዩጵያ ችግር እምን ደረጃ እንደደረሰ ለመረዳት ችለዋል። እነዚህ የአውሮፓ ህብረት የፖርላማ አባላት ኢትዩጵያ በምን አይነት ሰዎች እንደምትመራ ለመረዳት እንደቻሉና የተለየ አግራሞት እንደፈጠረባቸዉ በቀላሉ መረዳት ይቻላል ፤ ከዚህም የተነሳ ይመስላል የህብረቱ አባላት የታሰሩ ጋዜጠኞችና የተቀዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ከስር እነዲለቀቁ ፣ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዲከበር ፣የእምነትና የሀይማኖት ተቋማት መብትና ነፆነት እንዲከበር መግለጫ እስከማዉጣት የተገደዱት።
ይህ ብቻ አይደለም በሃገራችን በሁለቱ ትልልቅ የሐይማኖት ተቋማት አካባቢ ያለዉ « የፍትህ ያለህ » ጥያቄዎች በኢትዩጵያ መሪዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ባይነት ችግሩ እየተባባሰ ለመፍታት ወደሚቸግር አቅጣጫ እየመጡ መሆኑ የየዕለት ዜናዎች ሆነዋል።
ሌላው የሕወሐት/ኢሕሐዴግ ባለስልጣናት በመላው ዓለም ከኢትዩጵያን ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የሚገጥማቸዉ ተቃዉሞ በሌሎች  አገሮች ህዝቦች የሌለ በመሆኑ ህወሃቶች ምን ያህል በአገራቸዉ ዜጎች ዘንድ የተኮንኑ ለመሆናቸዉና አመኔታ የማይጥልባቸው መሆኑ እየታወቀ መምጣቱና በኢትዩጵያ አስክፊዉ ስርአት መሪዎች አካባቢ ትልቅ ድንገጤን እየፈጠረ መምጣቱ የቅርብ ጊዜያት እዉነታዎች ናቸዉ።
በቅርብ ደግሞ በሶስቱ ዋናዋና በአገር ውስጥ የስላማዊ ትግል አራማጅ ፓርቲዎች ማለትም በሰማያዊ ፓርቲ፣በአንድነትና በመድረክ ላይ እየደረሰ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ በህዝቡ ተቀባይነት ባይኖርዉም እንደለመደዉ ለጥቃት መዘጋጀቱንና በነዚህም ፓርቲዎች አባላተ ላይ እየደረሰ ያለዉ እስራትና ማዋከብ በሕወሐት/ኢሕሐዴግ ፓርቲ ላይ ትልቅ ውጥረትና ድንጋጤ መፍጠሩን ያመለክታል።
ሌላው በተለያዩ ጊዜያት ሕወሐት/ኢሕሐዴግ ለኤርትራ መንግስት የሚያቀርባችዉ በስጦታ የታጀቡ የንታረቅ ልምምጦች  ድንገት ሊነሳ የሚችል ጦርነት በስልጠናቸው ላይ የሚፈጥረዉ ችግር ትልቅ ፍርሃት እንደፈጠረባችውና ለስልጠናቸዉ ሲሉ የትኛውንም ነገር ለመስጠት መዘጋጀታቸዉን ያሳያል።
እነዚህ በገዢዉ ፓርቲ አካባቢ ያሉት ዉጥረቶች በስለላ መዋቅር ብዛት ፣ በስር ቤቶች ብዛት ፣ በወታደራዊ ትጥቅና ስልጠና ብዛት መፍትሄ  የማያገኙባቸዉ ዋናዋና ምክንያቶች ህዝቡ ክልክ ያለፈ ጭቆና ዉስጥ መዉደቁ ፣ግልጽ ዘር መድሎ መኖሩ፣ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሙስና መዘፈቃቸዉና የገዢዉ ፓርቲ ንግድ ተቋማት የንግድ ብዝበዛና ሌሎችም ህዝቡን ስላስመረረዉ ትግሉ የማይቆም ትግል መሆኑን ሁሉም ኢትዮዽያዊ እየተረዳ ያለው ሀቅ መሆኑም ጭምር ነው።
በአለፉት ዓመታት በዝርፊያ ፣በዘር ማጥፋት ተግባር ፣ ህዝቡን በማሰርና በመግደል፣በዘረኝነት መድሎ፣ በከፍተኛ ሙስና ተግባርና በሌሎችም ሀገርንና ህዝብን ሊጎዱ በሚችሉ ተግባራት ላይ መሰማራቱ ሊቀጥል እንደማይችል ሁሉም የተረዳዉ ሀቅ ሆኗል ።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች የስቪክ ማህበራትና ሌሎች የሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ አሁን ኢትዩጵያ ካለችበት ሁኔታ አንፃር  ኢትዩጵያን ከለየለት ጭቆና ለማላቀቅ በሚደርገዉ ትግል ይበልጥ መስባስብ ፣መመካከርና የመፍትሄ አቅጣጫን አስቀምጦ መንቀሳቀስ ጊዜዉ የሚጠይቀዉ ጉዳይ በመሆኑና የሕወሐት/ኢሕሐዴግ ውጥረት በህዝቡና በሃገሪቷ ላይ ሌላ ተጨማሪ ችግር እንዳይፈጥር አስቀድሞ መከላከል ጠቃሚ ነው እላለሁ።
እግዚአብሔር ኢትዩጵያን ይባርክ!

Tuesday, July 30, 2013

መረጃ በጨዋታ፤ በዱባይ ኤንባሲያችን ሆኗል አሉ “ገዳይ”

መረጃ በጨዋታ፤ በዱባይ ኤንባሲያችን ሆኗል አሉ “ገዳይ”

ዱባይ ሆይ የእህቶቻችን ሀገር እንደምን ነሽ… ለመሆኑስ እህቶቻችንን እንዴት ናቸው…በሻርጃ እና አቡዳቢ ጉያዎችሽ የደበቅሻቸው ጎረምሶችሽ በዚህ ሰዓት ምን እያሏቸው ይሆን… “ማዳሞችሽስ” ስንቷን የሀገሬ ሴት እየገላመጡ ስነቷንስ እያመናጨቁ ይሆን…

በፌስ ቡክ የመልዕክት ሳጥኔ አንድ መልዕክት መጣ፡፡ እንዲህ ይላል “በዱባይ ኤንባሲያችን እየሆነ ስላለው ነገር ልነግርህ ነበር” እኔስ ማነኝ፤ እስቲ አምጪው አልኳታ፤

በዩናይትድ አረብ ኢምሬት ዱባይ ኢትዮጵያ ኤንባሲ አሰራሩ ከይሲ ቢባል ይቀላል፡፡ እህቶቻችን ፓስፖርት ለማሳደስ ወይም ለአንድ ጉዳይ ወደ ኤንባሲ ደጃፍ ልክ ሲደርሱ የድሮ ቀበሌ አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ ቀበሌ ትዝ ይልዎታል ወዳጄ… ዘበኛውም ሊቀመንበሩም እኩል ሰው የማመናጨቅ ስልጣን የተሰጣቸው ቦታ እኮ ቀበሌ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ አሁን ግን ቀበሌ ተሸሽሏል፡፡ እኔ ሽሮሜዳን ትቼ “ልነካው” የነበረ ሰሞን ቀበሌ የሄደ ሰው የሚደረግለት እንክብካቤ… እንደው ያ ደህንነት ወዳጄ “ወግሞ” ባይዘኝ ኖሮ ለቀበሌያችን ፀባይ መሻሻል ስልስ እዛው ብኖር እመርጥ ነበር፡፡)

እናልዎ ዱባይ ያለው ኤንባሲያችን መጀመሪያ ሲገቡ የሚቀበልዎ፤ ከድሮ ቀበሌ በበለጠ ደረጃውን ያልጠበቀ ማመናጨቅ አቅርቦ ነው፡፡ ከዛ ለምንም ጉዳይ ይሂዱ የመጀመሪያው ጥያቄ ቦንድ ግዢ የሚል ነው፡፡ በጣም ስናጋንነው ኤንባሲ የሚሰራ ሰው ሰላም ለማለት የሄደች እንኳ ቦንድ ግዢ መባል አይቀርላትም፡፡

ከዛ በተጨማሪ ደግሞ “የኮሚኒቲ አባልነት” የሚባል ነገር አለ፡፡ አባል ያልሆነ ሰው በኤንባሲው በኩል ምንም ግልጋሎት አያገኝም፡፡ እንደውም አሟሙቆ ማውራት ምን ጠቅማል ብለን እንጂ… የኤንባሲው ሰራተኞች “አባል ያልሆነ ሰው ባል እንኳ እንዳታደርጉ” ተብለዋል አሉ፡፡

ቀልዱ ቀልድ ነው… ይቺ ወዳጄ በቃለ ምህላ እንደነገረችኝ፤ (መቼም ምላ አትዋሸኝም) አንዲት ኢትዮጵያዊት በኤንባሲዋ በኩል የሆነ ግልጋሎት ከፈለገች የኮሚኒቲ አባል ለመሆን ከሚከፈላት አምስት መቶ ድርሃም ውስጥ መቶ ሰማኒያውን “ሆጭ” አድርጋ መክፈል አለባት፡፡

ታድያ የሀገራችን ኤምባሲ በዱባይ ሆኗል አሉ ገዳይ ብንል ምን ውሸት አለብን ይባላል…

እንደውም ይሄንን ያጫወትኩት አንድ ወዳጄ ይሄማ ኤምባሲ ሳይሆን “ካዚኖ” ነው ብሎኛል፡፡ (መጣች እንግዲህ የዲያስፖራ ቃል… “ካዚኖ” ቁማር ቤት ነው፡፡ ቁማር ቤትስ ምንድነው… የሚል ካለ፤ ትንሽ ሰው የሚጠቀምበት ብዙ ሰው የሚከስርበት ተቋም ማለት ነው፡፡)

ስለዚህ እንላለን በዱባይ ካዚኖአችን ፈርሶ ኤንባሲያችን ይሰራ!
abetochichaw

ETVዬ፤ ይሄኛው መንገድ የት ያደርሰ ይሆን!?

ETVዬ፤ ይሄኛው መንገድ የት ያደርሰ ይሆን!?

አንድነት ፓርቲ ፤

“የፀረ ሽብር ህጉ ከሀገሪቱ ህገ መንግስት ጋር የሚፃረር በመሆኑ” ሊሰረዝ ይገባዋል አሉ፡፡

የኢቲቪው ጋዜጠኛ፤

ተቃዋሚዎች የሽብርተኞች ህግ ይሰረዝ እና ሀገራችን በሽብረኞች ትሞላ እንደ ሴሪያ እና እንደ ግብጽ ትበጣበጥ ይላሉ… እርስዎ በዚህ ላይ ምን የሚሰጡን አስተያየት አለ…?

አስተያየት ሰጪ፤

(ድንግጥ ብለው) “እንዴ… እንዴት እንደዚህ ይላሉ ነውር አይደለም አንዴ… መበጣበጥ ለማን ይጠቅማል… ይሄ ከአንድ ሀገር ሊመራ ካሰበ የፖለቲካ ፓርቲ አይጠበቅም…”

ድምፃችን ይሰማዎች፤

“የሼክ ኑሩ ግድያ የተቀነባበረ ድራማ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሟችንን የምናሰማው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው፡፡ የምንሞትለት እንጂ የምንገድልበት ሀይማኖት የለንም፤ ስለዚህ የሼሁ ግድያ መንግስት ነው የፈፀመው” ሲሉ ይከሳሉ…

የኢቲቪ ጋዜጠኛ፤

ፅንፈኞቹ የሼህ ኑሩ ግድያ ድራማ ነው እንጂ አልሞቱም ይላሉ እርስዎ ይሄንን እንዴት ያዩታል…?

አስተያየት ሰጪ፤

(ግራ ተጋብተው) “እንዴ… እንዴት እንደዚህ ይባላል… ይሄ ጭካኔ ነው፡፡ ለእነርሱ ድራማ ቢመስላቸውም እኛ ግን የቀበርነው አባት ነው፡፡”

አንድነት ፓርቲ፤

“የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ደላሎችን ማሰር ብቻ መፍትሄ አይሆንም ስር ነቀል የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል” አለ፡፡

የኢቲቪ ጋዜጠኛ፤

ተቃዋሚዎች በቅርቡ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሳታፊ የሆኑ ደላሎች መታሰራቸውን እንቃወማለን ብለዋል፡፡ እርስዎ በዚህ ላይ ምን የሚሰጡን አስተያየት አለ…?

አስተያየት ሰጪው፤

(ተደንቀው) “ይገርማል… እንግዲህ የህገ ወጥ ዝውውር ደላሎቹ ራሳቸው ናቸው ማለት ነዋ… ሰው እንዴት ወንጀለኛ አይታሰር ይላል… ወገኖቻችን ለከፋ አደጋ እየተጋለጡ ደላሎቹ አይታሰሩብን ካሉ ራሳቸውም ወንጀለኞች ናቸው ማለት ነው”

በጁምዓው ተቃውሞ፤

አንድ ሰውዬ ያረጀ ባንዲራ ይዞ ታየ፡፡ ልብ አድርጉልኝ አንድ ሰውዬ ነው፡፡ ሰውዬው ምናልባትም በቤቱ ያገኛትን አሮጌ ባንዲራ ይዞ ወጥቷል ወይ ደግሞ…. (ወይ ደግሞውን እንተወው… ብቻ ግን አንድ ሰውዬ ብቻ ነው ይሄ ሰውዬ በፍፁም ሚሊዮኖቹን ሊወክል አይቻለውም፤ ተቃውሞ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች የተሳተፉበት ነው)

የኢቲቪው ጋዜጠኛ፤

አክራሪ ሀይሎች ባለፈው አርብ ባንዲራውን ሲቀዳድዱ ነበር ይሄ የሀገር ክህደት አይደለም ይላሉ…

አስተያየት ሰጪ፤

እንዴ የሀገራቸውን ባንዲራ መቅደድማ አይገባም… ኢትዮጵያ እኮ ሀገራቸው ናት…ነውር አይደለም እንዴ…

ሌላም ሌላም…

ልብ አድርጉልኝ ኢቲቪ ይሄንን ድራማ የሚሰራው ሊዝናናን አይደለም፡፡ የምሩን ነው፡፡ ኮስተር ብሎ ነው፡፡ እየቀለደ አስደለም እየቀለደብን ነው እንጂ…

እና የምሬን ልጠይቅ ETVዬ፤ ይሄኛው መንገድ ግን የት ድረስ ያስኬድ ይሆን!?
abetockichaw...

ኢትዮጵያ የሀይል አጠቃቀም ፖሊሲዋን እየከለሰች ነው

ኢትዮጵያ የሀይል አጠቃቀም ፖሊሲዋን እየከለሰች ነው


አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 23 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ  የሀይል አጠቃቀም ፖሊሲ  አስራ ዘጠኝ አመታትን አስቆጥሯል ።
ይህ ፖሊሲው እስካሁን ያገልግል እንጂ አሁን ካለው የአገሪቱ  ነባራዊና  አለም አቀፍ ሁኔታዎች ጋር የሚጣጣም አይደለም።
በሀገራችን  በየዓመቱ በፍጥነት እያደገ ያለውን የሀይል ፍላጎት መናርን ከግምት ውስጥ አለማስገባቱም ሌላው እጥረቱ ነው ።
ከዚህም ባሻገር ለሀይል አቅርቦት ሲባል በርካታ የውጭ ምንዛሬ እያወጣች የምታስገባቸውን ምርቶች እዚሁ ልታመርት ስትችል ይህን እምቅ ሀይል እንድትጠቀም ብዙም የሚያበረታታ አይደለም ይላሉ  በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ጥናትና ልማት ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ መንግስቴ ።
ዳይሬክተሩ  እንደሚሉት ፥ በስራ ላይ  ያለው  የሀይል ፖሊሲ አገሪቱ  ታዳሽ  ሀይል እንድትጠቀም ቢያበረታታም ፥ ኢትዮጵያ ካስቀመጠችው መካከለኛ  ገቢ ካላቸው አገራት  ተርታ  የመሰለፍ ግብ  ጋር  የሚናበብም  አይደለም ።
ለአብነትም  ኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት እንዳላት ጥናቶች ቢያሳዩም አሁን ሁሉንም የነዳጅ ፍላጎቷን በውጭ ምንዛሬ እያስገባች ነው ።


የጋዝ ክምችት
በዘርፉ  በተካሄደው ጥናት መሰረት በምስራቅ ኢትዮጵያ ብቻ  ሌሎች አይነት የሀይል ምንጮች ሳይካተቱ አንድ መቶ አስራ ሁለት ቢሊዮን ኩዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አላት።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2000 እስከ 2009 ድረስ ብቻ የኢትዮጵያ የፔትሮሊየም ፍላጎት በ87 በመቶ አድጓል።
በተመሳሳይ በ2009 ብቻ ሀገራችን ነዳጅ ለማስገባት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር አውጥታለች።
ይህ ማለት ሀገሪቱ በወቅቱ ከውጭ ንግድ ከምታገኘው ብር አብላጫውን ይወስዳል እንደማለት ነው ።
ክለሳው የሚወልደው አዲስ ፖሊስ ተግባር ላይ ሲውል ታዲያ ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን ፔትሮሊየም ባዮ ፊውል በመሰሉት የታዳሽ  ሀይሎች ዓይነት  መተካት የሚያስችላት ነው ።
በተጨማሪም ፖሊሲው ሀገራችን የራሷን የተፈጥሮ ጋዝ እንድታለማ በእጅጉ እድል ይሰጣል።

 የሀይል ብክነት
ፖሊሲው የሀይል ብቃትና የቁጠባን አሰራር በጥብቅ የሚያዝ ሲሆን ፥ በተለይም የኤሌክትሪክ ሀይል ብክነትን ከመከላከል አንጻር የጎላ ሚናን ያበረክታል ተብሎም ነው የታመነበት ።
የኢትዮጵያ  ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽንን በመሰሉ የሀይል አቅራቢና  በተጠቃሚው መካከል መሟላት ያለባቸው የሀይል አጠቃቀም መስፈርቶች ላይም ልዩ ትኩረት ይሰጣል ።
በ6 ሺህ የሀይል ተጠቃሚ ድርጅቶች ላይ የተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው ፥ ድርጅቶቹ ሙሉ ለሙሉ የሀይል አጠቃቀማቸው በብክነት የተሞላ ነው።
ድርጅቶች ከሚያገኙት የኤሌክትሪክ ሀይል ቢያንስ ዘጠና በመቶውን መጠቀም እንዲኖርባቸው ይጠበቃል።
ሆኖም እጅግ ጥቂት የሚባሉት ድርጅቶች ከሚደርሳቸው የኤሌክትሪክ ሀይል ሰማንያ በመቶውን እንደሚጠቀሙና ብዙዎቹ ከሚያገኙት ሀይል ከግማሽ በላይ የሚሆነውን እንደሚያባክኑ ነው ጥናቱ የሚያመለክተው ።
አዲሱ ፖሊሲ ድርጅቶች የሚበቃቸውን ሀይል ብቻ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን እንዲጠቀሙ የሚያስችሉ አሰራሮችን ያበረታታል።


የአቶም ሀይል ለኢትዮጵያ
አዲሱ ፖሊሲ የአቶሚክ ሀይልን በረጅም ጊዜ ከጥንቃቄ ጋር መጠቀምን አካቷል።
በሀገሪቱ በህክምና ተቋማትና በግብርናው ላይ የአቶም ሀይል ጥቅም ላይ ቢውልም ፥ ከሀይል አንጻር ያለው አቅርቦት ግን ምንም ነው ማለት ይቻላል።
አቶ ጎሳዬ መንግስቴ  እንዳሉት ለአቶም ሀይል ማበልፀጊያ  ከሚያስፈልጉት ሀብቶች መካከል ዩራንየም በአገሪቱ  እንደሚገኝ ለማወቅ ጥናቶች እየተደረጉ ነው ።
በተጓዳኝ  ግን አገሪቱ የአቶም  ሀይልን መጠቀም  የሚያስችላትን የአቅም  ግንባታ  ስራ  የሚከናወን ይሆናል ነው የሚሉት ።
ፖሊሲው የግሉ ዘርፍ በሀይል ዘርፍ እንዲሳተፍ እድልን ይከፍታል።
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የታዳሽ ሀይል ማዕከል ሆና እንድትወጣ ያለመም ሲሆን ፥ ይህም የሚፈጥረው የሀይል ንግድ ትስስር ሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ያደርጋታል ተብሎ ታምኗል።

በካሳዬ ወልዴ

source...fanabc.com

ንዋዬ ቅድሳት ለማስጠበቅ የሚጥር ማኅበር፣


ንዋዬ ቅድሳት ለማስጠበቅ የሚጥር ማኅበር፣

የኢትዮጵያን አብያተ ክርስቲያን ንዋዬ ቅድሳትና የተለያዩ ቅርሶችን በሥርዓት ለመጠበቅ ባለመቻሉ፣ የሚያስጠብቅም ባለመኖሩ ፣ ባለፉት አያሌ ዓመታት እጅግ በዛ ያሉ ንዋዬ ቅድሳትና የተለያዩ የቤተክርስቲያኒቱ ቅርሶች ወደ ውጭ እየተጋዙ ገበያ ላይ መዋላቸው እንግዳ ነገር አልሆነም።
ከዚህ ቀደም ለቅርስ ጥበቃ ቆመናል የሚሉ ድርጅቶች ባይታጡም፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች እንክብካቤና ልማት ማኅበር የተሰኘ አንድ ሌላ አዲስ ድርጅት መመሥረቱን ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ የላከልን ዘገባ ያስረዳል። አዲሱ ማኅበር፤ አዲስ አበባ ውስጥ በኢንተር- ኮንቲኔንታል ሆቴል ባዘጋጀው የምክክር መድረክ፤ በህገ ወጥ መንገድ ቅርሶች ከሀገር የሚወጡበት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ለይ መድረሱን ጥናት ያካሄዱ ምሁራን ገልጸዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
dw.de

Ethiopia: The Contradiction of Religious Equality and Democracy የሃይማኖት እኩልነት በዲሞክራሲ ሥርዓት እንዴትነት የፈጠረው ተቃርኖ

Ethiopia: The Contradiction of Religious Equality and Democracy የሃይማኖት እኩልነት በዲሞክራሲ ሥርዓት እንዴትነት የፈጠረው ተቃርኖ

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው amsalugkidan@gmail.com የሃይማኖት እኩልነት በዲሞክራሲ ሥርዓት እንዴትነት የፈጠረው ተቃርኖ በዚህ “መንግሥት” የዚህ ጽፉፍ መቸት ከጥቂት ወራት በፊት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አሁን ሥራ ላይ ያዋለውን መመሪያ ባወጣበት ወቅት ጋዜጣ ላይ የጻፍኩት ጽፉፍ ነው እነሆ፡- መሰንበቻውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስቴር የእምነት ተቋማትን ለመመዝገብ (ለመቆጣጠር) አንድ መመሪያ ማውጣቱና እያነጋገረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ መመሪያ የተረቀቀውና ተግባራዊ ሊደረግ ታስቦ የነበረው በተመሳሳይ ዓላማና አንቀጾች በተለያዩ ሰብአዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰማርተው ይሠሩ የነበሩትን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (NGOs) ያሽመደመደው፣መፈናፈኛ ያሳጣውና ከአገልግሎት ውጪ ያደረገው ደንብ ወይም መመሪያ ወጥቶና ተግባራዊ ሆኖ ለዓላማቸው አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበላቸው ባወቁ ጊዜ ነበር፡፡ ይህንን ውጤት በማየትም በተመሳሳይ መልኩ ደንቡን ወይም መመሪያውን በሃይማኖት ተቋማትም እንዲፈጸም ቢያደርጉ የልባቸው ሊደርስ እንደሚችል እምነት አሳድረው በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ በመሀሉ ያልታሰቡ ሁለት የሞት አደጋዎች በመከሰታቸው እስከአሁን ሊቆይ ቻለ፡፡ አሁን ቀጥታ ወደ መመሪያው ዝርዝር ጉዳዮች ገብቼይሄ ይሄ ከማለቴ በፊት ለዚህና መሰል የቤተክርስቲያንን ጥቅም ለሚጋፉ መመሪያዎች መውጣትና መተግበር መሠረት ወደ ሆነው የተሳሳተ አስተሳሰብ ተመልሼ ጥቂት ብል ነገሩን በሚገባ ግልጽ ያደርገዋልና መለስ አድርጌ ልያዛቹህ፡፡ አንድ አሠሪ ለሠራተኛ በወር ክፍያ ሊከፍል ተዋውሎ ሥራውን ሲያሠራ ይቆያል በሥራው ላይም ተሠማርቶ በትጋት ደፋ ቀና ይል የነበረው አንድ ሠራተኛ ብቻ ነበር፡፡ የተቀሩት ሠራተኞት ነን ባዮች ወሩ ሊያልቅ ሳምንት ሲቀር በመንጠባጠብ ተቀላቀሉት፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ቀዳሚው ሠራተኛ በትጋት ሊሠሩ ይቅርና ጭራሽም ሥራቸው የተሠራውን ማፍረስና ማበላሸት ሆነ በወሩ መጨረሻ ቀን ላይ ግን አሠሪው ሰው ባልታወቀ ሁኔታ ከምኑም ነገሩ ሳይቆጥብና ሳይሳሳ በትጋት ደፋ ቀና ይል ለነበረው ሠራተኛ የተሠራውን ሲያፈርሱና ሲያበላሹ ከነበሩትና በወሩ መጨረሻ ሳምንት ላይ እየተንጠባጠቡ ከመጡት “ሠራተኞች” ጋር እኩል ከፈለው፡፡ ይህ አሠሪ ብልህና አስተዋይ አሠሪ ነው? አከፋፈሉስ ትክክለኛ ፍትሐዊና ተቀባይነት ያለው አከፋፈል ነው? በቀጣዩ ወርስ ለዚህ አሠሪ ሥራውን በትጋት የሚሠራለት ሠራተኛ ይገኛልን? ይህ ግፍና በደል በሀገራችን አሁን በሥልጣን ላይ ባለው “መንግሥት” ተፈጽሟል እንደሚታወቀው ይሄ “መንግሥት”እንደ ሐሳቡ የዲሞክራሲያዊ (የበይነሕዝባዊ) አስተዳደር ሞዴሉ (አርዓያው) የአሜሪካ ዲሞክራሲ (በይነ ሕዝብ) ነበር፡፡ እንግዲህ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው በአሜሪካ አገባብ አውድ (Context) የሃይማኖት እኩልነት ሥርዓት መስፈኑ ትክክለኛና አማራጭ ያልነበረው ነው፡፡ ምክንያቱም በዚያች ሀገር ከሌሎቹ ተነጥሎ ቀድሞ በመገኘት ዋጋ የከፈለ ለሀገሪቱ ህልውናና ሥልጣኔ የደከመ ሃይማኖት አልነበረምና ሁሉም የገቡት በስደት በተመሳሳይ ወቅት ነውና፡፡ በመሆኑም እኩል መብት እንዲኖራቸው መዳረጉ ትክክለኛና አማራጭም ያልነበረው ውሳኔ ነበር፡፡ ወደ አውሮፓ ስንመለስ ግን ነገሩ ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በርካቶቹ ዲሞክራሲ (በይነ ሕዝብ) የሰፈነባቸው የአውሮፓ ሀገራት ብሔራዊ ሃይማኖት ያላቸው ናቸው በአንዳንዶቹ ኦርቶዶክስ በሌሎቹ ካቶሊክ በከፊሎቹ ፕሮቴስታንት፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በየ ሀገራቸው ቀድሞ በመገኘት ለሕዝቡና ለሀገር ህልውና የደከመ የለፋውን ምንም እንዳላደረገ ቆጥሮ ዛሬ ላይ 15 ሆነው ከሚመሠረቱት የእምነት ተቋማት ጋር እኩል መቁጠር ኢፍትሐዊነት እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉና፡፡ የኛ ‹‹መሪዎች›› ዲሞክራሲና (በይነሕዝብና) ፍትሐዊነት ያላቸው ቁርኝትና ዝምድና የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ያህል ሊነጣጠሉ የማይችሉ መሆኑን መረዳት ስለተሳናቸው ፍትሐዊነትንና በሕነ ሕዝብን (ዲሞክራሲን) ሊነጣጥሉ ቻሉ፡፡ በመሆኑም ከመጀመሪያው ቀን ጀምራ ያለማሰለስ ለዚህች ሀገርና ሕዝብ ከነጻነቷ እስከ ሥልጣኔዋ ድረስ በብቸኝነት በከፍተኛ ትጋት ጻዕርና ጋዕር ስትለፋ ስትደክም የኖረችውን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በሕገ መንግሥታቸው ድንጋጌ መሠረት 15 ሰዎች ሆነው የሆነ ስም ሰጥተው ዛሬና ነገም ከሚመሠረቱት የእምነት ድርጅቶች ጋር እኩል ናት፡፡በማለትና በማድረግም ከባድ የድንቁርና ሥራ ሊሠሩ ቻሉ፡፡ እምነቱ ምንም ይሁን ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉ የዚህን ድርጊት ኢፍትሐዊነት መረዳት ይቸግረዋል ብዬ አልገምትም፡፡ ፍትሕ ወይም ፍትሐዊነት የዲሞክራሲ(የበይነሕዝብ) የጀርባ አጥንት ነው፡፡ ያለ ፍትሕ ዲሞክራሲን ማሰብ ጨርሶ የሚቻልነገር አይደለም፡፡ ምንም እንኳ እያነው ያለነው ነገር ይሄው ቢሆንም፡፡እናም ኢፍትሐዊነት ኢሚዛናዊነት፣ በደል የአንባገነን እንጅ የዲሞክራሲ (የበይነሕዝብ) ምሰሶዎች ሊሆኑ አይችሉም አይገባምም፡፡ እንግዲህ ይህ መሠረተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን 15 ሰዎች ሆነው ዛሬ ነገም ከሚመሠረቱት የቃልቻም ይሁን የባዕድ አምልኮ ወይም የሌላ በእምነት ስም ከሚቋቋሙ የእምነት ድርጅቶች፣ በሀገሪቱ ሥልጣኔና ሌሎች ጸጋዎች ላይ አስተዋጽኦ ከሌላቸውና ካልነበራቸው ከማይኖራቸውም፣ ለሀገሪቱና ለሕዝቡ ህልውናና ነጻነት ኢምንት ዋጋ ካልከፈሉ ጋር እኩል መብትና ዕውቅና እንዲኖራት ያደረጉትና አሁን ደግሞ ተመዝግበሽ ካልተቆጣጠርሽ እንዲሉ ያበቃቸው፡፡ ልቦና ቢኖረን እውነትም ብንነጋገር ይህች ሀገር ካሏት ኩራቶች፣ የሥልጣኔ ፍሬዎች ፣ መታወቂያ መገለጫዎች የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያልሆነ ምን አለ? የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ከሀገራችንም አልፋ ለስንት ሀገራት ስንት ነገር እንዳበረከተች የማይታወቅ የተሰወረ ሆኖ ነውን? ይህች ቤተክርስቲያን መላው ዓለም ዛሬ ለደረሰበት የአስተሳሰብ ብስለትና የቴክኖሎጂ (የኪነብጀታ) እድገት ከፍተኛና የማይተካ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡አሁን ይሄ ይሄ ብሎ መዘርዘር መጽሐፍ መጻፍ ነው የሚሆነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ይከፈለኝ ብትል አይደለም የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም መንግሥታት እንኳ ሊከፍሉ ይችላሉን?ለዚህ ሊከፈል ለማይቻለው ውለታዋስ ሊከፈላት የሚገባው ወረታ ፈጽሞ ይሄ አልነበረም፡፡ ረ የልብ ያለህ! እናንተ ምን ይሻላል? ስናያቸው ኢትዮጵያዊያን ይመስላሉ ወይም ናቸው ምን ነው ታዲያ በገዛ ማንነታቸው ላይ የጥፋት ዘመቻ ላይ መጠመዳቸው? ምን የሚሉት በሽታ ነው ይሄ? ይሄን ሁሉ ጉድ እውን የራስ ዜጋ ያደርገዋል ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻላል? ይህ መመሪያ ኃላፊነት ከሚሰማውና ጥቅሙ ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም ጋር ከሚቃረን ሳይሆን ከሚስማማ ከሚጣጣም መንግሥት የወጣና ቀደምም ያለ ቢሆን ኖሮ ማንነታችንን ለማጥፋት የራሳቸውን ጥቅምና ዓላማ ለማስጠበቅ ለማስፈጸምም ከባድ ገንዘብ እያፈሰሱ ከገጠር እስከከተማ በተደራጁ በእርዳታና በማባባያ ጥቃቅን የልማት ሥራዎች እየተታለለ እምነቱንና ማንነቱን እንዲክድ የተደረገውንና በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሩቡን የሕዝባችንን ቁጥር ያሳጣንን እምነት መሰል የምዕራባዊያንን የጥፋት ድርጅቶች የጥፋት ዘመቻን መከላከልና መቋቋምም ባስቻለን ነበር፡፡ አሁን ያለንበት ሁኔታ ግን የተበሉብንን ወይም የተማረኩብንን ዜጎች በመመሪያ የምንመልስበትና እነሱ በኢትዮጵያና በኢትየጵያዊነት ላይ የጋረጡትን አደጋ የምንቀለብስበት ሳይሆን ዋጋ የምንከፍልበት ጊዜ ነው፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ በተአምሩ ይታደገን እንጅ፡፡ ነገር ግን አስቀድመው እነዚህን ድርጅቶች ለዚህ ያበቃቸውን ምቹ ሁኔታ ከፈጠሩና ሁለት ዐሥርት ዓመታት ካለፉ በኋላ በመመሪያ ለመቆጣጠር ማሰቡ ለቡድን ህልውና በመሥጋት ካልሆነ በስተቀር ለሕዝብና ለሀገር ህልውና በመሥጋት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም መመሪያው አግባብነት በሌለውና እንግዳ በሆነ ሁኔታ ጨርሶ ለሀገርና ለሕዝብ ህልውና ሥጋት ያልሆነችን ቤተክርስቲያን አካቷልና፡፡ እዚህ ላይ ግልጽ ማድረግ የምፈልገው ነገር ዜጎች ዜጋ እንደመሆናቸው በሀገራቸው የሕዝብንና የሀገርን ወይም የጋራ ጥቅማችንን አደጋ ላይ የምጥል አይሁን እንጅ የመሰላቸውን የማመን የማምለክ ዜግነታዊ ነጻነት ብቻ አይደለም አምላካዊ ነጻነትም አላቸው፡፡ ፈጣሪ ራሱ በፈቃድ እንጅ በግዴታ አምልኩኝ አላለምና፡፡ እሳትና ውኃን አቀረብኩልህ እጅህን ወደመረጥከው ላክ ከማለቱ ጋር እሳትን ቢመርጥ የሚያጋጥመውን አደጋ ውኃን ቢመርጥ የሚያገኘውን ጥቅም በሚገባ በማስረዳትና በማስተማር ጭምር፡፡ በመሆኑም ፈጣሪ የሰጠውን ነጻነት መንግሥት ይከልክል ማለት ተገቢ አይሆንም፡፡ነገር ግን ለዚህች ሀገርና ሕዝብ ማን ያስባል ፣ማን ይጠቅማል ፣ማን ይቆረቆራል ፣ማን ይገደዋል ከሚለው እሳቤ ጋር ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል፣ ላገለገለ ክፍያው(ደሞዙ) ይገባዋል ለአጥፊም ቅጣቱን የሚባሉት ፍትሐዊና በይነ ሕዝባዊ (ዲሞክራሲያዊ) መርሆች በፍጹም በምንም ተአምር መዘንጋት አይኖርባቸውም፡፡ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው በምንም መመዘኛ አሠራሩ ፍትሐዊ አለመሆኑን አበክሬ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ እንደሚታወቀው በተለይ እንደዚህ ዓይነት ሥራ ሲሠራ የራሱ የሆነ ዓላማና ግብ ይኖረዋል የዚህ መመሪያ ዓላማና ግብም ፡- 1. ለቤተክርስቲያን (ለሃይማኖት) አስተምህሮዋን ጠብቃ ለመቀጠል የግድ የሚለውን የተማከለ አስተዳደር በማፈራረስ ጥንካሬ እንዳይኖራት አድርጎ ልክ በምዕራቡ ዓለም በተመሳሳይ አሠራር አንድ የነበሩት ተፈረካክሰው እንደ አሸን እንደፈሉትና በየቀኑ እንደሚፈሉት ሁሉ ቤተክርስቲያናችንንም ለመፈረካከስ ለመበታተን የታለመ ነው፡፡ 2. ፓርቲው ጥቅሜ የሚለውን ነገር ለማስጠበቅ የእምነት ተቋማቱን በገዛ ገንዘባቸው ለራሱ ቀጥሮ የራሱ ቡድናዊ ጥቅም አገልጋዮች ለማድረግ፡፡ 3. እዛው መመሪያው ላይ በግልጽ እንደሠፈረው የእምነት ተቋማቱ ግዴታዎች በሚለው ርእስ ሥር ዓይን ባወጣና የእምነት ተቋማቱን መንፈሳዊ ግዴታ ጨርሶ ግንዛቤ ውስጥ ባላስገባ መልኩ ፓርቲው የሕልውናዬ አደጋ ናቸው ከሚላቸው ማናቸውም ነገሮች ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርጉ ከልክሎ ሃይማኖቶቹን እንደየእምነታቸው ከአምላክ የተሰጣቸውን መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ (ግብረገባዊ)እና ሰብአዊ ግዴታዎቻቸውን እንዳይወጡ በማገድ መገልገያ እቃው ማድረግ ነው፡፡ የዚህ መመሪያ ግብም እንደመመሪያው አርቃቂዎች እምነት የእምነት ተቋማቱን እግዚአብሔር (ፈጣሪ) ከሚባለው ምናባዊ ነገር እንዲራራቁና እንዲረሳሱ በማድረግ የእነሱ ጉዳይ ፈጻሚዎችና አምላኪዎች እንዲሆኑ በማድረግ ሊፈጥሯት የሚፈልጓትን ከማንነቷ ፣ከታሪኳ ፣ከመለያዎቿ ተለያየችና የተካካደች አዲስ ሀገርና ሕዝብ መፍጠር ነው፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን በዚህች ሀገር የተገኘችው ለዚህችም ሀገር መጣር መድከም የጀመረችው 2000 ዓመታት ብቻ አይደለም፡፡ የሀገራችንም ታሪክ የ3ሺ ዓመታት ታሪክ የሚባለውም ስሕተት ነው 3ሺ ዓመታት የሚባለው ሰሎሞናዊው ሥርዎመንግሥት ከመጀመሩ ወዲህ ያለው ዘመን ብቻ ነው ከዚያ በፊት 74 ነገሥታት ኢትዮጵያን አስተዳድረዋል፡፡ ቤተክርስቲያንም ስሟ ወደ ቤተክርስቲያንነት ከመለወጡ በፊት ቤተምኩራብ ትባል በነበረበት ጊዜና ቤተምኩራብም ከመባሏ በፊት ባጠቃላይ ከክርስቶስ ልደት በፊት ለ3300ዓመታት በላይ ይህችን ሀገር እንደ ኦሪቱ ሥርዓት መንግሥት መሥርታ ነገሥታትን ቀብታ ከማንገሥ ጀምሮ ዜጎችን በሥነ ምግባርና በጥበብ አንፃና አስተምራ የበቃ ዜጋ እስከማድረግ ድረስ ይህችን ሀገርና ሕዝብ ስታገለግል ቆይታለች ከክርስቶስ ልደት በኋላም በሐዲሱ ኪዳን መሠረት ቤተክርስቲያን ከተባለች በኋላም ይሄው እስከዛሬ ለ2005ዓመታት ያህል እያገለገለች ትገኛለች ባጠቃላይም 5305ዓመታት በላይ አገልግሎት ስትሰጥ ኖራለች፡፡ ብዙ ጊዜ በስሕተት ሲነገር የምሰማው ነገር አለ ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ንግሥተ ሳባ ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄዷ ጋር ተያይዞ በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ነው የሚል፡፡ ኢትዮጵያ ሃይማኖት ከየትም አልመጣላትም፡፡ የመጣለት ነገር ቢኖር ኪዳናቱ ብቻ ናቸው፡፡ ሃይማኖት ማለት የእግዚአብሔርን የፈጣሪን ማንነት በትክክል ዐውቆና ተረድቶ እሱን ማምለክ ለእሱም መገዛት ማለት ነው፡፡ አምልኮተ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ተቋርጦ አያውቅም በኢትዮጵያ ያለው ሃይማኖት ከአዳም ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣና ሳይቋረጥ የኖረ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሊቀ ነቢያት ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን ሊያገባ የቻለው፡፡ ወንድሙ አሮን እና እኅቱ ማርያምም ሙሴ ኢትዮጵያዊቷን በማግባቱ ‹‹እግዚአብሔር በእኛ ብቻ ተናግሯልን በእሱም የተናገረ አይደለምን?›› ብለው አጉረመረሙ፡፡ የእስራኤል ልጆች ከዘራቸው ውጪ ከአሕዛብ ወገን ጋር እንዳይጋቡ እንዳይዋለዱ በእግዚአብሔር ተከልክለው ነበርና፡፡ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደሌላው ሕዝብ ከአሕዛብ ወገን ሳንሆን ከሕዝብ ወገን ነንና በመሆኑም የሙሴና የሲፓራ ጋብቻ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጠላም አልተነቀፈም፡፡ እንዲያውም ሳይገባቸው አጉረምርመው የነበሩት እኅቱ ማርያም እና ወንድሙ አሮን በማጉረምረማቸው በእግዚአብሔር ተቀጡ ዘኁ. 12 ፤1-15 / ዘጸ. 2፣16-22 ፡፡ ወደ ኋላ ላይ ነገሩ ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕዝበ እግዚአብሔር መሆኑ በደንብ ግልጽ ሆኖ ተጽፏል፡፡ ለምሳሌ በትንቢተ አሞድ 9-7 ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ብናይ ጭራሽ እንዲያውም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች በኩራት ነን ከሚሉት ከእስራኤል ልጆች ይልቅ በእግዚአብሔር የተወደድንና የከበርን ሆነን እናገኘዋለን፡፡ ቃሉ እንደሚለው ‹‹የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር ›› በማለት እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆችን ልክ እንደ እኛ አድርጎ እንደሚያያቸው ከ እኛ አሳንሶ እንደማያያቸው እነሱን በማጽናናት መናገሩ ተጽፏል፡፡ እንግዲህ የእኛ ማንነት በእግዚአብሔር ፊት የተገለጸውን ያህል ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢትዮጵያ ከመቼ ጀምሮ በእግዚአብሔር እንዳመነች አልተገለጸም፡፡ የሚታወቀው ነገር ቢኖር ከቀደሙት የቀደምን መሆናችን ብቻ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተዋወቃቸው አብርሃም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አብርሃምን የባረከውና አብርሃምም ዐሥራትን ያወጣለት የእግዚአብሔር ካህን መልከጸዴቅ ግን ኢትዮጵያዊ ነበረ ወይም ነው፡፡ የእሱ ትውልድ አልተገለጸም በምን ታወቀ ቢሉ በስሙ፡፡ የመልከጸዴቅ ስም በየትኛውም የዓለማችን ቋንቋ በተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ ብታዩ ተቸግረውም ቢሆን የሚያስቀምጡት ያው ራሱ መልከጸዴቅ የሚለውን ነው፡፡ ይህ ስም የግእዝ ስም ነው፡፡ ለሌሎች ቋንቋዎች ግን ይህ ቃል ወይም ስም ባዕድ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ስለ መልከጸዴቅ ሲናገር የስሙ ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉሥ ነው፡፡ በኋላ ደግሞ የሳሌም ንጉሥ ማለት የሰላም ንጉሥ ነው ብሎ በቋንቋቸው ተርጉሞ ለወገኖቹ በመልእክቱ አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም እናትና አባት የትምልድም ቁጥር የሉትም ብሎታል፡፡ ይህን ማለቱ ሰው አይደለም ለማለት ሳይሆን በአይሁድ መጽሐፍ ወይም የትውልድ ኃረግ ስሙ የለም አልተጠቀሰም ማለቱ እንጅ፡፡ ያልተጠቀሰበትም ምክንያት አይሁድ ባለመሆኑ ነው ይህንንም እዚያው ላይ ገልጾታል፡፡ እንጅ ሥልጣነ ካህነቱና ክብሩማ የሱን የሚያህል ማን ነበር ? እንዲያውም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ብሎም ይጠራዋል፡፡ ለዘመኑ ጥንት ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም ሲል ሞቶ እንደሆነም የሞተበት ቀንና እድሜ አይታወቅም ማለቱ ነው፡፡ ዕብ. 7፣1-3 በመሆኑም እግዚአብሔርን በማምለክ ከእስራኤላዊያንም እንቀድማለን ማለት ነው፡፡ እናም ይህች ቤተክርስቲያን በቀጥታና በተዘዋዋሪም እስራኤላዊያንን ሕዝበ እግዚአብሔር እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን መረዳት ይቻላል፡፡ እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ ብቻም ሳይሆን የሕዝብ አስተዳደር ሥርዓትንና ሕግንም ጭምር ለእስራኤላዊያን አስተምራለች፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ በእግዚአብሔር ተመርጦ ሕዝቡን ከግብጽ አውጥቶ እየመራ ወደ ምድረ ርሥት በሚወስድበት ወቅት ሕዝቡን ማስተዳደር መዳኘት ለሕዝቡና ለራሱም አስቸጋሪና አድካሚ ሆኖ ነበር፡፡ አማቱ ኢትዮጵያዊው ካህን ዮቶር ወይም ራጉኤል ይህ ሙሴ እያደረገ ያለው ነገር ትክክል ያልሆነና ለሕዝቡም ለራሱም አድካሚና ሥራ አስፈቺ መሆኑን አስረድቶ ከሕዝቡ የነቁ የበቁትን ሰዎች እንዲመርጥ ከእነሱም የሺ የመቶ የሃምሳ የዐሥር አለቆችን እንዲሾምላቸውና በሕዝቡ ላይ እንዲፈርዱ እንዲዳኙ አውራውንና የሚከብዳቸውን ብቻ ወደ አንተ ያምጡ ብሎ መክሮ በዚያ መሠረት በአንድ በሙሴ ብቻ ሙሉ ቀን ሥራ ፈተው ሲዋትቱ የነበሩበትን አሠራር ቀይሮ የተሳለጠና ምቹ የአስተዳደር ሥርዓት እንደሠራላቸው ይህም አሠራር ዛሬ ለመላው ዓለም ሁሉ ተዳርሶ እነሆ እየተጠቀመበት እንዳለ መረዳት ይቻላል፡፡ ዘጸ. 18፣13-27 እንግዲህ ይህች ቤተክርስቲያን ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን ከራሷ አልፋ ለመላው ዓለም የዋለችው ቁም ነገር ሁሉ እጅግ ብዙና ውለታን ለሚያስብ ኅሊናም ላለው የሰው ፍጡር ሁሉ ውለታዋ ከክብደቱ የተነሣ የሚያስጨንቅና ዕረፍት የሚነሳ ነው ፡፡ ይህች ቤተክርስቲያን (ቤተምኩራብ) ለዚህች ሀገር ሁለንተና መሠረትና ባለ አደራም ናት ፡፡ በነገሥታቱ ዘመን ይሄ ታውቆላት ማንም የማይጋራት የማይጋፋት ክብርና ሞገስ እንዲሁም ካላት ሚናና አስተዋጽኦ አንጻር በቂ ባይሆንም ሲሦ መንግሥትም ሁሉ ነበራት ፡፡ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ዛሬ ላይ የድካም ዋጋዋ የነበረው ያ ሁሉ ክብርና ሞገስ ሥልጣንም ተገፎ ጭራሽ ዛሬና ነገም 15 ሰዎች ብቻ ይዞ ከሚመሠረት የምንም ዓይነት የእምነት ድርጅት ጋር እኩል ተደርጋ እንድትቆጠር ተደረገ ፡፡ በዚህ የሚደሰት የሌላ ‹‹ሃይማኖት›› ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ካለ ማስተዋል የጎደለውና ንክ እራሱን ለማጥፋት ፈንጅ የታጠቀ እንደሆነ ልነግረው እወዳለሁ ፡፡ ዛሬ በብዛት የሚርመሰመሰውና ኢትዮጵያዊያኑን የተቀራመተው የእምነት ድርጅት ሁሉ ትላንት አልነበሩም፡፡ ትላንት የነበረችው ሁሉም እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ ናት፡፡ ዛሬ ከዚህች ቤተክርስቲያን ውጪ ሆነው የሚቃወሟት ዜጎች አባቶቻቸውና አያቶቻቸው ቆራጥ የቤተክርስቲያን ምእመን (ክርስቲያኖች) የነበሩ ናቸው፡፡ በታሪክ አጋጣሚ በተከሰቱ የጥፋት ጦርነቶች በሰይፍ እና በተለያዩ ችግሮች በተፈጠሩ ክፍተቶች ‹‹ የእሳት ልጅ አመድ እንዲሉ›› ዛሬ የነሱ ልጆች ከበረት ወጥተው ወይም ተማርከው ከባዕዳን በረት ታጉረው የማንነት መገለጫቸውን እናት ቤተክርስቲያናቸውን የገዛ ሀብታቸውን ቤታቸውን የሚፃረሩ የሚዋጉ የሚቃወሙ ለመሆን በቁ፡፡ ጥቂት መቶ ዓመታትን ብቻ ወደ ኋላ ብንመለስ ግን አይደለም አሁን ኢትዮጵያ ብለን በምንጠራው ሀገር ይቅርና ሞቃዲሾ ላይ እንኳ ከሰባት በላይ አብያተ ክርስቲያናት እና ሕዝበ ክርስቲያን የነበርን ነበርን፡፡ ስለሆነም ሌላው ሁሉ ቢቀር እምነታቸው ምንም ቢሆን በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ሊያከብሩ ሊጠብቁ ሊንከባከቡ እንጂ በጠላት ዓይን ሊያዩ ጨርሶ የሚገባ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያዊነት መገለጫ እና መለያ ናትና፡፡ የኢትዮጵያዊነት መገለጫዎችን፣እሴቶችን ጠልቶ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ኢትዮጵያዊነትንም መግለጽ ጨርሶ አይቻልምና፡፡ ሌሎች መገለጫዎች የሌሎች ማለትም የባዕዳን እንጂ የኛ አይደለምና፡፡ የኛ ያልሆነው ደግሞ የኢትዮጵያዊነት መገለጫና ማንነት ሊሆን አይችልምና፡፡ ከዚህ ውጪ ማንነት፣ መለያ፣ መገለጫ ሊገለጽ የሚችልበት ሌላ አማራጭ ወይም ዕድል ከቶውንም የለም፡፡ የእኛ የእኛ ነው፡፡ የሌላው ደግሞ የሌሎች ነው አለቀ፡፡ ኢትዮጵያ በዓለማችን ካሉ ጥቂት የራሳቸው ማንነት እና መገለጫ ካላቸው ሀገሮች አንዷ ናት፡፡ ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኘት ዕድለኛነት ነው፡፡ ላወቀውና አክብሮ ለያዘው፡፡ በመሆኑም ማንም ዜጋ እምነቱ ሌላ ቢሆንም ኢትዮጵያዊነቱ ግን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምን ግዴታና ኃላፊነት እንደጣለበት ሁሉም የሌላ ‹‹ሃይማኖት›› ተከታይ የሆነ ዜጋ ሁሉ በሚገባ ሊረዳው ይገባል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ከታሪካችን እንደምንረዳው ወንድሞቻችን ይሄንን ግዴታና ኃላፊነት ሳይረዱ ቀርተው የሚከተሉት እምነትና ያእምነት የመጣበት ሀገር በሀገራችን ላይ ያለው የጥቅም ፍላጎት ባሳደረባቸው ተጽዕኖ እነኝህ ወንድሞቻችን ለገዛ ሀገራቸው መልካም ነገር ሊመኙና ሊውሉ አልቻሉም፡፡ በሚከተሉት እምነት ምክንያት ብቻ ከጠላት ጋር አብረው ተሰልፈው የገዛ ሀገራቸውንና ወገናቸውን አመቺ ሁኔታ ባገኙ ቁጥር በተለያዩ ጊዜያት የወጉ እንዳሉ ታሪካችን ይነግረናል፡፡ ሌሎኞቹ ደግሞ እስከ አሁን ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም ዕድል ባያገኙም ባጠቃላይ ግን ለኢትዮጵያዊነትና ለማንነታችን ያላቸውና የሚያራምዱት ጥላቻ በግልጽ ይታወቃል፡፡ እነዚያ ባዕዳን ሰባኪዎቻቸው ወይም የእምነቶቻቸው መሪዎች እነኝህ ወንድሞቻችንን እንዴት ባለ አዚም ወይም ምትሐት ወርቅ የሆነ የገዛ ማንነታቸውን እንዲጠሉና እንዲክዱ ከአኩሪ ማንነታቸው ጋር እንዲቆራረጡ ሊያደርጓቸው እንደቻሉ ለእኔ ሊፈታልኝ ያልቻለ የዘወትር እንቆቅልሽ ነው፡፡ እነሱን ትዝብት ላይ ከጣላቸው አጋጣሚዎች አንዱን ብጠቅስ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በየ አዳራሾቻቸው በአንድ ድምፅ የመንፈስ መልእክት ነው እያሉ “እኛ ሀገራችን በሰማይ ነው፣ ዜግነታችን ክርስትና ነው የማንም ወገን አይደለንም ከሥጋዊያን እርሾ ተጠበቁ እንዳትተባበሩ”ወዘተ. እያሉ ተከታዮቻቸውን በመስበካቸውና በዜግነታቸው ለሀገራቸው ሊያደርጉ የሚጠበቅባቸውን ነገር ሁሉ እንዳያደርጉ በመስበካቸው በወቅቱ መንግሥትን አስቆጥቶት በእነኝህ የእምነት መሪዎች ላይ የሥነ ሥርዓት እርምጃ የወሰደበት ሁኔታ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ እነኝህ ሁለት ታሪካዊ መረጃዎች የሚያሳዩትና የሚናገሩት ጉዳይ አለ ሰዎቹ ወይም እምነቶቹ ለዚህች ሀገርና ሕዝብ በደባል የያዙትን ዓላማና አመለካከት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ማንነታቸውን ከሃይማኖታቸው ነጥለው ማየት ባለመቻላቸውና እምነታቸው የመጣበት ሀገር ለራሱ ዓላማ መጠቀሚያ እያደረጋቸው እንደሆነ ባለመረዳታቸው ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከመወለዱ በፊት በእናቱ ማኅፀን እያለ ገና ሀገሩ ኢትዮጵያ ማንነቱም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ግልጽ ነው እምነት ግን ከተወለደ በኋላ ከወደደና ከፈቀደ የሚከተለው ካልፈለገ የሚተወው በመሆኑ ሰዎች እዚህ ላይ ባይሳሳቱና ቢጠነቀቁ መልካም ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜ አልፎ አልፎ ለማየት እንደቻልነው ከእነዚህ ወንድሞቻችን ውስጥ እንዳንድ የገባቸው እምነትንና ማንነትን ነጣጥለው ለማየት የቻሉና እምነታቸው ሌላ ቢሆንም ማንነታቸውንና መለያቸውን ግን በተቻላቸው መጠን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የተዋደቁ በጣት የሚቆጠሩ ዜጎች እንዳሉ ከታሪካችን ለመረዳት ይቻላል፡፡ ወደ መመሪያው ስመለስ ሚንስቴር መ/ቤቱ ወይም “መንግሥት” ይሄንን መመሪያ ፈጽሞ ሥራ ላይ ሊያውለው ከማይችልባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች 3ቱን ብቻ ጠቅሼ ልጨርስ፡፡ 1. የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዳሰበው ቤተክርስቲያን ዶግማዋንና ቀኖናዋን፣ሕግና ሥርዓቷን መሠረት እድርጋ የምትሠራቸውን መንፈሳዊ ሥራዎቿንና አገልግሎቶቿን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ሕግ መመሪያ ወይም ደንብ ጋር ማግባባት ፣ማስማማት፣ ማዋሐድ፣ ፈጽሞ የማይቻለው ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም በግልጽ ማየት እንደሚቻለው የሁለቱም ርዕዮተ ዓለም (Ideology) መሠረተ እምነት እጅግ የተለያዩ የተራራቁ የማይስማሙ የሚቃረኑም ስለሆነ፡፡ ቤተክርስቲያን እያንዳንዱን መንፈሳዊ አገልግሎት ስትሠራ ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ በዓይን የማይታየውን በጆሮ የማይደመጠውን የመንፈስ ቅዱስን ፈቃድና ፈጻሚነት መሠረት አድርጋ ሲሆን ለዚህም ደግሞ ማረጋገጫ ልትሰጥ አትችልም፡፡ የሚንስትር መ/ቤቱ ደግሞ በእጅ በሚጨበጥና በሚዳሰስ ሊረዳው በሚችለው አሠራርና ክወና ነው ማረጋገጫም ይፈልጋል በመሆኑም ሁለቱን አግባብቶ አንድ ሥራ መሥራት ፈጽሞ የማይታለም ነገር ነው፡፡ 2. ‹‹ሞኝ አሉ ብልጥን አሸነፈው ምን ብሎ ቢሉ እምብኝ ብሎ›› እንደተባለው የሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ የቀረቡትን መከራከሪያ ነጥቦችና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን የፍትሕ ጥያቄ ወደ ጎን ትቶ ከአቋሙ የማይመለስ ከሆነ ደንቡን ወይም መመሪያውን ከእምነት ተቋማቱ ሕግጋትና ሥርዓት ጋር የሚቻሉትን ያህል ብቻ እንኳን ለማጣጣምና ለመዳኘት ተፈጻሚ ለማድረግ ቢያንስ የየእምነት ተቋማቱን መሪዎችና ‹‹ሊቃውንት›› ያህል ስለእየ እምነቶቹ አስተምህሮ እውቀትና መረዳት ሊኖረው ግድ ይላል፡፡ በመሆኑም ከቶውንም የማይታሰብና ፈጽሞ የማይቻል ነገር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ 3. የሚንስቴር መ/ቤቱ ሊያስጠብቀው በሚፈልገው የቡድን ጥቅም ሳቢያ የዚያን ሃይማኖት አምላካዊ ተልእኮ ሲያደናቅፍና መመሪያው እንደሚለው በቀላል መዘናጋቶች በሚፈጸሙ ትናንሽ መተላለፎች የዚያን ሃይማኖት ፈቃድ ሠርዞ ያንን ሃይማኖት መዝጋት እንደሚችል ማሰቡና መዘጋጀቱ አንድ ነገርን ይጠቁማል ይህ መመሪያ የተረቀቀው በእግዚአብሔር በማያምኑና እግዚአብሔርን በማይፈሩ ሰዎች መሆኑን፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም ሃይማኖቶች በእግዚአብሔር የተፈቀዱ ወይም ተቀባይነት ያላቸው አይደሉም መጽሐፉም እንደሚለው እግዚአብሔር የሚያውቀውና ለሰው ልጆች የሰጠው አንድ ሃይማኖትን ብቻ ነው፡፡ ኤፌ4፡5 አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት የሚኒስቴር መ/ቤቱ መዝግቤ በራሴ መንገድ እመራቸዋለሁ ከሚላቸው “ሃይማኖቶች” አንዱ ብቻ እግዚአብሔር የቆመለትና በእግዚአብሔር ጥበቃ የሚደረግለት ሃይማኖት ነው የሚንስቴር መ/ቤቱ በትናንሽ የደንብ መተላለፍ ያችን እግዚአብሔር የቆመላትን አንዲት ሃይማኖት ፈቃዷን ሠርዥ እዘጋለሁ ሲልና በቡድን ጥቅም ሳቢያ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን ሲያደናቅፍ እንግዲህ የሚጣላው ከጠባቂዋ ከኃይሉ እግዚአብሔር ጋር መሆኑንና ለዚህም አቅም ጨርሶ ሊኖራቸው እንደማይችል በቅስፈት እንደሚጠፋም ጨርሶ አልተረዱም ካለማመናቸው የተነሣ ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም በእነኝህ ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚንስቴር መ/ቤቱ ጨርሶ የማይታለም ነገርን እንዳለመና ሊተገብረውም እንደማይችል መረዳት እንችላለን፡፡ ተስፋ ባላደርግም የሚንስቴር መ/ቤቱ ‹‹በመንግሥት›› ጭንቅላት አስቦና መክሮ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ለዚህ መመሪያ ተገዥ እንድትሆን ማሰቡ በተሳሳተ ግንዛቤ መሆኑን ተረድቶ ውሳኔውን እንዲቀለብስ እንደዜጋና እንደ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምእመን እጠይቃለሁ እለምናለሁ፡፡ መቸም ቤተክርስቲያን አባሪ ተባባሪ እንጅ ለመብቷ የሚከራከር የለም አይሆንም የሚል አስተዳደር (Active alert responsible and comitted administration) አስቀድሞ እንዳይኖራት በመደረጉ በምን ተአምር ከዚህ ጣጣ ልንወጣ እንደምንችል እግዚአብሔር ይወቀው፡፡ “መንግሥት” እንደሆነ ምንም ቢያደርግ ማንም ምንም እንደማይለው የተቋውሞ ምላሽ እንደማያጋጥመው የዘመኑ ሕዝበ ክርስቲያን ለሆዱ እንጅ ለአምላኩ እንደማይገዛ በተለያየ ጊዜ በቤተክርስቲያን ላይ ባደረሰው ጥቃትና በደል ጥፋት እስከቅርብ ጊዜው በዋልድባ ገዳም ላይ ባደረሰው ግፍ ጥፋትና ውድመት አይቶ አረጋግጧልና ማንንም ፈርቶ ወደ ኋላ ይላል ብዬ አልጠብቅም፡፡ ቸሩ መድኃኔዓለም እንደ ኃጢአታችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ተመልክቶ የሀገራችንንና የቤተክርስቲያናችንን ክብርና ልዕልና ይመልስ ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ይታደገን አሜን !!! I beg you in the name of Ethiopian church to share it to Twitter and Facebook, to Email and Blog it . thank you ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው amsalugkidan@gmail.com
sorce... http://sodere.com

ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት

ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት

እውቀቱ ስዩም

ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡
ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡
ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡
‹‹…ኢትዮጵያን የመሠረታት የሶሰትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡በአማራው፣በኦሮሞው፣በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭት እና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡…የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለው የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው››
ጃዋር የኢትዮጵያን መሠረት የሦስት ብሄረሰቦች የስልጣን ግብግብ አድርጎ ወስኖታል፡፡ በመጀመርያ፣ ሌሎች ብሄረሰቦች በግብግቡ ተሳትፎ እንዳልነበራቸው አድርጎ ማቅረቡ አንድ
ጉድለት ነው፡፡ ግን ዋናው ቁምነገር ይሄ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የግጭት ውጤት ብቻ እንደሆነች አድርጎ ማቅረቡ ነው ትልቁ ስሕተት፡፡ ሲጀምር፣ የግብግብ ታሪክ መሠረት ይንዳል እንጂ መሠረት አይገነባም፡፡ እንደኔ ግምት፣የኢትዮጵያ መሠረት የሆነው ብሄረሰቦች ለጋራ ሕልውና ሲሉ የሚያደርጉት የመደጋገፍ ታሪክ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ፣ ታሪክ ከላሾች፣የብሄሮችን የ‹‹ግብግብ››ታሪክ ሞቅ አድርገው፣አኳሽተው ሲጽፉ፣የብሄሮች መደጋገፍ ታሪክን ግን ቸል ይሉታል፡፡ አለያም እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት፣ በጥቂት መስመሮች ብቻ ጨረፍ አድርገው ያልፉታል፡፡ለነገሩ፣ከፋፋይነትን ብቸኛ ያስተዳደር ፈሊጥ አድርጎ የሚቆጥር ሰው በታሪክ ገጾች ውስጥ መመልከት የሚፈልገው ክፍፍልን ብቻ ነው፡፡ታሪክ ግን ብዙ በጎ የትብብር ገጠመኞችን መዝግቧል፡፡ለምሳሌ ጀግናው አጼ ዮሐንስ አራተኛ በበዛሬይቱ ኤርትራ የግብጽን ወራሪ ጦር ድል የነሡት የትግራይ ጀግኖችን ብቻ አሠልፈው አልነበረም፡፡ በዚህ ጦርነት ከግብጽ ጎን ሆኖ፣የተዋጋው አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ዊልያም ዴይ እንደመሠከረው ወልቃይቶች፣ጥልጣል የተባሉ የአፋር ንኡስ ክፍሎች፣የወረኢሉ ኦሮሞዎች ለንጉሰነገስቱ ድጋፍ ለማድረግ ተሸቀዳድመዋል፡፡በራስ ወሌ የሚመሩ የአማራ ወታደሮች ተሳትፈዋል፡፡የጎንደር ቀሳውስት ለጦርነቱ ድጋፍ ለማድረግ አድዋ ገብተዋል፡፡ የጎጃሙ ራስ አዳል የደርሼልሀለሁ አለኝታቸውን አሳይተዋል፡፡ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ ሳይቀር በመቶ የሚቆጠሩ በቅሎዎችንና ማበረታቻ ልከዋል፡፡ ዝርዝሩን ማንበብ ለሚፈልግ Muslim Egypt Christian Abyssinia የተባለውን የዚህ ደራሲ ማስታወሻ ገጽ 291-292 ያንብብ፡፡ መጽሐፉን በኢንተርኔት ቤተ-መጻህፍት ውስጥ በብላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡
ከተለያየ መአዘን የመጡ እኒህ ኢትዮጵያውን ከዘመቻው የሚያገኙት ድልን ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመቻ ወቅት ባህል ይዋዋሳሉ፣ቃላት ይወራረሳሉ፣ ስንቅ ያዋጣሉ፣ ልምድ ይለዋወጣሉ፡፡ በሂደት ተቃራኒ ከሚመስሉ ልማዶች የነጠረ ኢትዮጵያዊ ባህል እንደ አረቄ ይወጣል፡፡ ይህን በመዋጮ የተገኘ ባህል ‹‹የአማራ ባህል ››ብሎ ማጥበብ የጸና ድጋፍ ያለው አይመስለኝም፡፡
ጃዋር‹‹አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭትና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች›› በማለት ሳይወሰን ‹‹የኢትዮጵያ አገራዊ መለያ ማንነት የምንለው አማራ ብሄራዊ ማንነት ነው›› ሲል ይጨምራል፡፡ ጎበዝ ኧረ በህግ አምላክ!!! የኢትዮጵያ ባህልኮ ካንድ አለት የተጠረበ ሕንጻ አይደለም፡፡ ከብዙ የመዋጮ ጡቦች የተገነባ ነው፡፡ ጃዋር እያንዳንዱን ጡብ ቀርቦ ቢመረምረው እዚህ የደረሰበት እርግጠኝነት ውስጥ የሚደርስ አይመስለኝም፡፡
እስቲ ከደቃቅ ምሳሌ እንጀምር፡፡ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ስራ ሲሠራ አስቀድሞ የሚመጣው የቡና ስነ-ስራታችን ነው፡፡ አንዲት ጠይም ፣ባለሹርባ ሴት፣ያበሻ ቀሚስ ለብሳ ቡና ስትቀዳ የሚያሳይ ምስል በየቦታው ማየት የተለመደ ነው፡፡ይህ ችክ ያለ ምስል በስነ-ስእል ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ቢዮንሴና ጆን ኬሪ አገራችንን በጎበኙበት ሰአት የቡና ስነስርአት ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት የውጭ እንግዳ የቡና ስርአታችንን እንደ ኢትዮጵየዊ መለዮ እንዲመዘግብልን ፈልገናል ማለት ነው፡፡ ለዋለልኝ መኮንን እና ለጃዋር መሀመድ ይህ የአማራ ባህል መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ እይታ ይመስላል፡፡ ጉዱ ዝርዝሩ ላይ ነው፡፡ የሴትዮዋ ሹርባ ከሐማሴን ወይም ከተንቤን ሴቶች ልማድ ጋር ስምም ነው፡፡ ያበሻ ቀሚሱን የሽሮሜዳ ጋሞ የሸመነው ሊሆን ይችላል፡፡ ጀበናው የጂማ ሙስሊም ኦሮሞዎች ያስተዋወቁት ነው፡፡ አቦል ቶና በረካ አረብኛ ወይም የተወላገደ አረብኛ የተገኙ ቃላት ናቸው፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ትንሳኤ በአል በሉባንጃ የሚታጀብ ቡና የማያፈላ ክርስትያን ኢትዮጵያዊ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ከጥቂት መቶ አመታት በፊት ግን ቡና የእስላም ልማድ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ የቡና ትርኢት የሙስሊም አበው በኢትዮጵያ ባህል ላይ የጨመሩት በጎ መዋጮ እድርገን ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያ ጊዜ በተባለው አናጢ ከብዙ ጡቦች የተገነባች ናት የምንለው ለዚህ ነው፡፡
ጃዋር አማራው የራሱን ባህል በኦሮሞው ላይ እንደጫነ ሲያምን ተገላቢጦሹ ያለው አይታየውም፡፡ ኦሮሞ በረጅም ዘመን፣በሠፊ ምድር፣ ሰፍሮ የመኖሩን ያክል በጎረቤቶቹና በወደረኞቹ ላይ የባህል ተጽእኖ አላሳደረም ማለት ብርቱ ባህል የለውም ከማለት አይለይም፡፡ ባገራችን ዋና ዋናዎቹ የባህል ቀራጺዎች ጦርነትና ሐይማኖት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ፣ጀግኖችን እና ነገስታትን አባ በዝብዝ አባ ታጠቅ፣ አባ ዳኘው አባ ነጋ ወዘተ እያሉ መሰየም ገናና ኢትዮጵያዊ ባህል መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ብዙዎቻችን የማናውቀው ይህንን ባህል ያስተዋወቁት ለግማሽ ምእተአመት ያክል ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ነው፡፡ ብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ቼ በለው በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን እንዲህ በማለት ያረጋግጣሉ-
‹‹ነገስታቱ በ‹‹አባ›› ወይም የእገሌ ባለቤት በሚል ቅጽል ስም መጥራት የጀመሩት የኦሮሞዎችን ወይም የወረሸሆችን ልምድ በመከተል ነው ከ1838 ዓም ወዲህ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ወትሮ ግን በተለይም 1474-1713 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ ቅብዓ መንግሥቱ በሚደረግላቸው ሰአት ይወጣላችው የነበረው የግርማ ስም ወይም ስመ መንግስት ‹‹ሰገድ›› የሚል ኃይለቃል በመጨመር እንደነበር ቀጥሎ ያለው ያረጋግጣል፡፡ ወናገድ ሰገድ፣ አጽናፍ ሰገድ፣ አድማስ ሰገድ፣ መለክ ሰገድ፣አድያም ሰገድ ሉል ሰገድ››በማለት ይዘረዝራሉ፡፡
ከጥቅሱ ሦስት ፍሬ ነገሮችን መረዳት ይቻላል፡፡
1- ይህ ባህል ባንድ የዘመን ምዕራፍ ላይ ከኦሮሞ ብሄረሰብ የመነጨ የኢትዮጵያ ባህል ነው፡፡
2- ባህሉ ብርቱ ተጽእኖ ከመፍጠሩ የተነሳ አማራና ትግራይ ነገስታት ለረጅም ዘመን ይጠቀሙበት የነበረውን የስያሜ ዘይቤ ሽሯል፡፡
3- አማራው ታሪክ ጸሀፊ ለባህሉ አስተዋዋቂዎች የባለቤትነት እውቅና ሰጥተዋል፡፡
በሃይማኖት ረገድም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚገጥመን፡፡ ለምሳሌ አቴቴ የሚለውን ቃል ደስታ ተክለወልድ ሲተረጉሙ ‹‹ዛር፣በሴት ስም የምትጠራ፣ ውቃቤ ፣ አማሮች ከኦሮሞዎች የወረሷት ጨሌ የሚያጠልቁላት አቴቴ ጊንቢ ሐራ አቴቴ ዱላ እያሉ እንቀት የሚቀቅሉላት አምልኮ ባእድ፣ትርጓሜ ጠባቂ ማለት ነው››ይላሉ፡፡
‹‹አምልኮ ባእድ ››የሚለውን አሉታዊ ሐረግ፣የክርስትያን አድልኦ ያለበት ፍርድ አድርገን እንለፈው፡፡ ዋናው ፍሬ ነገር፣ የአሮሞው ባህል በአማራው ባህል ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን ማወቃችን ነው፡፡ ይህም አንዱ ብሄረሰብ ሁልጊዜ ጫኝ ፣ ሌላው ብሄረሰብ ሁልጊዜ ተሸካሚ እንደነበረ አድርገው ሊነግሩን የሚፈልጉትን ሰዎች ያስተባብላል፡፡ በሁለቱ ግዙፍ ብሄረሰቦች መካከል የነበረው ግኑኝነት የእኩዮች ልውውጥ ነው፡፡ የባህሎች ውርርስ ነው ማለት እንችላለን፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና፣ የማንኩሳ ዘመዶቼ የሚያስደነግጥ ነገር ሲገጥማቸው ‹‹አቲቲን ወሰድከው›› ይላሉ፡፡ ቀልቤን ገፈፍከው ለማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ባህላዊ ተጽእኖ በወለጋ ድንበር ላይ ቆሟል ያለው ማነው?
ስለጉዲፈቻ ባህል ብዙ ሰዉ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ በጦርነት ወቅት ምርኮኞችን ባርያ ማድረግ ወይም መግደል በብዙ ማህበረሰቦች የተለመደ ነው፡፡ በኦሮሞ አበዋዊ ባህል ውስጥ ግን ምርኮኞች በልጅነት ይታቀፋሉ፡፡ ከሌላ ብሄረሰብ ቢመጡም የኦሮሞ ብሄረሰብ የሚያገኘውን መብት ሳይነፈጋቸው ያድጋሉ፡፡ ይህንን ልማድ በአማራው ማህበረሰብ ውስጥም እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ በጎጃሙ ንጎስ ተክለይማኖትና በወለጋ መሳፍንት መሀል በተደረገው ጦርነት የተማረከው ብላቴና ነገሮ ዋቅጅራን እንደልጅ አሳድገውታል፡፡ ክርስትና አስነስተው ተክለኢየሱስ አሰኝተውታል፡፡ ራሱ በጻፈው ማስታወሻ ‹‹በጠጅና በስጋ አደግሁ›› በማለት የመሳፍንት ልጆች ያገኙት የነበረውን ምቾት ሳይነፈገው ማደጉን ይመሰክራል፡፡ ነገሮ ፣ ከማእረግ ወደ ማእረግ እየወጣ የንጉሱ ጸሐፌ ትዝዛዝ እስከመሆን ደርሷል፡፡ ተመሳሳይ መልኩ በሸዋ ምርኮኛው ቆሴ ዲነግዴ በቤተመንግስት እየተቀማጠለ አድጎ ሐብተጊዎርጊስ በሚል ስመ ክርስትና የኢትዮጵያ የጦር ምኒስትር እስከመሆን ደርሷል፡፡ ሰዎችን በልዩ ቋንቋቸው ምክንያት ባይተዋር ማድረግ ኢትዮጵያዊ ባህል አልነበረም፡፡
እኩዋን ባህላችን አማርኛችን እንኳ የጉራማይሌነታችን ምስክር ነው፡፡ አሁን ኦሮምኛ ያልተነካካ አማርኛ ማግኘት ይቻላል?፡፡ እሰቲ ለናሙና ያክል ‹‹ተወርዋሪ ኮከብ›› ከተባለው የዮሐንስ አድማሱ ምርጥ የአማርኛ ግጥም ውስጥ ጥቂት መስመሮች ልቆንጥር፡፡
1) ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ በምናውቀው ሰማይ ነበረ በይፋ
2) ሜዳና ተራራ በመሐል ሸለቆ
ጨፌውና መስኩ በኒህ ተደብቆ
3) ሐቀኛ ጠፍቶበት በዋለበት መልቲ
ጌጥ ነው ድንቁርና የገዳዮች ሎቲ
4) ብልጭ ብሎ ጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ የሐሳብ አንጋፋ
በመረጥኳቸው መስመሮች ውስጥ የሚገኙት ‹‹ይፋ፣ ጨፌ፣ መልቲ፣ ሎቲ፣ አንጋፋ፣›› የተባሉት ቃላት ኦሮሚኛ ናቸው፡፡ ካንድ የአማርኛ ግጥም ይህን ያህል ኦሮሚኛ ከተገኘ በሙሉ መዝገበ ቃላት ውስጥ ምን ያህል ሊገኝ እንደሚችል አስቡት፡፡ ይህን ያክል ነው የተዋሀድነው፡፡
የኢትዮጵያ ባህል የተውጣጣ ባህል እንጂ ጃዋር እንደሚለው የአማራ ባህል ብቻ አለመሆኑን በመጠኑም ቢሆን ያሳየሁ ይመስለኛል፡፡ ጃዋርን እዚህ ላይ ላሰናብትና ለማጠናቀቂያ የምትሆን አንዲት አንቀጽ ልጨምር፡፡
ባህልን ማክበር ጥሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በስሜት ሚነድደው የብሄርብሄረሰብ ፖለቲካችን፣ ዜጎች ለባህል ያላቸውን ፍቅር ወደ ጭፍን አምልኮአዊ ፍቅር እያዘቀጠው ነው፡፡
ባባቶቻችንና በእኛ መካከል የባህል ፋይዳ ልዩነት ያለ ይመስለኛል፡፡ አባቶች ባህላቸውን ያገኙት በኑሮ ጣጣ አስገዳጅነት ነው፡፡ ለምሳሌ የኔ አያት ቁምጣ ሱሪ የሚታጠቀው ከሌሎች ብሄረሰቦች ለየት ብሎ ለመታየት አይመሰለኝም፡፡ በቂ አቡጀዲ ስላላገኘ ነው፡፡ ወይም ለስራ እንዲያመቸው ባጭር መታጠቁ ይሆናል፡፡ እኔ ግን የብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ቁምጣ ለብሼ ራሴን በማስጎብኘት እንድኮራ ይጠበቅብኛል፡፡ ጉድ እኮ ነው!!! ጋቢ በጥንት ጊዜ የሙቀት ምንጭ ነበር፡፡ ዘንድሮ የኩራት ምንጭ ሊሆን ይቃጣዋል፡፡
የዛሬዎቹ ባህል አምላኪዎች ባህል ሲያስቡ ለውጥን ይረሳሉ፡፡ ባንድ ወቅት የሚያኮራው ያንድ ብሄረሰብ ባህል በሌላው ወቅት ይናቃል፡፡ ባንድ ወቅት የሚያስሸልመው በሌላ ጊዜ ያስቀጣል፡፡ ከጥቂት መቶ አመት በፊት ዝሆን መግደል በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ የሚያጎናጽፍ ተግባር ነበር፡፡ ዝሆን የገደለ ልዩ አምባር ክንዱ ላይ ያጠልቃል፡፡ እስኪ ዛሬ ያባቶቼን ባህል ለማክበር ነው ብለህ ፓርክ ውስጥ አርፎ የተኛውን ዝሆን ግደል፡፡ በአምባር ምትክ ካቴና ይጠልቅልሀል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት የተባለውን የተደጋገመ ግን ያልታሰበበት ቃል ከዚህ አንጻር ቃኙት፡፡ ሲጀምር ፣ዛፍ እንኳ ቅርፊቱን በሚቀያይርበት ዓለም፣ብሄር ብሄረሰቦች በየጊዜው አልባሳታቸውን አይቀያይሩም ወይ?፡፡ የብሄረሰቡ አልባስ ሲባል በየትኛው ዘመን የሚለበሰው ነው? የእንዳለጌታ ከበደ እናት ሲነግሩን፣ ዛሬ በጉራጌ ዘፈን ላይ በቲቪ የምናየው የሴቶች ሻማ ቀሚስ በደርግ ዘመን የተጀመረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው ሸማ ነው፡፡ ከሸማው በፊት ደግሞ የቆዳ ቀሚስ ይለበስ ነበር፡፡
ሌላው፣ አንድ ማህበረሰብ አልባሳት በየማእረጉ ልዩ ልዩ ልብሶች ይኖሩታል፡፡ ወታደሩ ያባ ገዳውን ልብስ የሚለብስ አይመስለኝም፡፡ ባሮች ከጌቶች ልብስ ጋር የሚመሳሰል ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ በፊውዳል ማህበረሰብ ከላይ አስከታች መልበስ መከናነብ የጨዋነት ምልክት ነው፡፡ ይህንን በሸዋና በትግራይ ብቻ ሳይሆን በቅድመ ምኒልክ ከፋ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ባንጻሩ፣ባሮች በከፊል ተራቁተው መታየት አለባቸው፡፡ ባጠቃላይ በኢትዮጵያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አለባበስ በበሄረሰብ ላይ ሳይሆን በመደብ ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ የብሄር አልባሳት የሚባለው እንደ ማንኛውም ሾላ በድፍን ሐሳብ በጥርጣሬ መታየት አለበት፡፡
ትውልዱ የባህል ፈጣሪ መሆን ሲገባው፣የባህል ሙዚየም ሆኖ ተተክሏል፡፡አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ባንድ ወቅት እንዳለው ‹‹ካባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ፣ እንዳልተፈጠረ ይቆጠራል››
ማሳረጊያ
ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ያቆያት የነገስታቱ ጉልበት ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ኢትዮጵያ የተሸመነችበትን ውስብስብ ክር ማየት ያልታደሉ ናቸው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያን በታትነን ክልላችንን እናድናለን ብለው ባደባባይ ሳያፍሩ የሚናገሩ ሰዎችን የምናይበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡በርግጥ ኢትዮጵያ ማእበል ከበረታባት እንደ ታይታኒክ ትሰጥም ይሆናል፡፡ግን መርከቢቱ ስትሰጥም የመርከቢቱ ሳሎን ብቻውን አይንሳፈፍም፡፡የመርከቢቱ ጓዳ ብቻውን አይተርፍም፡፡ኢትዮጵያ ስትከስም ብሄሮች ተነጥለው ይለመልማሉ ማለት ተፈጥሮ አመሏን እንደ ግትቻ የትም ጥላለች ማለት ነው፡፡
source.... https://freedom4ethiopian.wordpress.com

የግብፅ ፖለቲካዊ ትርምስ


የግብፅ ፖለቲካዊ ትርምስ

የአዉቶማቲክ ጠመንጃ ተኩስ ይሰማናል።ተቃዋሚ ሠልፈኞቹ (እኛ እንዳንመታ) ዙሪያችንን ከበዉ ሠብአዊ ጋሻ ሠሩ።ጥይቶችና የሲ ኤስ ጋሶች ይተኮሱብናል።አየሩ በጢስ ታፍኗል።ሰዎች ያስታዉካሉ።የመስክ ሆስፒታሎቹ ወለል ደም ተንጣሎባቸዋል።---"
የዩናይትድ ስቴትሱን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪን፥ ቅዳሜ እንዳሉት «በጣም አሳስቧል።» የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ካትሪን አሽተንን ዛሬ እንዳደረጉት ወደ ካይሮ አስጉዟል።ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ለፓን ጊ ሙን፥ ያስደነግጣል።ገሚስ ግብፆችን ሲያስፈነጠዝ ሌሎቹን ዋይታ ያስረግዳል።የግብፅ የግድያ፥ የጥፋት፥ ዉድመት ጉዞ።

ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል ሲሲ የሚመሩት ጦር ከዓረብም፥ ከአፍሪቃም ሐገራት አቻዉ በቁጥር፥ በታጠቀዉ መሳሪያ ብዛት፥ ጥራት፥ ዘመናይነትም አንደኛ ነዉ።አንደኛዉ ፈርጣማ ጦር የሰለጠነ፥ የተቀጠረ፥ የተደራጀዉ ከድሮ እስከ ዘንድሮ በይፋ እንደሚታወቀዉ ባብዛኛዉ እስራኤልን እንዲወጋ ነዉ።ምናልባት ከወር በፊት ከካይሮና ከአዲስ አበባ እንደተሰማዉ ኢትዮጵያን ሊሆን ይችላል፥ ምናልባት ገማል አብድናስር የመን ላይ እንዳደረጉት ከሶሪያ ተፋላሚዎች አንዱን ደግፎ ለመዋጋት ይዘምትም ይሆናል።ወይም ተመሳሳይ ነገሮች።

ብቻ በብዙዉ ዓለም ብዙ ጊዜ እንደሚባለዉ የታላቅ፥ ታሪካዊ፥ ጥንታዊ ሐገር፥ ሕዝቡን ከዉጪ ጠላት ጥቃትና ወረራ ለመከላከል ነበር።ባለፈዉ አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ግን «ጀግናዉ» የግብፅ ጦር ርዕሠ-ከተማ ካይሮ መሐል የሱን ጥበቃና ከለላ በሚፈልጉ፥ የሱን ደሞዝ፥ ቀለብ የሚከፍሉ ሲቢል ዜጎች ላይ ጀግንነቱን አሳየ።
Supporters of deposed Egyptian President Mohamed Mursi throw stones from behind a makeshift barricade they built as they take cover from the police during clashes in Nasr city area, east of Cairo July 27, 2013. At least 70 people died on Saturday after security forces attacked supporters of deposed President Mohamed Mursi in Cairo, Muslim Brotherhood spokesman Gehad El-Haddad said, adding the toll could be much higher. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST TPX IMAGES OF THE DAY) ግችት


ያልታጠቀ ተቃዉሞ ሠልፈኛኝ ግንባር ደረቱን እያፈለሰ ጣለዉ።ከካይሮ ሆስፒታሎች የአንዱ ሐኪም ያርዳሉ ወይም ያስረዳሉ።


«ሁሉም የቆሰሉት ጭንቅላታቸዉ፥ ወይም ደረታቸዉ ላይ ነዉ።አንድ ሰዉ ብቻ ጀርባዉ ላይ ተመትቷል።እስካሁን ሃያ ስምንት (አስከሬን) ተረክበናል።ሌሎች ደግሞ አሁን መጥተዋል።ሁለቱ ሰዎች ጭንቅላታቸዉ ሙሉ በሙሉ ተፈርክሷል። አንጎላቸዉ ተበትኗል።ሁሉም የተመቱት በአይኖቻቸዉ መሐል-ግንባራቸዉን ነዉ።ከከፍታ ቦታ ቁልቁል በተተኮሰ ጥይት ነዉ የተመቱት።ሁሉም ጭንቅላቱን፥ ደረቱን ወይም ልቡን ተመታል።»


የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ፍፃሜ ለጦርነቱ ቆስቋሽ፥ ዋና ተፋላሚዎች፥ ለአዉሮጳ-አሜሪካኖች የሰላም ብልፅግናቸዉ ጅምር፥ በኮሚንስት ካፒታሊስት የመከፋፈል፥ መነታረካቸዉ ሠበብ፥ የነሱን ግጭት ጦርነት ወደተቀረዉ ዓለም የመላክ፥ መግፋታቸዉ ብልሐት ዉጥን ነዉ።በጦርነቱ ወቅት ማርሻል ሞትጎመሪ፥ ከጄኔራል ሮሚዎ ጋር ለተፋለሙበት ግብፅ ባንፃሩ እንደ ብዙዉ የአፍሪቃና የዓረብ ሐገራት ሁሉ የጦርነቱ ፍፃሜ የሌላ ጦርነት ዉጊያ ሰበብ ምክንያት ነዉ።


የግብፅ ጦር፥ የመጀመሪያዉ የአረብ እስራኤሎች ጦርነት፥ የሲዊስ ቦይ ወይም (የብሪታንያ፥ የፈረንሳይ፥ የእስራኤል እና የግብፅ) ጦርነት፥ የስድስቱ ቀን ጦርነት፥የየመኖች ጦርነት፥ የዮም ኩፑር ጦርነት እየተባለ ከጦርነት ተለይቶ አያዉቅም።በዚሕ ሁሉ ጦርነት መሐል ያለፈዉ የአረብ፥ አፍሪቃዉ ሐያል ጦርን እንዲያዙ ባለፈዉ ዓመት በፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የተሾሙት ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል-ሲሲ ወታደራዊ ትምሕርት፥ ሥልጠናዉን ከግብፅ እስከ አሜሪካ፥ ብሪታንያ ድረስ ሔደዉ ተምረዉታል።



A member of the Muslim Brotherhood and supporter of deposed Egyptian President Mohamed Mursi hides from tear gas thrown by police during clashes in Nasr city area, east of Cairo July 27, 2013. The Muslim Brotherhood said at least 31 people were killed on Saturday when security forces opened fire on a protest by supporters of deposed President Mohamed Mursi in Cairo. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST) አስለቃሽ ጢስ
ጦርነት እንዳደረዉ የጦር ጄኔራል ግን አንድም ጦርነት ተዋግተዉ፥ አዋግተዉ አያዉቁም። አሌክሳንደሪያ የሠፈረዉን ክፍለ-ጦር ላጭር ጊዜ ከማዘዝ በስተቀር ብዙ ጊዚያቸዉን በግብፅ ኤምባሲዎች በወታደራዊ አታሼነት ከርዕሠ-ከተማ ርዕሠ-ከተማ ሲያቀያይሩ ነዉ-ያሳለፉት።


በሁለት ሺሕ አስራ-አንድ መጀመሪያ (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) በአደባባይ ሕዝባዊ ተቃዉሞ ከሥልጣን የተወገዱትን ፕሬዝዳት ሆስኒ ሙባረክን የተካዉ የጦር ሐይሎች ላዕላይ ምክር ቤት አባል ሆነዉ የታሪካዊቱን ሐገር ትልቅ ቤተ-መገንስት ወጣ ገባ ይሉበት ያዙ።የሙባረክ መወገድ ብዙም ለማይታወቁት ጄኔራል ሳይደግስ-አይጣላም እንደነበረ ሁሉ የሙርሲ መመረጥም የመሾም-መሸለማቸዉ ብሥራት ነበር።
እንደ ወታደራዊ አታሼ ዲፕሎማሲዉን፥ እንደ ወታደራዊ ገዢ የምክር ቤት አባል ቤተ-መንግሥትን የለመዱት አል-ሲሲ አንዴም ሳይዋጉ፥ ከጦርነት ተለይቶ የማያዉቀዉን ጦር የአዛዥነት ሥልጣን በያዙ በአስራ-አንደኛ ወራቸዉ የማያዉቁትን ጦርነት በሚያቁ ሹዋሚያቸዉ ላይ ከፈቱ።
ጀግናዉ ጄኔራል በሕዝብ የተመረጡትን ግን ተቃዋሚዎቻቸዉ ባደባባይ ሠልፍ የሚያወግዟቸዉን ፕሬዝዳት መሐመድ ሙርሲን ከስልጣን አስወግዱ።ሐምሌ ሰወስት።ሕዝብ በአብላጫ ድምፅ ያፀደቀዉን ሕገ-መንግሥት ሻሩ።በሕዝብ የተመረጠዉን ምክር ቤት በተኑ።እና ያደረጉት ሁሉ መፈንቅለ መንግሥት አይደለም አሉ።
ዳኛ አዲሊይ መንሱርን እንደ መጋረጃ ዘርግተዉ ታሪካዊቷን ሐገር ከጀርባ ይዘዉሩ ገቡ።መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ወገኖችን አስገደሉ።መፈንቅለ መንግሥቱ ከተደረገበት እስካለፈዉ ቅዳሜ በተቆጠረዉ ሃያ-ሰወስት ቀናት ዉስጥ ብቻ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ሁለት መቶ ሠዎች ተገድለዋል።በሺ የሚቆጠሩ ቆስለዋል።በመቶ የሚቆጠሩ ታስረዋል።እርምጃዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በጣም አሳስቧቸዉ ነበር።
«ባለሥልጣናት ከሁለት መቶ በላይ የሙስሊም ወንድማማቾች አባላትን ማሠራቸዉ በጣም አሳስቦኛል።ይሕ የብቀላ እና የመቀጣጫ ጊዜ አይደለም።ጊዜዉ ሁሉንም አሳታፊ እና የእርቀ-ሠላም ጊዜ ነዉ።»
ከአፍሪቃ ሕብረት በስተቀር «ዓለም አቀፍ» የሚባለዉ ማሕበረሰብ መፈንቅለ መንግሥቱን በግልፅ ቋንቋ አለወገዘም።አለመወገዙን ጄኔራል ሲሲ እና ተከታዮቻቸዉ ለእርምጃቸዉ እንደ ትክክለኛ ማረጋገጪያ ሰርቲፊኬት ቢቆጥሩት አይፈረድባቸዉም።በመግደል-ማሰሩ ቀጠሉበት።አላረካቸዉም። መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ተጨማሪ ሰዎችን ለማሠር እና ምናልባትም ባለፈዉ ቅዳሜ እንዳደረጉት ባደባባይ ለመግደል ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ እንዲደግፋቸዉ ጠየቁ።

Supporters of deposed Egyptian President Mohamed Mursi run from tear gas fired at them by police during clashes in Nasr city area, east of Cairo July 27, 2013. At least 70 people died on Saturday after security forces attacked supporters of deposed President Mohamed Mursi in Cairo, Muslim Brotherhood spokesman Gehad El-Haddad said, adding the toll could be much higher. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST TPX IMAGES OF THE DAY) አስለቃሽ ጢስ

ጄኔራሉ ሰዉን ለማሰር እና ለመግደል ሕግ እንዲወጣ አልጠየቁም።አቃቤ-ሕግ እንዲከስ፥ ጠበቆች እንዲከራከሩ፥ ዳኞች እንዲፈርዱ አልፈቀዱም።ትዕዛዛቸዉን የሚፈፅመዉ ጦርና ከየሥፍራዉ ለቅመዉ የሾማቸዉ የጊዚያዊ መንግሥት አባላት የሚወስዱትን እርምጃ፥ ሕዝብ ባደባባይ መፈክርና ጫጫታ እንዲያፀድቅላቸዉ በይፋ ጠየቁ።
«አሸባሪዎችንና አመፀኞችን ለመቅጣት (ሕዝቡ) በሠልፍ ሐላፊነቱን እንዲሰጠን እጠይቃለሁ።»
መፈንቅለ መንግሥቱን በመቃወም በተከታታይ አደባባይ የሚወጣዉን ሕዝብ የሚያስተባብረዉ የቀድሞዉ ፕሬዝዳት የመሐመድ ሙርሲ የቀድሞ ማሕበር ሙስሊም ወንድማማቾች የጄኔራል ሲሲን ጥሪ ከእርስ በርስ ጦርነት አዋጅ ነዉ የቆጠረዉ።ይሁንና የጄኔራሉን አዋጅና እርምጃ እንደሚፈግፉ በጭብጨባ ከገለፁት ታዛዥ ወታደሮቻቸዉ በተጨማሪ ጄኔራሉን ፈርቶም ይሁን ወድዶ ፍላጎታቸዉን ለማሟላት ባለፈዉ አርብ በርካታ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ነበር።እሱ አንዱ ነዉ።
«እዚሕ የመጣነዉ የጦር ሐይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብዱል ፈታሕ አል-ሲሲን ለመደገፍ ነዉ። አሸባሪዎችን እንዲመነጥሩ አረንጓዴ መብራት ለማሳየት ነዉ።ብዙ መጠበቅ አንችልም።ሐገሪቱ እየተቃጠለች ነዉ።»
ሐገሪቱ በርግጥ እየጋየች ነዉ።ሐገሪቱን የሚያጋየዉ ማነዉ ነዉ-ነዉ እንጂ ጥያቄዉ።ታንክ መትረየስ የታጠቀዉ ወይስ መስገጂያ ምንጣፍና መፈክር ያንጠለጠለዉ?የጄኔራል አል-ሲሲ ጦር ዳግም መልስ ሰጠ።
አርብ ለቅዳሜ አጥቢያ፥-የቢቢሲዉ ጋዜጠኛ ካይሮ ነበር።
«ጥቃቱ ከትናንት ማታ እስከ ጠዋት ቀጥሏል።የአዉቶማቲክ ጠመንጃ ተኩስ ይሰማናል።ተቃዋሚ ሠልፈኞቹ (እኛ እንዳንመታ) ዙሪያችንን ከበዉ ሠብአዊ ጋሻ ሠሩ።ጥይቶችና የሲ ኤስ ጋሶች ይተኮሱብናል።አየሩ በጢስ ታፍኗል።ሰዎች ያስታዉካሉ።የመስክ ሆስፒታሎቹ ወለል ደም ተንጣሎባቸዋል። አብዛኞቹ ቁስለኞች ጭንቅላታቸዉ ተበጥርቋል።አንድ በግምት አስራ-ሁለት ዓመት የሚሆነዉ ሕፃንም እዚያ ነበር።ሰዉነቱ በደም ተሸፍኗል።---» እያለ ይተርካል።

Egypt's Defense Minister Abdel Fattah al-Sisi is seen during a news conference in Cairo on the release of seven members of the Egyptian security forces kidnapped by Islamist militants in Sinai, in this May 22, 2013 file picture. To match Special Report EGYPT-PROTESTS/DOWNFALL REUTERS/Stringer/Files (EGYPT - Tags: MILITARY HEADSHOT POLITICS) አል ሲሲ
የተገደሉትን ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር የሚያዉቅ የለም።ሲበዛ-ሁለት መቶ ሲያንስ ሰማንያ ይገመታል።ይሕ ካይሮ ነዉ።አሌክሳንደሪያ ደግሞ በትንሽ ግምት አስር ሰዉ ተገድሏል።በሌሎች ከተሞችም እንዲሁ።የሙስሊም ወንድማማቾች ማሕበር ቃል አቀባይ የወታደራዊ ሁንታ እርምጃ መጥፎ ገፅታ ይሉታል።
«የምናየዉ የወታደራዊ ሁንታዉን አስጠሊታ ገፅታ ነዉ።ከአንድ መቶ ሐምሳ በላይ ሠዎች ተገድለዋል።በሺ የሚቆጠሩ ቆስለዋል።የከፋ ሠብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነዉ።ሰዎች በዘፈቀደ ይታሰራሉ።ወታደራዊ አገዛዝ በአንድ ሐገር ላይ ሊፈፅም የሚችለዉን መጥፎ ነገር ሁሉ እያየን ነዉ።ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱ ወደ ቀድሞዉ የሙባረክ ሥርዓት እየመለሰን ነዉ።»
የሁለት ሺሕ አምስቱን የዓለም ታላቅ የሠላም ሽልማት ኖቤልን የተሸለሙት ዶክተር መሐመድ አል-በራዳይ ጄኔራል ሲሲ ከጀርባ የሚያዙት ጊዚያዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸዉ።ግብፅ ግን የሠላም ኖቤልን ሜዴሊያ ያንጠለጠለ ምክትል ፕሬዝዳት እንጂ ሠላም አይደለችም።ግብፅ ሠላም አለመሆኗ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ እንዳሉት ሐገራቸዉን ያሳስባታል።«(ለግብፅ ሹማምንት) ሰላማዊ ተቃዉሞ ሰልፍ የማድረግ መብትን እንዲያከብሩ ነግሬያቸዋለሁ።» አሉ አሜሪካዊዉ ትልቅ ዲፕሎማት።
የአዉሮጳ ሕብረቷ የዉጪ ጉዳይ የበላይ ሐላፊ ካትሪን አሽተን አሳሳቢዉን ጉዳይ በቅርብ ለማየት ወደ ካይሮ ተጉዘዋል።«አሳሳቢ፥ በጣም አሳሳቢ፥ በጥልቀት አሳሳቢ» ከሚለዉ የዲፕሎማሲ ሽርደዳ ባለፍ ቅዳሜ የተፈፀመዉን ግድያ በግልፅ ያወገዘ-የሐያል ሐገር ባለሥልጣን የለም። ግድያዉን ለማዉገዝ ትንሽም ቢሆን የደፈሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባን ኪ ሙን ብቻ ናቸዉ።
ጄኔራል ሲሲ፥ መሐመድ ሙርሲን ካስልጣን ካስወገዱ ወዲሕ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በትንሽ ግምት ሰወስት መቶ ሰዎች ተገድለዋል።የቆሰሉትን የቆጠራቸዉ የለም።በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟል።ምጣኔ ሐብቷ ደቋል።ከሁሉም በላይ አምና ይሄኔ ብልጭ ብሎ የነበረዉ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ጅምር ባይጠፋ ተዳፍኗል።የሙስሊም ወድማማቾች ማሕበር ቃል አቀባይ ከዚሕም አልፈዉ ተዘርፏል ባይ ናቸዉ።

Protesters cheer and dance with flares as they gather for a mass protest to support the army in front of the presidential palace in Cairo July 26, 2013. At least seven people were killed and hundreds wounded in scattered violence across Egypt during mass rallies for and against the army's overthrow of Islamist President Mohamed Mursi, who was placed under investigation for murder. REUTERS/Asmaa Waguih (EGYPT - Tags: POLITICS CIVIL UNREST) ካይሮ «ትነዳለች»


«ዴሞክራሲያችን ተወስዶብናል።የመረጥናቸዉ ዴሞክራሲያዊ ተቋማት በሙሉ ተወስደዉብናል።እዚሕ የምገኘዉ መጀመሪያ ግብፃዊ በመሆኔ ነዉ።የሙስሊም ወንድማማቾች ተወካይነቴ ሁለተኛ ደረጃ የሚሰጠዉ ነዉ።ትናንት-ቅዳሜ አደባባይ የወጡት በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩት ሰዎች የሙስሊም ወንድማማቾች ደጋፊዎች ብቻ አልነበሩም።ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የቆሙ ሁሉ ነበሩበት።»

ምዕራባዉያን መገናኛ ዘዴዎች «እስላማዉያን» የሚሏቸዉ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙትና ባንፃራቸዉ የቆሙት የመፈንቅለ መንግሥቱ ደጋፊዎች ግጭት፥ዉዝግብ የሰለቻቸዉ ግብፃዉያን «ሰወስተኛ ግንባር» የሚባል ሥብስብ ፈጥረዋል።ባብዛኛዉ የዩኒቨርስቲ መምሕራንና ባለሙያዎች የመሠረቱት ስብስብ ሙርሲንም፥ ጄኔራሉንም ይቃወማል።በዚሕም ብሎ በዚያ ግብፅ ቁልቁል እየተንደረደረች ነዉ፥ባፍጢሟ ሳትደፋ አዳኝ ታገኝ ይሆን?

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ
source... http://www.dw.de

ፍርድ ቤቱ በእነ መላኩ ፈንታና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መዝገቦች በተጠረጠሩ 19 ግለሰቦች ላይ ለ8ኛ ጊዜ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት በእነ መላኩ ፈንታ እና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መዝገቦች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ 19 ግለሰቦች ላይ ለ8ኛ ጊዜ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ።
የፈዴራሉ ስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን የምርመራ ቡድን በመዝገቦቹ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉ 19 ግለሰቦች ላይ የካሄደውን የምርመራ ሂደት ለፍርድ ቤቱ ዛሬ አቅርቧል።
የተጠርጣሪ ጠበቆች የፌደራሉ ስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ቡድን በየጊዜው የሚያቀርበው የምርመራ ሂደት ተመሳሳይነት ያለው ነው ሲሉ ፥ ፍርድ ቤቱ በበኩሉ መዝገቡን በመመርመር ሂደቱ በየጊዜው መሻሻል እያሳየ ነው ብሏል።

ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 2ኛ የወንጀል ችሎት የቀረቡ ተጠርጣሪዎች በሁለት መዝገብ የተካተቱ 19 ግለሰቦች ሲሆኑ ፥ የቀድሞው የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ በእርሳቸው በተሰየመው መዝገብ የተጠቀሱት አቶ እሸቱ ወልደሰማያት ፣ አቶ ማርክነህ አለማየሁ ፣ አቶ አስመላሽ ወልደማርያም ፣ አቶ ከተማ ከበደ ፣ አቶ ስማቸው ከበደ ፣ ዶክተር ፍቅሩ መሃሩ እና የአቶ ማርክነህ እህት ወይዘሮ ትእግስት አለማየሁ ናቸው ።

አቶ መላኩ በሚሌ ፍተሻ ጣቢያ ህገ ወጥ በሆነ ትእዛዝ ሳይፈተሹ ያለፉና ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ እቃዎችን አስመልክቶ እጃቸው ነበረበት በሚል በተጠረጠሩበት ወንጀል ፥ እየተካሄደ ባለው ምርመራ ሂደቱ ወደፊት እየተጓዘ መሆኑን የምርመራ ቡድኑ ገልጿል ።

ቡድኑ ያከናወናቸው ተግባራት

በመዝገቡ ከተካተቱ ስምንት ተጠርጣሪዎች መካከል ከአቶ ከተማ ከበደ ፣ አቶ ስማቸው ከበደ እና ወይዘሮ ትእግስት አለማየሁ ውጪ ፥ የተቀሩት በህገ ወጥ መንገድ በጅምላ የተቋረጡ መዝገቦች እና ያአግባብ የታክስ ኦዲት በመከለስ ተግባር የመንግስት ገቢ ዝቅ እንዲል ማድረግ የሚለው ሌላው የምርመራ ቡደኑ እድገት ያሳየ ምርመራ ካካሄደባቸው ወንጀሎች ተጠቃሽ ነው።

መላኩ ፈንታን ጨምሮ በመዝገቡ ተካተው የነበሩ የመንግስት ሰራተኞች ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አካብተዋል በሚል በየተረጠሩበት ወንጀል ፥ የምርመራ ቡድኑ በተሰጠው ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የሃብት ጥናት መረጃ ማሰባሰቡንም አስታውቋል።

ቡድኑ ተያያዥነት ያላቸው የምርመራ ስራዎችን ማከናወኑን እና ለቀሪ ምርመራ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት የጠየቀ ሲሆን ፥ የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላችው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄው በዝቷል፤ ተጠርጣሪዎች በዋስ ቢለቀቁ የነበራቸው ሃላፊነት አሁን ከእነርሱ ጋር ስለሌለ እንደተባለው ምስክሮችን አያስፈራሩም፣ ማስረጃም አያጠፉም፤ የሚሉና ሌሎችንም አቅርበዋል።

ከተጠርጣሪዎች አቶ ማርክነህ ጠበቃቸው ሳይመጡ በመቅረታቸው በግላቸው በጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ ምንም የማቀርበው የመከራከሪያ ነጥብ የለኝም ፍርድቤቱ ራሱ የመሰለውን ትእዛዝ ይስጥ ፤ ነገር ግን የዋስትና መብቴ ይከበርልኝ ሲሉ አመልከተዋል።

የኮሚሽኑ የምርመራ ቡድን በበኩሉ ከተጠርጣሪዎች እና ከጠበቆቻቸው ዘንድ በዋስትና ጥያቄው ላይና የተነሳው የተቃውሞ ሃሳብ ፥ የወንጀሉ ውስብስብነት እና ከባድነት ካልሆነ በስተቀር፤ ቡድኑ በየጊዜው በልዩ ትኩረት በትጋት እየሰራ መሆኑንና ተጓተተ ለተባለው  የሁለት ኩባንያዎች የኦዲት ስራም እንዲሁም መስክ የሄደው የምርመራ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ የምርመራ ስራ ማካሄዱን በምሳሌነት አንስቷል።

ግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ቡድኑ ቀሪ የምርመራ ስራዎች እንዳሉት በመገንዘብ የተጨማሪ 10 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዶ የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቀ ለነሃሴ 2, 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በሌላኛው እና በአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ስም በሚጠራው መዝገብ ደግሞ የምርመራ ቡድኑ በኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በነበሩት አቶ ገብረዋህድ አቶ በላቸው በየነ እና አቶ ጥሩነህ በርታ ፥ በህገ ወጥ መንገድ በጅምላ አቋርጠውታል በሚል በተጠረጠሩበት ወንጀል ላይ በተፈቀደው 10 የምርመራ ቀን ውስጥ የሁለት ምስክሮችን ቃል መቀበል እና የሰነድ ማስረጃ የማሰባሰብ ስራዎችን አከናውኛለሁ ብሏል ።

ሁሉም ተጠርጣሪዎች በመመሳጠር የመንግስት ቀረጥና ታከስ እንዳይሰበሰብ በማድረግ ያለአግባብ ተጠቅመዋል በተባለው የሙስና ወንጀል ላይ ፥ በተመሳሳይ የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰብሰቡን አስረድቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንግስት ሲሚንቶ ያለቀረጥ በአስመጪዎቸ መጥቶ ለታለመለት ስራ እንዲውል ፍቃድ የሚሰጥ ሲሆን ፥ አቶ ነጋ ያለቀረጥ እንዲገባ የተደረገውን ሲሚንቶ ከአስመጪው ኮንትራት በመውሰድ አሁን ኮሚሽኑ እየደረስኩበት ነው ባለው የምርመራ ሂደት አቶ ነጋ ከባለሰልጣኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ሲሚንቶውን እያጓጓዙ በተለያዩ ሱቆች አራግፈዋል ብሏል።

ቡድኑ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ወደ አዲስ አበባ ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት በማምራት ስሚንቶው ለታለመለት አላማ መዋል አለመዋሉን የተመለከተ መረጃ ኮፒ አድርጎ መውሰዱን ያመለከተ ሲሆን ፥ ለቤቶች ልማት ይገባል ተብሎ በየሱቆች ለገባው ሲሚንቶ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ ከባለስልጣኑ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተወልደ ብስራት እና አሞኘ ታገለ ተጠያቂ ተደርገዋል።

ቡድኑ በዚህ መዝገብ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እና አቶ ጥሩነህ በርታ ላይ የመንግስት ግብር የሚሰውሩ ግብር ከፋዮችን ማጋለጥ ይቻል ዘንድ በተዘረጋው ስርአት መሰረት ፥ ለጠቋሚዎች የሚከፈል አበል ጠቋሚ ሳይኖር ጠቋሚ እንዳለ ተደርጎ ለግል ጥቅማቸው አውለውታል በተባለው ከፍተኛ ገንዘብ ምዝበራ ዙሪያ የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማሰባሰቡን አስታውቋል።

በአጠቀላይ በዚህ መዝገብ የምርመራ ቡድኑ ከ27 የሚልቁ የምስክሮችን ቃል ሲቀበል ፥ 26 የሚሆኑ ምስክሮች ይቀሩኛል ብሏል።

ቀሪ ተግባራትን ለማከናወንም ቡድኑ ተጨማሪ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ያስፈልገኛል በማለት ሲጠይቅ ፥ የግራ ቀኙን የመረመረው ችሎቱ ቀሪ የምርመራ ስራዎች እንዳሉ ተገነዘቢያለው በማለት  የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ ለ8ኛ ግዜ በመፍቀድ ፥ የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅ ለነሃሴ 2 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።



በጥላሁን ካሳ



source...http://www.fanabc.com/index.php?option=com_content&view=article&id=4776%3A---------19---8----&catid=102%3Aslide


የዘመኑ መንፈስ

July 29, 2013
በእውቀቱ ስዩም
Bewketu-Seyoum-young-Ethiopian-writer
ባገራችን ባሁኑ ጊዜ ብዙ ተከታይ ያለው ሃይማኖት ብሄርተኝነት ይባላል፡፡የብሄርተኝነት ምእመን ከሆንክ የነፍስ አባት ይኖርሀል፣በጭፍን የምትቀበለው ቀኖና ይኖርሀል፣ነገ የምትገባባት የተስፋ ምድር ይኖርሀል፣ከሁሉ በላይ ደግሞ ብርቱ ችግርህን የምትደፈድፍበት የመስዋእት በግ ይኖርሀል፡፡
ሃይማኖቶች ምእመናንን ብቻ ሳይሆን መናፍቃንንም ያፈራሉ፡፡ብሄርተኞች በስሜት የሚነድደውን ምእመን ብቻ ሳይሆን የኔ ቢጤውን መነፍቅም እንደሚያፈሩ አንርሳ፡፡በነገራችን ላይ ሃይማኖትን መካድ ማለት ሃይማኖት የሚያነሳቸውን አብይ ጥያቄዎች መካድ ማለት አይደለም፡፡እንዲሁም፣ ብሄርተኝነትን መካድ ማለት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ህልውና መካድ ማለት አይደለም፡፡በዚህ ጉዳይ ፣መናፍቅ መሆን ማለት፣ የብሄርተኛ ነቢያት ሰለ ጭቆና ስለ ነጻነት ብሎም ስለ ኢትዮጵያዊነት የሚያቀርቡትን አጉል እምነት መጠራጠር ማለት ነው፡፡
ከኢትዮጵያዊነት እንጀምር፡፡
ከዘመናችን የብሔርተኝነት ነቢያት አንዱ ጃዋር መሐመድ በቅርቡ ከእንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ ስለኢትዮጵያዊነት የሚከተለውን ይላል፡፡
‹‹…ኢትዮጵያን የመሠረታት የሶሰትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡በአማራው፣በኦሮሞው፣በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭት እና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡…የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለው የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው››
ጃዋር የኢትዮጵያን መሠረት የሦስት ብሄረሰቦች የስልጣን ግብግብ አድርጎ ወስኖታል፡፡ በመጀመርያ፣ ሌሎች ብሄረሰቦች በግብግቡ ተሳትፎ እንዳልነበራቸው አድርጎ ማቅረቡ አንድ
Bewketu Seyoum is a young Ethiopian writer
በእውቀቱ ሥዩም
ጉድለት ነው፡፡ ግን ዋናው ቁምነገር ይሄ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ የግጭት ውጤት ብቻ እንደሆነች አድርጎ ማቅረቡ ነው ትልቁ ስሕተት፡፡ ሲጀምር፣ የግብግብ ታሪክ መሠረት ይንዳል እንጂ መሠረት አይገነባም፡፡ እንደኔ ግምት፣የኢትዮጵያ መሠረት የሆነው ብሄረሰቦች ለጋራ ሕልውና ሲሉ የሚያደርጉት የመደጋገፍ ታሪክ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ፣ ታሪክ ከላሾች፣የብሄሮችን የ‹‹ግብግብ››ታሪክ ሞቅ አድርገው፣አኳሽተው ሲጽፉ፣የብሄሮች መደጋገፍ ታሪክን ግን ቸል ይሉታል፡፡ አለያም እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት፣ በጥቂት መስመሮች ብቻ ጨረፍ አድርገው ያልፉታል፡፡ለነገሩ፣ከፋፋይነትን ብቸኛ ያስተዳደር ፈሊጥ አድርጎ የሚቆጥር ሰው በታሪክ ገጾች ውስጥ መመልከት የሚፈልገው ክፍፍልን ብቻ ነው፡፡ታሪክ ግን ብዙ በጎ የትብብር ገጠመኞችን መዝግቧል፡፡ለምሳሌ ጀግናው አጼ ዮሐንስ አራተኛ በበዛሬይቱ ኤርትራ የግብጽን ወራሪ ጦር ድል የነሡት የትግራይ ጀግኖችን ብቻ አሠልፈው አልነበረም፡፡ በዚህ ጦርነት ከግብጽ ጎን ሆኖ፣የተዋጋው አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ዊልያም ዴይ እንደመሠከረው ወልቃይቶች፣ጥልጣል የተባሉ የአፋር ንኡስ ክፍሎች፣የወረኢሉ ኦሮሞዎች ለንጉሰነገስቱ ድጋፍ ለማድረግ ተሸቀዳድመዋል፡፡በራስ ወሌ የሚመሩ የአማራ ወታደሮች ተሳትፈዋል፡፡የጎንደር ቀሳውስት ለጦርነቱ ድጋፍ ለማድረግ አድዋ ገብተዋል፡፡ የጎጃሙ ራስ አዳል የደርሼልሀለሁ አለኝታቸውን አሳይተዋል፡፡ የሸዋው ንጉስ ምኒልክ ሳይቀር በመቶ የሚቆጠሩ በቅሎዎችንና ማበረታቻ ልከዋል፡፡ ዝርዝሩን ማንበብ ለሚፈልግ Muslim Egypt Christian Abyssinia የተባለውን የዚህ ደራሲ ማስታወሻ ገጽ 291-292 ያንብብ፡፡ መጽሐፉን በኢንተርኔት ቤተ-መጻህፍት ውስጥ በብላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡
ከተለያየ መአዘን የመጡ እኒህ ኢትዮጵያውን ከዘመቻው የሚያገኙት ድልን ብቻ አልነበረም፡፡ በዘመቻ ወቅት ባህል ይዋዋሳሉ፣ቃላት ይወራረሳሉ፣ ስንቅ ያዋጣሉ፣ ልምድ ይለዋወጣሉ፡፡ በሂደት ተቃራኒ ከሚመስሉ ልማዶች የነጠረ ኢትዮጵያዊ ባህል እንደ አረቄ ይወጣል፡፡ ይህን በመዋጮ የተገኘ ባህል ‹‹የአማራ ባህል ››ብሎ ማጥበብ የጸና ድጋፍ ያለው አይመስለኝም፡፡
ጃዋር‹‹አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባህላዊ ሥርጭትና በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች›› በማለት ሳይወሰን ‹‹የኢትዮጵያ አገራዊ መለያ ማንነት የምንለው አማራ ብሄራዊ ማንነት ነው›› ሲል ይጨምራል፡፡ ጎበዝ ኧረ በህግ አምላክ!!! የኢትዮጵያ ባህልኮ ካንድ አለት የተጠረበ ሕንጻ አይደለም፡፡ ከብዙ የመዋጮ ጡቦች የተገነባ ነው፡፡ ጃዋር እያንዳንዱን ጡብ ቀርቦ ቢመረምረው እዚህ የደረሰበት እርግጠኝነት ውስጥ የሚደርስ አይመስለኝም፡፡
እስቲ ከደቃቅ ምሳሌ እንጀምር፡፡ ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ ስራ ሲሠራ አስቀድሞ የሚመጣው የቡና ስነ-ስራታችን ነው፡፡ አንዲት ጠይም ፣ባለሹርባ ሴት፣ያበሻ ቀሚስ ለብሳ ቡና ስትቀዳ የሚያሳይ ምስል በየቦታው ማየት የተለመደ ነው፡፡ይህ ችክ ያለ ምስል በስነ-ስእል ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ቢዮንሴና ጆን ኬሪ አገራችንን በጎበኙበት ሰአት የቡና ስነስርአት ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት የውጭ እንግዳ የቡና ስርአታችንን እንደ ኢትዮጵየዊ መለዮ እንዲመዘግብልን ፈልገናል ማለት ነው፡፡ ለዋለልኝ መኮንን እና ለጃዋር መሀመድ ይህ የአማራ ባህል መሆን አለበት፡፡ በመጀመሪያ እይታ ይመስላል፡፡ ጉዱ ዝርዝሩ ላይ ነው፡፡ የሴትዮዋ ሹርባ ከሐማሴን ወይም ከተንቤን ሴቶች ልማድ ጋር ስምም ነው፡፡ ያበሻ ቀሚሱን የሽሮሜዳ ጋሞ የሸመነው ሊሆን ይችላል፡፡ ጀበናው የጂማ ሙስሊም ኦሮሞዎች ያስተዋወቁት ነው፡፡ አቦል ቶና በረካ አረብኛ ወይም የተወላገደ አረብኛ የተገኙ ቃላት ናቸው፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ትንሳኤ በአል በሉባንጃ የሚታጀብ ቡና የማያፈላ ክርስትያን ኢትዮጵያዊ ማግኘት ይከብዳል፡፡ ከጥቂት መቶ አመታት በፊት ግን ቡና የእስላም ልማድ ተደርጎ ይቆጠር ነበር፡፡ የቡና ትርኢት የሙስሊም አበው በኢትዮጵያ ባህል ላይ የጨመሩት በጎ መዋጮ እድርገን ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያ ጊዜ በተባለው አናጢ ከብዙ ጡቦች የተገነባች ናት የምንለው ለዚህ ነው፡፡
ጃዋር አማራው የራሱን ባህል በኦሮሞው ላይ እንደጫነ ሲያምን ተገላቢጦሹ ያለው አይታየውም፡፡ ኦሮሞ በረጅም ዘመን፣በሠፊ ምድር፣ ሰፍሮ የመኖሩን ያክል በጎረቤቶቹና በወደረኞቹ ላይ የባህል ተጽእኖ አላሳደረም ማለት ብርቱ ባህል የለውም ከማለት አይለይም፡፡ ባገራችን ዋና ዋናዎቹ የባህል ቀራጺዎች ጦርነትና ሐይማኖት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ፣ጀግኖችን እና ነገስታትን አባ በዝብዝ አባ ታጠቅ፣ አባ ዳኘው አባ ነጋ ወዘተ እያሉ መሰየም ገናና ኢትዮጵያዊ ባህል መሆኑን ብዙዎቻችን እናውቃለን፡፡ ብዙዎቻችን የማናውቀው ይህንን ባህል ያስተዋወቁት ለግማሽ ምእተአመት ያክል ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት የየጁ ኦሮሞዎች መሆናቸውን ነው፡፡ ብላቴን ጌታ ማህተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል ቼ በለው በተሰኘው መጽሐፋቸው ይህንን እንዲህ በማለት ያረጋግጣሉ-
‹‹ነገስታቱ በ‹‹አባ›› ወይም የእገሌ ባለቤት በሚል ቅጽል ስም መጥራት የጀመሩት የኦሮሞዎችን ወይም የወረሸሆችን ልምድ በመከተል ነው ከ1838 ዓም ወዲህ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ወትሮ ግን በተለይም 1474-1713 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ ቅብዓ መንግሥቱ በሚደረግላቸው ሰአት ይወጣላችው የነበረው የግርማ ስም ወይም ስመ መንግስት ‹‹ሰገድ›› የሚል ኃይለቃል በመጨመር እንደነበር ቀጥሎ ያለው ያረጋግጣል፡፡ ወናገድ ሰገድ፣ አጽናፍ ሰገድ፣ አድማስ ሰገድ፣ መለክ ሰገድ፣አድያም ሰገድ ሉል ሰገድ››በማለት ይዘረዝራሉ፡፡
ከጥቅሱ ሦስት ፍሬ ነገሮችን መረዳት ይቻላል፡፡
1- ይህ ባህል ባንድ የዘመን ምዕራፍ ላይ ከኦሮሞ ብሄረሰብ የመነጨ የኢትዮጵያ ባህል ነው፡፡
2- ባህሉ ብርቱ ተጽእኖ ከመፍጠሩ የተነሳ አማራና ትግራይ ነገስታት ለረጅም ዘመን ይጠቀሙበት የነበረውን የስያሜ ዘይቤ ሽሯል፡፡
3- አማራው ታሪክ ጸሀፊ ለባህሉ አስተዋዋቂዎች የባለቤትነት እውቅና ሰጥተዋል፡፡
በሃይማኖት ረገድም ተመሳሳይ ነገር ነው የሚገጥመን፡፡ ለምሳሌ አቴቴ የሚለውን ቃል ደስታ ተክለወልድ ሲተረጉሙ ‹‹ዛር፣በሴት ስም የምትጠራ፣ ውቃቤ ፣ አማሮች ከኦሮሞዎች የወረሷት ጨሌ የሚያጠልቁላት አቴቴ ጊንቢ ሐራ አቴቴ ዱላ እያሉ እንቀት የሚቀቅሉላት አምልኮ ባእድ፣ትርጓሜ ጠባቂ ማለት ነው››ይላሉ፡፡
‹‹አምልኮ ባእድ ››የሚለውን አሉታዊ ሐረግ፣የክርስትያን አድልኦ ያለበት ፍርድ አድርገን እንለፈው፡፡ ዋናው ፍሬ ነገር፣ የአሮሞው ባህል በአማራው ባህል ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን ማወቃችን ነው፡፡ ይህም አንዱ ብሄረሰብ ሁልጊዜ ጫኝ ፣ ሌላው ብሄረሰብ ሁልጊዜ ተሸካሚ እንደነበረ አድርገው ሊነግሩን የሚፈልጉትን ሰዎች ያስተባብላል፡፡ በሁለቱ ግዙፍ ብሄረሰቦች መካከል የነበረው ግኑኝነት የእኩዮች ልውውጥ ነው፡፡ የባህሎች ውርርስ ነው ማለት እንችላለን፡፡ ነገርን ነገር ያነሳዋልና፣ የማንኩሳ ዘመዶቼ የሚያስደነግጥ ነገር ሲገጥማቸው ‹‹አቲቲን ወሰድከው›› ይላሉ፡፡ ቀልቤን ገፈፍከው ለማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ባህላዊ ተጽእኖ በወለጋ ድንበር ላይ ቆሟል ያለው ማነው?
ስለጉዲፈቻ ባህል ብዙ ሰዉ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡ በጦርነት ወቅት ምርኮኞችን ባርያ ማድረግ ወይም መግደል በብዙ ማህበረሰቦች የተለመደ ነው፡፡ በኦሮሞ አበዋዊ ባህል ውስጥ ግን ምርኮኞች በልጅነት ይታቀፋሉ፡፡ ከሌላ ብሄረሰብ ቢመጡም የኦሮሞ ብሄረሰብ የሚያገኘውን መብት ሳይነፈጋቸው ያድጋሉ፡፡ ይህንን ልማድ በአማራው ማህበረሰብ ውስጥም እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ በጎጃሙ ንጎስ ተክለይማኖትና በወለጋ መሳፍንት መሀል በተደረገው ጦርነት የተማረከው ብላቴና ነገሮ ዋቅጅራን እንደልጅ አሳድገውታል፡፡ ክርስትና አስነስተው ተክለኢየሱስ አሰኝተውታል፡፡ ራሱ በጻፈው ማስታወሻ ‹‹በጠጅና በስጋ አደግሁ›› በማለት የመሳፍንት ልጆች ያገኙት የነበረውን ምቾት ሳይነፈገው ማደጉን ይመሰክራል፡፡ ነገሮ ፣ ከማእረግ ወደ ማእረግ እየወጣ የንጉሱ ጸሐፌ ትዝዛዝ እስከመሆን ደርሷል፡፡ ተመሳሳይ መልኩ በሸዋ ምርኮኛው ቆሴ ዲነግዴ በቤተመንግስት እየተቀማጠለ አድጎ ሐብተጊዎርጊስ በሚል ስመ ክርስትና የኢትዮጵያ የጦር ምኒስትር እስከመሆን ደርሷል፡፡ ሰዎችን በልዩ ቋንቋቸው ምክንያት ባይተዋር ማድረግ ኢትዮጵያዊ ባህል አልነበረም፡፡
እኩዋን ባህላችን አማርኛችን እንኳ የጉራማይሌነታችን ምስክር ነው፡፡ አሁን ኦሮምኛ ያልተነካካ አማርኛ ማግኘት ይቻላል?፡፡ እሰቲ ለናሙና ያክል ‹‹ተወርዋሪ ኮከብ›› ከተባለው የዮሐንስ አድማሱ ምርጥ የአማርኛ ግጥም ውስጥ ጥቂት መስመሮች ልቆንጥር፡፡
1) ተወርዋሪ ኮከብ በራሱ ነበልባል በራሱ ነዲድ ተቃጥሎ የጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ በምናውቀው ሰማይ ነበረ በይፋ
2) ሜዳና ተራራ በመሐል ሸለቆ
ጨፌውና መስኩ በኒህ ተደብቆ
3) ሐቀኛ ጠፍቶበት በዋለበት መልቲ
ጌጥ ነው ድንቁርና የገዳዮች ሎቲ
4) ብልጭ ብሎ ጠፋ
ተወርዋሪ ኮከብ የሐሳብ አንጋፋ
በመረጥኳቸው መስመሮች ውስጥ የሚገኙት ‹‹ይፋ፣ ጨፌ፣ መልቲ፣ ሎቲ፣ አንጋፋ፣›› የተባሉት ቃላት ኦሮሚኛ ናቸው፡፡ ካንድ የአማርኛ ግጥም ይህን ያህል ኦሮሚኛ ከተገኘ በሙሉ መዝገበ ቃላት ውስጥ ምን ያህል ሊገኝ እንደሚችል አስቡት፡፡ ይህን ያክል ነው የተዋሀድነው፡፡
የኢትዮጵያ ባህል የተውጣጣ ባህል እንጂ ጃዋር እንደሚለው የአማራ ባህል ብቻ አለመሆኑን በመጠኑም ቢሆን ያሳየሁ ይመስለኛል፡፡ ጃዋርን እዚህ ላይ ላሰናብትና ለማጠናቀቂያ የምትሆን አንዲት አንቀጽ ልጨምር፡፡
ባህልን ማክበር ጥሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በስሜት ሚነድደው የብሄርብሄረሰብ ፖለቲካችን፣ ዜጎች ለባህል ያላቸውን ፍቅር ወደ ጭፍን አምልኮአዊ ፍቅር እያዘቀጠው ነው፡፡
ባባቶቻችንና በእኛ መካከል የባህል ፋይዳ ልዩነት ያለ ይመስለኛል፡፡ አባቶች ባህላቸውን ያገኙት በኑሮ ጣጣ አስገዳጅነት ነው፡፡ ለምሳሌ የኔ አያት ቁምጣ ሱሪ የሚታጠቀው ከሌሎች ብሄረሰቦች ለየት ብሎ ለመታየት አይመሰለኝም፡፡ በቂ አቡጀዲ ስላላገኘ ነው፡፡ ወይም ለስራ እንዲያመቸው ባጭር መታጠቁ ይሆናል፡፡ እኔ ግን የብሄረሰቦች ቀን ሲከበር ቁምጣ ለብሼ ራሴን በማስጎብኘት እንድኮራ ይጠበቅብኛል፡፡ ጉድ እኮ ነው!!! ጋቢ በጥንት ጊዜ የሙቀት ምንጭ ነበር፡፡ ዘንድሮ የኩራት ምንጭ ሊሆን ይቃጣዋል፡፡
የዛሬዎቹ ባህል አምላኪዎች ባህል ሲያስቡ ለውጥን ይረሳሉ፡፡ ባንድ ወቅት የሚያኮራው ያንድ ብሄረሰብ ባህል በሌላው ወቅት ይናቃል፡፡ ባንድ ወቅት የሚያስሸልመው በሌላ ጊዜ ያስቀጣል፡፡ ከጥቂት መቶ አመት በፊት ዝሆን መግደል በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ የሚያጎናጽፍ ተግባር ነበር፡፡ ዝሆን የገደለ ልዩ አምባር ክንዱ ላይ ያጠልቃል፡፡ እስኪ ዛሬ ያባቶቼን ባህል ለማክበር ነው ብለህ ፓርክ ውስጥ አርፎ የተኛውን ዝሆን ግደል፡፡ በአምባር ምትክ ካቴና ይጠልቅልሀል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች አልባሳት የተባለውን የተደጋገመ ግን ያልታሰበበት ቃል ከዚህ አንጻር ቃኙት፡፡ ሲጀምር ፣ዛፍ እንኳ ቅርፊቱን በሚቀያይርበት ዓለም፣ብሄር ብሄረሰቦች በየጊዜው አልባሳታቸውን አይቀያይሩም ወይ?፡፡ የብሄረሰቡ አልባስ ሲባል በየትኛው ዘመን የሚለበሰው ነው? የእንዳለጌታ ከበደ እናት ሲነግሩን፣ ዛሬ በጉራጌ ዘፈን ላይ በቲቪ የምናየው የሴቶች ሻማ ቀሚስ በደርግ ዘመን የተጀመረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት የነበረው ሸማ ነው፡፡ ከሸማው በፊት ደግሞ የቆዳ ቀሚስ ይለበስ ነበር፡፡
ሌላው፣ አንድ ማህበረሰብ አልባሳት በየማእረጉ ልዩ ልዩ ልብሶች ይኖሩታል፡፡ ወታደሩ ያባ ገዳውን ልብስ የሚለብስ አይመስለኝም፡፡ ባሮች ከጌቶች ልብስ ጋር የሚመሳሰል ልብስ እንዲለብሱ አይፈቀድላቸውም ነበር፡፡ በፊውዳል ማህበረሰብ ከላይ አስከታች መልበስ መከናነብ የጨዋነት ምልክት ነው፡፡ ይህንን በሸዋና በትግራይ ብቻ ሳይሆን በቅድመ ምኒልክ ከፋ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ባንጻሩ፣ባሮች በከፊል ተራቁተው መታየት አለባቸው፡፡ ባጠቃላይ በኢትዮጵያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አለባበስ በበሄረሰብ ላይ ሳይሆን በመደብ ላይ የተመሰረተ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለዚህ የብሄር አልባሳት የሚባለው እንደ ማንኛውም ሾላ በድፍን ሐሳብ በጥርጣሬ መታየት አለበት፡፡
ትውልዱ የባህል ፈጣሪ መሆን ሲገባው፣የባህል ሙዚየም ሆኖ ተተክሏል፡፡አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ባንድ ወቅት እንዳለው ‹‹ካባቶቹ የማይበልጥ ትውልድ፣ እንዳልተፈጠረ ይቆጠራል››
ማሳረጊያ
ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ያቆያት የነገስታቱ ጉልበት ብቻ ነው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ኢትዮጵያ የተሸመነችበትን ውስብስብ ክር ማየት ያልታደሉ ናቸው፡፡ዛሬ ኢትዮጵያን በታትነን ክልላችንን እናድናለን ብለው ባደባባይ ሳያፍሩ የሚናገሩ ሰዎችን የምናይበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡በርግጥ ኢትዮጵያ ማእበል ከበረታባት እንደ ታይታኒክ ትሰጥም ይሆናል፡፡ግን መርከቢቱ ስትሰጥም የመርከቢቱ ሳሎን ብቻውን አይንሳፈፍም፡፡የመርከቢቱ ጓዳ ብቻውን አይተርፍም፡፡ኢትዮጵያ ስትከስም ብሄሮች ተነጥለው ይለመልማሉ ማለት ተፈጥሮ አመሏን እንደ ግትቻ የትም ጥላለች ማለት ነው፡፡
source... http://freefreedomalon.wordpress.com/2013/07/29/0410/