ኢትዮጵያ በግብፅ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዷል ብላ ባታምንም የህብረቱን ቻርተር ታከብራለች - ጠ/ሚ ሀይለማርያም
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 16 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ
በግብፅ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ሰፍኖ የሕዝቡ ሠላማዊ ኑሮ እንዲቀጥል ድጋፏን እንደምታደርግ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር
ኃይለማርያም ደሳለኝ ከግብፅ የሽግግር መንግሥት የተላከላቸውን መልዕክት ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ልዩ መልክተኛ
አምባሳደር ሞና ኦመር እጅ ተቀብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር
ኃይለማርያም በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በግብጽ የተካሄደው የመንግሥት ለውጥ ኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግሥት ነው የሚል እምነት ባይኖራትም
የአፍሪካ ኅብረት ቻርተርን ታከብራለች።
ያም ሆኖ ከሥልጣን
የተወገዱት የፕሬዝዳንት ሙርሲ ደጋፊዎች ቁጥርም ቀላል ግምት የማይሰጠው በመሆኑ የሽግግሩ መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች ችግሩን
በሠለማዊ መንገድ መፍታት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የግብፅ
ሠላምና መረጋጋትን አጥብቃ ከመሻቷ የተነሳ ወደ አገሪቱ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኗን አመልክተዋል።
አምባሳደር ሞና ኦመር
በበኩላቸው በግብጽ የተካሄደው የመንግሥት ለውጥ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ሳይሆን የአብዛኛውን ሕዝብ ፍላጎትና ጥያቄ መሰረት
በማድረግ የተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።
በቅርቡ የአፍሪካ
ኅብረት የሠላምና የፀጥታው ምክር ቤት ግብፅን ከኅብረቱ አባልነት እንድትታገድ ማድረጉ ምክር ቤቱ በአገሪቷ የተካሄደውን ለውጥ በውል
ካለመገንዘብ የመነጨ እንደሆነም ጠቅሰዋ።
እናም አምባሳደሯ
ጉዳዩን የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ለሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዝርዝር ለማብራራት አዲስ አበባ መምጣታቸውን
እንደገለፁ የዘገበው ኢዜአ ነው ።
No comments:
Post a Comment