Tuesday, July 23, 2013

የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ቅሌትና መዘዙ


የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ቅሌትና መዘዙ

ሥለ NSA የተለያዩ መፅሐፍት ያሳተመዉ ጋዜጠኛ ጀምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ፥ እርስዎ ከዱባይ ወይ ከለንደን አዲስ አበባ ላለች ፍቅረኛዎ የፍቅር ኢሜል ይመይላሉ እንበል።ስኖዳን እና ብጤዎቻቸዉ ሐዋይ፥ ሜሪላንድ ወይም የፈለጉበት ቦታ ሆነዉ-ከፍቅረኛዎ እኩል ምናልባትም ቀድመዉ ኢሜልዎን ያነባሉ።ስልኩም---
የትንሹ ሠላይ ትልቅ ድፍረት፥ የትልቂቱ ሐገር ታላቅ ቅሌት።የልዕለ ሐያሊቱ ሐገር የሥለላ ቅሌት መነሻ፥አስተጋብኦቱ ማጣቀሻ፥ ያስከተለዉ ዉዝግብ መድረሻችን ነዉ-ላፍታ አብራችሁን ቆዩ።
የመረጃ ሰዎች ካንዱ መንግሥት ወደ ሌላዉ መኮብለል፥ ወይም መንግሥታት የተቀናቃኛቸዉን መንግሥት ሰላይ ማስኮብለል እንግዳ አይደለም።በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት በሞስኮ ዋሽግተኖች የሚተወን የዉሎ አምሽቶ ድራማ አይነት ነበር።

በፕሪስተን ዩኒቨርስቲ የዓለም አቀፍ ሕግ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፋልክ አንዱን ያስታዉሳሉ።ሉዊስ ፖሳዳ ካሪለስ ዛሬ የሰማንያ አምስት አመት አዛዉንት ናቸዉ።የካሊፎርኒያ ነዋሪ፥ ኩባዊ፥ ቬኑዙዋላዊ አሜሪካዊ ናቸዉ።ድሮ-በተማሪነቱ በእድሜ አንድ ዓመት የሚበልጠዉ የፊደል ካስትሮ ወዳጅ ብጤ ነበር።ኋላ ጠላት ሆኑ።

በ1963 (ዘመኑ በመሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የአሜሪካዉ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት (CIA በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) የማሸበር፥ የመግደልና የመሻጠር ሙያ አሰለጠነዉ።ከእንግዲሕ አንቱ ናቸዉ።ፖሳዶ ካስትሮን ለመግደልና ለማስገደል በተደጋጋሚ ሞክሩ።በተፈጥሮ ያዳበሩት ድፍረት፥ ጥላጫ፥ ከአሜሪካኖች የቀሰሙት ዕዉቀት፥ መሳሪያ ገንዘብም ብዙ አልፈየዳቸዉም።ሰዉዬዉ አልተገኙም።ፖሳዳም ደም-ለማፍሰስ ማድባታቸዉን አልተዉም።

A protester wearing a Guy Fawkes mask holds a paper-made mock TV camera during a demonstration against the National Security Agency (NSA) and in support of U.S. whistleblower Edward Snowden, outside the Dagger Complex, which is used by the U.S. Army intelligence services, in Griesheim, 20 km (12.4 miles) south of Frankfurt, July 20, 2013. REUTERS/ Kai Pfaffenbach (GERMANY - Tags: POLITICS CIVIL UNREST CRIME LAW TPX IMAGES OF THE DAY) የሥለላዉን ድርጅት በመቃወም


1976 ሰላዩ ለካስትሮና ለተከታዮቻቸዉ ያነጣጠሩትን የጥፋት ለበቅ ተራ-ወገኖቻቸዉ ላይ ሊያወርዱት ወሰኑ።የበረራ ቁጥር 455 ፥ የኩባ የመንገደኞች አዉሮፕላን ወደ ኪንግሰቶን-ጃማይካ ሊበር ከባርቤዶስ አዉሮፕላን ማረፊያ ተነሳ።ብዙም አልቆየ።ጋየ።ሰባ-ሁለት መንገደኞቹም ከሰሉ።

የየዋሕ መንገደኞች ቤተሰቦች፥ ዘመድ፥ ወዳጆች፥ ሲላቀሱ፥የብዙዉ ዓለም መንግሥታት ሽብሩን ሲያወግዙ የሲ አይ ኤዉ ጀግና ተደሰቱ።ዩናይትድ ስቴትስም አሸባሪ ጀግናዋን እጇን ዘርግታ ተቀበለችዉ።ዘንድሮ በሰላሳ ሰባት ዓመቱ የሰላሳ ዓመቱ አሜሪካዊ ሰላይ ኤድዋርድ ስኖደን ከሐዋይ በሆንግ ኮንግ አድርጎ ሞስኮ ገባ።

ስኖደን አንድም ሰዉ አልገደለም።ለመግደልም አልሞከረም።ገንዘብ አልዘረፈም።ለመዝረፍም አልሞከረም።የታላቂቱን ሐገር ትልቅ ደባና ሚስጥር ግን በርግጥ አጋለጠ።እና ፖሳዳና ብጤዎችን አሸባሪዎች የምትንከባከበዉ፥ትልቅ ሐገር ትንሹን የቀድሞ ሰላይዋን ለመያዝ በትላልቅ ጥፍር ጥርሶቻ መንግሥታትን ትቧጭር፥ ትናከስ ያዘች።

«እኔ አሁንም የምጠብቀዉ ሩሲያም ሆነች፥ ሌሎች ለሚስተር ስኖደን፥ ጥገኝነት ለመስጠት እንፈልጋለን የሚሉ ሐገራት የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አካል መሆናቸዉን ይገነዘባሉ፥እና ለዓለም አቀፉ ሕግ መገዛት አለባቸዉ ብዬ ነዉ።»

ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ፥ ዓለም አቀፍ ሕግ ትርጉም ብያኔ እንዴትነት ሁሌም እንዳወዛገበ፥ እንዳነጋገረ በጉልበተኞች ልክ የሚሰፋ-ወይም የሚጠብ ነዉ።የድፍን ዓለም ማሕበራት፥ የዜጎች፥ የፖለቲከኞች፥ የሙሕሯን፥ የጋዜጠኞችን፥ የደራሲዎችን፥ የጦር መኮንኖች ወዘተ የስልክ ንግግር፥ የኢሜይል ልዉዉጥ፥ ባንዲት ሐገር እንዲቀዳ፥ እንዲከማች፥ ለተፈለገ ወገን እንዲሰጥ የፈቀደ ዓለም አቀፍ ሕግ፥ ዓለም አቀፍ ማሕበረሰብስ ካለም ዓለም አቀፉ ጉልበት፥ ሐብት፥ ወይም ለሕግ አለመገዛት መሆን አለበት።

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍፃሜ በሕዋላ የዓለምን የልዕለ-ሐይልነት ጉልበት ጠቅላላ የያዘችዉ ዩናይትድ ስቴትስ እንደ ጦር ጉልበቷ፥ እንደ ሐብቷ ሁሉ በስለላዉም የሚስተካከላት የለም።NSA በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ ብሔራዊ የፀጥታ ድርጅት ሠላሳ አምስት ሺሕ ቋሚ ሠራተኞች አሉት።


Bildnummer: 59982415 Datum: 03.07.2013 Copyright: imago/Christian Ohde
Kopfhörer mit USA-Fahne auf einem Tisch, Symbolfoto Abhörskandal Prism Symbolfoto Abhörskandal USA xcb x0x 2013 quer Abhörprogramm Abhörprogramme Computerprogramm Computerprogramme Datensammlung Kontrolle NSA Prism Spionage Spionageprogramm Spionageprogramme Spähprogramm Spähprogramme Symbolbild Symbolbilder Symbolfoto Symbolfotos ausspähen kontrollieren online spionieren von Späh-Skandal Spähaktion Spähaktionen Abhörskandal Abhörskandale Abhör-Skandal abhören Kopfhörer mithören Zahlencode binär binärer Binärcode USA-Fahne US-Fahne Fahne Flagge 
59982415 Date 03 07 2013 Copyright Imago Christian Ohde Headphones with USA Flag on a Table Symbolic image Wiretapping scandal Prism Symbolic image Wiretapping scandal USA x0x 2013 horizontal Computer program Computer programs Data collection Control NSA Prism Espionage Symbol image Symbol Pictures Symbolic image Icon photos Spying control Online Spy from Scandal Wiretapping scandal Interception Scandal Interception Headphones Listening Numeric code binary binary Binary code USA Flag U.S. Flag Flag Flag የሥልክ ጠለፋ ምሳሌ
የስኖደን ብጤ የኮንትራት ሠራተኞች ቁጥር ከቋሚዎቹ አይተናነስም።ሥለ NSA የተለያዩ መፅሐፍት ያሳተመዉ ጋዜጠኛ ጀምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ፥ እርስዎ ከዱባይ ወይ ከለንደን አዲስ አበባ ላለች ፍቅረኛዎ የፍቅር ኢሜል ይመይላሉ እንበል።ስኖዳን እና ብጤዎቻቸዉ ሐዋይ፥ ሜሪላንድ ወይም የፈለጉበት ቦታ ሆነዉ-ከፍቅረኛዎ እኩል ምናልባትም ቀድመዉ ኢሜልዎን ያነባሉ።
«በኢንተርነት የሚደረገዉ ከዘጠና ዘጠኝ በመቶ በላይ ግንኙነት አንድም ወደ አሜሪካ ይገባል አለያም በአሜሪካ በኩል ያልፋል።ሥለዚሕ ዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ አቅም አላት።መቼም እንዲሕ አይነቱን አቅም ኔዘርላንድስ ወይም ሌላ የአዉሮጳ ሐገር ይኖረዋል ብለሕ አትጠብቅም።»

ሥልክ የደዉሉት ከጂዳ፥ የተደወለልዎት ካፓርስ ነዉ እንበል።ወዴትም ይደዉሉ፥ ከየትም ይደወልዎት ከሰማንያ ከመቶ የሚበልጠዉ የሥልክ ንግግር በአሜሪካ በኩል ነዉ የሚያልፈዉ።

«በስልክ ንግግርም ቢሆን ከሰማንያ በመቶ የሚበልጠዉ በአሜሪካ በኩል ነዉ የሚተላለፈዉ።ሥለዚሕ ዩናይትድ ስቴትስ የዓለምን ግንኙነት ለመምጠጥ ከፍተኛ ዕድል አላት።»

አሜሪካን ሳይነካ የሚያልፈዉን የሥልክ ጥሪ እነ ስኖደን ከያለበት ጠላልፈዉ፥ ለቃቅመዉ ከዚያ የመረጃ ትልቅ ጎተራቸዉ ያክቱታል።ከዚያ እያስተረጎሙ፥ እያስተነተኑ ለአለቆቃቸዉ ያቀርባሉ። እርስዎ ተራ ሰዉ ነዎት።በNSA አይን ግን የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክልም ከርስዎ መለየታቸዉን እራሳቸዉ እንዳሉት እርግጠኛ አይደሉም።

Bildbeschreibungen: Bei seinem ersten öffentlichen Auftritt traf sich Edward Snowden am Freitag, den 12 Juli 2013 auf dem Moskauer Flughafen Scheremetjewo mit Menschenrechtlern und Anwälten. Der US-Amerikaner möchte in Russland bleiben, solange er nicht nach Südamerika ausreisen kann.
Menschenrechtsbeauftragter der RF Wladimir Lukin inmitten der Journalisten.
Foto: Jegor Winogradow / DW ስኖደን ከመብት ተሟጋቾች ጋር


«እኔ እራሴ የሥልክ ንግግሬ የት እንደተቀዳ አላዉቅም።ባዉቅ ኖሩ ለፓርላማዉ ኮሚቴ አናገር ነገር።»

ለዩናይትድ ስቴትስ ኢራን፥ ሶሪያ፥ ቬኑዙዌላ፥ ቦልቪያ፥ ኢኳዶር የቅርብ ክትትል የማይለያቸዉ «ጠላቶች» ናቸዉ።ብራዚል «ወዳጅ» ናት።ከካራካስ ባለሥልጣናት፥ እኩል የብራዚሊያ ሹማምንት፥ ከቦሊቢያ ዜጎች እኩል የብራዚሎች ንግግር፥ ፅሁፍ፥ እየተጠለፈ፥ እንቅስቃሴያቸዉ እየተቀዳ ይጠራቀማል።

ለዋሽግተኖች፥ ሞስኮዎች ወይም ቤጂንጎች የቀዝቃዛዉ ጦርነት ዘመን ጠላት ናቸዉ።አሁን ደግሞ በተለይ ቻይና የምጣኔ ሐብት ተፎካካሪ፥ የዓለም አቀፍ መርሕ ተፃፃራሪ ናት።የጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ መስተዳድር የባግዳድን ቤተ-መንግሥት ያስረከባቸዉ የኢራቅ የሺዓ ፖለቲከኞች አፍ-አይ’ናቸዉ ከአዋሽግተኖች፥ ልብ ቀልባቸዉ ደግሞ ከቴሕራኖች ጋር ነዉ ይባላል።ለክፉዉም ለደጉም በቅጡ መሰለል አለባቸዉ።

ጀርመን ባንፃሩ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት አባል፥የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ተሻራኪ ጥብቅ ወዳጅ ናት።ግን ስኖደን ያጋለጠዉ መረጃ እንዳመለከተዉ ጀርመኖች ከቻይኖች እና ከኢራቆች እኩል ይመረጃሉ።ለጀርመኖች በርግጥ አስደንጋጭ ነዉ።ጋዜጠኛና የስለላ መፅሐፍት ደራሲዉ ጄምስ ባምፎርድ እንደሚለዉ አሜሪካኖች ጀርመን ላይ የጨከኑት ጀርመኖች የአሜሪካ «ጠላት» ሥለሆኑ አይደለም ባይ ነዉ።

«ጀርመን በብዙ ምክንያት የአሜሪካንን ትኩረት ትስባለች።አንደኛዉ ምጣኔ ሐብታዊ ነዉ።ጀርመን የአዉሮጳ የምጣኔ ሐብት ዋና ማዕከል ናት።ሁለተኛዉ የመስከረም አንዱ የአሸባሪዎች ጥቃት የተጀመረዉ ከጀርመን ነዉ።ሰወስተኛዉ ጀርመን አዉሮጳ ዉስጥ ምጣኔ ሐብታዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ተፅዕኖም ታሳርፋለች።ሥለዚሕ የጀርመንን ንግግር ማድመጥ ማለት የኔዘርላንድስ፥ የስጳኝ፥ የግሪክ የሌሎችንም የአዉሮጳ ሐገራት እንቅስቃሴን በዚሕ በሚስጥር መገናኛ ዘዴ አማካይነት ማወቅ ማለት ነዉ።»

ጀርመኖችን በመሠለሉ ሒደት የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣናት በተለይም የሐገሪቱ ፌደራላዊ የሥለላ ድርጅት (ቡንደስ ናኽሪሽተን ዲኒስት) መሪዎች ከአሜሪካኖች ጋር ተባብረዋል የሚለዉ ዘገባ የጀርመን ፖለቲከኞችን እያወዛገበ ነዉ።የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የሥለላዉ ተቋም ባለሥልጣናት ከሥልጣን መዉረድ አለባቸዉ እስከማለት ደርሰዋልም።

የአገር አስተዳደር ሚንስትር ሐንስ ፔተር ፍሬድሪሽ አሜሪካኖች ጀርመንን ሥለመሠለላቸዉ ማብራሪያ እንዲሰጧቸዉ ዋሽግተን ድረስ ሔደዉ ጠይቀዉ ነበር።የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ጥያቄና ጥርጣሬ የሚያስወግድ መልስ ግን አልሰጡም።ወይም አላገኙም።መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልም የአሜሪካ ሠላዮች የጀርመንን ሕግ ሥለ መጣስ-አለመጣሳቸዉ የማዉቀዉ ነገር የለም ባይ ናቸዉ።


Barack Obama telefoniert im Oval Office
picture alliance / Photoshot ኦባማ
«የጀርመንን ሕግ አለማክበራቸዉን የሚያረጋግጥ መረጃ የለኝም።ባለሙያዎቻችን ይሕን ጉዳይ እንዲያጣሩ ለነሱ እንተወዋለን።ባስቸኳይ መታወቅ አለበት።በዚሕ ሒደት የአገር አስተዳደር ሚንስትሩና የምክር ቤቱ ልዩ ኮሚቴ የሚያጠናክሩትን ዘገባ ካየን በኋላ መወሰድ ሥላለበት ጉዳይ እናጤናለን።ለወደፊቱ ግን በምንም መንገድ የጀርመን ሕግ መጠበቅ አለበት።»
ጀርመኖችን ከጀርመኖች የሚያጨቃጭቀዉ የሥለላ ቅሌት አሜሪካኖችን ከሩሲያዎች፥ ጋር እያወዛገበ ነዉ።የፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ቃል አቀባይ ጄ ካርኒ ልክ እንደ ኦባማ ሁሉ ሩሲያ የቀድሞዉን አሜሪካዊ ሠላይ ለአሜሪካ አሳልፋ መስጠት አለባት ይላሉ።

«ከቦስተኑ ማራቶን የቦምብ ጥቃት በኋላ ከሩሲያ ጋር ያለንን የተጠናከረ ትብብር ከግምት በማስገባት እና በሩሲያ ጠያቂነት ከፍተኛ ወንጀል የፈፀሙ ሰዎችን አሳልፈን መስጠታችንን ጨምሮ፥ ሕግን በማስከበሩ መስክ ለረጅም ጊዜ ካለን ትብብር አኳያ የሩሲያ መንግሥት ሚስተር ስኖደንን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ያባርራሉ ብለን እንጠብቃለን።»

የቦሊቪያዉ ፕሬዝዳት ኢቮ ሞራሌስ ሞስኮ የገቡት ሞስኮ-ዋሽግተኖች ጠጣር ቃላት ሲወራወሩ ነበር።ድፍን ዓለምን የሚሰልለዉ የልዕለ-ሐያሊቱ ሐገር ግዙፍ የሠላላ ባለሙያዎች ፕሬዝዳት ሞራሌስ ታዳኙን ሠላይ ኤድዋርድ ስኖደንን ባዉሮፕላናቸዉ ይዘዉ ወደ ሐገራቸዉ ሊመለሱ ነዉ አሉ።የዩናይትድ ስቴትስን ቁጣና ግልምጫ የሚፈሩት የፈረንሳይ፥ የስጳኝ፥ የፖርቱጋልና የኢጣሊያ መንግሥታት የሞራሌስ አዉሮፕላን በአየር ክልላቸዉ እንዳይበር አገዱ።

የኦስትሪያ ባለሥልጣናት አዉሮፕላኑን አሳርፈዉ ፈተሹ።ሶኖደን አልነበረም።የደቡብ አሜሪካ መንግሥታት እንደ ብዙዉ ዓለም መንግሥታት በአሜሪካ በመሠለላቸዉ ኦባማ «ዓለም አቀፍ» በሚሉት ሕግ መሠረት እንክሰስ አላሉም። ቢሉም የሚሰማቸዉ የለም። ከፕሬዝዳንታቸዉ አንዱ በሐሰት መረጃ ለአዉሮፕላን አደጋ መጋለጣቸዉን ግን አልታገሱትም።አወገዙት።

ቁጣ ዉግዘቱ ግን ከአፍታ የመገናኛ ዘዴዎች ዜናነት አላለፈም።የፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን አፀፋ እንደ ጀርመኖች-በአገም ጠቀም፥ እንደደካማዎቹ የደቡብ አሜሪካ ሐገራት ባፍታ ቁጣ የሚያበቃ አይነት አይደለም።

«እኛ እንደሌሎች መንግሥታት አናጎበድድም።ሩሲያ የራስዋ ነፃ የዉጪ መርሕ አላት።ይሕ መርሐም በዚሁ ይቀጥላል።ወዳጆቻችን ይሕን አጢነዉ አደብ ቢገዙ ጥሩ ነዉ።ከሥለላ ዉዝግብ ይልቅ የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነት በጣም አስፈላጊ ነዉ።»

Russian Prime Minister Vladimir Putin visits the Far Eastern State University in Vladivostok, about 9,300 kilometers (some 5,750 miles) east of Moscow, on Monday, Sept. 1, 2008. A portrait of Czar Nicholas II is at left. (AP Photo/ RIA Novosti, Alexei Druzhinin, Pool ) ፑቲን


አሜሪካኖች ግን አላረፉም።በመጪዉ ነሐሴ ማብቂያ ሩሲያ በምታስተናግደዉ የቡድን ሃያ አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ፕሬዝዳት ኦባማ እንዳይካፈሉ ወግ አጥባቂዎቹ የአሜሪካ ፖለቲከኞች እየጎተጎቱ ነዉ።ቬኑዙዌላ፥ የኢኳዶር እና የቦሊቪያ መንግሥታት ሞስኮ አዉሮፕላን ማረፊያ «ለታገተዉ» የቀድሞ የአሜሪካ ሠላይ ጥገኝነት ለመስጠት በመፍቀዳቸዉ ከዋሽግተን የሚሰነዝርባቸዉ የቅጣት ዛቻ፥ ማስፈራሪያም እንደቀጠለ ነዉ።እኛ ለዛሬዉ ከዚሕ በላይ መቀጠል አንችልም።ነጋሽ መሐመድ ቸር ያሰማን።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

source....http://www.dw.de

No comments:

Post a Comment