Tuesday, July 23, 2013

ሻለቃ ኅይሌ ገብረስላሴ ከሀገር አቋራጭ(ማራቶን) ወደ መተካካት የዱላ ቅብብል የብሔር ማሟያ ሆኖ ሊሾም ነው!።

ሻለቃ ኅይሌ ገብረስላሴ ከሀገር አቋራጭ(ማራቶን) ወደ መተካካት የዱላ ቅብብል የብሔር ማሟያ ሆኖ ሊሾም ነው!።

*ኢህአዴግን(ራዕይና ሌጋሲውን)የሚያውቀው የለም።ኢትዮጵያም አውሮፕላን እንዳላት ደሪምላነርም ገዝተን ለምነን እንደምንበላ ‘ደሮነርም’ የሚሠራ አትራፊ የመከላከያ ኅይል እንዳለን የሚመሠክረውና የሚያውቀው ያው የፓርላማ አባል፣አርቲስቱ፣ የኤምባሲ ካድሬና ቤተሰቦች ተሰብስበው ቡና በማፍላትና በመጨፈር ነው። ስለዚህ ፖለቲካን ከእስፖርት ጋር እናደባልቀው…በአነስተኛና ጥቃቅን የታቀፉ ሴቶችን፣ አርቲሰቶችን፣ ሙዘቀኛና ታዳጊ የብሔር ካድሬዎችን የጨበጠው ኢህዴግ፣ የእስፖርት ቤተሰቦችን ሊያስተዛዝል ነው።፣ ውሃና መብራት፣ የሌለው፣ ረዕይና ወኔ አልባ ትውልድ! “ወንድማችን በእውቀቱ ሥዩም ልጁ ከሱዳን የላከለትን ደብዳቤ ለሕዝብ እንዳነበበው “ሱዳን መብራት ጠፋ የሚባለው ሳሎን ጠፍቶ መኝታቤት ሲበራ ነው” ኢትዮጵያ መብራት ተቋረጠ የሚባለው ህዝብ በፈረቃ ለ፫ አብርቶ ጅቡቲ ሌሊቱን ስትጠቀም ነው። መብራት ጠፋ የሚባለው ግን የተቦካው ሊጥ ተበላሽቶ ሲደፋ ብቻ ነው። ቲማቲም ፲፭ብር ኪሎውን የሚገዛ የወያኔ ትውልድ ፣፷ሺህ ተመልካች የሚይዝ፣ አፉን ከፍቶ፣ ቂጡን የሚያደነዝዝበት፣ እንዳያነብ፣ እንዳይፅፍ፣ እንዳይጠይቅ፣ የሚጀዝብበትና የሚሞላፈጥበት፣ እስታዲየም ሊገነባለት ነው። ታዲያ ኅይሌ ፕሬዘዳንት ካልሆነ እንዲህ ያለ የውድቀት ዕድገት ይገኛልን? የፖለቲካውን ምሕዳር መስፋት በእስታዲየም ስፋት ቀሸበው ይሉሃል ይህ ነው።ጭንቅላታቸው ጠቧልን?
**(አብዮታዊ ዴሞክራሲያውዊና ኦሎምፒካዊት ኢትዮጵያ !) ሆነችልህ በለው!*
ኅይሌ ገብረስላሴ ስንት ታላላቅ ሰዎችን ጨብጧል ሲሸነፍ የሚስቅ ተብሏል፡ በሀገር ውስጥም በሠራው አድርባይነትም ተጨብጧል!። ምንም ቢሆን ከ፻ ዓለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በምን ያንሳል? ዶ/ር ነው። ሻለቃ ነው። ቢያንስ ደብዳቤ ተቀብሎ ደብዳቤ ላይ ፈርሞ፣ ተነስቶ ጨብጦ ተቀምጦ ስቆ በፈገግታው ሀገራችንን ማንነት ከፍ ያደርግልናል።ኢትዮጵያ አውሮፕላን አላትን? ሲሉ ለመሆኑ ሀይሌገብረስላሴ ለሩጫ ይህንን ሁሉ ሀገር የሄደው እየሮጠ ነው ወይንስ በበቅሎ ነበር ብለው ነው? እኛስ የተጠቀለሉ መሪ አፍሪካን የወከሉት በባዶ እግራቸው ሄደው ነበር? ወይ ንቀት ብታምኑም ባታምኑም ኢህአዴግ ተደፍሯል! ተንቋል!ተዋርዷል!
በዓለም ኢህአዴግ ለመኖሩና ሥልጣን ለሠፊው ሆዳም ህዝብ እንደሚሰጥ ከመድብለ ፓርቲ የተዳበለ ወንበር በ፪ጠ/ሚኒ በ፩ ምጠ/ሚ በ፪ም/ጠ ሚኒ መሳይ (በደቦ)የምትመራ ፓርቲ ለፈገግታ እንግደህ ኅይሌን ትጨምርና ይህ ሰው ይገደል ሲሉት ይፈርም ፣ ይህ ሰው ምህረት ያግኝና ይፈታ ሲሉት ሮጦ ይጠፋል። ግን በአበባ ተከቦ በተቀመጠ ቁጥር መናፈሻው(እሪዞርትቱ) ያለ መስሎት በቁምጣ እንዳይቀመጥና እንግዳ እንዳይመጣ! እንዳያሳጠን በለው! ፻ አለቃም እንዲሁ የሹመት ደብዳቤ ለአመጣው ሁሉ “እስቲ ትኩስ የማር ጠጅ ይላሉ አሉ።”
***ምን አባቱ የተናቀ ሠፈር በዲያስፖራ ይከበባል አሉ! መቼም በስታዲየም መሮጥና በፖለቲካ መሮጥ አንድ ነው። ቢያንስ ፓርላማ ገብቶ ሥቆ ማሳቅ ያቅተዋል? ። በእንግሊዘኛ ከአቶ መለስ አያንስም! ለነገሩ ልጆቹም አማርኛ አይችሉም በእንግሊዘኛ ይረዱታል መውለድ ጉዱ!? በፈገግታ ከአቶ ኅይለመልስ አይተናነስም!። ሰውዬው በፈገግታ ነው የተመረቁት ? በሚያናድድ የሀገር ጉዳይ “ኢሳያስ ኣፈዋርቄ አሸባሪ! የቀጠናው አተራማሽ! ወንበዴ! ብለው ሱደነፉ ከርመው እቤቱ ሄጄ ጸሎት አድርጌ እግሩ ላይ ወድቄም ቢሆን እደራደራለሁ አሉ። እሪ በይ ወያኔ አለ የእኛ ሀገረ ሰብ …
ኅይሌ ገብረስላሴ በገንዘብ ከሼክ አላሙዲን አይተናነስም! እንዲያውም በአንድ ደምፅ “እኛ ኢንቨስተሮች ሥራ ሥለምንከፍት ስንሳሳትም ዝም በሉን ብታዩንም እንዳላያችሁ ሁኑ እንስራባችሁ አደለም ያሉት !!”በአርግጥ በኢንቨስትመንት ሥም ቦታ አጥሮ ያለ ግብር መቆየትስ ባህሪያቸው አደለምን! ሌላው ከሩጫ በኋላ ባንዲራ ይዞ ይሮጣል ፕሬዘዳንቱም ሲሆኑ ሁልጊዜ በመኪና ላይ ያውለበልባል ለነገሩ ትርጉሙን ቢያውቁት ባትሉኝ እንጂ!..
እንግዲያውስ መለስ ከቻይና(የቡድን) ቤተሰባዊ ብሔር ተኮር አመራር ፣ ኅይለማርያም ከህንድ(የኀብርት)(የደቦ)ከፊት ያላችሁ ሁሉ መሪ ናችሁ አመራር ፣ ኅያሌ ገ/ስላሴ ከኦሎምፒክ( በይቻላል)(በይሆናል) እየመከረ ወይ ከመካከለኛ ወይ ከመጨረሻ አጥር ግቢ ውጭ እንሠለፋለን ! እግዝኦ…የቡድን የኅብረትና ኦሎምፒክ አመራር ያለህ…ኅይለመንግስቱመለሰማርያምገብረስላሴ…..በለው!!በቸር ይግጠመን ከሀገረ ከናዳ
በለው ! aferawm@sympatico.ca     www.freedom4ethiopian.wordpress.com

No comments:

Post a Comment