Sunday, July 21, 2013

መድረክ በመቀሌ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ

መድረክ በመቀሌ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ


መድረክ በመቀሌ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በስኬት እንደተጠናቀቀ የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የትግራይ ዞን ጸሀፊ አቶ ክብሮም ብርሃነ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2005 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ያካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች የተገኙበት ነበር፡፡ በአብዛኛው ወጣት የሆኑ የመቀሌ ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ስብሰባ የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር በሆኑት በአቶ ጥላሁን እንደሻው፣ በአቶ ገብሩ አስራትና በአቶ ብርሀኑ በርኸ የተመራ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ስብሰባውን ስኬታማ አድርገውታል፡፡
በተሰብሳቢዎቹ በትግራይ ክልል የሚታዩትን የመልካም አስተዳደር፣የሙስናና የግብር አሰባሰብ ችግሮችን በመንቀስ በመንግስት ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ ማንፀባረቃቸውንም አቶ ክብሮም አስረድተዋል፡፡ “መድረክ ላይ የነበሩት ተናጋሪዎች ሞቅ ባለ ጭብጨባ ታግዘው ተናግረዋል” ያሉት አቶ ክብሮም ስብሰባውን ለማደናቀፍ በአዳራሹ ውስጥና ውጪ በተደራጀ ሁኔታ ተሰብስበው የነበሩት ከየቀበሌው የተውጣጡ ካድሬዎች የተሰብሳቢው ሁኔታ አስደንድጧቸው እንደተበተኑም ተናግረዋል፡፡ በትላንትናው እለት የመኪና ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩ ሁለት የአረና ትግራይና አንድ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች መቀሌ ውስጥ ከነመኪናቸው በህገወጥ መንገድ ታስረው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
posted by Aseged Tamene

source... freedom4ethiopian

No comments:

Post a Comment