Monday, July 29, 2013

ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማት የወገኖቻቸውን ሬሳ ሸጡ !

ሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማት የወገኖቻቸውን ሬሳ ሸጡ !

ሰሞኑንን ሪያድ ሳውዲ አረቢያ በተካሄደው ስብሰባ ኢትዮጵያውያኑ ዲፕሎማት የወገኖቻቸውን አስከሬን ሸጠዋል በሚል የቀረበባቸው ክስ የአያሌ ኢትዮጵያውያን የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ መሰነበቱን ምንጮች ከመዲናይቱ ሪያድ ገልጸዋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ቀኑን በጾም አሳልፈው በሃይማኖታቸው ህግጋት መሰረት ጸሎታቸውን አድርሰው ከተመለሱ በሃላ የተጠቀሰው ስብሰባ ማታ እንዲካሄድ ቀደም ብሎ በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ሃምሌ በ18/07/2013 ምሽት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ አዳራሹ ተሞልቷል ።
በህዝብ ዘንድ አድናቆት እንዳተረፉ በሚነግረላቸው ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት አቶ መስፍን ድባቡ እና መሰሎቻቸው መሪነት በኢትዮጵያ ሰአት አቋጣጠር ከምሽቱ 03 00 በተጀመረ በዚህ ስብሰባ አያሌ ተበዳዮች ተራ በተራ እየተነሱ በዲፕሎማቱ ደረሰብን ያሉትን ዘግናኝ እና አሳዛኝ ታሪካቸውን እየዘረዘሩ ብሶታቸውን ያሰሙ ጀመር ። በተለይ በኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቱ በደል ደርሷብናል በልው ከገለጹ የስብሰባው ተሳታፊ አንዱ የአካባቢ ነዋሪ መሆናቸውን ጠቅሰው የወንድማቸውን በድገተኛ አደጋ ህልፍተ ህይወት መረዳታቸውን ተከትሎ እንባ እየተናነቃቸው ሲገልጹ ሞቹ ወንድሜ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌለው ብቻ የቀበር ስረአቱን ለማስፈጸም በኤንባሲ በኩል ትብብር እንዲደረግልኝ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ባቀርቡም ሰሚ በማጣቴ የወንድሜን ቀብር በወግ ሳላስፈጽም በሃዘን እይተንገበገብኩ ከ1 ወር በላይ ሃዘኑ ውስጤን እየራደው ተሰቃይቻለሁ ብለዋል። ከዚህ በማስከተል በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ አባት የውጩን አለም ኑሮ ለማሸነፍ አጋር ይሆነኛል ብዬ ህጋዊ በሆነ መንገድ ያስመጡት ልጃቸው የሚሰራበት ቦታ ባልታወቀ ሰው በጩቤ ተወግቶ ህይወቱ በማለፉ የልጃቸው ገዳይ እንዲጣራላቸው በጉዳዩ የኢትዮጵያ ኤንባሲ መግባት ስለሚገባው ኤምባሲው ከጎናቸው እንዲቆሙ ቢማጸኑም ዲፕሎማቱ «እኛ የማንም ወሮበላ ጠበቃ አይደለንም» የሚል አሳዛኝ፡መልስ እንደሰጧቸው እንባ እየተናነቃቸው መግለጻቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። http://freedom4ethiopian.wordpress.com
እኚህ አስተያየት ሰጪ በማከል ከሁለት ያጣሁ እንዳልሆን የልጄን በድን ከሆስፒታል አውጥቼ በክብር ለመቅበር ለኤምባሲው ዲፕሎማቶች መክፈል የሚገባኝን ደረሰኝ የሌለው ገንዘብ ከፍዬ ከብዙ ውጣውረድ በሃላ ተሳክቶልኝ፡ የልጄ አሞሞት አንቆቅልሽ እንደሆነ ከትምህረት ገበታው እና ከናቱ ጉያ ነጥዬ ያመጣሁትን የአብራኬን ክፋይ ሳላስታምመው እና ገዳዩን ሳልውቅ በሰው ሃገር ለብቻዬን መቅበሬ እየተሰማኝ ሃዘኑ አልወጣልህ ብሎኝ ለአይምሮ ጭንቀት ዳርጎኛል ሲሉ ተናግረዋል። በጣም የሚያሳዝነው አንድ አባት የደረሰባቸውን በደል ሲገልጹ ከሁሉ የከፋው የእህቴን አስከሬን ለመቅበር በኢትዮጵያ ውጭ፡ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት የኤንባሲው ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ከድር ሁሴን እስከ 7 ሺህ ሪያል ጉቦ መጠየቄ እስካሁንም የሆድ ወስጥ፡እሳት ሆኖብኛል ብለው በዲፕሎማቱ የተፈጸመባቸውን በደል ሳግ እየተናነቃቸው ሲገልጹ የመድረኩ መሪ ዲፕሎማት መስፍን ሊያስቋሞቸው ቢሞክሩም ተበዳይ አሳዛኙን ታሪካቸውን በመቀጠል ዲፕሎማቱ በሬሳ ጉቦ የበሉ በቁም ያለነውን ምንሊያድርጉ እንደሚችሉ እስኪ እናተ ገምቱት ብለው አንጀት በሚያላውስ ንግግር ሲገልጹ ፀጥ ብሎ ያዳምጥ የነበረው ህዝብ አዳራሹን በሃዘን ለቅሷ በቅጽበት ናጠው። ዘንድሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሹሞ የላካቸው ዲፕሎማቶች የዜጎቻችንን ከብር ማስጠበቅ የማይችሉ በመሆናቸው ክቡር የሆነውን የወገኖቻችንን ሬሳ በየቆሻሻ ገንዳ በሻንጣ ተጥሎ እና በየመሳጂዱ በር ላይ በሳንጃ ተዘልዝሎ ማየት የተለመደ መሆኑንን ገልጸው ዛሬ ያለ ኢትዮጵያ መንግስት የሁለትዮሽ ስምምነት እንደ አሸን ኢትዮጵያ ውስጥ፡ በተከፈቱ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አማካኝነት ወደ ሳውዲ አረቢያ መጠተው በተለያዩ አጋጣሚ በሚደርስባቸው አደጋ ህይወታቸው የሚቀጠፍ ለጋ ወጣት እህቶቻችን በድን ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሺሜሲ እየተባለ የሚጠራውን ሆስፒታል የሬሳ ክፍል እንደተጨናነቁ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል፤፡
ለሪያድ አካባቢ እንግዳ መሆናቸውን የተናገሩ አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው እንደዚህ አይነት ተዕይንት ያየሁት ከዛሬ 20 አመት በፊት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የኢ.ህ.አ.ፓ ጨፍጫፊዎችን ለህግ ለማቅረብ የማጋለጥ እርምጃ ይወስድ በነብረበት ወቅት መሆኑን አስታውሰው ትላንት ከደርጎች ላይ የልጆቹን አስከሬን ለመግዛት የተገደደውን ትውልድ አሳዛኝ ዘመን አስታውሰው ድርጊቱ ከእንግዲህ እንደማይደገም ቃል ቢገባልንም ዛሬ በእጅ አዙር የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት እራሱ ባስቀመጣቸው በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ዲፕሎማቶቻ የወገን አስከሬን በገንዘብ መለወጡ እንዳስደነገጣቸው በመግለጽ የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ ተወካዮቹን ልኳ በሪያድ የሚኖርውን ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ብሶት አድምጦ መፍትሄ መፈለግ እንደሚገባው አሳስበዋል።
ጉዳዩን የበለጠ ለማጣራት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች በስልክ ለማግኘት ባደረኩት ሙከራ አንድ ስሜ እንዳይጠቀስ ያሉ ዲፕሎማት «በወገኖቻችን አስከሬን የሚነግድ ዲፕሎማት የለም ሊኖርም አይችልም »ካሉ በሃላ በእርግጥ የስከሬን ክፍያን በተመለክተ ወደ ሀገር የሚሄድ አስከሬን የራሱ ወጪ እንዳለው ገልጸው እዚህ ዘመድ የሌላቸውን ወገኖቻችንን ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው በሚቀርብልን መረጃ መስረት የቀብር ስረአት ለማስፈጸም አሊያም ከሃገር የቀብር ውክልና ደብዳዴ ከቤተሰቦቻቸው ለማስመጣት በምናደርገው የደብዳቤ ልውውጥ የወገኖቻችን አስከሬን ለብዙ ቀናት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚጉላላ ሳይሸሽጉ አብራርተዋል። በማያያዝ ቀብር ለማስፈጸም ኤንባሲው ለማህበረስቡ መስጠት ያለበትን ሰነዶች ዲፕሎማቱ ገንዘብ ይቀበሉባቸዋል ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ «ማንኛውም ሰው ጉዳይ ለማስፈጸም የሚከፍለው ክፍያ እንዳለ ሁሉ የተጠቀሱትም ሃዘንተኞች ለስከሬኑ መክፈል የሚገባቸውን ክፍያ መፈጸም አለባቸው ብለዋል»። ዲፕሎማቱም አያይዘው በዚህ ዙሪያ ከህዝብ የቀረበባቸውን ወቀሳ አስመልክተው አስተያየት ሲሰጡ አሁን በነሱ ላይ እየተሰነዘረ ያለው የስምማጥፋት ዘመቻ ከግል ጥላቻ የመነጨ መሆኑንን ገልጸው ….. እኛ ፍጹም አይደለንም እና በምንሰራው ስራ ስህተት አይፈጠርም ማለት አይደለም ካሉ በሃላ ህዝቡ ስህተቶቻችንን ቀርቦ ማስረዳት ሲችል በተወሰኑ ሰዎች ቅስቀሳ ህዝብ እና መንግስትን ለማጋጨት እንዳሴርን ተደርጎ በተለያዩ ድህረ ገጾች ሰሞኑንን እየተጻፈ ያለው የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደ ዜጋ ያስተዛዝባል ብለዋል።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

source.... freedom4ethiopian.wordpress.com

No comments:

Post a Comment