የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች የታሠሩትም ፊርማ ለማሰባሰብ፥ ሠልፍና ስብሰባዉን ለማደራጀት ሲንቀሳቀሱ ነዉ።ከሰኔ
ሃያ-ሁለት እስከ ሰላሳ በነበረዉ አንድ ሳምንት ብቻ ዘጠኝ የፓርቲዉ አባላት በፀጥታ አስከባሪዎች ታስረዋል።አብዛኞቹ
የታሠሩት ሰሜን ጎንደር ነዉ።አንዱ ታስረዉ ተለቀዋል።አስራ-አንደኛዉ ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል።
የኢትዮጵያ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች አሠረዋቸዋል
ያላቸዉ አባላቱና ደጋፊዎቹ እንዲፈቱ በደብዳቤ ጠየቀ።የፓርቲዉ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ለሐገሪቱ ጠቅላይ
ሚንስትር ለአቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ በፃፉት ደብዳቤ እንዳሉት ሠላማዊ ሠልፍ ለማደራጀት እና የአቤቱታ ፊርማ
ለማሰባሰብ በሕጋዊ መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የፓርቲዉ አባላት አላአግባብ ታስረዋል።አብዛኞቹ የታሠሩት ሰሜን
ጎንደር ነዉ።አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት እንዲከበር፥የዜጎች መብት እንዲጠበቅ የፀረ-ሽብር ሕግ
እንዲሠረዝ በመጠየቅ በመጪዉ ዕሁድ ጎንደርና ደሴ ከተሞች የአደባባይ ሠልፍ መጥራቱንም ሊቀመንበሩ አስታዉቀዋል።ነጋሽ
መሐመድ ዶክተር ነጋሶን በስልክ አነጋግሯቸዋል።
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት፥ ያሁኑ የተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት ባጭሩ) ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ።እንቅስቃሴዉ፥ በጥቅሉ የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥት እንዲከበር፥ የሕዝቡ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ መጠየቅ ነዉ።ጥያቄዉ ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት በሰወስት መንገድ ይገለፃል።
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት፥ ያሁኑ የተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት ባጭሩ) ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ።እንቅስቃሴዉ፥ በጥቅሉ የሐገሪቱ ሕገ-መንግሥት እንዲከበር፥ የሕዝቡ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ መጠየቅ ነዉ።ጥያቄዉ ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት በሰወስት መንገድ ይገለፃል።
ዶክተር ነጋሶ ለጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማይርያም ደሳለኝ በፃፉት ደብዳቤ እንደዘረዘሩት የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች የታሠሩትም ፊርማ ለማሰባሰብ፥ ሠልፍና ስብሰባዉን ለማደራጀት ሲንቀሳቀሱ ነዉ።ከሰኔ ሃያ-ሁለት እስከ ሰላሳ በነበረዉ አንድ ሳምንት ብቻ ዘጠኝ የፓርቲዉ አባላት በፀጥታ አስከባሪዎች ታስረዋል።አብዛኞቹ የታሠሩት ሰሜን ጎንደር ነዉ።አንዱ ታስረዉ ተለቀዋል።አስራ-አንደኛዉ ከግድያ ሙከራ አምልጠዋል።
ዶክተር ነጋሶ «ሕገ-ወጥ» ያሉት እስራት እንዲቆም የታሠሩትም እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ባለሥልጣኖቻቸዉን ይዘዙ ነዉ የደብዳቤያቸዉ የመጨረሻ መልዕክት።
«እንቀጥልበታለን»፥ እና «የፈለገዉ ይምጣም» ብለዋል ዶክተር ነጋሶ።ይቀጥላሉ።
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ
source ... http://www.dw.de
No comments:
Post a Comment