Tuesday, July 16, 2013

ከትናንቱ ሰልፍ በኋላ ዛሬ በአ.አ 40 ወንድና 2 ሴት የአንድነት አባላት ታሰሩ (ስም ዝርዝራቸውን ይዘናል)

(ዘ-ሐበሻ) አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ትናንት በደሴና በግንደር ሰላማዊ ሰልፉን አድርጎ በሰላም ካጠናቀቀ በኋላ ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2005 (ጁላይ 15 ቀን 2013) ዓ.ም መንግስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን የወረዳ አመራሮችንና አባላትን በዘመቻ ማሰር መጀመሩ ተዘገበ፡፡
አንድነት ፓርቲ በድርጅቱ ፌስቡክ ላይ እንዳስታወቀው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሰዓትም 42 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላት በፖሊስ ታስረዋል። የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ እያሰራጨ ያለውን ህጋዊ በራሪ ወረቀት ለህዝብ እያደሉና በማደልም ላይ በመሆናቸው የተያዙት አባላት ከአዲስ ከተማ 15፣ ከጉለሌ7 ፣ ከየካ 9 እንዲሁም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ እንደሆኑ ፓርቲው ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አረጋግጧል።
“የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል አንድነት የጀመረው እንቅስቃሴ ለዴሞክራሲና ለሰላም ቆሚያለው የሚለው በጠመንጃ ሃገሪቷን በማስፈራራት ላይ የሚገኘው የኢሕ አዴግ መንግስት የአንድነት አባላትን ማሰሩ ከድንጋጤ የመጣ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ተደምጠዋል።
ዛሬ ከታሰሩት 42 የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከልባ ለፈው ሳምንት ቄራ አካባቢ ተመሳሳይ ወረቀት ሲበትኑ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስረው የነበሩት ስንታየሁ ቸኮልና ዳንኤል ፈይሳ ዛሬም በድጋሚ እንደታሰሩ ፓርቲው አጋልጧል።
ዛሬ የታሰሩት የተፈፀመባቸው የአንድነት አባላት ዝርዝር፦
1ኛ. ስንታየሁ ቸኮል
2ኛ. ዳንኤል ፈይሳ
3ኛ. ኤፍሬም ሰለሞን
4ኛ. ታሪኬ ከፋ
5ኛ. ዘገዬ እሸቴ
6ኛ. ተፈሪ ተሾመ
7ኛ. ሀብታመ አድነው
8ኛ. ፍቃዱ በቀለ
9ኛ. ብስራት ተሰማ
10ኛ. መኳንንት ብርሀኑ
11ኛ. ፋና ወልደጎርጊስ
12ኛ. ሽፈራው ተሰማ
13ኛ. ፋንቱ ዳኜ
14ኛ. ገነት ሰለሞን
15ኛ. አላዛር አርአያ
16ኛ. ሳሙኤል ኢሳያስ
17ኛ. ደመላሽ ሙሉነህ
18ኛ. አማኑኤል መንግስቱ
19ኛ. ታሪኩ ጉዲሳ
20ኛ. አስማረ ንጉሴ
21ኛ. ፍቃደስላሴ ግርማ
22ኛ. አሸናፊ አስማረ
23ኛ. ዳንኤል
24ኛ. ለሚ ስሜ
25ኛ. ሰይፈ
26ኛ. ባዩ ተስፋዬ
27ኛ. ሰለሞን አክሊሉ
28ኛ. ወርቁ አንድሮ
29ኛ. ኃይሉ ግዛው
30ኛ. ሸዋአገኘው ማሞ
31ኛ. ቴዎድሮስ ገብሬ
32ኛ. አክሊሉ ሰይፉ
33ኛ. ንጉሴ ቀነኒ
34ኛ.ደረጀ ጣሰው
35ኛ. ገዛኸኝ አዱኛ
36ኛ. ሰፊው መኮንን
37ኛ. ታደለ ድሪባ
38ኛ. ሀብታሙ ሺበሺ
39ኛ. ሽመልስ ድንቁ
40ኛ. በየነ አበበ
በተጨማሪም 2 ስማቸውን ለጊዜው ማግኘት ያልተቻለ ሰዎች ታሰረዋል።
አንድነት በጀመረው የሰላማዊ ትግል የኢሕ አዴግ መንግስት አባላቱን ጠራርጎ አንድ ሰው እስከሚቀር ድረስ እንደሚታገል መግለጹን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል።


source...http://revolutionfordemocracy.com

No comments:

Post a Comment