Monday, July 29, 2013

የነጀማነሽ ማህበር ከነብዩ ኤልያስ ለፓትርያርኩ አመጣን ያሉትን መልእክት ይፋ አደረጉ Artist Jemanesh and Co. revealed message from "Prophet Elias"

የነጀማነሽ ማህበር ከነብዩ ኤልያስ ለፓትርያርኩ አመጣን ያሉትን መልእክት ይፋ አደረጉ Artist Jemanesh and Co. revealed message from "Prophet Elias"

አርቲስት ጀማነሽ ሰሎሞንን ያካተተው የማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ አባላት፣ ለፓትርያርኩ ያመጣነውን “የቅዱስ ኤልያስ” መልእክት የሚቀበለን አጥተናል በማለት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ አደረጉ፡፡ በብሔረ ሕያዋን ይኖራል ከተባለው ነብዩ ኤልያስ ተልከን መልእክታችንን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ እንዳናደርስ የጥበቃ አባላት ከልክለውናል ያሉት የማህበሩ አባላት፤ ከመልዕክቶቹ መካከል ትክክለኛው ሰንበት ቅዳሜ ስለሆነ በእሁድ ፋንታ በብሔራዊ ደረጃ ታውጆ መከበር ይገባዋል የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “ኦርቶዶክስ” የሚለውን ስያሜ የሚቃወሙት የማህበሩ አባላት፤ “ተዋህዶ” የተሰኘው እምነት ጥንታዊ የጉባኤ እለታትን ጨምሮ አራት የቅዱሳን መታሰቢያ ቀናት በብሔራዊ በዓልነት ለማስከበር ፓትሪያርኩ ከፌደራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ቅዱስ ኤልያስ በ2000 ዓ.ም ከመንግስተ ሰማያት ወደ ቅድስት ምድር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አስተምሯል ያሉት የማህበሩ በቅዱስ ኤልያስ፣ በሄኖክና በመልከፄዴቅ የተባረኩ በመሆናቸው እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡ የዳዊት መዝሙር ላይ በመመስረትና፣ ፓትሪያርኩ የቅዱሳን ሊቃውንት ክብረ በዓላት በብሔራዊ ደረጃ ለማስከበር በቦታው መገኘት ይገባቸዋል በማለት ፓትርያርኩን አሳስበዋል፡፡ የማህበር አባላት በኢትዮጵያ ደረጃ መስከረም 7፣ 12፣ 21 እና የካቲት 21 ብሔራዊ በዓላት እንዲሆኑ ነው ፓትሪያሪኩን ለመጠየቅ የፈለጉት፡፡

 Written by መልካሙ ተክሌ, AddisAdmassNews.com

source....sodere.com

No comments:

Post a Comment