· የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እስከ መስከረም አጋማሽ ፳፻፮ ዓ.ምድረስ እንዲቋረጥ ተወስኗል
· ደቀ መዛሙርቱ በቀጣይ ርምጃዎቻቸው ላይ እየመከሩ ነው
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ›› ለቀው እንዲወጡ የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት በይፋ አዘዘ፡፡
ልዩ ጽ/ቤቱ ዛሬ፣ ሐምሌ፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ከቀትር በኋላ በኮሌጁ የለጠፈው ማስታወቂያ፣ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ማስታወቂያው ከወጣበት ከዛሬ ሐምሌ ፰ እስከነገ ሐምሌ ፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ‹‹በሰላማዊ መንገድ››ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ አሳስቧል፡፡
‹‹የቀኑ ትምህርት የተቋረጠ መኾኑን ስለማሳወቅ›› በሚል በቁጥር ል/ጽ/445/339/05 በቀን 8/11/05 ዓ.ምበፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ ተፈርሞ በአድራሻ ለቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተላከው ይኸው ደብዳቤ፣የቀኑ መርሐ ግብር የተዘጋው ከኮሌጁ የሥራ አመራር ቦርድ የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ከተመረመረ በኋላ መኾኑን አስታውቋል፡፡
ከመጋቢት ፬ ቀን ፳፻፭ዓ.ም ጀምሮ የኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ሲስተጓጎል መቆየቱን የልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ ጠቅሶ፣ ከሐምሌ ፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም ጀምሮደግሞ ደቀ መዛሙርቱ የኮሌጁን ቢሮ በመዝጋትና የመንፈቅ ዓመቱን የማጠቃለያፈተና ለመፈተን የመጡ መምህራን ወደ ቢሮ እንዳይገቡ በመከልከልበፈቃዳቸው መፈተን እንደማይፈልጉ ማረጋገጣቸውን ገልጧል፡፡
የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት እና የቅድስት ሥላሴ ሥራአመራር ቦርድ ደብዳቤው በግልባጭእንዲደርሳቸው የተደረጉ አካላት ሲኾኑ ውሳኔውን በጽኑ የተቃወመው የቅዱስሲኖዶስ ጽ/ቤት በዝርዝሩ ውስጥ አልተጠቀሰም፡፡
እንደ መንበረ ፓትርያሪኩምንጮች፣ ከቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ሰባት አባላት መካከል የኮሌጁ የቀን መርሐ ግብር እንዲዘጋ የሥራ አመራር ቦርዱ አቅርቦታል በተባለውየውሳኔ ሐሳብ በተለይ የተስማሙትና የወሰኑት ከኮሌጁ ‹‹የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ›› ጋራ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው ፓትርያሪኩ ብፁዕወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብቻ ናቸው፡፡ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊውን ብፁዕ አቡነ ሉቃስን ጨምሮ የወቅቱ የቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ አባላት -ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ- ኮሌጁን መዝጋት የፓትርያሪኩ ሥልጣን እንዳልኾነ በግልጽ ከማሳሰብ ጀምሮ የአጣሪ ኮሚቴው የመፍትሔ ሐሳቦች ተግባራዊ እንዲደረጉየተሟገቱ ናቸው፡፡
የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤትየበላይ ሓላፊ አቡነ ገሪማ እንደ ቀድሞው ዘመነ ፕትርክና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚጥሱ ውሳኔዎችን በጎማ ማኅተም በመሸኘት የጥፋትተባባሪነታቸውን መቀጠላቸውን ያስረዱት ምንጮቹ፣ በዚህና ሌሎች የፓትርያሪኩ አቋሞች የእንደራሴነት ሚና እየተጫወቱ ናቸው ያሏቸውንበአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያሪኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነእስጢፋኖስንም በትችት እየሸነቋጧቸው ነው፡፡ ከረዳት ሊቀ ጳጳስነት ባለፈ ፓትርያሪኩን ከብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ጋራ በወሳኝጉዳዮች ላይ በማማከር የእንደራሴነት ሚና ይጫወታሉ የሚባሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የደቀ መዛሙርቱ ችግር ዘልቆ የተሰማቸውናለኮሌጁ የሚቆረቆሩ አገልጋዮችና ምእመናንን ተማኅፅኖ/ሽምግልና ለመቀበልም ጭምር ሲቸገሩ መታየታቸው ነው የተዘገበው፡፡
በቃለ ዐዋዲው መሠረትእያንዳንዱ አህጉረ ስብከት ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ፈሰስ ከሚደረገለት ፳% እና ከሌሎች ምንጮች ከሚያገኘው አጠቃላይ ገቢ 5%የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ድርሻ ነው፡፡ ይህን ድንጋጌ በመመርኮዝ ኮሌጁ የሕዝብ መኾኑን በትላንትናው የቅድስት ሥላሴ ክብረበዓል ላይ ለምእመኑ ሲያብራሩ የዋሉት የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ምእመኑ ገንዘብ ከመስጠት ባሻገር ስለ ቤተ ክርስቲያኑን ጉዳይ በመጠየቅ በቤተ ክርስቲያኑ ጉዳይ በባለቤትነት ስሜት ቀጥተኛ ተሳታፊ በመኾን ከጎናቸውእንዲቆም ሲጠይቁ ውለዋል፡፡
በዛሬው ዕለት ጠዋትምወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዘንባባ በመያዝ አመርተው ሙስናን በሚያጋልጡና የኮሌጁን አላግባብ መዘጋት በሚቃወሙኀይለ ቃሎች እንዲሁም በበመዝሙርና በስብከት አቋማቸውን ሲገልጹ ውለዋል፡፡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የደቀ መዛሙርት ማፍርያ እንጂ የሙሰኞች መሸሸጊያ አይኾንም›› ያሉት ደቀ መዛሙርቱእንዳሰቡት ምእመኑ በአካል ከጎናቸው ባይቆምም በተለያዩ መንገዶች ድጋፉን ገልጦላቸዋል፤ በገንዘብም ደረጃ እስከ ብር 30 ሺሕ ድጋፍመሰብሰቡ ነው የተዘገበው፡፡
በዛሬው የተቃውሞ ውሎፓትርያሪኩ የደቀ መዛሙርቱን አምስት ተወካዮች እንደሚያነጋግሩ ቀትር ላይ ተገልጾላቸው ተወካዮቹን በብዙ አስጠብቀዋቸው ሲያበቁ ‹‹አምባሳደርእያነጋገሩ ነው›› በሚል እንደወትሮው ያለውጤት ወደ ግቢያቸው ከተመለሱ በኋላ ነው ከልዩ ጽ/ቤቱ ወጥቶ በግቢያቸው ስለተለጠፈውማስታወቂያ የተረዱት፡፡
‹‹ይህ ዐይነቱ ማስታወቂያ የእብደት እንጂ ከጤነኛ አእምሮ አይመነጭም፤መሄድ እስከምንችለው ድረስ በተቃውሟችን እንቀጥላለን››ያሉት ደቀ መዛሙርቱ፣ ቀጣይ ርምጃዎችን በተመለከቱ የትግል አማራጮች ላይ እየተወያዩ መኾኑ ታውቋል፡፡
source.... http://sodere.com

No comments:
Post a Comment