በአዉሮጳ ኢትዮጵያዉያን የስፖርትና የባህል ፊዴሪሽን የዘንድሮዉን ዝግጅቱን በስዊዘርላንድ ጄኔቭ አጠገብ በምትገኘዉ ኒዮ ከተማ በደማቅ ዝግጅት አካሂድዋል።
ባለፈዉ ሳምንት ለአራት ቀናት በተካሄደዉ በዚህ ዝግጅት ላይ በሺዎችየሚቆጠሩ እድምተኞች እንደተገኙ ተነግሮአል።በኒዮ
የስዊዘርላንድ ከተማ የተካሄደዉ 11ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ባለፈዉ ሳምንት
መጨረሻ ቅዳሜ ነበር የተጠናቀቀዉ። ከተለያዩ የአዉሮጳ ሀገራት፤ ከሰሜን አሜሪካ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የመጡ እጅግ
በርካታ ኢትዮጵያዉያን እና በተለይ የእስፖርት አፍቃሪዎች በዝግጅቱ ላይ መገኘታቸዉን እና እጅግ አስደሳች ግዜ
እንደነበር የኢትዮ-ኮለኝ የእስፖርት ሊቀመንበር ወጣት ተስፋዪ አበበ ገልጾልናል። በእንጊሊዝ ነዋሪ የሆኑት እና
በአዉሮጳ የኢትዮጵያዉያን የስፖርትና ባህል ፊዴሬሽን ዋና ተጠሪ አቶ ዩሃንስ መሰል በበኩላቸዉ እጅግ ብዙ ህዝብ
እንደነበር፤ በተለይ ዘንድሮ ለህጻናት ልዩ ልዩ ዝግጅት እንደነበር ገልጸዋል።
ልዩ ልዩ የህጻናት ባህላዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶችን ያካተተዉ ይህ ፊስቲቫል፤ በተለይ እግር ኳስ ሰፊዉን መድረክ ይዞት እንደነበር ታዉቋል። ከሰሜን አሜሪካ እና ከደቡብ አፍሪቃ የመጡ የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድኖችእንዲሁም ከአዉሮጳ ወደ 24 የእግር ኳስ ቡድኖች ተሰባስበዉ ነበር። እዚህ በኑረንበርግ ነዋሪ የሆነዉና በአዉሮጳ የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የስፖርት ማህበር ዋና ፀሃፊ ፤ወጣት ካሱ ለገሰ፤ ኢትዮ- ኑረንበርጎች፤ በስዊዘርላንድ ሊዮ ከተማ ዝግጅት ላይ ተገኝተዉ እንደነበር ገልጾልናል። ሙሉ ዝግጅቱኑ ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ
source....http://www.dw.de

No comments:
Post a Comment