የአረቡ ዓለም አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብለህ ታስባለህ ብለው ጠይቀውኛል” – ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ዝግጅቱ የነበረው አሜሪካ ኤምባሲ ውስጥ ነው፡፡ ጥሪውም የደረሰን በአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ነው፡፡ የተነገረኝም
ቀደም ብሎ ነው፡፡ ከሦስት ሣምንት ወይም ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ነው፡፡ ጊዜውን በትክክል ስለማላስታውሰው ነው፡፡
እኛ በዛ መሠረት ስብሰባውንም ይመሩ የነበሩት የአሜሪካ አምባሣደር ነበሩ፡፡ ስለዚህ እኔ የደረስኩት ግማሽ ላይ
የእነሱ ስብሰባ እያደረጉ /አመታዊ ስብሰባ/ የለጋሽ ሀገሮች ስብሰባ፡፡ ስለዚህ ለኛ የተያዘው ፕሮግራም ከዘጠኝ
ሰአት እስከ 10፡30 ነበር፡፡ እና የአሜሪካ አምባሣደር ንግግር እንዳደረጉ የእለቱ ልዩ እንግዳቸው እንደሆንኩ
ካስተዋወቁ በኋለ ይዤ የቀረብኩትን ንግግር አቀረብኩ፡፡
ይዤ የቀረብኩት ፅሁፍ መጀመሪያም ስጋበዝ እንደተናገረኝ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካና ቀጠናው ላይ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ወደፊት ምን ሊያደርግ አስቧል እንደ አንድ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል ሲመጣ ይዟቸው የተነሣቸው መሠረታዊ ሀሣቦች ዝርዝር የፖሊሲ አማራጮች ምንድን ነው የሚለውን አጠቃላይ የሆነውን የመጨረሻ እይታ ለማሣየት ነው የሞከርኩት፡፡ አቅጣጫውን የኢትዮጵያ የተቃውሞ ፖለቲካ አሠላለፍ ፣ የመንግስትን እርምጃዎችና ከ1997-2005 የሆኑትን ነገሮችን በእኛ እቅድ ላይ ያሉትን አጠቃላይ ሁኔታዎች ለማሣየት እንዲሁም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ናት፡፡ የምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ትልቅና የረጋ የብሔር ስብስብ ነው ያለው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ሰላሙና ኃይሉ ለምስራቅ አፍሪካ ቅርብ ነው፡፡ ሜድትራኒያን አለ፣ ቀይ ባህር አለ፣ አባይ አለ፡፡ ሁለተኛ ነገር ይሄ ሽብርተኝነት የሚባለው ነገር አለ፡፡ ነዳጅ አለ እነዚህ ሁሉ ያሉበት ቀጠና ስለሆነ፣ እንደ አንድ የፖለቲካ አማራጭ ስንመጣ እንደዚህ ያሉት ችግሮች ሁሉ አጠቃላይ የሆነ እይታ ሊኖረን እንደሚችል ጠይቀውኛል፡፡ እኔም በፅሁፌ አብራርቻለሁ፡፡
በወቅቱ የነበረው የአምባሣደሮች ቁጥር ወደ 35 አካባቢ ይሆናሉ፡፡ የትላልቅ ሀገሮች አምባሣደሮች በሙሉ አሉ፡፡ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ አውስትራሊያ፣ እንግሊዝ፣ ስፔን እንደመሰለኝ እንደውም የምእራባውያን ብቻ ይመስለኝ ነበር፡፡ ዳሩ የለጋሽ ሀገሮች ቡድን ግን እንግሊዘኛ በደንብ የማይናገሩ መልካቸው ወደ ጃፓን የሚያደላ ሲናገሩ ነበር፡፡ እዛ ውስጥ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ለጋሾች ናቸው፡፡ ማን ነው ያለው ፣ ማን ነው የሌለው የሚለውን ባላውቅም የፖሊሲ አፈፃፀማቸውን የሚገመግሙበት ስብሰባ መሆኑን አውቃለሁ፡፡
እዛ ካገኙኝ በኋላ ብዙ ነገር ጠይቀውኛል፡፡ እኔ አጠቃላይ እይታዬን ነው ያቀረብኩት፡፡ እነሱም ቢሆን በጣም ብዙ ጥያቄ ጠይቀውኛል፡፡ “የአረቡ አለም አብዮት ኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብለህ ታስባለህ ወይ; እንደዛ አይነት ሰፊ የተቃውሞ ሰለፍ እንዴት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማደራጀት ቻላችሁ; በብዛት ወጣቶች ላይ ትኩረት እንደማድረጋቸው ወጣቶች ላይ የፖሊሲ ትኩረት አላች ወይ; እዛ ሰልፍ ውስጥ የወጣው የተለያየ የሕብረተሰብ ክፍል አይነት ነው፡፡ እስራትን በመቃወም የሚጠይቅ አለ፣ የኑሮ ውድነቱን በመቃወም የሚጠይቅ አለ፣ የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ የሚጠይቅ አለ፡፡ ስለነፃነት የሚጠይቅ አለና እነዚህ ሁሉ በሰማያዊ ፓርቲ የፖሊሲ አቅጣጫ እንዴት ነው ሊፈቱ የሚችሉት” እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ጠየቁኝ፡፡ ብዙ አይነት ዝርዝር ጉዳዮችንም ጠይቀውኛል፡፡ ብዙ ነው ያነሱት በጣም ትኩረት ሰጥተው ነው የሚጠይቁት፡፡ ከዛም በኋላ ስለ 2007 ምርጫ ሁሉ ጠይቀውኛል፣ እንዴት ነው ተሣትፏችሁስ ዝግጅታችሁስ ሲሉኝ እኔም ያው እንደምናሸንፍ መጠነኛ የሆነ እንኳን መስፈርቱን የሚያሟላ ምርጫ ከተገኘ ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ኃይል አላቸው ተብለው የሚታዩ፣ የሚታመኑ፣ በሙሉ በኃይማኖት መሪዎቹም ዘንድ ፣ በእስልምናና በክርስትናም እንዲሁም በአደባባይ ምሁራን ዘንድ በሌሎቹም የሕብረተሰብ ክፍሎችም ውስጥ በሙሉ ትልቅ ድጋፍ በዩንቨርስቲዎችም ሆነ በተቋሞች ውስጥ ድጋፍ ያገኘ በሚዲያውም ጭምር በአለም አቀፉ ኮሚቴውም ከዛ ሲያልፉ ደግሞ ወጣቱን የሚያንቀሣቅሰው ፓርቲ በሙሉ ወጣቶች በመሆናቸው እነዚህ ኃይሎች ተዳምረው ውጤት ለማምጣትና ለውጥን ለመሸከም ዝግጁ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 እንደሚያሸንፍ ነገርኳቸው፡፡
ስታሸንፉስ ማለትም ኢህአዴግን በልጣችሁ ድል ብታገኙ ከኢህአዴግ ጋር የሚኖራችሁ ግንኙነት እንዴት ነው; ብለው ጠየቁኝ፡፡ እኛ ጋር ችግር እንደሌላ እኛ ለይቅርታ ዝግጁ እንደሆንን ወደፊትም እንደምናይ ምናልባት ከቦታቸው ላይ የሚለቁት ምርጫ ሲመረጥ የተሸነፉት ብቻ እንጂ ወታደራዊ ክፍሉም፣ ፖሊሱም፣ ደህንነቱም፣ ሲቪል ሰርቪሱም እንደሚቀጥል፡፡ ለብሔራዊ እርቆች ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆንን ተቋማት እንደተቋማት እንደሚቀጥሉ አስረድቻቼዋለሁ፡፡
በወቅቱ ተገኝቼ ያየሁት መንፈስ አሁን እንግዲህ እኔ እንደሚመስለኝ ኢህአዴግ የማታለል ፖሊሲውና ተግባራዊው ነገር እየተራራቀ እንደሆነ ነው የምረዳው፡፡ ኢህአዴግ ሁሌ ማታለል ነው ስራው፡፡ የሚላቸው ዳታዎቹና የሚሰራቸው ነገሮች እጅግ የተራራቁ ናቸው፡፡ ስለዚህ በአንፃሩ ደግሞ ካለው መንግስት ጋር መስራት አለባቸው፡፡ ያለውን ብሔራዊ ጥቅማቸውን በቀጠናውም ሆነ የአገራቸውን ነገር ለማስጠበቅ፡፡ ስለዚህ ከእነሱ ጋርም ያላቸው ነገር በቀላሉ እንዲበላሽ የሚፈልጉ አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ዲፕሎማሲ ሲበዛ በጣም ጣጣ አለው፡፡ ሚዛን ጠብቀህ መሂድ አለብህ፡፡ ለአንድ የተለየ አድሎ እንዳለህ አሣይተህ መሄድ የለብህ፡፡ ስለዚህ ካለው ኃይል ጋር ዋናው ነገር ብሔራዊ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ ስለሆነ ያንን ሚዛን ጠብቀው ይሄዳሉ፡፡ ግን የኢትዮጵያዊያን ዋናው ጥሩ ነገር አሁን ያገኘነውን እድል እንዲታወቅ የምፈልገው፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው ከጠነከርን አማራጩንም የአገራችንን ጉዳይ በራሣችን ኃላፊነት መፍታት እንደምንችል ሲረዱ እነሱ ለኛ ለመስራት ይመጣሉ፡፡ እነሱ ይጫኑልናል፣ መንግስትን ይገፉልናል አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይልቃል የሚባል ፓርቲም አልነበረም፡፡ መጣን ተነቃነቅን ፣ ተስፋ አሣየን፣ ሚዲያውም ስለኛ ፃፈ ፣ ወጣቶችም ተነቃቁ፡፡ ጥያቄያቸውን አንሣንላቸው ወጡ፣ ከዛ በኋላ ደግሞ ኢንተርናሽናል ኮሚኒቲውም ከኛ ጋር ለመስራት መጣ ፣ ማየት ያለብን እኛ ኢትዮጵያዊያን ከጠነከርን ከአለም ጋር ለመስራት ጥሩ ባህሪ አለን፡፡ ሚዛናዊነት አለን፣ አስተዋይነት አለን፣ ስስት የለብንም ፣ ከጐረቤቶቻችን ጋር የመኖር ጥሩ ባህል አለን፡፡ ይህንን ጠብቀው ከኛ ጋር ለመስራት ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን እኛ በተዳከምን ቁጥርና ኢህአዴግ ዘላቂነቱን ካረጋገጠ ግዴታ ከኢህአዴግ ጋር ለመስራት ይገደዳሉ፡፡ ስለዚህ እኛ ጋር ነው ቁም ነገሩ ያለው፡፡ የለውጥ አማራጭ ሆነን በታየን ጊዜ ሕዝባችንን ማንቀሣቀስ የምንችል ሆነን በታየን ጊዜ ፣ መሠረታዊ ድጋፉ እንዳለን ባወቁ ጊዜ ከኛ ጋር ይሰራሉ፡፡
ባለፈው ሰልፍ በወጣንበት ጊዜ ያነሣናቸው ጥያቄዎች ላይ የታሰሩ ሰዎችን በሚመለከት ጥያቄ አንስቻለሁ፡፡ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ሁኔታ ስገልፅ ሰዎች ያለአግባብ እንደሚታሰሩ፣ ስለኃይማኖት ነፃነት የጠየቁ ፣ የመንግስትን አሠራር የተቹ እስክንድር ነጋን የመሳሰሉ፣ በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት የታሰሩ እንደ አንዱላምን የመሰሉ፣ ርዕዩትን የመሰሉ ጋዜጠኞች እንዲሁም በእስልምና እምነት ላይ ነፃነት ያስፈልገናል በኃይማኖታችን ጉዳይ መንግስት ጣልቃ አይገባ፣ ኃይማኖትና መንግስት የተለያየ ስለሆነ ይህንን ነገር ኢህአዴግ ያቁም ብለው የራሣቸውን መሪዎች እንምረጥ በማለታቸው እስር ቤት የወረዱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመፍትሄ አፈላላጊዎች በብዛት ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህንን ነገር በአስቸኳይ እንዲያስተካክል እኔም ጠይቂያለሁ፡፡ አሁንም ቢሆን እኛ የምንሰራበት ሁኔታ ግፊት አይነት መሆኑን እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲደርስ ደግሞ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝም ማለት እንደሌለበት በሞራልም ፣ በሀሣብም ከኛ ጋር መቆም እንዳለበት መንግስትንም መጠየቅ እንዳለበት ደጋግሜ አስረድጃለሁ፡፡

Short URL: http://www.zehabesha.com/amharic
No comments:
Post a Comment