Saturday, February 1, 2014

“የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የሃቀኝነት ጥያቄ ይነሳባቸዋል”


ለ46 ዓመታት በፖለቲካ ትግል ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት የ70 ዓመቱ አዛውንት የቀድሞ የኢፌዲሪ ኘሬዚዳንት ኋላም
የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ በቅርቡ ከፓርቲ-ፖለቲካ ራሳቸውን አግልለዋል።
ዶ/ር ነጋሶ፤ ለምን ከአንድነት ፓርቲ ለቀቁ? ስለተቃዋሚዎችና ስለኢህአዴግ ምን ይላሉ? በስጋት ስለሚኖሩበት
የመንግስት ቤት ጉዳይስ?
በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ ብሥራተ ገብርኤል በሚገኘው መኖሪያ
ቤታቸው አግኝቶ  በስፋት አነጋግሯቸዋል፡፡
በስጋት ነው የምኖረው መውደቂያዬን አላውቀውም
እኔ የታገልኩት ቁስ ለመሰብሰብ አይደለም
ታጋይ እንጂ ዲኘሎማት አይደለሁም
ለ46 ዓመታት በፖለቲካ ትግል ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት የ70 ዓመቱ አዛውንት የቀድሞ የኢፌዲሪ ኘሬዚዳንት ኋላም የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ በቅርቡ ከፓርቲ-ፖለቲካ ራሳቸውን አግልለዋል። ዶ/ር ነጋሶ፤ ለምን ከአንድነት ፓርቲ ለቀቁ? ስለተቃዋሚዎችና ስለኢህአዴግ ምን ይላሉ? በስጋት ስለሚኖሩበት የመንግስት ቤት ጉዳይስ? በእነዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ ብሥራተ ገብርኤል በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አግኝቶ በስፋት አነጋግሯቸዋል፡፡ በስጋት ነው የምኖረው መውደቂያዬን አላውቀውም እኔ የታገልኩት ቁስ ለመሰብሰብ አይደለም ታጋይ እንጂ ዲኘሎማት አይደለሁም ለምንድነው የፓርቲ-ፖለቲካ በቃኝ ያሉት? አንደኛው፤ የእድሜ ጉዳይ ነው፡፡ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም 70 ዓመት ሞልቻለሁ፡፡ ለ46 ዓመት ያህል በቀጥታ ህይወቴን ከፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር አቆራኝቼ ኖሬያለሁ፡፡ አሁን ይበቃል የሚል ስሜት አደረብኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ለወጣቶች ቦታውን መልቀቅ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ በኔ በኩል የተቻለኝን ያህል በፓርቲ-ፖለቲካ ውስጥ አገልግያለሁ፡፡
አሁን ይበቃኛል፡፡ ይህን ስል ትግሉን አቆማለሁ ማለቴ አይደለም፡፡ ሁለተኛ፤ የጤንነት ጉዳይ ነው፡፡ የስኳር ህመምተኛ ነኝ፡፡ በክኒን ነው የምኖረው፡፡ የደም ግፊትም አለብኝ፡፡ እንደልቤ መንቀሣቀስ አልችልም፡፡ በሊቀመንበርነት ከመሩት “አንድነት” ፓርቲ ጋር ስላለዎት የአመለካከት ልዩነት ይንገሩን? ለእኔ ከፓርቲ-ፖለቲካ መገለል ከላይ ከጠቀስኳቸው ምክንያቶች በበለጠ ይሄኛው ዋናው ምክንያቴ ነው፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው ሊደረግ በታቀደ ጊዜ፣ በአመራር ውስጥ መግባት የሚፈልጉ እንዲወዳደሩ ብለን ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ ለሊቀመንበርነትም ሆነ ለብሔራዊ ምክር ቤት ለመወዳደር አልፈለግሁም። ያልፈለግሁበት ምክንያት ደግሞ እኔ ወደ አንድነት የመጣሁት በመድረክ ምክንያት ነው፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ በፈጀ ውይይት ነው መድረክ የተመሠረተው፡፡ መጀመሪያ መድረክ ወደ ጥምረት ሲሸጋገር ድርጅቶች ናቸው ተስማምተው ጥምረቱን ያቋቋሙት፡፡ እኔ ደግሞ በወቅቱ በየትኛውም ድርጅት ያልታቀፍኩ ስለነበርኩ ሁለት ምርጫ ብቻ ነበረኝ፡፡
ወይ ከመድረክ ጋር ያለኝን ግንኙነት ማቆም አለያም በፓርቲ ጥላ ስር ሆኜ መንቀሣቀስ፡፡ ተሣትፎዬ እንዲቀጥል ስለፈለኩ፣ የግድ ወደ አንድ ፓርቲ መግባት ነበረብኝ። ኘሮግራሙን በማዘጋጀት ብዙ ረድቻለሁ፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ሊሠሩ የሚችሉበት ጠንካራ ኘሮግራም ነው፣ በጣምም ደስ ስለሚለኝ ተሣትፎዬን መቀጠል ፍላጐቴ ነበር፡፡ ስለዚህ በፓርቲ ለመታቀፍ ከስድስቱ የመድረክ ተጣማሪ ፓርቲዎች የትኛው ኘሮግራም የበለጠ ለኔ ይስማማኛል መምረጥ ነበረብኝ፡፡ እናም አንድነትን መረጥኩ፡፡ በዚህ መልኩ ነበር ወደ አንድነት የመጣሁት፡፡ ከመጣሁ በኋላም መድረክ ራሱን አሣድጐ ወደ ግንባር ተሸጋገርን፡፡ ይህን ስናደርግ በሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ብዙ ውይይቶች ነበሩ፡፡ ከየድርጅቱ ሁለት ሰዎች የተወከሉበት የሥራ አስፈጻሚ አለ፡፡ የዚያም አባል ነበርኩ፡፡ የአንድነት ፓርቲ ኘሮግራም ያስቀመጠው አቅጣጫ፤ ሁሉም ፓርቲዎች ቢዋሃዱ ለዚህች ሀገር ጠቀሜታ እንዳለው የሚገልጽ ነው፡፡ ህዝቡም ተመሣሣይ ግፊት ያደርግ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ነው መድረኩ ከጥምረት ወደ ግንባር የተሸጋገረው። የመድረኩ ሥራ አስፈጻሚ፤ የግንባሩን ኘሮግራም እና የወደፊት አቅጣጫዎች ሠርቶ ለየፓርቲዎቹ ሥራ አስፈጻሚዎች አቀረበ፡፡ የድርጅቶቹ ሥራ አስፈጻሚዎች ከተወያዩበት በኋላ በኘሮግራሙ ተስማሙ፣ አንድነትም ተስማማ፡፡ የአንድነት ሥራ አስፈጻሚ ከተስማማ በኋላ፣ የመጨረሻ ወሣኝ የሆኑት ሁለት አካላት ውሣኔ ይጠበቅ ነበር፡፡ አንደኛው፤ ብሔራዊ ምክር ቤት ሲሆን ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡
በዚህ ተዋረድ መሠረት፣ ሥራ አስፈጻሚው የተስማማበትን የግንባሩን ኘሮግራም ወደ ብሔራዊ ምክር ቤት አወረደ፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ተቀበለው፡፡ ከዚህ በኋላ የመጨረሻ ወሣኙ ጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠራንና፣ ጠቅላላ ጉባኤው በበጐ ተቀበለው፡፡ ይሄን አካሄድ እንግዲህ ሁሉም የመድረክ ተጣማሪ ድርጅቶች ናቸው የተገበሩት፡፡ አንድነትን ጨምሮ ሁሉም ድርጅቶች በዚህ ሂደት “ግንባሩ ይፈጠር” የሚለውን ከወሰኑ በኋላ የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠራ፡፡ ከእያንዳንዱ ድርጅት በደንቡ መሠረት 10 ሰው ተወከለ፡፡ 10 የአንድነት ወኪሎችም በመድረኩ ጉባኤ ተገኙ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ችግሮች ነበሩ፡፡ አንደኛ፤ መድረክ የገንዘብ ችግር ነበረበት፡፡ ሁለተኛ፤ ደግሞ ሰዎች በትርፍ ጊዜያቸው ነበር የሚሠሩት፡፡ እነዚህ የስራ መጓተቶች ፈጠሩ፡፡ በዚህ የተነሳም አንዳንድ ጭቅጭቆች ተነሱ፡፡ ለምሣሌ ኘ/ር በየነ፤ በግርማ ሠይፉ ላይ ሲሠጡ የነበረው አስተያየት፣ ግርማም ሲሰጠው የነበረው ምላሽ፤ አቶ ቡልቻም በአንድነት ላይ ሲሰነዝሩት የነበረው አሉታዊ አስተያየት…፤ እነዚህ ሁኔታዎች በአንድነት አባላት ላይ ቀላል የማይባል ተጽዕኖ ፈጥረዋል፡፡ እንዴት የመድረክ አባል ሆነን አሉታዊ አስተያየት ይሰነዘርብናል የሚሉ ቅሬታዎች ነበሩ፡፡ ይሄ አሉታዊ ሁኔታ እያለ ከአንድነት አባላት አንድ ሃሣብ መጣ፡፡ “የመድረክን ሂደት እንገምግም” የሚል፡፡ በብሔራዊ ምክር ቤቱም ሂደቱን ገምግመን ማጠናከር አለብን የሚል ውሣኔ ላይ ተደረሰ፡፡ አንድ ኮሚቴም ተቋቋመ፡፡ ድጋሚ የተቋቋመው ኮሚቴ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግምገማውን አጠናቆ፣ ውጤቱን ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አቀረበ፡፡ እዚያ ላይ ነው እንግዲህ ችግሮች መፈጠር የጀመሩት፡፡
ገምጋሚ ኮሚቴ ያመጣው አንደኛው የግምገማ ውጤት፤ የመድረክ አባል ድርጅቶች ከአንድነት ኘሮግራም ጋር የማይስማሙ አቋሞችና አላማዎች አሉት፤ በዚህ ሁኔታ ግንባር ፈጥሮ አብሮ መሥራት አይቻልም የሚል ነው፡፡ሁለተኛው ደግሞ ግንባር እንዲሆን የተወሰነው በደንብ ጥናት ተደርጐበትና በቂ ውይይት ተካሂዶበት ሳይሆን አመራሩ ብቻ ያደረገው ነው የሚል ሆነ፡፡ ይሄ ነው በእኔና በአንድነት አባላት መካከል ልዩነት የተፈጠረው፡፡ በእርግጥ ቀድሞም ቢሆን መድረክ እና አንድነት የሚለያዩባቸው አንዳንድ ነጥቦች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ለምሣሌ የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ጉዳይ፣ የግለሰብና የቡድን መብት ጉዳይ፣ የመሬት ጥያቄ አፈታት፣ የፌዴራሊዝም ጥያቄ የመሣሠሉት ላይ ልዩነት ነበረው፡፡ እንዴት እነዚህ ልዩነቶች እያሉ ግንባር እናቋቁማለን የሚል ጉዳይም ተነስቷል፡፡ በወቅቱ እኔያቀረብኩት አስተያየት “እነዚህ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ዋናው በዴሞክራሲያዊ አካሄድ ወደፊት ልዩነቶቹ የሚፈቱበት ሁኔታ በኘሮግራሙ መቀመጡ ነው” የሚል ነበር፡፡ በመድረክ ያሉ ፓርቲዎች ፌዴራሊዝምን የሚደግፉ ቢሆንም በኢትዮጵያ አንድነት እምነት አላቸው፡፡ በኘሮግራሙም መገንጠልን አንደግፍም የሚል አቋም ላይ ተደርሷል። “ልዩነቶች ሊያለያዩን አይገባም፤ አብረን እየሠራን ከምርጫው በፊት ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ምህዳር እንዲፈጠር በማድረግ፣ የጋራ ማኒፊስቶ አዘጋጅተን፣ ወደ ፓርላማ እንገባለን ነበር የተስማማነው፤ እኛ ብቻ ሣንሆን ኢህአዴግን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም ፓርላማ ይገባሉ፣ ይህን መነሻ አድርገን የጋራ መንግስት እናቋቁማለን፡፡ ዴሞክራሲያዊ የመንግስት መዋቅር ከተፈጠረ በኋላ፣ የመድረኩ ግንባር ተጣማሪዎች የየራሣቸውን ኘሮግራም ይዘው ወጥተው አሊያም አንድ ሆነው የመሠላቸውን ትግል” ይቀጥላሉ በሚል ይሄን ስምምነት የፓርቲው ግምገማ አፈረሰው። በዚህ የተነሣ በሃሣብ ተለያየን፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ግምገማውን ተቀበለው እኔ ተቃወምኩኝ፡፡
ይሄ የሆነው በ2005 ሚያዚያ ወር ነው፡፡ ሁለተኛው ልዩነት የተፈጠረው ደግሞ የግምገማው ውጤት ምን ይሁን በሚለው ላይ ነው፡፡ የግምገማው ውጤት ወደ መድረክ ይሂድና ለውይይት ይቅረብ፤ በሌላ በኩል ወደ ሚዲያ ወጥቶ ህዝቡ ይወያይበት፤ ይሄ በሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደረግ በሚል ብሔራዊ ምክር ቤቱ ወሰነ። ነገር ግን ጉዳዩ በማግስቱ ከውሣኔው ውጪ ሚዲያ ላይ ቀድሞ ወጣ፡፡ አንድ ግለሰብ ጋዜጣ ላይ በስፋት አወጣው፡፡ ይሄን የመድረክ ሰዎች ሲያዩት ትልቅ ቁጣ አስነሣ፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ አንድነት ራሱን ሂስ ያድርግና ማስተባበያውን በጋዜጣ ያውጣ ወይም ይሄን ባደረገው ሰው ላይ እርምጃ ውሰዱ የሚል ማስጠንቀቂያ ከመድረክ ቀረበ፡፡ የእኔ አቋም “በሚዲያ ቢወጣ ምናለበት፣ ሂስም ማድረጉ ክፋት የለውም” የሚል ነበር፡፡ ሌሎች ግን አልተስማሙም። እንግዲህ በዚህ ላይም በእኔና በሌሎች የፓርቲው አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጠረ ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በመድረኩ ስብሰባዎች ላይ በሙሉ ህሊናዬ ሆኜ አንድነትን ለመወከል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገባሁ፡፡ እንደ ሊቀመንበር የግድ አንድነትን መወከልና የፓርቲውን ሃሣብ ማስተጋባት አለብኝ በሌላ በኩል ደግሞ ህሊናዬ ይሞግተኛል፡፡ በዚህ ምክንያት ዘንድሮ የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ ከመግባት ተቆጠብኩ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ የውህደት ጉዳይ ተጀመረ፡፡ መኢአድ እና አንድነት ይዋሃዱ ተብሎ ድርድር ተጀመረ፡፡ የቅድመ ውህደት ሠነድም ተዘጋጀ፡፡ በዚያ ሰነድ ላይ እኔና ብሔራዊ ምክር ቤቱ አሁንም ተለያየን፡፡ ብዙ የልዩነት ነጥቦች ናቸው፡፡ እነሱን አሁን መዘርዘር አልፈልግም፡፡ እርስዎ ውህደቱን አይደግፉም ማለት ነው? ውህደት እደግፋለሁ፤ ነገር ግን ሲዋሃዱ በምን ላይ ነው የተመሠረቱት፤ የውህደት ስምምነቱስ ምንድን ነው? በሚለው ላይ አንዳንድ ጥልቀት ያለው ውይይት ሊካሄድባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ግን እነዚህን ውይይት የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች እንዳለ ተቀብሏል። ለምሣሌ የህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ጉዳይ አለ። አንቀጹ የመገንጠል መብትንም ያካትታል፡፡ ይሄን አንቀጽ የውህደቱ ተደራዳሪ ኮሚቴ አይደግፍም፤ ከህገ መንግስቱም መሰረዝ አለበት ሲል ተስማምቶበታል፡፡ በእኔ በኩል ደግሞ ይሄ የማይቻል ነው፡፡ አንቀጽ 39ን ይደግፋሉ? አዎ! እደግፋለሁ፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው የመብት ነው፡፡ መብቱ ይከበር ነው እንጂ መገንጠል ይኖራል ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ እኔ አንቀጽ 39 ከህገ መንግስቱ ይሠረዝ የሚለውን አልደግፍም፡፡ ይህን ተቃውሞዬን በማሠማበት ጊዜ፣ እኛ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ አንደራደርም የምትል ማሻሻያ በድርድር ሰነድ ላይ ቀረበች፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ይሄን ሙሉ ለሙሉ ተቀበለው፡፡ በእኔ በኩል አሁንም ይሄ አባባል አስቸጋሪ ነው አልኩ፡፡ መብት አክብረህም አንድ ክፍለ ህዝብ መብቴ አልተከበረም፤ እገነጠላለሁ ካለ ምንድነው የሚሆነው? ወደ ጦርነት ነው የሚኬደው ወይስ ሌላ አማራጭ አለ? እዚህ ላይ ልዩነቶች ተፈጠሩ፡፡ አሁን መጨረሻ ላይ ደግሞ በአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የምረጡኝ ቅስቀሣ ሲካሄድ ነበር። እዚያ ላይ ጠቅላላ ጉባኤው፤”ውህደቱ ያስፈልጋል በማለት በ3 ወር ጊዜ ውስጥ ከመኢአድ፣ ከአረና እና ከመሣሠሉት ፓርቲዎች ጋር ውህደት እንዲፈጸም” ብሎ የወሰነውን ውሣኔ ኢ/ር ግዛቸው ወሰደና፣ “እንዲያውም ለውህደቱ የተሰጠው ጊዜ ዘግይቷል በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅ አደርጋለሁ” ሲል ቅስቀሣ ማካሄድ ጀመረ፡፡ በተጨማሪም “ከአሁን ጀምሮ በጥምረት፣ በግንባር በመሣሠሉት ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም፤ ውህደት ብቻ ነው የሚያስፈልገው፤ በዚህ አካሄድ ነው የምሠራው” ሲል አቋሙን ገለፀ ፤ በዚህም በከፍተኛ ድምጽ ተመረጠ፡፡ ይሄ ለኔ ሌላ ትርጉም አለው፡፡ የእኔ ግልጽ አቋም ምን መሠለህ? ከተቻለ ውህደት ጥሩ ነው፤ ወደ ውህደት የምትደርሰው ግን ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ነው እንጂ አድርጉ ስለተባለ መሆን የለበትም፡፡ ውህደት ላይ ሁሉም በአንድ እጅ ማጨብጨብ አለበት፤ በኘሮግራም ሙሉ ለሙሉ መስማማት አለበት፡፡ ይሄን ለማድረግ ደግሞ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ብዙ ውይይት ያስፈልጋል፡፡ እንግዲህ ይሄ የመጨረሻው ውሣኔ ላይ እንድደርስ እና ከፓርቲው እንድወጣ ያደረገኝ ጉዳይ ነው፡፡
በዚህና ከላይ ባስቀመጥኳቸው ምክንያት አቅጣጫው የተለወጠ ይመስለኛል፡፡ እኔ ደግሞ ከአቅጣጫ ለውጡ ጋር ህሊናዬ ተስማምቶ ሊሠራ አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት ከአንድነት ልወጣ ችያለሁ፡፡ ከፓርቲው ከወጣሁ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ሣስብም የደረስኩበት ድምዳሜ የፓርቲ-ፖለቲካ ይበቃኛል የሚለው ሆነ፡፡ አብዛኞቹ ፖለቲከኞች ከፓርቲ ፖለቲካ ሲገለሉ መጽሀፍ ይጽፋሉ፣ልምዳቸውን ያካፍላሉ፡፡ እርስዎ ምን አሰቡ? ርዕሱንና ይዘቱን መግለጽ አልፈልግም እንጂ መጽሃፍ እየጻፍኩ ነው፡፡ በሌላ በኩል የፖለቲካ ምክር መስጠትና ልምድ ማካፈልም አለ፡፡ እኔ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው በአንድነትም ሆነ በመድረክ ላይ “ትክክል አይደሉም” ብዬ ጫና ለመፍጠር አልፈልግም፡፡ እንዲጐዱም አልፈልግም፡፡ ለዚህች ሀገር ፖለቲካ አስፈላጊ ኃይሎች መሆናቸውን በሚገባ አምናለሁ፡፡ ከአንድነት የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ከነበሩት ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ጋርም አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይታወቃል፡፡ መነሻው ምን ነበር? ኢ/ር ዘለቀ የድርጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ ነበር፡፡ የፓርቲውን የድርጅት ስራ ማንቀሣቀስ ነበረበት፡፡ ግን እንደታሰበው ሣይሆን ድክመት ተፈጠረ፡፡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የተቻለውን ያህል መከርን፤ ግን አልሆነም፡፡ እኔ ነበርኩ ኃላፊነቱን የሠጠሁት፡፡ ሥራው ከተዳከመ አልንና ኃላፊነቱን እንዲለቅ አደረግን፡፡ እሱ ግን ደብዳቤ አልደረሰኝም ብሎ ጋዜጣ ላይ አወጀ፡፡ ይሄ ግን አይደለም፤ በወቅቱ ደብዳቤውን ሰጥቼዋለሁ፡፡ ይሄ ነው የግል ፀብ ያስመሰለው እንጂ የአለመግባባቱ መንስኤ የአሠራር ጉዳይ ነው፡፡ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ራሱ በአንዳንድ የዲስፒሊን ግድፈቶች የተነሳ በአባልነቱ ላይ ጥያቄ አንስቶ ነበር፡፡ በእኔና በአሥራት ላይም በየጋዜጦቹ ያወጣቸው ጉዳዮች ነበሩ፡፡
አሁን ደግሞ ኢ/ር ግዛቸው በሥራ አስፈጻሚነት መልምሎታል፡፡ እኔ በዚህ ምንም ቅር አይለኝም፡፡ በግል ግን እኔና እሱ ፀብ የለንም፤ እንቀራረባለን፡፡ በ46 ዓመታት የፖለቲካ ህይወትዎ ለኢትዮጵያ ህዝብ አበርክቻለሁ የሚሉት ጉልህ አስተዋጽኦ ምንድን ነው? ዴሞክራሲና ፍትህ ከሌለ፣ ጭቆናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ከተንሰራፋ፣ ሰው ሁሉ መታገል አለበት የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኔም በዚህ መርህ መሠረት፣ የራሴን ድርሻ ህሊናዬ በፈቀደው መንገድ እየተጓዝኩ አበርክቻለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ዴሞክራሲ እንዲኖር፣ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ አነቃቅቻለሁ ለማለት እችላለሁ፡፡ ለህሊና መኖር እንደሚቻል ያሣየሁም ይመስለኛል፡፡ ዋናው ነገር ሰው ሁልጊዜ መብቶቹ ካልተከበሩ መታገል አለበት፡፡ ባላደርግሁት ብለው የሚቆጩበት ፖለቲካዊ ውሣኔ ይኖርዎት ይሆን? አየህ… አሁን ለምሣሌ ሶሻሊዝምን እደግፍ ነበር። ደርግ ሶሻሊስት ነኝ ባለ ጊዜ ልደግፈው እችል ነበር፤ ነገር ግን አምባገነን ነው፡፡ ወጣቶችን የሚገድልና መብቶችን የሚደፈጥጥ ነበር፤ በዚያ ሶሻሊስት ስለሆነ ብቻ ሁሉን ሃጢያቶቹን ትቼ እሱን ለመደገፍ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም ነበር፡፡ ኦነግን ረድቻለሁ፤ ነገር ግን ኋላ ላይ ተጣላን፤ የተጣላንበት ምክንያት ተበታትኖ በየጐጡ እየተደራጁ የሚደረጉ ትግሎችን ተቃውሜ፣ ወደ አንድ መድረክ መሰባሰብ ይገባል የሚል አቋም በመያዜ ነበር፡፡ በአውሮፓ ይገኙ የነበሩ ሁለት የኦሮሞ ድርጅቶችን ለማቀራረብ ስንቀሣቀስ አንደኛው ድርጅት፤ “ይሄ ጐበና ዳጩ /የሚኒልክ ጦር አዝማች የነበሩት/ ነው “አለኝና አገለለኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ኦፒኤልኤፍ ከሚባል ድርጅት ጋር እየሠራን እያለ፣ በ1983 “ዱለ ወልቂጡማ ቢሊሱማ” /ዘመቻ ለነጻነትና ለእኩልነት/ ሲታወጅና ጦሩ ከጐጃም ተነስቶ ወደ ወለጋ ሲጓዝ “ይሄ ደግሞ ቅኝ ግዛት ነው” አሉ፡፡ እኔ በወቅቱ “ይሄ ዳግም ቅኝ ግዛት ሊሆን አይችልም።
ምክንያቱም ደርግ ሌላ ቦታ ተሸንፎ መሠረት ያደረገው ኦሮሚያ ውስጥ ነው፤ ስለዚህ ይህን ኃይል ለመደምሰስ የሚደረግን ዘመቻ ዳግም ቅኝ ግዛት ነው ብሎ ያለመደገፍ ደርግ እንዲቀጥል ማድረግ ነው ብዬ አቋም በመያዝ ከእነሱ ጋር ተለያየን፡፡ እንደገና ወደ ኦህዴድ ከመጣሁ በኋላ በ1993 ዓ.ም ከኢህአዴግ የተለየሁት በአቅጣጫ ልዩነት ነው፡፡ ሶሻሊስት ነን ብዬ አብሬ ስሰራ እነሱ ነጭ ካፒታሊዝምን ነው የምንከተለው ብለው በድንገት አወጁ፤ እኔ ደግሞ በካፒታሊዝም አላምንም፡፡ ምክንያቴም ካፒታሊዝምን እንከተላለን ሲባል እንዲሁ የውሸት በመሆኑ ነው፡፡ ፓርቲዎች በነጻነት መንቀሣቀስ ባልቻሉበት እና የብሔር ጥያቄ ባልተፈታበት ሁኔታ ካፒታሊዝምን እንከተላለን ማለት ሌላ ችግር ያመጣል ብዬ ተለያየን ፡፡ ከዚህ አንጻር ህሊናዬ በሚፈቅደው መንገድ ነው ስሄድ የነበረው ማለት ነው፡፡ ህሊናህ በፈቀደው መንገድ ስትጓዝ ደግሞ የሚቆጭህ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ እኔ አንዳችም የሚቆጨኝ ነገር የለም በውሣኔዎቼ ሁሉ ደስተኛ ነኝ፤ የራስን ሃሣብና የህሊና ጥያቄ ገፍቶ ለድርጅታዊ ውሣኔ ብቻ መገዛት በእኔ በኩል ትክክል አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች “ልዩነት ቢኖርህም ልዩነትህን ውጠህ እዚያው ብትቆይ ይሻልህ ነበር” የሚል ሃሣብ ያመጣሉ፤ ለኔ ግን ይሄ ትክክል አይደለም፡፡ አንዳንዶች እርስዎ ዶ/ር ነጋሶ፤ “ቀጥተኛ ሁሉን ነገር በግልጽ የሚናገሩ ስለሆኑ ለፖለቲካው የሚሆኑ ሰው አይደሉም ይላሉ…. አዎ! እኔ ዲኘሎማት አይደለሁም፡፡ ቀጥተኛ ታጋይ ነኝ፡፡ ፖለቲካው ወደዞረበት እየዞረ የሚሄድ ፖለቲከኛ ዲኘሎማት አይደለሁም፡፡ ዲኘሎማት የሆኑ ሰዎች ብዙ ጊዜ በዚህም በዚያም ብለው ግባቸው ላይ ለመድረስ ነው የሚጥሩት፡፡ እኔ ያንን አልችልበትም ፡፡ ቀጥተኛ መሆንዎ ያሣጣዎት ነገር አለ? ምን ያሣጣኝ ነገር አለ? /ረጅም ሣቅ/ ምናልባት በቁሣቁስ አሣጥቶኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ማቴሪያል ደግሞ ድሮም አልነበረኝም፤ አሁንም የለኝም፡፡ ሰዎች ከኢህአዴግ ጋር ባትጣላ ኖሮ ቢያንስ እንደ መቶ አለቃ ግርማ ትኖር ነበር ይሉኛል፡፡
ያንን ካየህ በቁስ ደረጃ ያጣሁት ነገር አለ ተብሎ ሊታሠብ ይችላል፡፡ ይሄ ያለሁበት ቤትም የኔ አይደለም፤ ከዚህም ውጣ ከተባልኩ ቆይቷል፡፡ መውደቂያ ስለሌለኝ እምቢ ብዬ ነው እንጂ፡፡ አበል የለኝም፣ ከአንድነት ትሠጠኝ የነበረች 3 ሺ 800 ብር አበልም ከበቀደም ጀምሮ ቆማለች፡፡ የምኖረው እንግዲህ ከቀበሌ በማገኛት 1300 ብር ጡረታዬ ነው፡፡ ባለቤቴም መጠነኛ ገቢ የምታገኝባት ሥራ አላት፡፡ እንግዲህ አሁን ያለሁበትን የኑሮ ደረጃ ካየህ፣ አጥተሃል የሚሉኝ ሰዎች ሃሣብ ትክክል ነው ልትል ትችላለህ፤ ነገር ግን ይሄ ለኔ አይቆጨኝም፤ ስሜትም አይሰጠኝም፤ ምክንያቱም እኔ በዚህ አይደለም የታገልኩት ቁስ ለመሰብሰብ አይደለም ፡፡ እስቲ ስለፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ አናውራ…. በአሁኑ ወቅት ለህዝብ መብትና ጥቅም በሃቀኝነት የሚታገሉ ፓርቲዎች አሉ? በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሃቀኛ ናቸው አይደሉም የሚለው ግምገማ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሁሉም በመሠለው መንገድ እየታገለ ነው፡፡ ለኔ ግን ካየኋቸው ተሞክሮዎች፣ በእርግጥም ሃቀኛ ድርጅት ነው ብዬ የማምነው የህዝብን ሉአላዊ የስልጣን ባለቤትነትን የሚቀበል ፓርቲ ነው፡፡
ለዚህ ተግባራዊነት የሚንቀሣቀስ መሆን አለበት እንጂ ለፓርቲ ኘሮግራም እና ዓላማ ብቻ የሚሠራ መሆን የለበትም፡፡ እዚህ አገር ሁሉም ፓርቲዎች ለህዝብ ነው የሚታገሉት ይባላል። ግን ከገዥው ፓርቲ ጀምሮ በሁሉም ላይ ችግር አያለሁ፡፡ ኢህአዴግ ለስሙ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ ምናምን ይላል፤ የሚሠራው ግን ሌላ ነው፡፡ ሌሎች ፓርቲዎችም የምንታገለው ለህዝብ የስልጣን ባለቤትነትና ለዴሞክራሲ ነው ይላሉ፤ ያ ከሆነ በጋራ መሥራትን ለምን ይፈሩታል? ከዚህ አኳያ ከተመለከትነው ሁሉም ፓርቲዎች ላይ የሃቀኝነት ጥያቄ ይነሣባቸዋል ማለት ነው፡፡ እርሶ ሲመሩት የነበረው አንድነት፤ “ገዥው ፓርቲ ሀገሪቱን በብሔር ከፋፍሎ ኢትዮጵያዊነትን ሸርሽሯል” የሚል አመለካከት አለው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በቅርቡ “የቁጫ ብሔረሰብ ማንነቱ ለምን አይከበርም ሲል የብሔር መብት ጥያቄ ያነሣል፡፡ እነዚህ ነገሮች እርስ በእርሣቸው አይጋጩም? በአንድነት ኘሮግራም ላይ አንድ አንቀጽ አለ። የኘሮግራሙ 3.1.5 አንቀጽ፤ “አብይ የፖለቲካ ጥያቄዎች በፖለቲካዊ መንገድ ነው የሚመለሱት፤ ይሄም በህጋዊና በዲሞክራሲያዊ መንገድ፤ በውይይት እና በድርድር ነው፤ በዚህ መንገድ አብይ ጥያቄዎች ካልተፈቱ ወደ ህዝብ ነው የሚሄደው” ይላል፡፡ ይሄ አንቀጽ እውነት ይታመንበታል ወይ የሚለው ለኔ ጥያቄ ነው፤ ለእኔ ከፖለቲካ ጥያቄዎች አንዱ የብሔር ጥያቄ ነው፡፡ አብይ የፖለቲካ ጥያቄ እንደሚኖር የምታምን ከሆነ፣ አንቀጽ 39ን መቃወም የለብህም ማለት ነው፡፡ የብሔር ጥያቄ የምታምንበት ከሆነ “በኢትዮጵያ አንድነት አልደራደርም” አትልም ማለት ነው፡፡ እኔ ተቃርኖውን በዚህ መንገድ ነው የማየው፡፡የቁጫን ህዝብ በተመለከተ ግን የአንድነት ኘሮግራም ላይ የግለሰብ እና የቡድን መብት መከበር እንዳለበት ተቀምጧል፡፡ የቁጫ ህዝብ አንድ ቡድን ነው፤ አንድነት የማንነት ጥያቄ ሣይሆን የመብት ጥያቄውን ነው የደገፈው፡፡
ጥያቄያቸው ይሰማ ነው ያለው። እነሱ የጠየቁት ይሰማ ከሚለው አኳያ ነው እንጂ ማንነታቸው ይታወቅ የሚል አይደለም፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ጥሩ አቅጣጫ ይዟል፤ በቀጣይ ምርጫም የስልጣን ባለቤት ሊሆን ይችላል ብለው ተስፋ የጣሉበት ፓርቲ አለ? አሁን ይህን ማለት ጥሩ አይደለም፡፡ ይሄኛው ከዚህ የተሻለ ነው ብዬ መወሰንም አልችልም፡፡ ፓርቲዎች ይደራጁ፣ ይሞክሩ፤ ከተመረጡ ይመረጡ፤ አሁን አለ ወይም የለም የሉም ብዬ ከደመደምኩኝ ጥሩ አይሆንም ነገር ግን ሁሉም በተቻለ መጠን ከልባቸው ለህዝብ የስልጣን ባለቤትነት ይታገሉ፡፡ በኢህአዴግ በኩልም የፖለቲካ ምህዳሩን መክፈትና ሁሉንም ፓርቲዎች በእኩል ማስተናገድ አለበት፡፡ ፓርቲዎች ከአሁን ጀምረው ተሰባስበው፣ ለዲሞክራሲ መሥራት አለባቸው፡፡ አሁን ጥሩ እየሠሩ ነው የሚሏቸው ፓርቲዎች የሉም? እየሞከሩ ነው ሶስተኛ አማራጭ አለ። አክትቪዝምን የሚከተሉ አሉ፣ አንድነትም፣ መድረክም…. ሌሎችም አሉ፡፡ በአሁኑ ሁኔታ ግን ይሄኛው ይሻላል ያኛው አይሻልም ወይም ሁሉም አይረቡም በሚለው ላይ ግን አስተያየት መስጠት አልፈልግም፡፡ ከፓርቲ ፖለቲካ ራስዎን ቢያገሉም በግልዎ የፖለቲካ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ በግልዎ ለፓርላማ መወዳደርስ? የለም ይበቃኛል፡፡ ወደ ፓርላማው መግባትም አልፈልግም፡፡ ምናልባት በፓርቲዎች መካከል ስምምነት ለመፍጠር፣ በኢህአዴግና በተቃዋሚዎች መካከል መቻቻል እንዲኖር፤ ሁሉም በብሔራዊ ጉዳይ እንዲስማማ የማድረግ እንቅስቃሴዎች ለመሳተፍ እሞክራለሁ፡፡ ምናልባት ኢህአዴግ፤ ለሁለተኛ ጊዜ አብረውት እንዲሰሩ ወይም በማማከር እንዲያግዙት ቢጠይቅዎ ፈቃደኛ ይሆናሉ? ምክር ከፈለገ አብሬ ብሠራ ምንም ችግር የለብኝም፡፡
ስብሰባዎች ካሉ እሣተፋለሁ፡፡ በቅርቡ አቶ ስብሃት ነጋ በሂልተን ሆቴል አንድ ሴሚናር አዘጋጅቶ ጋብዞኝ ነበር፡፡ እዚያ ላይ ተሣትፌያለሁ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጆርናሊዝምና ኮሚኒኬሽን ኢንስቲትዩት የፌዴራሊዝም ጥያቄ ላይ በተደረገ ውይይት ጋብዞኝ አስተያየቴን ሰጥቻለሁ፡፡ በቅርቡም ሌላ ውይይት ላይ እንድገኝ ጠይቀውኛል፡፡ የዚህ ዓይነት ሁኔታ ከተፈጠረ ለምን እምቢ እላለሁ፡፡ የመድረክ ሰዎች ብዙዎቹ እኮ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ከቀጠረኝ የመንግስት ስለሆነ አልፈልግም አልልም፡፡ ኢህአዴግም በምክር ከፈለገኝ አማክረዋለሁ፤ “ይሄን ብታደርግ ይሻላል፤ ይሄ ጥሩ አይደለም” ለሚለው ሃሣብ በሩን ከከፈተ ጥሩ ነው፡፡ ድሮ የትግል አጋርዎ የነበሩት የቀድሞ የኦነግ አመራር አቶ ሌንጮ ለታ “ወደ ሠላማዊ ትግል ተመልሻለሁ አዲስ ፓርቲም አቋቁሜያለሁ” ማለታቸው ለኢትዮጵያ ፋይዳው ምንድን ነው? ተቀባይነትስ ያገኛሉ ብለው ያስባሉ? በአገር ውስጥ 72 ፓርቲዎች ስላሉ የእነሱ አዲስ ፓርቲ ይዞ መምጣት ብዙም ፋይዳ የለውም፡፡ ከሌሎች ጋር ቢቀናጁ ይሻላል የሚል ሃሣብ አለኝ። ምክንያቱም በኦሮሞ ስም የተደራጁ ብዙ አሉ፡፡ “በኢትዮጵያ ጥላ ስር መኖር ይቻላል” ከሚለው አኳያ ስንመለከተው የእነ ሌንጮ መምጣት የሚጨምረው እሴት ይኖራል፡፡
በሌላ በኩል በአጠቃላይ በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሣቀሱ ፖርቲዎች ሁለት አቅጣጫ ነው የያዙት፡፡ አንዱ እንገንጠል፣ ሌላው በኢትዮጵያ ጥላ ስር ሆነን እንኑር የሚሉ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ጥላ ሥር እንኑር ለሚሉት የእነ ሌንጮ መመለስ ድጋፍ ሲሆን እንገንጠል ለሚሉት ደግሞ ድጋፉን ያጐድልባቸዋል፡፡ አገር ውስጥ በሠላማዊ መንገድ ሲታገሉ የቆዩትን የኦሮሞ ድርጅቶችና የእነ ሌንጮ ፓርቲ ውዝግብ ውስጥ እንዳይገቡ እፈራለሁ፡፡ በሌላ በኩል ኦነግ በእነ ሌንጮ ላይ ትግሉን ገድለውታል የሚል ሃሣብ የሚያነሣ ይመስለኛል፡፡ በተለይ ለኦሮሚያ “ህዝብ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ እንኑር” የሚለውን አስተሣሠብ የበለጠ ያጠናክራል፡፡ በእኔ እይታም የኦሮሞ ህዝብ ይሄንን ነው የሚፈልገው፡፡ የዳያስፓራውን ፖለቲካ እንዴት ይገመገሙታል? አንዳንዶች የሃይማኖት ተቋማትን በዘር እስከ መከፋፈል ደርሰዋል በሚል ይተቻሉ… ጨለምተኛነት አለ፣ አክራሪነት አለ፣ በሀይማኖትና በጐሣ መከፋፈል የእነ ሌንጮ ፓርቲ ተቀባይነት ያገኛል ወይ የሚለው አስቸጋሪ ጥያቄ ነው፡፡ እኔ 17 ዓመት ጀርመን ሀገር ስለኖርኩ አውቀዋለሁ፤ ከአንዳንድ የኦሮሞ ጓደኞቼ ጋር የምጣላው ለዚህ ነበር፡፡ ለምሣሌ እኔ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ አስመጥቼ ሳነብ ሲያዩ፡፡ “እንዴት ይሄን የአማራ ጋዜጣ ታነባለህ?” ይሉኛል ወይም መንገድ ላይ ሰውን በአማርኛ ሰላም ስል ደስ አይላቸውም ነበር፡፡ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ዛሬም አሉ፡፡ እዚያ ነጻነት አለ፤ ግን ነጻነት በዚህን ያህል ደረጃ መከፋፈላቸው፤ በአገር ቤቱ ፖለቲካ ላይ ተጽዕኖ አለው፡፡ ከኢህአዴንም ከአንድነትም የወጡት በአቅጣጫና በአመለካከት ልዩነት ነው፡፡ ከሁለቱ የበለጠ ያልተመቾት የቱ ነው? በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡
የኢህአዴጉ በአንድ በኩል “የህወኃት አንጃ” ያላቸውን ሰዎች ያስተናገደበት መንገድ አስከፊ ነው፡፡ ያኔ እኔ ምርጫ ቦርድ ብሆን ኖሮ፣ ኢህአዴግን ሠርተፊኬቱን እሠርዝበት ነበር። ምክንያቱም ሰዎቹ ህገ-መንግስቱና የምርጫ ህጉ በሚፈቅደው መንገድ አይደለም የተባረሩት፡፡ ዴሞክራሲያዊ መብታቸው አልተጠበቀም ያ ለኔ ብዙ ራስ ምታት ፈጥሮብኛል፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ በሰኔ ላይ አቅጣጫ መቀየር መጣ፡፡ እንግዲህ እሱ እና አሁን በአንድነት ያጋጠመኝ ይመሣሠላል፡፡ እኔ ላይ ጭቅጭቅና አለመግባባት በመፍጠር ረገድ ግን የኢህአዴጉ ነው የሚበዛው፡፡ ከአንድነት ስወጣ በእድሜ መግፋት እና በጤና እንደምለቅ አስቀድሜ ስለገለፀኩ ከጭቅጭቅ ያመለጥኩ ይመስለኛል። አንድነት በዚህ በኩል ሊበራል ነው፡፡ ሃሣብን ያከብራል፤ ያለ ቅሬታ ነው የተለያየነው፡፡ የኢህአዴጉ ግን የልብ ድካም ሁሉ ያመጣብኝ ነበር፡፡ አዲሱን የኢፌዲሪ ኘሬዚዳንት በተመለከተ አስተያየት አለዎት? የኘሬዚዳንት ተቋም ኃላፊነትና ተግባር እንዲሆን የተፈለገው የእንግሊዙ ሲስተም ነው፡፡ በእንግሊዝ ንግስቲቱ ሀገርን ትወክላለች፤ ሆኖም ግን እዚያ ብዙ ጥንቃቄ አለ ንግስቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ትደግፋለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፊናው እያንዳንዷን ነገር ማማከር፣ ሪፖርት ማድረግና የውሣኔ ሃሣቦችን መቀበል አለበት፡፡
እዚህ ያ የለም፤ አሁን ተፈጥሮ እንደሆነ አላውቅም፡፡ እኔ ባለሁበት ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማክሮኝ አያውቅም፡፡ እኔም ብዙ ጊዜ የኦህዴድን የድርጅት ሥራ በመሥራት ላይ ተጠምጄ ስለነበር በሌሎቹ ሥራዎች ላይ አልተንቀሣቀስኩም። ኘሬዘዳንት ግርማም በህመም ምክንያት አልተንቀሣቀሱም፡፡ የአሁኑ እንግዲህ እየተንቀሣቀሱ እንደሆነ አላውቅሁም፡፡ ሆኖም ግን በእድሜም በጤናም ደህና ናቸው፡፡ በትምህርትም ደህና ናቸው፤ በግርማ ሞገስም ገጽታቸው ለኘሬዚዳንትነት አይከፋም፡፡ ነገር ግን የኛ ህገ መንግስት ለኘሬዚዳንቱ ስልጣን አይሠጥም፡፡ በግል ቂም አለው ወይ እንዳትለኝ እንጂ የአሁኑ ኘሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና ዳዊት ዮሐንስ ነበሩ ያኔ በእኔ ላይ የፈረዱት። ሁሉን ነገር እንዳጣ የወሰኑት እነሱ ናቸው፡፡ በ97 ዓ.ም ምርጫ ጊዜ ምርጫ ውስጥ ገብተሃል፤ ብሎ አዋጅ ጥሰሃል ስለዚህ ጥቅማ ጥቅሞችህንና መብትህን ታጣለህ” ብለው የወሰኑት እነሱ ናቸው፡፡ ዶ/ር ሙላቱ ያኔ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ነበር፡፡ አሁን የሚኖሩበት ቤት ከኘሬዚዳንትነት ሲለቁ የተሰጥዎ ነው? ከኘሬዚዳንትነት የለቀቅሁ እለት የት እንደሚያስገቡኝ ጨንቋቸው፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጠገብ ካለች አንዲት ቤት ነበር ያስገቡኝ፡፡ እዚያ 6 ወር ከኖርን በኋላ ወደ ቦሌ ወሰዱን፤ ጥሩ ቤት ነበረች፤ 3 መኝታ ቤት አላት፣ ቢሮ ግን የላትም፡፡ ግድግዳውና መስታወቱ ተሠነጣጥቆ በጋዜጣ ነበር እየሸፈንን ሁለት አመት ቆየን፡፡ ከዚያ አሁን ያለሁበት ቤት አመጡን፡፡ አሁን ከፓርቲ ፖለቲካ ሲገለሉ ጥቅማ ጥቅሜን መለሼ ላገኝ እችላለሁ የሚል ተስፋ የሎትም? የቀድሞ ኘሬዚዳንት ከወገንተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መገለል አለበት ይላል፡፡ አተረጓጐሙ እንግዲህ በኢህአዴግ እይታ አፍህን ዘግተህ ተቀመጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው ማስጠንቀቂያ የደረሰኝ አዳማ ላይ የሮያል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በክብር እንግድነት ጋብዞኝ ባደረግሁት ንግግር ነው በወቅቱ ኢህአዴግ እንደሚለው “ልማት ያስፈልገናል፣ ልማት እንዲመጣ ዴሞክራሲ ያስፈልገናል፣ ዴሞክራሲ እንዲመጣ የመብት ጥያቄዎች መልስ ያስፈልጋቸዋል” አልኩ። አክዬም፤ “በኦሮሚያ ሠላም ስለሌለ እንደሌሎች አካባቢዎች ልማት እየተፋጠነ አይደለም፣ ይህ የሆነው ደግሞ ዲሞክራሲ ስለሌለ ነው” ብዬ ተናገርኩ፡፡ ከሁለት ሣምንት በኋላ ዳዊት ዮሐንስ ጠራኝና የኦሮሚያ ክልል ከሶሃል አለኝ፡፡ “ፖለቲካ ውስጥ እየገባህ ነው፤ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚህ ሁኔታ የምትቀጥል ከሆነ ጥቅማ ጥቅምህን ታጣለህ” አለኝ፡፡ “የፈለከውን አድርግ፤ እኔ አቋሜን ከማራመድ ወደ ኋላ አልልም” አልኩትና ሄድኩ፡፡ በዚያው ውሣኔያቸውን ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ እኔም ክስ መስርቼ፣ ከስሼ ሰበር ደርሶ ለእነሱ ተወሰነ፡፡
የሚሠጠኝ አበል፣ መኪና፣ ሠራተኞች፣ ቤት የመሣሠለውን አጣሁ እኔ አሁን ከፓርቲ ፖለቲካ በመውጣቴ በድጋሚ ጥቅማ ጥቅሜን አገኛለሁ የሚል ተስፋ የለኝም፡፡ ኢህአዴግ ይህን ካደረገ ተለውጧል ማለት ነው፡፡ እኔ ግን አሁንም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ መተቸቴንና መቃወሜን እቀጥላለሁ፡፡ ለኘሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በ4ዐዐሺህ ብር መኖሪያ ቤት መከራየቱን የሚተቹ ወገኖች አሉ? እርስዎ ምን ይላሉ? እኔም ከሚቃወሙት ወገን ነኝ፡፡ በዚህች ድሃ ሀገር ለምን ይሄ አስፈለገ? አንደኛ እኔ እንደሠማሁት ቤቱ 2ዐ ክፍሎች ነው ያሉት፡፡ አሁን በተሻሻለው ህግ ደግሞ ኘሬዚዳንቱ ከ3 እስከ 4 ክፍል ቤት ይሠጠዋል ነው የሚለው፡፡ በሀገራችን የድህነት ሁኔታ በ4ዐዐ ሺህ ብር ቤት መከራየት ያስፈልጋል ወይ?” የሚለውን ጥያቄ ከሚያቀርቡት ወገን ነኝ፡፡ አሁን እርስዎ የሚተዳደሩት በምንድነው? እስከአሁን ድረስ ለኢኮኖሚ የሚጠቅመኝን ሥራ አልሠራሁም፡፡ ለፒኤችዲ የጻፍኳት መጽሃፍ አለች ከዚያች ትንሽ ገንዘብ አግኝቻለሁ፡፡ ከዚያ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” ከሚለው መጽሃፌ ደግሞ ሩብ ያህሉን አግኝቻለሁ፡፡ ሌላው ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሲቋቋም፣ ዘመዶች አክስዮን ግዛ ብለውኝ በ4 ሺህ ብር የገዛሁት አለኝ፡፡ ከዚያ በስተቀር ምንም የኔ የምለው ሃብት የለኝም፡፡ ደምቢዶሎ ያለው የወላጆቻችን ቦታ ተወስዷል፡፡ እዚህም የራሴ የምለው ቤትም ሆነ ቦታ የለኝም፡፡ ከዚህ ከምኖርበት ቤትም ውጣ ብለውኝ ነበር፡፡ ነገር ግን አቤቱታ በማቅረቤ እስከአሁን ድረስ ዝም ብለውኛል፡፡ ግን በፈለጉ ጊዜ እንደሚወስዱት አውቃለሁ፡፡ ዋስትና የለኝም፤ በስጋት ነው የምኖረው፤ ቀጣይ መውደቂያዬንም አላውቀውም፡፡ ልጆችዎ የት ናቸው? ልጃችን አሁን የፊልም ትምህርቷን ጨርሳ ሎስአንጀለስ ውስጥ ሥራ እያፈላለገች ነው፡፡ ከቀድሞዋ ባለቤቴ የወለድኳቸው ደግሞ አንደኛው ጀርመን ሀገር ይሠራል፤ ሴቷ ደግሞ ለንደን ነው ያለችው፡፡
ልጅ ወልዳለች አሁን የእነሱ ጉዳይ አያሣስበኝም፡፡ እኔ አንድ ነገር ብሆን ባለቤቴ ምን ትሆናለች የሚለው ነው የሚያስበኝ፡፡ በቅርቡ በኢቲቪ በተላለፈ ዶክመንተሪ ላይ እርስዎና ሌሎች የአንድነት አመራሮች በ“ኢሳት” ጣቢያ ላይ ቃለ ምልልስ መስጠታችሁ ተተችቷል… ዶክመንተሪውን ተከታትየዋለሁ፡፡ የመጀመሪያው ላይ አሥራት ጣሴ፣ እኔ እና ዳንኤልን ነበር የሚያሳዩት ሁለተኛው ላይ እኔና ዳንኤል ኢንተርቪው ሰጥተዋል የሚል ትችት አቀረቡ ያቀረቡት፡፡ በቃለ ምልልሱ ምን እንዳልን ግን አላቀረቡም፡፡ ይህ እንግዲህ እነ ነጋሶ ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው ለማለት ተፈልጐ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ይህ የአሁኑ ሌላ የኘሮፖጋንዳ ሥራ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ጨዋታ ጥሩ አይደለም፡፡ የትም አያደርሣቸውም፡፡ ቢተውት ጥሩ ነው፡፡ ለወደፊት እርሶ ምን ዓይነቷን ኢትዮጵያ ለማየት ይመኛሉ? መብትና ነጻነት የተከበረባት፣ ሁሉም የፈለገውን የሚያስብባትና ያሻውን አቋም የሚገልጽባት ኢትዮጵያን ባይ ደስ ይለኛል፡፡ ሰው በፈለገው መንገድ እየተደራጀ የፈለገውን ተቃውሞ በመንግስት ላይ የሚያቀርብባት፣ የፈለገውን ግለሰብ እና ፓርቲ የሚመርጥባት፣ዜጐች በሁሉም ጉዳዮች ላይ ወሣኝ የሚሆኑባት ኢትዮጵያን ማየት ምኞቴ ነው፡፡ የሰው ልጅ ሙሉ ነጻነቱ ከተከበረለት፣ አቅሙን መጠቀም ይችላል፤ ያኔም ልማት ይመጣል፡፡ ይች ሀገር በተፈጥሮ ሀብት እግዚአብሔር የባረካት ነች፣ ይህን ተጠቅመን ድህነትን የምንቀርፍባትን ኢትዮጵያ እመኛለሁ፡፡
addis admas

መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት” ኢሳያስ ኣፈወርቂ


ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ
ከኣሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ ያማርኛው ክፍል
ከጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ
ጋዜጠኛ ኣዲሱ ኣበበ፥ እየተገባደደ የነበረውን የኣውሮጳውያን የ1992 ዓ.ም. ምክንያት በማድረግ በተገባደደው ዓመት
ከተከስቱ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹን ሲያስተናግድ፤ “1993 ዓ.ም. ላይ ደርሰናል፤ እንደ ኣውሮጳ ኣቆጣጠር። ኣቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ስለ
ኤርትራ ሬፈረንደም፥ ማለትም ህዝበ ውሳኔ፥ ይህን ብለው ነበር።” በሚል መክፈቻ የስራ ባልደረባው የሆነቺው ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ
ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር ቀደም ሲል በድምፅ ያደረገችውን ቃለመጠይቅ ይለቃል።
ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤
በግዴታም ይሁን በውዴታ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስስራ ቆይታለች። እና፥ እንግዲህ፥ የነፃነት ጥያቄ፥ የመገንጠል
ጥያቄ ከማን? የሚለው [መልሱ] ከኢትዮጵያ ነው። እንግዲህ፥ [ኤርትራ] ከኢትዮጵያ ጋር ተሳስራ ስለቆየች። እና፥ ይህ የሬፈረንደሙ ነጥብ
ራሱ ምንድንነው የሚለው፤ “ነፃነት ትፈልጋለህ? ኣዎን ወይም ኣይደለም” ዓይነት ነው። እና፥ ለምንድነው እንደዛ የጠበበው? ትንሽ ሰፋ ብሎ
ወይም ደግሞ ከኢትዮጵያ ጋር ኣንድነት ወይም ኮንፌደረሽን ወይም ፌደረሽን ወይም ሰፋ ያለ የራስ ገዝ ኣስተዳደር ወይንስ ነፃነት ነው
የምትመርጠው? በሚል ሰፋ ባለ ይዘት ለምን ኣልቀረበም?
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤
በመጀመሪያ ኤርትራ ከኢትዮጵያ እየተገነጠለች ነው የሚለውን ጥያቄ እኛ በበኩላችን ከመጀመሪያውም
ኣልተቀበልነውም። የምንቀበለው ነገርም ኣይደለም። በኛ ኣስተያየት ጥያቄው ምንደንነው? ህጋዊ ያልሆነ ጋብቻ ወደ ፍች በሚያመራበት
ወቅት ወደ ህግ መልሶ ለማረጋገጥ የሚቻል ኣይመስለኝም። የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጋር ስለመዋሃዱ ጉዳይ በህጋዊ መንገድ የተደረገ
ኣልነበረም። ስለዚህ ለኤርትራዊያን የሚቀርበው ጥያቄ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ትፈልጋለህ? ወይንም ኣትፈልግም? የሚል ሳይሆን፥ ነፃ ኣገር
እንድትሆን ትፈልጋለህ? ኣትፈልግም? የሚለው መሆኑ ባህሪያዊ የሆነ ነገር ይመስለኛል። ይህ ማለት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ትጠላዋለህ፥
ኣትወደውም፥ ከኢትዮጵያ ጋር ዝምድና የለህም፥ ኣይኖርህምም ማለት ኣይደለም።
ጋዜጠኛ ኣዳነች ፍስሃየ፤
ያኔ፥ ጋዜጣዊ መግለጫ በተደረገበት ጊዜ፥ የኤርትራ ህዝብ ወይም መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር የኤኮኖሚ ውህደት ወይም
ኢንቲግሬሽን እንደሚፈልግ፥ ከዛም ኣልፎ እንዳውም እስከ በኮንፌደርሽን የመዋሃድ ደረጃ ሊደርስ እንደሚችል ጠቅሰው ነበረ። እና ይህ
ኣባባል ምን ያህል እውነትነት ኣለው? ምን ያህልስ የሚገፋበት ነገር ይመስለዎታል?
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ፤
ከዚያም በኋላ ደጋግሜ እንደገለፅኩት ሁሉ፥ ጥያቄው ስለቀረበ፥ ለረጅም ጊዜ በቆየው ኣመለካከታችን መሰረት
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለያድግ ስለሚችል ዝምድና በሚመለከት ጭንቅላታችን ምን ጊዜም ቢሆን ክፍት ነው። በኤርትራና
በኢትዮጵያ መካከል ሊኖር ስለሚችል ማንኛውም ዓይነት ገንቢ መረዳዳት ገደብ የሚደረግበት ነገር ኣይሆንም። በኮንፌደረሽን መዋሃድ
የሚፈለግ ከሆነ፥ ለምን ኣይሆንም እንላለን። መንግስታት ፈለጉት ኣልፈለጉት በኤርትራና በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ለወደፊት ትውልዶች
የሚቀጥል የመዋሃድ ዝምድና መኖር ኣለበት። በፍላጎትና በምኞት ላይ ብቻ ሳንወሰን በተጨባጭ ወደ መዋሃድ ወደሚያመሩን እቅዶች
መግባት ኣለብን። እንዲህ ሲባልም ምንልባት ኣንዳንዶቹ፥ እነዚህ ችጋራሞች የሚበላና የሚጠጣ ስለሌላቸው ሊጠቀሙብን ፈልገው ነው
ኣሁን ውህደት የሚሉት፤ ለጥቅማቸው ሲሉ ነው፤ ይሉ ይሆናል። ይህ ግን ገንቢ ኣይሆንም።”
ታሪካዊ ምክንያቶች በመነሳት የኢትዮጵያና
የኤርትራ ህዝብ ኣንድነት ከራሳችን ኣልፎ ለኣካባቢያችንና ለመላው ኣፍሪካ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በውል በመገንዘብ
የኢትዮጵያና የኤርትራ ፌደራላዊ ኣስተዳደር እንድንመሰርት ያለንን ፍላጎት ቀደም ኣድርገን ለወያነ መንግስት ኣቅርበናል። የወያነ
መንግስት በማናውቀው ምክንያት ሃሳባችንን ካለመቀበሉም ሌላ ይህንን ሃሳብ ካቀረብንበት ጊዜ ኣንስቶ በሁለቱም ኣገሮች
ለነበረው መልካም ግኑኝነት ሳንካ ለመፍጠር እንደተንቀሳቀሰ ኣስተውለናል። ለወደፊትም ቢሆን ስርዓት በተከተለና ኣግባብ
ባለው መንገድ ከህዝባችን ጋር መክረን በህዝባችን ፍላጎትና ውሳኔ ተመስርተን ይህንኑ ሃሳብ የምናራምድ መሆናችንን
ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።
· በብሄር ከተደራጁ ድርጅቶች ብቻ ግንኙነት ታደርጋላችሁ ለተባለው ቅስቀሳው የወያነ ቅስቀሳ ከመሆኑ ባሻገር ትክክለኛ መረጃ
ኣይደለም። እኛ የምናደርገው ግንኙነት ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በብሄርም ሆነ በህብረ-ብሄራት ከተደራጁ ድርጅቶች ጋር
እንደሆነ ለማንም ግልፅ ሊሆንለት ይገባል። ከዚህ ውጭ ኣንተ በብሄር ኣንተ ደግሞ በህብረ-ብሄር ተደራጅ እያልን መመሪያ
የመስጠት መብት የለንም። ድርጅቶች በህብረት እንዲሰሩ ለማድረግ ሙሉ ፍላጎታችን ቢሆንም እጅ ኣየጠመዘዝን ድርጅቶችን
እንዲያብሩ ማድረግ ግን በድርጅቶቹ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ከመሆኑም በላይ ስራው የኢትዮጵያዊያኖች እንጂ የኛ ሊሆን
11
ኣይገባም። የኛ ዕቅድና ፍላጎት ኢትዮጵያን ለመበተን ቢሆን ኖሮ በደርግ ውድቀት ማግስት ልናደርገው እንችል ነበር።
የተበታታነች ኢትዮጵያ ደግሞ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለኛም ጠንቅ እንድምትሆን ኣጠያያቂ ኣይደለም። እኛ ግን በተቃራኒው
በሽግግሩ ጊዜ በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዲሰፍን ያበረከትነው ኣስተዋፅኦ ወዳጅም ጠላትም በሚገባ ያውቀዋል። በኢትዮጵያ
መበታተን የኤርትራ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል ብሎ የሚያስብ ካለ የታመመ ሰው ብቻ መሆን ኣለበት። ስለዚህ ወያነ ለራሱ
ህልውና ሲል የሚለፍፈውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ከመሆን በመታቀብ ታጋይ ኢትዮጵያዊያንና ባጠቃልዩም የኢትዮጵያ
ህዝብ የኤርትራ ችግር የተከሰተበትን ምክንያትና ለሰላሳ ዓመታት ያህል የተካሄደው ትግል ምንነት በማጤን ሁላችንም
ከስህተቶቻችን ተምረን ስህተቶች እንዳይደገሙ በውይይትና በመግባባት ህዝባችንን ለተሻለ ህይወት ለማብቃት ከመታገል ሌላ
ኣማራጭ የሌለን መሆኑን ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል።
· በኢትዮጵያ ውስጥ ኣሳሳቢ ችግር ያለ መሆኑን እንገነዘባለን። ችግሩን በሚገባ ተረድቶ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ደግሞ የሁላችን
ተሳትፎ እንደሚጠይቅ እናምንበታለን። ኣሁን የገባንበት የኢትዮጵያና የኤርትራ ችግር በኣንድ ተጨባጭ ፎርሙላ ማስተካከል
ከተቻለ ደግሞ ሌላው የውስጥ ችግር ህይወት ኖሮት ሊቀጥል ስለማይችል ወዲያውኑ እንደሚፈታ ለመገንዘብ ኣስቸጋሪ
ኣይደለም። ስለሆነም ችግሩ በተናጠል የኢትዮጵያ የውስጥ ችግር ተብሎ የሚቀርብ ሳይሆን የጋራ ችግር መሆኑን ተረድተን
መፍትሄውን በጋራ ለማስገኘት በኤርትራ መንግስትና ህዝብ በኩል ይህ ቀረው የማይባል ትብብር እንዳለና ለወደፊቱም በዚሁ
እንደሚቀጥል ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2014/01/29/521-4/

የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ


በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡
በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም አህጉሪቱ ለበለጠ ቀውስ የተጋለጠች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡
በቀዳሚነት የመፈንቅለ መንግሥት የሚያሰጋቸው አገራት ጊኒ፣ ማዳጋስካር፣ ማሊ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኒጀር፣ ጊኒ ቢሳው እና ሱዳን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡ ከአውሮጳ ምንም አገር በዝርዝሩ ውስጥ ያልገባ ሲሆን ዩክሬይን አደጋው ጥላ ካጠላባቸው በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሆናለች፡፡ ከወደ አሜሪካ ዩኳዶርና ሃይቲ ቀዩ የአደጋ ምልክት የታየባቸው ሲሆን ከእስያ ታላንድ፣ አፍጋኒስታን እና ፓኪስታንን ጨምሮ ስድስት አገራት የመፈንቅለ መንግሥት የቀይ ምልክት አደጋ ካለባቸው 40 አገራት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ከ40ዎቹ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 25ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህወሃት/ኢህአዴግ ሥልጣኑን ለራሱ ታማኞች ብቻ በመከፋፈል እንዲያም ሲል በቤተሰብ ደረጃ በማውረድ እየሸነሸነው በመሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይ ተመልካች ሆኗል፡፡ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ አዲስ አድማስ ሲዘግብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን እና የነጻው ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገልጾ ነበር፡፡
አፋኝ ሕጎችን በማውጣትና ማንኛውንም ዓይነት የግለሰብ መብት በመንፈግ በአንጻሩ ሊኖር የማይችል የቡድን መብት አስከብራለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በተመሳሳይ የሚወጡ መረጃዎችን በማጣጣል ዋጋ ቢስ ሲያደርግ መቆየቱን የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡ በተቀረው ደግሞ “ልማት፣ ህዳሴ፣ ውዳሴ፣ … ” በማለት የለውጥ ሃሳብ ከመጣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይስተጓጎላሉ በሚል በሕዝቡ ዘንድ ማደናገሪያ በመፍጠር በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጸረ ልማት” በማለት እንደሚወነጅላቸው ያማርራሉ፡፡ በምርጫ ማጭበርበርና ማንኛውንም ፖለቲካዊ ሆነ ማኅበራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ በሙሉ ቁጥጥር ሥር ማዋል ኢህአዴግ በሥልጣን ለመቆየት የሚጠቀምባቸው ዓይነተኛ መንገዶቹ እንደሆኑ በስፋት ይጠቀሳል፡፡
ይህንን የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ የቀመሩት ምሁር ስሌታቸውን ለማቀናበር የተለያዩ መረጃዎችን መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የአገራቱ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ በቅኝ ግዛት የመያዝ ሁኔታ፣ የአገራቱ ዕድሜ፣ ከነጻነት በኋላ የኖሩበት ዓመታት፣ የፖለቲካ መረጋጋት፣ የእርስበርስ ግጭት፣ የነጻ ምርጫ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በየቀጣናው ያለ የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ፣ ወዘተ የተወሰኑት ናቸው፡፡ ይህንን አያይዘውም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ማድረግ የግድ መፈንቅለ መንግሥት ይሆናል ማለት እንዳይደለ ነገር ግን አደጋውን ተመልክቶ አስፈላጊ እርምጃዎች በመውሰድ እንዳይሆን መከላከል ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ (ካርታዎቹ የተወሰዱት ከጄይ ዑልፌልደር ብሎግ ነው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የዛሬ ዓመት የአሜሪካንን የደኅንነት ምክርቤት ጠቅሶ ባወጣው ዜና በ2030 እኤአ ከሚከሽፉ መንግሥታት (failed states) መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘግቦ ነበር፡፡ ዜናውን ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”

ዘገባው የ15 አገራትን ዝርዝር አውጥቷል
የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡
እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡
የም/ቤቱ ዘገባ በተለይ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ ለመጪው ፕሬዚዳንት የወደፊቱን የዓለማችን መልክ ምን እንደሚመስል የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰቦች እና ዓለምአቀፋዊ ዝንባሌዎች ላይ አቅጣጫ የሚጠቁም ትንበያ ያደርጋል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ ዓለምአቀፋዊ የደኅንነት ዘገባ ያቀርባል፤ ለብሔራዊ የጸጥታ ምክርቤት እና ለአገር ውስጥ ደኅንነት መ/ቤት ምክር ያቀብላል፤ በአጠቃላይ የአሜሪካን የስለላና የደኅንነት ማኅበረሰብ ሊከተል በሚገባው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ የሚያስይዝ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
በዚሁም መሠረት ባለፈው የታህሳስ ወር “በ2030 የዓለም አቅጣጫ፡ አማራጭ አገራት” በሚል ርዕስ አንድ ዳጎስ ያለ ጥናት አቅርቧል፡፡ ይኸው 160ገጽ ያለው ዘገባ የዛሬ 17ዓመት የዓለማችን ገጽታ ምን እንደሚመስል ከየአገራቱ በተወሰደ ጥናትና እዚያው በሚገኙ ተመራማሪዎች የሰበሰበውን ያካተተ ነው፡፡ ዓለማችን የምታዘነብልባቸው ቀዳሚ ሁኔታዎች አንዱ ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ድህነትን ለመቀነስ፣ በትምህርት ለማደግ፣ በቴክኖሎጂና በህክምና ለመራቀቅ እንዲሁም በገቢም የመካከለኛው መደብ ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቀሱት አንዱ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፡፡
ሌሎቹ ዓለምን አንድ አድርጎ በመዳፉ ሥር የሚገዛ ኃይል የማይነሳ መሆኑ ከሚታዩት ከፍተኛ ዝንባሌዎች ተጠቃሽ ሲሆን አሜሪካ ምንም እንኳ “የዓለም ፖሊስ” የመሆኗ ሁኔታ የሚቀንስ ቢሆንም የዓለምን አቅጣጫ መቆጣጠሯ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ይጠቁማል፡፡ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ከመጨመሩ አኳያ “እያረጁ” የሚሄዱ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገታቸው እንደሚያሽቆለቁልና ከገጠር ወደከተማ ፍልሰት እንደሚጨምር፤ 60በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በከተሞች አካባቢ ኑሮውን እንደሚያደርግ ይተነብያል፡፡ በዚህም ምክንያት የውሃ፣ የምግብና የኃይል (ኤነርጂ) ፍላጎት ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ይናገራል፡፡ የቴክኖሎጂ ምጥቀትና የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎትም የዓለማችንን አቅጣጫ እንደሚቀይር ያስረዳል፡፡
የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በስፋት እንደሚቀጥልና በበርካታ ፈርጆች ትብብርና ስምምነት እየፈጸሙ ሰፋ ያለ ዓለምአቀፋዊ ኅብረት እንደሚያደርጉ የሚናገረው ይህ ሪፖርት በየአገራቱ እየሰፋ የመጣው በድሃና በሃብታም መካከል ያለው ክፍተት የማኅበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ይጠቁማል፡፡ ይህም ቀውስ በአንዳንድ አገራት ውስጥ እየሰፋ በመምጣት ለተባባሰ ግጭትና ክስረት እንደሚያጋልጥ የኑሮ ልዩነቱም የማኅበራዊ ቀውሱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ይተነትናል፡፡ የሃይማኖት ሚና እንደሚጨምር የጠቆመው ዘገባ ይህንኑ ተከትሎ መካረርና ግጭት እንዲሁም አሸባሪነት ለመስፋፋት ሃይማኖት ምክንያት እየሆነ እንደሚሄድ ይናገራል፡፡
በዘገባው ከተነገረው በተጻጻሪ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ወዲህ እስካሁን በ44 አገራት ጉዳይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ጣልቃ በመግባት ጦርነት ያካሄደችው አሜሪካ የዓለም ኃያል ሆና እንደምትቀጥል በመናገር ሪፖርቱን የሚያጣጥሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እንደማስረጃም አድርገው አሜሪካ በተለያዩ አገራት ያላትን 737 የወታደራዊ ተቋማት ይጠቅሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘገባው የአሜሪካ የበላይነት የመቀነሱን ጉዳይ አንስቶ የተናገረውን አይቀበሉም፡፡
ዘገባው የዓለማችንን የወደፊት ሁኔታ ሲተነብይ በዋንኛነት ከጠቀሳቸው ጉዳዮች አንዱ በ2030 የሚከሽፉ መንግሥታትን ዝርዝር ሰጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” የሚከሽፉ መንግሥታት ተብለው ከተጠቀሱት 15 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እንዷ ስትሆን አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ኬኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሃይቲና የመን የተቀሩት ናቸው፡፡
ይሁንና ይኸው ም/ቤት እኤአ በ2015 ፓኪስታን የምትከሽፍ አገር ትሆናለች በማለት ትንቢት ሰጥቶ ይኸው እስካሁን አለች በማለት ዘገባውን የሚያጣጥሉ ክፍሎች ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎቹ አገራት ለመክሸፋቸው በቂ ማስረጃ የለም በማለት የዘገባውን ጥቆማ ይቃረናሉ፡፡ በሌላ በኩል እንዲህ ያለው የመክሸፍ ሁኔታ ሊዋጥለት የማይችለው ኢህአዴግ “ህዳሴ፣ ውዳሴ” ከማለት ይልቅ ይህንን ጉዳይ አጥብቆ ሊያስብበት እንደሚገባና የሥርዓት መበስበስ አመላካች የሆነውን “የመንግሥት ሌቦች” መበራከት መፍትሔ ሊያበጅለት እንደሚገባ ደጋፊዎቹና አመራሩ በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡
በዚሁ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመክሸፍ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አሁን ካላቸው ተግባር አኳያ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በአውሮጳ የሚገኙ የፖለቲካና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ተመራማሪ “ችግሩ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውም ነው” ይላሉ፡፡ “በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ ከውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና ከስብሰባ/ውይይት ጋጋታ ባለፈ መልኩ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የተቀናጀና ውጤታማ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባቸዋል” የሚሉት ምሁር በውጭ ያለውም “ከጊዜያዊና ጥቃቅን የራስ ክብር የመፈለግ አካሄድ በመላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ጡንቻውን በወያኔ ላይ ማሳረፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡ “የደኅንነት ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ በግልጽ እንደተነበየው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ የመጨመሩ ያህል በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ለውጥ ማምጣት የሚችል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለአሉባልታና ተራ የፖለቲካ ወሬ ከመጠቀም ይልቅ አገር ለማዳን ተግባር ሊጠቀምበት ይገባል” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡
source: ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ወያኔን ያሸበረው የግንቦት 7 መንገድ ምንድነው?


የትግራይን ሕዝብ ከብሄር ጭቆና ነጻ አወጣለሁ በሚል ጠባብ ዓላማ ተደራጅቶና ታጥቆ ለበትረ ሥልጣን የበቃው ህወሃት ወይም ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣን ከተቆጣጠረ 23 አመት ሊሞላው እነሆ ጥቂት ወራቶች ብቻ ቀርተውታል።
ለጋራ ቤታችን ለሆነቺው አገራችን ኢትዮጵያና በአስተዳደር በደል ለከፋ ድህነት ለተዳረገው መላው ሕዝቦቿ የሚሆን አንዳችም ራዕይ ሳይኖረው ለመንግሥትነት ሥልጣን የበቃው ይህ ቡድን ላለፉት 23 ዓመታት ከግል ኑሮአቸው አሻግረው የአገርንና የወገንን ጥቅም ማየት የማይችሉ ወይም የማይፈልጉትን በዙሪያው አሰባስቦ እያካሄደ ካለው ዘርፈ ብዙ የሃብት ምዝበራ ወንጀል በተጨማሪ እየፈጸመ ያለው የመብት ጥሰትና አፈና ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።
ሰሞኑን እያፈተለኩ በመውጣት ላይ ከሚገኙ ምስጥራዊ የድምጽ መረጃዎች ለማረጋገጥ እንደተቻለው ደግሞ ለጥቂቶች የሃብትና የብልጽግና ምንጭ የሆነው ሥልጣን ከእጃቸው እንዳይወጣ በአንድ በኩል በምርጫ ስም እንዴት አድርገው ሕዝቡን ቀፍድደው የምርጫው ተሳታፊ ማድረግ እንደሚችሉ ሲዶልቱና በሌላ በኩል ደግሞ በቁጥጥራቸው ሥር የሌሉትንና ለሥልጣናቸው ያሰጉናል ያሉዋቸውን የደሃዉን ልጅ በማጋፈጥ እንዴት በጦርነት እንደሚጨፈልቁዋቸው ሲመክሩ ተሰምተዋል።
ከወያኔው ቁንጮ አንዱ የሆነው በረከት ስሞን በየደረጃው ላሉት የአገዛዙ ሹሞችና ካድሬዎች ባደረገው ገለፃ መሬትን የመንግሥት ባደረገው ኮሚኒስታዊ አዋጅ ምክንያት የመንግሥት ጭሰኛ ለመሆን የተፈረደበትን ሰፊውን አርሶ አደር “ተኛ ስንለው ይተኛል፤ ቁም ስንለው ይቆማል ፤ እንደፈለግን ብንበድለው እንኳ አያማርረንም ” እያለ ሲዘባበትበት ተደምጦአል ። በአንድ ለአምስት ኮሚንስታዊ አደረጃጀት ተጠርንፎ የወያኔ የንግድ ድርጅቶች ብቻ የሚያቀርቡትን ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ያለውዴታው እንዲራገፍበትና ከአቅሙ በላይ ዕዳ እንዲቀፈቅፍ የተፈረደበት የኢትዮጵያ አርሶ አደር በዚህ አይነት ንቀት ደረጃ የሚዘባበትበትን መሪ ከወያኔው በረከት ስሞን በፊት ገጥሞት አያውቅም ። ለወደፊትም ሊያይ አይፈልግም ። ወያኔን ሥልጣን ላይ ለማምጣት የሰሜኑ ክፍለአገራችን አርሶ አደር የተጫወተው ሚና ተዘንግቶ በበረከት ስሞን እንዲህ መዋረዱ እጅግ ያሳዝናል። ለነገሩ ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ ለድል ያበቃው የትግራይ ሕዝብ ቁም ስቅሉን እያየ አይደል?
ሌላው አስገራሚ ክስተት በአገር ደህንነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ባደረጉት ዝግ ስብሰባ ታማኝነታችን ለአገራችን ነው ወይስ የሥርዓቱን አገዛዝ ዕድሜ ለማራዘም? ብለው ላነሱት ጥያቄ የጠቅላይ ሚንስትር ተብዬው የህግ አማካሪ ጌታቸው ረዳ የሰጠው መልስ ነው። ደህንነት ብቻ ሳይሆን የመከላኪያ ሠራዊትና ፖሊስ ጭማር ታማኝነታቸውና ግዴታቸው ሥርዓቱን ሥልጣን ላይ ማቆየት መሆን አለበት ሲል ጌታቸው እንቅቹን ነግሮአቸዋል ። በምላሹ “ላለፉት 23 አመታት እያደረግነው ያለው ይሄው ሆኖ ሳለ አሁን ምን ብታስቡ ነው ጥያቄ ያነሳችሁ?” የሚል ይመስላል ። ይባስ ብሎም ሥርአቱን ለመጠበቅ ያልቻለና በግንቦት 7 መንገድ የሚጓዝ ደህንነት ሠራተኛ የተስፋየ ገብረስላሴን ያህል የደህንነት እውቀት ቢኖረውም ሆነ እስራኤል አገር የዓመታት ስልጠና ያገኘ ቢሆን ዋጋ የለውም ብሏቸዋል።
ለመሆኑ ወያኔዎች እንደመርገም የቆጠሩትና ተከታዮቻቸውን የሚያስፈራሩበት የግንቦት 7 መንገድ ምንድ ነው።?
ግንቦት 7 የፍትህና፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አገራችን ኢትዮጵያ የእያንዳንዱ ዜጋ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት የተከበረባት፤ የኢኮኖሚ ብልፅግናና ማኅበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ፤ የዜጎች ሕይወት፣ ደህንነትና ጥቅም የተከበረባት እና የሕዝቧ አንድነትና ትስስር የጠነከረባት ሃገር ሆና ማየትን ብቸኛ ራዕይ አድርጎ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ ደግሞ እስከ ዛሬ በጠመንጃ ኃይልና በጉልበተኖች ጡንቻ ከአንዱ ወደሌላው የሚፈራረቀው የመንግሥት ና የፖለቲካ ሥልጣን በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሂደት የሚያዝበትን ፤ የሃገሪቱ ዜጎች ምርጫ በተግባር የሚገለፅበት፤ ማኅበራዊና የፖለቲካ ችግሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የሚፈቱበት እና ዲሞክራሲያዊ ባህል የሚበለፅግበት ብሄራዊ የፖለቲካዊ ሥርዓት መገንባት አማራጭ የሌለው ነው ብሎ ያምናል።
ይህ ደግሞ ያለምክንያት አይደለም። ወያኔ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ሲል ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ በሩን ከፈት አድርጎ በነበረበት ምርጫ 97 ወቅት ከተገኘው ልምድና ከተመዘገበው ውጤት ሕዝባችን በአምባገነኖችና በከፋፋዮች ለመገዛት አለመፈለጉን በግልጽ አስመስክሮአል።
ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ሕዝባችን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በነቂስ ወጥቶ መሪዎቹን የመረጠበትንና ድሉን የተነጠቀመበትን ታሪካዊ የግንቦት 7 1997ን ቀን ምን ጊዜም አይረሳም። መጠሪያ ስሙንም በዚያ ታሪካዊ ቀን የሰየመው ሕዝብ የተነጠቀውን ድል በማስመለስ ፍትህ የሰፈነባት፤ የበለጸገችና የተከበረች አገር ባለቤት እንሆን ዘንድ ነው። ሁላችንም አትራፊ እንጂ ተጎጂ ለማንሆንበት ለዚህ ቅን አለማና ራዕይ ደንቃራ ሆኖ የተገኘው ወያኔና ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከወያኔ ጋር የተጣበቁ አንዳንድ ባዕዳን አገሮች ናቸው።
ወያኔ የግንቦት 7 መንገድ የሚለው ለዚህ ክቡር ዓላማ ሲባል እንቅፋት የሆነውን ሥርዓቱን በሁለ- ገብ ትግል አስገድዶ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር አካል ማድረግ ካልተቻለ ደግሞ በተባበረ ትግል አስወግዶ በምትኩ በሕዝብ ለሕዝብ ከሕዝብ የሚመጣ ሰላማዊ የመንግሥት ሥርዓት መመሥረትን ነው። ይህንን የተቀደስ አላማ ለማክሸፍና የተጀመረውን ትግል ለመጨፍለቅ ሲባልም ወደ ሥልጣን ለመምጣት በጦርነት ማግዶ ካስጨረሳቸው የደሃ ልጆች በእጥፍ የሚበልጡትን መልምሎ በጸረ ሽምቅ ውጊያ ከማሰልጠን ጎን ለጎን ለግንባታ ቢውል ስንት ፋይዳ ሊያስገኝ ይችል የነበረ በርካታ ገንዘብ በማፍሰስ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ድምጽ ለማፈንና ለመሰለል እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ለአገራችን ሉአላዊነት ጠቀሜታው እስከዛሬ ምንም ባልታወቀ ጦርነት ወደ መቶ ሺ የሚጠጉትን ያስጨፈጨፈ፤ የተልዕኮ ጦርነት ለማካሄድ በመንግሥት አልባዋ ጎረቤት ሱማሌ እስከዛሬ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ወገን ያስፈጀ ፤ ለሥራ ፍለጋ ውትድርና የገቡትን ወጣቶች ለይቶ በሰላም አስከባሪ ስም በድንበር ዘለል ጦርነቶች እየማገደ ገንዘብ የሚቀበል፤ ስለአገርና ስለወገን ምን ሊገደው ይችላል?
ትናንት ትግል ላይ በነበሩበት ወቅት የቀደምቶቹ መንግስታት ልጆቻቸውን ለትምህረት ወደ ፈረንጅ አገር እየላኩ የደሃውን ልጅ በጦርነት ይማግዳሉ በማለት በጅምላ ሲከስ የኖረ ዛሬ በተራቸው ልጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን ዘርማንዘሮቻቸውን ታይቶ በማይታወቅ ብዛት ወደ ፈረንጅ አገር ለትምህርት እየላኩ ለነጻነታችንና ለክብራችን የምንታገለውን እርስ በርስ ለማጨራረስ ሲዶልቱ ዝም ብሎ መመልከት ከየትኛውም ቅን ዜጋ የሚጠበቅ አይሆንም።
ስለሆነም የበላይ አዛዦቻቸው በሚሰርቁት የሕዝብ ገንዘብ ፎቅ ላይ ፎቅ እየገነቡ ሃብት በሚያካብቱት አገር ሠራዊቱን እረፍት ለመንሳት ሆን ተብለው በሚቀሰቂሱት ግጭቶች ከአንዱ ማዕዘን ወደ ሌላው ማዕዘን ያለ ዕረፍት እየተንከራተተ ያለው የመከላኪያ ሠራዊት ፤ የፖሊስና የደህንነት ኃይል ለአገዛዙ አልታዘዝም በማለት ተገዶ ሥልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክብ የማድረግ ወገናዊ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ግንቦት 7 የፍትህ የነትጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ጥሪውን ያቀርባል።
የግንቦት 7 መንገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት የተጠማውን ፍትህ እኩልነትና ነጻነት በአገራችን ለማስፈን አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የጎጠኞችና የዘራፊዎች ስብስብ በማስገደድ ወይም በማስወገድ ሰላማዊ ህጋዊና ዲሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር እንዲኖር ማድረግ ነው። ይህንን ደግሞ የሚፈሩት በሥልጣን ቱርፋትና በሃብት ዘረፋ የሰከሩ ብቻ ናቸው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2014/01/31/418/

አሳሳቢዉ የስነ- ምግባር ጉድለት


ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተግባብተዉና ተዋህደዉ በስርዓት የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን በዓለማችን እየታየ ያለዉ ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ይዞት የቆየዉን እምነቱን እና ባህሉን እየተፈታተኑት ነዉ ተብሎአል። ባለፈዉ ሰምወን «ስነ- ምግባር ለእድገት መሰረት ነዉ» በሚል ርዕስ፤ በአዲስ አበባ የትምህርት ቢሮ፤ የኢትዮጵያ የሰላም ፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ የተሰኘ፤ ቡድን አዲስ አበባን ጨምሮ ሰፋፊ በሚባሉ የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ፤ ከአንደኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች፤ ለከፍተኛ የስነ- ምግባር ጉድለቶች መጋለጣቸዉን በጥናት በተደገፈ መረጃ ይፋ አድርጎዋል። ቡድኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮችን ጠርቶ ለሁለት ቀናት ባደረገዉ ዉይይት፤ ታዳጊ ወጣቶች በተለይ በከተሞች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ ባሉ ህገ-ወጥ የአልኮል፤ የአደንዛዥ እጽ መጠቀሚያና፤ የወሲብ ፊልሞች ማሳያ ቤቶች በመበራከታቸዉ፤ ለችግሩ መጋለጣቸዉን አፅንዖት ሰጥተዉ ተናግረዋል። ዓለማችን እያስተናገደችዉ ያለችዉ ፈጣን ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ከትዉልድ ትዉልድ ይዞት የቆየዉን ትዉፊትና ስነ- ምግባሩን ወደ አልሆነ አቅጣጫ ሊወስደዉ ይገባልን? የዕለቱ የባህል መድረካችን የሚቃኘዉ ርዕሱ ነዉ ።
ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተግባብተዉና ተዋህደዉ በስርዓት የሚኖሩባት ሀገር ስትሆን በዓለማችን እየታየ ያለዉ ለዉጥ፤ ማህበረሰባችን ይዞት የቆየዉን እምነቱን እና ባህሉን እየተፈታተኑት ነዉ ይላል፤ የሰላም ፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ የተሰኘ፤ ቡድን አዲስ አበባ ላይ ባወጣዉ የስብሰባ ጥሪ። በስብሰባዉ ላይ በአሁኑ ወቅት ከተማ ያሉ አንዳንድ ወጣቶች ለአልኮል ለጫት እና ለልቅ ወሲብ መጋለጣቸዉን በጥናት የተደገፈ ፅሁፋቸዉን ያቀረቡት መምህርት ጽዮን አክሊሉ፤ በተለይ በዚህ ችግር ላይ ያሉት የገንዘብ አቅምና የተማሩ ቤተሰቦች አሉዋቸዉ የሚባሉ ታዳጊ ወጣቶች እንደሆኑ ተናግረዉናል።
መምህርት ጽዮን ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲና ከዓለም የጤና ድርጅት ምርምር ተነስተዉ ያቀረቡት የጥናት ጽሁፍ እንደሚያመለክተዉ የታዳጊ ህጻናት ስነ-ምግባር እጅግ እየተበላሸ እንደሆነ ይናገራሉ። ከሀገራዊ ስነ-ምግባር ጋር በተገናኘ በዉይይት መድረኩ ተሳታፊ የነበሩት አባ በአማን ግሩም እንደሚሉት በቴክኖሎጂ ዓለም እጅግ በጠበበችበት በአሁኑ ወቅት፤ በተለያየ የስራ ዘርፍና የእድሜ ክልል፤ የሀገርን ገፅታ የሚያበላሽ የስነ-ምግባር ጉድለቶች እየታዩ ነዉ።
በእዚህም ይላሉ አባ በአማን በመቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ይህ ሀገራችን ላይ የሚታየዉን አስከፊ የሆነዉን የስነ ምግባር ወረርሽኝ ሊያወግዙና ትምህርት ሊሰጡበት ይገባል። የግብርና ባለሞያ የሆኑትና «ስነ- ምግባር ለእድገት መሰረት ነዉ» በተሰኘዉ የዉይይት መድረክ ላይ የጥናት ፅሁፋቸዉን ያቀረቡት ሌላዉ የመድረኩ ተሳታፊ፤ አቶ ንጉሴ ዘዉዴ፤ በሀገራችን ታዳጊ ወጣቶች ዘንድ የሚታየዉ ፈር የለቀቀ ስነ-ምግባር ካልታረመ ሀገር ተረካቢ ትዉልድ እናጣለን የሚል ስጋት አለኝ ሲሉ ገልፀዉልናል።
የኢትዮጵያ የሰላም ፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ደብርነህ በበኩላቸዉ መጤ ልማዶችን ለማስቀረት ሁሉም የማህበረሰብ አካል የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል።
የኢትዮጵያ የሰላም፤ የልማትና የዴሞክራሲ ህዝባዊ የምክክር መድረክ የተሰኘ፤ በሁለት ቀኑ ስብሰባ ላይ ፤ በሃገራችን በተለይ በከተሞች አካባቢ በአንዳንድ ወጣቶች ዘንድ የሚታየዉ የስነ-ምግባር ጉድለት እና የማህበረሰባዊ እሴትች ዉድቀት፤ የሕግ ክፍተት መኖሩ አንዱ እንደሆነ እና የመንግሥት መገናኛ አውታሮችን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለህዝብ የሚተላለፉ የማስታወቂያ መልዕክቶች፤ የቃላት አመራረጥ ላይ ጥንቃቁ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጾዋል። በሌላ በኩል ለአንባቢ የሚደርሱ ስነ-ምግባር የጎደላቸዉ ፅሁፎች፤ ህዝብ አይን ላይ ከመድረሳቸዉ በፊት አራሚ ሊቃኛቸዉ እንደሚገባና፤ በዚህ ረገድ መንግስትም ሆነ ህብረተሰቡ ትኩረት እንዲሰጥ ያሉንን ፤ የዕለቱን እንግዶቻችን ለሰጡን ቃለምልልስ እናመሰግናለን። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ መጫኛዉን በመንካት ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ

dw.de

“ውድ ኢትዮጳያ ልጆች ሰዉ አትመኑ ዘመኑም ከፍቷል በራችሁን ዝጉ!!”በለው!


“የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ሆይ፣ ከቀጥተኛ የሠራዊት ጦረኛ ሸማቂ ባንዳ ይጎዳል!…ጥርሳቸው ያገጠጠ ሁሉ አይስቁም!… የተኮሳተሩም ክፉዎች አደሉም!…በውሸት ፈገግታ በሐዘናችሁ ላይ ከውስጥ የሚደሰቱትን ግን ተጠንቀቁ!…. አገባላት…አገባችለት … አተራመሳቸው!አጋጨው! …የተለየ ሀሳብ አቀረበና አፋጨው እየተባሉ መሸታ ቤት የሚያስጨበጭቡት፣ በፈቶች ቤት ልጅ እየጠበቁ ዕድሜያቸውን የሚቃትሉት ..እነ ተስፋአምካኝ አበበ …በአዳራሽና በሰልፍ ሜዳ የሚፎልለው ታዋቂው ዝነኛው ወጣቱ የሙስሊም ኦሮሞ ፓለቲካ በታኝ ጃዋር መለስ ዜናዊ…ይህ ሞን ኦሮሞ ሀገር በመፈክር ይገኝ መሰሎት የትኬቱንና ትራንስፖርት እየከፈለ ያስለፈልፈዋል ለመሆኑ የውጭ ሀገር ኦሮሞዎችን በካናዳ ትልልቅ ገበያ አዳራሽ ቲም ሆርተን ጠረጴዛ ከበው ሳይሰሩ እአወሩ እንደሚውሉ…በካናዳ ያሉትን የልመና (የድራጎት መስጫ) ቤቶች ማን እንዳጣበበ ያውቃሉን? 60ከመቶ ኦሮሞ የውሸት ፍቺ እየጠየቀ ሶስት አራት ልጅ እየፈለፈለ ባለሀብት ሆኖ ተደብቆ ሁለት ሥራ እሰራና የመንግስት ገንዘብ እየበላ ሀገር እንደሚበድል ያውቃሉን?ይህ በእያዳራሹ የምታያቸው የሜንጫ አብዮተኞች በድብቅ መኪና ጥበቃ እየሰሩ፣ የታክሲ ሥራ ማታ እየሰሩ የራሳቸውንም የታክሲ ታርጋ ያላቸው፣ የመንግስት ቤት ውስጥ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ደብቀው፣የሌላ ሰው ሚስት እያፋቱ ሲያባልጉ እንደሚኖሩ ታውቃላችሁ? እነኝሁ ሰዎች ኢትዮጵያ ኢንቨስተር ተብለው እንደሚያጭበረብሩ…፵/፷ ኮንደሚኒየም ቤት እየገዙ እንደሚያከራዩና/እንደሚሸጡ በሀገሩ የሚኖረውን ድሃ ኑሮን በማናር ኢኮኖሚው እንዲገለው የሚያደርጉ…ሌላውን ድሃ ህዝብ ..ሙት፣ተባላ፣ቀውጠው፣አፈንዳው፣አቃትለው፣እረደው፣እያሉ ገንዘብ እንደሚያዋጡ ያውቃሉን? ለመሆኑ እነኝህ ናቸው ሀገር የሚመሩት ሌብነትን ቅጥፈትን መሥርተው ሰዶማዊነትን ከመገንባትና ትውልድ ከማጥፋት በቀር…ሌላው አውርቶ አደር- ከባሕር ማዶ ደቻሳ እየወቃ..እሬቻ ላይ ውሃ የሚረጨውና የሚመቀረው..የገንዘብ አቁፋዳ ይዞ እነኛው ጋሎች እግር ላይ የሚወድቀው ጋልኛን… ወደ ኤርትራዊኛ…ከዚያ ወደትግሪኛ በኋላም ወደ ኢህአዴግኛ ቀጥሎ ወደ ብሔር ሔረሰቦች የሚተረጉመው ሚስጥራዊ ግንኙነቱና ፅሑፎቹ እውቅና የሚያገኙት ከሕዝቦች(ህወአት)የሆነው የኦሮሞው የጉዲፈቻ ማደጎ ተስፋዬ ግበረእባብ…በማኅበር የታቀፉና በሻቢያህወአት ወታቦ የተቀፈቀፉ ፅንፈኛ ፀረሕዝቦችን በተለያየ አቅጣጫ አሰማርቷል…ከላይ ልጅና አለቃ(አለቅላቂ) ተክሌ ይህ ፅሑፍ የራሱ እንዳልሆነ ከኦሮሞ ዝምታ! ከሰላቢው ማስታወሻ ከሰላዩ ጉዞ ላይ የተቀዳ እነደሆነ ተናግሬአለሁ አልዋሸሁም!!!እደግመዋለሁ አልዋሽም! ለምን?የካናዳ ስደተኛ መጀመሪያ የቀኝና የግራ እግሩን ጫማ አይለይምና!!!ካልጋሪ፩ ኦታዋ፪ ቶሮንቶ፫ አሜሪካ ከተሞች፬ የሚንቀዠቀዥ በከናዳ መንቀሳቀስና መዘዋወር ሙሉ መብት ቢኖርም በካናዳ ሳይንስ የአዕምሮ በሽተኞች.. ሱሰኛና ..ሴሰኞች ..አጭበርባሪዎች ይላቸዋል። ፖለቲካውም አማሳይ/ሸቃይ ይላቸዋል!።
****The Inexhaustible Eritrean Poison – On Tesfaye Gebreab (Dr. Assefa Negash ) በሚል አርዕስት ግረጌ (የሰለሙና ወጎች የሚል የጋላ የጉዲፈቻው ወሬ ተያይዞ ቀርቧል)
***አንድ ቀን ግን ያለቀጠሮ በአጋጣሚ አስመራ እህል ተራ ተገናኘን። ሳያየኝ ከጀርባው እንደ ቀዌሳ ድምፅ አጥፍቼ ተጠጋሁት፣ ( ለመሆኑ ማን ከማን ጋር ይሰራል..ይሳረራል..ይሰረስራል…ለመሆኑ ጆሌ ቢሸፍቱ ፓርላማ ይውላልን?)
“ግንቦት 7 እህል ተራ ምን ያደርጋል?” ብዬ ስናገር ፈጥኖ ዞረ።
እኔ መሆኔን ሲያውቅ ወቅታዊ ቀልድ ቀለደ፣
“እየሰለልከኝ ነው እንዴ?”
በጣም ስቄ መልስ ሰጠሁ፣
“አለማችን የምትመራው በስለላ ተቋማት ነው።”
ከዚህ ሁሉ የፉገራ ዴሞክራሲና የቁጭ በሉ ምርጫ
በሁዋላ እንኳ፣ ኢትዮጵያ ፈንጂ ላይ የተቀመጠች አገር መሆኗ እውነት ሆኖአል። የአንድነት ሃይሎች ራሳቸው
በአንድ የአመለካከት መስመር ላይ አይጓዙም። በብሄር የተደራጁ ወገኖችም ቢሆኑ ግባቸው ለየቅል ነው።
ህወሃት፣ ኦነግ እና ግንቦት 7 ከፊታችን አሉ እንበል። በርግጥ አርበኞች ግንባር፣ ኦብነግ፣ መድረክ፣ ዴምሕት፣ ኢህአፓ እያሉ መቀጠልም ይቻል ይሆናል። የመጪውን ዘመን የሃይል አሰላለፍ ለመተንበይ የፖለቲካ ድርጅቶች በይፋ በሚታወቅ ፕሮግራማቸው ሳይሆን፣ በድብቁ እና በእውነተኛው አመለካከታቸው ለያይቶ ማየቱ ይበጃል።***(ጋሶ ጊዳዳ..ቡልቻ ደመቅሳ…ሊ/ጠበብት በየነ ጴጥሮስ ጃዋር መሀመድ፣ተስፋሚካኤል አበበ፣ ሌንጮ ለታ ቃለ ምልስ ሄዳችሁ አንብቡ…አድምጡ!)ህወአት/ኢህአዴግ ኮፒ ፔስት! አንድነት ፓርቲና አመራረሮች ባማራ ተፈርጀዋል አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው!!። የተጠመደላቸውን መጥመድ ተመልከቱ **” በቅርብ ከማውቃቸው የኦነግ አባላት ጋርም በጉዳዩ ላይ ተወያይተንበታል። ጉዳዩ ሲጀመር “ኦሮሚያን መገንጠል የመጨረሻ ግብ መሆን የለበትም።” ይላሉ። በአንፃሩ ደግሞ “ኢትዮጵያን ጠቅልለን የመግዛት ፍላጎት የለንም” ይላሉ። በዚህ መካከል “የደቡብ ኢትዮጵያ” አሳብ ብቅ ይላል። የኦሮሞ ህዝብ ከደቡብ እና ከምእራብ ህዝቦች ጋር ተመሳሳይ የጭቆና ታሪክ አለው። ኢትዮጵያ የሚለው ስም “ጠይም” ወይም “ጥቁር” ማለት ከሆነ ደግሞ ቃሉ ለኦሮሞና ለደቡቦች ይቀርባል። ስለዚህ ከደቡብ ብሄረሰቦች፣ ከኦጋዴኖች፣ ከወሎ፣ ከሃረሪዎች፣ ከቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ጋር ግንባር በመፍጠር፣ ዋና ከተማቸውን “ፊንፊኔ” በማድረግ “ደቡብ ኢትዮጵያ” የተባለች አገር መመስረት እንደሚችሉ ይናገራሉ። ይህ አሳብ ከእነ ሌንጮ ለታ አዲስ እንቅስቃሴ ጋር ይቀራረባል።!
***ሶስተኛው ግንባር “የአንድነት ሃይሎች” በአብዛኛው የአማራዎች ሲሆን፣ ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ተቀላቅለው የተወለዱትን፣ ማለትም “ኢትዮጵያዊ” መባሉን ብቻ የሚመርጡትንም ጨምሮ ያቀፈ ነው። አማራ ያልሆኑ እንደ ቡልቻ ደመቅሳ፣ነጋሶ ጊዳዳ፣ ሃይሉ አርአያ እና በየነ ጴጥሮስ ያሉ የፖለቲካ ሰዎች የሚመሯቸው ድርጅቶችም ከአንድነት ሃይሎች ማእቀፍ ውስጥ ይካተታሉ።መረራ ጉዲናት ክክለኛው አቋሙ በግልፅ አይታወቅም። ከሁለቱም ተቃራኒ ሃይሎች ጋር ተግባብቶ ዘልቆአል። የአንድነት ሃይሎች “የኢትዮጵያን የቀድሞ የግዛት ክልልና አደረጃጀት እንደነበረ አስጠብቀን፣ አማርኛ የመግባቢያ ብሄራዊ ቋንቋችን ሆኖ፣ ኢትዮጵያውያን ተብለን በጋራ መኖር እንችላለን”ይላሉ። በጥቅሉ ሲታይ የቀድሞው ቅንጅት እና ኢህአፓ የዚህ አመለካከት ዋነኛ ባለቤት ሊባሉ ይችላሉ።>>>>
****“ዱጋሳ በከኮን የማያውቅ፣ በሌንጮ ለታ ይደነግጣል!” እንዲሉ እኔ ስለራሴ እስከማውቀው የአማራ ህዝብ ባለውለታ ስለመሆኔ ነው። ሊመጣ የሚችለውን አደጋ፣ በርግጥም አሁን እየታየ ያለውን የአደጋ ፍንጭ አስቀድሜ፣ “የቡርቃ ዝምታ” ላይ ጠቁሜ ነበር። አክራሪ “የአንድነት” ፖለቲከኞች ትምክህታቸውን ቀንሰው የመቻቻል ፖለቲካ እንዲጀምሩ መክሬያለሁ። አሁንም እመክራለሁ። አኖሌ ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ መካድ መፍትሄ አይሆንም።ድርጊቱ መፈፀሙን ማመን እና ዳዴኡኦ በገነባው ሃውልት ስር የይቅርታ እቅፍ አበባ ማኖር ይገባል። የተፈፀመውን መካድ ዋጋ የሚያስከፍል ይመስለኛል። በርግጥም ውጤቱን እያየነው ነው። Harma muraa Annoleeን እየዘፈነ የሚያድግ የኦሮሞ ልጅ፣ በተጨማሪ በአባቶቹ ላይ የተፈፀመው የሰቆቃ ታሪክ ሲካድ፣ መንጫ እንጂ እቅፍ አበባ ሊታየው አይችልም። ከዘረኝነቱ አረንቋ ለመውጣት “እርቅና መቻቻል” ያስፈልጋል። (ተክለሚካኤል…ጃዋር መሀመድን ለፈርድ ለማቅረብ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ ሲባል የምምህር ተስፋዬ ግበረእባብን ቃል ለውጦ” የእኛ ነገር፡ የተሸነፈ ርዕዮተ አገርና ገፊ ፖለቲካ” ሲል ሀገራችን ገፊ እነደሆነች የተሸነፈች ሀገር እንደሆነች…ፖለቲካ በፓል ቶክ የሚያስተምረው ወጣት ተንታኝ( ወደፊት ጠ/ሚ ሊሆን የተመኘው ውርጋጥ የሜንጫ አብዮተኛ ታቅፎ ከመሳምና ከማባባል ይልቅ ተገፍቶ ፀረ-ሕዝብ፣አሸባሪ፣ፅንፈኛ ሊሆን ጦሩን ማዘጋጀቱን ገልብጦ ፃፈው። ሌባ ነህ በለው!**(የተስፋዬን ገብረእባብ ፅሑፍ በደንብ አንብቡ) ከኤርትራ አስከ ኬንያ..ከሞቃዲሾ አስከ ኤርትራ ቤንሻንጉል ጠላትና ወዳጆቻችሁን ኢህአዴግ ቢሮ ሳትሄዱ ፓርላማ ሳትገቡ በማኅበር ሳትታቀፉ በራሳችሁ ድረገፅ ከሌቦች ተረዱ!ተማሩ!ከዚህ ቀጥሎ ባይጋ ፎረም ተፅፈው የሚለጠፉ በኢቲቪ ሽመልስ ከማል ስብሃት ነጋ..ሬድዋን ሁሴን..በረከት ስምኦንና አዜብ መስፍን ተናገሩትን አስተካክሎ በፓል-ቶክ፣ከተቃዋሚ ከድህረገጽ ከኦሮሞ ቁቤ(የእቁብ ልጆች)የጃራ ጎረምሳና ኤርትራ ሚስጥር አቀባዮቹ ከኢህአዴግ ውስጥ ፋልፋይ አፕዲዮ..ኦፍዲዮ የቃረማትን መልሶ ሲተፋው አንብቡ!…
**<<በአባ ታጠቅ ካሳ ዘመዶች የተገነባው የአንዳርጋቸው ጦር፣ ከ“አርበኞች”ና ከ“ዴምሕት” ጋር ግንባር ፈጥሮ በጌምድርን ሲቆጣጠር፣ “የቋራው አንበሳ – በ200 አመቱ ቢያገሳ – ስንቱን! ቀሰቀሰውሳ” የሚል ነጠላ ዜማ እያዜመ ከሰሜን አሜሪካና ከአውሮፓ፣ ወደ ጎንደር የሚፈስ የብረት ጎርፍ በአሳብ ማየት ይቻል ይሆን? ወይ ደግሞ ኦነግ (ABO) ሌንጮና ዲማን ሸገር ላይ አስቀድሞ በስውር ተክሎ ሲያበቃ፣ በባሌና በሶማሌ ግንባር ብቅ ይል ይሆን? ኦነግ Odaa ባንዴራውን በጋራሙለታ እና በጭላሎ ተራሮች አናት ላይ እየተከለ፣ Harma muraa Annoleeን እየዘፈነ ወደ ፊንፊኔ ሲገሰግስ በአይነ ህሊናችሁ ተመልከቱ። አሊያም ይልቃል ጌትነት ሳይቀደም ቀድሞ፣ በአራዳውና በፈረሰኛው ጊዮርጊስ እርዳታ፣ ሲተከል እንጂ ሲወረወር የማይታየውን ሰማያዊ ጦር ወርውሮ የወያኔን የልብ ትርታ ማቆም ከቻለ፣ እንደምኞቱ ነብርና ፍየል ተደጋግፈው የሚተኙባት፣ ሰላም ቁርሷ፣ ፍቅር ምሳዋ፣ እስክስታ ራቷ የሆነች ሰማያዊት ኢትዮጵያን ያለምንም ደም መመስረት ይቻለው ይሆናል። ነገን ማንም አያውቃትም! ምናልባት ይህ ሁሉ ወግ የእሳት ዳር ተረት ሆኖ ሲያበቃ፣ የዳግማዊ ወያኔ የልጅ ልጆች፣ ሳልሳዊ ወያኔ ተብለው እስከ 3000 ምእተ አመት በጠመንጃ እየቀጠቀጡ ሊገዙ ይችላሉ።…. የጦርነት መንገድ የመጨረሻ አማራጭ ነው። ወደ መጨረሻው አማራጭ ላለመድረስ የተደረገው ሙከራ በተደጋጋሚ መክሸፉ ያሳዝናል። በጣም ያሳዝናል። ቢቻል አሁንም የመጨረሻውን አማራጭ ላለመጠቀም መሞከር ይገባል።(ጃዋርና ሌንጮ አንድ ባንዲራ ይዘው ..አልተናገርኩም ወይ እዚሁ ብው ብዬ የእባቡ ቆዳ አሁን ደግሞ ታየ የውስተናው እሳት ከውች እያጋየ….ጃዋር…ኢትዮጵያ ከኦሮሞሚያ ትውጣ! ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊ አደለንም፣ ኢትዮጳያዊነት የአማራ ብቻ ነው፤ ፷፭ ከመቶ ሀብትና ዕድገት የኦሮሞ ቡና ነው! ኢትዮጵያዊነት በግድ የተጫነብን ነን..፺፱ ከመቶ የኦሮሞ ሙስሊም እንጂ የሌላ ሙስሊም ድምፅ የለም! ሲል ሌንጮ ለታ..ቡልቻ..ነጋሶ (ቋንቋ፣ መሬት፣ባንዲራ፣ ሥልጣን፣ አግኝተናል መከላከያውና መገንጠል ቀርቷል ከውጭ መሆኑ ቀርቶ ከውስጥ ሆነን እንታገላለን” ማንን? ለምን? ምን? ይታገላሉ? ብዬ ነበር። (አንድነት የሚባል ፓርቲ (ቃል) እንደአማራ ህዝብ መሰባሰብ ማንሰራራት (ኢትዮጵያዊነት!) ተቆጥሮ አሁን በግልና በኅብረት(በጋራ) (በደቦ) ይጠፋል ማለት ነው። እንኳን ከመለስ የቡድን (አንድ ብሄር፣ ጓደኛ፣ ዘመድ፣ አበልጅ፣ አብሮአደግ፣ አመራር) ወደ ኅይለመለስ የኅብረት አማራር( ብሔር ብሔረሰብ ከፊት ሻቢያህወአት ከኋላ የሚነዳው የደቦ አመራር አሸጋገራችሁ፡ (ከፊትም፣ ከኋላም ሆናችሁ ደግፉኝ ምሩኝ በጠ/ሚ ማዕረግ የብሄር ብሄረሰቦች ሊቀመንበር የሻቢያህወአት ጉዳይ አስፈፃሚ ኀይለመለስ እያለቀሱ ከተናገሩት የተወሰደ በለው!! እንቢኝ በል/በይ! እንቢኝ ባልን ነው ታፍረንም ተከብረንም የኖርነው!የምንኖረውም!
ዘንድሮ አለ ነገር በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2014/01/31/511-4/

የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከሃገር ፈረጠጡ


(ዘ-ሐበሻ) ራሳቸው በጠሩት ግምገማ፣ ራሳቸውን አስገምግመው ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸው የንጽህናቸው ውጤት መሆኑን ሲናገሩ እንደነበረ የሚነገርላቸውና በአንድ ወቅት በጋምቤላ ስለነበረው ጭፍጨፋ ተጠያቂ ነህ ሲባሉ “መሳሪያውን ያቀበለው መለስ ዜናዊም መጠየቅ አለበት” ብለዋል የተባሉት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትና የአሁኑ የፌዴል ጉዳዮች ሚ/ር ደኤታ አቶ ኦሞት ኦባንግ ከሃገር መፈርጠጣቸው ተሰማ። omot obang
በስልጣን ዘመናቸው ፕሬዚዳንቱ የክልሉን ደን እያስጨፈጨፈና ህዝቡን እያፈናቀለ ስላለው የመሬት ሽያጭና ነጠቃ የክልሉ እጅ የለበትም በሚል የተናገሩት ኦሞት ሂይውማን ራይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት ላይ በክልሉ ስለሚካሄደው የመሬት ነጠቃ አቶ በረከት ስምኦን በበኩላቸው ምላሽ ሲሰጡ በክልሉ ከሶስት ሚሊዮን ሄክታር በላይ ባለቤት የሌለው መሬት መኖሩን መናገራቸው አይዘነጋም።
ኦሞት ኦባንግ ከሃገር እንዳይወጡ ከፍተኛ የሆነ ጥበቃ ሲደረግባቸው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በተለይም በጋምቤላ ክልል ስለተፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋዎች በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ምስክር ይሆናሉ በሚል ፍራቻ በሕወሓት/ኢሕአዴጎች ከሃገር እንዳይወጡ ይፈራ እንደነበርና የፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ደኤታ የተደረጉትም “ጠላትህን አታርቀው፤ አቅርበውና እንስቅቃሴውን ተከታተለው” በሚለው የፖለቲካ አካሄድ እንደነበር የውስጥ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ይህን በማስመልከትም አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለጋራ ንቅናቄ በአንድ ወቅት ባወጣው መረጃ “አቶ ኦሞት ካገር ከወጡ አቶ መለስና መንግስታቸው ላይ ምስክር ይሆናሉ። አቶ ኦሞት ከተሰደዱ በአካል ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምስክርነታቸውን መስጠት ግዳጃቸው በመሆኑ የህወሃት ሰዎች ስጋት አለባቸው። ስለዚህ አቶ ኦሞት በተቀመጠላቸው የስድስት ወር የሃላፊነት ዘመናቸው አድርጉ የተባሉትን እየፈጸሙ ይኖራሉ። የህወሃት ሂሳብ ይህ ቢሆንም በመጨረሻ ያልታሰበ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል እገምታለሁ። ምክንያቱም ነገሮች ተነካክተዋል” የሚል አስተያየት አስነብቦ እንደነበር ይታወሳል።
የሚኒስትር ዲኤታውን ኩብለላ በተመለከተ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተጠየቁት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም አቶ ኡመt በስራ ገበታቸው ላይ እንደሌሉ ማረጋገጣቸውን ገልጸው መስሪያ ቤታቸው ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝ ሲናገሩ አቶ ኡመትም ወደ ሃገራቸው መመለስ እንደማይፈልጉ መናገራቸውን ጨምሮ የመጣው መረጃ ሲጠቁም፤ አሁን ግን የት ሃገር እንዳሉ ለጊዜው ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ተጠቁሟል።
በጋምቤላ በተፈፀመው ጭፍጨፋ የሚከተሉት ሰዎች በዋነኝነት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።
1. አባይ ፀሀዬ (በጊዜው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የነበረ)
2. ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ (በጊዜው ሚኒስትር ደኤታ የነበረና በቦታው በመገኘት ጭፍጨፋውን ያስተባብር የነበረ)
3. ኮለኔል ፀጋዬ (በጊዜው በቦታው የነበረው ወታደራዊ ሀይል አዛዥ)
4. ኡመት ኦባንግ (አሁን ከሃገር የፈረጠጡት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል አስተዳዳሪ)።
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

ሰዎች በሀይማኖት ለምን ተልያዩ?




ኤሎሄ! ቅዱስ! ኤልሻዳይ! አዶናይ! ያህዌ! ጸባዖት! ኢየሱስ! ክርስቶስ! አማኑኤል! በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ሥም! አሜን!
አቤቱ አባት ሆይ ከእኛ ወገን ለአንተ እናት ሆናህ በእሷ በኩል በሥጋ ትዛመደን ዘንድ በመረጥካትና ስለብዙዎች ልቧ (አእምሮዋ) ሐዘንን (ነብዩ እንደተናገራት ፍላጻዎችን) ሁሉ ያስተናግድ ዘንድ ባጸናሀት፣ ቅድስት፣ ንፅህትና ዘላለማዊት ድንግል በሆነች እናትህ ማሪያም ሥም ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እለምንሀለሁ! አሜን!
ከዚህ በፊት ከእምነት ጋር በተያያዘ አንዳንድ መሠረታዊ ጥያቄዎች ለአንባብያን አንሲቼ ነበር፡፡ ዋናው ጥያቄ መንፈስ የሚባል ነገር አለ ወይ? የሚል ነበር፡፡ ከዚሁም ጋር  ሰይጣን የሚባል ነገር አለ ወይ? አኛ ማን ነን? እኔ ራሴ ማን ነኝ? የሚሉ ጥያቄዎችን ከነሙሉ የጥያቄዎቼ መነሻ ነበር ያቀረብኩት፡፡ ይህንን ጥያቄ በኢሜልም የላኩላቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም መልስ ሊሰጠኝ የደፈረ የለም ከአንድ ፈላስፋ በቀር!  በእግዚአብሔር እናምናለን ብላችሁ ከምታስቡት ምን ያህሎቻችሁ የሰይጣንንም መኖር እናውቃለን እንደምትሉ አላውቅም፡፡ እኔ ግን እግዚአብሔርን አምናለሁ ብዬ ከሚያስቡት ግን ሰይጣን የሚባል ነገር የለም ብለው ደረታቸውን ነፍተው ከሚናገሩት ስለነበርኩ አሁን ላይ ያለውን እውቀት ከፈላስፋው ስረዳ በጣም ነበር የደነገጥኩት፡፡ የጥንታዊው ፈላስፋ ከእግዚአብሔር ከሆንን ዓለም በሞላው በክፉ እንደተያዘ እናውቃለን የሚለው ንግግር ወደ አእምሮዬ የገባው ያኔ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ አንቢቤው ይሆናለ ግን ምን ዋጋ ነበረው፡፡ አዎ እርግጥ ነው ደግ እንዳለ ሁሉ ክፉ አለ! እግዚአብሔርን እናምናለን የምንል ሰይጣን እንደሌለ የምናምን እግዚአብሔርንም ማመናችን እውነት እንዳልሆነ ልንረዳው ይገባናል፡፡ እግዚአብሔር በሰው ልጆች ዘንድ በሕሊናቸው እንደሚወከል አምናለሁ፡፡ ሕሊናን መሸወድ በፍጹም አይቻልም፡፡ ሆኖም አንዴ ለማይረባ አእምሮ ተላልፈን ከተሰጠን በኋላ ሕሊናችንም ሊነጠቅ እንደሚችል አውቃለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ከለላ አይኖረንምና አእምሮአችን ሙሉ በሙሉ በክፉው ኃይል ይያዛል፡፡ ያን ጊዜ ማስተዋል የሚባል ነገር አይታሰብም፡፡ ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አእምሮአችን በእርግጠኝነት ትክክል እንደሆኑ ማሰብ ይችላናልና ወደትክክለኛው ነገር ለመመለስ ዕድል የለውም፡፡  
ከመጀመሪያው ሰዎች በአንድ የሰማይ አምላክ የሚያምኑ፣ በተለያዩ ጣዖታት የሚያመልኩ እንዲሁም ምንም እምነት የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በእርግጥም የሰው ልጅ አእምሮ አንድ ፈጣሪዬ ብሎ እንዲያምንበት የሚፈልገው ነገር ስላለ ያለ ምንም እምነት ለመኖሩ አጠያያቂ ነው፡፡ አእምሮአችንም እኛ በፈለግንው የሚታዘዝ ሳይሆን በሌላ ኃይል ቁጥጥር ሥር ያለ ነውና፡፡ እኔ አእምሮዬየን እቆጣጠራለሁ የሚል ካለ እንደተሸወደ ልጠቁመው እወዳለሁ፡፡ ይህ ሌላ የጠለቀ ትንታኔ ስለሚያስፈልገው ወደተነሳሁበት የሀይማኖቶች/እምነት መለያየት ልቀጥል፡፡  በአንድ እምነት ሥርም ሆነው ሰዎች የተለያየ የእምነት አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ እንደ መጽሐፍ ከመጀመሪያው አዳምና ሔዋን እኩል የእምነት አቅም እንዳልነበራቸው እንረዳለን፡፡ አዳም አምቢ ያለው ሰይጣን ወደሴቲቱ ሄዶ አታሏታልና፡፡ ከዚህ በኋላ ነው አዳም በሴቲቱ የተሸነፈው፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሁለት ተቃራኒ መንፈሶች ወደ ሰው ልጆች እንደ ገቡ ፈላስፎች ይናገራሉ፡፡ ቀጥሎ በዚያው ትውልድ በአቤልና በቃየን መካከል ያለ የእምነት ልዩነት በገሀድ ተገልጦ አናየዋለን፡፡ በአንድ እግዚአበሔር እናምናለን የሚሉት ሰዎች ሌሎች ጣዖታትን የሚያመልኩትን በሰይጣን ምሪት እንደሆነ ቢናገሩም እናምነዋለን የሚሉትን እግዚአብሔር ብዙዎች በትክክል ያገኙት አይመስልም፡፡ ብዙም ጊዜ ከጣዖት አምላኪዎቹ የተለየ እምነት ሳይኖራቸው አንዳንዴም ጣዖት ከሚያመልኩት በባሰ ለጣዖታት የተገዙ እግዚአብሔርን አናምናለን በሚል አፋዊ እምነት ብቻ  የሚኖሩ ጥቂት አይደሉም፡፡  
እንደ መጽሐፍ ትልቁ የእግዚአብሔር ተከታይ የሚባለው ሕዝብ የእስራኤል (ያቆብ) ነገድ ቢሆንም፣ ከጥንት ጀምሮ ብዙዎች ሊያውም እስራኤል ከተባለው ሕዝብ በተሻለ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ነገዶች እንደነበሩ እንረዳለን፡፡ ለዚህ ምሳሌ ብንጠቀስ የኛዎቹ (ኢትዮጵያዊ የተባሉት) እንደሆኑ የሚነገርላቸው የሙሴ አማት ዮቶር (ካህን ነበር)፣ ካህኑ መልከጼዴቅ (የክርስቶስ ምሳሌ የሚባለው) እንዲሁም ከሙአባውያን (ከኤሳው ነገድ) ወገን የሆነው ፈላስፋው በለዓም ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እንግዲህ የእነዚህ ሰዎች ነገድ ተብለው በኋላ የመጡት ትዎልድም እግዚአብሔርን ቢያንስ የተወስኑት ያመልኩት እንደ ነበር እንረዳለን፡፡ አንዳንዶቹም እስራኤል ከሚባለው ሕዝብ በተሻለ መልኩ እንደሚያመልኩ እንረዳለን፡፡ ለዚህም የበለዓም ዘር ተብለው የሚታመንላቸው ሰብዓ ሰገሎች ከእስራኤሎቹ በላቀ ሁኔታ ስለክርስቶስ ማንነትና መቼ እንደሚመጣ ጠንቀቀው የተረዱ መሆናቸውን እንደ ምስክር ልናቀርበው እንችላለን፡፡ በተቃራኒው እስራኤሎቹ ብዙ ጊዜ ከእግዚአብሔር አምልኮ እየወጡ እናያቸዋለን፡፡ ብዙ ተዓምራትን እያሳያቸውና መና ሳይቀር ከሰማይ እያወረደ እየመገባቸው እንኳን በእግዚአብሔር ማመንን አልቻሉም ነበርና፡፡ ይህ የሚያሳየን በምናየውም ነገር እንኳን ማመን እንደማንችል ጭምር ነው፡፡ የአእምሮአችን ጉዳይ በእኛ ቁጥጥር ሥር አደለም ከሚያሰኝ አንዱ መገለጫም ይሆናል፡፡ በትክክል ያወቅናቸውንም ነገሮች ለማሰብ የራሳችን ፍቃድ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በመጽሐፍ የምናነባቸው በሰዎች የተነገሩን ሁሉንም አወቅናቸው እንጂ አስተዋልናቸው ወይም አመንባቸው ለማለት አያስደፍርም፡፡ ብዙም ጊዜ አፋችን ያንን ያወቅንውን እየተናገረ አእምሮአችን ሌላ ያልተጻፈ ነገር ያነባል፡፡
ታላቁ ፈላስፋ በእግዚአብሔር የሆነች አንዲት እምነት/ሀይማኖት ብቻ እንዳለች ይናገራል፡፡ በገሀድ ጣዖትና ሌሎች ነገሮችን የሚያምኑትን ትተን በእግዚአበሔር እናምናለን የሚሉ የዛሬዎቹን የሀይማኖት ብዛቶች ስንመለከት ነገሩ እንዴ ነው? ከማለት አልፎ በሕይወታችን የቱ ይሆን ትክክሉ እያልን ውዥምብር ውስጥ እንደከተተን አረዳለሁ፡፡  አሁንም በጥንታዊያኑ የኦሪት ተከተዮችና በክርስትናው መካከል ያለውን ትተን በአንድ ክርስትና በሚባለው ሥር እንደ አሸን በፈሉት የእምነት ብናኞች ባክነናል፡፡ ይህ ሁሉ ግን አሁንም አንዲት እምነት የምትለውን የፈላስፋውን ብሒል ሊቋቋመው የሚችል አይመሰለኝም፡፡ ሁሏም በየፊናዋ ትክክለኛዋ የኔ ናት እያለች ትኖራለች እንጂ፡፡ ይሄው አንዲት እምነት ያለው ፈላስፋ ያቺ እሱ የተናገረላት እምነት ፍቀር፣ ሰላም፣ ወዘተ እያለ የበጎ ነገር ሁሉ ምንጭ እንደሆነች ይናገርላታል፡፡ እንግዲህ ዛሬ እምነት ነን የሚሉት ሁሉ ራሳቸውን ከፈላስፋው መስፈርቶች ጋር ሊመዝኑት ይችላሉ፡፡ የብዙዎችን የዛሬዎቹን የአምነት ጉዳዮች ስንመለከት አጀማመራቸውም አካሂዳቸውም አኔ ከማን አንሳለሁ በሚሉ ግለሰቦች ሀሳብ ተጀምረው ቀስ እያሉ ትልልቅ ጎራዎች ሆነው የጦርነት ያህል በእውንም ጦርነት ሳይቀር ከፍተው የተፋለሙ እየተፋለሙ የሚገኙ ናቸው፡፡ ብዙዎቹም ሠረታዊ የሆነ የፍልስፍና ልዩነት እንዳላቸውና እንደሌላቸው አያውቁትም፡፡ ተከታዮቻቸውም የጅምላ ተጓዥ እንጂ መሠረታዊ ነገሮችን (ፈላስፋው ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች) አይረዱም ለመረዳትም አይፈልጉም፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ያሉ ክፍፍሎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ አንግዲህ ፈላስፋው አንድ ጌታ ያለው በእሱ የሚያምን ሁሉ በአንዲት እምነት ጥላ ሥር እንዳለ የተናገረለት ሲሆን ብዙዎች ግን የየራሳቸውን ክርስቶስ ነው የሚያምኑት፡፡
ከመጀመሪያው ከእስልምና በፊት ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ሁለት ጎራዎች እንዳሉ እናያለን፡፡ የክርስትናና የአይሁድ ተብለው የተሰየሙ፡፡ ኋላ ደግሞ ክርስትናው ራሱ ዛሬ ካቶሊክና ኦርቶዶክስ ወደምንላቸው ተመነዘረ፡፡ ቀጥሎ የአይሁዳውያኑንና ክርስትናውን ያዋሀደ የመሰለው የእስልምናው እምነት መጣ፡፡ እነዚህ ሁሉ በጥቂት ግለሰቦች ማፈንገጥ ተጀምረው ወደ ትልልቅ የእምነት ጎራዎች እንደተቀየሩ እናስተውል፡፡ እስኪ እነዚህን ሶስት እምነቶች ብቻ እንመልከት፡፡ ሁላችንም ግን ሕሊናችንን ሳንሸሸው በቀጥታ እምነቶቹ እንመራባቸዋለን በሚሉት መጻሕፍት የተጻፉትን እንጋፈጣቸው፡፡  የካቶሊኩና ኦርቶዶክሱ ልዩነታቸውን በአዋጅ ቢከፍሉትም ያንንው አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ይከተላሉ፡፡ እስልምናው ደግሞ ቁርዐንን ይከተላሉ፡፡ ቁርዓኑም መጽሐፍ ቅዱሱም ስለክርስቶስ የሚሉት ነገር ግን ተመሳሳይ ነው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ የአንዱ እምነት ተከታይ ሌላውን በጠላትነት ሊያስመለክተው የሚችል አንዳችም ነገር የለም፡፡ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በድንግልና እንደተወለደ፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፣ ወደ ሰማይ እንዳረገ፣ በኋለኛውም ዘመን ለፍርድ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱሱም፣ ቁርዐኑም ይናገራሉ፡፡ ልዩነቱ በቁርዐኑ ሞቶ የተነሳው ክርስቶስ ሳይሆን እግዚአብሔር ልጁን ሊሰውረው ሌላ ሰው አይሁዶች እንዲገድሉ አድርጎ ልጁን ከሞት አተረፈው በኋላም ወደ ሰማይ ወሰደው የሚለው ነው፡፡ ወደ እምነቱ ስንመጣ በመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ አምላክ (እግዚአብሔር) እንደሆነ ይናገራል በእስልምናው ግን ነብይ እንደሆነ ይታመናል፡፡
ከመጀመሪያው በክርስትናው አማኞች (ካቶሊክና ኦርቶዶክስ) በውልም ግልጽ ባልሆኑ ልዩነቶች ጥላቻዎች ነግሰው እንደነበር እንጂ ተሳስቷል በሚል አንዱ ስለሌላው በፍቅር ለድህነቱ ሁሉንም ማድረግ ይችላል የሚሉትን አምላክ ስለፍቅር አልተገዳደሩትም ፡፡ ይባስ የሰው ልጆችን እልቂት ያስከተሉ ጦርነቶችን ቀሰቀሱ እንጂ፡፡ በክርስትናውና በእስልምናው መካከል ስናይም በክርስቶስ ስም ምክነያት ምንም ጥላቻ የሚፈጥር ነገር እንደሌለ እንረዳለን፡፡ ክርስቲያኖቹ አምላካቸው እንደሆነ ቢያምኑም ሙስሊሞቹም ነብያችን ነው ብለው ያምናሉና፡፡ ዛሬ ላይ ስናይ ግን በእስልምናው አለም የኢየሰሱ ክርስቶስን ስም መጥራት እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ እንግዲህ እናስተውል በኋለኛው ዘመን መጥቶ ይፈርዳል ተብሎ በቁርዓናቸው የተጻፈላቸው የኢየሱስ ክርስቶስን ሥም ለመስማት እንኳን ፍቃደኛ ያለመሆናቸውን አስቡ፡፡
ቀጥሎ ወደ ተፈጠሩት የክርስትናው ክፍፍሎች ስናመራ በካቶሊኮችና ዛሬ በጅምላው ፕሮቴስታነት በሚባሉት መካከል የሆነውን የጎራ ልዩነት እናያለን፡፡ ከመጀመሪያው (በነማርቲን ሉተር ጊዜ) የዚያን ያህል ባይሆንም እየቆየ በመጣ የእርስ በእርስ ጥላቻ የሁለቱ እምነቶች ልዩነት ሰፍቶ ፍጹም ተቃራኒ ሆነዋል፡፡ ይህ የፕሮቲስታን እምነት በተመሳሳይ የኦርቶዶክሱንም የሚቃረን ሆኗል፡፡ ካቶሊኮቹና ኦርቶዶክሶቹ የቀዱሳንን ምልጃና ተራዳኢነት ሲያምኑ ፕሮቲስታንቶቹ ግን ኢየሱስ  ብቻ እንጂ ሌላ አያስፈልግም ባይ ናቸው፡፡ በተለይም ደግም ከክርስቶስ እናት በድንግል ማርያም ጋር በተያያዘ ተቃርኖው የበዛ ነው፡፡ ልክ የእስልምናው አማኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥም ሲነሳ እንደሚያስደነበረው የፕሮቴስታንቱም እምነት ተከታይ የክርስቶስ እናት የማርያም ሥም ሲነሳ ይደነበራል፡፡ ያስቆጣዋልም፡፡ አሁን አሁን ይባስ የክርስቶስን እናት በግልጽ የሚሳደቡ የፕሮቲስታንት ተከታይ ሰባኪዎችንም እንሰማለን፡፡ ኢየሱሰ ጌታ ነው እያሉ የሚፎክሩት የእምነቱ ተከታዮች የቱ ኢየሱስ? የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ? ተብለው ሲጠየቁ ሌላ ድንጋጤ ይፈጥርባቸዋል፡፡ በክርስትናው መጽሐፍ ብዙ ኢየሱሶች እንደሚነሱ ተጽፏል፡፡ የክርስትናው ኢየሱስ ግን በእርግጥም በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ፣ በስጋ የድንግል ማርያም ልጅ የሆነው ብቻ እንደሆነ እናውቃለን፡፡
በተመሳሰይ በአገራችን ደግሞ የተሀድሶና የድሮ ኦርቶዶክስ በሚል ጎራ የተፈጠሩ ዛሬ የምናያቸው አሉ፡፡ ተሀድሶዎቹ ከፕሮቴስታንትና ከኦርቶዶክስ መሐከል ላይ የቆመ የሚመስል እምነት አራማጅ ናቸው፡፡ በቅርቡ ኢየሱስ ጌታ ነው! እያሉ እንደሚፎክሩት በኦርቶዶክስም ውስጥ ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት አለም አይድንም በሚል ፉከራ ምክነያት በብዙዎች ዘንድ ክርክር እንዲነሳ ሆኗል፡፡  እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስም ጌትነት፣ የወላዲተ አምላክም አማላጅነት አውነት ነው፡፡ ግን እነዚህን መፈክሮች ማንሳቱ ለምን ተፈለገ በማንስ መፈክሮቹ ተነሱ ብንል፡፡ ችግሩ የመጣው ከውስጥ በሆነ የእምነት ማጣት በአፍ ራስን ለመሸንገል በሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው እያለ የሚለፈልፍ ሰው በትክክልም በኢየሱስ ጌትነት ከውስጥ ማመን እንዳቃተው እንረዳለን፡፡ ብቻ ለሌሎች ይምሰል ወይም ከሱ ሌላ እምነት የሚከተሉ የመሰለውን ለመቃረን በአፉ ይፎክራል፡፡ በተመሳሳይ ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት አለም አይድንም ብለው አብዝተው የሚለፈልፉት ከውስጥ የሆን የወላዲተ አምላክን አማላጅነት መረዳት እንደቃታቸው እናስተውላለን፡፡ ከውስጥ ለአባቷ ፍቀር የሌላት ልጅ አባቷን አስሬ አወድሀለሁ በማለት የውስጥ ማጣቷን ለማካካስ የመታደርገው አይነት ነው፡፡ አባቷን በጣም የምትወደው ግን ሥሙን እንኳን ደጋግማ ከጠራች የሚያልቅባት ስለሚመስላት ትሰስታለች፡፡ በተመሳሳይ ፍቀረኛዋን/ውን አወድሀለሁ/ሻለሁ በማለት የሚያበዛ ነው፡፡  በሳይኮሎጂ ይህ ሕክምና የሚያሻው ችግር ነው፡፡ ትክክለኛውና ከውስጥ የሆነው ሁሉም በመሳሳት ስለሚሆን በቁጠባ ነውና፡፡  የክርስቶስም ጌትነት የእናቱም አማላጅነት በአፍ በሚሆን ልፍለፋ ሳይሆን እጅግ በሚያስጨንቅ ፍልስፍናና ጥበብ ውስጥ የምናስበው ከባድ ጉዳይ ነውና፡፡ ክርስቶስ ጌታ መሆኑን ሁሉም ያውቃል ግን ምን አይነት ጌታ፣ የክርስቶስ እናት ድህነትን የምታሰጥ አማላጅ እንደሆነች እናውቃለን ግን እንዴት፡፡ ክርስቶስ (በባሕሪው አማላክ የሆነ) በሥጋ እንደመጣ (ከእኛ ወገን (ሰው) የሆነችውን እናቱን ባሕሪ እንደተዋደ) ስንረዳ ያኔ ሁሉም ይገባን የሆናል፡፡
እንግዲህ ሀማኖቶች የእኔ ሀሳብ ከአንት ይበልጣል በሚል ፉክክር፣ ያም ፉክክር በሰይጣን አጋዥነት ወደ ገዘፈ ልዩነት አየሰፋ፣ ጎራ በመሆን እንደተፈጠሩ እናምናለን፡፡ ከመጀመሪያው ፈላስፋው ለሐይማኖት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች ለአንዳቸውም የሀይማኖት መፈጠር ምልክት አይሆኗቸውም፡፡ ሰላም፣ ፍቅር፣ ትዕግስትና የመሳሰሉት በሐይማኖት በለያየት ዘመን የሉም፡፡ በተቃራኒው ግን ፀብ፣ ክርክር፣ ትዕቢትና አልፎም ጦርነት መገዳደል የመሳሰሉት ግን በእርግጥም በእነዚህ ወቅቶች በዝተዋል፡፡
ለሁሉም ሚስጢራትን ሁሉ የሚገልጽ አምላክ ማስተዋልን ይሰጠን ዘንድ በፊቱ እንንበርከክ፡፡ አቤቱ አባት ሆይ አእምሮአችንን ክፈት!
የታላቋ ቀን ልጅ ጥር 22 2006 ዓ.ም (Son of the great day January 30, 2014)          
   

ድንበሩ፤ ጎንደር - መተማ (ትንሽ ወግ)

ድንበሩ፤ ጎንደር - መተማ (ትንሽ ወግ)
መቼ መሰላችሁ በ 1999 ሚሊኒየሙ እንደ ነገ ሊጠባ እንደ ዛሬ በሉት እኔ እና ጓደኞቼ ወደ መተማ ለአንድ ስራ ተጉዘን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ፤ ወደ መተማ ስትሄዱ ጭልጋ ላይ ከደረሳችሁ በኋላ በጣም ብትንደረደሩ መተማን አልፋችሁ ሱዳን ጋላባት የመግባት እድላችሁ የሰፋ ነው፡፡ የሱዳኗ ጋላባት እና የእኛቱ መተማ ማለት አፍንጫ እና አፍ እንደማለት ናቸው፤ አረ አፍንጫ እና አፍ በጣም ይራራቃሉ… እኛም እዛ ለመድረሳችን ማስረጃ እንዲሆነን ከ ሱዳኗ ጋላባት ገበያ ሸበጥ ጫማ ገዝተን ነበር፡፡

በዛ ጉዞ ከነበረን ትዝታ ውስጥ ፈፅሞ የማይረሳን አርበኞች ግንባር ፈፀማቸው የሚባሉት ጀብዱዎች እና የአካባቢው ህዝብ ለግንባሩ የነበረው አድናቆት እና ፍቅር ነበር፡፡ ቦታው አርበኞች ግንባር አባላት ሲመቻቸው መሳሪቸውን፤ ሳይመቻቸው ደግሞ ቀበቷቸውን ታጥቀው የሚንጎማለሉባት ስርፋ ነበረች፡፡

በአካባቢው ከሱዳን ጋር ስላለን ድንበር ጉዳይ ከመተማ ወደ ውስጥ ገብተው ያሚገኙ ገበሬዎች ጥቂት ጥቂት አጫውተውኛል፡፡

በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር ሰፊ አውላላ ሜዳ ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ፕሮፌሰር መስፍን ሲናገሩ እንደሰማነው ሁለት አይነት ድንበር አለ አንደኛው መንግስት የሚያውቀው ሌላኛው ደግሞ ህዝቡ የሚያውቀው ነው፤ እንደ ፕሮፍ አባባል …ህዝቡ ይሄ ነው ሀገሬ የሚለው እና መንግስት ይሄ ነው ካርታዬ የሚለው አንዳንዴ ይለያያል አንዳንዴ ደግሞ ይመሳሰላል፡፡

የአካባቢው ገበሬዎች ስለ ድንበሩ አካባቢ ሲያወሩ አካባቢው ለዘመናት ሲጋደሉበት የነበረ አካባቢ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የመጋደሉ መነሾ ጎንደሮች የዘሩትን የሱዳን አርብቶ አደሮች በከብት ሲያሳጭዱት በሚነሳ ግጭት መሆኑን ስሙን የዘነጋሁት ገበሬ አውግቶኝ ነበር፡፡ ገበሬው እንደነገረኝ አካባቢው ላይ ሱዳኖችም የእኛ እኛም የእኛ የምንለው ሰፊ መሬት አለ እኛ እህል እንዘራበታለን እንርሱ ደግሞ ከብት ይዘሩበታል፡፡ በዚህም የተነሳ የሀገሬ ገበሬ እና የጎረቤታችን አርብቶ አደር ማዶ ለማዶ ሆነው ይታኮሳሉ፤ ይጋደላሉም፡፡

ባለፈው ጊዜ አንድ የሱዳን ድረ ገፅ ጽፎት አንዱ ወዳጄ ደግሞ አጋርቶን እንዳየሁት ሱዳኖች ከኢትዮጵያ ጋር የድንበር ግጭት ደጋግሞ ሲከሰት የነበረበት አካባቢ ችግር መፈታቱን ጽፈዋል፡፡ አክለውም በአካባቢው ላይ መንግስታቸው ወደ አስራ ሰባት መንደሮችን ሊያሰፍር እቅድ መያዙን አውርተዋል፡፡

ማን መሬት ላይ ማን ይሰፍራል… ይሄ በውል አለየም፡፡ ሰዳኖች የገዛ መሬታቸው ላይ ነው ይሄንን መንደርተና ሊያሰፍሩ ያቀዱት ወይስ የገዛ አውላላ ሜዳቸውን ሊስጠብቁ ነው… (ትላንት ስለ ፕሮፍ ስናወራ ያነሳነውም ይሄንኑ ነው)

የሀገሬ ሰዎች መሬታቸው ላይ እንኳንስ መንደር መስርተውባቸው ይቅርና ሳሬ ላይ ከብት ተለቀቀ ብለው የሚታኮሱ ናቸው፡፡ መንግስታችን በአካባቢው ላይ ያለውን እንደ አርበኞች ግንባር የመሳሰሉ ታጣቂዎችን ለመቆጣጠር ሲል መሬቱን ለሱዳኖች "እንሆ በረከት" ሊል አይችልም ብሎ የሚከራከር ካለ እርሱ ኢህአዴግ መስተፋቅር ያሰራችበት ምስኪን አፍቃሪዋ ብቻ ነው፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን መንግስት አይምሮውን ጨለፍ አድርጎት መሬቱን ለመስጠት ሲስማማ የአካባቢው ገበሬዎች የሚያስቀምሱ ናቸው ብሎ ማሰብም ከባድ ነው፡፡

ትልቁ ቁምነገር መንግስት እንዲህ አይነት ትልልቅ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ሲያደርግ ለህዝቡ ግልጽ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ገንዘብ ሲቸገር ብቻ ቦንድ ግዙልኝ ብሎ ወደ ህዝቡ መምጣት ከመንግስትነት ወደ የኔብጤነት ዝቅ የሚደርግ አሰራር ነው!

በነገራችን ላይ ለነገ ጎንደር ላይ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራው ሰልፍ መልእክትም ይሄው ነው፡፡ መንግስት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በመንሾካሾክ መስራቱን ያቁም… ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለበት አስራር ይስፈን! 


abetokichaw