ከቅድስት አባተ
(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 57 ላይ ታትሞ የወጣ)
የሴቶች ጉዳይ ብንላቸው የምንግባባቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ ወር ጠብቆ ፅንስ ለመፍጠር ዝግጁ
መሆናቸውን ለመናገር የሚመጣው የወር አበባ ነው፡፡ እጅግ በርካታ የሆኑ እና ሴቶች የወር አበባቸው በሚመጣ ወቅት
ከቀላል መነጫነጭ አንስቶ ሁሉን ነገር እስከመጥላት የሚያደርስ የህመም እና ምቾት የማጣት ስሜት ይገጥማቸዋል፡፡
ሁነቱ ተፈጥሯዊ የሆነና ለክፉ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ይሁንና የዚያን ሰሞን ስሜት እና ህመም ማቅለል እና ንጭንጩንም
ጭምር ማቃለል እንደሚቻል ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡ የዛሬው ትኩረታችንም ይህ ነው፡፡ ቀላል የሚባሉ እና የህክምና
ጥበብን እጅግም በማይጠይቁ ስልቶች የወር አበባ ሰሞንን ማቅለል የምትችይባቸውን ስልቶች እነሆ ብለንሻል፡፡
የወር አበባ ለምን?
ተፈጥሮ የወር አበባን ስትፈጥር መራባትን አስባ ነው፡፡ ሴቶች አዲስ ነፍስ የመፍጠር ስልጣን በየወሩ
ይሰጣቸዋል፡፡ አብሮ ለመፍጠር የተዘጋጀ ጥንድ እስካለ ድረስ ይህ ይሰራል፡፡ በየወሩ የሚዘጋጁት እንቁላሎች
የሚዳብርና ፅንስ የሚያደርጋቸው የወንድ ዘር ሲያገኙ እዚያው ሆነው ጽንሱ ሲፈጠር ያ ካልሆነና ሴቲቱም በመፀነስ
እቅድ ውስጥ ካልሆነች ደግሞ እንቁላሎቹ ወደ ውጪ መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ እንግዲህ በየወሩ ከደም ጋር ተቀላቅለው
የሚወጡት እነዚህ እንቁላሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክስተት በብዙ ሆርሞኖችና የሰውነት ውስጥ ውስብስብ ተግባራት
የሚከወን እንደመሆኑ ብዙ ለውጦችን ሴቶች ማስተናገዳቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቢያንስ 80 ከመቶ
የሚሆኑ የዓለማችን ሴቶች ከቀላል ህመም አንስቶ እስከ ከበዱት ድረስ በወር አበባ ሰሞን ይገጥማቸዋል፡፡ እጅግ
አሳማሚ የሆድ ቁርጠት፣ የስሜት መቀያየር፣ መነጫነጭ ራስ ምታት እና ሌሎቹም የሚጠቀሱ ማሳያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን
የወር አበባ ሰሞን ችግሮች ማቅለያ ዘዴዎችን ታዲያ የህክምና ሰዎች ለሴቶች ሁሉ ያጋራሉ፡፡ የዲስከቨሪ መፅሔት እና
ውሜን ሄልዝ ኤክስፐርቶች ካነሷቸው መካከል ዮጋ ማዘውተር ጨው መቀነስ፣ አመጋገብ ማስተካከልና አንዳንድ ቀለል ያሉ
መድሃኒቶችን መውሰድን ያነሳሉ፡፡
የወር አበባ ሰሞን ጨው ቀንሺ
በወር አበባ ሰሞን እንቁላሎች ዝግጁ ሆነው የሚጠብቁት ልጅ እንደሚፈጠር በማሰብ ነው፡፡ ስለሆነም ጽንሱ ቢፈጠር
የሚያስፈልገውን የጨው ፈሳሽ እና ኤሌክትሮላይት ለመሙላት ሰውነትሽ ብዙ ጨው የዚያን ሰሞን ይኖረዋል፡፡ ብዙ ጨው
መኖሩ ደግሞ ውሃን የመሳብና በሰውነት ውስጥ መጠራቀምን ይፈጥራል፡፡ ይህ በራሱ የሚፈጥረው ሰውነትን የማስጨነቅ
ተፅዕኖ ስለሚኖር ከውጪ የምትወስጂውን ጨው የወር አበባ ከሚመጣባቸው ቀናት አስቀድመሽ ቀንሽ፡፡ በተለይ የተጠባበሱ
ምግቦች ውስጥ ከፍተኛ የጨው ክምችት ስለሚኖር ከእነዚህ ምግቦች በዚያ ሰሞን መቆጠብ ጥሩ እንደሆነ ባለሞያዎቹ
ያሰምሩበታል፡፡
ዮጋ እንደ መዝናኛም እንደ መድሃኒትም
የወር አበባ ወቅትን ህመም ለማስታገስ መዝናናት፣ ውጥረትን መቀነስ እና የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ
የሚመከሩ መላዎች ናቸው፡፡ ዮጋ ደግሞ ሁሉንም በአንድ አዋህዶ የያዘ የተመስጦ ስፖርት ከመሆኑ አንፃር ቁጥር አንድ
ተመራጭ ስፖርት ያሰኘዋል፡፡ ‹‹ዮጋ ስፖርት ብቻ አይደለም፣ አዕምሮና አካልን በአንድነት ከውጥረት መንጥቆ የሚያወጣ
መድሃኒትም ነው›› ይላሉ የዲስክቨሪ መፅሔት የህክምና አማካሪ፡፡ በኢንዲያን አካዳሚ ኦፍ አፕላይድ ሳይኮሎጂ
የጥናት መፅሔት ላይ የሰፈረ የጥናት ውጤትም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ያነሳል፡፡ ጥናቱ ዮጋ የስነ ልቦና እና የአካላዊ
መዝናናትን በማጎናፀፍ ከወር አበባ ወቅት ህመምና ምቾት ማጣት በመገላገል በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው
ይናገራል፡፡
ካልሲየምና ቫይታሚን ዲ ውጤት አላቸው
በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ውስጥ በዚህ ላይ ምርምር ያደረጉ ባለሞያዎች ቫይታሚን ዲ እና ካልሲየም ማዕድን
የወር አበባ ጊዜዎትን በእጅጉ ቀላል የማድረግ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በጥናቱ በየዕለቱ እስከ ስድስት መቶ
ሚሊግራም ካልሲየም የወሰዱ ሴቶች ዘንድ የወር አበባ ወቅት ህመሞች የሚባሉት እንደ ሆድ ቁርጠት፣ ራስ ምታት፣
የምግብ አምሮት እና የስነ ልቦና ጫናው በግማሽ ቀንሶ መገኘቱን በጥናታቸው ፅፈዋል፡፡ ይህ የካልሲየም መጠን አንድ
ብርጭቆ ወተትና አንድ ብርጭቆ እርጎ በጋራ ቢጠጡ የሚያገኙት ምጣኔ ነው፡፡ ባለሞያዎቹ ካልሲየምን በክኒን መልክ
መውሰድ ቢቻልም ተመራጩ ግን ከወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ማግኘቱ እንደሆነ አበክረው ያሳስባሉ፡፡ ቫይታሚን ዲ ተመሳሳይ
ተፅዕኖ እንዳለው ባለሞያዎቹ አስረድተዋል፡፡ እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶች ቫይታሚኑን ማግኘት ወር አበባን
ቀለል ያደርጋል፡፡
ለማይግሬይንና ራስ ምታቱስ?
በወር አበባ ወቅት የሚከሰተው ራስ ምታት ከወትሮው በተለየ አናትን የሚነቁርና ሁሉን ነገር የሚያስጠላ ሊሆን
ይችላል፡፡ ቀደም ሲል ያነሳናቸው የመዝናኛ እና ችግሩን የመቅረፊያ ስልቶች እየሰሩ ካልሆነ በባለሞያ የሚታዘዝ ህመም
ማስታገሻን መውሰድ ይመክራል፡፡ ምናልባት ሌላ ጊዜ ከሐኪም ትዕዛዝ ውጪ የምንወስዳቸው ማስታገሻዎች በዚህ በኩል
ውጤታቸው አርኪ ስለማይሆን ነው፡፡ ሌላ ማስታገሻ ለመጠየቅ ባለሞያን እንዲያዩ የሚመክረው በውጪ ሀገራት ለዚህ
ተብለው የሚሰሩ ልዩ ማስታገሻዎች አሉ፡፡ በእኛ ሀገር ፋርማሲዎች በስፋት የሚገኙ ባለመሆናቸው ባለሞያ መገናኛቸውን
ሊያመላክትዎት ይችላል፡፡
ፋይበር ያላቸውን ጠጠር ያሉ ምግቦች ጥቅም
ባለሞያዎቹ እንደሚሉት በወር አበባ መምጫ ሰሞን ህመሙን እና ሆድ ቁርጠቱን የሚያመጡት የሆርሞን ለውጦች የሆድ
ህመም እና ተቅማጥ ከሚያመጡት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ስለሆነም ሆድን ያዝ የሚያደርጉ እንደ ጎመን አጃ፣ ሙዝና
የመሳሰሉትን ምግቦች ብትወስጂ ሆድሽን ያዝ አድርገው የምግብ አምሮቶሽን ይገቱታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ዘንድ
የሚታየውንም የዚያን ሰሞን የሆድ መለስለስና መለስተኛ ተቅማጥ ለመቆጣጠር ያግዛሉ፡፡
በዚያ ሰሞን ዋና መዋኘት?
ብዙ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰሞን ከሰው ራቅ ብለው ቤት አካባቢ ሆነው ቢቆዩ ይመርጣሉ፡፡ የባለሞያዎች ሀሳብ
ግን ይለያል፡፡ ከሰው መቀላቀሉ እና ዘና ማለቱ ይመከራል፡፡ በተጨማሪም ዋና መዋኘት ከፍተኛ ጠቀሜታም እንዳለው
ጨምረው ያስረዳሉ፡፡ በዋና ወቅት በሰውነት እና በውሃው መካከል በሚደረገው ፍትጊያ የሚፈጠረው ግፊት የሆድ ቁርጠትና
የዚያን አካባቢ ቁስለት የሚመስል ስሜት አዝናንቶ የማፍታትና ህመምንም የመቀነስ አቅም አለው፡፡ በቀን ቢያንስ
ለ20 ደቂቃ ብትዋኚ ጥሩ ነው ተብሎ ተመክሯል፡፡ ነገር ግን የግድ ወደ ዋና ገንዳ እንድትገቢ አትገደጂም፡፡ የዋናው
ነገር ካልተመቸሽ በቤት ውስጥ መታጠቢያ ቤት ለብ ያለ ውሃ በገንዳው ሞልተሽ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነትሽን
ብታሳርፊው የዋናውን ያህል ባይሆንም ጥሩ ውጤት ታገኚያለሽ፡፡
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of
various information and content providers. The Website neither
represents nor endorses the accuracy of information or endorses the
contents provided by external sources. All blog posts and comments are
the opinion of the authors
ውድ የዘ-ሐበሻ የ እንመካከር አምድ አዘጋጅ፡
ዛሬ ችግሬን ይዤ ብቅ ብያለሁና እንደማታሳፍረኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በጣም የዓናፋርነትና የድብቅነት ባህሪይ አለብኝ።
ሰዎች ምን ይሉንኛል ብዬ ስለምፈራ የምገልገውን ነገር መጠየቅ አልችልም። ሴት ልጅ ለመቅረብ ዳገት ስለሚሆንብኝ
አሜሪካን ሃገር ከመጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴክስ ማድረግ አልቻልኩም። ስለዚህ ራሴን በራሴ አረካለሁ። በፊት እንዲህ ያለ
ችግር ነበረብኝ፤ ሆኖም ራሴን አረጋግቼ ነበር፤ ግን አሁን ይህ ችግር ተመልሶ መጥቶብኛል። ሴት ልጅ ስቀርብ
አልረጋጋም፤ በጣም ችግር አለብኝ። ምን ትሉኛላችሁ? ስሜን ደብቁልኝ
የኢሳያስ
ከበደ ምላሽ፦ ውድ ጠያቂያችን ጥያቄህ ብዙ ማብራሪያ ቢያስፈልገውም የተረዳነውን ያህል ለመመለስ እንሞክራለን። ወደ
ጥያቄዎችህ ስንመጣ ግለ ወሲብ መፈፀምህ፣ አይናፋርነትህ፣ ድብቅነትህ፣ ይሉኝተኛነትህና እራስህን መጥላትህ ችግሮችህ
እንደሆኑና መፍትሄ እንድንሰጥህ ጠይቀኸናል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚያግዙህን ነገሮች ከመጠቆማችን በፊት
ችግሮቹ ከምን መነጩ? /መንስኤያቸው ምንድነው?/ የሚለውን መመለሱ ተገቢ ይሆናል፡፡ የነዚህ ሁሉ ችግሮች መንስኤ
አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም በራስህ ያለህ እምነት ዝቅተኛ /Low self-confidence/ በመሆኑ ነው፡፡
በራስህ ያለህ እምነት ዝቅተኛ ሲሆን አይንአፋር፣ ይሉኝተኛ፣ ድብቅ እንደምትሆን የስነ ልቦና ባለሙያዎች
ይተነትናሉ፡፡ ይህ እምነት ደግሞ የሴት ጓደኛ የመፈለግ ሁኔታህን ደካማ ያደርገዋል፡፡ ስለሆነም ግለ ወሲብ ወደ
ማድረግ እንድታተኩር ያደርግሃል፡፡ ምክንያቱም ወሲባዊ ፍላጎትህን /sexual desire/ መቀነሻ ብቸኛው አማራጭ
ሆኖ ስለሚታይህ ይህን ተግባርህን ደግሞ በተደጋጋሚ ስትፈጽመው ወደ ሱስነት ይቀየራል፡፡ ተነግሮህ እያለ ደግሞ ማቆም
አልችል ስትል የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማህና እራስህን ወደ መጥላት ትጓዛለህ፡፡
ጠቅለል ባለ መልኩ ስንመለከተው ችግሮችህ በራስህ ላይ ባለህ እምነት ምክንያት የመጡ ናቸው ማለት ነው፡፡ ያ
ማለት ደግሞ በራስህ ያለህ እምነት ወደ ተሻለ ደረጃ መድረስ ከቻለ ችግሮችህ በሙሉ ከመሰረታቸው መነቀል ይችላሉ
ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱን ችግርህን በተናጠል ለመቅረፍ በመሞከር የችግሮቹን መንስኤ ነቅሶ አውጥቶ መቅረፍ
የተሻለ እና አዋጭም ስለሆነ በራስህ ላይ ያለህ መተማመንን ለመጨመር የሚረዱ መፍትሄዎችን ልጠቁምህና አንተም
ተግብራቸው፣ በስተመጨረሻ የጠቀስካቸው ችግሮች በሙሉ በራሳቸው ጊዜ ከባህሪህ ውስጥ እየጠፉ ይመጣሉ፡፡ በመጀመሪያ
ስለ ራስህ ያለህ እምነት ከየት መጣ? እና እንዴትስ ዝቅተኛ ሆነ የሚለውን መመለሱ ተገቢና አስፈላጊ በመሆኑ በእሱ
እንጀምር፡፡
በራስ መተማመናችን እንዴት ተፈጠረ?
አንድ ህፃን እንደተወለደ የሚመራው ንቁ ባልሆነው የአዕምሮው ክፍል /the unconscious mind/ ነው፡፡
በመሆኑም ማንኛውንም ስሜቱን የመደበቅ፣ የመፍራት፣ በይሉኝታ ማለፍም ሆነ ማፈር የሚባል ነገርን አያውቅም፡፡
እያደገ ሲመጣ ከአካባቢው ጋር መስተጋብር የሚፈጥርበትና ተጨባጭ ሁኔታዎችን /reality/ የሚቃኝበት የአዕምሮ
ክፍል ስለሚያስፈልገው ንቁ የሆነውን የአዕምሮ ክፍል /conscious mind/ በመገንባት ከአካባቢውና ከተጨባጭ
ዓለም ጋር ግንኙነትን ይፈጥራል፡፡ ይህኛው የአዕምሮው ክፍል የተለያዩ መረጃዎችን በመሰብሰብ ወደ ንቁ ያልሆነው
የአዕምሮ ክፍል በማስገባት እዛው ይጠራቀማል፡፡
እነዚህ የተጠራቀሙ መረጃዎች ደግሞ የኔን ማንነት ይወስኑታል፡፡ በመሆኑም በራሴ ያለኝ እምነት ከነዚህ መረጃዎች ይገነባል ማለት ነው፡፡ መረጃዎቹን በሁለት መንገድ ላገኛቸው እችላለሁኝ፡፡ እነሱም፡-
1. ከራሴ ልምዶች፡- /experience/ ልጅ ሆኜ የተለያዩ ነገሮችን መስራት /መሞከር/ እጀምራለሁ፡፡
በዚህን ጊዜ ለመስራት የሞከርኩት ነገር ውጤታማ ከሆነልኝ መስራት እችላለሁ በሚል እምነትን ሳያጎለብት በተቃራኒው
ካልተሳካልኝ ደግሞ ‹‹እኔ አልችልም›› የሚል እምነትን እያጎለበትኩ እመጣለሁ፡፡
2. ከሌሎች ሰዎች ገለፃ /Other explanation/፡-
እያደግሁ በምመጣበት ሰዓት እኔ ከራሴ ልምድ ከማገኘው ነገር በተጨማሪ በአካባቢዬ ያሉ ሰዎች ስለኔ የተለያዩ
ገለፃዎችን ለአዕምሮዬ ያቀብሉኛል፡፡ ያም ከአዕምሮዬ ውስጥ ተቀርፆ ይቀርና በራሴ እምነት ላይ የራሱን ተፅዕኖ
ያሳርፋል፡፡ ለምሳሌ አንድን ስራ ለመሞከር ስነሳ ‹‹ተው አትችለውም /አይሆንልህም/›› የምባል ከሆነ ንቁ ያልሆነው
የአዕምሮዬ ክፍል እንደማይችል አድርጎ ይቀበላል፡፡ በመሆኑም ለራሴ ያለኝ አመለካከት ዝቅተኛ ሆኖ ያድጋል፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ያንኑ ስራ ስሰራ ‹‹ጎበዝ አንተኮ ትችላለህ›› ወይንም ‹‹አያዳግትህም›› ወዘተ… ከተባልኩኝ እኔ
መስራት እችላለሁ የሚል ስሜት /sense of initiative/ አዕምሮዬ ውስጥ ይጎለብታል፡፡ ስለሆነም ለራሴ
ያለኝ እምነት ጥሩ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ከእነዚህ ሁለት የመረጃ ማግኛ መንገዶች በማገኘው መረጃ መሰረት እያደግሁ ስመጣም በራሴ ያለኝ እምነት እየጨመረ ወይም እየቀነሰ ይመጣል፡፡
(ለዚህ ጽሁፍ የተሰጠው ምላሽ ረዥም ነው። ሙሉውን ለመጨረስ ከፈለጋችሁ በድረ ገጻችን ላይ ማግነት ትችላላችሁ)
በተጨማሪ እያደግንና ወደ ወጣትነት ደረጃ እየገባን ስንመጣ ሁሉን ነገሮች የኛ የማድረግ ፍላጎት ይፈጠርብናል፡፡
በመሆኑም የምፈልጋቸውን ነገሮች ማግኘት አልችልም ስል ‹‹እኔ ደካማ ነኝ፣ አልችልም፣ ይህን ማድረግ የሚችሉት
ሌሎች ናቸው፣ እድሌ ጠማማ ነው፣ ወዘተ…›› የሚሉ አፍራሽ ቃላቶችን በተደጋጋሚ መጠቀም እጀምራሁ፡፡ እነዚህን
ነገሮች ንቁ የሆነው አእምሮዬ በተደጋጋሚ ሲያብሰለስለውና ምናልባትም ከውጪው ዓለም /ከአካባቢዬ ሰዎች/ ሲነገረው
ንቁ ያልሆነው የአእምሮ ክፍል አምኖ ይቀበልና በራሴ ያለኝ እምነት እየቀነሰ ይመጣል ማለት ነው፡፡
ውድ ጠያቂያችን ኤል ያንተን የአስተዳደግ ሁኔታህን ከላይ ከጠቀስኩልህ ሁኔታ ጋር ለማያያዝ ሞክር፡፡
እንደገለፅክልን ቤተሰቦችህ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ከልጅነትህ ጀምሮ የተለያዩ ነገሮችን
የመሞከር እድልህ ዝቅተኛ ነበር፡፡ ብትሞክርም ተው አትችለውም የመባል እድልህ ከፍተኛ ነበር፡፡ በተጨማሪም እስከ
ዘጠነኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ እንደነበርክ ከዛ ግን ትምህርታዊ ብቃትህ እየቀነሰ እንደመጣ ነግረኸናል፡፡ ለዚህ
መንስኤው ምንድን ነው? ብለን ስንነሳ በመጀመሪያ በልጅነትህ የነበሩት ልምዶችህና ከአካባቢህ ሰዎች ስለ አንተ
የሚነገርህ በተለይም ላንተ ቅርብ የሆኑ ሰዎች /significant others/ የነገሩህ ነገር ነው፡፡ በተጨማሪም
ወደ ወጣትነት የምትገባበት ዕድሜ በመሆኑና ብዙ ነገሮችን የማድረግ ፍላጎትህ በተለያዩ ምክንያቶች መገደባቸው
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በራስህ ያለህን እምነት ዝቅተኛ አድርገውታል፡፡
ይህንንም የሳልከው ስዕል በሚገባ ይገልፀዋል፡፡ ዛፍ ስር ቁጭ ብለህ ስታነብ የሆነ ቅርንጫፍ ከላይ ሊወድቅብህ
ሲል አንተ መሸሽህን ያሳያል፡፡ ምን ማለት ነው የማጥናት ፍላጎት አሁንም እንዳለህ ነገር ግን አንድ ነገር ከሌላ
አካል እየመጣብህ እንዳለና አንተ ደግሞ ተቋቁሞ ማለፍ ወይንም መከላከል ስለማትችል እየሸሸህ እንደሆነ ይገልፃል፡፡
በቀላል አማርኛ ለመግለፅ ውጫዊ ግፊት ሲመጣብህ የምትፈልገውን ነገር ትተህ የምትሸሽ ሰው መሆንህን ይገልፃል፡፡ ያ
ማለት አንተ ስለ ራስህ ያለህ እምነት ችግሮችን መቋቋምና ማለፍ የማልችል ነኝ›› የሚል ነው ማለት ነው፡፡
በአጠቃላይ ከአካባቢህ በመጡ ገለፃዎችና አንተም በልምድ /በሙከራ/ ካገኘሃቸው ነገሮች በመነሳሳት አሁን ያለህን
የራስ እምነት እንድትይዝ ሆነሀል ማለት ነው፡፡ ዋናው ነገር ግን አሁን ያለኝ የራስ እምነት ዝቅተኛ ነው ብሎ
ማሰቡ ሳይሆን ያለህን የራስ እምነት ማሻሻሉ ነው፡፡ በመሆኑም የራስ እምነትህን ለማሻሻል ወደሚያግዙህ ዘዴዎች ጥቆማ
ላምራ፡፡
በራስ መተማመንን ለማሻሻል የሚያግዙ ዘዴዎች
አንድ ሰው በራሱ ላይ ያለውን እምነት ለመለወጥ /ለማሻሻል/ የሚያግዙ የተለያዩ ዘዴዎች አሉ፡፡ ነገር ግን
እነሱን ተግባራዊ ከማድረጋችን በፊት አንድ ልናውቀው የሚገባ ሀቅ አለ፡፡ ይኸውም አሁን ያለው የራስ እምነታችን
ከልጅነት ጀምሮ እያደገ የመጣና አብሮንም የኖረ በመሆኑ ለመለወጥ ስንነሳ ቀስ በቀስ መሆን አለበት፡፡ አንድ ዛፍ
በለጋነቱ እየተጣመመ ያደገ ከሆነ ቀጥ እንዲል ከተፈለገ ቀስ በቀስ እያቃናነው መምጣት አለብን፡፡ አለበለዚያ ግን
በአንዴ ልናቃናው ከሞከርን መሰበሩ አይቀሬ ነው፡፡ ስለሆነም የራስ እምነታችንን ቀስ እያልን ከጊዜ ወደ ጊዜ
እያሻሻልነው መምጣት አለብን፡፡
ውድ ጠያቂያችን ኤል ይህንን አምነህ ከተቀበልክ በራስ መተማመንህን ለማሻሻል ወደሚያግዙህ ዘዴዎች ላምራ፡፡
1. በመጀመሪያ ወረቀትና እስክሪብቶ ይዘህ የህይወት ታሪክህንና ለወደፊቱ ምን መሆን እንደምትፈልግ ወይንም
እንዳለብህ አጠር አጠር አድርገህ ፃፍ፡፡ ይህ ማንነትህን፣ ከየት እንደመጣህና ለወደፊትስ የጉዞ አቅጣጫህ ወደየት
እንደሚያመራህ ጠቋሚ ነገር ነው፡፡ ይህንን የፃፍከውን ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ማታ ልትተኛ ስትልና ጠዋት
ከእንቅልፍህ ስትነሳ አንብበው፡፡
2. ሁላችንም እንደምናውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው ፍፁም፡፡ በመሆኑም አንተ ፍፁም እንዳልሆንክና ሁሌም ግን
እየተሻሻልክና እየተለወጥክ የምትሄድ ሰው መሆንህን አምነህ ተቀበል፡፡ ብዙዎቻችን ይህንን እናምናለን የምንል ቢሆንም
ተግባራችን ግን አይመሰክረውም፡፡ እነሱ ይህንን እየሰሩ እኔኮ መስራት አልችልም ወይንም ለመስራት አልታደልኩም
እያልን ስናማርር እንደመጣለን፡፡ ይህ ፈፁም እንዳልሆንን ችግሮች ያሉብን ግን የማንሻሻል መሆናችንን አለመቀበላችንን
ያሳያል፡፡ በመሆኑም ራስህን ከሌሎች ሰዎች ጋር አታወዳድር፡፡ ይልቁንም ራስህ ውስጣዊ ደረጃዎችን አዘጋጅና ከአንዱ
ወደ ሌላኛው መሸጋገርህ ላይ ብቻ ትኩረት አድርግ፡፡ ትላንትና ቤተሰቦችህን አትረዳም ነበር፡፡ ዛሬ ቤተሰቦችህን
ወደ መርዳት መሸጋገር ከቻልክ እየተለወጥክ ነው ማለት ነው፡፡ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የህይወት ዙሪያ ደረጃ
አውጣና ትኩረትህን ከአንዱ ወደ ተሻለው ደረጃ መሸጋገር ላይ አድርግ፡፡
3. ጥሩና ደካማ ጎኖችህን የሚያመላክት ሰንጠረዥ አዘጋጅና አስር ጥሩ ጎኖችን በአንደኛው ረድፍ ፃፍ፡፡ አስር
ደካማ ጎኖችህን ደግሞ በሌላኛው ረድፍ ፃፋቸው፡፡ ከደካማ ጎኖችህ ውስጥ አንዱን ብቻ ለይተህ አውጣውና እሱኑ ብቻ
ለመለወጥ ከፍተኛ ጥረት አድርግ፡፡ በዚህ ጊዜ ሌሎቹን ደካማ ጎኖችህን አታስታውሳቸው፡፡ በተቃራኒው ግን አስሩንም
ጥሩ ጎኖችህን በተደጋጋሚ እያቸው አስታውሳቸው፡፡ ከዛም ያን ደካማ ጎን አሻሽየዋለሁ ብለህ ካሰብክ ሌሎቹን ተራ
በተራ እያነሳህ ለመለወጥ ተንቀሳቀስ፡፡
4. ቀጥና ቀና ብለው በፍጥነት የሚራመዱ ሰዎች በራሳቸው የሚተማመኑ ብሎም ወዴት እንደሚሄዱ የሚያውቁ ሰዎች
እንደሆኑ የስነ ልቦና ባለሙያዎች በጥናት አረጋግጠዋል፡፡ ስለሆነም ቀጥና ቀና ብለህ በፍጥነት መራመድን ተለማመድና
ቋሚ ባህሪህ አድርገው፡፡
5. ምንም እንኳ የተለያዩ ሰዎች የተለያየ አስተያየት ቢሰጡህም ሁሌም ልብሶችህን እያጠብክ ንፁህ ልብስ ልበስ
/ሽክ በል/፣ አዳዲስ ሰዎች ጋር ስትገናኝ ቀድመህ ስምህን ተናገር፣ ፈገግታ አይለይህ፣ ሰዎች ሲያሞግሱህና ውለታ
ሲውሉልህ ትሁት በሆነ መልኩ ምስጋናህን አቅርብ፡፡
6. ብዙዎቻችን ለመልመድ የሚያዳግተን ነገር ግን በጣም ውጤታማ የሆነ ዘዴ ልጠቁምህና ፅሑፌን ላብቃ፡፡ ለራስህ
ጊዜ ስጠው፡፡ በቀን ውስጥ ከራስህ ጋር የምትወያይበት 30 ደቂቃ መድብ፡፡ በዚህ በመደብከው 30 ደቂቃ ውስጥ
ብቻህን ቁጭ በልና እራስህን በራሱ የሚተማመን፣ እራሱን የሚለውጥና ለወደፊት ያለውን አላማ ጠንቅቆ የሚያውቅ
አድርገህ በአአምሮህ በመሳል ተደሰት፡፡ መድረስ የምትፈልገው ደረጃ ላይ ደርሰህ ምን ምን እንደምታደርግ ከራስህ ጋር
ተነጋገር፡፡ ለምሳሌ የሀገር መሪ መሆንን የምትፈልግ ከሆነ በዚህች 30 ደቂቃ ውስጥ ስለ ራስህ ስታስብ የሀገር
መሪ እንደሆንክና ምን ምን መስራት እንዳለብህ አስብ፣ ከየትኛው ሀገር መሪ ጋር መገናኘት አለብህ፣ ስታገኘውስ ምን
ትለዋለህ? ወዘተ…
ውድ ጠያቂያችን ኤል እነዚህን ዘዴዎች በሚገባ ተግባራዊ ካደረክና የሚያጋጥሙህን መሰናክሎች በትዕግስት ማለፍ የምትችል ከሆነ ትልቅ ደረጃ የማትደርስበት ምንም ምክንያት የለምና በብርታት ስራ ባይ ነኝ፡፡
መልካም ጊዜ!!
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of
various information and content providers. The Website neither
represents nor endorses the accuracy of information or endorses the
contents provided by external sources. All blog posts and comments are
the opinion of the authors.
Written by መታሰቢያ ካሣዬ, AddisAdmassNews.com
በፀጉር ቀለሞች ውስጥ ካንሰር የሚያመጡ ኬሚካሎች አሉ የመዋቢያ ምርት አትዋዋሱ! የመዋቢያ ምርቶችን በውሃ ማቅጠን አደጋ አለው
በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የሆነችው ህሊና ለፊቷ
ቀለል ያሉ ሜካፖችን መጠቀም የጀመረችው ከዓመታት በፊት ነበር፡፡ ፊቷ እጅግ ወዛማ በመሆኑ ወዙን እየመጠጠ የተሻለ
ገጽታ ሊያጐናጽፋት እንደሚችል የተነገራትን የፊት ማጽጃ ሜካፕ ለአመታት ስትጠቀም ቆይታለች፡፡ በሥራዋ አጋጣሚ
በየደረሰችባቸው አገራት ሁሉ የኮስሞቲክስ (የመዋቢያ ዕቃዎች) መሸጫ መደብሮችን ሳትሳለምና የተለያዩ አይነት
ኮስሞቲክሶችን ሳትሸምት ወደ አገሯ አትመለስም፡፡ ከፊቷና ከምትለብሳቸው ልብሶቿ ጋር የሚሄዱ (ማች የሚያደርጉ)
የፊት ማስዋቢያ ኮስሞቲክሶችን በየቀኑ ትጠቀማለች፡፡ እንደ አይኗ ብሌን በምትሣሣለትና ከወር ገቢዋ አብዛኛውን ወጪ
እያደረገች ዕለት በዕለት በምትንከባከበው ፊቷ ላይ ችግር ሊደርስ ይችል ይሆናል ብላ ለአፍታም አስባ አታውቅም፡፡ ከወራት
በፊት ለሥራ ወደ ካናዳ ተጉዛ በነበረችበት አጋጣሚ የገዛችውንና ጓደኞቿ ሁሉ ብራንድ ምርት ነው እያሉ ያደነቁላት
ሜካፕ መኪናዋ ውስጥ ለሣምንታት መቀመጡ ትዝ አላትና አውጥታ መጠቀም ጀመረች፡፡ ከቀናት በኋላ ፊቷን የማሳከክና
የመለብለብ ስሜት ይሰማት ጀመር። ግራ ገባት፡፡ ምንድነው? ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡ የማሳከክ ስሜቱ ቡግርና ሽፍታን
አስከትሎ ቀጠለ፡፡ ግራ ቢገባት የተለያዩ ተፈጥሮአዊ የፊት መንከባከቢያ መንገዶችን ተጠቅማ ችግሯን ለማስወገድና
የህመም ስሜቱን ለመቀነስ ጥረት አደረገች፤ ግን አልተሳካላትም፡፡ ከዕለት ዕለት የፊቷ ገጽታ እየተበላሸ የቡግርና
የሽፍታው መጠን እየጨመረ መሄዱ እጅግ አሳሰባትና የቆዳ ሃኪም ለማግኘት ወደ አለርት ሆስፒታል አመራች፡፡ የመረመሯት
ሐኪም የተበላሹ የኮስሞቲክስ ምርቶችን በመጠቀሟ ሳቢያ የፊቷ ቆዳ በእጅጉ መጐዳቱንና ረዘም ያለ የህክምና ክትትል
ማድረግ እንደሚኖርባት ነገሯት፡፡ እንዴት ተደርጐ? አለች፡፡ የምጠቀመው ብራንድ በሆኑ ምርቶች ነው፡፡ የመጠቀሚያ
ጊዜያቸውን በሚገባ አንብቤና አረጋግጬ ካልሆነ ገዝቼ አላውቅም፡፡ ታዲያ እንዲህ አይነት ችግር እንዴት ሊገጥመኝ
ቻለ? ስትል ዶክተሯን ጠየቀች፡፡ ሃኪሟ የኮስሞቲክስ
ምርቶች በጤና ላይ ችግር ሊያደርሱ የሚችሉበትን ሁኔታ በዝርዝር አስረዷት። በምርቶቹ ውስጥ ባክቴሪያና ፈንገስ
እንዳይራባ ለማድረግና የኮስሞቲክሶቹን ጠረን ለመቀየር ታስበው የሚጨመሩት ኬሚካሎች በቆዳ ላይ ከባድ ችግር
እንደሚያስከትሉና ችግሩ የቆዳ ካንሰርን ሊያስከትል እንደሚችል አረዷት፡፡ ለሣምንታት በመኪናዋ ውስጥ ያቆየችው ሜካፕ
በፀሐይና ሙቀት ሣቢያ የኬሚካሉ ይዘት ተቀይሮ ለባክቴሪያና ፈንገስ መራቢያ ምቹ በመሆን የደረሰባትን ችግር
እንደፈጠሩባት ነገሯትና ህክምናውን እንድትጀምር አደረጓት፡፡ ላለፉት
ሁለት ወራት ህክምናዋን እየተከታተለች የተበላሸ የፊት ገጽታዋን ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ ነች፡፡ እንደህሊና
ሁሉ በርካቶች በሜካፕ መዘዝ ሣቢያ የሃኪም ቤት ተመላላሽ ደንበኛ ለመሆን ተገደዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የመዋቢያ
ምርቶችን አጠቃቀም አለማወቅ፣ በኮስሞቲክሶቹ ላይ የተፃፉ መረጃዎችን በአግባቡ አንብቦ መረዳት አለመቻል፣ ጊዜ
ያለፈባቸውን ምርቶች መጠቀም እንዲሁም የመዋቢያ ምርቶችን እየተዋዋሱ መጠቀም ዋንኞቹ ምክንያቶች ናቸው፡፡ የመዋቢያ
ምርቶችን (ኮስሞቲክሶችን) ቀደም ብለው መጠቀም የጀመሩት ጥንታውያኑ ግብፃውያን እና ሮማውያን ሲሆኑ ጊዜው
ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ይጠቁማሉ፡፡ ሊድ፣ መዳብና የተቃጠለ የአልሞንድ ፍሬ ተቀላቅሎ
የሚሰራው የአይን ማስዋቢያ (ኩል) ግብፃውያኑ በስፋት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ቀስ በቀስም የመዋቢያ ምርቶቹ በአሠራር
እየተሻሻሉ የብዙዎችን ቀልብ መሳብ ጀመሩና በርካቶች ተጠቃሚ ሆኑ፡፡ ለሜካፕ መስፋፋት ትልቁን ሚና የተጫወተው
የሆሊውድ መቋቋምና የፊልም አክተሮቹ ራሳቸውን ለማሳመርና ለመቀየር በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ዋንኛ ተፈላጊ ነገር
እየሆነ መምጣቱ ነው፡፡ የባሌትና የኦፔራ ዳንሰኞች
በመድረክ ሥራቸው ወቅት ሜካፖችን መጠቀም እያዘወተሩ መሄዳቸው ለሜካፕ መስፋፋት ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ ውጫዊ
ገጽታችንን ለማስዋብና ለመቀየር ከምንጠቀምባቸው የመዋቢያ ምርቶች (ኮስሞቲክሶች) መካከል የፊት ሜካፖች፣ የእጅ፣
የፊትና የእግር ክሬሞቹ፣ ከፀሐይ ብርሃን ለመከላከል የምንጠቀምባቸው ቅባቶች (ዱቄት መሰል ምርቶች) ሽቶዎች፣
የፀጉር ቀለሞች፣ ዲኦደራንቶች፣ የከንፈር ቀለሞችና የጥፍር ቀለሞች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የመዋቢያ ምርቶች
ውስጥ አብዛኛዎቹ (ሁሉም ማለት ይቻላል) የጠረን መቀየሪያና ምርቶቹ እንዳይበላሹ አድርገው ለማቆየት የሚረዱ
ኬሚካሎች ይጨመርባቸዋል። እነዚህ ኬሚካሎች ደግሞ በአብዛኛው ለከፍተኛ የጤና ችግር ሊዳርጉ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቆዳና
የአባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር ታደገ ኃይሉ እንደሚናገሩት፤ በኮስሞቲክስ ሣቢያ ለሚከሰቱ የጤና ችግሮች
ዋንኞቹ ምክንያቶች የኮስሞቲክሶቹን ጠረን ለመቀየርና ኮስሞቲክሶቹ እንዳይበላሹ አድርጐ ለማቆየት እንዲረዱ ታስበው
የሚገቡ ኬሚካሎች ናቸው፡፡ እነዚህ ኬሚካሎች ካንሰርን ለሚያስከትሉና የሰውነታችንን የሆርሞን ምርቶች ሊያዛቡ ለሚችሉ
የጤና ችግሮች ይዳርጋሉ። ካንሰር አምጪ የሆኑ
ኬሚካሎችን በስፋት እንደሚይዙ ከሚነገርላቸው የመዋቢያ ምርቶች መካከል ዋንኛው የፀጉር ቀለም እንደሆነ የገለፁት
ዶ/ር ታደገ፤ ዛሬ ዛሬ የፀጉር ቀለም አምራች ድርጅቶች ካንሰር አምጪ የሆኑ ኬሚካሎችን በተመሳሳይ ምርቶች በመተካት
ከገበያ እያወጧቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ጉዳይ በፀጉር ቀለም ሳቢያ የሚከሰተውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት
አስችሏል ማለት አይደለም፡፡ ዛሬም በዚሁ ኬሚካል ሳቢያ ለካንሰር የሚዳረጉ በርካታ የፀጉር ቀለም ተጠቃሚዎች አሉ
ብለዋል፡፡ ባይቲዮኖል፣ ክሎይፎርም፣ ሜቲሊን ክሎራይድና ሜሪኩሪ ኮምፓውንድ የተባሉት ኬሚካሎች ካንሰር አምጪነታቸው ከፍተኛ በመሆኑ፣ ከፀጉር ቀለም ምርት ግብአትነት እንዲታገዱ ተደርገዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የኮስሞቲክስ
ምርቶች ለፀሐይ ብርሃንና ለሙቀት ተጋልጠው መቀመጥ እንደሌለባቸው የሚናገሩት ዶ/ር ታደገ የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት
በኮስሞቲክሶቹ ውስጥ ያሉትን ኬሚካሎች ይዘታቸውን በመቀየር ባክቴሪያ እንዲራባባቸው እንደሚያደርግና ይህም ለከፍተኛ
የጤና ችግር እንደሚዳርግ ገልፀዋል። የመዋቢያ ምርቶች የራሳቸው የሆነ የመጠቀሚያ ጊዜና የአጠቃቀም ሥርዓት አላቸው
ያሉት ባለሙያው፤ መመሪያዎችን በአግባቡ ማንበብና መረዳት እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ የመዋቢያ
ምርቶች በመግለጫቸው ላይ ተጽፎ በግልጽ የተቀመጠ ነገር ከሌለ በስተቀር በውሃ ማቅጠን እጅግ አደገኛ መሆኑን
የሚናገሩት ዶክተሩ፤ ውሃ የኬሚካሎችን ይዘት በቀላሉ በመቀየር ለጤና አደገኛ ይሆናል ብለዋል፡፡ የአይን ማስካራ
ከሌሎች የኮስሞቲክስ ምርቶች በበለጠ በቀላሉ ጉዳት ያደርሣል፡፡ ማሳካራን በምንጠቀምበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄን
ማድረግ እንደሚገባን ያስገነዘቡት ዶክተር ታደገ፤ ያለጥንቃቄ በሚደረግበት ወቅት የአይን ሽፋሽፍቶች እንዲረግፉ፣
እንዲጐብጡና ተሰብረው በአይን ብሌናችን ላይ ጭረት በመፍጠር አይነ ሥውርነትን ሊያስከትሉ ለሚችሉ የጤና ችግሮች
ሊዳርጉን እንደሚችሉ አስገንዝበዋል፡፡ ኮስሞቲክሶችን መዋዋስና ችግሩ በመዋቢያ
ምርቶች ሣቢያ የሚከሰት የጤና ችግሮች መካከል መዋቢያዎችን በመዋዋስና በጋራ በመጠቀም ሳቢያ የሚከሰቱ ችግሮች
ናቸው። በመዋቢያ ምርቶች መቀቢያዎች (ስፖንጆች፣ የማስካራ ብሩሾች) የመሳሰሉት ባክቴሪያዎችን አጣብቀው በላያቸው
መያዝና ማስቀረት ስለሚችሉ፣ በጋራ በምንጠቀምበት ወቅት በቀላሉ ኢንፌክሽኖችንና ቫይረሶችን ከአንዱ ወደ አንዱ
ለማስተላለፍ ይችላሉ፡፡ አንድን የመዋቢያ ምርት ተቀብተው ሳያስለቅቁና በአግባቡ ከሰውነትዎ ቆዳ ላይ ሳያራግፉ ሌላ
አይነት የመዋቢያ ምርት መጠቀምም እጅግ አደገኛ ነው፡፡ ሌላኛውን አይነት መዋቢያ በቆዳዎ ላይ ከማሳረፍዎ በፊት
ቀድሞ የነበረው መዋቢያ መልቀቁን ማረጋገጥ ይጠበቅብዎታል፡፡ መዋቢያዎችን ከፊትዎ ላይ ሳያስለቅቁ ወደመኝታዎ
አይሂዱ፡፡ ኮስሞቲክሶችና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሁሉም
ኮስሞቲክሶች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው በግልጽና ሊታይ በሚችልበት ሁኔታ መገለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የመጠቀሚያ
ጊዜያቸው ከመድረሱ በፊት በተለያዩ የአቀማመጥ ችግሮች ሳቢያ ለብልሽት ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡ የውበትና ጤና ባለሙያዎች
እንደሚስማሙበት፤ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የተቃረበ የመዋቢያ ምርቶችን ስንጠቀም ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል፡፡
አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገልፁት፤ የከንፈር ቀለሞች (ሊፒስቲክና ቻፒስቲኮች) ተመርተው ለገበያ ከዋሉበት
ጊዜ ጀምሮ ለአንድ አመት ያለስጋት መጠቀም ይቻላል፡፡ ምርቶቹ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ በኋላ ግን
ከአራት ወራት በላይ ማቆየቱ አደጋን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ኮስሞቲክሶችን በዘፈቀደ መጠቀምና ችግሩ የመዋቢያ
ምርት ተጠቃሚዎች በአብዛኛው ስለሚጠቀሙት የመዋቢያ ምርት ምንነት፣ በውስጡ ስለሚይዛቸው የኬሚካል አይነቶችና
ስለሚያስከትሏቸው ችግሮች፣ መዋቢያውን በምን መልኩ መጠቀም እንደሚገባቸው እንኳን ሣያውቁ በዘፈቀደ ሲጠቀሙባቸው
ይስተዋላል፡፡ ይህ ደግሞ በጤና ላይ ሊያደርስ የሚችለው ችግር በቀላሉ የሚገለጽ አይሆንም። ሌላው የመዋቢያዎችን
ምንነት ሳያውቁ ከየሱቁና ከየመደብሩ በመግዛት በጥቅም ላይ የማዋል ችግር ነው፡፡ በአገራችን
በገበያ ላይ ከሚገኙት የመዋቢያ ምርቶች መካከል በሰለጠኑት አገራት ሙሉ በሙሉ በበቅም ላይ እንዳይውሉ የታገዱና
ከገበያ የወጡ ምርቶች ይገኙበታል። እነዚህ ምርቶች በአገራችን በየሱቁና በየመንደሩ ይቸበቸባሉ፡፡ ከየት እንደመጡ፣
ከምን እንደተቀመሙ፣ ለምን ጥቅም እንደሚውሉ አንዳች መረጃ በሌለበት ሁኔታ በየሱቁ ይሸጣሉ፡፡ ቤትኖቬትና
ዳርኖቬት የተባሉት ቅባቶች በርካታ ሴቶች ለፊት ውበት ማሳመሪያ እያሉ ከየሱቁ እየገዙ ከሚጠቀሟቸው ምርቶች መካከል
ዋንኞቹ ናቸው። እነዚህ ምርቶች በውስጣቸው በያዙት ለጤና እጅግ አደገኛ ኬሚካሎች ሣቢያ ከሰለጠኑት አገራት
የኮስሞቲክስ ገበያ ውስጥ እንዲወገዱ ተደርገዋል፡፡ ተፈጥሮአዊ የመዋቢያ ምርቶች ጠቀሜታቸውና የሚያስከትሉት የጤና ችግር ከተለያዩ
የእጽዋት አይነቶች እየተቀመሙ የሚዘጋጁ የመዋቢያ ምርቶች በውስጣቸው ምንም አይነት ኬሚካል ባለመኖሩ ለጤና
የሚሰጡት ጠቀሜታ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ምንም አይነት የጐንዮሽ ጉዳት የላቸውም። ይሁን እንጂ እነዚህን ምርቶች
በምንጠቀምበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ እነዚህን መዋቢያዎች ወዲያውኑ በጥቅም ላይ የማናውላቸው
ከሆነ የሚያስከትሉት ጉዳት የከፋ ይሆናል። ምክንያቱም መዋቢያዎቹ በውስጣቸው ባክቴሪያና ፈንገስ እንዳይራባባቸው
ለማድረግ የሚያስችል ኬሚካል ባለመኖሩ ለኢንፌክሽንና መሰል ችግሮች ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ በአጠቃቀም ወቅት ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ ሜካፕዎን ለሙቀትና የፀሐይ ብርሃን አያጋልጡት በመዋቢያ ምርቶች ላይ ውሃን ፈጽመው አይጨምሩ ሜካፕዎ ቀለሙና ጠረኑ ከተቀየረ ፈጽመው አይጠቀሙት ሜካፕ ተዋውሶ መጠቀም እጅግ አደገኛ ለሆነ የጤና ችግር ያጋልጣል ሜካፕዎን በአግባቡ ተጠቅመው፣ በአግባቡ ከድነው በትክክለኛው ቦታ ያስቀምጡ በመኪና እየተጓዙ ኮስሞቲክሶችን አይጠቀሙ የፊት ማስዋቢያ ፓውደሮችና የፀጉር ስፕሬይዎች ሽታቸው በሳንባ ላይ ችግር ሊፈጥር ስለሚችል ወደ አፍንጫዎ አስጠግተው በጥልቀት አያሽትቱአቸው፡፡ የአይን ኢንፌክሽን(ህመም) ካለብዎ ማስካራ፣ ሻዶ፣ ላይነር የመሳሰሉትን የአይን ማስዋቢያዎች አይጠቀሙ፡፡ ሲያጌጡ ይመላለጡ እንዳይሆን ሜካፕ ስንጠቀም በጥንቃቄ ይሁን!!
sodere

5 ways to be more attractive to your husband
ከሊሊ ሞገስ (አፕል ቫሊ)
የውጭ
አገር ሴቶችን እንተዋቸው እና ወደ ሀገራችን ስንመጣ በትዳር ውስጥ ያሉት ወይም ያልተጋቡ ሴቶችን ብናይ ብዙውን
ጊዜ ከመናገር ይልቅ ማዳመጥ፣ ከመወሰን ይልቅ ውሳኔ ተቀባይ መሆን፣ ከማዘዝ ይልቅ ታዛዥ መሆን ይታይባቸዋል፡፡ ወደ
ፍቅር ህይወታቸው ስንመጣ ደግሞ ከወንድ ጓደኛቸው ብዙ የሚፈልጉት ነገር እያለ ነገር ግን በውስጣቸው አፍነው
ይይዙታል፡፡ በተለይ በወሲብ ጉዳይ ላይ ሁሌ የወንዱን ስሜት ብቻ ይቀበላሉ፡፡ እርካታ ቢያገኙም አኩርፈው ከመተኛት
ውጭ የሚያመጡት ነገር የለም፡፡ ይህ ደግሞ በግልፅ ካለመወያየት መፍትሄ የለውም ብሎ ከመገመትና ከእውቀት ማነስ
የሚመጣ ችግር ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የዚህን ችግር መፍትሄ አንድ በአንድ እናያለን፡፡
በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ዝምታ ወርቅ ነው የሚለው አባባል ቦታ የለውም፡፡ ባለቤትሽ አልጋ ላይ ስህተት ቢሰራ
እንኳ ስሜቱን ላለመጉዳት ስትይ ዝም ትያለሽ፡፡ ታዲያ እርካታ ካላገኘሽ ‹‹ዛሬ ምንም አልረካሁም›› ትያለሽ ወይስ
አትዪውም?
1. ማነቃቃቱ ከአንቺ ይጀምር
መኝታ ቤት ብዙ ጊዜ ፊሽካ ነፍቶ ጨዋታው እንዲጀመር የሚያደርገው ወንዱ ነው፡፡ ባለቤትሽ መኝታ ቤት ውስጥ ስሜት
አልባ ሆኖ እንደ በረዶ ከቀዘቀዘብሽ ምክንያቱን በግልፅ ጠይቂው፡፡ ምናልባት ያን ቅዝቃዜ አጥፍተሽ መኝታ ቤቱን
የሰሐራ በረሐ የማድረጉ ስራ የአንቺ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ቀስ በቀስ ስሜቱ እንዲነሳሳ የማድረግ ግዴታ አለብሽ፡፡
ቀለሽ ጀርባሽን በመስጠት መተኛቱ ዋጋ የለውም፡፡
2. ፍላጎትሽን ግለጭ
ለምሳሌ የእርሱ አሳሳም ሊደብርሽ ይችላል፡፡ ይህን ጊዜ በቀጥታ ጥፋቱን አትናገሪ፡፡ ቅሬታዎችሽን የምትገልጭበት
መንገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ምን እንደምትፈልጊ ስትናገሪ የአንቺን ፍላጎት ብቻ አትከተይ፡፡ ይህን የምታደርጊ
ከሆነ ወደ ጠብ ሊያመራ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ‹‹አንተ ስትስመኝ መንግስተ ሰማያት የገባሁ ይመስለኛል ግን ደግሞ
አንገቴንም ብትስመኝ ዛሬውኑ ብሞት አይቆጨኝም ነበር››
3. በቃላትና በአካልሽ ባልሽን ምሪው
አንቺ ብልጥ ከሆንሽ በቀላሉ መቆጣጠር ትችያለሽ፡፡ ውብ ቃላትን ሁሌ መናገር ይልመድብሽ፡፡ እርሱ ለምን ቀድሞ
እንዲስምሽ ትፈቅጂያለሽ? ቀድመሽ አንቺ ጀምሪው፡፡ ለምሳሌ ባለቤትሽ ፀጉርሽን ሲዳስስ ደስተኛ ከሆንሽ ደስተኛ
እንደሆንሽ የሚገልፅ ድምፅ ብታሰሚው የበለጠ በራሱ እንዲተማመን ታደርጊዋለሽ፡፡ እጆቹ በማይመችሽ ቦታ ላይ ካረፈ
ቀስ ብለሽ በእጆችሽ ቦታ ላይ ካረፈ ቀስ ብለሽ በእጆችሽ ወደ ምትፈልጊው ቦታ መውሰድ ትችያለሽ፡፡ ለምሳሌ በእጁ
ጀርባሸን እየዳሰሰ ከሆነ ቀስ ብለሽ እጆቹን ወደ ታች እንዲንሸራተት ማድረግ ትችያለሽ፡፡
4. ትክክለኛ ሙድ ፍጠሪ
ግንኙነታችሁ ሁሌ ደረቅና ሲሪየስ መሆን የለበትም፡፡ ከጓደኛሽ ላይጥሩ ሙድ በፈጠርሽ ጊዜ ተመሳሳይ ቋንቋ
ትነጋገራላችሁ፡፡ አለባበስሽ ቋንቋ ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡ መኝታ ቤት ብትገቢ ሱሪ (ጅንስ) ለብሰሽ የምትገቢ
ከሆነ ተሳስተሻል፡፡ ይልቁንስ የውስጥ አካላቶችሽን ግልፅ አድርጎ የሚያሳይ የሌሊት ልብስ ብትለብሽ የባለቤትሽን
ስሜት በቀላሉ ትስቢዋለሽ፡፡ ጉርድ ቀሚስ በራሱ ጥሩ ሙድ የመፍጠር ሀይል አለው፡፡ የምትቀበያቸው ሽቶዎች፣ ሙዚቃዎች
የመብራቱ አይነት የዕቃዎች አቀማመጥ እነዚህ ሁሉ ልዩ ሙድ ይፈጥራሉ፡፡
5. ባልሽን በስጦታ አስደንግጭው
ወንዶች ብዙ ጊዜ ስጦታ ሊሰጣቸው በቃ የተፈቀዱ እንደሀኑ ይሰማቸዋል፡፡ አንድ የሚወደውን ነገር ገዝተሽ ማታ በጣም
ከጓጓሽ በኋላ ያኔ ስጦታ አበርክችለት፡፡ አቤት ያ ምሽት እንዴት እንደሚያስደስት ባየሽው፡፡ በመሆኑም ሁሌ ወንዶችን
ፍፁም አድርገሽ አትመልከቻቸው፡፡ ሰው ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ መፍትሄው ያለው በአንቺ እጅ ላይ ነው፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ተግባራዊ አድርጊያቸው፡፡ በተለይ በዚህ ዙሪያ የተፃፉ መጽሐፍትን በሚገባ አንብቢ፡፡
ያለ ጥርጥር መኝታ ቤት ውስጥ ዋና ኤክስፐርት ትሆኛለሽ፡፡ ይህን በማድረግሽ ፍቅራችሁን ዘላለማዊ ማድረግ
ትችላላችሁ፡፡
zehabesha