Saturday, August 31, 2013

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።


 ኢሳት ዜና :-  በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ሲነገራቸው መሰንበቱን ወኪሎቻችንን ዘግበዋል።
መንግስት ለፖለቲካ ትርፍ ብሎ የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፣ መንግስትም ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ይዞበት ሊመጣ እንደሚችል ምልክቶች እየታዩ ነው። ድምጻችን ይሰማ የተባለው አካል ከአመት ከመንፈቅ በላይ ያካሄደውን ተቃውሞ ኢህአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቶ ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚያሰማ መግለጫ ማውጣቱ እሁድ ምን ይፈጠር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ድምጻችን ይሰማ ባወጠው መርሀግብር ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖት አባቶች ንግግር ካደረጉ በሁዋላ ነጭ ወረቀት ወይም የጨርቅ ማህረም እንዲያውለበልቡ፣  የመጅሊስ ሹሞች ንግግር ሲያደርጉ ጆሮን በመድፈን፣ ያለምንም ድምጽ ሁለት እጅን ወደ ላይ በማንሳትና በማጠላለፍ የታሰሩት የኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ድምጻችን ይሰማ ይህን መርሀግብሩን በተግባር ካዋለ፣ አንድ መንግስት ለድጋፍ በማለት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ሲስተናገድበት በታሪክ የመጀመሪያው ይሆናል። ምናልባትም ለኢህአዴግ ታላቅ የፖለቲካ ክስረት ሊያመታበት እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ኢህአዴግ ከውርደት ለመዳን የጸጥታ ሀይሎችን በብዛት ከማሰማራት ጀምሮ የክልል ደህንነቶች ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ እያደረገ ነው።
ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ሊቀጥል እንደሚችል መታወቁ ሌላ ድራማ ሊፈጥር እንደሚችልም ይጠበቃል።
ሰሞኑን በተደረገው የሀይማኖት ጉባኤ አቶ በረከት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ሲናገሩ አቶ ሀይለማርያም ደግሞ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።
ESAT

የማርቲን ሉተር ኪንግ ራዕይና ወጣቱ


የማርቲን ሉተር ኪንግ ራዕይና ወጣቱ

የማርቲን ሉተር ኪንግ ራዕይ እስከ ምን ድረስ እውን ሆኗል? የሳቸውን ራዕይ ዕውን በማድረጉ አኳያ ያሁኑ ትውልድ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
የአሜሪካ የጥቁሮች መብት ተሟጋች ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ የሀገሪቱ ጥቁሮች በእኩልነት መኖር እንዲችሉ ምኞታቸውን የገለጹበት ንግግር ሐምሳኛ ዓመት ባለፈው ሮብዕ በዋሽንግተን ዲሲ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
የዶክተር ኪንግ ህልም ምን ያህል እውን ሆኗል የሚለውን ከመጠየቃችን በፊት ግን ያኔ የጥቁር አሜሪካውያን የትግል መሳሪያ የነበረውን መዝሙር እና ሙዚቃ መለስ ብለን እናስታውስ፤ " we shall overcome" የሚለው የወንጌላውያን መዝሙር እኢአ በ1903 ዓም ከብዙ ጥቁር አሜሪካውያን አፍ አልተለየም። መዝሙሩ ለብዙዎች አንድ ቀን ይህም ቀን እንደሚያልፍ ተስፋ ሰጪ እና የነፃነት ትግሉም መሳሪያ ነበር።
30th March 1965: American civil rights campaigner Martin Luther King (1929 - 1968) and his wife Coretta Scott King lead a black voting rights march from Selma, Alabama, to the state capital in Montgomery. (Photo by William Lovelace/Express/Getty Images) እኢአ 1965 የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ
ወቅቱ የመብት ተሟጋች ንቅናቄ የተጠናከረበት እና ብዙ ጥቁሮች በዘረኞች የተበደሉበት ነበር፤ በወቅቱ ታዋቂ ያልነበረችው ዘፋኝ ኒና ሳይመን ባለቤቷ ከውጭ ወደ ቤት ሲመጣ በብረት ሽጉጥ ለመስራት ስትሞክር ያገኛታል « በቃ በዛን ሰዓት ወጥቼ አንዱን መግደል ነበር የፈለኩት፣ ማንን እንደሆነ አላውቅም ግን አንዱን፤ የ300 ዓመት የእኩልነት ትግላችንን እንቅፋት የሆነውን ሰው» ስትል ለማጥፋት እንደፈለገች ሳይመን ይህንኑ «ጥቁሩ መንፈሴ» በሚል ባሳተመችው መፅሀፏ አስፍረዋለች። ባለቤቷም የእኩልነትን ትግል ለማሳካት መሳሪያዋ ሽጉጥ ሳይሆን ሙዚቃ መሆን እንዳለበት አሳምኗት ሳይመን የዛኑ ዕለት «ሚሲሲፒ ጋዴም» የሚለውን ዘፈን ፅፋ ጨረሰች።

U.S. President Barack Obama speaks from the steps of the Lincoln Memorial during the commemoration of the 50th anniversary of the March on Washington and Reverend Martin Luther King Jr.'s I have a dream speech in Washington August 28, 2013. The bell behind Obama had hung in the 16th Street Baptist Church in Birmingham, Alabama, before the church was bombed in 1963 just weeks after King's famous speech. REUTERS/Kevin Lamarque (UNITED STATES - Tags: POLITICS CIVIL UNREST ANNIVERSARY) // eingestellt von se 
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግር 50ኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ-ስረዓት ላይ
ግልጽ ፖለቲካዊ አቋም የያዘ ሌላው ታዋቂ ድምጽ « sly and the family stone» የተሰኘው ባንድ ነው።ባንዱየተለያ የየቆዳ ቀለም፣ ባህል እና ፆታ ካላቸው ሰዎች የተውጣጣ ነበር። ቡድኑም በዚያን ጊዜ "don’t call me nigger, whitey" የተሰኘውን ዘፈን አወጣ። ሌሎች ብዙ ታዋቂ ዘፋኞችም በነፃነት ትግሉ ተሳትፈዋል። ጀምስ ብራውን “say it loud-I am black and I am proud“ በሚል ዘፈኑ የጥቁሮችን በራስ መተማመን አበረታቷል።
ዛሬ በርካታ ጥቁር አሜሪካውያን በስፖርቱ፣ በፊልሙና በፖለቲካው መስክ የመሪነትን ቦታ ይዘው መኖር ችለዋል። ከጥቁርና ከነጭ የተወለዱት ባራክ ኦቦማም ፕሬዚዳት ለመሆን በቅተዋል። ከዚሕ ቀደም የዶክተር ኪንግ ትግል ባይኖር ኖሮ -ኦባማ፤ ፕሬዝዳት መሆን እንደማይችሉ ተናግረው ነበር። በማርቲን ሉተር ኪንግ 50ኛ ዓመት የንግግር መታሰቢያ ሥነ-ስረዓትም ላይ ኦባማ ምንም እንኳን በሀገሪቱ ዮናይትድ ስቴትስ ብዙ መሻሻሎች ቢታዩም በተለያዩት ዘሮች መካከል ኢኮኖሚያዊ አለመመጣጠን እንዳለ አስታውሰዋል። በዚሁ የመታሰቢያ ዝግጅትም ላይ የተገኙት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ስለ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ሲያስታውሱ « ኪንግ እጃቸውን ከፍተው እንጂ ቡጢ ጨብጠው አይደለም ነጮችን የገጠሟቸው። ለዚህም ነው የሚሊዮንን ሰዎች ስሜት የሳቡት » ።የሮብዕ የመታሰቢያ ሥነ ስርዓት ትልቁ ይሁን እንጂ፤ በ10 ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ግልጽ ለሆነ የስራ መመሪያ ለማስገኘት እና ጭቆናን በመቃወም ባለፈው ቅዳሜ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ለበለጠ የድምፅ ዘገባው ይጫኑ።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

የማለዳው ወግ … ተመስገን እላለሁም ፣ አልልምም !

በሰላም አውሎ ላሳደረኝ ፈጣሪ ስተኛም ሆነ ስነሳ ” ተመስገን ፈጣሪየ! ” የምትለዋን ምስጋና ከማቅረብ ተቆጥቤ አላውቅም ። ቸርነቱ የማያልቅበት ፈጣሪ አምላኬ አጉድሎብኝ አያውቅም!  ጤና ስጠኝ ስለው ጤናውን ፣ ጥበብ  መላ ላጣሁለት መላ ስጠኝ ስለው መላ ብልሃቱን ፣ ጉልበቴን አበርታው ስለው ብርታቱን ፣ ቅን ልቦና ስጠኝ ስለው ርህራሔውን እና የፈለግኩትን ሁሉ አያጓድልብኝም!  እናም ዘወትር ተመስገን እለዋለሁ !
   ገና ከአልጋየ ሳልነሳ ከአፊ ውስጥ አንድ ቃል ይመላለሳል ፣ ቃሉ ወደ አረፍተ ነገር ሺር በሎ ተቀየረ ! በጨለማ የማያይ አይኔን ወደ ድቅድቁ ጨለማ የመኝታ ክፍል ጣራ አፍጥጦ በምናብ አነበንበዋለሁ … በጀርባየ ተኝቸ ወደ ጣራ ካፈጠጥኩበት ወደ ጎን ግልበጥ እልና  እጆቸን ጭንቅላቴ ስር ወሸቅ አድርጌ  ከአፊ የማወጣውን አረፍተ ነገር ደጋገምኩ  ” ተመስገን ተመስገን ተመስገን አልልም !”  …  እል ይዣለሁ!
የጋዜጠኛ ተመስገን ድብደባ  ሰሞነኛው መነጋገሪያ …
       ለምጀዋለሁና እንደቀሩት ቀናት በአርቡ የሳውዲ የእረፍት ቀን መዳረሻ በድቅድቁ ጨለማ ሌሊት ላይ ነቅቸ የሚነበብ የሚታይ ካለ ዳሰስ ዳሰስ አደረግኩ። የሚሞነጫጨር የማለዳ ወግ መነሻ የሚሆነኝ ጉዳይ ከአንድ የፊስ ቡክ ወዳጀ በኩል በውስጥ መልዕክት ደርሶኛል ። ይህው መልዕክት የደረሰኝ የኢቲቪ ዜና አንባቢ ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ በተባለ ቅጽበት ነበር ። መረጃው ሲሰራጭ እኔም በጅዳ ቆንስል ከድብደባ ያላነሰ ግፍ ተፈጽሞብኝ ነበር ።  በደል እየተፈጸማቸው ፡ እየታመሙና እያበዱ ስላሉ ወገኖቸ ጉዳይ መፍትሔ ፍለጋና ምክክር ስብሰባ “አትሰበሰብም ፣አትመክርም!” ተብየ የታገድኩበት አጋጣሚ ነበርና የሰማሁትም የሆነብኝም አበሳጭቶኝ አዘንኩ ! የቆንስሉን እገዳ መረጃ በጻፈ እጀ በተመስገን ላይ የተቃጣውን ድብደባ የተሰማኝን ስሜት ሳላንዛዛ በተሰራጨው መረጃ ስር አስተያየቴን እንዲህ በማለት አስቀመጥኩ  ” እርምጃው በማንም ይወሰድ በማን ፣ አላስደሰተኝም! ” በማለት …
     ይህ ከሆነ በኋላ በውስጥ መልዕክት መቀበያ ሳጥኔ ብዙ የተቃውሞና ድጋፍ መልዕክት ደረሰኝ!  የለመድኩት ነበርና ሁሉንም በጥንቃቄ እያነበብኩ አለፍኩት ። ከትናነት በስቲያ ከደረሱኝ መካከል ከላይ የጠቀስኩት መልዕክት እንዲህ ይላል” ሰላም ነብዩ በኢባሲ የደረሰብህ በጣም አሳዝኖኛል አሁን የሰማሁት መረጃክ ስለተመስገን መደብ እጅግ አዝኛለው አንተም ሀቅን እንናገር ስላልክ ከኢባሲክ ከተከለከልክ እደተመስገን አንዳያደርጉህ ተጠንቀቅ ” ይላል መልስ የሚያሻው አስተያየት!…  እርግጥ ነው ባለኝ ትርፍ ሰአት መረጃ በማቀበሌ እና ሃሳቤን ባንሸራሸርኩ ፣ ከተቃዋሚ ጽንፈኛ ተብየ እስከ መንግስት ጽንፈኛ ደጋፊዎች የሚሰነዘርብኝ የማስፈራሪያ የዛቻና የ”እንገድልሃለን !” ፉከራ እኔ ለምጀው ባልፍም ብዙዎቹን ያሳስባቸዋል! ከእኒህ ወዳጆቸ መካከል ምክር ለለገሱኝ ወዳጀ ምስጋና ካቀረብኩ በኋላ በሰጠሁት ምላሽ ከጋጠዎጦች ባልተናነሰ እኔንም ሆነ የዜጎች መብት መገፈፍ ያገባናል የምንልን ወገኖች መብት የማያከብሩ ፣ ሰላም የነሱን ፣ መብት ማስከበሩ ቀርቶ የሚገፉን የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ናቸው የሚል መልሴን ሰጠሁ … በዚህ ዙሪያና በተመስገን በምንም ሚዛን ተቀባይነት የሌለው ድብደባ ዙሪያ የማለዳ ወግ አምዴ ልሞነጫጭር ባስብም ድካም የመጻፍ ፍላጎቴን ጎድቶት እንቢ አለኝ !
ዛሬ ሌሊት ….
በድቅድቁ ጨለማ በነቃሁ ሰአት ይህንን እያሰላሰልኩ መረጃዎችን መፈተሽ ይዣለሁ … በኢቲቪ ጋዜጠኛ በተመስገን በየነ ላይ ደረሰበት የተባለውን ድብደባ ተከትሎ የቅርብ ወዳጆቹ ፣ አድናቂዎቹና  የኢቲቪ ጋዜጠኞች የሰጧቸው አስተያየቶች ተበራክተዋል ። ይህን ሁሉ ቃኝቸ ተመልሸ ገደም እንደልኩ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ  !
በማለዳው ግን ተነሳሁ … እናም ሰሞነኛው ተመስገን አልለቀቀኝም  “ተመስገን አልልም ” እያስባለ ያሚያንሰላስለኝን ሃሳብ ከተጋደምኩበት ቀና ብየ መጻፍ ጀመርኩ  ! ግጥም ሆነ …
ተመስገን ማለቱ ክፉ ነው ባልልም
ስጋቱ ተገፎ ስላላየሁ ዛሬም
ተመስገን ተመስገን ተመስገን አልልም !
የቱ ነው እውነቱ የዝብርቅርቁ አለም ?
ሰው ያለ ሃጢያቱ ከቶ አይወነጀልም ?
ወህኒ አይወረወር አይደበደብም ?
ፍትህን ተነፍጎ ከቶ አይገደለም ?
ለዚህ የሚያስደስት ዛሬ መልስ የለኝም!
ስል በስሜት መነጫጨርሙ … ቀጠልኩ …
ተመስገን ተመስገን ተመስገን ባልልም
ድብደባ ግድያን ፍጹም አልደግፍም !
…  አልኩና አንገቴን አቅንቸ በኩራት ተሞልቸ ተመስገን ተመስገን አልልም ስል የቅርብ ሩቁን ፣ ግራ ቀኙን የነፍስ ማጥፋት እኩይ ምግባር አጠየቅኩ … ምክርም መክሬ ፍላጎት ምኞቴን እንካችሁ አልኩ …
በጠራራ ጸሃይ በሚንቀለቀለው
“ኢትዮጵያዊ ክብሬ” ስላለ ቢከፋው
ቆፍጣናውን መምህር ያን አሰፋ ማሩን ከቶ ማን ገደለው ?
ያንን ጋዜጠኛ ተስፋየ ታደሰን ማነው ያጋደመው?
በምሽት ጨረቃ ድምቅ ፍንትው ባለው ?
ጀኔራል ሃየሎም ማነው የደፈረው ?
በጥይቱ ባሩድ ከእኛ የለያየው ?
ማለዳው ጸሃይ ጸጥ ረጭ ባለው
የደህንነቱን ሰው ክንፈን ገብረ ማን አጠፋው ?
አመት እንኳ ቀርቶ መንፈቅ ባልደፈነው
ወሎ ሰማይ ስር ረግቶ በሚታየው
በምሽት ጨረቃ ሸሁን በጭካኔ ማነው ገዳያቸው?
አልኩና ውጋት ህመም የምለውን ፣ ምክር ዝክር ይሆናል የምለውን ገጣጠምኩትን ! ከሙሉው ግጥም ግጥሜን በቀነጨብኳት ስንኝ ውጌን ልቋጭ …
ችግሩን ለማጥፋት ከሆነ የምናልም
ለድብደባ ፣ እስራት ፣ ለተበራከተው የሰው ልጅ ግድያም
መፍትሄ ፍለጋ ከሆነ ምንሻው እንዳይደጋገም
“ምንድነው ሰበቡ ” ብሎ ማጠየቁ ሳይጠቅም አይቀርም !
ህግ ባለበት ሃገር ግፉ ተበራክቶ ፣ ልዩነቱ ከሰፋ
ችግሩን እንመርምር ያለ መቁረጥ ተስፋ
ፍርድን አናዛባ ፣ ግፉንም አናብዛ ሰውን አናስከፋ
ሃገር አናሰድብ ሰሟን አናስጠፋ
ሰላምን አናውርድ ልዩነቱ ይጥበብ እንድንኖር በተስፋ
ይህን ሳናሟላ ፣ በልዩነት ሰበብ ሰውን አንበድለው
ሰው ከሃገሩ በምድሩ ክብሩን አናሳጣው
መብት በጠየቀ አሸባሪ አንበለው !
ይህን ካደረግ ሰውን ካከበርነው
ማግለልን ካቆምን በዘር በቀለሙ ብሎም በእሳቤው
ያኔ ነው ቀናችን ድብደባ ግድያ የሚጠፋውማ
ያኔ ነው ቀናችን ተመስገን መባያው
እልል የሚባለው ሰለም የሚኖረው!
ጥላቻን አጥፍተን ፣በእርቅ በይቅርታ ደምቀን ስንታይ ነው
ተመስገን  ፣ ተመስገን ፣ ተመስገን የምንለው !
ከእንቅልፍ አንቅቶ ያብተከተከኝን ሙሉ የስንኝ ቋጠሮ በወግ አሰናድቸ እስካቀርበው ለዛሬ የማለዳ ወግ ይህችን  ታክል ካወጋን አይከፋም !  ለእናንተ ለወዳጆቸ መልካም ቀንን ተመኝቸ  አንድየን አመስግኘ እንለያይ ! ፈጣሪ ሆይ አንተን አልፋና ኦሜጋ እናመሰግንሃለን  ! ተመስገን !
ሰላም
ነቢዩ  ሲራክ
ከወይና ደጋው ሳውዲ በአንዷ ከተማ

የሀገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊ በቁጥጥር ስር ዋሉ

የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥር ስር ዋሉ።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለ አባብ መጠቀም  ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል  ተጠርጥረው ነው
ከፌደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው  ተጠርጣሪው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል።
ኮሚሽኑ ግለሰቡ ፈጽመውታል ከተባሉ የሙስና ተግባራት ጋር በተያያዘ ሌሎች ተያያዥ ምርመራዎችን እያካሄደ ይገኛል።
የዛሬ አመት ገደማ ኮሚሽኑ በአቶ ወልደስላሴ  ወንበር ላይ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ አቶ አይቼው ተፈታን በተመሳሳይ ወንጀል ከሷቸው በአሁን ጊዜ  ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው  
አቶ አይቼው ከገቢ በላይ ምንጩ ያልታቀ ሃብት አፍርተዋል የተባሉባቸው ሆቴሎች እና ሌሎች ንብረቶች በአሁን ጊዜ መታገዳቸው ይታወቃል።


ምንጭ ፡-(ኤፍ)

የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ተቃዉሞ በለንደን


የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ተቃዉሞ በለንደን

ብሪታንያ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵዮዉያን በዛሬዉ ዕለት ሎንደን ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ አካሄዱ።
ተሰላፊዎቹ ሰላማዊ ትግሉ ይቀጥላል፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሙስሊሞች መብት ይከበር፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ሃይማኖት ሀገር ናት የሚሉ መፈክሮች ሲያሰሙ እንደነበር ተገልጿል። ሰልፉ የተካሄደዉ በእንግሊዝ የፓርላማ አደባባይ ከፓርላማዉ ፊት ለፊት ሲሆን በስፍራዉ ተገኝታ ሁኔታዉን በተከታተለችዉ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ግምት ከሁለት መቶ በላይ ሰልፈኞች ተገኝተዋል። ወደሎንዶን ደዉዬ ሰልፉ በሚካሄድበት ሰዓት እዚያ የተገኘችዉን ሃናን እና ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱን ስለሁኔታዉ አነጋግሬያለሁ፤
ሃና ደምሴ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ
dw.de

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡- በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ (ከተ/ሚካኤል አበበ)

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡ ክፍል 13
በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

ከተክለ ሚካኤል አበበ

1-      ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው። የአንድነት ምሽት በቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል። የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስም መከሰስም የለበትም። ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስት ወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።
የፖለቲካ ተንታኝና የፖለቲካ መሪ
2-      የፖለቲካ መሪ ከፖለቲካ ተንታኝ መለየት አለበት። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ የጋዜጠኞችንና የፖለቲካ ተንታኞችን/የምሁራንን ስራ ይጋፋል። ያ ብቻም አይደለም። መምራት አቅቶት፤ ወይም መምራት ጠፍቶት፡ በአካልና በስም የፖለቲካ መሪነቱን ወንበር ተቆናጦ፤ በግብር ግን የፖለቲካ ተንታኝነትን ቦታ ይዞ፤ የፖለቲካ መሪነትን ስራ በፖለቲካ ትንታኔ ሊያካክስ ይሞክራል። ያም ብቻ አይደለም፡ የፖለቲካ መሪነት ሚናን ከፖለቲካ ተንታኝ ጋር ያደባለቀ መሪ፤ የያዘውን የፖለቲካ መሪነት ሀላፊነት ከተንታኝነት ሲለሚቀይጠው፤ ትንታኔው ንጹህ አይሆንም። ስለዚህ የፖለቲካ ትንታኔውን መቀበል ይከብዳል። ባይከብድም ትንታኔው ጎዶሎና ወደሁዋላ የሚጎትት፤ ወይንም ወደፊት የማያራምድ ይሆናል። ወይም ትንታኔው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ የሚደረግ ጥልቅ ያልሆነ ትንታኔ ይሆናል።
3-      ለምሳሌ ብርሀኑ ነጋ ባለፈው የኢሳት ስብሰባ ላይ ያቀረበውን የንግግሩን ገጽ 16 መጨረሻና ገጽ 17 መጀመሪያ ብንመለከት ሀሳቡ ጥልቅ ወይም ሀቀኛ አለመሆኑን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/6563 ለዚህም ነው ምሁር ፖለቲከኛ መሆንን ከመረጠ፤ ምሁርነቱን ቀንሶ መሪነቱን እንዲያጠብቅ ግድ ነው የምንለው። ኦባማን ውሰዱ። ኦባማ ሲመረጥ ምሁር ነበር። ከአራት አመት በሁዋላ ግን ምሁርነቱ እየቀነሰ፤ ወደቡሽነት እየተጠጋ መጥቷል። የኦባማ የሶሪያ አቋም፤ ከቡሽ የኢራቅ አቋም ብዙ አይለይም። አሳድን እንበለው ወይም እንብላው እያለ ነው። ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ብርሀኑ ነጋ (ዲባቶ) ያንን መለየት ነው የተሳነው። በፖለቲካ መሪነት መጥቶ (በግንቦት ሰባት ሊቀመንበርነት) የፖለቲካ መሪነቱን ግን ትቶ፤ ምሁር ለመሆን ሞከረ። ተንታኝ። የፖለቲካ ተንታኝ በመሆን የጋዜጠኞችንና የምሁራንን ስራ መሻማት ብቻ ሳይሆን፤ ሁለቱንም ሳይሆን ቀረ። በዚህ ረገድ ጃዋር ይሻላል። እንደተንታኝ በደንብ ይተነትን ነበር። የተንታኝነቱን ሚና ትቶ ባለፈው ሰሞን የራሱን የፖለቲካ አቋም ሲያንጸባርቅም፤ ብዙ ሰዎችን ቢያበሳጭም፤ እቅጩን ነው ያስቀመጠው። ብሬ አድበሰበሰው። በእስር ላይ የሚገኙትም ይሁኑ በነሱ የተተኩትን ከነሱም የቀደሙትን ሙስሊሞች አካሄድና እንቅስቃሴ የሚጠራጠሩ ካሉ፤ ጥርጣሬያቸው በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ነው የተፈጠረው ለማለት ይከብዳል። በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የማይበገሩም ከተጠራጣሪዎቹ ተርታ ውስጥ አሉበትና።
4-      የዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ያልጠራ ትንታኔ የመነጨው፤ ፖለቲካዊ መሪ መሆንና ፖለቲካዊ ምሁር/ተንታኝ መሆንን አጣምሮ ለመሄድ ከመሞከር ነው። የፖለቲካ ተንታኝ የምለው፤ በፖለቲካ ውስጥ በቀጥታ በአድራጊ-ፈጣሪነት ሳይሳተፍ ወይም መሳተፍ ሳይጠበቅበት፤ የአንድን ፖለቲካዊ ስብስብ/ማህበረሰብእ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየቃኝ፤ ከአካባቢያዊና አለማቀፋዊ ሁነቶች ጋር እያጣቀሰ፡ የሁነቶቹን ምክንያት የሚያብራራ፤ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን የሚጠቁም፤ አደጋዎችን የሚተነብይ፡ ተመልካችና ተናጋሪ ማለት ነው። የፖለቲካ መሪ የፖለቲካ ተንታኝ ሲሆን፤ አደናጋሪ ነው የሚሆነው። የፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ተንታኝ መሆን የለባቸውም እያልኩ አይደለም። እኔ የምለው፤ አንደኛ ፖለቲካ መሪዎች የፖለቲካ ትንታኔ ችሎታቸው የሚገለጸው በፖለቲካዊ አመራራቸው በሚወስዱት ፖለቲካዊ እርምጃ ውስጥ መሆን አለበት ነው። ሁለተኛ፡ ፖለቲካን መተንተን የፖለቲካ መሪዎች ዋና የአደባባይ ስራ መሆን የለበትም ነው። እዚያው ድርጅታቸው ውስጥ እንደፍጥርጥራቸው። ይፋዊ ፖለቲካዊ ስራቸው ግን፤ መምራት እንጂ መተንተን አይደለም። አቶ መለስ ከሞቱ በሁዋላ ብቻ ያለውን ሁኔታ እንኳን ብንለመከት ግን፤ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ብርሀኑ ነጋ፤ ከሲሳይ አጌና ጋር ያደረጋቸውን ቃለምልልሶች ወይንም ያለፈው ሰሞንን የኢሳት መድረክ ጨምሮ፤ በቀረበባቸው መድረኮች ላይ የሚናገራቸወን ስንለመከት አድራጊ የፖለቲካ መሪ ሳይሆን፤ ተንታኝ ጋዜጠኛ ወይንም እዚህ አገር እንደሚሉት ጠቢብ ምስክር ለመሆን ነው የጣረው።
5-      ያ ብቻም አይደለም፤ አሁን በእመ-ብርሀን፤ ሰላሳ ድርጅቶች የኢትዮጵያን እጣፈንታ ከህዝብ ጋር ሊመክሩ በተሰበሰቡበት መድረክ ላይ ለመነሻ የሚሆን የአስር ደቂቃ ንግግር አድርጎ የተቀረውን ሰዓት ለህዝብ ውይይት መተው እንጂ፤ የ55 ደቂቃ ድርሳን ማንበብ ምን የሚፈይደው ነገር አለ? ብርሀኑ ነጋ ባለፉት ሶስት ወራት በኢሳትም ይሁን በተለያዩ መድረኮች ያገኘውን እድልና ሰዓት ስንመለከተው ደግሞ የንግግሩ መርዘም ስህተትነትና አበሳጭነት ይጎላል። ያ ብቻም አይደለም፤ ሶስት ሺህ ምናምን አመት፤ መጀመሪያ በጸሀዩም በጨረቃውም በማምለክ፤ ከዚያ ብሉይን በመቀበል፤ ከዚያ ክርስትናን፤ ከዚያ እስልምናን፤ ከዚያ ካቶሊክን፤ ከዚያ ፕሮቴስታነንስዝምን፤ በመቀበልና በማቻቻል ለኖረች አገር፤ የሊበራሊዝምና ዴሞክራሲ መፍትሄ ለሀይማኖት ነጻነት የሚል የአንድ ሰዓት ስብከት ያስፈልጋታል? ቢቀርብንስ?
6-      በዚህ ኢሳት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ፤ ግንቦት ሰባትን ወክሎ ንግግር ካቀረበው ብርሀኑ ነጋ ይልቅ፤ የሽግግር ምክርቤቱ እጥር ምጥን ባለች ባለአራት ገጽ ወረቀቱ፤ የተሻሉ የሽግግር ሀሳቦችን አቅርቧል። http://etntc.org/ENTC/wp/wp-content/uploads/ESAT-Presentation-0818.pdf። እነሱ የሚመኟት ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለበት፤ ሽግግሩ ምን እንደሚመስል፤ የሽግግር ሰነድ የሚያረቅ ኮሚቴ ስለማዋቀራቸው፤ አለማቀፍና አገርአቀፍ የእምቢተኝነት ቡድን ስለማቋቀም፤ ድርጅታቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል። ከሽግግር ምክርቤቱ አራት አመት ቀደም ብሎ የተቋቋመው ግንቦት ሰባት ግን ጥምረት ከተቋቋመ ከሶስት አመት በሁዋላ፤ የከማል ገልቹ ኦነግ ከተመለሰ ከሁለት አመት በሁዋላ፤ ገና ስለድርጅቶች አንድነት፤ በጋራ ትግል ወያኔን ስለማስወገድ አጣዳፊነት ይሰብካል። የዛሬ አመት፡ የዛሬ ሁለት አመት፡ የዛሬ ሶስት አመት ከነበርንበት ብዙም ፈቀቅ አላልንም።
7-      ኢሳት ይሄንን ስብሰባ ማዘጋጀቱ ይደነቃል። ይሁን እንጂ፤ የኢሳት አስተዳዳር የሆነው ወዳጄ ነአምን ዘለቀ የዛሬ አመት አካባቢ እንዲህ ያለው ተመሳሳይ ስብሰባ ሲዘጋጅ፤ (ያኔ ስብሰባው የተዘጋጀው በኢሳት ሳይሆን በግንቦት ሰባትና በነኑሮ ደደፎ (ዲባቶ)/ከማል ገልቹ ኦነግ ነበር)፤ እባክህን መሪዎቹ ንግግር ያሳጥሩና ለሰዉ እንዲተነፍስ ግዜ ይስጡት ብዬ አሳስቤው ነበር። ነአምን አንዳንዴ አይሰማም። ወይም ቢሰማም አያደምጥም። እነሆ፤ ባመቱ፤ ሌላ ውድ መድረክ ባከነ። የብርሀኑ ነጋ ጽሁፍ፤ የመጀመሪያው አስራሶስት ገጽ ለዚያ መድረክ አስፈላጊ አልነበረም። ነገር መቁረጥና ማሰጠር፤ እንዲሁም መድረክ ላይና ምድር ላይ የምናቀርበውን መምረጥ አለብን። ያለበለዚያ ትክክለኛና ውጤታማ ሚናችንን መለየት አለብን።
ተስፋ፡ አድናቆትና፤ ግብዣ
8-      መቼም ተቃጥላችሁ አትሙቱ ያለን ፈጣሪ መጽናኛ አያሳጣንም፤ በግንቦት ሰባት ሊቀመንበር አቀራረብ ብንበሳችም፤ አላህ የሚያጽናናን አላሳጣንም። የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ እኛ በምናደርገው ነገር ምንም ቀስቀስ በማይልበት፤ ፖለቲካዊ አየሩ ጸጥ ረጭ ባለበት ሁኔታ ነው፤ የዛሬ ሶስት ወር አካባቢ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ የተሳካ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ላለፉት ስምንት አመታት ሰልፍ አይታ ለማታውቀው አዲስ አበባ ሀያ መቶም የሁን ሀያ ሺህ ሰው ያስወጣ ሰልፍ ተከሰተ። ያ ያጽናናል። እነሆ ያኔ በያዙት ቀጠሮ መሰረት፤ ሁለተኛው የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በመጪው እሁድ ይቀጥላል። መቼም ብዙዎቻችን ፈሪዎችና ሸሺዎች በሆንበት ሁኔታ፤ ጥቂት ዠግኖች አልጠፉምና፤ የሰማያዊ ፓርቲዎች ድፍረትና ቁርጠኝነት የሚያስደንቅ ነው። የህወሀት ኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር በኩል ሰልፉ ህገወጥ ነው ቢሉም፤ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ግን ሰልፉ ህጋዊ ነው፤ እንገፋበታለንም እያሉ ነው። የመጪው እሁድ ትልቅ ተጋድሎ ዋዜማ ላይ ነን።
9-      እንዲህ ያለውን ትእይነት ቆሞ መመልከት ብቻ ግን ነውር ነው። መቼም አንዴ ሸሸተን ወጥተናል፤ በወጣንበትም ቢሆን ግን፤ የምንችለውን እንኳን በማድረግ ተዋናይ መሆንም አለብን። የኛ የተቀናቃኙ/ተፎካካሪው/ተቃዋሚው ጎራ፤ በተለይ በውጪ የምንኖረው ተቃዋሚዎች ትልቁ ችግር፤ ማድረግ የምንችለውን እንኳን ማድረግ አለመቻላችን ነው። በሰላማዊም ይሁን ደማዊ መንገድ፤ በአመጽም ይሁን በጸሎት ለሚታገሉት ስንቅና ትጥቅ ማቀበል። ስንቅና ትጥቅ ላለማቀበል ብዙ ምክንያት መደርደር ይቻላል። ምንም ምክንያት ግን አጥጋቢ አይሆንም። ቅዳሜና እሁድ የዱለትና የቁርጥ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ እያብራራ የሚተነትነው፤ የምእራባዊያንን ሴራ የሚመሰጥረው ወዳጄ፤ የኢሳት ዝግጅትን የ20 ብር ትኬት ስሰጠው ፊቱን እንዳጨፈገገው መሆን የለብንም። ለሰማያዊ ፓርቲ ሁለተኛ ሰልፍ መሳካት እንጸልያለን። በጸሎት ብቻ አናበቃም። በግብርም እንከተላለን።
10-   መቼም በየከተማው ብዙ የማይደክማቸው ሰዎች አሉ። እነሆ በመጪው ቅዳሜ ማታ፤ በዚህ በኛ ከተማ ትንሽ ተንፈስ እንላለን። ተሰብስበን ኢህአዴግን ከመዘልዘል ባሻገር፡ የትግሉ በረከት እንጥፍጣፊ ይደርሰን ዘንድ የአንድነት ምሽት ያዘጋጁ አሉ። “የአእላፋት ድምጽ ለነጻነት” የተሰኘውን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ዘመቻ በመደገፍ እዚህ ቶሮንቶ ከተማ፤ እንደፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር፤ ቅዳሜ ኦገስት 31 ማታ ከ6ሰኣት ጀምሮ’፤ 2050 ዳንፎርዝ ጎዳና በሂሩት ሬስቶራንት የቤተሰብ አዳራሽ የእራት ምሽት ተዘጋጅቷል። በሰሀን $ 50 ብቻ። ለጥንዶች $ 60። ለኔቢጤው ደሀ ደግሞ $ 30 ብቻ። ገቢው፤ ከወጪ ምላሽ ለአንድነት ፓርቲ የሚሄድ ነው።
11-   እነሆ፤ በአካል ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ጋር ላንዘምት እንችላለን። በአካል ከሰማያዊ ፓርቲም ጋር አንሰለፍ ይሆናል። ከአንድነት የነጻነት ድምጾች ጋር ለመጮህ ግን አይሳነንም።ለሚጮሁት ጉልበት፤ ለሚሰለፉት ብርታት፤ ለሚዘምቱትም ጽናት ልንለግስ እንችላለን። በያለንበት አካባቢ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንርዳ። እዚህ ቶሮንቶ ያለን፤ ቅዳሜ ሂሩት ሬስቶራንት ብቅ እንበል። ቅዳሜ እንኩዋን፤ ላሊበላና ብሉናይል፤ ዞብልና ራንዴቩ ይቅሩብን። ቅዳሜ ማታ፤ ሂሩት ጋር እንገናኝ።
እኛው ነን። ከቶሮንቶ። ነሀሴ፡ 2005/2013።

Friday, August 30, 2013

ከአህያ ጋር ብጣሪ በልታ ከፈረስ ጋር ገብስ ትበላለች

946847_524794230895033_334002608_n
August 30, 2013
ከአድባይነት እርግማን ይሰውረን!”
የሃይማኖት መሪው ቡድሐ የሚሰጠን አንድ እንቆቅልሽ የሚከተለውን ይመስላል። አንድ ነጋዴ ሩቅ ሄዶ ሲመለስ፤ ቤቱ በሽፍቶች ተዘርፎና ተቃጥሎ ይደርሳል፡፡ ከቤቱ ከተረፈው ረመጥ – መካከል አንድ ተቃጥሎ የከሰለ የሰው ገላ ያያል፡፡ “ይሄ ትንሹ ልጄ መሆን አለበት” አለ፡፡ በዚህ ምክንያት ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ደረቱን መታ፡፡ ፀጉሩንም ነጨ፡፡ ገላውን እንደገና የማቃጠል፤ የሐዘን ሥነ-ስርዓት እንዲካሄድም አደረገ፡፡
ይህ ወንድ ልጁ ነው፡፡ ከልጁ የናፍቆት ስሜት ለመላቀቅ በጭራሽ ካለመፈለጉ የተነሳ፣ ለቅጽበት እንኳ ሳይለየው የልጁን አስከሬን አመድ በከረጢት አንጠልጥሎ ይዞር ጀመር፡፡ ቆይቶም ከሀር የተሰራ ከረጢት አሠርቶ ይሸከመው ጀመር፡፡ ቀን ከሌት ይዞት ይዞራል፡፡ ሥራም ቦታ ቢሆን ተሸክሞት ይውላል፡፡ በእረፍት ሰዓቱም እንደዚያው፡፡ ከአመዱ የሚለይበት አንዳችም ደቂቃ የለም፡፡
አንድ ሌሊት፤ ለካ ወንድ ልጁን ሽፍቶቹ አግተው ወስደውት ኖሮ፤ ከታሠረበት አምልጦ አባቱ አዲስ ወደ ሠራው ቤት ይመጣል፡፡ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ደርሶ፤ የአባቱን ቤት በር በስሜት ፍንድቅድቅ ብሎ አንኳኳ፡፡ አባቱ፤ አሁንም የከረጢት አመዱን እንደተሸከመ ነው፡፡ “ማነው፤ በዚህ ሌሊት የሚያንኳኳው?” አለና ጮኾ ጠየቀ፡፡ “እኔ ነኝ ወንድ ልጅህ ነኝ አባባ” አለ ልጁ፤ በበሩ ሽንቁር እያየ
“አንተ ባለጌ ሰው፤ አንተ “የእኔ ልጅ ልትሆን ከቶ አትችልም፡፡ የእኔ ልጅ ከሶስት ወር በፊት ሞቷል፡፡ አመዱ እዚሁ እጄ ውስጥ አለ” አለው፡፡ ትንሹ ልጅ ግን በሩን መደብደቡን ቀጠለ፤ ጮኾ፤
“ኧረ አባባ እኔ ያንተው ልጅ፣ የምታውቀኝ ውዱ ልጅህ ነኝ፤ አስገባኝና እየኝ!” ደጋግሞ ለመነው፤ ተማጠነው፤ አባትዬው ግን፤ “ዘወር በል ብዬሃለሁ! ከዚህ ወዲያ አልታገስህም፡፡ ድራሽህ ይጥፋ! አለዚያ ብትንትንህን ነው የማወጣህ”
ለመጨረሻ ጊዜ ልንገርህ፤ የእኔ ልጅ በሽፍቶች ተቃጥሎ ሞቶ፣ እኔ አስከሬኑን አመድ አድርጌ፣ አመዱን ተሸክሜ ስዞር ከርሜያለሁ፡፡ ስለዚህ አንተ የመጣኸው የልጄን ሐዘን ዳግመኛ ለመቀስቀስና የእኔን አንጀት ለማቃጠል ነው! አንት ጨካኝ አረመኔ፤ ጥፋ ከፊቴ ይለዋል። ልጅየው ተስፋ ቆርጦ ሰፈሩን ጥሎ ጠፋ፡፡ አባት፤ በህይወት ያለ እውነተኛ ልጁን ለአንዴም ለዘለዓለም አጣ፡፡* * *እንደ ቡድሐ አመለካከት፤ ከአንድ አስተሳሰብ ጋር እኝኝ ብለን ከተጣበቅንና “አንዱና አንዱ እውነት” ይሄ ብቻ ነው ብለን ካከረርን፣ እውነተኛውን እውነት የማወቅ እድላችንን እንዘጋለን። እውነት እንድ ሰው ደጃፋችሁ ቆሞ ቢያንኳኳም እንኳ የአዕምሮአችሁን በር ለመክፈት ዝግጁ አትሆኑም፡፡ ስለዚህ ስለ አንድ እውነት የምትገነዘቡበትን መንገድ ሥራዬ ብላችሁ መርምሩት፡፡ ተጠንቀቁ፡፡
የነገር ሁሉ መጀመሪያው፤ ከሃሳብ እሥር ነፃነትን ማወጅ ነው፡፡ ይህን እውነት ወደ እኛ አገር ፖለቲካ ስንመነዝረው፤ ቁልጭ ያሉ አመድ የማቀፍና ህያው ልጅን የመካድ፤ እውነታን እናገኛለን፡፡ እውነተኛውን ልጃችንን እንለይ፡፡ በከረጢት ውስጥ ያለው አመድ በህይወት ካለው ልጅ የተለየ መሆኑን እርግጠኛ እንሁን፡፡ ከአመዱ ከግትር ሃሳባችን እንገላገል፤ እኛ የጀመርነው መንገድ ብቻ ነው ዳር የሚያደርሰው ብለን ድርቅ ከማለት አባዜ ተላቀን የጀመርነው መንገድ መጨረሻ የማያሳልፍ -ግድግዳ (Dead End) ቢሆንስ? አብረውን ከሚጓዙት መካከል ሃሳባቸውን የሚለውጡ ቢገኙስ? የመኪናው ጐማ ቢተነፍስስ? የባቡሩ ሃዲድ ቢጣመምስ? ብለን እንጠይቅ።
አንድ የአገራችን ፀሐፌ ተውኔት እንዳለው፤ “ገና ላልተወለደ ልጅ ሥም እናውጣ ብለን ለምን እንጣላለን፡፡“ዐይናማው” ብለነው እውር ሆኖ ቢወለድስ? ክንዴ ብለነው እጁ ቆራጣ ቢሆንስ?…” ብለን መጠራጠር ቢያንስ ከጭፍንነት ያድነናል። ከአንድ መሥሪያ ቤት በሙስና፣ በፍትሐዊነት ወይም በኢዲሞክራሲያዊነት፤ በግምገማ የተነሳን ሰው ለሌላ መሥሪያ ቤት በኃላፊነት ማስቀመጥ አልሸሹም ዞር አሉ፤ ነው፡፡
ይሄኛው መሥሪያ ቤት አንቅሮ የጣለውን ግለሰብ ያኛው መሥሪያ ቤት በምን ዕዳው ይሸከማል? የሀገሪቱን የሥራ ሂደት ባለቤቶች በበኩር ልጅነት አቅፈንና “የባለቤቱ ልጅ” አሰኝተን ስናበቃ በሀቅ የሚለፉላትን ሀቀኛ ልጆች በር እያንኳኩ ሳንከፍት እያባረርናቸው ምን ዓይነት ለውጥ ማምጣት ይቻለናል?
በቡድናዊና ድርጅታዊ መንፈስ፤ እስከመቼ እከክልኝ፤ ልከክልህ ተባብለን እንዘልቀዋለን?“እብድ ሆኜ ስለማላውቅ፣ እብድ የሚያስበውን አላውቅም፤ ዝም፣ ጭጭ ብለህ ተቀምጠህ ሳይህ ምናልባት ይሄ እብደትህ ልዩ ሰላም ሰጥቶህ ይሆንን? ብዬ እቀናብሃለሁ፤ መንሳፈዊ ቅናት ማለቴ ነው” ይላል የአገራችን ፀሐፊ፡፡
ዝምታ ማስቀናቱ ይገርማል፡፡ ስንት ግፍ ሲሰራ እያየህ ዝም ስንት ዘረፋ ሲካሄድ እያየህ ዝም፤ ጓዳህ እየተራቆተ፤ ኢኮኖሚህ እየተንኮታኮተ እያየህ ዝም ለማለት ከቻልክ የሚያስቀና ዝምታ አለህ፤ ታድለሃል ማለት ነው፡፡ ከእብደት ውስጥ የሚገኘው ልዩ ሰላም ይሄ መሆኑ ነው፡፡ ዝም የሚሉ ያሉትን ያህል፣ ሃያ አራት ሰዓት በመለፍለፍ እኛ ነን ጀግና የሚሉም አገራችን ያፈራቻቸውና በተገለባባጭነት፣ በአድር ባይነት፣ በጥገኝነት ንፍቀ – ክበብ ውስጥ የሚኖሩ አያሌ “ቀልጣፋ” ሰዎች አሉ፡፡ ከጠቆረው መጥቆር፣ ከነጣው መንጣትን ተክነውበታል፡፡“እንደ ወዶ-ገባ ኮርማ፣ ተነስ ሲሉት የሚነሳ፤ ተኛ ሲሉት የሚተኛ!” ያለው ዓይነት ነው ገጣሚው፡፡
ከየትኛውም ማዕድ ለመቋደስ እጃቸውን (የዓለም የእጅ መታጠብን ቀንን እያከበረ እንደማለት) ታጥበው፣ ዝግጁ ሆነው የሚጠብቁ ናቸው፡፡ ለእነሱ ፖለቲካ በየትኛውም የሳንቲሙ ገጽ – ማለትም በአውሬውም በሰዉም በኩል – ለመጠቀም የሚችሉ ናቸው፡፡ መቼም ቢሆን መቼም በየትኛውም ገዢ ዘመን አድርባይነታቸውን አያቋርጡም። The pendulum of opportunism never stops oscillating እንዳለው ነው ሌኒን፡፡ “ከአህያ ጋር ብጣሪ በልታ፣ ከፈረስ ጋር ገብስ ትበላለች” ይለዋል የወላይታው ተረት፡፡ ከአድባርባይነት እርግማን ይሰውረን!
ታክሎ

http://daniboy8935.wordpress.com/2013/

“ምስጢር ያልሆኑ ምስጢራት” ‑ ድንበር ተሻጋሪው የኢሕአዴግ ዕኩይ ፕሮፖጋንዳ

946847_524794230895033_334002608_n
August 30, 2013
ከኢትዮጵያዊ ሙስሊም
እዚህ አሜሪካ ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የሚሰራጨው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ራዲዮ ጣቢያ በቅርቡ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ነፃነትና መብትን የማስከበር ሰላማዊ ትግልን ከ‹ፖለቲካዊ እስልምና› ጋር ለማያያዝ የሚቃጣ “የራዲዮ ዝግጅት” አቅርቧል፡፡ ዝግጅቱ ዊኪሊክስ በተሰኘው ድረ‑ገፅ አምና ይፋ የተደረጉ የስቴት ዲፓርትመንት ምሥጢራዊ ሰነዶችንና ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ከተከሰቱ ግጭቶች ጋር የተያያዙ የድምፅ ግብዓቶችን በመጠቀም ወቅታዊውን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት ነፃነትን የማስከበር ሰላማዊ ትግል ከ‹ፖለቲካዊ እስልምና› ጋር በማያያዝ ጭቃ ለመቀባት፣ ብሎም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችን ግንዛቤ ለማዛባት ይሞክራል፡፡
ይህ ጽሑፍ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየተነዛና እየተሰበከ ባለው ጥላቻና ግጭትን የመቀስቀስ ዓላማ ያዘለ ፕሮፖጋንዳ አኳያ፣ ወቅታዊውን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት ነፃነትን የማስከበር ሰላማዊ ትግል በአጭሩ በማስቃኘትና፣ በአሁኑ ወቅት መንግሥትና አጫፋሪዎቹ እያካሄዱ ያሉትን ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ያለመ ዕኩይ ዘመቻ አደገኛነት በማመላከት ዓላማ የተዘጋጀ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ራዲዮ ያቀረበውን ዝግጅት አሉታዊነት በድፍኑ ከመተቸት ይልቅ፣ በዝግጅቱ ይዘት ላይ ያተኮረ ሰፋ ያለ ሒስ ማቅረብ አስፈላጊ ይመስለናል፡፡ እናም በዚህ ጽሑፍ የራዲዮ ጣቢያው ባቀረበው ዝግጅት ይዘት ጥቂት አንኳር ጉዳዮች ላይ በማተኮር የጣብያውን አሳዛኝና አሳፋሪ ሥራ ለማስቃኘት እንሞክራለን፡፡
ምሥጢራዊ ሰነዶችና ይፋ የመውጣታቸው ፖለቲካዊ አንድምታ
የዳያስፖራው ራዲዮ “በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እስልምና እየተስፋፋ ነው” የሚል ክስ ያቀርባል፡፡ ለዚህ ክሱ ካቀረባቸው ማስረጃዎች መካከል ‹ዊኪሊክስ› የተሰኘው የዊሊያም አሳንጅ ድረ‑ገፅ ይፋ ያደረጋቸውን ከስቴት ዲፓርትመንት ያፈተለኩ ምሥጢራዊ ሰነዶች ይገኙበታል፡፡ እንደ ማስረጃ በተጠቀሱት ‹ዊኪሊክስ› ይፋ ያደረጋቸው ሰነዶች ይዘት ላይ ከማተታችን በፊት ግን፣ የእነዚህ ሰነዶች ከስቴት ዲፓርትመንት ዳታቤዝ ተሠርቆ በ‹ዊኪሊክስ› ድረ‑ገፅ ይፋ የመደረጉን ፖለቲካዊ አንድምታዎች መመልከት ተገቢ ይመስለናል፡፡
እንደሚታወቀው፣ ማንኛውም መንግሥት በ“ጥብቅ ምስጢር”ነት የሚይዛቸው ጉዳዮች ይኖሩታል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰነዶች “ጥብቅ ምስጢር” (CLASSIFIED) በሚል ተፈርጀው በጥንቃቄ ይቀመጣሉ፡፡ በመንግሥት ሥራ ላይ አንድን ጉዳይ “ጥብቅ ምስጢር” የሚያደርጉ ተቀባይነት ያላቸው ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል አንዳንድ ጉዳዮች/ሰነዶች በ“ጥብቅ ምስጢር”ነት የሚይያዙት ይፋ ቢሆኑ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተቃውሞን ሊያስነሱ፣ ጠንካራ ትችትና ውግዘት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ስለሚታወቅ ነው፡፡ በ“ጥብቅ ምስጢር”ነት የሚያዙ ጉዳዮች/ሰነዶች ይፋ መውጣት ብሄራዊ እና/ወይም ዓለምአቀፍ ሕግን መሠረት ያደረገ ተጠያቂነትን ሊያስከትል፣ ወይም ደግሞ እንደ ይዘቱ በአገራት ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ የሆኑ ኦፊሴላዊ የ“ጥብቅ ምስጢር” ሰነዶች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ከደረሱ፣ እንደሁኔታው በምሥጢር ሊካሄዱ የታቀዱ መርኃ‑ግብሮችን ሊያሰናክሉም ይችላሉ፡፡
በብዙ አጋጣሚዎች መንግሥታት፣ ይበልጡኑም በከፍተኛ የሥልጣን እርከን ላይ ያሉ ፖለቲከኞች ዕውን ሊያደርጉ የሚሹትና በአደባባይ ለህዝብ የሚናገሩት ፍፁም ለየቅል ሊሆን ይችላል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ የአንድን መንግሥት ተግባራት እውነተኛ መግፍዔ (Motive) ለማወቅ፣ አልያም የቅርብ ግምት ለመስጠት የሚቻለው በጥልቅ ፖለቲካዊ ትንተና ነው፡፡ … በዓለምአቀፍ የቴሌቪዥን ኔትወርኮች ዘወትር እንደምናየው፣ የአንድን መንግሥት እርምጃዎች፣ ውሳኔዎች ወይ የአቋም ለውጦች ከተለያዩ ማዕዘናት በመዳሰስ በይፋ ያልተነገሩ ብዙ መረጃዎችን የሚሰጡት የፖለቲካ ተንታኞች ናቸው፡፡ ግና ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው በ“ጥብቅ ምስጢር”ነት የተያዘ የመንግሥት ሰነድ ድንገት ሾልኮ ቢወጣስ? ይህ ሲሆን፣ የፖለቲካ ተንታኙን የዙርያ‑ገብ ትንተና ድካም በመቀነስ፣ በቀላሉ ወደ እውነተኛው የጉዳዩ ምንነት ያደርሳል፡፡ በ“ጥብቅ ምስጢር”ነት የተያዘ የመንግሥት ሰነድ ይፋ መውጣት እንደ ጉዳዩ የክብደት ደረጃ አንድን መንግሥት በከፍተኛ ኃፍረት አልያም ቅሌት ውስጥ ሊከተውም ይችላል፡፡
በዚህ ማዕቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ራዲዮ ጣቢያ ባቀረበው ዝግጅት በስፋት ያጣቀሳቸውን በ‹ዊኪሊክስ› ይፋ የተደረጉ የስቴት ዲፓርትመንት “ምስጢራዊ ሰነዶች” በምን መልኩ ለዕኩይ ዓላማ እንደዋሉ ስናይ በጣም እንገረማለን፡፡ … እናዝናለንም፡፡
“ዊኪሊክስ” ማንን እና ምንን ነው ያጋለጠው?
በመሠረቱ፣ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸው የስቴት ዲፓርትመንት “ምሥጢራዊ ሰነዶች” በአሁኑ ወቅት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እያካሄዱ ከሚገኙት ሕገ‑መንግሥታዊ የሃይማኖት ነፃነትን የማስከበር ትግል ጋር ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ግንኙነት የላቸውም፡፡ በአንጻሩ ግን “ምሥጢራዊ ሰነዶቹ” የኢሕአዴግ መንግሥት ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት ነፃነት ላይ የከፈተው ግብታዊነት የሚታይበት “የጥሰት ዘመቻ”፣ የአሜሪካ መንግሥት “አሳስቦኛል” ከሚለው አንድ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ሳይኖረው እንዳልቀረ ይጠቁማሉ፡፡ ሰነዶቹ ከምንም በላይ ዛሬ የኢሕአዴግ መንግሥት ከህዝበ‑ሙስሊሙ ጋር የተፋጠጠበት ጉዳይ፣ በኢትዮጵያዊ ዓይን የታየ ሳይሆን፣ በአሜሪካ መንግሥት ዓይን የታየ፣ በአሜሪካዊኛ የተተነተነ፣ በአሜሪካ ልዩ ፍላጎት ላይ ተመሥርቶ የተቃኘ መሆኑን ነው በግልፅ የሚያሳዩት፡፡ … ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዳያስፖራ ራዲዮ ጣቢያ፣ የአሜሪካ መንግሥት በራሱ ምክንያት ምሥጢር አድርጎ ሊይዝ ይፈልገው የነበረውን ይህን ሰነድ በማጣቀስ፣ ወቅታዊውን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሃይማኖት መብትን የማስከበር ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማጠልሸት ዓላማ አውሎታል፡፡ ይህ በአንድ በኩል በጣም የሚያስቅና የጣቢያውን ብስለት-የለሽነት የሚያሳይ ሲኾን፣ በሌላ በኩል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፍትኅና የነፃነት ተሟጋቾች (አክቲቪስቶች) ከአንድ ዓመት በፊት በፌስቡክ ላይ እንደነገሩ ነካክተው ያለፉትን ነገር ዛሬ ጠበቅ አድርገን እንድንመለስበት የጋበዘ በመሆኑ የሚመሰገን ነው፡፡
እስከምናውቀው ድረስ፣ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸው አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ስቴት ዲፓርትመንት የተላለፉ “ምሥጢራዊ ሰነዶች” በቁጥር ሦስት ሲኾኑ፣ ሦስቱም እ.አ.አ በኦገስት 2009 (በኢት. አቆጣጠር በነሐሤ 2001) የተዘጋጁ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰነዶች፣ የኢሕአዴግ መንግሥት በኢት. አቆጣጠር በሐምሌ 2003 በይፋ የጀመረው የአህባሽ አስተምህሮን በህዝበ‑ሙስሊሙ ላይ የመጫን መርኃ‑ግብር፣ ከዚያ ሁለት ዓመታት ቀደም ብሎ የአሜሪካ መንግሥት በዊኪሊክስ ላይ ባንፀባረቀው በጥልቀት ያልተተነተነ ስጋት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ነው ያጋለጡት፡፡ … እነዚህ “ምሥጢራዊ” የነበሩ ሰነዶች በይዘታቸው በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ መንግሥት በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ እያካሄደ የሚገኘው የአገሪቱን ሕገ‑መንግሥት የሚጻረር (የሃይማኖት ነፃነትን የመገደብ) መርኃ‑ግብር በእውነትና በእውቀት ላይ የተመሠረተ ከመሆን ይልቅ፣ የአሜሪካ መንግሥት ከራሱ ዕይታ ያንፀባረቀው፣ ኢሕአዴግ በጥልቀት ሳያጠናውና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሙስሊም ዜጎቹ (ቢያንስ ከሚያምናቸው ሙስሊም ምሁራን) ጋር ሳይማከርበት ዓይኑን ጨፍኖ በግብታዊነት ሊያስፈጽም የተቀበለው የቤት ሥራ መሆኑን ነው በግልፅ የሚያሳዩት፡፡ ዊኪሊክስ ምሥጢራዊ ሰነዱን ይፋ ባያደርግ ኖሮ፣ የአሜሪካ መንግሥት እ.አ.አ እስከ 2019 (በኢት. አቆጣጠር እስከ ነሐሤ 2011) ድረስ ይህንን ሐቅ በምሥጢር ሊይዘው ነበር የፈለገው፡፡ ምናልባት ሰነዱን ምሥጢር ማድረግ የተፈለገው ተግባሩ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንደመግባት ሊቆጠር ይችላል ከሚል ስጋት በመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራው ራዲዮ “እኛ” በተሰኘ ፕሮግራሙ፣ በዊኪሊክስ ይፋ በመደረጋቸው የአሜሪካ መንግሥትና ኢሕአዴግ የተጋለጡባቸውን እኒህኑ በምሥጢር ተይዘው የነበሩ ሰነዶች ዋቢ በማድረግ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሃይማኖታዊ ነፃነታቸው ላይ የተቃጣውን ጥሰት በመቃወም የሚያካሂዱትን ሰላማዊ ትግል ሊያጠለሽ ይሟሟታል፡፡ የራዲዮ ጣቢያው ዝግጅት ከአገረ‑አሜሪካ ለሚገኝ ዳረጎት ሲሉ የ“አክራሪነት”ን ነጋሪት እየጎሰሙ ሙስሊሙን ዜጋ ቁም ስቅል የሚያሳዩት ገዢዎቻችን የተጋለጡበትን “የአደባባይ ምሥጢር” እየተረከ፣ በአገሪቱ ሕገ‑መንግሥት ስለተደነገገው የሃይማኖት ነፃነታቸው መከበር የሚጮሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በ‘ፖለቲካዊ እስልምና’ አስፋፊነት በመወንጀል ሊያሸማቅቅ ይሞክራል፡፡ በሌላም በኩል፣ የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ሕጋዊ፣ ፍትኃዊና ሰላማዊ ጥያቄ ደግፈው የቆሙ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችንን ግንዛቤ ለማዛባትና የሙስሊም ወገኖቻቸውን ሰላማዊና ሕጋዊ ትግል በጥርጣሬ እንዲመለከቱት ለማድረግ ይተጋል፡፡ በዚህ ብቻ ግን አያበቃም፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአገራችን አንድ ክፍል በተከሰተ የማንም አዕምሮ የማይቀበለው ግጭት ላይ የደረሱ ጥፋቶችን፣ ስሜት በሚኮረኩሩ የድምፅ ግብዓቶች አጅቦ በማቅረብ፣ ሙስሊም ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በሙስሊም ወገኖቻቸው ላይ ጥላቻና ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው የሚገፋፋ መሠሪ ፕሮፖጋንዳ ይነዛል፡፡ እግረ መንገዱንም፣ ወቅታዊውን የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ የመብት ትግል ስውር ዓላማ ያለው ለማስመሰል ዳር ዳር ይላል፡፡
በቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ አማካይነት የተዘጋጀውና ዊኪሊክስ ይፋ ያደረገው የመጀመርያው ሰነድ ‹‹GROWING WAHABI INFLUENCE IN ETHIOPIA: AMHARA›› የሚል ርዕስ አለው፡፡ ሰነዱ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የህዝብ ጉዳዮች ክፍል (Public Affairs Section) ኃላፊዎች በአማራ ክልል፣ ደሴ አቅራቢያ በሚገኙ የገጠር ወረዳዎች (እ.አ.አ. ከጁን 3‑5፣ 2010) ባካሄዱት የሦስት ቀናት ቅኝት ላይ ተመሥርቶ የተዘጋጀ ነው፡፡ የኤምባሲው ባልደረቦች ይህን ቅኝት ያካሄዱት ከአንድ የዞን መሥተዳድር ኃላፊ ጋር መሆኑም በሰነዱ ላይ ተጠቁሟል፡፡ …
ሰነዱ በአማራ ክልል ‹ወሃቢያ› የተባለው የእስልምና አስተምህሮት እየተስፋፋ መሆኑን፣ በገጠር ከተሞች በርካታ መስጊዶች ከኩዌት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኘ ፈንድ መታነፃቸውን፣ የኤምባሲው ኃላፊዎች በጎበኟቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሙስሊም ሴቶች ሃይማኖታዊ አለባበስ በመከተል ፊታቸውን እንደሚሸፍኑ፣ ወንዶች ደግሞ ሱሬያቸውን እንደሚያሳጥሩ፣ ፂማቸውን ግን እንደማያሳድጉ ወዘተ. ይጠቃቅሳል፡፡ በተጨማሪም፣ የወሃቢያ አስተምህሮ የነቢዩ ሙሐመድን ልደት (መውሊድ) ማክበርን ስለሚቃወም፣ በዚህ ረገድ በወሃቢ አስተምህሮና በሱፊ አስተምሀሮ ተከታዮች መካከል፣ በተለይ የሱፊ እስልምና ተከታዮች መውሊድን በሚያከብሩበት የጀማ ንጉስ መስጂድ አካባቢ ከዚያ ቀደም ባለ ጊዜ ሁኔታው ወደ ግጭት አምርቶ እንደነበረ ይገልፃል፡፡ አክሎም የሱፊ እስልምና ተከታዮች የመውሊድ በአልን ለሚያከብሩበት የጀማ ንጉስ መስጂድ እድሳት በማድረግ ባህላዊ ቅርሱን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት ያወሳል፡፡ ለዚህም አሜሪካ ከአምባሳደሩ የባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ ፈንድ ድጋፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት ይጠቁማል፡፡ [http://wikileaks.org/cable/2009/07/09ADDISABABA1672.html#]
ሰነዱ የኤምባሲው የስራ ኃላፊዎች ለሦስት ቀናት ባካሄዱት ቅኝት፣ ከአካባቢው መስተዳድር የሥራ ኃላፊ እንዲሁም ከወቅቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) በተገኘ መረጃ ላይ ተመሥርቶ፣ በኢትዮጵያ የወሃቢ አስተምህሮ መስፋፋት ለዘመናት የቆየው የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች የመቻቻል ዕሴት አደጋ እንደተደቀነበት ይጠቅሳል፡፡ ሰነዱ በገፅ 3 [8.(C)] በዚህ ጉዳይ ላይ ጠቅላይ ምክር ቤቱን ሲጠቅስ እንዲህ ይላል፡‑
the IASC continues to be very concerned about growing Wahabi influence in Ethiopia. The newly appointed Council is decidedly anti-Wahabi and speaks openly of their concern about Wahabi missionaries and their destabilizing influence in Ethiopia.
ሰነዱ በገፅ 4 (13.(C)) ላይ ደግሞ የመጅሊሱን ኃላፊዎች ዋቢ በማድረግ በወቅቱ (እ.አ.አ. በ2010) መጅሊሱ ከወሃቢ አስተምህሮ ተከታዮች እንደፀዳ ይጠቅሳል፡፡
13. (C) In a shift from past practice, the IASC is now completely purged of Wahabi members. […] the Council members acknowledged that the Council is now all Sufi and in their public statements they repeatedly make reference to Ethiopia’s tradition of religious tolerance and co-existence with the Christian communities.
በተጨማሪም በዚሁ ገፅ ላይ፣ የእስልምና ምክር ቤቱ [የአመራር] አባላት በመንግሥት እንደሚሾሙ በግልፅ ይናገራል፡‑
As the Ethiopian government appoints the members of the Islamic Council, it is clear that the GoE shares this concern about growing Wahabi influence and is supporting moderate Muslim leaders in trying to counter that influence.
እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ቁም ነገር የመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የጋራ ተቋም እንደሆነ በሚታሰበውና ለረዥም ጊዜያት የሱፊና የሰለፊ አስተምህሮ ተከታዮች በጋራ ሲያስተዳድሩት በኖረው መጅሊስ ላይ፣ በዚህ ወቅት (እ.አ.አ. በ2010) መንግሥት ሙሉ በሙሉ የአህባሽ አስተምህሮ ተከታዮችን የሾመ መሆኑ ነው፡፡ የአህባሽ አስተምህሮ፣ ከሰለፊ አስተምህሮ ጋር የከረረ ተቃርኖ እንዳለው የሚታወቅ ሲኾን፣ በሰለፊ አስተምህሮ ተከታዮች ላይም እጅግ የመረረ ጥላቻ ያንፀባርቃል፡፡ ከዚህ በላይ በጠቀስነው የዊኪሊክስ ሰነድ ላይ እንደተመለከተው፣ መንግሥት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ላይ የአህባሽ አስምህሮ ተከታዮችን የሾመው ለዘብተኛ ሙስሊሞችን በመደገፍና የወሃቢን ተፅዕኖ ለመቋቋም ነው ተብሏል፡፡ ይህም ‹‹እርምጃው የወሃቢ አስተምህሮ በሃይማኖቶች የመቻቻል እሴት ላይ ደቅኖታል የሚባለውን ስጋት የማስወገድ ዓላማ ያለው ነው›› የሚል አንድምታ አለው፡፡ ነገር ግን እውን ሐቁ ያ ነዉን? የወሃቢ አስተምህሮ ደቅኖታል የተባለውን ስጋት የማስወገጃው መንገድስ ይህ ነውን? ብለን ስንጠይቅና … መሬት ላይ ያለውን ሐቅ ስንፈትሽ የምናገኘው ምላሽ ይህንን አያረጋግጥልንም፡፡ [ለዚህ አባባላችን ዋቢ የሚሆኑ ተግባራዊ ምሳሌዎችን ወደኋላ ላይ እናቀርባለን፡፡]
ዊኪሊክስ ይፋ ባደረጋቸው ሰነዶች ላይ፣ የአሜሪካ መንግሥት የሱፊ ስርዓተ‑አምልኮ የሚከናወንባቸውን ጥንታዊ መስጂዶችና የቅዱሳን የመቃብር ሥፍራዎችን ጠብቆ በማቆየት ዓላማ መሠራት አለባቸው ብሎ የሚያምናቸው ተግባራት ተጠቅሰዋል፡፡ … የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ በተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ፀንቶ የኖረው የመቻቻል ባህል በዘላቂነት ይቀጥል ዘንድ የራሱን ጥረት ለማድረግ በመሻቱ ሊመሰገን እንጂ ሊወቀስ አይገባውም፡፡ ነገር ግን፣ እንዲህ ዓይነቱ ጥረት፣ የቱንም ያህል ቀና ቢሆን እንኳ፣ ጉዳዩን እጅግ በቅርበትና በጥልቀት መመርመር የሚጠይቅ መሆኑ አይካድም፡፡ ከዚያም በላይ ግን፣ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ማኅበረሰብ፣ ከማኅበረሰቡም ተደማጭነት ያላቸውን የእምነቱ መሪዎች ወይም የሃይማኖቱን ሊቃውንት ባላካተተ መልኩ ሲካሄድ የሚፈለገውን አዎንታዊ ውጤት ያመጣል የሚል እምነት የለንም፡፡ በየትኛውም የሃይማኖት ማኅበረሰብ ውስጥ ከእምነት‑ተኮር አስተሳሰብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ልዩነቶች ሊፈጥሩ የሚችሉትን አላስፈላጊ ፍጥጫና ይህም ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ውጤት በማስቀረት ጥረት ውስጥ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የሃይማኖት ማኅበረሰብ እና ተደማጭ መሪዎቹ ያላቸው ሚና በምንም የሚተካ አለመሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ የወሃቢያ መስፋፋትም ሆነ ከሱፊያ አስተሳሰብ ተከታዮች ጋር ያሉ ልዩነቶችንና ከልዩነቶቹ ሊመነጩ ይችላሉ ተብለው የሚታሰቡ ውጥረቶችን በዘላቂነት ለመፍታትም የጉዳዩ ባለቤቶችን የመፍትኄ አካል በማድረግ ፈንታ የችግር ምንጭ አድርጎ ማሰብ ትክክለኛ ነው ብለን አናምንም፡፡
ወሃቢያ እንደ ስጋት …
ለመሆኑ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ነው የሚለውን የ‹ወሃቢ› አስተምህሮ ከምን አኳያ ነው እንደ ስጋት የተመለከተው? … ይህ ስጋት በመሬት ላይ ያለ ነውን? ካለስ ስጋቱን የማስወገጃው መንገድ ምንድን ነው? … ሙስሊም ኢትዮጵያውያንስ ይህን ስጋት በማስወገድ ረገድ ያላቸው አቋምና አስተሳሰብ ምን ይመስላል? … በተግባርስ ይህን ስጋት ለማስወገድ ምን አድርገዋል? … ‘ዊኪሊክስ’ ይፋ ያደረጋቸውን “ምስጢራዊ ሰነዶች” መነሻ አድርጎ ስለ ‘ፖለቲካዊ እስልምና በኢትዮጵያ’ ሀተታ ያቀረበው የዳያስፖራ ራዲዮ እነዚህን ቁልፍ ጥያቄዎች አልጠየቀም፡፡ ባለመጠየቁም በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አላየም፡፡ ከዚያ ይልቅ፣ ሰነዱን ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እያካሄዱ ያሉትን ሃይማኖታዊ ነፃነትን የማስከበር ሰላማዊ ትግል ጥላሸት ለመቀባት ዓላማ አውሎታል፡፡
በእኛ እምነት በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ የሚንፀባረቁ የጽንፈኝነት ዝንባሌዎችን ማረቅ የሚቻለው ትምህርትና እውቀትን በማስፋፋት ብቻ ነው፡፡ በዚህም መንፈስ በኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ ውስጥ የአገሪቱ ሙስሊሞች የጋራ ተቋም ከሚሰኘው መጅሊስ ይልቅ የሃይማኖቱ ምሁራን በርካታ አዎንታዊ ተግባራትን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ ከአስተምህሮ ልዩነቶች የሚመነጩ ውጥረቶችን ከማስወገድ አኳያም አንዱን ወገን በጽንፈኝነት ፈርጆ የማሳደድን አማራጭ ከሚያራምደው የመንግሥትና የመንግሥታዊው መጅሊስ መንገድ ይልቅ፣ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንጋፋ የሃይማኖት ሊቃውንት በጥልቅና በሳል ውይይቶች አማካይነት ኅብረተሰቡን ወደጋራ መግባባት ለማምጣት በርካታ አዎንታዊ ሥራዎችን አከናውነዋል፡፡ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከ2000/2001 የተለያዩ አስተምህሮ የሚከተሉ አንጋፋ የሙስሊም ሊቃውንት፣ በሱፊው በኩል በሸኽ ዑመር ኢድሪስ መሪነት፣ በሰለፊ በኩል ደግሞ በዶ/ር ጀይላን መሪነት፣ ይህን በመሰሉ ጉዳዮች ላይ ተከታታይ የሆኑ በሳል ውይይቶችን በማድረግ ከመግባባት ላይ ደርሰው፣ የአንድነት ጉባዔ ለማካሄድ የመጨረሻ ዝግጅት እያካሄዱ ነበር፡፡ ይህን መሰል ታላቅ አዎንታዊ እርምጃ ከኢትዮጵያ በቀር በሌሎች ሙስሊሞች በሚበዙባቸው አገራት እንኳ መካሄዱ ያጠራጥራል፡፡ ግና ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተለየ አዎንታዊ ተግባር በህዝብ ባልተመረጠው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮችም ሆነ በመንግሥት ዘንድ በበጎ ዓይን አልታየም፡፡ እናም መንግሥት እና ምክር ቤቱ ይህንን ሰላምና አንድነትን የማምጣት ዓላማ የነበረውን ሂደት ሆን ብለው አስተጓጉለውታል፡፡ ከቶ ይህ ለአገር እና ለህዝቦች ሰላም የማሰብ ተግባር ነውን? መልሱን ቅን ልቦና ላላቸው ወገኖች ኅሊና ትተነዋል፡፡
በሙስሊሙ ኅብረተሰብ መካከል የሚፈጠሩ የሃይማኖት አስተምህሮን መሠረት ያደረጉ ማናቸውም ችግሮች ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በራሱ ሊፈታቸው የሚገባ፣ የውስጥ ጉዳዮቹ ናቸው፡፡ የጋራ ተቋማችን በምንለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ላይ በመንግሥት የተሾሙ አመራሮች ይህንን የማድረግ ኃላፊነታቸውን አለመወጣታቸው ሳያንስ፤ ጭራሽ በዚህ መንፈስ ይካሄዱ የነበሩ የሙስሊም ሊቃውንት ውይይቶችን ማሰናከላቸው እየታወቀ፣ የኢሕአዴግ መንግሥትን እና በእርሱ ሹማምንት የሚመራውን መጅሊስ ፀረ‑አክራሪ፣ ህዝበ ሙስሊሙን ግን የፖለቲካዊ እስልምና አስፋፊ አድርጎ ለመሳል የሚደረገው ሙከራ በጣም የሚያሳዝን እና የሚያስተዛዝብ ነው፡፡
ስለ እኛ ማን ይናገር …
ዊኪሊክስ ይፋ ያደረጋቸው የስቴት ዲፓርትመንት የ2010 ሰነዶችን ዋቢ በማድረግ በዳያስፖራ ራዲዮ በ‘ፖለቲካዊ እስልምና’ ዙርያ በቀረበው ዝግጅት ላይ የምናቀርበው ሌላው ዐብይ ሒስ፣ ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ማንነትና ምንነት ማን ነው የሚነግራቸው በሚል ጥያቄ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በእኛ እምነት ሙስሊም ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ማንነትና ምንነት በሦስተኛ ወገን ሊነገራቸው አይገባም፡፡ መንግሥታችን የገዛ ዜጎቹን፣ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችንም ለዘመናት አብረናቸው የኖርን ሙስሊም ወገኖቻቸውን በውጭ መንግሥት ዕይታ፣ ግንዛቤ፣ አረዳድና አስተሳሰብ ላይ ተመሥርተው ሊያዩን ይገባል ብለንም በፍፁም አናምንም፡፡ በእኛ እምነት ይህ ለዘመናት አብሮ በመኖር ያጎለበትነውን ተዋድዶ፣ ተፋቅሮና ተከባብሮ የመኖር ታላቅ እሴት ትርጉም‑አልባ የሚያደርግ የተሳሳተ አካሄድ ነው፡፡ …
**********
በኢትዮጵያ፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በህዝብ ሀብት የሚንቀሳቀሱትና ሙሉ በሙሉ በኢሕአዴግ ቁጥጥር ሥር ያሉት መገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት አንስቶ እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ያሉ የኢሕአዴግ ካድሬዎች፣ “ወሃቢ!” የሚለውን ስያሜ ህዝብን፣ በተለይም ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖቻችንን የሚያስፈራሩበት ጭራቅ አድርገውታል፡፡ … ከኩዌት መንግሥት በተገኘ የገንዘብ እርዳታ መስጊዶች መገንባታቸው አልያም አሮጌ መስጊዶች መታደሳቸው የወሃቢ እምነት መስፋፋቱን ይገልጻል ብሎ መደምደም የሚቻል አይመስለንም፡፡ በአዲስ አበባ ፒያሳ አቅራቢያ የሚገኘው ኑር (በተለምዶ በኒ) መስጂድ ከኩዌት በጎ አድራጊዎች በተገኘ የገንዘብ እርዳታ ነው ፈርሶ በአዲስ መልክ የተገነባው፡፡ ነገር ግን መስጂዱ የአንድ የተለየ አስተምህሮ ማስፋፊያ አይደለም፡፡
በምሥጢራዊ ሰነዱ ላይ ባህላዊ ወረራ በማስፋፋት የተጠቀሰችው ሳዑዲ አረቢያ፣ ከኢትዮጵያም በላቀ መልኩ ለዩናይትድ ስቴትስ ወዳጅ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ምናልባትም ሰነዱን ምስጢራዊ (Classified) ተብሎ እንዲፈረጅ ካደረጉት ነጥቦች አንዱ፣ “የሳዑዲ ባህላዊ ኢምፔሪያሊዝም” ‘ያሳስበኛል’ የሚለው የአሜሪካ መንግሥት በባህላዊ ኢምፔሪያሊዝም አስፋፊነቷ ከሚያማት አገር ጋር ባለው ወዳጅነት አኳያ ሰነዱ በሚያንፀባርቀው ተቃርኖ ላይ የተመሠረተ ይመስለናል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሰላምና ፀጥታ ለምን ያሳስባታል አንልም፡፡ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለቀጣናውም ሆነ በይበልጥም ለአገራችንና ለመላው ህዝቧ ሰላም፣ ዕድገትና ብልፅግና ያለን መቆርቆር ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የበለጠ እንጂ ያነሰ እንዳልሆነ ማንም ሊዘነጋው አይገባም፡፡ የአገራችን ሰላም፣ ፀጥታና ደኅንነት ቢረጋገጥ፣ ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር የእነዚህ ዕሴቶች ትሩፋት በሆነው ዕድገትና ብልፅግና ተጠቃሚዎቹ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ነን፡፡ በአንፃሩ፣ የእነዚህ ዕሴቶች መጓደል ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችንም ጭምር ነው የሚጎዳው፡፡
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሃይማኖታችን ኢስላም የአገራችንን ሰላም የሚያውክ የየትኛውም የውጭ ኃይል መሣርያ እንዲሆን የምንፈቅድ ዜጎች አይደለንም፡፡ ነገር ግን በተለምዷዊ አሉታዊ ዕይታ፣ ሃይማኖታችን ኢስላምም ሆነ ተከታዮቹ ሙስሊሞች በድፍኑና በጭፍኑ የችግር ምንጮች ተደርገን መታሰብንም አንቀበልም፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከሃይማኖታችን ጋር ተያይዞ ለሚነሳ፣ ወይም ይነሳል ተብሎ ለሚታሰብ ማንኛውም ችግር የመፍትኄ አካል እንጂ የችግር ምንጭ አይደለንም፡፡ እዚህ ላይ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እ.አ.አ ጁን 4 ቀን 2009 በካይሮ ዩኒቨርሲቲ፣ ግብፅ፣ ተገኝተው ለሙስሊሙ ዓለም ከደረጉት ታሪካዊ ንግግር ላይ መጥቀስ እንወዳለን፡‑ “ኢስላም ነውጠኛ ጽንፈኝነትን ለመዋጋት በሚደረገው ትግል ሰላምን እውን ለማድረግ የሚያግዝ አጋር እንጂ፣ ከቶም የችግሩ አካል አይደለም፡፡”
ፕሬዚደንት ኦባማ በዚሁ የካይሮ ታሪካዊ ንግግራቸው፣ “አንድን ንፁህ ነፍስ የገደለ፣ መላውን የሰው ልጅ እንደገደለ ነው፡፡ አንድን ንፁህ ነፍስ በግፍ ከመገደል ያዳነ መላውን የሰው ልጅ ያዳነ ያህል ነው” የሚለውን ቁርአናዊ ቃል ጠቅሰውታል፡፡ ይህ ቁርአናዊ ቃል ምንጊዜም ህያው ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በዚሁ መድረክ ላይ እንደተናገሩትም፣ “ከአንድ ቢሊዮን የሚበልጡ ተከታዮች ያሉትን ዘመናትን ያስቆጠረ እምነት ከጥቂቶች ጠባብ እና በጥላቻ ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ እጅግ የገዘፈ” የመሆኑ እውነታ ከቶውንም ሊዘነጋ አይገባም፡፡
የዊኪሊክስ ሰነዶች ይፋ ያደረጋቸው አዎንታዊ ነጥቦች
በዊኪሊክስ ላይ ይፋ ከተደረገውና የአሜሪካ መንግሥት፣ በአዲስ አበባው ኤምባሲው አማካይነት ካስተላለፈው መልዕክት ውስጥ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሃይማኖታዊ ትውፊቶችና ቁሳዊ ቅርሶችን ከጥፋት ለመታደግ አስቦ ያከናወናቸው ተግባራት ተጠቅሰዋል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በዚህ የአሜሪካ መንግሥት ተግባር በጣም ደስተኞች ከመሆናችንም በላይ ምስጋናችንም ከፍተኛ ነው፡፡ በእርግጥም፣ ጠንካራ የሃይማኖት ተቋም ቢኖረን ኖሮ፣ ይህ በእኛው ተቋም ሊፈፀም ይገባው የነበረ እጅግ ትልቅ ተግባር ነበር፡፡ እኛ ልንሠራው ይገባን የነበረውን ሥራ የአሜሪካ መንግሥት በራሱ ተነሳሽነት ስላከናወነልን እጅግ ትልቅ ውለታ እንደዋለልን ሳናወሳ አናልፍም፡፡
**************
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በላይኛው የሥልጣን እርከን ላይ ካሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ወረዳ ያሉ የኢህአዴግ ካድሬዎች አለአንዳች እፍረት እኛን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ስለ ሱፊያ እና ሰለፊያ ሊያስተምሩን ይገዳደራሉ፡፡ ካድሬ ጋዜጠኞችና የፌደራል ፖሊስም በመግለጫዎቻቸው፣ “ታላቁ መሪ” የተጠነቀቁትን ያህል እንኳ ሳይጠነቀቁ፣ “የወሃቢያ/ሰለፊያ ምንደኞች” እያሉ በአደባባይ አፋቸውን ይከፍቱብናል፡፡ ከቶውኑ እነዚህ ስያሜዎች ዊኪሊክስ ይፋ ካደረጋቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምሥጢራዊ ሰነዶች የተለቃቀሙ አይደሉምን?! ለመጀመርያ ጊዜ ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አንደበት የተሰሙት “ነባሩ” እና “አዲሱ እስልምና” የሚሉ ስያሜዎችስ ከወዴት ተቃረሙና ነው እኛን ለመወንጀል ዊኪሊክስ የሚጠቀሰው?! … እኛማ ዊኪሊክስን እናመሰግነዋለን! ምክንያቱም፣ የተመሰገነው ዊሊያም አሳንጅ የኢሕአዴግ መንግሥትን በሃይማኖት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት፣ በህዝብ‑ሙስሊሙ ተቋም ላይ ሹማምንቱን እንደሚያስቀምጥ ነውና ያጋለጠልን! …
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት “የሳዑዲ ባህላዊ ወረራ” ሲል የጠራውን ይህን መሰሉን ተግባር ለመቀናቀን የወሰደው ለኢስላማዊ ቅርሶችና ታሪካዊ እሴቶች ጥበቃ እገዛ የማድረግ ባህላዊ መርኃ‑ግብር የሚደገፍ ቢሆንም፣ የጉዳዩ ባለቤት የሆነውን ህዝበ‑ሙስሊም ባሳተፈ መልኩ የተካሄደ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት፣ ኤምባሲው በህዝብ ካልተመረጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራር ጋር በመተባበር ያከናወናቸው የቅርስ ጥበቃና ተሃድሶ ተግባራት ብዙዎችን ከጀርባው ሌላ ዕኩይ ዓላማ ያዘለ ሳይሆን አይቀርም ወደሚል ጥርጣሬ ገፍቷቸዋል፡፡
የኢሕአዴግ መንግሥት፣ የቴልአቪቭ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሐጋይ ኤርሊች፣ ከሌላ አንድ ምሁር ጋር በጣምራ የሠሩትን ጥናት፣ እንዲሁም ምናልባት የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ዶ/ር ዴቪድ ሺን በተለያዩ አጋጣሚዎች የሰጧቸውን የግል አስተያየቶች ዋቢ በማድረግ ይመስላል፣ አለ ብሎ የሚያስበውን የወሃቢያ አክራሪነት ለመቋቋም የአህባሽ አስተምህሮን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣትን እንደመፍትኄ አድርጎ ወስዶታል፡፡ መንግሥት ከወሃቢያ አስተምህሮ ሊመነጭ ይችላል ብሎ የሚያስበውን የ“አክራሪነት” ስጋት ለመቋቋም፣ ከላይ በተጠቀሱት ምሁራን “ለዘብተኛ” ተብሎ የተሞካሸውን ሊባኖስ‑ወለድ አስተምህሮ በህዝበ‑ሙስሊሙ ላይ ለመጫን የህዝበ‑ሙስሊሙን የጋራ ሃይማኖታዊ ተቋም (መጅሊስን) መሣሪያ ለማድረግ በመሻት በተቋሙ ላይ የአህባሽ አስተምህሮ ተከታዮችን ሾሟል፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ፣ በ2003 መገባደጃ ላይ የኢሕአዴግ መንግሥት “አክራሪነትን መዋጋት” በሚል ምክንያት፣ በዋነኛነትም የወሃቢያ አስተምህሮን ዒላማ በማድረግ የወሰዳቸው እርምጃዎችና፣ ይበልጡንም በህዝበ‑ሙስሊሙ ላይ የአህባሽን አስተምህሮ ለመጫን የተደረገው ሙከራ ከላይ የተጠቀሰውን ጥርጣሬ በማጠናከር እነሆ ሁለት ዓመታት ሊደፍን ለተቃረበው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ መነሻ ሆኗል፡፡ መንግሥት ይህን ድርጊት በመፈፀም ከጣሰው ሕገ‑መንግሥት ባሻገር የህዝበ‑ሙስሊሙን የጋራ ተቋም ለአንድ እንግዳ አስተምህሮ ተከታዮች አሳልፎ በመስጠት የወሰደው እርምጃ በአገራችን በአስተምህሮ ላይ የተመሠረተ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ውጥረት ከመፍጠር በቀር ምንም ያመጣው አዎንታዊ ውጤት የለም፡፡ …
ላለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አጥብቀው እየተቃወሙ ያሉት እነዚህን የተሳሳቱ የችግር አፈታት መንገዶች ነው፡፡ የእኛ ሁኖ ሳለ የእኛ ያልሆነው የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ይህን የተሳሳተ የችግር አፈታት ከማረም ይልቅ፣ የተሳሳተው አካሄድ ዋነኛ ተዋናይ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተቃውሞ እንቅስቃሴ በዋነኝነት ይህን ተቋም እውነተኛ የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም በማድረግ ላይ ለማተኮር ተገዷል፡፡ በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ዓመታት እየተካሄደ በሚገኘው የህዝበ‑ሙስሊሙ ሰላማዊ ትግል የተነሱት ቁልፍ ጥያቄዎች በግልፅ የሚያመለክቱትም ይህንኑ ሐቅ ነው፡፡ ሰላማዊ ትግሉ በጠራ ግንዛቤና ግብ ላይ የተመሠረተ፣ በመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ እንቅስቃሴ በአገራችን ሕገ‑መንግሥት በሠፈሩት የሃይማኖት ነፃነት ድንጋጌዎች ላይ እየተቃጡ ያሉ የመንግሥት ጥሰቶች እንዲቆሙ በግልፅ የሚጠይቅ እንጂ፣ ከቶውንም በሌላ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ዕኩይ ነገር ያለመና የተለመ አይደለም፡፡ ነገር ግን፣ ይህንን ህዝባዊ፣ ሕጋዊ እና ፍትኃዊ ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ብልህነት መሆኑን ያልተረዳው የኢሕአዴግ መንግሥት፣ የህዝበ‑ሙስሊሙን ጥያቄዎች ላለመመለስ በወሰደው፣ በእኛ እምነት ፍፁም የተሳሳተ ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት፣ የፕሮፖጋንዳ አውታሮችን በመጠቀም ጉዳዩን ወዳልተፈለገ እና አደገኛ ወደሆነ አቅጣጫ እየለጠጠው ይገኛል፡፡ ከእነዚህ አደገኛ አካሄዶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው በአገራችን ለረዥም ዘመናት በሰላምና በፍቅር አብሮ የመኖር እሴትን ባጎለበቱት የእስልምና እና የክርስትና ተከታይ ህዝቦች መካከል የእርስ በርስ ጥርጣሬና ግጭትን የመፍጠር ዕኩይ ስትራቴጂው ተጠቃሽ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ዲያስፖራ የራዲዮ ጣቢያዎች ዊኪሊክስን ዋቢ በማድረግ የቀረቡት ዝግጅቶች ይህንን ዕኩይ ዓላማ ከመመገብ ውጪ ለኢትዮጵያ ህዝቦች በሰላም እና በፍቅር መኖር የሚያበረክቱት አንዳችም አዎንታዊ አስተዋጽዖ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ በሰነዶቹ ላይ የተጠቀሱትን የአሜሪካ መንግሥት ፖለቲካዊ ምሥጢራት ልክ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከክርስትያን ወገኖቻቸው የደበቁት ምሥጢር አስመስሎ ለማቅረብ መሞከር እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ ከዚህ በላቀ የሚያሳዝነው ግን በዚሁ የራዲዮ ዝግጅት ጥቅም ላይ የዋሉት ምንጫቸው የማይታወቅ የድምፅ ግብዓቶች ናቸው፡፡ ከዓመታት በፊት በውሱን አካባቢዎች ከተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ ስሜት ኮርኳሪ ድምፆችን እንደ በግብዓትነት ተጠቅሞ የሰዎችን ስሜት መኮርኮርም፣ ለአገር ሰላም ተቆርቋሪነትን ያሳያል ብለን አናምንም፡፡
ውድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ራዲዮ “ጋዜጠኞች” እና የኢሕአዴግ የፕሮፖጋንዳ ድረ‑ገፆች ሆይ! ስለምን ተወናብዳችሁ የኢትዮጵያ ህዝብን ለማወናበድ ትሟሟታላችሁ?! እውን ተወናብዶ ህዝብን በማወናበድ አገር ይቀናል ብላችሁ ታስባላችሁን?! … እውነት እንላችኋለን፣ የምትጓዙበት መንገድ ደግ አይደለም፡፡ ግዴላችሁም አድምጡን፣ … እንደምናየው ደግ ነገርን አላለማችሁም፡፡ … ከመጎራበትም በላይ አንድ ግርግዳ ተጋርተው ለአያሌ ዓመታት በሰላምና በፍቅር በኖሩ ህዝቦች መካከል የጥላቻና የቁርሾ እሳትን ለመጫር የምትተጉት ከቶ ለዚህች አገር ምን ብትመኙላት እንደሆነ ሊገባን አልቻለም፡፡… እመኑን፣ ፍፁም በተሳሳተ መንገድ ላይ እየሄዳችሁ ነው፡፡ ግዴላችሁም ይህንን የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ግሣፄ ከልቦናችሁ ሁናችሁ አድምጡት፡፡ … ወደ አቅላችሁ ብትመለሱ መልካም ነው፡፡ … ወደ አቅላችሁ ተመለሱና እንደማመጥ፡፡ … በሰላም መብታችንን በጠየቅን እየደረሰብን ያለው መገፋት ፈጽሞ ለርካሽ ፕሮፖጋንዳ ተንበርክከን የያዝነውን ሐቅ እንድንለቅ አያደርገንም፡፡ ይህንን ብታውቁት መልካም ነው፡፡ … ከእኛ ይልቅ እናንተ ፅንፍ ሄዳችኋል፡፡ … ግዴለም ዓይኖቻችሁን ክፈቱ፡፡
መልዕክታችንን ከፕሬዚደንት ኦባማ የካይሮ ንግግር በመጥቀስ እንደምድመው፡‑
“የግንኙነታችን ውል በልዩነቶቻችን ላይ እስከተመሠረተ ድረስ፣ ከሰላም ይልቅ ጥላቻን ለሚዘሩት፣ እንዲሁም መላ ሕዝቦቻችን ፍትኅና ብልጽግናን ያገኙ ዘንድ አስፈላጊ የሆነውን የትብብር መንፈስ ከማጎልበት ይልቅ የግጭትን ጎዳና መጥረግ ለሚሹት (ጽንፈኞች) ሁነኛ አቅም እንፈጥርላቸዋለን (የልብ ልብ እንሰጣቸዋለን)፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የጥርጣሬና የቅራኔ ዑደት ማብቃት አለበት፡፡”

የህይወት ዋጋ ያስከፈለው ትንሽዬ ሰነድ “የተገንጣዮችና የሲ.አይ.ኤ. ግንኙነት”

ርዕስ፡- “የተገንጣዮችና የሲ.አይ.ኤ. ግንኙነት”
ጸሓፊ ተስፋሚካኤል ጆርጆ
——-
በዚህ አነስተኛ ጽሁፍ የማወጋችሁ ስለአንድ አስገራሚ ሰነድ ነው፡፡ ሰነዱ የያዘው ታሪክ ብቻ ሳይሆን የሰነዱ ጸሐፊም አስገራሚና አሳዛኝ ታሪክ አለው፡፡ ይህ ሰው “ኦሮማይ” በተሰኘው የበዓሉ ግርማ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ገጸ-ባህሪዎች አንዱ ነው። በዚህ ሰነድ የምታነቡትንም ታሪክ በኦሮማይ ውስጥ በትንሹ ታገኙታላችሁ፡፡ ጸሓፊው በዚህ ሰነድ የህይወት ዋጋ ከፍሎበታል። ታሪኩን በአጭሩ እነሆ!
——-
አቶ ተስፋሚካኤል ጆርጆ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመን በደቡብ ምስራቅ ኤርትራ የሚገኘው የደቀምሐረ ወረዳ ገዥ ነበሩ። ሻዕቢያ (EPLF) ከጀብሀ (ELF) ተገንጥሎ የትጥቅ አመጽ የጀመረውም በዚህ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው የዓላ በረሃ ነው። በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኤርትራ ገዥ የነበሩት ልዑል ራስ አስራተ ካሳ እነዚህ የሻዕቢያ ተገንጣዮች በሰላም እጃቸውን ሰጥተው ወደ ህብረተሰቡ እንዲመለሱ ለማግባባት እንዲያመቻቸው ሶስት አባላት የነበሩት የሰላም ኮሚቴ ያቋቁማሉ። ተስፋሚካኤል ጆርጆም የኮሚቴው አባል ሆነው ይሰየማሉ።
ኮሚቴው በታቀደው መሰረት ሻዕቢያን አግባብቶ የመመለስ ተግባሩን ጀመረ። ነገር ግን እቅዱ መልኩን ቀየረና ሻዕቢያን ከሲ.አይ.ኤ ጋር ያቆራኘ ሆነና አረፈው። ይህ ቁርኝት እንዴት ተከሰተ? ከዚያ በኋላ ምን ተከተለ? መጨረሻውስ ምን ሆነ? በዘመኑ የድራማው ተሳታፊ የነበሩት አቶ ተስፋሚካኤል ጆርጆ ዝርዝሩን በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ይነግሩናል። ስለዚህ ታሪኩን ረጋ ብላችሁ አንብቡት። 
ከላይ እንደገለጽኩት አቶ ተስፋሚካኤል በዓሉ ግርማ በጻፈው “ኦሮማይ” ውስጥ ካሉት ዋና ዋና ገጻ ባህሪያት አንዱ ናቸው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ የተወከሉት “ስዕላይ ባራኺ” በሚባለው ዝነኛ ገጸ-ባህሪ ነው። ይሁንና በዓሉ ኦሮማይን ሲጽፍ የአቶ ተስፋሚካኤልን እውነተኛ ታሪክ በእጅጉ ለዋውጦታል። በቅርብ ጊዜ ስለኦሮማይ ገጸ ባህሪያት ስጽፍ ያየኝ Yosef Berhe የሚባል ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ከሰጠኝ መረጃ ለማወቅ እንደቻልኩት በኦሮማይ ውስጥ ያለው የ“ስዕላይ ባራኺ” ገቢር በሁለት ግለሰቦች ታሪክ የተመሰረተ ነው፡፡ “ስዕላይ ባራኺ” ወደ ሳህል በረሃ ከመውጣቱ በፊት የነበረውን ህይወቱን የሚያትተው ክፍል የአቶ ተስፋሚካኤል ጆርጆ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ “ስዕላይ ባራኺ” በሰሃል በረሃና ከዚያም በአስመራ የነበረውን ህይወቱን (በዓሉ ግርማ የዐይን ምስክር ሆኖ የተመለከተው) የሚያወሳው ክፍል “ተክላይ አደን” (ተክላይ ገብረ ማሪያም) በሚባል የሻዕቢያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡
***** ***** *****
አቶ ተስፋሚካኤል ይህንን ጽሁፍ ያቀረቡት በዘመነ ቀይ ኮከብ በተካሄደው የምጽዋ ሲምፖዚየም ላይ ነው (በዓሉም በ“ኦሮማይ” ውስጥ “ስዕላይ ባራኺ” ጽሁፉን በሲምፖዚየሙ ላይ ማቅረቡን ገልጿል)። ይሁንና ይህ ጽሁፍ ከፍተኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ሊሆን የቻለውና ታሪካዊ ጠቀሜታው ጎልቶ የወጣው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት (የባድመ ጦርነት) በፈነዳበት ማግስት በኢትኦጵ መጽሔት ላይ ሐምሌ 1991 በታተመበት ጊዜ ነው፡፡ 
አቶ ተስፋሚካኤል ጆርጆ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሚተርኩት ታሪክ የነበራቸው ተሳትፎ ጦስ ሆኖባቸው እስከ ሀይለስላሴ መንግሥት ፍጻሜ ድረስ በእስር ላይ ቆዩ፡፡ ከእስር ሲፈቱ የሻዕቢያ አዳኞች ለግድያ እንደሚፈልጓቸው በማወቃቸው ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ጀብሃ ገቡ፡፡ እስከ 1972 መጀመሪያ ድረስ ከጀብሃ ጋር ከቆዩ በኋላ ጀብሃ በሀይለኛ ሁኔታ በሻዕቢያ ሲመታ እንደገና ህይወታቸው ለአደጋ ተጋለጠ፡፡ በዚህን ጊዜም ወደ ሱዳን ተሰደዱና ካርቱም ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እጃቸውን ሰጡ፡፡ የደርግ መንግስትም አስፈላጊ ሰው መሆናቸውን በመረዳቱ ወደ አዲስ አበባ አስመጣቸው፡፡ ከዚያም ይህንን ታሪክ ለመንግሥት ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡ ከላይ እንደተገለጸውም ባለስልጣናቱ ታሪኩን በጽሑፍ ጽፈው በቀይ ኮከብ ዘመቻ ዘመን በተካሄደው የምጽዋ ሲምፖዚየም ላይ እንዲያቀርቡት ስላደፋፈሯቸው እርሳቸውም ይህንኑ አደረጉ፡፡ 
አቶ ተስፋሚካኤል እስከ ደርግ መውደቂያ ድረስ በአዲስ አበባ ኖሩ። በ1984 መጨረሻ ገደማ ግን እርሳቸውን ሲያሳድዱ የነበሩት የሻዕቢያ ኮማንዶዎች ከሳር ቤት ዝቅ ብሎ ባለው የቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ ወደቤታቸው በመግባት ላይ እያሉ ገደሏቸው። ጽሁፋቸው ግን አልሞተም። ዛሬም አስገራሚውን ታሪክ ይናገራል። 
ይህንን አስገራሚ ሰነድ ከሚከተለው የኢንተርኔት ገጽ በቀጥታ ዳውንሎድ አድርጉትና እዩት፡፡ የዛሬ 40 ዓመት ግድም የነበረውን የኤርትራ ምስቅልቅልና የአፍሪቃ ቀንድ የጂኦፖለቲካ ሁኔታ በደንብ ትማሩበታላችሁ፡፡ ለሁሉም ጋሽ ስብሐት እንዳለው ሰነዱን “እነሆ በረከት” ብያለሁ። መልካም ንባብ!
freedom4ethiopian

ኢቲቪው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ



በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜናዎችንና መንግስታዊ መግለጫዎችን በማንበብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ መደብደቡን ጓደኛው ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ አረጋገጠ። ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ “ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው – ጥቂት ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ” በሚል በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ የጋዜጠኛውን መደብደብ ማረጋገጡን ገልጾ መደብደቡን ግን አውግዟል።
ጽሑፉ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል ዘ-ሐበሻ እንደወረደ እንዲህ አቅርባዋለች፦

ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው -
ጥቂት ነገር ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ

(ከደመቀ ከበደ)
ከትናንት በስቲያ አንድ ወዳጄ ‹‹ተመስገን በየነ ተደበደበ የተባለው እውነት ነወይ›› ሲል ኢንቦክስ አደረገኝ፡፡ ላጣራና እነግርሀለሁ ብዬው ተለያየን፡፡
****** **** ***** *****
ተመስገንን በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ በጣም ሰላምተኛ፣ ትሁትና ስራውን አክባሪ ነው፡፡ ከውድነህ ክፍሌ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ የአየር ሰአት ወስደው ይሰሩ በነበረበትና እኔም ከመልቀቄ በፊት ወደ ስቱዲዮ በመጣ ቁጥር የበዛ ትህትናውን እየለመድኩት መጣሁ፡፡ ከዚያ በኋላም ሜሮን ጌትነት፣ አንሙት አብርሀም፣ እሱ /ተመስገን/ እና ሌሎች አምባሳደር ለሆኑለት የልመና ማስወገድ ጉዳይ የተቻለውን ሲያደርግ በዘገባ ጉዳይ ብዙ ተረዳድተናል፡፡ በቃ ስራውን ያከብራል፤ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ትጉህና አርአያ ነው – አሁንም ከትህትና ጋር፡፡
ሰሞኑን ስለ እሱ የሰማሁትን በሁለት መልኩ ለማጣራት ጣርኩ፡፡ አንደኛው ከእሱ ከራሱ እና ከባለቤቱ /የቀድሞ ባልደረባዬ እምርታ አስፋው / ጋር ደወልኩ፡፡ የሁለቱም ስልኮች ኦፍ ናቸው በተደጋጋሚ ብሞክርም፡፡ / እስካሁን ድረስ/
ሁለተኛው ከቅርብ ወዳጆቼ እውነቱን ለማጣራት ደወልኩ፤ /ከባለቤቱ ወዳጆችና ከ‹‹አምባሳደርነት›› ወዳጆቹ ማለት ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው ናቸው/
‹‹ጉዳት መድረሱንና ህክምና በመከታተል ላይ›› መሆኑን ነገሩኝ፡፡
‹‹ማን እና ለምን›› ለሚለው ግን መልስ አልነበራቸውም፡፡ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡
ከተደጋጋሚ ሙከራዬ በኋላ የባለቤቱ /ከደቂቀቃወች በፈት/ እምርታ ስልክ ጠራ – አነሳችው፡፡
‹‹አሁን በመልካም ጤነነት ላይ ይገኛል፡፡ ትንሽ ቆይተህ ደውልለትና ራሱን አናግረው፤ አሁን ደክሞት ሰለተኛ ነው እንጅ እየተሸለው ነው፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ምክንያቱ ግን ምንድን ነው›› ስል ደገምኩ ጥያቄዬን፡፡
‹‹አላወቅንም፤ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞታል፡፡ ከተጣራ በኋላ እንነግርሃለን›› ብላኝ ‹‹እግዜር ይማረው ብዬ›› ተለያየን፡፡
የሆነውን እስኪ ከሰብአዊነት ብቻ እየመዘንን ‹‹እየተወሩ ያሉ›› ምክንያቶችን እንይ፡፡ ሰብአዊነትን ሰው ከመሆን ጋር ብቻ ሚዛናችን ነው!!
‹‹ተመስገን የተደበደበው በኢቴቪ ዜና የተነሳ ነው›› – እንበል፡፡ ‹‹ማን ደበደበው›› የሚለውን ማጣራቱ ለኔ ፅሁፍ ጠቃሚ አይደለምና ብዙ አልዘላብድም፡፡ ግን ‹‹በኢቴቪ ዜና የተቆጡና የተበሳጩ አካላት ወይም ግለሰቦች ነናቸወው ከተባለ ይሀህ መታየት አለበት፡፡
በሚዲያ ህግ አንድ የሚዲያ ተቋም የሚተዳደረው ‹‹በኤዲቶሪያል ፖሊሲው›› ነው፡፡ የሚዲያ ህገ መንግስት ይባላል፡፡ ይህ ‹‹ኤዲቶሪያል›› እንደየ ሚዲያው ፍላጎት፣ እንደየ ሚዲያው ማሰራጫ አገር፣ እንደየሚዲያው ገዥዎች እሳቤና እውቀት የሚወሰን ነው፡፡ እንደኛ አገር ባሉ ታዳጊ አገራት የሚዲያዎች ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ከአገሪቱ ህገ – መንግስት ጋር የተቆራኜ ነው፡፡ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይበዛበታል፡፡ ኢቴቪም ከዚህ የወጣ እንዳልሆነ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል ፡፡
ታዲያ በማንኛውም ሚዲያ ተቀጥሮ የሚሰራ ሁሉ / ይህ የግል ሚዲያዎችንም ይጨምራል/ ኤዲቶሪያሉን አክብረው የመስራት ግዴታ አለባቸው፡፡ በኤዲቶሪያሉ ያልተስማማ መልቀቅ ብቻ ነው ምርጫው፡፡ ጋዜጠኞች የቤቱ ኤዲቶሪያል ፈፃሚ ሲሆኑ አለቆች ደግሞ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
ወደ ዜና አንባቢዎች ስንመጣ ደግሞ፤ ዜና አንባቢዎች የተሰፃቻን ዜናች ያላንዳች መነካካት የሚያነቡ ናቸው – ፖስተኛ ማለት ነው ዜና አንባቢነት፡፡ የተሰጠህን መቀበል ብቻ!!
የሙሉ ጊዜ ዜና አንባቢ / የሚዲያው ቋሚ ተቀጣሪ/ እና የፍሪላንስ ዜና አንባቢዎች አሉ፡፡
ተመስገን በየነ የፍሪላንስ ዜና አንባቢ ነው፡፡ የኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰሩትን ዘገባ ከማንበብ የዘለለ ምንም ሚና የሌለው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ወጥቶ መረጃ ቃርሞ ወይ ኤዲት አድርጎ የማቅረብ አንዳች ተልዕኮ የለውም፡፡
ይህን ነው ‹‹ለምን›› እንድል ያደረገኝም ፤ ብዬም ወደእናንተ ያስፃፈኝም ‹‹ይኸወ የአንባቢነት እንጅ የመረጃ ቃራሚነት ወይም ሃያሲነት›› ሚና የሌለው መሆኑ ነው፡፡
አሁንም ‹‹ተደባዳቢው›› አካል ማንም ሆነ ምንም ድርጊቱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ‹‹ድብደባ›› በሰው ልጅ ላይ ተገቢ አለመሆኑን የማልደግፈው ሰው በመሆኔ ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ያነበባቸው ዜናዎች ያስቆጡት ‹‹አካል›› ወይም ‹‹ግለሰብ›. የፈፀመው ከሆነ ለኔ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› ይሆንብኛል፡፡ አሁንም እደግመዋለሁ ፤ ተመስገን በዜና አንባቢነቱ ከሆነ የተደበደበው ነውር ነው – ፖስተኛ ሳይሆን ፖስታውን የፃፈው ነው መጠየቅ ካለበት መጠየቅ ያለበት፡፡ / መደብደብ ያለበት አላልኩም/
እህስ ሌላ ጉዳይ አስደብድቦት ከሆነስ ብለን እንጨምር፤
ዘረፋ የሚፈፅሙ ማጅራት መቺዎች ከሆኑም ‹‹ህግና እግዜር›› መፍትሄ ይሰጡት ዘንድ እመኝለታለሁ፡፡
በማንኛውም ምክንያት ‹‹በቂም ተነሳስቶ›› ተፈፅሞ ከሆነም ‹‹ከድብድብና ስድብ›› ወደ ቅርርብና ፍቅር መምጣት ይቻላል ባይ ነኝ፡፡ በእኔ እምነት ሰውን ከማያግባባው የሚያግባባው ነገር ይበልጣል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!

ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው

ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡
ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡
ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ፀሐፊን፣ ሊቀመንበሩንና የሰልፍ አስተባባሪዎችን ለማነጋገር ጥሪ እንዳቀረበላቸው ታውቋል፡፡
በፀጥታ ዙሪያ ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን የሚለው የፖሊስ መጥሪያ ፓርቲው የእሁዱን ስብሰባ እንዲሰርዝ ለማግባባት ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲያቸው የእሁዱን ስብሰባ ለማካሄድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ተናግረው፤ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ ከያዙት አቋም እንደማያስቆማቸው ለኢሳት ተናግረዋል፡፡
በታሪክ፣ በሞራልም ሆነ በህግ ተጠያቂ የሚያስደርገን ነገር ስለሌለ ሰላማዊ ሰልፉ የማይቀር መሆኑን የፓርቲው አመራር ተናግረዋል፡፡
በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማህበራት ፍቃድ ጽ/ቤት የፓርቲውን ሰልፍ ህገወጥ ነው ማለቱን አስመልክቶ የተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ‹ሕጋዊ ወይም ህገ ወጥ› የሚባል ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
የፓርቲው የሰልፍ አስተባባሪ ዝግጅት ክፍል ለእሁድ ሰልፍ የሚያደርገው ዝግጅት ከገዥው ፓርቲ የተለያየ ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
መብራት በተደጋጋሚ የመጥፋት ተግባርና በመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ በፀጥታ ሀይሎች ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡
የኢህአዴግ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ ህዝቡ ለእሁድ የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ እንዲወጣ ቅስቀሳ ማድረግ ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
መንግስት እያስተባበረ የሚገኘው የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ ህዝቡ አክራሪነትን እና ጽንፈኝነትን ለማውገዝ በሚል የተጠራ ቢሆንም እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ ያለመ እንደሆነ የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
ሁለት ቀን ብቻ የቀረው የእሁዱ የመንግስትና የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያጋጠመ ክስተት ተደርጎ ታይቷል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰማያዊ ፓርቲ 3 ከፍተኛ አመራሮችን ነሀሴ 26 የሚደረገውን ሰልፍ በተመለከተ እንወያይ የሚል ጥሪ አቀረበ፡፡
ከዚህ ጥሪ ተከትሎ
1. ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት (የፓርቲው ሊቀመንበር)
2. አቶ ስለሺ ፈይሳ (የፓርቲው ም/ሊቀመንበር)
3. አቶ እንዳሻው እምሻው በመሆን ለውይይቱ አዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን ይገኛሉ፡፡

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/08/29/70-2/

ጓደኛውን በገጀራ ቆራርጦ የጣለው ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነው

በተስፋሁን ብርሃኑ
ፖሊስና ርምጃው
‹‹እኔ ስራ አስገብቼው ሳለ ለአለቃዬ ዘወትር ስለ እኔ መጥፎ ነገር ይናገራል ያለውን ጓደኛውን ሶስት ቦታ ቆራርጦ የጣለው በፍርድ ቤት ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡
ተጠርጣሪ ሀጎስ ገብሩና ሟች አምሳሉ ምትኩ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11/12 ልዩ ቦታው አራት ኪሎ ዩንቨርሳል ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ውስጥ በጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኙ ነበር፡፡ ተጠርጣሪው ‹‹ዋና ፀባችን ነው ያለው እኔ ስራ አስገብቼው ልወደድ በማለት ዘወትር ስለ እኔ መጥፎ ነገር መናገርና እያመሸ እየመጣ ስራ ተበድሏል በማለት ያጣላኝ ነበር›› ብሏል፡፡ በምርመራ ወቅት፡፡ ይሄኔ ቂም የያዘው ተጠርጣሪ ሀጎስ ገብሩ ከሁለት ወር በፊት ለግድያ መዘጋጀት ይጀምራል፡፡
ለግድያ የሚያስፈልገውንም ከብረት የተሰራ ገጀራ ከመርካቶ እንደገዛ ተናግሯል፡፡ ሟች አምሳሉ ሲመጣ ‹‹እባክህ ራት በልቼ ልምጣ ስለው ባትበላ ምን አገባኝ አፈር ብላ ብሎኝ ወጣ›› ይላል ተጠርጣሪው በምርመራ ወቅት፡፡ ሟች በዚሁ ቀን አምሽቶ ሲመጣ በደሉ በዛብኝ ያለው ተጠርጣሪ በሩን ከከፈተለት በኋላ ሟችን በሩን እንዲዘጋው ከነገረው በኋላ ፊቱን ወደ በሩ ሲያዞር በያዘው ገጀራ ፊቱን ይመታዋል፡፡ ከዚያም ከመሬት ከወደቀ በኋላ አንገቱ አካባቢ ሲመታው ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉ ተገልጿል፡፡
ተጠርጣሪው የሟችን አስክሬን ውሃ ወዳለበት ቦታ በመውሰድ በገጀራው ወገቡንና ሁለት እግሮቹን ቆራርጧል፡፡ ከወገብ በላይ አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኝ ድልድይ መሻገሪያ ውስጥ የጣለው ሲሆን ግራና የቀኝ እግሩን ደግሞ በቢጫ ኩርቱ ፌስታል ጠቅልሎ የሚሰሩበት አካባቢና ብርሐንና ሰላም ማተሚያ ቤት ከፍ ብሎ በሚገኘው ሳጠራ ጠጅ ቤት አካባቢ ሊጥለው ችሏል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሰው መግደል ወንጀል መርማሪ ቡድን ወንጀሉ በተፈፀመ ሰሞን ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገ ቅንጅት ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ችለዋል፡፡ መርማሪ ግሩም ታረቀኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ የግድያ ወንጀል መርማሪ አስፈላጊውን የሰውና የሰነድ ማሰረጃ አሰባሰበው ካጠናቀቁ በኋላ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መዝገቡን ልከው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
freedom4ethiopian

Thursday, August 29, 2013

የኢትዮጵያውያን አይሁዶች አቀባበል

ቀሬ ቤተእስራኤላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ የትናንቱ ጉዞ የመጨረሻው እንዳይደለ ቤተ እስራኤላዊ የፓርላማ አባል ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ትንናት እስራኤል የገቡት ኢትዮጵያውያን አይሁዶች እጎአ በ2010 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የሚገኙ ቀሪ የቤተ እስራኤል ወገኖች በ 3 ዓመት ውስጥ ተጠቃለው እስራኤል እንዲገቡ በታቀደው መሠረት የተከናወነ ነው።
ላለፉት 30 ዓመታት እስራኤል ከኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዉያንን ስትወስድበት የነበረዉን ዘመቻ ማጠናቀቋን ከቴልአቪቭ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። አዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደዘገበዉ ዘመቻ «የእርግብ ክንፎች» በተሰኘዉ ጉዞ የመጨረሻዎቹ 450 ቤተ እስራኤላዉያን በሁለት አዉሮፕላን ትናንት ቴል አቪቭ አዉሮፕላን ማረፊ ደርሰዋል። እንደዘገባዉ የአይሁድ ዝርያ አለን የሚሉ ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ከእንግዲህ ወደእስራኤል የሚገቡት በተናጠል ይሆናል። እስራኤል ይህ ዘመቻ ከተጀመረ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 1984ዓ,ም አንስቶ አንድ መቶ ሺህ ገደማ ቤተ እስራኤላዉያንን ከኢትዮጵያ መዉሰዷ ገልጿል።
ትናንት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት ደጃፍ ለሰልፍ የወጡ አምስት መቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን አይሁዶች ገና 5000 ወገኖቻቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደቀሩ አመልክተዋል። ተሰላፊዎቹ የአይሁድ እምነትን ይከተላሉ የሚል እዉቅና ያልተሰጣቸዉ ቀሪ ወገኖቻቸዉን ወደእስራኤል የማምጣቱ ሂደት እንዳይቋረጥም ተማጽነዋል።
ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል በመግባት የመጨረሻዎቹ የተባሉት 450 የሚደርሱ ቤተ እስራኤላውያን ትናንት ቴላቪቪ እስራኤል ሲደርሱ ይፋ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። በአቀባበሉ ላይ የእስራኤል ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ቤተ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል ። በሌላ በኩል ቀሬ ቤተእስራኤላውያን ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ የትናንቱ ጉዞ የመጨረሻው እንዳይደለ ቤተ እስራኤላዊ የፓርላማ አባል ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ትንናት እስራኤል የገቡት ኢትዮጵያውያን አይሁዶች እጎአ በ2010 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ የሚገኙ ቀሪ የቤተ እስራኤል ወገኖች በ 3 ዓመት ውስጥ ተጠቃለው እስራኤል እንዲገቡ በታቀደው መሠረት የተከናወነ መሆኑን የእስራኤል ወኪላችን ግርማው አሻግሬ ዘግቧል ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

dw.de

በብሔርተኝነት ስም ታሪክንና የኢትዮጵዊነትን መንፈስ ማጣጣል ተቀባይነት የለውም

በፍቅር ለይኩን
በአንድ ወቅት በደቡብ አፍሪካዊቷ ከተማ በኬፕታውን የሚኖር አንድ በንግድ ሥራ የሚተዳደር  ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ አንድ አሳዛኝ ገጠመኙን እንዲህ አጫውቶኝ ነበር፡፡ ይህን ታሪኩን ያካፈለኝ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ የሥራ ቦታው ላይ ከአንድ ከኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጋር በተነሳ ጠብ በተፈጠረ ግጭት የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን አንድ የፊቱን ጥርሱን በቦክስ ያወልቀዋል፡፡ የጥርሱን መውለቅ የሰሙ የዚህ ሰው ጓደኞችም ተሰባስበው ይህን ሰው ካልገደልን በማለት ሲጋበዙ ነገሩ በሰላም ያልቅ ዘንድ አንዳንድ የሚያውቋቸው ሰዎች ለሽምግልና ጣልቃ ይገባሉ፡፡
በሽምግልና ድርድር ላይ እያሉም የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆነው ጓደኛውን ጥርስ ያወለቀው ሰው የአያቱ ስም የኦሮሞ ስም ሆኖ ይገኛል፡፡ እነዛም በእንዴት ተደፍረን፣ ይህን ሰው ካልገደልን በማለት ሲዝቱ የነበሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችም፣ ይኽ ሰው ለካ ወገናችን ነው በማለት ለበቀል ያነሱትን ሰይፋቸውን ወደ ሰገባው ይመልሳሉ፡፡ ሐሳባቸውን በመቀየር ጉዳዩ በሰላም ተቋጭቶ፣ በሃያ ሺሕ የደቡብ አፍሪካ ራንድ ካሳ ክፍያ እንዲጠናቀቅ ተስማምተው እርቅ ማውረዳቸውንና አያቴ ስም የኦሮሞ ስም በመሆኑ ከጉድ ወጣሁ ሲል በግርምት መንፈስ ሆኖ ገጠመኙን አጫወተኝ፡፡
ይህ ሰው እስከዛች ቀን ድረስ ስለ አያቱ ኦሮሞነትም ሆነ ስለመጣበት ብሔር ወይም ጎሳና ማንነት በቅጡ አስቦ ወይም ትዝ ብሎት እንደማያውቅና ይህ ገጠመኙ ግን ከሚኮራበት ከኢትዮጵያዊነት ማንነቱ ባሻገርም ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ስለሰኟት ሕዝቦቿ ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ቅርስ ለማጥናት የማንቂያ ደወል ሆነኝ ሲል ነግሮኛል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰው በተለያዩ ጊዜያት ወደ ደቡብ አፍሪካ በስደት የገቡና ኖሮአቸውን በዛው ያደረጉ የኦሮሞ ተወላጆች ለደቡብ አፍሪካ መንግሥት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ በሚያቀርቡበት ወቅት የተፈጠረውን እሰጥ አገባም እንዲህ ጨምሮ ተርኮልኛል፡፡
የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ሆኑ ስደተኞች ለፖለቲካ ጥገኝነት ብቁ የሚያደርጋቸውን ቅፅ በሚሞሉበት አጋጣሚ አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች ዜግነት ወይም አገር በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ‹‹ኦሮሚያ›› በማለት በመሙላታቸው የደቡብ አፍሪካ ‹‹ሆም አፌር ቢሮ›› የሥራ ባልደረቦች እኛ ‹‹ኦሮሚያ›› የሚባል አገር አናውቅም በማለታቸው በተነሳ ክርክር፣ እነዚህ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆኑ የፖለቲካ ጥገኝነት ፈላጊዎች፣ ‹‹ኦሮሚያ በቀድሞዋ አቢሲኒያ በአሁኗ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ስር ምትማቅቅ አገር ናት፡፡›› በማለት በማስረዳት ዜግነት በሚለው ክፍት ቦታ ላይ ‹‹ኦሮሚያ›› የሚለው ማንነታቸው እንዲሞላላቸው ቢጠይቁም ተቀባይነት በማጣታቸው እየጎመዘዛቸው ቢሆንም የማያምኑበትን የኢትዮጵያዊ ዜግነት በክፍት ቦታው ላይ ይሞሉ እንደነበር ይህ ሰው ጨምሮ ነግሮኛል፡፡
ይህንና ይህን የመሳሰሉ ብሔርን ማእከል ያደረጉ አሳዛኝ ገጠመኞች በኢትዮጵያም ሆነ በውጭ አገር ተደጋግመው የሚከሰቱ መሆናቸው ደጋግምን ያየነውና የሰማነው እውነታ ነው፡፡ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በአውስትራሊያና በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ዛሬ በትግሬ፣ በአማራ፣ በኦሮሞ … ወዘተ ስምና ማንነት የራሳቸውን ወሰን ወስነውና አጥር ከልልው የሚኖሩና ይህና ያ ብሔር በእኔና በዚህ ብሔር ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል፣ ግፍና ጭቆና አድርሶብናል በሚል የየራሳቸውን የጭቆና ታሪክና የተጋድሎ ገድል ጽፈውና አጽፈው ያሉ፣ ከዚህም የተነሳ ደግሞ ለበቀል የሚፈላለጉና በጎሪጥ የሚተያዩ ሕዝቦች ኢትዮጵያ በምትባለው ምድር ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ነው፡፡
ይህን ከላይ በመግቢያችን የገለጽኩትን አሳዛኝ ገጠመኝ ወይም ታሪክ ለዚህ ጹሑፍ መግቢያ ይሆነኝ ዘንድ የመረጥኩት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ስለ ኢትዮጵያዊነትና ኦሮሙማ (ኦሮሞ ናሽናሊዝም) በተመለከተ ‹‹በገዳ ዶት ኮም›› እና በሌሎች በተለያዩ ድረ ገጾች ሰፋ ያለ ውይይትና ክርክር ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ከስምንት የማያንሱ ማእከላቸውን አውሮፓና አሜሪካ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የኦሮሞ ምሁራን ባደረጉት ውይይትና ክርክር ከተሳተፉት ፖለቲከኞችና የኦሮሞ ምሁራን መካከል ዶ/ር በያን አሶቦና ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ይኸው የኢትዮጵያዊነትና የኦሮሙማ ሙግትም የፓል ቶክ ዋና የመወያያ ርዕስ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ውይይትና ክርክር ገና ሳይበርድና ሳይቋጭ ነበር በዛው ሰሞን ወጣቱ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና ተንታኝ ጃዋር ሙሐመድ ከአልጄዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ለዓመታት በዘለቀው የኦሮሞ ጥያቄ፣ የነፃነት ትግል ታሪክ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሰጠው፡፡ ጃዋር I am First Oromo. Ethiopia is imposed on me የሚለው አቋሙን ግልጽ ካደረገ በኋላ የኦሮሞን ታሪክና የኦሮሞን የዓመታት ጥያቄ በተመለከተ የፖለቲካ ተንታኙን የጃዋርን ትንታኔና አቋም በመቃወምም ይሁን በመደገፍ የተለያዩ ሐሳቦች መንሸራሸር ጀመሩ፣ አሁንም ድረስም እየተንሸራሸሩ ነው፡፡
ባለፉት ሰሞናትም በተለያዩ በይነ መረቦችና በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጃዋርን ሐሳብ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በየበኩላቸው አቋማቸውን ለመግለጽ ሞክረዋል፡፡ አንዳንዶችም ስድብ ቀረሽ በሚመስል ጨዋነትና ቅንነት በጎደለው መንፈስ ጃዋር ባነሳው ሐሳብ ላይ የውይይት መድረኩን የሚያጠለሹና የሚበርዙ እሳቤዎችን ከስድብ፣ ከዛቻና ከማስፈራሪያ ጭምር ሲያዘንቡም ታዝበናል፡፡ ከዚህ ውጪ ደግሞ ሰብአዊ ፍቅር፣ ጨዋነትና ቅንነት በተሞላበት መንፈስ ከኦሮሞም ይሁን ከሌላ ብሔር ተወላጆች ዘንድ፣ ሚዛናዊ የሆነ፣ ከጭፍን ጥላቻና ከበቀል ስሜት በጸዳ መንፈስ  ሐሳባቸውንና አቋማቸው የገለጹም ጥቂት ጸሐፊዎችና ተንታኞችም ብቅ ብቅ ብለው ነበር፡፡
እኔም በዚሁ ሰሞነኛ በሆነው የኦሮሞ ሕዝብን ታሪክና ጥያቄ በተመለከተ ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነትና መብት ቆመናል በሚሉ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዘንድ በኦሮሙማ (በኦሮሞ ናሽናሊዝም)፣ በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያዊነት ላይ በሚያነሷቸው አንኳር ሐሳቦችና በሚያራመዱት አቋሞቻቸው ዙሪያ ላይ ጥቂት የመወያያ ሐሳቦችን ለማጫር ወደድኩ፡፡
በእርግጥ ይህ ለውይይት ማጫሪያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ አጭር ጽሑፍ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራንና ፖለቲከኞችን፣ አሊያም ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ስም ተቋቋመው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ታሪክና በኢትዮጵያዊነት ላይ ያላቸውን አቋማቸውንና ለኦሮሞ ሕዝብ አለን ስለሚሉት የትግል አቅጣጫዎቻቸውን ለመተንተን፣ ለመተቸትና ለመገምገም አይደለም አነሳሱ፡፡ ይህን ለማድረግ እንሞክር ቢባል እንኳን በእነዚህ ጥቂት ገጾች ለመሞከር የሚታሰብ አይሆንም፡፡
ለዚህም እንደ ዋና ሆነው ከሚነሱት ዐበይት ምክንያቶች መካከል ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ስም እየተንቀሳቀሱ ያሉ በዓላማም በአቋምም የተለያዩ ፓርቲዎች መኖራቸው፡፡ እንዲሁም እነዚሁ ፓርቲዎችም የኦሮሞን ሕዝብን ታሪክና ጥያቄ  በተመለከተ የሚያራምዷቸው አቋሞችና ጥያቄዎች ‹‹ከባርነት ወይም ነፃነት›› ወይም ደግሞ ‹‹ከአቢሲኒያ/ከዛሬዋ ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ጥያቄ ነው፡፡›› ከሚለው ፖለቲካዊ አቋም አንስቶ በተለያዩ የኦሮሞ ተወላጅ ምሁራንና ፖለቲከኞች ዘንድ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ባሉ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ እምነትና ቅርስ አኳያ ያሉት አመለካከቶችና ትንታኔዎች መንገዳቸው የየቅል መሆኑን ነገርዬውን ቀላል አያደርገውም ብዬ ስለምገምት ነው፡፡
ለአብነትም ያህል የኦሮሞን ብሔርተኝነት በእጅጉ ያራምዱና ‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው፡፡›› ሲሉ የነበሩ አንዳንድ የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች በጊዜ ሂደት ኦሮሞ በኢትዮጵያ በቆዳ ስፋት ትልቁና የሕዝቡም ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ውስጥ ግዙፍ ሆነ ቦታ ሊሰጠው ይገባል፣ የኦሮሚፋም በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት ፖለቲካ አሥተዳደር ውስጥ የፌዴራል መንግሥቱ  ቋንቋ መሆን የሚችልበት መንገድ ሊታሰብብት ይገባዋል፣ የሚሉ የተለሳለሱ አቋሞችን የሚያራምዱ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ፖለቲከኞችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቅ ብቅ ማለታቸውንም ታዝበናል፡፡
ስለሆነም በዚህ ጽሑፍ የኦሮሞን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነት፣ የኦሮሞን የመብት ጥያቄና ትግል ተመለከተ በፊትም ሆነ በተለይም ደግሞ ከሰሞኑን የፖለቲካ ተንታኙ ጃዋር ሙሐመድ ባነሳው የኢትዮጵያዊነትና የኦሮሙማ አንኳር እሳቤዎች ላይ ተመርኩዤ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ወደድኩ፡፡
እንደሚታወቀው ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት ውስጥ የእከሌ ብሔር ወይም ጎሳ በዚህኛው ብሔር ወይም ጎሳ ላይ ለፈጸመው በደልና ጭቆና በሚል ያልተወራረዱና ጊዜ እየጠበቁ ቦግ እልም የሚሉ ምሬቶችን፣ ቁጣዎችንና የበቀል ሰይፎችን በተለያዩ የአገራችን ክልሎች መከሰታቸውን ታዝበናል፡፡ ይህን እኩይ የሆነ የበቀል ሒሳብ በማወራረድ የተጠመዱ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ፖለቲከኞችና ግለሰቦችም ሆን ብለውና ያልተገባ ፖለቲካዊ ትርፍ ለማግበስበስ ሲባል እውነታን በማጣመም በሚጻፏቸውና በሚያጽፏቸው የተዛቡ የታሪክ ድርሳናትና ገድሎቻቸው፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ትናንትና ያልነበረ ዛሬም የሌለ ቅዠት ወይም ሕልም ነው እስኪባል ድረስ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በርካታ ትንታኔዎቻቸውን ሰምተናል፣ የዳጎሱ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውንም አስነብበውናል፡፡
በዚህ እነዚሁ የብሔር ፖለቲካ ጽንፈኞች፣ በቀልን ሰባኪዎች፣ የብሔራዊ መግባባትና እርቅ ተቀዋሚዎች በተጻፉ የተዛቡ ታሪኮችና ያልተወራረዱ የበቀል ሒሳቦች ክፉ ስብከት የተነሣም ለዘመናት ተዋደውና ተከባብረው፣ በጋብቻና በአምቻ ተሳስረው፣ እኔ ትብስ አንተ ትብስ ብለው የኖሩ ሕዝቦች የተሳሰሩበትን የአንድነት ድርና ማግ ለመበጠስ ሲባል የተደረጉ አያሌ ዘመቻዎችንም በዘመናችን በሐዘንና በግርምት ሆነን አስተውለናል፡፡
ዛሬም ድረስ ለኦሮሞ ሕዝብ መፍትሔው የእኔ የፖለቲካ አቅጣጫ ነው የሚሉ በርካታ የኦሮሞ ምሁራን፣ ፖለቲከኞችና ፓርቲዎች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሆነው ለኦሮሞ ሕዝብ ይጠቅማል በሚሉት መንገድ የራሳቸውን አቋም በማራመድ ይጻፋሉ፣ ይወያያሉ፣ ይከራከራሉ፣ ይሟገታሉም፡፡
ይሁን እንጂ እስካሁኗ ቅጽበት ለኦሮሞ ሕዝብ ነፃነት፣ መብትና ጥቅም ቆመናል በሚሉት በበርካታ የኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራንንም ሆነ ፓርቲዎች ዘንድ ቢያንስ ባለፉት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክና ጥያቄ በማስተጋባትና በመፍትሔ አቅጣጫዎችም ዙሪያ በሚያራምዱት አቋማቸው እርስ በርሳቸው የተለያዩና የተከፋፈሉ መሆናቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ዐይተናል፡፡ በዋነኝነት የኦሮሞ ሕዝብን ጥያቄ ለመፍታት ከእኔ ወዲያ ለአሳር በማለት ሲምል ሲገዘት የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በዕድሜ የሚያክለውና የሚስተካከለው ባይኖርም ዛሬም ድረስ በተለያዩ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ውስብስብ ችግሮች ተተብትቦ እየዳከረ ያለ ፓርቲ መሆኑን የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት በፓርቲው አመራሮቹ መካከል በተፈጠረ ልዩነትና ውዝግብ የፓርቲው ህልውና አበቃለት እስኪባል ድረስ የነበረውና አሁንም በያዝ ለቀቅ በፓርቲው ውስጥ የሚነሱት ወጀብና ዐውሎ ንፋሶች ዛሬም ድረስ ገና መፍትሔና መቋጫ ያገኙ አይመስሉም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው፣ ነፃነትን የማወጅ፣ ሉዓላዊነትን የማስከበር፣ የማንነት፣ የታሪክና ፖለቲካ ጥያቄ ነው፣ በማለት ጽንፈኛ አቋሙን በሚያራምደው ኦነግና ደጋፊዎቹ ዘንድ ዛሬም ድረስ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በሸዋው ንጉሥ በምኒልክ ሰይፍ ተቀጥቅጦ በአማራ ታሪክና ማንነት ላይ የተገነባ ነው የሚለው መከራከሪያቸው አሁንም ድረስ በአቋም ደረጃ በግልጽ የሚንጸባረቅ ነው፡፡
ወጣቱ የፖለቲካ ምሁርና ተንታኝ ጃዋር ሙሐመድም ይህንኑ ሐሳብ በመድገም እንዲህ ብሎአል፡- ‹‹ … ኢትዮጵያን የመሠረታት የሦስትዮሽ ጦርነት ግብግብ ነው፡፡ በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በትግሬው ግብግብ ውስጥ ወደ መጨረሻ ላይ በአመራር ስር የበላይነቱን የያዘው አማራው ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ አሁን የምናያት ኢትዮጵያ ማንነቷ በአማራ ባሕላዊ ሥርጭትና  በአማራ ፖለቲካ የተገነባች ነች፡፡ … የኢትዮጵያ አገራዊ ማንነት የምንለውም የአማራ ባህላዊ ማንነት ነው፡፡›› ሲል ከኢትዮጵያ ታላቅ ሥልጣኔ፣ ታሪክና ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ወይም ማንነት ጋር የሚጣረስ ድምዳሜን ሰጥቶአል፡፡
ይህ ዓይነቱ ትንታኔ የኢትዮጵያን ታሪክ በአግባቡ ያለመረዳት ቀውስ ወይም ደግሞ ሆን ብሎ  የታሪክ እውነታን የማዛባት ዘመቻ ነው የሚመስለው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባለው ምድርና ሕዝቦቿ ትናንትና ከመቶ ዓመት በፊት ምኒልክና ተከታዮቹ በኃይልና በሰይፍ በሚፈልጓት ቅርፅና ይዘት ቀጥቅጠው የፈጠሯት እንጂ የሚለው መከራከሪያ ሐሳብ በምንም መንገድ ውኃ ሊያነሳ የሚችል ሐሳብ አይመስለኝም፡፡ ይህ ዓይነቱ አመለካከት ከሺሕ ዓመታት በፊት ጀምሮ በገናና ሥልጣኔዋና ታሪኳ በዓለም መድረክ ስሟ ገኖ የወጣውን፣ ከአፍሪካ አልፎ በሰሜን አሜሪካና በካረቢያን በባርነትና በቅኝ ግዛት ቀንበር ስር ተይዘው ሲማቅቁ ለነበሩ ሕዝቦች የነፃነት ምድር፣ የጥቁር ሕዝቦች ተስፋ ‹‹የጥቁር ሕዝቦች የከነዓን ምድር›› በሚል በሰቀቀንና በናፍቆት ሲያስቧትና ሲዘክሯት የኖረችውን ኢትዮጵያን ህልውና የመካድ ያህል የሚቆጠር ይመስለኛል፡፡
ኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የነፃነት ተምሳሌት፣ የአንድነትና የፍቅር ኪዳን ሆኖ በብዙዎች ልብ ውስጥ ሲንቀለቀልና ለዘመናት ሲያበራ የኖረ እውነት መሆኑን መካድ አንችልም፡፡ ከአፍሪካ አስከ አሜሪካ፣ ካረቢያና ጃማይካ ይህ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በእውቁ የነፃነት ታጋይ በእነ ማርከስ ጋርቬይ፣ በሬጌው ንጉሥ በእነ ቦብ ማርሌይ፣ በእነ ፒተር ቶሽ፣ በአፍሪካውያኑ የነፃነት አባቶች፣ በእነ ጆሞ ኬንያታ፣ በንኩርማ፣ በማንዴላና በበርካታ የነፃነት ታጋዮች ዘንድ የሞራልና ወኔ ስንቅ ሆኖ ያገለገለ፣ ክቡር ታሪክ፣ ሕያው አሻራና ቅርስ መሆኑን መዘንጋት ከታሪክ ሐቅ ጋር መጣላት ነው የሚሆነው፡፡
በተጨማሪም ለዚህችው በሺሕ ዘመናት ገናና ሥልጣኔዋ፣ ነፃነቷ፣ ታሪኳና ሉዓላዊነቷ ሲሉ በዐድዋ ጦር ግንባር ከወራሪው የአውሮጳ ኃይል ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ለሕዝቦቿም ነፃነት ዋጋ የከፈሉትን የኦሮሞ ተወላጆቹን የእነ ባልቻ አባ ነፍሶን፣ የእነ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪን፣ የእነ ራስ አበበ አረጋይን፣ አውሮጳ ምድር ድረስ ዘልቆ በሮማ አደባባይ የኢትዮጵያውያንን አይበገሬነትና ለነፃነታቸው ቀናኢ ሕዝብ መሆናቸውን ያሳየውን የአብዲሳ አጋንና የበርካታ እልፍ የሚሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ለሰው ልጆች ነፃነት የፈሰሰ ደምና መሥዋዕትነት ማራከስ ነው የሚሆነው፡፡
ከሰሞኑን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መረራ ጉዲና፡- ‹‹የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች፡- ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ›› በሚል ርዕስ በጻፉት መጽሐፋቸውም በዓድዋው ጦርነት ከየትኛውም ሕዝብ ይልቅ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ጦር አዝማቾችና ጀግኖች ታላቅ መሥዋዕትነት መክፈላቸውን በመግለጽ የዓድዋ ድል የምኒልክን ቅኝ ግዛት ዘመቻ ያጠናከረ ዓውደ ግንባር ነው የሚለውን ሐሳብ አጣጥለው በመከራከር ጽፈዋል፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ታላቅነትና አይበገሬነት በኦሎምፒክ መድረክ ከፍ ያደረጉ አበበ በቂላ፣ ዋሚ ቢራቱ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ጌጤ ዋሚ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ደራርቱ ቱሉ … እነዚህ ሁሉ በሮጡበት መድረክ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ብሔርና ሃይማኖት ሳይለዩ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ አብረው ሮጠዋል፣ ስለ ኢትዮጵያ ክብርና ድልም አብረው አምጠዋል፣ ተጨንቀዋል፡፡ በባርሴሎና ኦሎምፒክ መድረክ አበባችን ደራርቱ ቱሉ በአሥር ሺሕ ሜትር የመጀመሪያቱ አፍሪካዊት ሴት ወርቅ ሜዳሊስት በሆነችበት ድሏ የአገሯ ብሔራዊ መዝሙርና ሰንደቅ ዓላማ በስፔን ሰማይ ላይ ሲናኝና ከፍ ብሎ ሲታይ በጉንጯ ላይ ኮለል ብሎ የፈሰሰውን ዕንባዋን የታዘብን ሁሉ፣ በኢትዮጵያዊነት ኩራትና አይበገሬነት መንፈስ አብረናት በደስታ ሲቃ አንብተናል፣ መሬት ስመናል፡፡
ይህን ታሪክ በወርቅ ቀለም የጻፈውን የበርካታ ኦሮሞ ጀግኖችን ገድልና ለኢትዮጵያዊነት የተከፈለ መሥዋዕትነትን ማቃለልና ታሪክን ማዛባት ጤነኛ አካሄድ አይደለም፡፡ በዘመናችን ኦሮሙማን/የኦሮሞን ብሔርተኝነት በእጅጉ የሚሰብኩና የሚያራግቡ ሰዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ኦሮሙማን ወይም የኦሮሞ ብሔርተኝነነትን ለመገንባት ሲሉ የኢትዮጵያን የሺሕ ዘመናት ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ማጣጣልና መንኳሰስ ጤነኛ አካሄድ አይመስለኝም፡፡
ኢትዮጵያዊነት እንደ ኮሶ ተበጥብጦ በግድ እያነገፈገፈን የተጋትነው፣ እየቀፈፈንና እየኮሰኮሰን የተደረበብን ማንነት ብለው ለሚከራከሩ ሰዎች በእርግጥም በግድ ሳይወዱ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ እንደማይቻል አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ኢትዮጵያዊ ለመሆን ያለመፈለግ መብታቸውንም በግሌ አከብራለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ታሪክን በማዛባት ጥቁር ሕዝቦች፣ መላው አፍሪካና በአጠቃላይ ነፃነትን አፍቃሪ የሆኑ ሕዝቦች ልብ ውስጥ ትልቅ ዋጋና ክብር ያለውን የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ ማራከስ፣ በኢትዮጵያና በሕዝቦቿን ታሪክ፣ ቅርስና ማንነት ላይ መዘባበት ጤነኛ አካሄድ እንዳልሆነ አሁንም በድጋሚ አስረግጬ ለመናገር እወዳለሁ፡፡

 https://ecadforum.com/Amharic/archives/9594/