Showing posts with label ሶፍትዌሮች. Show all posts
Showing posts with label ሶፍትዌሮች. Show all posts

Friday, November 1, 2013

የግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ አጋለጠ


ኢትዮቴሌኮም የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሰ መንጸባረቂያ መሆኑን የግንቦት 7 የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ አጋለጠ
ይህንን ጥናት በPDF ዳወንሎድ ለማድረግ ከዚህ ላይ ይጭሃኑ 2665272d78511e341383257989 
 የመረጃ ቴክኖሎጂ መሠረት የሆነዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ አፍሪካ፤ ላቲን አሜሪካና ኢሲያ ዉስጥ የሚገኙ በእደገት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮችን ለዘመናት ከተዘፈቁበት የኋለ ቀርነት ማጥ ዉስጥ ጎትቶ አዉጥቶ ወደ ፈጣን የእድገት ጎዳና ይወስዳቸዋል ተበሎ የታመነበትና በአንዳንድ አገሮች ዉስጥ ይህ ለእድገት አመቺነቱ በተግባር የተመሰከረለት ዘርፍ ነዉ። ይህ ዘርፍ ገበሬዉ፤ ሰራተኛዉ፤ ተማሪዉ፤ ወታደሩና ለሌላም በማንኛዉም የስራ ዘርፍ ለተሰማራ የህብረተሰብ ክፍል የእዉቀት ምንጭ በመሆን የስራ ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የሚረደና በህብረተሰብ መካከል ፈጣን የሆነ የመረጃ ልዉዉጥ አንዲኖር የሚያደርግ ዘርፍ ነዉ። በእድገት ወደ ኋላ ለቀረችዉ አገራችን ኢትዮጵያም ይሀ ዘርፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ዘርፍ ነዉ። ነገር ግን በአፍሪካ ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ወደኋላ ከቀርችባቸዉና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ሆን ብሎ እድገታቸዉ እንዲገታ ካደረጋቸዉ ኋላ ቀር ዘርፎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ይሄዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ ነዉ።
እራሱን “ልማታዊ መንግስት” ብሎ የሚጠራዉ የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ከያዘባቸዉ የመጀመሪያዎቹ አመታት ጀምሮ አስከ ቅርብ ግዜ ድረስ እንደ ቤት ዉስጥ ዕቃዉ ከተቆጣጠራቸዉና የኢትዮጵያን ህዝብ በሚጠቅም መልኩ እንዳያድጉ ካደረጋቸዉ ቁልፍ መስሪያ ቤቶች ዉስጥ አንዱ ኢትዮቴሌኮም ነዉ። ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ያላደረገዉ ነገር የለም። ዘረኝነትን በሚጠቅም መልኩ አደራጅቶታል፤ የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆበታል፤ ቻይናዎችን አምጥቶ የስለላ ተቋም አድርጎታል፤ የሚገርመዉ ዛሬ ኢትዮቴሌኮም የተራቀቀዉ በስልክ፤ በኢንተርኔትና በሌሎችም የመገናና አገልግሎቶች ሳይሆን ዜጎችን በመሰለልና የመረጃ ጨለማ በመፍጠር ርካሽና ጎታች ስራዎች ነዉ። ይህንን ርካሽ ስራ ደግሞ በቅርቡ የአገዛዙ የኢንፎርሜሺን ደህንነት ኤጀንሲ ሹም ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን” የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠርና የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን የማገድ አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁም ይህ ነዉ በማለት በአዳባባይ አረጋግጧል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በላፉት አስራ ሁለት ወራት ይህንኑ ኢትዮቴሌኮም በሚል መጠሪያ የሚተወቀዉንና በስለላ ስራ ላይ የተሰማራዉን የሲቪል መስሪያ ቤት አደረጃጀት፤ አወቃቀርና የሰዉ ኃይል አመዳደብ በቅርብ ተከታትሎ ከዚህ ቀትሎ የሚታየዉን መረጃ አጠናቅሯል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚገባ እንደሚያዉቀዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን ቴሌኮሚኒኬሺን ተቋም ከኋላ ቅርነት ለማላቀቅ በሚል ሰበብ የኮርፖሬሺኑን የማኔጅመንት ዘርፍ ለፈረንሳይ ኩባኒያ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ። ወያኔ እንደሚለዉ የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ለፈረንሳዩ ኩባኒያ የተሰጠዉ የኮርፖሬ ኑን አቅም ለማሳደግ ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ወያኔ የሚናገረዉና የሚሰራዉ ስራ የተለያየ በመሆኑ ዛሬ ወያኔ ኢትዮቴሌኮም በየዘርፉ የረጂም ግዜ ልምድ ያላቸዉን ባለሙያዎች አባርሮ ታማኝ የህወሀት ታጋዮችን በመተካት ኮርፖሬሺኑን የለየለት የስለላ ተቋም አድርጎታል። ስለሆነም ዛሬ ብዙ የአፍርካ አገሮች ትልቅ ግስጋሴ ያደረጉበትና የዜጎቻቸዉን ህይወት የለወጡበት ዘርፍ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎችን እየሰለለ አገረን የመረጃ ጨለማ ዉስጥ የከተተ ተቋም ሆኗል።
ባላፉት ሁለት አመታት የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ኤን አንድና ኤን ሁለት በሚባሉ ሁለት ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች ተከፍሎ በሁለቱም ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ዉስጥ የሰዉ ኃይል ተመድቧል። ይህ በከፍተኛ ማነጅመንት ደረጃ የተመደበዉ የሰዉ ኃይል ኢትዮጵያዉያንንና የፈረንሳይ ዜጎችን የሚያጠቃልል ነዉ። በኤን አንድና በኤን ሁለት የማነጅመንት ደረጃ የስራ ድርሻ የተሰጣቸዉ ኢትዮኦጵያዉያን በቁጥር 54 ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ 46.3 በመቶ ወይም ሃያ አምስቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በዚህ ከፍተኛ የማነጅመንት እርከን ዉስጥ የኦሮሞ፤ የአማራና የተቀሩት ስድሰት ክልሎች ድርሻ በቅደም ተከተል 18. 5 በመቶ፤ 29.6 በመቶና 5.6 በመቶ ብቻ ነዉ። ከሁለቱ የማነጅመንት እርከኖች ዉስጥ ኤን አንድ የሚባለዉ ከፍተኛዉ ሲሆን በዚህ እርክን ዉስጥ ሰምንት የትግራይ ተወላጆች ሲኖሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች እያንዳንዳቸዉ ሁለት ቦታ የያዙ ሲሆን በዚህ ከፍተኛ የአመራር እርከን ዉስጥ ከተቀሩት ስድስት ክልሎች የተመደበ አንድም ሰዉ የለም።
ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት አራት ብቻ ነዉ (ሁለት ከኦሮሚያ ሁለት ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን ስምንት ሰዎች ኤን አንድ በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ከተቀሩት ስድስት የአገሪቱ ክልሎች የመጡትን ሰዎቸ ስንመለከት የሚታየዉ ስዕል እጅግ በጣም የሚያሳዝንና ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት እያለ ከሚሰብከዉ ስብከት ጋረ የሚጋጭ ነዉ። በ2012 ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል ዉጭ በተቀሩት ስድስት ክልሎች ዉስጥ የሚኖረዉ ህዝብ 25,627,349 እንደሚሆን ይገመታል። ከዚህ ህዝብ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ እድል ያገኙት 0.000012 በመቶ ብቻ ወይም ከእያንዳንዱ 8.5 ሚሊዮን ህዝብ አንዱ ብቻ ነዉ። እንግዲህ ይህንን ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነታቸዉን ተጎናጽፈዋል እያለ የሚናገረዉ።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ ቀደም ወያኔ “የኢትዮጵያ መከላከያ” ጦር እያለ የሚጠራዉን ሠራዊት ምን ያክል የኔ በሚላቸዉ የህወሀት ሰዎች ብቻ እንደሚቀጣጠር የሚያሳይ መግለጫ በመረጃ አስደግፎ ለህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። አሁንም ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ምን ያክል የራሱ የቤት ዉስጥ እቃዉ እንዳደረገዉ የሚያሳየዉን በጽሁፍና በአኀዝ የተፈገፈ መረጃ በዛሬዉ እለት ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸ ከአሁን በኋላም የወያኔን ዘረኝነትና ህግወጥነት የሚያጋልጡ ስራዎችን በተከታታይ እየሰራ ለህዝብ የሚያቀርብ መሆኑን ይገልጻል።

የጥናቱ እጠቃላይ ውጤት

ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication1
ማስታወሻ: ከላይ በስዕሉ የሚታየው እንደተጠበቀ ሆኖ በኢትዮ-ቴሌኮም ቁልፍ የሃላፊነት ቦታወች ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ ወደ 50% የሚሆነው ቦታ የተያዘው በትግራይ ተወላጆች ነው።
ይንንም ለማብራራት ያህል በአሁኑ ሰአት ካለው ጠቅላላ የሃፊነት ቀልፍ ቦታወች 14ቱ በፈረንሳውያን የተያዙ ቢሆንም ከ14 የፈረንሳይ ባለሙያወች ከያዟቸው ቀልፍ ቦታወች ውስጥ 7ቱ በትግራ ተወላጆች እንደሚያዙ ይጠበቃል። ይህም ማለት በትግራይ ተወላጆች የተያዙትን እና የሚያዙትን ቁልፍ የኢትዮ-ቴሌኮም ቦታወች ከተጠቅላለው 64ቱ የሃላፊነት ቦታቸው ውስጥ 32ቱ በትግራይ ተወላጆች የተያዙ ይሆናሉ። ይህም ማለት ከጠቅላላወ የኢትዮ-ቴሌኮም ቁልፍ የሃልፊነት ቦታቸው ውስጥ ግማሹ ማለትም 47% የሚሆኑትን በትግራይ ተወላጆች የተያዙ መሆናቸው ያሳያል።

የጥናቱ ዝርዘር ማብራያ

በዚህ ሰነድ ላይ የተጠቃለሉት ስሞች በኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት ዉስጥ በሁለት ከፍተኛ (N1 & N2) የአመራር እርከኖች ዉሰጥ የተመደቡ ሰዎች ስምና የመጡበት ብሔር ስብጥር ነዉ። ባጠቃላይ በሁለቱ የአመራር እርከኖች ዉስጥ 68 ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ አስራ ሰባቱ (N1 ዉስጥ 8 N2 ዉስጥ 9) የፈረንሳይ ተወላጆች ነበሩ። ሆኖም ቀስ በቀስ በተደረገዉ መሸጋሸግ የፈረንሳይ ዜጎች የለቀቁት ቦታ እየተመረጠ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ በመሰጠቱ አሁን በN1 ዉስጥ 5 N2 ዉስጥ 9 ባጠቃላይ 14 የፈረንሳይ ዜጎች አሉ ፤ በቅርቡ አንድ ሌላ የፈረንሳይ ዜጋ በኢትዮጵያዊ የተተካ ቢሆንም ይህ ሠኢድ አራጋዉ የተባለ ግልሰብ አማራ ይሁን ትግሬ ለግዜዉ በዉል ለይቶ ማወቅ አልተቻለም። በእርከን አንድ ዉስጥ ስምንት የትግራይ፤ ሁለት የአማራና ሁለት የኦሮሞ ተወላጆች ሲኖሩበት ከሌሎቹ ሰባት ክልሎች የመጣ አንድም ሰዉ በዚህ N1 በሚባለዉ የአመራር አርከን ላይ አልተመደበም። በአጠቃላይ በ N1 የአመራር አርከን ዉስጥ 17 ሰዎች ሲኖሩ አስራ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን አምስቱ ደግሞ የፈረንሳይ ተወላጆች ናቸዉ። ከአስራ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን ዉስጥ ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። N2 በሚባለዉ የአመራር አርከን ዉስጥ ደግሞ 51 ግለሰባኦች በአመራር ቦታ ላይ የተመደቡ ሲሆን 42 ኢትዮጵያዉያን 9ኙ ፈረንሳዉያን ናቸዉ። ከአርባ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን ዉስጥ አስራ ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ።
ይህ በከዚህ ቀጠሎ የተቀመጠዉ ግራፍ እና ሰነተረዥ የሚያሳየዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡትን ሰዎች የብሔር ስብጥር ነዉ። ግራፉ የሚያሳየዉ ሦስቱን ማለትም ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል የተመረጡ ሰዎችን ለየብቻቸዉ ሲሆን ከተቀሩት ሰባቱ ክልሎች የመጡት ሰዎች ግን ተጨፍለቀዉ አንድ ላይ ነዉ የቀረቡት።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication2ማስታወሻ: ከላይ በሰንጠረዡ የጠቀሰው የህዝብ ብዛት እኤአ በ2007 CSO ያወጣዉን የህዝብ ብዛት መግለጫ ተንተርስሶ በ2012 የኢትዪጵያ ህዝብ ብዛት 90,076, 661 ይሆናል በሚል ግምት የተቀመረ ነዉ።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication3
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች የብሔር ስብጥር
ከላይ በተቀመጠዉ የህዝብ ብዛት መሠረት በ N-1 እና በ N-2 የአመራር እርከን ኢትዮ ቴኦኮም ከተመደቡ ሰራተኞች ዉስጥ የሚከተለዉን ገሀድ እዉነት መመልከት ይቻላል። ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 193.9 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66.2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት 4 ብቻ ነዉ (2 ከኦሮሚያ 2 ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን 7 ሰዎች N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የሚያሳየዉ ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-1 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር ነዉ፤ በዚህ ስብጥር ዉስጥ የፈረንሳይ ዜጎችም አሉበት። በ N-1 አመራር እርከን ዉስጥ ከትግራይ፤ ከኦሮሚያና ከአማራ ብሔረሰቦች ዉጭ ከሌሎቹ የተካተተ ማንም የለም።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication4
ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-1 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር
ከላይ ካለው ሰንጠረዥ ላይ እንደምንመለከተዉ በ N-1 የአመራር እርከን ደረጃ ላይ የተቀመጡ ኢትዮጵያዉያን ብዛት አስራ አንድ ሲሆን ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። የእነዚህን 7 ሰዎች የስልጣን ቦታ ስንመለከት ደግሞ ሁሉም የያዙት ቦታ ቁልፍ ቁልፋዩን ቦታ ነዉ። ለምሳሌ የፕሮግራም ማነጀር፤ ፕሮግራም ዳይረክተርና የቺፍ ፋይናንሻል ኦፊሰርነቱን ቦታ የያዙት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የኦሮሞዉና የአማራዉ ተወላጆች በቅደም ተከተል የህግ አማካሪነቱንና የኢዲተርነቱን ቦታ ነዉ የያዙት።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የሚያሳየዉ ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-2 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር ነዉ። በ N-2 ከፍተኛ የአመራር እርክን ዉስጥ ዘጠኝ የፈረንሳይ ዜጎች የሚገኙ ቢሆንም በሰንጠረዡ ዉስጥ የፈረንሳይ ዜጎች ቁጥር አልተካተተም (N-2 ከ N-1 ያነሰ ደረጃ ነዉ)።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication5
ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-2 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር
ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ብዛትም ሆነ በተማረ ሰዉ ሀይል ብዛት ከፍተኛዉን ቦታ የያዘዉ የኦሮሚያ ክልል ነዉ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ከፍተኛዉን የመቀመጫ ቁጥር የያዙት የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ናቸዉ። ሆኖም በሰንጠረዡ ላይ እንደምንመለከተዉ ኢትዮቴሌኮም ዉስጥ በN-1ም ሆነ በN-2 ደረጃ በአመራር ላይ ከተቀመጡት መሪዎች ዉስጥ የኦሮሚያ ድርሻ ከክልሉ ትልቅነት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነዉ ወይም ከትንሿ ትግራይ ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ። በፖለቲካ ሀይል መስክም ቢሆን እንደዚሁ ነዉ። ህወሀት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ ብዛት 8 ብቻ ነዉ። ሆኖም የፖለቲካዉ ጡንቻዉ 178 መቀመጫ ካለዉ ኦህዴድ ጋር ሲወዳደር ሰማይና ምድር ነዉ። ህወሀት የአገሪቱን ጦር ሀይል፤ ፖሊሰ ሰራዊት፤ የደህንነት ተቋምና የኤኮኖሚ መዋቅሮች ይቆጣጠራል። ኦህዴድ ግን ከሰሞኑ እንደማስተዛዘኛ ከተወረወረለት የይስሙላ ምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ዉጭ ይህ ነዉ የሚባል የፖለቲካ ጡንቻ የለዉም።
ከሦስቱ ክልሎች ማለትም ከአማራ፤ ከኦረሚያና ከትግራይ ክልሎች ዉጭ በሌሎቹ ስድስት ክልሎች ዉስጥ 25,627,349 ያክል ህዝብ እንደሚኖር ይታመናል። ኢትዮቴሌኮም ዉስጥ በ N- 1 ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የእነዚህ ሰባት ክልሎች ድርሻ ሦስት ብቻ ነዉ። እንግዲህ ዜጎች በሞያቸዉ በሚሰሩት ስራ፤ በፖለቲካ ህይል አሰላለፍና በኤኮኖሚዉ ዘርፍ ዉስጥ በሚጫወቱት ሚና እንዲዚህ አይነት አይን ያወጣ አድሎ የሚደረግባቸዉ ከሆነ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፈጠርኩት የሚለዉ እኩልነት ምኑ ላይ ነዉ? የባህል ዘፈን መዝፈን ከሆነ እንደዛሬዉ በቴሉቪዥን አይታይም እንጂ ድሮም እንዘፍናለን።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication6
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication8
danyboy

Monday, September 2, 2013

አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል ፮)

timthumb
September 2, 2013
ናደዉ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ
በጨዋታችን መሐል አንድ አባት እንቅርትም ያገለግላል አሉ። የተናገሩት ምሳሌያዊ አነጋገር ስላልገባኝ አባባሉን እንዲያስረዱኝ መጠየቄ አልቀረም ፧እሳቸዉም ፈገግ ብለዉ ሰማህ ልጄ ፧በድሮ ግዜ የሆነ ነገር ነዉ ፦ባል ሚስቱ በጣም ታበሳጨዉና ስለት ይዞ መሬት ላይ ይጥላትና አንገትዋን ይቆጣትና ገደልኩ ብሎ አገር ጥሎ ይጠፋል፧የቆረጠዉ አንገትዋን ሳይሆን እንቅርቷን ኖሮ ሴትየዋ ከሞት ትድናለች። ይቺ ሴት እንቅርት ባይኖራት ኖሮ ሞተችም አልነበር ?!አሉና በመቀጠል አንተም የዚህን የወያኔ ግብረበላ ተላላኪ ሃጢያት ማስረጃዎች በማኖርህም አይደል ዛሬ ለማጋለጥ የረዳህ ብለዉ እኔንም ፈገግ አሰኙኝ ። የወያኔዉ ጉጅሌ ተላላኪ ምርጫዉ ስንሻዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ሁለት የተቃዋሚ ርድርጅት አመራር አባላትን እንደጀሀዳዊ ሃራካት የወያኔ ድራማ ከየስርቻዉ እየሰበሰበ ያጠራቀማቸዉን ንግግሮች ቆራርጦ በመቀጣጠል የሚያቀርባቸዉን የሚያቅሸልሹ አሉባልታዎችና የአኩራፊ ቃለምልልስና በጥላቻ የተደራረቱ ተራ ዘለፋዎቹን የተከታተለዉ ጓደኛዬ፧ይህ ሰዉ የወያኔ ጭፍን ተላላኪ መሆኑን እዉነት ነዉ። ወስላቶች።በነገራችን ላይ በራስ ዓሊ ጊዜ የደነቆረ በራስ ዓሊ ይምላል እንዲሉ ጋሻው ካሴ የሚባል ሞፈሩን አስቀምጦ አዲስ አበባ የገባ ፣ ወያኔ አዲስ አበባን በተቆጣጠረ ወቅት የአ.አ. ዩ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝደንት ስልነበርኩ “ታላቅ ታጋይ ነኝ ፤ አንቱ በሉኝ በሚል የከንቱዎች ፈሊጥ ያለአቅሙ ራሱን የቆለለ ግለሰብ በፍርሻው ስንሻው ሬድዮ ከቀረቡት አንዱ ነው። ይህ ግለሰብ፣ በኬንያ ተስዶ እያለ አብረውት ለተሰደዱት ተማሪዎች የሚላክውን ገንዝብ ብቻውን ሲያጠፋ የነበረ፣ ወስላታና ግብዝ ግለስብ ማንነት ኬንያ በስደት በስደት የነበርን እናውቃለን።
የሆነ ሆኖ በትናቸው ስንሻውም ሆነ እንደ ጋሻው ካሴ አይነት መሸ በከንቱዎች አሁን ወያኔ አየፈፀመ ካለው ጸረ ህዝብና ጸረ አገር ተግባራት አኳያ የአንድነት ሀይሉን ማስተባበር ሲገባ ፧ተቃዋሚ መሪዎች ላይ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ማካሄድ ምን ይባላል ?! አለ ጓደኛዬ ለብዙ አመታት የሱ ራዲዮ ጣቢያ ደቀመዝሙር የነበረዉ፧ ዛሬ ግን እንደኢሠፓዋ ባለቤቴ ለሱም እሱነቱ ተገለፀለት በሚገባ አነበበዉ በትናቸዉን እዉነትም በትናቸዉ አለ ጭንቅላቱን በሁለት እጆቹ ይዞ !!ዛሬ ይህ ከሃዲ ባንዳ ከጥቂት ቀላዋጮች ጋር ሆኖ አጥፍቶ ሊጠፋ ሲንገዳገድ ሊጥልበት ያሰበዉ ቦታ ላይ ሳይደርስ የያዘዉ ፈንጂ እጁ ላይ ፈነዳበት ። በወያኔ በሚመፀወተዉ የመንደር ራዲዮኑ ላይ እንደሚያላዝነዉ፥ ዳያስፖራ ዉስጥ እገሌ ተብሎ የሚጠቀስ የተደራጀ የተቃዋሚ ፖርቲ የለም አገር አሳልፎ ለጠላት የሚሸጥ ተቀጣሪ ብቻ ነዉ ። እኔ የማቋቍመዉን ፖርቲ ተቀላቀሉ ብሎ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከከፈተዉ ቤተክርስቲያን አባል ከሆኑ ከአንዲት ባልቴት ሰማሁ። በቅንጅት መሪዎች እስር ማግስት አቋቍሜአለሁ ብሎ ያወጀዉና ሰዉም አይንህን ላፈር ብሎ ስቆበት እሱም ትቶት የነበረዉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ንቅናቄ ብሎ ራሱ ብቻ በምናቡ የመሰረተዉን የኮሚኒስት ፓርቲ ከስምንት አመት በኋላ ከእንቅልፉ ሲነቃ ዛሬ ከጥቂት ተስፈንጣሪ ግለሰቦች ጋር የአዲስ ፓርቲ ምሥረታ ዘፈን ሊዘፍንልን ይዳዳል ይህ አጉራ ዘለል ካድሬ በቤተክርስቲያን ስም የሚያስገባዉ የሙዳየ ምፅዋት ገቢ ሲቀንስ በዚህ በኩል ሌላ የደም ገንዘብ ለመስራት ማሰቡ እዉነት ነዉ። ግን ይሳካለት ይሆን?! ወደፊት የምናየዉ ይሆናል፧የተላላኪዎችን ትያትር ማየት አይሰለቸን!!!
የትንቢተ ዳንኤል ምእራፍ ፮ ከቁጥር አሥራአንድ እስከ ሃያአራት፧መልእክቱ በአጭሩ እንዲህ ይላል ፦ ዳንኤል ለንጉስ ብልጣሶር የወርቅ ጣዖት አልሰግድም አለ፥ለእግዚአብሔር አምላኩ ብቻ ፀሎት በማድረሱም ምክንያት በቤተመንግሥቱ አካባቢ በሚገኙት ሆድ አደር ተላላኪዎች ተከሶ ንጉሡ ዘንድ ቀረበ ንጉሡም ወደ አንበሶች ጉድጓድ እንዲጣል አዘዘና ተጣለ ። እግዚአብሔር አምላክም የአንበሶችን አፍ ዘጋ ዳንኤልም በአንበሶች ሳይበላ ቀረ ንጉሡም የእግዚአብሔርን ተአምራት ተመለከተ አደነቀ የዳንኤልንም ከሳሾችና ሆድ አደር ተላላኪዎች አስጠርቶ በሱ ምትክ ቅጣቱ እንዲፈፀምባቸዉ አዘዘ ከነቤተሰቦቻቸዉም ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣሉ ፣ወደ ጉድጓዱ መጨረሻ እንኳ ሳይደርሱ አንበሶቹ ያዝዋቸዉ አጥንታቸዉንም ሁሉ ሰባበሩ ይላል ቅዱሱ መፅሐፍ።
አዎ!ነገም ለወያኔዉ አምባገነን አገዛዝ እድሜ ለማርዘም ለከርሳቸዉ ያደሩ የወያኔ ግብረበሎች ተመሳሳይ ሕዝባዊ ፍርድ ይጠብቃቸዋል ወደ አንበሶች ጉድጓድ ይጣላሉ ።ያ ቀን ሲመጣ ፧ለቅሶና ዋይታ መቆጨት ዋጋ አይኖራቸዉም ዛሬ በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚፈፅሙት ወንጀል ነገ ትፋረዳቸዋለች፧ የነ ወጣት ሽብሬ ደም፧ የነ አሰፋ ማሩ ደም በቅንጅት ድጋፍ የተቃዉሞ ሰልፍ ምክንያት በጠራራ ፀሐይ የተጨፈጨፉት የመቶ ዘጠናሶስት ኢትዮጵያዉያኖች ደም በደኖ ገደል ከነሕይወታቸዉ የተወረወሩት ንፁሃን ደም በየመስጊዱ አንገታቸዉ እየተቀላ የሚገደሉት ሙስሊሞች ደም በዋልድባ ገዳም በጭካኔ የተጨፈጨፉት መናንያን ደም ጎጆዋቸዉ ዉስጥ ሆነዉ እሳት የተለኮሰባቸዉ ንፁሃን ደም እንዲሁ ሜዳ ላይ ዉሻ ልሶት አይቀርም ነገ ዋጋ ያስከፍላል ።በምድርም በሰማይም!!!
ይህንኑ እዉነት ትናንት ኢራቅ በሳዳም ሁሴን፣ሊቢያ በጋዳፊ፤ ግብፅ በሙባረክና በሌሎችም ጨፍጫፊ አምባገነን መሪዎችና ቤተሰቦቻቸዉ ተላላኪ ሆድአደሮቻቸዉ አይተናል አንበሳ ጉድጓድ ሲጣሉ ነገ የአገራችን ጨፍጫፊዎችና አስጨፍጫፊዎች ተረኞች ይሆናሉ። ተላላኪዎቻቸውም እንዲሁ ለመሆኑ ዛሬ በሁለቱም አምባገነን አገዛዝ እጆቻቸዉን በንፁሃን ዜጎች ላይ ያሳረፉት እነ በትናቸዉ ስንሻዉን ጨምሮ በአካለ ስጋ ዛሬ የምናያቸው ፅንፈኞች ካለፈዉ ስህተቶቻቸዉ ምን ተማሩ?!ነገስ በአሁኑ ወቅት እነሱ በሚሰሩት ወንጀል ቤተሰቦቻቸዉ አንበሳ ጉድጓድ መጣል አለባቸዉ?!ፈራጁ ንጉስ እዉነት ነዉ!የኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ የኢትዮጵያ አምላክ ነው!!ለመሆኑ ልጆቻቸውስ በነሱ ወንጀል አንገታቸዉን ደፍተዉ ቀሪዉ ዘመናቸዉን የሰዉ አይን እየሸሹ በወላጆቻቸዉ ስም መጠራትን እያፈሩ እንዲኖሩ ለምን ይፈርዱባቸዋል??!!
ትናንት ቀይ ባሕርን አቋርጦ የመሪዎችን እጅ ለመሳም ለያዥ ለገናዥ አስቸግሮ የነበረዉ የዉስጥ እጅ እንደምንም ተሹለክልኮ በሳመ ማግስት ለወያኔ ፍርፋሪ የተንበረከከው እሱም ዜሮ ዜሮ የሆነዉ ሆድ አምላኪው አቀንቃኝ ሰለሞን ተካልኝ ከወያኔ ተላላኪነት ጡረታ መዉጣቱ በሰፊዉ በከተማችን እየተወራ ነዉ። ለሱ ተመድቦ የነበረዉ የራዲዮ የአየር ሰአት በጀትም በአዉራምባዉ ድሕረገፅ አምደኛ በታጋይ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ በኩል ለበትናቸዉ ስንሻዉ እንደሚዘዋወርለት በሰፊዉ በከተማችን ይወራል። በትናቸዉ ስንሻዉ ደግሞ ሰሞኑን አንጋፋዉንና የአርባ አመት ትግል እያካሄደ ዛሬም ድረስ አለ የሚባለዉን ኢሕአፓንና ግንቦት ሰባትን የማፍረስ እንቅስቃሴዉ በወያኔዎች ተወዶለታል፥ለዚህ ይመስላል ሰሞኑን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከነበረከት ስምኦን በታጋይ ዳዊት ከበደ በኩል የተቸረዉ። ሰለሞን ተካልኝም ዳያስፖራውን ይቅርታ ሊጠይቅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አንድ ለቤተሰቡ ቅርብ የሆነ ሰዉ ከወደ ቨርጂንያ ሹክ አለኝ። ምን ችግር አለ እንቀበለዋለን !ቂም መያዝ ድሮ ቀረ !ቂም መያዝ ያረጀ አካሄድ ነዉ ፧የፋራ ነዉ ይባልልኛል ። እንደተለመደዉ በራችን ወለል አድርገን እንቀበለዋለን ፧የጠፋዉ በግ ተገኘ ብለን ርችት እንተኩስለታለን ፧ሲሄዱ መሸኘት ፧ያጠፉትን አጥፍተዉ ሲመለሱ መቀበል ለምደን የለ?! ወያኔም እንደሸንኮራ ምጥጥ አድርጎ ይተፋቸዋል ትፋቱን እላያችን ላይ ጠራርገን እንቀበላቸዉና ትልልቅ ቦታ ይሠጣቸዋል ለዚህ በምሳሌነት ስም መጥቀስ ይቻል ነበር ግን ወቅቱ አይፈቅድልኝም ። ድል አድርጎ እንደተመለሰ ጀግና?!!የዳያስፓራውም ሚዲያዎች ይቀባበልዋቸዋል። ብዙዎቹ ባዶ እጃቸዉን ያለመረጃ ይመጣሉ ነገ አንደለመዱት ጓዳ ጎድጓዳችንን ፈትሸዉ ምስጢራቱን በዝብዘዉ ተመልሰው ይሄዳሉ ያሞኙናል ፧ገንዘብ ይሰሩብናል ልበል በአራዳ ቋንቋ!!!? የዳያስፖራ ፖለቲካ ይሄ መሆኑ ነዉ ወገኖቼ ኢትዮጵያዉያን ።ለዚህ ነዉ ይህ አጓጕል አካሄዳችን ልቤን አሳምሞኝ ፦፦እስቲ ቂማችን ጥቂት እንኳን እናቆየዉ የሚል ርእስ ለክፍል አንድ ፅሁፊ የሰጠሁት።
ዛሬ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልና ደጋፊ ነን የሚሉ አስተሳሰበ ደሀ ግለሰቦች የጋራ ጠላት የሆነዉን የወያኔ ኢሕአዲግን ፓርቲና ባለስልጣኖቻቸዉን ከማዉገዝና ከመታገል ይልቅ የተቃዋሚዉን ጎራ ስም ጥላሸት መቀባትና ማዉገዝ ይመቻቸዋል ጊዜያቸዉንም በዚህ አይነት ልፊያ ላይ ማዋል ያስደስታቸዋል ፥ መጠላለፍ ይወዳሉ ሰዉን ማዋረድና ሰድቦ ለተሳዳቢ መስጠት አነሱን ያገዘፋቸዉ አዋቂ ያስባላቸዉ ይመስላቸዋል አገሪቱን በሚችለዉ አቅሙ ለመታደግ የተነሳዉን ጎትቶ መጣል ከምንም በላይ ያስደስታቸዋል በቃ በነሱ ቤት ይሄ ትልቅ ትግል ነዉ። በዚህ አይነት እኩይና መሰሪ እንቅስቃሴያቸዉ ደግሞ ገንዘብ ይሰሩበታል መንደርተኛ ራዲዮን ከፍተዉ የከፋፋይና በታኝ ተግባራቸዉን ያራግቡበታል፧ለወያኔ ዱላ ያቀብሉታል በብዙ ገንዘብ ሊያገኝ የማይችለዉን መረጃ በአየር ላይ ቤቱ ድረስ ይልኩለታል፧ እንደነበትናቸዉ አይነት ማፈሪያዎች ሥራቸዉ ይኸዉ ነዉ፧በቃ!!
ሌላዉ እዚህ አገር ለሚደመጡ ራዲዮኖች መልእክት አለኝ የሚሰማ ጆሮ ያለዉ ይስማ መቸም አገራችን ዉስጥ ላለፉት አርባ አመታት ያላየነዉ የፖለቲካ ድርጅት የለም ብዙዎቹ ዛሬ የሉም። በህልዉና ዘመናቸዉም በዉስጣቸ የሃሳብ ልዩነቶችን አስተናግደዋል ። ያጠፋዉንም በድርጅቱ ዉስጠ ደንብ ዲሲፕሊን የእርምት እርምጃ ተወስዷል ።አንጃዎችም ተፈጥረዉ ተለያይተዋል ።በሥርአት በመከባበር የተፈፀመ ጨዋ ተግባር ፧ጨዋ ዘመን አይተናል። ዛሬስ ?!በተለይ በዳያስፓራዉ የፈረደበት የመዋጮ ራዲዮ ተከፍቶ በአንድ ወቅት ለአንድ አላማ ተሰልፈዉ የሕይወት መስዋእትነት ለመክፈል ቃልኪዳን ገብተዉ የተሰለፉ ወገኖች ጓዶቻቸዉንም ለዚህ አላማ አሰልፈዉ ፧ያጡ የወጣትነት ዘመናቸዉን ለዚህ ሕዝባዊ ትልቅ አላማ መስዋእት ያደረጉ ሁሉ ፧ዛሬ አዎ ዛሬ ፧በራዲዮ ላይ ወጥቶ መገላለጥና መዘራጠጥ ሃላፊነት የጎደለዉ ተግባር ይመስለኛል።ለዚያዉም የህቡእ ድርጅት የተዋቀረ ድርጅት የጠንካራ ፓርቲዎች ሞዴል ይባል የነበረ እጅግ መዉረድ ነዉ ወገኖቼ!!ለዚህ ፓርቲ ዉድና ተተኪ የማይገኝለትን ሕይወታቸዉን መስዋእትነት የከፈሉትን ዜጐች መርሳት ነዉ ። ለጠላት መሳለቂያነት መዋል!? ሀላፊነት የጎደላቸዉ ኪራይ ሰብሳቢዎች ደግሞ እሰጥ አገባዉን ይወዱታል የሬዲዮናቸዉን አድማጭ ይናፍቃሏ!! ገንዘብም አይደል!? እነሱ ምን ጎደለባቸዉ የየዋሃን ገንዘብ አይደል?! ወገኖቼ ቆም ብላችሁ ሁኔታዉን በዚህ መስታወት ተመልከቱት ፥ብዙዎቻችን ዛሬ ከዚህ ፖርቲ ጋር ባንኖርም ኢሕአፓ የልጅነት ትዝታችን ነዉ።
ወንድም እሕቶቻችን እናት አባቶቻችን ገብረንበታል። ብዙዎቻችን አሁንም ድረስ ህሊናችን ቆስሎአል አካለ ጐደሎም የሆንለት ጥቂቶች አይደለንምና እና እባካችሁ!? ማራገቡን ተዉት ክቡራን አራጋቢዎች!አዛኝ ቅቤ አንጓች አትሁኑ የጥላቻና የብቀላ ስራ ይመስልባችኋል።
ይቀጥላል ክፍል፯
አስተያየት ወይም መረጃ ካለዎት በዚህ አድራሻዬ ይላኩልኝ። kifeleta11@gmail.com

Friday, August 30, 2013

ኢቲቪው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ



በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜናዎችንና መንግስታዊ መግለጫዎችን በማንበብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ መደብደቡን ጓደኛው ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ አረጋገጠ። ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ “ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው – ጥቂት ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ” በሚል በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ የጋዜጠኛውን መደብደብ ማረጋገጡን ገልጾ መደብደቡን ግን አውግዟል።
ጽሑፉ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል ዘ-ሐበሻ እንደወረደ እንዲህ አቅርባዋለች፦

ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው -
ጥቂት ነገር ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ

(ከደመቀ ከበደ)
ከትናንት በስቲያ አንድ ወዳጄ ‹‹ተመስገን በየነ ተደበደበ የተባለው እውነት ነወይ›› ሲል ኢንቦክስ አደረገኝ፡፡ ላጣራና እነግርሀለሁ ብዬው ተለያየን፡፡
****** **** ***** *****
ተመስገንን በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ በጣም ሰላምተኛ፣ ትሁትና ስራውን አክባሪ ነው፡፡ ከውድነህ ክፍሌ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ የአየር ሰአት ወስደው ይሰሩ በነበረበትና እኔም ከመልቀቄ በፊት ወደ ስቱዲዮ በመጣ ቁጥር የበዛ ትህትናውን እየለመድኩት መጣሁ፡፡ ከዚያ በኋላም ሜሮን ጌትነት፣ አንሙት አብርሀም፣ እሱ /ተመስገን/ እና ሌሎች አምባሳደር ለሆኑለት የልመና ማስወገድ ጉዳይ የተቻለውን ሲያደርግ በዘገባ ጉዳይ ብዙ ተረዳድተናል፡፡ በቃ ስራውን ያከብራል፤ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ትጉህና አርአያ ነው – አሁንም ከትህትና ጋር፡፡
ሰሞኑን ስለ እሱ የሰማሁትን በሁለት መልኩ ለማጣራት ጣርኩ፡፡ አንደኛው ከእሱ ከራሱ እና ከባለቤቱ /የቀድሞ ባልደረባዬ እምርታ አስፋው / ጋር ደወልኩ፡፡ የሁለቱም ስልኮች ኦፍ ናቸው በተደጋጋሚ ብሞክርም፡፡ / እስካሁን ድረስ/
ሁለተኛው ከቅርብ ወዳጆቼ እውነቱን ለማጣራት ደወልኩ፤ /ከባለቤቱ ወዳጆችና ከ‹‹አምባሳደርነት›› ወዳጆቹ ማለት ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው ናቸው/
‹‹ጉዳት መድረሱንና ህክምና በመከታተል ላይ›› መሆኑን ነገሩኝ፡፡
‹‹ማን እና ለምን›› ለሚለው ግን መልስ አልነበራቸውም፡፡ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡
ከተደጋጋሚ ሙከራዬ በኋላ የባለቤቱ /ከደቂቀቃወች በፈት/ እምርታ ስልክ ጠራ – አነሳችው፡፡
‹‹አሁን በመልካም ጤነነት ላይ ይገኛል፡፡ ትንሽ ቆይተህ ደውልለትና ራሱን አናግረው፤ አሁን ደክሞት ሰለተኛ ነው እንጅ እየተሸለው ነው፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ምክንያቱ ግን ምንድን ነው›› ስል ደገምኩ ጥያቄዬን፡፡
‹‹አላወቅንም፤ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞታል፡፡ ከተጣራ በኋላ እንነግርሃለን›› ብላኝ ‹‹እግዜር ይማረው ብዬ›› ተለያየን፡፡
የሆነውን እስኪ ከሰብአዊነት ብቻ እየመዘንን ‹‹እየተወሩ ያሉ›› ምክንያቶችን እንይ፡፡ ሰብአዊነትን ሰው ከመሆን ጋር ብቻ ሚዛናችን ነው!!
‹‹ተመስገን የተደበደበው በኢቴቪ ዜና የተነሳ ነው›› – እንበል፡፡ ‹‹ማን ደበደበው›› የሚለውን ማጣራቱ ለኔ ፅሁፍ ጠቃሚ አይደለምና ብዙ አልዘላብድም፡፡ ግን ‹‹በኢቴቪ ዜና የተቆጡና የተበሳጩ አካላት ወይም ግለሰቦች ነናቸወው ከተባለ ይሀህ መታየት አለበት፡፡
በሚዲያ ህግ አንድ የሚዲያ ተቋም የሚተዳደረው ‹‹በኤዲቶሪያል ፖሊሲው›› ነው፡፡ የሚዲያ ህገ መንግስት ይባላል፡፡ ይህ ‹‹ኤዲቶሪያል›› እንደየ ሚዲያው ፍላጎት፣ እንደየ ሚዲያው ማሰራጫ አገር፣ እንደየሚዲያው ገዥዎች እሳቤና እውቀት የሚወሰን ነው፡፡ እንደኛ አገር ባሉ ታዳጊ አገራት የሚዲያዎች ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ከአገሪቱ ህገ – መንግስት ጋር የተቆራኜ ነው፡፡ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይበዛበታል፡፡ ኢቴቪም ከዚህ የወጣ እንዳልሆነ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል ፡፡
ታዲያ በማንኛውም ሚዲያ ተቀጥሮ የሚሰራ ሁሉ / ይህ የግል ሚዲያዎችንም ይጨምራል/ ኤዲቶሪያሉን አክብረው የመስራት ግዴታ አለባቸው፡፡ በኤዲቶሪያሉ ያልተስማማ መልቀቅ ብቻ ነው ምርጫው፡፡ ጋዜጠኞች የቤቱ ኤዲቶሪያል ፈፃሚ ሲሆኑ አለቆች ደግሞ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
ወደ ዜና አንባቢዎች ስንመጣ ደግሞ፤ ዜና አንባቢዎች የተሰፃቻን ዜናች ያላንዳች መነካካት የሚያነቡ ናቸው – ፖስተኛ ማለት ነው ዜና አንባቢነት፡፡ የተሰጠህን መቀበል ብቻ!!
የሙሉ ጊዜ ዜና አንባቢ / የሚዲያው ቋሚ ተቀጣሪ/ እና የፍሪላንስ ዜና አንባቢዎች አሉ፡፡
ተመስገን በየነ የፍሪላንስ ዜና አንባቢ ነው፡፡ የኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰሩትን ዘገባ ከማንበብ የዘለለ ምንም ሚና የሌለው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ወጥቶ መረጃ ቃርሞ ወይ ኤዲት አድርጎ የማቅረብ አንዳች ተልዕኮ የለውም፡፡
ይህን ነው ‹‹ለምን›› እንድል ያደረገኝም ፤ ብዬም ወደእናንተ ያስፃፈኝም ‹‹ይኸወ የአንባቢነት እንጅ የመረጃ ቃራሚነት ወይም ሃያሲነት›› ሚና የሌለው መሆኑ ነው፡፡
አሁንም ‹‹ተደባዳቢው›› አካል ማንም ሆነ ምንም ድርጊቱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ‹‹ድብደባ›› በሰው ልጅ ላይ ተገቢ አለመሆኑን የማልደግፈው ሰው በመሆኔ ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ያነበባቸው ዜናዎች ያስቆጡት ‹‹አካል›› ወይም ‹‹ግለሰብ›. የፈፀመው ከሆነ ለኔ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› ይሆንብኛል፡፡ አሁንም እደግመዋለሁ ፤ ተመስገን በዜና አንባቢነቱ ከሆነ የተደበደበው ነውር ነው – ፖስተኛ ሳይሆን ፖስታውን የፃፈው ነው መጠየቅ ካለበት መጠየቅ ያለበት፡፡ / መደብደብ ያለበት አላልኩም/
እህስ ሌላ ጉዳይ አስደብድቦት ከሆነስ ብለን እንጨምር፤
ዘረፋ የሚፈፅሙ ማጅራት መቺዎች ከሆኑም ‹‹ህግና እግዜር›› መፍትሄ ይሰጡት ዘንድ እመኝለታለሁ፡፡
በማንኛውም ምክንያት ‹‹በቂም ተነሳስቶ›› ተፈፅሞ ከሆነም ‹‹ከድብድብና ስድብ›› ወደ ቅርርብና ፍቅር መምጣት ይቻላል ባይ ነኝ፡፡ በእኔ እምነት ሰውን ከማያግባባው የሚያግባባው ነገር ይበልጣል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!

Saturday, August 17, 2013

የሥላሴዎች እርግማን (ሦስት)

የሥላሴዎች እርግማን (ሦስት) ፦ አዳክሞ ማደህየት (ፕ/ር መሰፍን ወ/ማርያም)

አንድ በጣም የተገረመ ደቡብ አፍሪካዊ ይህንን ሁሉ መንገድና ሕንጻ በአንድ ጊዜ ለማሠራት ገንዘቡን ከየት ነው የምታገኙት? ብሎ ጠየቀኝና ከወርቅ-ቡና አልሁት፤ ሳቅ አለና እኔኮ ከልቤ ነው የምጠይቅህ አለኝ፤ እንግዲያው ዘክዝኬ ልንገርህ አልሁት፤ ለወትሮው ብዙ የምክር ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም ለመንግሥትህ እንዳትናገርና የዚሁ ዓይነት ሥራ በደቡብ አፍሪካ እንዳይጀመር ቃል ግባልኝ አልሁትና ቀጠልሁ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመንግሥት ባንኮች ደጃፍ ላይ የነበረውን መጨናነቅ አይተሃል ወይ? ብዬ ጠይቄው ማየቱን ካረጋገጥሁ በኋላ ጉዳዩን እንደሚከተለው አስረዳሁት፡፡
Prof. Mesfin Woldemariam
Prof. Mesfin Woldemariam
አገዛዙ መሬቱንም ሆነ ቤቶችን የራሱ ካደረገና ባለቤትነቱን ካረጋገጠ በኋላ በየመንገዱ ዳር እንጀራ፣ ዳቦ፣ ቆሎ፣ ጠላና ትናንሽ ነገር እየሸጡ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶች፣ በየቤቱ እየሠሩ በነዚህ ቤቶች ተዳብለው ኪራይ እየከፈሉ የሚኖሩ ሴቶች በብዛት ነበሩ፤ በነዚህ ደሀዎች ላይ ቀበሌዎች በየጊዜው እየዘመቱ ቤቱ እንደሚፈርስባቸው እያስፈራሩ ደሀዎችን ያሸብራሉ፤ በዚህ ዓይነት ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ለጥቂት ወራት ካቆዩአቸው በኋላ ክረምትን ጠብቀው በግድ ያስለቅቁአቸዋል፤ በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባ ውስጥ የተፈናቃይ ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ በአንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ የሚኖረው ሰው ቁጥር እየበዛ ለጤንነት ክፉ ጠንቅ እየሆነ ነው፤ ይህ ችግርና ስቃይ ትልቅ የሀብት ምንጭ ሆኖአል፤ ደሀ የሚበላው አንጂ የሚከፍለው አያጣም፤ ነጭ ደሀ ነጭ ማር ይከፍላል፤ እነዚህ ባህላዊ አነጋገሮች ተጠንተው በተግባር ላይ እየዋሉ ነው።
እንዴት? ማለት ጥሩ ነው፤ እነዚህ (ቤቶቻቸው ከማለት ይልቅ) መጠለያዎቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች ከረሀቡ ሌላ በብርድና በጸሐይ በመጉላላታቸው የመጠለያ ችግራቸው በጣም ከባድ ስለሆነ በቀላሉ የሚበዘበዙ ናቸው፤ ችግሩን መፍቻ የሚመስል የደሀውን ነፍስ በጉጉት ሰንገው የሚይዙበት ኮንዶሚንየም የሚባል ማቁለጭለጫም አለ፤ ደሀ ሁሉ ኮንዶ አግኝቶ የሚያልፍለት ይመስለዋል፤ ስለዚህ ሁሉም ይፈልጋል፤ ስለዚህ የኮንዶ ፈላጊው ሰልፍ በጣም ረጅም ነው፤ ስለዚህ በመስገብገብ እየተተኮሰ ዋጋው በጣም ከፍ ያለ ነው።
ማፍረስ ከመገንባት የቀለለ ቢሆንም በአዲስ አበባ የሚካሄደው አብዛኛው የመገንባት ሥራም ከማፍረሱ ሥራ የተሻለ መሆኑ በጣም ያጠራጥራል፤ እንዲያውም የማፍረሱንም ሆነ የመገንባቱን ሥራ የሚመሩት የውጭ አገር (ምናልባትም የቻይና) ሰዎች ናቸው ለማለት ያስደፍራል፤ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ነፍስ ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የተጋድሎ ጀግንነት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የአገር ፍቅር ውስጥ መሬት እንዳለ የውጩ አገር ሰው በምን መንገድ ሊያውቅ ይችላል? አንድ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ውስጥ ባለው ቤት ውስጥ ምን ምን ይሠራል? አንዴት ይሠራል? በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ አገሩ ሰው ምንም ያህል አያውቅም፤
ስቱድዮ በወር አንድ መቶ ዘጠና አምስት ብር፣ ባለአንድ መኝታ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር፣ ባለሁለት መኝታ አምስት መቶ ብር እንደሚከፈል ተወስኖአል፤ ይህ ኪራይ ሁላችንም እንደምናውቀውና እንደለመድነው ዓይነት ያለ ኪራይ አይደለም፤ ልዩ ነው፤ አንዱ ልዩ የሚያደርገውም መጠለያዎቹን ሁሉ ያፈረሱትና ችግሩን የፈጠሩት ራሳቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸው ነው፤ ዋናው ልዩ የሚያደርገው ግን ለኮንዶዎቹ ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ሕንጻዎቹ ተሠርተውና አልቀው ተከራዮቹ ከገቡ በኋላ አይደለም፤ የሕንጻዎቹ ሥራ የሚጠናቀቀው ቢያነስ ከአምስት ዓመት በኋላ ሲሆን ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ዛሬ ነው! ደሀዎች ለማይኖሩበት ቤት ኪራይ ይከፍላሉ! ማንም አላስገደዳቸውም፤ ያስገደዳቸው ደካማነታቸውና መናጢ ደሀነታቸው ነው፤ መስገብገባቸው ነው።
ከቀረበው መረጃ ተነሥተን እስቲ ትንሽ ስሌት እንሥራ፤ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ውስጥ ስምንት መቶ ሺህ ያህል ሰዎች ለኮንዶ ተመዝግበዋል እንበል፤ በስቱድዮ፣ በአንድ መኝታ፣ በሁለት መኝታ፣ በሦስት መኝታ በእያንዳንዳቸው የቤት ደረጃዎች ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ቢመዘገቡ ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት በዝቅተኛ የደሀነት ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሢሶ የሚሆኑት ደግሞ የደሀነት መሀከለኛ ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሌሎቹ ማለትም አንድ አምስተኛ የሚሆኑት በተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ ደሀዎች ቢሆኑ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በያመቱ የሚሰበሰበው ገንዘብ እንደሚከተለው ይሆናል፤
ደሀነት ሲበዘበዝ
Pro .Mesfin
እንግዲህ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከመጠለያ ማጣት ጭንቀት ለማምለጥና ያደረባቸውን የኮንዶ ጉጉት ለማሳካት ከአራት ቢልዮን ብር በላይ እየተራቡ ይገብራሉ፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ገና ኮንዶው ውስጥ ሳይገቡ ላባቸውን ያንጠፈጠፉበትን 20 625 000 000 ብር ይከፍላሉ ግፍ ሌላ ትርጉም የለውም።
ማፍረስም በጣም ትርፋማ ሥራ ሆነ።
በፈረሰው ላይ የሚገነባውስ? ስለኮንዶው ሕንጻ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሣት በግድ ያስፈልጋል፤ አንደኛ የኮንዶው ሥራ መቼ ተጀምሮ መቼ ያልቃል? ያልቃል ሲባልስ ለመኖሪያ ብቁ የሆነ፣ በሮችና መስኮቶች ተገጥመውለት፣ ወለሉና ጣራው፣ የመታጠቢያ ቤቱ ሁሉ ተሟልቶ ነው ወይስ ባለቤት የሚሆኑት ሰዎች የሚጠብቃቸው ሥራ አለው? ሁለተኛ የኮንዶው ሕንጻ ስንት ክረምትና ስንት በጋ የሚችል ይሆናል? ሦስተኛ ኮንዶው ሰዎችን ወደከፍተኛው ፎቅ የሚያደርሳቸው ‹ሊፍት› አለ ወይስ ሰዎች በእግራቸው በደረጃ ሊወጡ ነው? ይህ ከሆነ ለሽማግሌዎችና አሮጊቶች ምን ዝግጅት ተደርጎላቸዋል? ሽማግሌዎችንና አሮጊቶችን ወደምድር ቤቱ አካባቢ ለመደልደል ታስቦአል ወይ? አራተኛ የውሀ አቅርቦቱ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ውሀ በሚጠፋበት ጊዜ ነዋሪዎቹ ሊጠቀሙበት የሚችሉበት የመጸዳጃ ቦታ ካልተዘጋጀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አካባቢው ለጤና ጠንቅ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፤ ‹‹የአበሻ ኑሮ›› የሚባል ነገር ያለ ይመስለኛል፤ ቡናና ጌሾ መውቀጡ፣ ብቅልና በርበሬ ማስጣቱ፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ አንጀራ መጋገሩ፣ ማኅበሩ፣ ለቅሶው — እነዚህና ሌሎችም ማኅበራዊ ግዴታዎች ኮንዶው ሲሠራ ታስበው ነበር ወይ?
ደሀው ራሱን በማፈራረስ፣ ይበልጡኑ በሚደኸይበት ሥራ እንዲጠመድ፣ በፍርስራሽ እንዲነግድ በምናምን ተይዞአል! የሥላሴዎች እርግማን!
source... ecadforum.com

Saturday, July 28, 2012




እንደምን ናችሁ የእውነት ተከታታዮች መረጃ ልስጣችሁ ሶፍትዌር ይፈልጋሉ ይጻፉልኝ
ካሉበት ድረስ ይደርስዎታል ሌላም ጥያቆ ካለዎት ይጻፉልን፡፡
Ewunet team