Monday, September 30, 2013

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ! በግርማ ሠይፉ ማሩ

በግርማ ሠይፉ ማሩ

Girma-Seifu2
ግርማ ሠይፉ ማሩ
በ2005 ዓ.ም የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል፡፡ ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝ ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል፣ ለዚህ አዋጅ ድጋፍ መስጠት የፈለኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከበረሃ ይዘውት የመጡት ልዩ ልዩ አፋኝ ቡድን ስለማይኖራቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የነበሩትን አፋኝ ቡድንች ወደ አንድ መዋቅር በማጠቃለል ተጠሪነቱ ከተለያዩ መዋቅሮችና ግለሰቦች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (ወደ ተገቢው ማለት ነው) ቁጥጥር በማስገባት ለዜጎች ስጋት ሳይሆን ለዜጎች እና ለሀገር ደህንነት የሚስራ ተቋም ይሆናል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ይህ ተስፋዬም ዝም ብሎ ሳይሆን በአዋጁ አንቀፅ 3 “ይህ አዋጅ በመላው ሀገሪቱ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፌዴራልም ሆነ በክልል መንግስታት ደረጃ ሌላ የመረጃና ደህንነት ተቋም  ማቋቋም አይቻልም” የሚል ድንጋጌ በመያዙ ነው፡፡ በመስከረም 19 እሁድ ዕለት አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ “በሰላም” ከተጠናቀቀ በኋላ እጅግ አሰገራሚ የሆነ ተግባር አጋጥሞናል፡፡ ተስፋዬንም ስለአጨለመብኝ ይህን ጉዳይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያውቁትና የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎቱ ኃላፊውን ጠርተው ማብራሪያ እንዲጠይቁ መነሻ ለመስጠት ነው፡፡
የፓርቲያችን ወጣቶች በሰልፉ ላይ ወጣቶችን፣ ሙስሊሙን፤ ክርስቲያኑን፣ ሴቶችን እንዲሁም በግፍ የታሰሩትን ዜጎች በተመሳሌነት ለማሳየት እጃቸውን እና እግራቸውን በሰንሰለት አስረው ከፊት ሆነው ሰልፍ ላይ ሲታዩ ነበር፡፡ ማንነታቸው ያልታወቀ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከነዚህ ወጣቶች አንዱን ጎትተው ከታክሲ በማውረድ ወደ መኪና ውስጥ ለመጫና ሲሉ በአካባቢው የነበሩ የአንድነት ወጣቶች ደርሰው መውሰድ አትችሉም በሚል ግርግር ሲፈጠር በቦታው ደረስኩ፡፡ በቦታው ደርሼ ይህን የሚፈፅሙትን ሰዎች መታወቂያ እንዲያሳዩኝ ሰጠይቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በአካባቢው የነበሩትን ፖሊሶች (ባለ ኮከብ ማዕረግ ያለቸው ጭምር) አስጠርቼ መታወቂያ እንዲያሰዩን እንዲያደርጉ ቢሞከርም እነዚህን ጉልበተኞች መታወቂያ ሊጠይቅ የሚችል ሞራል ያለው ፖሊስ አጣን፤ ህዝብ በተሰበሰበበት ፖሊሶችን እንዴት እንደሚያደርጓቸው ማየት በእውነት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከፖሊሶቹ አንዱ ጠርቶኝ እነዚህ እኮ ከእኛ አቅም በላይ ናቸው ሲለኝ በቅርቡ በኢሳት ቴሌቪዥን ቀርቦ ምስክርነት የሰጠው የፖሊስ መኮንን ትዝ ብሎኝ የመንግስታችን ባሕሪ አሁንም ለውጥ እያሳየ ያለመሆኑ እና ፊት ለፊት ከምናያቸው ተቋሞች ጀርባ ሌላ ስልጣን እንዳለ ፍንትው ብሎ ታየኝ፡፡ የሚገርመው በዚያው ዕለት እኔን እያወቁኝ መኪናዬን በግዳጅ አሰቁመው መንጃ ፈቃድ፣ በሚያስገርም ሁኔታ የመኪና ባለቤትነት ደብተር፣ ሰለቦሎ ዕድሳት የማያገባቸውን ሁሉ እየጠየቁ ታዘን ነው በሚል ከገዢው ፓርቲ ጋር በመተባበር ስልፉ እንዳይሳካ  ሲሰሩ የነበሩ ፖሊሶች በሰዓታት ልዩነት መታዊቂያ ያለመጠየቅ ስልጣን ያላቸው ልዩ ዜጎች እንዳሉ አስገንዝበውናል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እነዚህን ሰዎች ማንነት ማወቅ ከፈለጉ ፎቶና ቪዲዮ በእጃችን እንደሚገኝ ላረጋግጥሎት እችላለሁ፡፡ ሲቪል የለበሱ አፋኞችን ሳይሆን ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶችንም ቢሆን መታወቂያ መጠየቅና ከወሮበላ ዱርዬ እራሳችን መጠበቅ መብታቸን እንደሆነ ግን ይታወቃል፡፡
በነገራችን ላይ ሰልፉ ከተጠናቀቀ በኋላ እነዚሁ ማፊያ ቡድኖች ፎቶ ይዘው ወጣቶችን በየመንገዱ እያስቆሙ እነዚህን ወጣቶች ማደን እንደያዙ ያረጋገጥን ሲሆን በዕለቱ ለደህንነታቸው ሲባል በአጀብ ወደ ቤታቸው ለማድረስ የቻልን ቢሆንም አሁንም እነዚህ ወጣቶች በምንም ዓይነት ሁኔታ ጉዳት ቢደርስባቸው ሌላ ምክንያት የሌለ እና ይህ የተደራጀ የማፊያ ቡድን የሚሰራው ስራ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ በማፊያዎቹ በመታደን ላይ ያሉት ወጣቶች ስንታየሁ ቸኮል፣ ዳንኤል ፈይሣ፣ ፋናዬ ወ/ጊዮርጊስ፣ ኤፍሬም ሰለሞን እንዲሁም አበበ ቁምላቸሁ የሚባሉ መሆናቸው እርሶም የዓለም ህብረተሰብም እንዲያውቀት መግለፅ ተገቢ መስሎ ታይቶኛል፡፡ በአደባባዩ ላይ ሲያሳዩ የነበረውም ምስል ይህንን ይመስላል፡፡ ወንጀላቸው ይህ ከሆነ ማለት ነው፡፡

የሰልፉ መሪዎቸ በተምሳሌታዊ አለባበስና ሁኔታ (ከስር ተቀምጠው የሚታዩት  ወጣቶች በደህንነት  ተብዬዎች የሚሳደዱት ናቸው

በሀገራችን የህግ ስርዓት እንዲሰፍን የምናደርገው ጥረት የሚሳካው እንደዚህ ዓይነት አፋኝ የማፊያ ቡድኖች በማሰማራት አይደለም፡፡ የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤትም እንዲህ ዓይነት የማፊያ ስራ እንዲስራ ኃላፊነት አልተሰጠውም፡፡ የተሰጡት ኃላፊነቶችና ተግባራት ከባድ በሀገር ላይ የተቃጡ ወንጀሎችን መከታተልና መረጃ መሰብሰብ ይህንንም በህግ አግባብ እንዲፈፅም ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በደርግ የመጀመሪያ ዘመን ተሰፋፍቶ የነበረውን በየቪላ ቤት እና በየመንደሩ አፍነው ወስደው ማሰቃየት በኢትዮጵያ ምድር እንዲቆም የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለቦዎት፡፡ ይህን ማድረግ የሚያስችል ስልጣን ከሌለዎት ለሰብዓዊ ክብር የሚስጠውን ክርስትና እምነት እየተከተሉ ይህንን ስልጣን መያዝ ትርጉም ስለሌለው ለእኛም ተሰፋ ስለማይሆኑን ስልጣን በመልቀቅ ሌላ ታሪክ መስራት ይችላሉ፡፡ ምርጫው የእርሶ ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሸንጉሊት ናቸው ከጀርባ የሚያሽከረክር ሌላ ኃይል አለ ለሚሉት ምስክርነት እየሰጡ ነው ብዬ ለመውሰድ እገደዳለሁ፡፡
ይህ በአዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ መዲና የደረሰውን መነሻ አድርጌ የፃፍኩት ቢሆንም በክልልም የፀጥት ክፍል የሚባል ማንነታቸው የማይታወቅ አሳሪዎች አሉ፡፡ የእነዚህን ልዩ የሚያደርገው እስረኛ በአደራ ፖሊስ ጣቢያ ስለሚያስቀምጡ ነው፡፡ ፖሊሶች በአደራ የገቡት መፍታትም ሆነ ፍርድ ቤት ማቅረብ አይችሉም፡፡ በክልል ለማስቃያ የሚሆን የቪላ ቤት እጥረት ስለአለ ሊሆን ይችላል፡፡ ከፖሊስ የበለጠ ስልጣን ግን እንዳላቸው በእርግጠኝነት እንዲያውቁት እፈልጋለሁ፡፡ አዋጁ በፍጥነት በስራ ላይ ውሎ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በአዋጁ የተሰጡትን ሀገራዊ ተግባር እንዲሰራ እንዲያደርጉ አደራ ጭምር እጠይቃለሁ፡፡
በዚህ አጋጣሚ የአንድነት ወጣቶች እነዚህን የማፊያ ቡድኖች በአደባባይ ህግን መሰረት አድርገው ሲያጋልጡዋቸው መመልከት ከምንም በላይ ኩራት የሚሰጥ መሆኑን መግልፅ ያስፈልጋል፡፡ አሁንም ቢሆን ሁላችንም በቃ ልንል ይገባል፡፡ ታክሲ ውስጥ ያለ ተሳፋሪ ሲቢል ለባሾች እንዲህ ሲያደርጉ ማንነታቸውን መጠየቅ መብቱ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ የደህንነት መስሪያ ቤቱ እነዚህን ቀሽሞች እንደ ሰውር ተከታታይ አሰማርቶ ከሆነ ከአሁን በኋላ እነሱ የሚስጥር ስራ ለመስራት ብቃት የሌላቸው መሆኑ ተገንዝቦ ለሆዳቸው መሙያ የሚሆን ሌላ ስራ እንዲፈልጉ ቢነግራቸው ጥሩ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን የምልበት ምክንያት በልጅነታችን የማሞ ውድነህን የስለላ መፅሐፍት ለአነበብን እንዲሁም አሁን ባለው ቴክኖሎጂ የስለላ ፊልም ለሚመለከቱ ወጣቶች የሚመጥን ስአአልሆነ ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የሚፈፅሙት ተግባር ተራ የዱርዬ ስራ ስለሆነ ነው፡፡ እኔ ለእንደዚህ ዓይነት ተቋም ላለኝ ክብር እንደዚህ ዓይነት ዱርዬዎች አይመጥኑትም፡፡ ይህ መስሪያ ቤት በእርግጥ የተጣለበትን ኃላፊነት የመወጣት ፍላጎት ካለው (ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግዴታ አለባቸው) መስሪያ ቤቱ በባለሞያ አንጂ በተራ ጆሮ ጠቢና የመንደር ወሬ ለቃሚ መሞላት የለበትም፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር 2006 ዓ.ም ተግባራዊ ስራ ለመስራት የሚችሉበት ዘመን እንዲሆን ምኞቴ ነው፡፡ በይፋም ባይሆን በልቦ እና በተግባር የግል አሻራዎን በዚህች ሀገር ላይ ለማኖር መልካም አጋጣሚ አግኝተዋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችለው ሀገራዊ መግባባት የሚፈጠርበትን እና የጠላትነት ሰሜት የሚወገድበትን ተግባር በመስራት ነው፡፡ መልካም አዲሰ ዓመት!!!!
ግርማ ሠይፉ ማሩ
zehabesha

“አንድ ሄክታር መሬት በ1 ፓኮ ሲጋራ ዋጋ መቸብቸብ ራዕይ ነው?” – የተስፋዬ ገ/አብ ቃለ ምልልስ


life magazine(ይህ ቃለመጠይቅ አዲስአበባ ላይ በየ15 ቀኑ ከሚታተመው “ላይፍ” መፅሄት ጋር የተደረገ ሲሆን፤ ቃለመጠይቁ የተካሄደው ከመፅሄቱ ጋዜጠኛ ጋር በፌስቡክ በኩል በተደረገ ግንኙነት በፅሁፍ ነው። መፅሄቱ ለአገር ውስጥ አንባብያን ቅዳሜ መስከረም 28 ገበያ ላይ የሚውል በመሆኑ ግልባጩ በዚህ መልኩ ቀርቦአል።)
• አዲሱ “የስደተኛው ማስታወሻ” መጽሐፍህ ከ“የደራሲው ማስታወሻ” እና ከ“የጋዜጠኛው ማስታወሻ” በምን ይለያል?
 “የስደተኛው ማስታወሻ” ከቀዳሚዎቹ ማስታወሻዎች የቀጠለ ነው። በዚህ ቅፅ በተመሳሳይ ገጠመኞቼን ነው ያሰፈርኩት። በርግጥ እንደ ሰንሰለት የተያያዙ የአውሮፓ የስደት ገጠመኞቼ ተተርከውበታል። ይህ ቅፅ የማስታወሻዎቼ መደምደሚያ ሲሆን፣ ከዚህ በሁዋላ ወደ ስነፅሁፍ ስራዎች ነው የምገባው።
• “የስደተኛው ማስታወሻ” አሳታሚ ማነው? መቼ ለገበያ ይቀርባል?
 “ነፃነት አሳታሚ” ይባላል። ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የኢትዮጵያውያን ንብረት የሆነ አሳታሚ ድርጅት ነው። ውል አድርገን መፅሃፉን አስረክቤያለሁ። የጀርባና የፊት ሽፋኑን ዲዛይን ሰርተው ልከውልኝ አፅድቄያለሁ። መፅሃፉ በህትመት ፕሮሰስ ላይ እንደሆነ መስከረም ወር መጀመሪያ ላይ ነግረውኛል። ጥቅምት ገበያ ላይ ይውል ይሆናል። በትክክል ቀኑን አላውቅም። መረጃዎቹን በድረገፃቸው በኩል ይፋ ያደርጉታል።
• አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ስራዎችህ የሁለት የተለያዩ ሰዎች ተጽዕኖ ውጤት ነው ይላሉ፡፡ ከአሰፋ ጫቦ ሽሙጥን፣ ከበዓሉ ግርማ ጀብደኝነትን። ምን ትላለህ?
 አሰፋ ጫቦ አሽሟጣጭ ነው ብዬ አላስብም። በአሉ ግርማም ጀብደኛ አይመስለኝም። ስለሁለቱ ብእረኞች በዚህ መንገድ ማሰብ ስህተት ነው። የአሰፋ ጫቦን ብዕር አደንቃለሁ። አሽሟጣጭ ሳይሆን እውነታዎችን በቀጥታና በግልፅ የሚናገር ደፋር ብእረኛ ነው። በአሉም የሰከነ ብዕር የነበረው ደራሲ ነው። ጀብደኛ ሊያሰኘው የሚችለው ስራው የቱ ነው? ምናልባት “ኦሮማይ”ን በማሰብ ከሆነ፣ በአሉ ግርማ በዚህ መፅሃፍ ምክንያት ሊገደል እንደሚችል ቢገምት ኖሮ ከዚያ የተሻለ ስራ ይሰራ ነበር። ወደ ጥያቄው ስመለስ የበአሉና የአሰፋ ጫቦ ተፅእኖ የለብኝም ለማለት አልችልም። ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ግን የወርቃማው ዘመን የሩስያ ደራስያን ብእረኞች ይበልጥ ቀልቤን ይስቡታል። እንደምገምተው ማስታወሻዎቼ ይበልጥ የቱርጌኔቭ የህይወት ታሪክ ማስታወሻዎች ተፅእኖ ሳይኖርባቸው አይቀርም። ወደ ትረካው ጥበብ ስንመጣ ስብሃት ገብረእግዚአብሄርና ጎርኪይ ምንግዜም አብረውኝ አሉ። ዞረም ቀረ አንድ የብዕር ሰው በጊዜ ሂደት በተለያዩ ፀሃፊዎች የአፃፃፍ ስልት ሊገነባ ይችላል።
• በአሁን ጊዜ ለአማርኛ ስነ ጽሑፍ ምን ያህል ቅርብ ነህ? ከታተሙት መፃህፍት መካከል የምታደንቀው አለ? ‘አብሬው በሰራሁ’ ስለምትለው ወይም በልዩ ሁኔታ ስለምታስታውሳቸው ደራስያን የምትገልፀው ካለም እድሉን ልስጥህ?
 ለአማርኛ ስነፅሁፍ ቅርብ ነኝ ለማለት አልችልም። የሚታተሙ መፃህፍትን እንደልቤ ለማግኘት ስለምቸገር ስለታተሙ መፃህፍት በልበ ሙሉነት አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ። በጥቅሉ ግን የአማርኛ ስነፅሁፍ አደጋ ላይ የወደቀ ሆኖ ይሰማኛል። አማርኛ በአዲሳባና በአማራ ክልል ቋንቋነት ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ብዙ ተሰርቶበታል። ይህ ሁኔታ የአማርኛ ስነፅሁፍን ክፉኛ ጎድቶታል። አማርኛ ቋንቋ ጠላት ስለበዛበት ስነፅሁፉም ባለቤት አጥቶአል። ይህ አሳዛኝ እውነት ነው።
ስለ ደራስያን ወይም ስለ ብዕር ሰዎች የጠየቅኸኝ ጥያቄ ስሜታዊ የሚያደርግ ነው። በልጅነቴ ሳመልካቸው የኖርኩት አንዳንዶቹ የብዕር አማልክት ዛሬ በህይወት የሉም። ከጥቂቶቹ ጋር ከመተዋወቅ በላይ አብሬያቸው ለመስራት በቅቻለሁ። የቅርብ ጓደኞቼ የሆኑም አሉ። ከስብሃት ገብረእግዚአብሄር ጋር አብሬ በመስራቴ በምንም ነገር የማይለካ ልምድ አጊንቼያለሁ። የአርትኦትን ጥበብ ከአረፈአይኔ ሃጎስ ተምሬያለሁ። እሸቱ ተፈራ ቤተመፃህፍት ማለት ነበር። ማሞ ውድነህ ወዳጄ ነበሩ። “እነዚህ አለቆችህ” እያሉ ወያኔን ያሙልኝ ነበር። አበራ ለማ ወጣቶችን በማገዝ ሱስ የተለከፈ ደራሲ ነበር። የሺጥላ ኮከብ ምርጥ ደራሲ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ነካ ያደርገዋል። የእፎይታ መፅሄትን አንደኛ አመት ስናከብር መጣና እንዲህ አለኝ፣
“አንድ የማይረባ መፅሄት አንድ አመት ስለሞላው ምንድነው ይህ ሁሉ ቸበርቻቻ?”
የሺጥላ ይህን ሲናገር ነጋሶ ጊዳዳ እና አለምሰገድ ገብረአምላክ በአካባቢው ነበሩ።
“ሞቅ ስላለህ ወደ ቤትህ ሂድ” አልኩት።
መአዛ ብሩና አበበ ባልቻ የልብ ወዳጆቼ ነበሩ። ሃይስኩል እያለሁ ከመአዛ ብሩ ድምፅና ሳቅ ጋር ፍቅር ይዞኝ ነበር። አሁንም አልተወኝም። የመአዛን ሳቅ ለመስማት ስል የሸገር ሬድዮ ቁራኛ ነኝ። ተፈሪ አለሙና ማንያዘዋል እንደሻውን አልረሳቸውም። የማንያዘዋል ወንድም ይሁን እንደሻው ራሱ አሪፍ ፀሃፊ ነው። ከሳህለስላሴ ብርሃነ ማርያም እና ከአያልነህ ሙላቱ ጋር ባለመስራቴ በጣም ይቆጨኛል። ከተሰደድኩ በሁዋላ ግን ለአያልነህ ደወልኩለት። የማክሲም ጎርኪይን የትውልድ ቦታ ኒዥኒይ ኖቭጎሮድን ለመጎብኘት ፈልጌ ስለነበር አስጎብኚ እንዲያዘጋጅልኝ ለመጠየቅ ነበር የደወልኩለት። ሃይለመለኮት መዋእል ከኔ ጀግኖች አንዱ ነው።
በፍቃዱ ሞረዳን አልወደውም። ምክንያቱም ከመሬት ተነስቶ ነገር እየፈለገ ያበሳጨኛል። ተወኝ ብለው ሊተወኝ አልቻለም። 2009 ላይ ጦርነት ገጥመን ነበር። በቅርቡ ግን አሪፍ ግጥም ፅፎ ሳነብ ያናደደኝ ሁሉ ብን ብሎ ስለጠፋ አድናቆቴን በፅሁፍ ገለጥኩለት።
ምነው አብሬያቸው በሰራሁ የምላቸው በርካታ ወጣት የብእር ጀግኖች አሉ። በእውቀቱ ስዩም፣ ኑረዲን ኢሳ፣ ሲሳይ አጌና፣ ኤፍሬም ስዩም፣ አዳም ረታ፣ ይስማእከ ወርቁ፣ ማረፊያ በቀለ…እንዲህ እያልኩ ትዝታዬን ከቀጠልኩ መቶ ገፅ አይበቃኝም። ጥያቄህን መልሼልህ ይሆን?
• ለአንድ ጀማሪ ደራሲ በአንተ አስተውሎት መጠንና ጉልበት እንዲጽፍ ምን ትመክረዋለህ?
 በርግጥ በአስተውሎትና በብርታት እየፃፍኩ መሆኔን ካመንክ አመሰግናለሁ። ተሰጥኦ ያለው ጀማሪ ደራሲ ጥሩ የሚባሉ መፃህፍትን በጥንቃቄ መርጦ በዝግታ ያነብ ዘንድ እመክረዋለሁ። ብዙ ማንበብ ብቻውን ጥሩ ደራሲ አያደርግም። መምረጥና በጥልቀት ማንበብ ይገባል። በጥልቀትና በዝግታ ማንበብ ሲባል ታሪኩን ብቻ አይደለም። ቃላት አመራረጥ፣ አረፍተነገር አሰካክ፣ የአገላለፅ ዘዴዎችን በጥንቃቄ መመርመር ማለት ነው። ሌላው ጉዳይ ጀማሪ ደራስያን ያልኖሩበትን ህይወት ለመፃፍ እንዳይሞክሩ እመክራለሁ። ልጅ ያልወለደ ሰው ስለ ልጅ ፍቅር ሊያውቅና ሊፅፍ አይችልም። ቢፅፍም የተሳካለት አይሆንም። ስለ ገበሬ መፃፍ ከፈለጉ ጥቂት ቀናትን ከገበሬዎች ጎጆ ማሳለፍ መቻል አለባቸው። ይህን ጉዳይ ቼኾቭ አጥብቆ መክሮ ነበር። ስሞክረው ልክ እንደሆነ አወቅሁ። “በብርታት መፃፍ” የሚለው መቸም አከራካሪ ነው። እኔ በብርታት እየሰራሁ ያለሁት (በርግጥ ከሆነ) ሙሉ ጊዜዬን በፅሁፍ ስራ ላይ ስላዋልኩ ሊሆን ይችላል። ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ሌላ ምንም ስራ ሳይሰሩ ፅሁፍ ላይ ብቻ የሚያተኩሩበት እድል ካገኙ በብርታት ብዙ ሊሰሩ ይችሉ ይሆናል። ኑሮውን ለመደጎም ሲል የማይወደው ስራ ላይ የሚባክን የብዕር ሰው የተሳካለት ስራ ለመስራት ይቸገር ይሆናል።
• ፖለቲካ ውስጥ ባይገባ ኖሮ “ስመጥር” ከሚባሉት ደራስያን መካከል አንዱ ይሆን ነበር ለሚሉት ምን ምላሽ አለህ?
 በአንድ ወቅት የኢህአዴግ አባል የሆንኩት ከፍላጎቴና ከእውቅናዬ ውጭ መሆኑን ተናግሬያለሁ። ከወያኔ ጋር በቆየሁበት ጊዜም ቢሆን ጋዜጠኛ ሆኜ ነው የሰራሁት። ከዚያ በሁዋላ ነፃ ሰው ነኝ። የማንም የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለሁም። “ፖለቲካ ውስጥ ባይገባ” የሚለው አባባል የተጋነነ ነው። የኛ ዘመን ሰው እንዴት ከፖለቲካ መራቅ ይችላል? እንራቅህ ቢሉትስ መች ይሆናል? እንደ ጭስ ቀዳዳ ፈልጎ መኝታ ቤታችን ድረስ ይገባል። በአጋጣሚ ፖለቲካ ውስጥ ስለገባሁ እንደ ጋዜጠኛ እና እንደ ደራሲ የፖለቲካ ገጠመኞቼን ፅፌያለሁ። ይህን በማድረጌ ስህተቱ ምን ላይ እንደሆነ ሊገባኝ አይችልም። እርግጥ ነው፣ አምርረው የሚጠሉኝ ወገኖች አሉ። ከፖለቲካ አመለካከታቸው ተነስተው ሊሆን ይችላል። የምሰራው ስራ ዋጋ ካለው ክብር ያገኛል ብዬ አስባለሁ። እኔ ማድረግ ያለብኝ ልቤን መከተል ብቻ ነው።
• “የስደተኛው ማስታወሻ” መጽሐፍህ ሃገር ውስጥ እንዲነበብ ምን ጥረት ታደርጋለህ?
 ለአዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር መልእክት ልኬ ነበር። ምላሽ አላገኘሁም። አንድ የኮክቴል ግብዣ ላይ በወሬ መካከል ስብሃት ነጋ፣ ለበረከት “ለምን አትተወውም? ያሳትም” ብሎት እንደነበር ሰምቻለሁ። በርግጥ ከዚህ አባባል ተነስቼ ችግሩ ያለው በረከት ስምኦን ጋር ብቻ ነው ለማለት አልችልም። በዚያም ሆነ በዚህ ግን ከመነበብ ሊያግዱት አይችሉም። ኮፒው በህገወጥ መንገድ ታትሞ መሰራጨቱ አይቀርም። የስርአት ለውጥ ሲደረግ ግን የታገዱትን መፃህፍት በድጋሚ አሳትማቸዋለሁ።
• ኢሕአፓዎች ይሔንንም መጽሐፍህ እንደማያባዙት ምን ዋስትና አለህ?
 መሞከራቸው አይቀርም። የሚያሰራጩባቸው ድረገፆችና የፊስቡክ ክፍሎች ስለሚታወቁ ህገወጡን ድርጊት ከፈፀሙ በህግ እንዲጠየቁ ጠበቆችን አዘጋጅተናል። በ’ርግጥ ኮፒ የማድረጉን ስራ የሚሰሩት የኢህአፓ ሰዎች ብቻ ናቸው ማለት አይቻልም። የምቀኝነት ህመም ያለባቸው አንዳንድ የአእምሮ በሽተኞችም ድርጊቱን ሊፈፅሙት ይችላሉ። በርግጠኛነት የምነግርህ ወያኔዎች ይህን ድርጊት እንደማይፈፅሙት ነው። የማይፈልጉትን መልእክት በማፈን እንጂ በማሰራጨት አይታወቁም። የኢህአፓ አመራር የኮሎኔል መንግስቱን መፅሃፍ ስካን አድርጎ ሲያሰራጭ መንግስቱ ሃይለማርያምን ገንዘብ ማሳጣት ነበር አላማቸው። የሚያስቅ ጅልነት ነው። መንግስቱ ገንዘብ አይፈልግም። ቀዳሚ አላማው መፅሃፉ እንዲነበብ ነው። ስለዚህ ኢህአፓ ማድረግ የነበረበት መፅሃፉን ገዝቶ ማቃጠል ነበር።
• ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ዕድሉ ያለ ይመስልሃል?
 የሕወሓት ስርአት ከወደቀ እመለሳለሁ።
• አዲስ አበባ ውስጥ የሚናፍቅህ የትኛው ቦታ ነው? ቁጭ ብለህ ቡና ወይም ቢራ ለመጠጣት የምትመርጠው ቦታስ?
 አዲስአበባ ብዙም አይናፍቀኝ። ይልቁን ደብረዘይት እና የስምጥ ሸለቆ ከተሞች ይናፍቁኛል።ጋራቦሩ ኮረብታ ላይ ቆሜ የረር ተራራን በሩቅ ማየት በጣም ይናፍቀኛል። ቢሾፍቱ ሃይቅ ዳርቻ ከሚገኙ መሸታ ቤቶች ተቀምጬ ማምሸት እፈልጋለሁ። የባቦጋያና የሆራ አርሰዲ ዳርቻዎች በህልሜ እንኳ ይታዩኛል። ድፍን አድአ፣ እስከ ጨፌ ዶንሳ፣ እስከ ሎሜ፣ ያደግሁበት አገር ነው። በቢሾፍቱ ገደሎች ደረት ላይ እንደ ወፍ በረናል። ጋራቦሩን ጋልበንበታል። በህይወት ዘመኔ አንድ ጊዜ ወደነዚህ የአድአ ገጠሮች መሄድ እፈልጋለሁ። ርግጥ ነው፣ የወያኔ ስርአት ሲወድቅ በሚቀጥለው አይሮፕላን ቦሌ ከሚያርፉት መንገደኞች አንዱ እኔ ነኝ። እና ሽው ወደ ቢሾፍቱ!
• በቡርቃ ዝምታ እና በቢሾፍቱ ቆሪጦች መጽሃፍትህ የተጸጸትክበት አጋጣሚ አለ? አሁንም ያለህ አቋም የመጽሐፍቱ ነጸብራቅ ነው?
 በመፃህፍቱ የምፀፀትበት ምክንያት የለም። ይህ ማለት ድክመት የለባቸውም ማለት አይደለም። በ20ዎቹ መጨረሻ እድሜ ላይ ሆኜ የፃፍኳቸው መፃህፍት እንደመሆናቸው ድክመት ሊኖርባቸው ይችላል። የህይወት ልምድ ማጣት፣ ሊንፀባረቅባቸው ይችላል። የቢሾፍቱ ቆሪጦች ከስነፅሁፍ አንፃር ሊተች የሚችል ነው። ድክመት አለበት። እንዲህ ያለ ነገር ሊያጋጥም ይችላል። በአሉ ግርማ “የቀይ ኮከብ ጥሪ” ተበላሽቶበታል። ጥሩ አልነበረም። ብርሃኑ ዘርይሁን በወጣትነቱ የፃፋቸውን፣ “ጨረቃ ስትወጣ” አይነቶቹን ተመልሰህ ብታነብ ብርሃኑ ነው የፃፋቸው ለማለት ትቸገራለህ። ስነፅሁፋዊ ክህሎት እያደገ ስለሚሄድ በገፀባህርያት ቀረፃ ላይ ድክመት ሊታይ ይችላል። የሃያስያን መኖር አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው። የቡርቃ ዝምታ መልእክቱ ላይ ችግር የለበትም። አሁንም የማምንበት ነው። የቡርቃ ዝምታን በመፃፌ እንደማልፀፀት ደጋግሜ ተናግሬያለሁ። የኦሮሞ ህዝብ ሰብእና ላይ የተፈፀመውን ግፍ የሚያሳዩ የጥበብ ስራዎች ወደፊትም መፃፍ አለባቸው። መሸፋፈን መፍትሄ አይሆንም። አብሮ ለመኖር ባለፈው ታሪክ ላይ መተማመን ይገባል። የቡርቃ ዝምታ የጭቆናውን ክብደት ለማሳየት የሞከረ መፅሃፍ ነው። የጭቆናውን ክብደት ማወቅ ተከባብሮ ለመኖር ያግዛል እንጅ የዘር ጦርነትን አይቀሰቅስም።
• ተስፋዬ ገብረአብ ጠቡ ከኢህአዴግ ጋር ሳይሆን ከኢትዮጵያ ነው የሚሉህ ሰዎች ለዚህ እንደ ማሳያ የሚያቀርቡት መጽሐፍህ በአማራ በትግሬ እና በኦሮሞ ህዝብ ቁርሾዎች ላይ ብቻ ያተኮሩ በመሆናቸው ነው ይላሉ? ምን ትላለህ?
 ስለ ዘር መነጋገር ወቅቱ ያመጣው አጀንዳ ነው። በየትኛውም የፖለቲካ ውይይቶች ላይ ቁርሾዎች የመወያያ አጀንዳ ሆነዋል። እኔ የጀመርኩት አይደለም። ክልላዊነትን ያስቀደመ የፖለቲካ ስርአት ነው ያለው። የማንነት ጥያቄ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖአል። አንድ የጥበብ ሰው የዘመኑን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጎ መፃፍ ግዴታው ነው። “በአማራና በኦሮሞ መካከል ፀብ ለመፍጠር” የሚል አባባል እሰማለሁ። ይህ አባባል ከቡርቃ ዝምታ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። የቡርቃ ዝምታ ታሪክ የኦሮሞ ህዝብ ስለ ራሱ ከሚያውቀው አንድ አራተኛውን እንኳ አልያዘም። ታሪኩን፣ አባባሎችን ቃላትን ያገኘሁት ከኦሮሞ ገበሬዎች እንጂ ከራሴ ፈጥሬው አይደለም። ያልተለመደ አቀራረብ ስለሆነ ሰዎች ሊሰጉ ይችላሉ። አዲሱ ወጣት ትውልድ መራራ ቢሆንም እንኳ እውነትን የመስማት ችሎታ አዳብሮአል። የሚደርሱኝ ደብዳቤዎች ይህን ጠቁመውኛል። በግልፅ በመነጋገር ችግሩ ይታወቃል። ችግሩ ከታወቀ ነው መፍትሄው የሚገኘው። በማድበስበስና በመሸፋፈን ግጭቶችን ማስቀረት አልተቻለም። ደርግም ሃይለስላሴም ሞክረውት አልተሳካም። ይልቁን ማፈን መፍትሄ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ሰጡ። የታመቀ ስሜት ቢፈነዳ ይመረጣል።ቢነገር ይሻላል። ሲተነፍስ መፍትሄውም አብሮ ይመጣል።
• ከዚህ በፊት በአንተ ብሎግ ላይ ያሰፈርካቸው “የልዑሉ እናት”፣ “የመነን 4ተኛ ባል” እና “የንጉሱ ሴት ልጅ” መጣጥፎች ያነበቡ ሰዎች የኢትዮጵያን ታሪክ ጥላሸት ለመቀባት ሆን ብለህ ያደረግከው ነው ለሚሉት ምን ትላለህ?
 በ’ርግጥ የመሪዎች ደካማ ጎኖች ላይ የመፃፍ ፍላጎት አለኝ። ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ በጎ እና ጠንካራ ጎናቸው ብቻ ነው ተደጋግሞ የሚፃፈው። መፃህፍት መሪዎችን በማሞገስ የተሞሉ ናቸው። ደካማ ጎናቸው በግልፅ ቢፃፍ አንባቢ ብዙ ትምህርት ያገኛል ብዬ አምናለሁ። በተለይ ደ’ሞ መሪዎች እንደ ማንኛውም ሰው ተራ ሰዎች መሆናቸውን ማሳየት እፈልጋለሁ። በአካባቢያችን መሪዎችን የማምለክ ዝንባሌ አለ። ከወረዳ አስተዳዳሪ ጀምሮ ለተቀመጡ መሪዎች መስገድ ባህል ሆኖአል። መነሻዬ ይህ እንጂ ሌላ አይደለም። እንደ ደራሲ ታሪኩ እውነት እስከሆነ ድረስ በማንኛውም ርስሰ ጉዳይ ላይ እንደፈለግሁ አገላብጬ የመፃፍ መብት አለኝ። ታሪክ ቀመስ ልቦለድ ልሰራባቸውም እችላለሁ። ያም ሆኖ ተፈሪ መኮንን ለመነን 4ኛ ባሏ የመሆኑ መረጃ ስለ ፖለቲካዊ ጋብቻ ግንዛቤ ይሰጣል እንጂ ንጉሱን አያዋርድም። ደጃዝማች ተፈሪ 4 ልጆች ያላት ወይዘሮ በማግባቱ አደንቀዋለሁ። “ልጃገረድ ካልሆነች አናገባም” ለሚሉ አክራሪዎች ጥሩ አርአያነት ነው። መንግስቱ ሃይለማርያም ውባንቺ ቢሻው የተባለች ሚስቱን ያገባው አስገድዶ በጠለፋ ነው። ከዚህ ምንም ትምህርት አይገኝም። አዜብ መስፍን ለመለስ ዜናዊ ሻይ እንድታፈላ በድርጅቱ የተመደበችለት ታጋይ ነበረች። በዚያው ጠቀለላት። ይሄ ጥሩ ነው። እንዲህ ያሉ ታሪኮችን የመፃፍ ፍላጎት አለኝ። እንዳልኩት በመሪዎች ትከሻ ላይ የተቆለለውን የመኮፈስ ካባ ገፍፌ መጣል እፈልጋለሁ። “የልዑሉ እናት” የሚለውን ታሪክ የፃፍኩት የጳውሎስ ኞኞን መፅሃፍ መሰረት አድርጌ ነው። “የመነን 4ኛ ባል” ዘውዴ ረታ ከፃፉት የተወሰደ ነው። እኔ ስፅፈው የተለየ የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው? እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች ልባቸው ውስጥ የሸሸጉትን የዘረኛነት በሽታ ያክሙት ዘንድ እመክራቸዋለሁ። ሰዎች ስለኔ የሚያስቡትን ግምት ውስጥ እያስገባሁ ልፅፍ አልችልም። በማንኛውም ርእሰ ጉዳይ ላይ በራሴው እይታ እንዳሻኝ እፅፋለሁ። አንባቢዎቼን ለማስደሰት ወይም ለማናደድ ብዬ አይደለም የምፅፈው። ቢታተምም ባይታተምም የኔ ችግር አይደለም። ኳስ መጫወት የሚወዱ ሰዎች ኳስ ይጫወታሉ። እኔም መፃፍ ስለምወድ እፅፋለሁ። ሽማግሌው ቱርጌኔቭ እንደሚለው በጎ ከሰራን፣ ስራችንም ዋጋ ካለው፣ ያን ዋጋ ህዝብ ማስተዋል ከቻለ ለስራችን ክብር ይሰጠናል።
• በብዙ ጽሁፎችህ ለኦሮሞ መብት ጥብቅና የመቆም ዝንባሌ ታሳያለህ፡፡ ነጋሶ እንዳሉት ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ነኝ ማለትን ታበዛለህ ለሚባለው ምላሽህ ምንድን ነው?
 የነጋሶን አባባል ሰምቼዋለሁ። More catholic than the Pope የሚለውን አባባል ገልብጠው ሊጠቀሙበት ነው የሞከሩት። ነጋሶ ጭንቅላታቸውን ተናግረው አያውቁም። ሌሎችን ለማስደሰት በማሰብ የመናገር ልማድ አዳብረዋል። ነጋሶ አሁን የአንድነት ሊቀመንበር ናቸው። አራተኛ ድርጅታቸው መሆኑ ነው። ከኦነግ ወደ ወያኔ፣ ከወያኔ ወደ አንድነት ሲዘሉ ምንም አልተደናቀፉም። መርህ ያለው ሰው እንዲህ በቀላሉ ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ መዝለል አይቻለውም። ጨለንቆ ላይ ጉድጓድ አስቆፍረው አፅም እየሰበሰቡ “ነፍጠኛውን” ያወግዙ እንዳልነበር፣ አኖሌ ላይ ስለ “ጡት መቆረጥ” ታሪክ ሲያስተምሩ እንዳልነበር አሁን 180 ዲግሪ ተገልብጠው የራስ ጎበና ዳጪ ተከታይ ሆነዋል። እድሜ ከሰጣቸው የነገውን አናውቅም። በተቀረ ለኦሮሞ ህዝብ ጥብቅና መቆም ሃጢአት አይደለም። ሃጢአት ሊሆን የሚችለው ከተገፋና ካመፀ ህዝብ ጎን አለመቆም ነው። ለኦሮሞ ህዝብ መቆም ሲባል ሌላውን ህዝብ ማጥቃት ማለት አይደለም። ጥያቄው የክብርና የእውቅና ማግኘት ጥያቄ ነው። የኦሮሞን የሞጋሳ ባህል የሚያውቅ በነጋሶ አባባል በጣም ይገረማል። ያም ሆኖ እኔ በኦሮሞ ህዝብ መካከል ተወልጄ ያደግሁ፤ ራሴን ኦሮሞ ብዬ ለመጥራት የሞራል ብቃት ያለኝ ሰው ነኝ። ልጅ እያለን የኢብሳ ኦሮሞ የጠበል ጠላ ስንቀምስ፣ Ijollee warra Bishoftu ነበር ፉከራችን! በእነዚያ የልጅነት ዘመናት ጋራቦሩ ላይ እርጎ ጠጥተን ስናበቃ ከአህያ እስከ ፈረስ እየጋለብን ነው ያደግነው። ይህ ፖለቲካ አይደለም። ህይወት ነው። ማንነት የተገነባበት ንጥረነገር ነው።
• በጹህፎቸህ ውስጥ የበቀል ስሜት የለህም ወይ? ጹህፎችህ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ የሚያደርግ ገንቢ ሃሳብ ምንም ቦታ ላይ የለም ትባላለህ። ለምን?
 በግልባጩ የኔ ፅሁፎች ለአንድነት የቆሙ ናቸው። ችግሮችን በግልፅ አውጥቶ መፃፍ ለመፍትሄ ፈላጊዎች ግማሹን ስራ እንደሰራሁላቸው ነው የሚቆጠረው። በቀል የሚለው ቃል እኔን አይገልፀኝም። በግል የበደለኝ ሰው ወይም ህዝብ የለም። ለበቀል የሚያበቃ የማስታውሰው ጉዳት አልደረሰብኝም። በቀል ቀርቶ በጥላቻ የማስታውሰው ሰው እንኳ የለም። በቀል የሚኖረው ቂምና ጥላቻ ሲኖር ነው። በኔ ልብ ውስጥ ለቂምና ለጥላቻ ቦታ የለም…
• ከኢትዮጵያና ኤርትራ ስሜትህ ለየትኛው ቅርብ ነው?
 ኢትዮጵያ የትውልድ አገሬ ናት። በደም ኤርትራዊ ነኝ። ማንነት የብዙ ግብአቶች ውጤት እንደመሆኑ ለሁለቱም አገራት ስሜት አለኝ። ቋንቋ፣ ባህል፣ አስተዳደግ፣ ወላጆች እነዚህ ሁሉ ማንነትን የሚገነቡ ግብአቶች ናቸው። ጥያቄው ስለ ዜግነት ከሆነ ሆላንድ የዜግነት አገሬ ሆናለች። በቀሪው የህይወት ዘመን በዚሁ የዜግነት ሰነድ መንቀሳቀስ እችላለሁ።
• ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደፊት የመዋሃድ ዕድል ይኖራቸው ይሆን?
 ተመልሰው የሚዋሃዱ ቢሆኑ ኖሮ 30 አመት ትግል አይደረግም ነበር። በሰላሳ አመታቱ ጦርነት ከሁለቱም ወገን በአስር ሺዎች ተሰውተዋል። እንደገና በድንበር ጦርነት በተመሳሳይ የብዙ ሺዎች ህይወት ተቀጥፎአል። ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ስለ አንድነትና ውህደት መነጋገር የሚቻል አይመስለኝም። ከመነሻውም የኤርትራ ጥያቄ የነፃነት ጥያቄ ነበር። ስለዚህ ሁለቱ አገራት ተከባብረው እንደ ጎረቤት በሰላም መኖር ከቻሉ እንኳ ትልቅ ድል ነው። እንደ አውሮፓውያን ድንበራቸውን አፍርሰው፣ የንግድ ህግ ደንግገው በሰላም መኖር ከቻሉ ትልቅ ስኬት ይሆናል። ሁለቱ አገራት የየራሳቸው ፀጋ አላቸው። ከመዋሃድ ባላነሰ ተግባራዊ ሊሆን በሚችል መልኩ በትብብር መስራት ይችላሉ። ኤርትራና ኢትዮጵያን በተመለከተ የኔ ምኞትና ፍላጎት በአዲሱ መፅሃፌ ላይ በግልፅ ተቀምጦአል። በአፍሪቃ ቀንድ ደረጃ በጋራ ለመስራት ከወዲሁ ጥርጊያ መንገዱን ቢያነጥፉ የአካባቢው 140 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል። የአፍሪቃ ቀንድ ህዝቦች ከጦርነት የሚገኘውን ኪሳራ ከማንም በላይ ይገነዘቡታል። ስለዚህ ሰላማዊ አካባቢ ለመፍጠር በቁርጠኛነት መተባበር ብቻ ነው የሚያዋጣቸው።
• “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” የተባለው መጽሐፍህ ግነት እንደነበረበት ተናግረህ ነበር። በአሁኖቹ መጽሃፍት በሆነ ወቅት ‘ግነት ነበራቸው’ ላለማለትህ ምን ዋስትና አለ? ለሚሉ አስተያቶች ምላሽህ ምንድነው?
 “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” በነፃነት የተሰራ ስራ አልነበረም። መፅሃፉ የኔው ፕሮጀክት ቢሆንም በመካከሉ ድርጅታዊ ጣልቃ ገብነት መጣ። ሁዋላ ከፕሮጀክቱ ራሴን ያገለልኩት በትእዛዝ መፃፍ ስላልፈለግሁ ነው። በግሌ በሰራሁዋቸው ስራዎች ላይ ስለ ግነትም ሆነ ስለ መፀፀት ተናግሬ አላውቅም።
• እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከመፃፍህ አንጻር ስለ ኤርትራ ምንም አለመጻፍህ ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው። ለምን?
 ገና ፅፌ መቼ አበቃሁ? የመሞቻዬ ጊዜም ገና አልደረሰም። የ45 አመት ሰው ነኝ። የመፃፊያ ጊዜዬ ገና መጀመሩ ነው። እነዚህ ማስታወሻዎች ወደ ስነፅሁፍ ስራ ለመግባት እንደመንደርደሪያ የተጠቀምኩባቸው ብቻ ናቸው። ከእንግዲህ ቢያንስ በየአመቱ አንድ መፅሃፍ ለማሳተም እቅድ አለኝ። በፕሮግራሜ መሰረት መቼ፣ ስለማን፣ ምን መፃፍ እንዳለብኝ መወሰን ያለብኝ እኔ ነኝ። ከዚህ ቀደም፣ “ስለ እዚህ ጉዳይ ለምን አልፃፍክም?” ተብሎ የተጠየቀ ደራሲ ያለ አይመስለኝም። ስለፃፍኩት እንጂ ስላልፃፍኩት ጉዳይ ልንነጋገር አይገባም። የሚገርመው “ለምን አልፃፍክም?” ተብዬ የምወቀሰው ስለማላውቀው ጉዳይ ነው። የምሰራው መፅሃፍ እንጂ ዜና አይደለም። በርግጥ ይህን ክስ የሚያራግቡት ወያኔዎች መሆናቸውን አውቃለሁ። ያቀረብኩትን መረጃ ማስተባበል ስላልቻሉ በዚህ ፕሮፓጋንዳ ከአንባቢ ሊነጥሉኝ ይሞክራሉ። ያም ሆኖ ባለፉት አመታት ወደ ኤርትራ የተጓዝኩ እንደመሆኑ የኤርትራ ጉዞዬን በአዲሱ መፅሃፌ ተርኬዋለሁ። ጀምሬያለሁ። እቀጥላለሁ…
• መለስ ራዕይ ነበራቸው በሚባለው ጉዳይ ብዙዎች ጥርጣሬ አላቸው። አንተስ? በቅርቡ በታተመ መጣጥፍህ፣ “መለስ ተመልሰው ቢመጡ አባይ ፀሐዬን እስር ቤት ያስገባው ነበር” ያልክበት ምክንያት ምንድነው?
 የመለስ ራእይ የሚባለውን የፕሮፓጋንዳ መፈክር መለስ ሲሞት በተደናበረ ሁኔታ የፈጠሩት ነው። መለስ ሲሞት እንደ ኢህአዴግ ማእከል ሆኖ ሊያሰባስባቸው የሚችል አይዲዮሎጂ አልነበራቸውም። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምን እንደሆነ ማንም ሳያውቀው አርጅቶ ሞቶ ነበርና አደጋ ላይ ወደቁ። “ምንድነው የመለስ ራእይ?” ብለህ ብትጠይቅ አንዳንዱ የዋህ ካድሬ፣ “የአባይ ግድብ”፣ “የባቡር ፕሮጀክት” ምናምን ይልሃል። የአባይ ግድብ ጥናት በጃንሆይ ዘመን የተጠና ነው። አቅም እና ምቹ ጊዜ እየተጠበቀ ነበር። ግብፅ ስትዳከም ምቹ ጊዜ ሆኖ ተገኘ። የባቡሩ ፕሮጅክት የሃይሉ ሻውል እቅድ ነው። ቅንጅት በ2005 ምርጫ ስልጣኑን ቢይዝ ሊፈፅመው ያቀደው ነው። ወያኔ ከአፍ እየቀለበ የመንጠቅ ልዩ ችሎታ አለው። “የመለስ ራእይ” የሚባል ነገር የለም። አሁን እንኳ ሽኩቻ ውስጥ ስለገቡ የራእዩ ከበሮ ረገብ ብሎአል። በመለስ ራእይ ስም መለስ የዘረጋውን መዋቅር በመበጣጠስ ላይ የሚገኘው አባይ ፀሃዬ ነው። አንዱ ጠንክሮ እስኪወጣ ድረስ ሽኩቻቸው ይቀጥላል።
• በመለስ ራእይ ስም መለስ የዘረጋውን መዋቅር በመጣጠስ ላይ የሚገኘው ዓባይ ፀሃዬ ነው ያልክበት ምክንያት ምንድነው?
 የሽኩቻው ድራማ ዋና አክተር አባይ ፀሃዬ ነው። በአፋቸው “የመለስ ራእይ” ይላሉ። በተጨባጭ ግን የመለስ ታማኞችን እየመነጠሩ ነው። መለስ ይዞት የነበረውን ብቸኛ አምባገነናዊ ሃይል ለመቆጣጠር እየሰራ ነው። ርግጥ ነው፣ አባይ ፀሃዬ በሚፈፅመው ድርጊት ተቃውሞ የለኝም። ለአገር ደህንነት ሲል አለመሆኑ ግን መታወቅ አለበት። አጤ ምኒልክ ሲሞቱ በደጃዝማች ተፈሪ እና በልጅ ኢያሱ መካከል የተፈጠረውን የስልጣን ሽኩቻ የሚያስታውስ ሁኔታ ላይ ነን። አባይ ወልዱ እንደ ወራሽ ልጅ እያሱ – አባይ ፀሃዬ እንደ ደጃዝማች ተፈሪ! በትክክል ተመሳሳይ የታሪክ ጊዜ ላይ ነን።
• እንደምታውቀው ኢሕአዴጎች “እዚህ ያለነው የመለስን ራዕይ ከግብ ለማድረስ ነው” ብለው ውሳኔ ላይ ደርሰው መንቀሳቀስ ከጀመሩ ዓመት አልፏቸዋል:: አንተ ደግሞ “የመለስ ራእይ” የሚባል ነገር የለም ብለሃልና ብታብራራው?
 መለስ ለመሞት አንድ ሳምንት ሲቀረው ነው ባለራእይ የሆነው? ምንድነው የሚያወሩት እነኚ ሰዎች? 20 አመታት ከመለስ አመራር የተገኘው ምንነበር? በዘር ከፋፍለው ህዝቡ እንዳይተማመን አደረጉት። ያልነበረበትን የሃይማኖት ግጭት ስር እንዲተክል ጥረት አደረጉ። በሰላም አስከባሪ ስም የዜጎችን ህይወት ቸበቸቡ። የምርጫ ኮሮጆ በመገልበጥ ህዝቡ በዴሞክራሲ ላይ ያለውን እምነት አሳጡት። ምንድነው የመለስ ራእይ የሚባለው ቀልድ? ጄኔራሎችን ከህወሃት ብቻ መሾም ራእይ ነው? ቡና ሲወቀጥ ግድግዳቸው የሚሰነጠቅ የኮንደሚንየም ቤቶችን መገንባት ራእይ ነው? ገበሬዎችን አፈናቅለህ ስታበቃ አንድ ሄክታር መሬት በአንድ ፓኮ ስጋራ ዋጋ መቸብቸብ ራእይ ነው? አንድ ፍሬ እህቶቻችንን ለአረብ ግርድና አሳልፎ መስጠት ነው ራእይ? በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙ፣ ኦልባና ሌሊሳ ለምን ታሰሩ? በመከላከያ ስም ሸቀጥ ያለቀረጥ በማስገባት የአገር ውስጥ ነጋዴዎችን መግደል ራእይ ነው? ምንድነው የመለስ ራእይ? ውሸትን በመደጋገም እውነት የማስመሰልን ጥበብ ተክነውበታል።
• በዚህ ወቅት ሕወኃት ለሁለት ተከፍሏል በሚባለው ትስማማለህ? ከሆነስ እነማን በአሸናፊነት የሚወጡ ይመስልሃል?
 በሁለቱ አባዮች (አባይ ፀሃዬ እና አባይ ወልዱ) መካከል ጦርነት መኖሩን እየሰማን ነው። መረጃው ግን የተረጋገጠ ነው ለማለት አልደፍርም። የምንሰማው እውነት ከሆነ ከመቀሌው አባይ በስተጀርባ ቴዎድሮስ ሃጎስ አለ። ከአዲሳባው አባይ ስር እነ ጌታቸው አሰፋ፣ እነ ደብረፅዮን መሰለፋቸው ይሰማል። ሳሞራ የአዲሳባውን አባይ ተቀላቅሎአል። አዜብ ‘አርፈሽ ቁጭ በይ! የመለስን ፋውንዴሽን ተከታተይ’ ተብላለች። እብድ ስለሆነች ያልተጠበቀ ነገር እንዳትፈፅም በመስጋት ሰንሰለቷን ሁሉ በጣጥሰውባታል። የዘረፋ ቀዳዳዎቿን እየዘጉባት ነው። ያም ሆኖ አዜብ አርፋ ትቀመጣለች ተብሎ አይታመንም። መሞከሯ አይቀርም። የግል አስተያየቴን ለመስጠት ያህል፣ የመቀሌ – አዲሳባ ሽኩቻ ይፋ ሳይወጣ ውስጥ ውስጡን ሊጠናቀቅ ይችላል። ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ሽጉጥ ከተኮሱ ቤተመንግስቷን ለዘልአለሙ እንደሚያጧት ያውቃሉና ሽጉጥ ወደ መምዘዝ የሚገቡ አይመስለኝም። ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛው እስኪያሸንፍ ሃይለማርያም ወንበሩን በታማኝነት ይጠብቅላቸዋል። ማን በአሸናፊነት ሊወጣ እንደሚችል አብረን እናየዋለን። የአዲሳባው ቡድን የሚበረታ ይመስለኛል። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሁለቱም ቡድኖች ገለልተኛ ሆኖ የአስታራቂነት ሚና ለመጫወት እሞከረ ነው። ምናልባት እሱን በማንገስ ልዩነታቸውን ይፈቱ ይሆናል።
• ሕወኃት በምርጫ ስልጣን የሚለቅ ይመስልሃል?
 በግልፅ ተናግረዋል። “ጀርባችንን በእሳት ሰንሰለት እያስገረፍን ያገኘነውን ወንበር በምርጫ ካርድ ስም ሳምሶናይት ይዘው ለመጡ ሰዎች አናስረክብም” ብለዋል። በርግጥ የምኒልክን ወንበር በምርጫ አላገኙትም። ስለዚህ በምርጫ መልቀቅ አይፈልጉም። በምርጫ እንደማይለቁትም በ2005 ምርጫ አስመስክረዋል። በተመሳሳይ በ2010 ማንኛውንም አይነት የማጭበርበር ዘዴ በሙሉ ሃይላቸው ስለተጠቀሙበት 99.6 በመቶ በማሸነፍ ወንበሮቹን ሁሉ ያዙ። በምርጫ በኩል ይገኛል የተባለውን የዴሞክራሲ ጭላንጭልም ደፈኑት። ከዚህ በሁዋላ ምንድነው የሚጠበቀው?
• የሕወኃት በኃይል ስልጣን ላይ የመቆየት አባዜ የሚያዛልቅ ይመስልሃል?
 አዛልቆአቸው 22 አመት ሆኖአቸዋል። ሌላ 22 አመታት እንደማይገዙ ምንም ዋስትና የለም። ወያኔና ሻእቢያ በጠመንጃ ባይመጡበት ደርግ እስከዛሬ ስልጣን ላይ ሊቆይ ይችል ነበር። ሙጋቤ አሁንም አለ። ጋዳፊ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ነበረ። ስዩም መስፍን ቻይና የሚማሩትን የህወሃት የአመራር አባላት ልጆች እያሰለጠነ ነው። በቻይና መንግስት ድጋፍ ተተኪ የአገሪቱ መሪዎች ሊያደርጓቸው ይፈልጋሉ። ይህ ተረት አይደለም። እስከቻሉት ድረስ ይሞክራሉ። ከአንዳንዶቹ ጋር እንዲህ በስልክ ስናወራ “ከዚህ በሁዋላ 40 አመታት መቆየት እንችላለን” ብለው በቀልድ መልክ ጣል ያደርጋሉ። እየቀለዱ ግን አይደለም። “የ65ሺህ ጓዶቻችንን ህይወት የከፈልነው ዋጋው ውድ ነው” ይላሉ። በጨዋታ መሃል ከምኒልክ እስከ ሃይለስላሴ የነበረውን ዘመን ያሰሉታል። የንጉስ ሳህለስላሴ የልጅ ልጆች የቤተሰብ ጥል እየተጣሉም ቢሆን ስልጣን ከቤተሰባቸው ሳይወጣ እየተተካኩ ቆይተዋል። ህወሃት በተመሳሳይ መንገድ ልዩነት የፈጠሩትን እያስወገደ ሁለት ወይም ሶስት ትውልድ ከዚያም በላይ ለመግዛት ይችላል አይነት ወጎች አሏቸው። በአደባባይ ደግሞ፣ “እኛ በስልጣን መቀጠል ካልቻልን ኢትዮጵያ ትበታተናለች” ብለው መዛታቸውን ቀጥለዋል። ኢትዮጵያ እንዳትበታተን በመስጋት ህዝቡ ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ይመኛሉ።
• ሕወኃትን ለ22 ዓመታት በስልጣን እንዲቆይ ያስቻለው ምንድነው ትላለህ?
 ምስጢሩ ህዝቡን ከፋፍሎ መግዛት በመቻሉ ነው። የፌደራል አገዛዝ ስርአቱን ለስልጣን ማራዘሚያ ተጠቅሞበታል። ክርስትያኑን በሙስሊሙ ያስፈራራዋል። የአማራው ሃይል ሲበረታ በኦሮሞው እየመታ ዘልቆአል። ሌላ ምስጢር የለውም። ከፋፍሎ በመግዛት፣ የኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ ስሜትን በማዳከም፣ ከተቻለ ጨርሶ በማጥፋት ዝንተ አለም መግዛት እንደሚችሉ አስልተው ጨርሰዋል። በርግጥ 95 በመቶ የመከላከያን አመራር ተቆጣጥረውታል። ደህንነቱ ሙሉ በሙሉ በእጃቸው ነው። ህዝቡ በዘር ተከፋፍሎአል። ለሃያላኑ አገራት ራሳቸውን በአገልጋይነት ስላቀረቡ በጫና ፈንታ እርዳታ እያገኙ ነው። የዚህ ሁሉ ድምር በስልጣን እንዲቆዩ አግዞአቸዋል።
• አሁን ያሉት ብዙዎቹ የሕወኃት ባለስልጣናት በአባት ወይም በእናት ኤርትራውያን ናቸው ይባላል:: የተባለው ትክክል ከሆነ ውሳኔዎቻቸው የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ ሊሆን አይችልም? ከዚሁ ጋር ተያይዞ የእነኚሁ ባለስልጣናት አያቶች ወይም ቅድመ አያቶች የጣሊያን ባለሟሎች የነበሩ ናቸው ስለሚባለው ምን መረጃ አለህ? የባንዳ ልጆች መሆናቸው የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ አይከታቸውም ?
 በአባት ወይም በእናት ኤርትራዊ መሆን የዘመናችን ዋና አጀንዳ መሆኑ ያሳዝነኛል። በረከት ስምኦን በእናቱም ሆነ በአባቱ ኤርትራዊ ነው። ለኤርትራ የፈፀመላት በጎ ነገር አለመኖሩን ግን አረጋግጥልሃለሁ። በረከት በኤርትራውያን ዘንድ እንደ ፖለቲከኛ እንኳ አይታይም። በኢትዮጵያውያንም አይታመንም። እድለኛ አይደለም። ይህ ሊሆን የቻለው በረከት የሚሰራው ለግሉ፣ ለዝናው፣ ለስልጣን ስለሆነ ነው። ግማሽ የኤርትራ ደም ያላቸው የህወሃት አመራር አባላት ለኤርትራ ያደላሉ ብዬ አስቤ አላውቅም። የተወለዱት እና ያደጉት ትግራይ ነው። ለትግራይ ነው የሚሰሩት። አንድን ሰው “ግማሽ ኤርትራዊ ነው” ብለን ከማሰባችን በፊት “ግማሽ ኢትዮጵያዊ ነው” የሚለውን ማስቀደም ለምን አልተቻለም? በአሉ ግርማ እኮ በአባቱ ህንዳዊ ነው። ገብሩ አስራት ግማሽ ጎጃሜ ነው። ጆሴፍ ስታሊን ሩስያዊ አልነበረም። ኦባማ በአባቱ ኬንያዊ ነው። ጥላሁን ግዛው የፊውዳል ቤተሰብ ነበር።ለኢትዮጵያዊነት ህይወታቸውን የከፈሉ ኤርትራውያንን ስም እንጥራ ብንል ሰአታት አይበቃንም። መለስ በአባቱ ኢትዮጵያዊ ነው። ለምንድነው ወደ እናቱ ጎሳ ያዘነብላል ተብሎ የሚታሰበው? ተወልዶ ያደገው ትግራይ ነው። መለስ ኢትዮጵያን ለመምራት ግማሽ ኢትዮጵያዊነቱ ከበቂ በላይ ነበር። እንደሚመስለኝ ችግሩ ግማሽ ኤርትራውያን መሆናቸው ሳይሆን መርህ አልባ፣ ወይም ስልጣናቸውን ብቻ የሚያስቀድሙ በመሆናቸው ሊሆን ይችላል። መለስ ዜናዊ የባንዳ ልጅ ስለመሆኑ ሲነገር የሰማሁት ከገብረመድህን አርአያ ነው። ገብረመድህን ስለሚያጋንን አይመቸኝም። የሆነው ሆኖ መለስ የባንዳ ልጅ ሊሆን ይችላል። የባንዳ ልጅ መሆኑ ግን እሱንም ባንዳ አያደርገውም። የመለስን ወላጆች እና ልጆች እንተዋቸው። መለስን ለመውቀስ የሚያበቃ በአገር ላይ የፈፀመው በርካታ ወንጀል አለ።
• መለስ ዜናዊ “የኤርትራ ህዝብ ከየት ወዴት“ የሚለውን መጽሐፍ መጻፋቸው፣ ኤርትራ ራስዋን ችላ ነፃ ሐገር ሆና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና እንድታገኝ ለዋና ጸሐፊው ቡትሮስ ጋሊ ደብዳቤ መጻፋቸው፣ ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብ ይገባኛል እንዳትል እንቅፋት መፍጠራቸውና ለኤርትራ ይገባል ማለታቸው ግማሽ ኤርትራዊ ባይሆኑ ኖሮ የሚሞክሩት ተግባር ነበር?
ኤርትራን በተመለከተ በተወሰኑ ውሳኔዎች የኤርትራ ደም የሌለባቸውም ተሳትፈው አብረው ወስነዋል። የፖለቲካ አቋማቸውን ነው ያስፈፀሙት። ትግራይ ከኢትዮጵያ ጋር ስለመቀጠሏ እንኳ ሁለት ልብ ስለነበሩ የኤርትራን ነፃነት የማይቀበሉበት ሁኔታ ላይ አልነበሩም። ከዚያም ባሻገር አቋማቸውን ለመለወጥ ቢያስቡ ኖሮ እንኳ በወቅቱ ምንም ማድረግ አይችሉም ነበር። ተዋጊ የገበሬ ሰራዊትና ፖለቲካ የሚያንበለብሉ ሸምዳጅ ካድሬዎች እንጂ ሌላ አቅም አልነበራቸውም። አዲሳባን እንዴት እንደሚያስተዳድሩ አሳቡ እንኳ አልነበራቸውም። በርግጥ መለስ ዜናዊ ኤርትራን በተመለከተ ስሜቱ ስስ መሆኑ ብዙ የተባለበት ነው። ስለ መለስ የልብ ሚዛን የሚያውቀው ራሱ መለስ ብቻ ነበር። ሳይፅፈው ተሰናብቶአል።
• መለስና ጓደኞቻቸው ሽንጣቸውን ገትረው ለኤርትራ ነፃነት ሲዋጉ የነበሩት ለምን ይመስልሃል?
እኔ እስከማውቀው ለኤርትራ ነፃነት የተዋጉት ኤርትራውያን ናቸው። መለስና ጓደኞቹ የራሳቸው አጀንዳና አላማ ነበራቸው። በቀይ ኮከብ ዘመቻ ወቅት ለስልጠና ኤርትራ ሄደው መስዋእትነት እንደገጠማቸው ሰምቻለሁ። የሻእቢያ ተዋጊዎችም በተመሳሳይ ህወሃትን በማገዝ ሂደት ውጊያ ላይ መስዋእትነትን ከፍለዋል። ይህ የጋራ ጠላትን ለመመከት ከተደረገ ታክቲካዊ ትብብር ያለፈ ስም ሊሰጠው አይችልም። የህወሃት እገዛ አንዳንድ ፀሃፊዎች አጋንነው እንደሚያቀርቡት አይመስለኝም።
• በኢትዮጵያ ባለጠመንጃ አስተዳዳሪ መሆኑ የሚቀርበት ጊዜ የሚመጣ ይመስልሃል?
ተስፋ አደርጋለሁ።
• የሕወኃትን በኃይል ከስልጣኑ እናባርረዋለን የሚሉት ተቃዋሚዎች ሚሳካላቸው ይመስልሃል?
 ህዝቡ የወያኔን ስርአት ተንኮል ጠንቅቆ ተረድቶ አማፅያኑን በሙሉ አይኑ ማየትና ማመን ከጀመረ የሚሳካላቸው ይመስለኛል። በርግጥ እኔ በግሌ ጠመንጃ እንዲተኮስ አልፈልግም። ወጣቶች በጦርነት እንዲሞቱ አልመኝም። እኔ ራሴ የጦርነት ትራፊ በመሆኔ ህመሙ ይሰማኛል። ጠመንጃ ከማንሳት ባሻገር አማራጭ መጥፋቱ ግን ያሳዝነኛል። 

zehabesha

“ኢህአዴግ፤ የምትቃወሙትንም እኔ ነኝ የምሰጣችሁ እንዳይለን” - ተቃዋሚዎች

        “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ ---- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ---- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ።
ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!) ምን እንደምል ታውቃላችሁ? “የእኔን እድል ይስጣችሁ” (እርግማን እኮ አይደለም!) “እንደእኔ ፕሬዚዳንት ሆናችሁ እዩት” ለማለት ነው። ልክ ነዋ! ኢህአዴግ በፕሬዚዳንትነት የሾመው ሰው ያለው ሥልጣንና ሃላፊነት የቱ ድረስ እንደሆነ ሳያውቁ እኮ ነው ተመቸን ብለው የሚናገሩት። ኢህአዴግ የሾመው ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ ተዓምር እንዲሰራ መጠበቅ “ፌር” አይደለም። (በኢህአዴግ ደግሞ ትግል እንጂ “ተዓምር” መስራት አይፈቀድም!) ከፓርቲው አፈንግጦ ተዓምር ለመስራት የሚወራጭ ካለም የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዓይነት እጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ከቤተመንግስት ወጥቶ ጣራው የሚያፈስ የኪራይ ቤቶች ቤት ውስጥ ይገባል።
ይሄም ታዲያ እጁን ከፖለቲካ ሰብስቦ ከተቀመጠ ብቻ ነው። ነጋሶ ግን እጃቸውን ሰብስበው አልተቀመጡም። በግላቸው በምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ ፓርላማ ገቡ። ራሴ ባረቀቅሁት ህገመንግስት ውስጥ የሰፈረውን ፖለቲካዊ መብቴን ከማስወስድ የሚያፈስ ቤታችሁን ውሰዱልኝ አሉ። (“የነጋሶ መንገድ” በሚለው መፅሃፋቸው እንደነገሩን) በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ “ውጤታማ አልነበሩም” የሚለውን የተቃዋሚዎች ትችት እየተቃወምኩም ሆነ እየደገፍኩኝ አይደለም። (“አይቻልም ወይ መኖር የማንም ሳይሆኑ” ያለችው ድምፃዊት ማን ነበረች?) እኔ ግን ጥያቄ አለኝ - በፕሬዚዳንቱ ላይ በተሰነዘሩት አስተያየቶች ዙሪያ። ፕሬዚዳንቱ ይሄን ሁሉ ዘመን ኖረው ኖረው ከቤተመንግስት ሊወጡ አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው “ውጤታማ ነበሩ? አልነበሩም?” የሚለውን የጦፈ ሙግት ምን አመጣው? ምናልባት ኢህአዴግ አዲስ ለሚሾመው ፕሬዚዳንት ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ለተሰናባቹ እኮ የሚተርፋቸው ፀፀት ብቻ ነው። (The damage is already done! አለ ፈረንጅ) እውነቱን ለመናገር--- ተቃዋሚዎች ስለፕሬዚዳንቱ የሰጡት አስተያየት የድሮ ተረት ከማስታወስ ያለፈ ፋይዳ አለው ብዬ አላስብም (“ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” አሉ) የሚገርመው ደግሞ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መሃል ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ወይም ስኬትና ውድቀታቸው ብሎ ከፋፍሎ ለማየት አንድ እንኳን የሞከረ የለም። ተቃዋሚዎቹ “የማርያም ጠላት” ያደረጓቸውን ያህል በፓርላማ የኢህአዴግ ደጋፊና ብቸኛው የግል ተመራጭ ዶ/ር አሸብርም እንከን የሌለባቸው ፍፁም ፕሬዚዳንት አድርገው ነው ያቀረቧቸው። (“ወልደህ ሳትጨርስ---”የሚለው ተረት ትዝ ብሏቸው ይሆን?) የፕሬዚዳንት ግርማ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ እንኳን የቱንም ያህል መላዕክ ቢያደርጓቸው አይፈረድባቸውም (ሥራቸው ነዋ!) እኔ ተቃዋሚዎችን ብሆን ግን ትችቴን አንድም ኢህአዴግ ላይ አሊያም የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን በገደበው ህገመንግስቱ ላይ ነበር የማነጣጥረው።
(“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” አሉ!) እኔ የምለው ግን--- ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በፕሬዚዳንት ግርማ ላይ የወረደውን የትችት ውርጅብኝ ሰምቶ ይሆን? ከሩጫ በኋላ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት አለኝ ስላለ እኮ ነው! (ፍላጎት ነው ምኞት?) በኋላ ከሚቆጨኝ ለአትሌታችን ምክር ቢጤ ጣል ባደርግለት ደስ ይለኛል። ለፖለቲካ ዲሲፕሊንና ልምምድ ብቻ በቂ አይደሉም። (ሩጫና ፖለቲካ ለየቅል ናቸው!) እንግዲህ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፉት 12 ዓመታት ሰሩም ተባለ አልሰሩ በቅርቡ ከሥልጣናቸው ይሰናበታሉ። ከወር በፊት ይመስለኛል--- ፕሬዚዳንቱ ከ“ሚት ኢቲቪ” አዘጋጅ ተፈራ ገዳሙ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ሲመረጡ የፍርሃት ስሜት አድሮባቸው እንደሆነ ጠይቋቸው፣ በመጀመርያው ጊዜ እንጂ በሁለተኛው ምንም ዓይነት ፍርሃት እንዳልተሰማቸው ገልፀው፣ለሦስተኛ ዙር በፕሬዚዳንትነት መቀጠል አለመቻሉ ትንሽ እንደሚያናድድ ተናግረዋል - በቀልድ መልክ። (ከአንጀታቸውም ሊሆን ይችላል!) ግን አያችሁልኝ--- የኢህአዴግን ምስጢር ወዳድነት። እስካሁን እኮ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ እንኳ አልሰጠንም። (ኢህአዴግ “ሰርፕራይዝ” ማድረግም ነፍሱ ነው አሉ!) እናላችሁ--- ችግር የለም፤ ቀኑ ሲደርስ አዲሱን ፕሬዚዳንት በፓርላማ አቅርቦ ሰርፕራይዝ ይለናል - እንደ ልደት ስጦታ (ስጦታውስ ለኛ ሳይሆን ለተሿሚው ነው!) ባለፈው ሳምንት “ታጋይ ደከመኝ አይልም እንጂ ኢህአዴግ ድክም ብሎታል” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ፅሁፍ ያነበቡ አንድ ደንበኛ ስልክ ደውለው እንዴት እንደወቀሱኝ አልነግራችሁም። ወቀሳው ምን መሰላችሁ? “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ነው። በመቆርቆር ግን አይመስልም፤ “23 ዓመት አንቀጥቅጦ ገዝቶን እንዴት 21 ዓመት ብቻ ትላለህ? ሁለቱን የት ደብቀህለት ነው?” ነበር ያሉኝ።
እኔ እንኳን መደበቄ አልነበረም። ሁለቷ ዓመት የልምምድ ጊዜ ናት ብዬ ነበር የተውኳት (ለካስ ሂሳብ ማወራረድ ተጀምሯል!) እኔ ግን 30 እና 40 ዓመት የመግዛት ራዕይ ላለው ፓርቲ ገና ወገቡ ላይ ሆነን ሂሳብ መተሳሰብ ፋይዳው አልታየኝም። ባይሆን 30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ የሥልጣን ዘመኑን መቆጣጠር እንጀምራለን፤ አሁንማ ምን ተነካና። በነገራችሁ ላይ --- ኢህአዴግ የሥራ ብዛትና ጫና ስላደከመው ከመውደቁ በፊት የአንድ ዓመት እረፍት ይውሰድ በሚል ያቀረብኩትን ሃሳብ አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት ክፉኛ እንደተቃወሙትና እንዳወገዙት ሰምቻለሁ - “ታጋይ አይደክመውም” በማለት። ከዚህ ሃሳቤ የማልታቀብ ከሆነም በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት እንደዛቱብኝ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ ብለውኛል። ከሁሉም የገረመኝ ግን ምን መሰላችሁ? አንዳንድ የኢህአዴግ ካድሬዎች በእኔ ላይ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ገና ካሁኑ መፈክሮች ማዘጋጀት መጀመራቸው ነው። (የሰልፍ ፈቃድ ሳያገኙ?) እስቲ ከመፈክሮቹ ጥቂቶቹን እንያቸው - “ኢህአዴግ ደክሞታል በሚል ማደናገርያ ሥልጣን በአቋራጭ መያዝ የህልም እንጀራ ነው!” “ሥልጣን ለኢህአዴግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” “ኢህአዴግ አረፍ እንዲል የሚፈልጉት የኒዮሊበራል ተላላኪዎች ናቸው!” እኔ ግን እንደነሱ አይደለሁም።
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ቀንደኛ አቀንቃኝ ስለሆንኩ በዛቻውም ሆነ በመፈክሮቻቸው ቅያሜ አላደረብኝም። እንደውም ያለውዝግብ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ካገኙ ከእነሱ ጋር ሰልፍ ለመውጣት ሁሉ አስቤአለሁ - ተቃውሞው በእኔ ላይ ቢሆንም። ከገዢ ፓርቲ ጋር ተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚፈጥር ማወቅ እፈልጋለሁ (ለጠቅላላ እውቀት እኮ ነው!) በዚያ ላይ ተቃዋሚዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚጠሩት በእያንዳንዱ ሰልፍ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍልና ከፖሊስ ጋር የሚጋቡትን እልህና ውዝግብ ሰበብ ለማወቅ እፈልጋለሁ። ኢህአዴግስ ተመሳሳይ ውዝግብና እልህ ውስጥ ይገባል ወይስ ነገሩ አልጋ በአልጋ ይሆንለታል? (የባለቤቱ ልጅ መሆኑ እኮ አልጠፋኝም!) ይሄን ሁሉ የመፈተሽና የማጥናት ፍላጎት አለኝ። ስፖንሰር ተደርጌ እኮ አይደለም። (የሃገሬ ጉዳይ አያገባኝም እንዴ?) ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ቦታው በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንደሆነና “ለልማት ነው ቅድምያ የምንሰጠው” የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልጿል።
በዚሁ ሰበብ ፖሊስ ከቢሮው ንብረቶች እንደወሰደበት እንዲሁም እሁድ እለት ሰልፉን ሊያካሂዱ ሲሉ መንገድ በመዝጋት ሰልፉን እንዳቋረጠባቸው ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። አንድነት ፓርቲም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ሌላ አማራጭ ቦታዎች አቅርብ ከተባለ በኋላ ያቀረበው ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰልፉን ጃንሜዳ አድርግ እንደተባለ አስታውቋል። በዚሁ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መውጣቱን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን ቦታና ጊዜ የሚወስነው መስተዳድሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ “አሁን የቀራቸው የምትቃወሙትንም የምንሰጣችሁ እኛ ነን” ማለት ብቻ ነው ሲሉ ክፉኛ አሽሟጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አዲስ ወጣ በተባለው መመሪያ ተናዶ ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? “እንደዚያ ከሆነማ ለምን ሰልፍ የሚወጣውንም ህዝብ እነሱ አይመድቡልንም?” በአሁኑ ጊዜ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎች ሰልፍ በጣም አስፈርቶታል የሚለው ይሄው የተቃዋሚ ደጋፊ፤ “በመኪና ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ለመበተን፣ ወዘተ--- ለሁሉ ነገር አስፈቅዱኝ እያለ ነው፣ ለምን መፈክሮቹንም እሱ አያዘጋጅልንም” በማለት አዲስ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለገዢው ፓርቲ አበርክቶለታል። “እናም ኢህአዴግ በቅርቡ “ሰላማዊ ሰልፍ እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ አጀንዳዎችን እንቀርፃለን፣ ለሰልፍ የሚወጣ ህዝብ እንመለምላለን፣ በራሪ ወረቀቶችን እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እናደርጋለን ወዘተ-- የሚል ልዩ ማስታወቂያ በኢቴቪ ሲያስተላልፍ ልንሰማ እንችላለን” ብሏል - የተቃዋሚ ደጋፊው። (ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!)

addis addmas

ሠላማዊ ሰልፍና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ


በኢትዮጵያ ኅብረ-ብሔራዊና በብሔር ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ፓርቲዎች ካለፉት 22 ዓመታት አንስቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ፓርቲዎች ሕገመንግሥቱን አክብረው በሠላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ በሕገመንግሥቱ ተቀምጧል። ሆኖም ከ1997ቱ ምርጫ ወዲህ በሠላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ማነቆዎች እንደበዙባቸው በተደጋጋሚ ሲገልፁ ይደመጣል።
ለአብነት ያህል ፓርቲዎች የተለያዩ ሕዝባዊ ስብሰባዎችንና የተቃውሞ ሠልፎችን ስንጠራ ያጋጥሙናል ያሉትን ችግሮች እንደማነቆ ያነሳሉ። የዛሬው የውይይት መድረክ ዝግጅታችንም ርዕስ «ሠላማዊ ሰልፍ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ» ይሰኛል። ለውይይቱ ሶስት እንግዶችን ጋብዘናል። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው። አቶ ዳንኤል ተፈራ፤ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ። እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃ/ማርያም የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብቶች ጉባኤ የቀድሞ የምርመራ ሠራተኛ፤ በአሁኑ ወቅት በቤልጂየም ብራስልስ የሕግ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የሠብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው። አቶ ያሬድ። እንግዶቻችን ለውይይቱ ፈቃደኞች በመሆናችሁ በአድማጮች ስም ከልብ አመሠግናለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ አድማጮች ለውይይቱ የያዝነው ጊዜና ቦታ ስለማይፈቅድልን በርካታ ፓርቲዎችን ማሳተፍ አልቻልንም። ሁለቱን ፓርቲዎች ስንጋብዝም ያለምንም መስፈርት እንደሆነ ከወዲሁ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋልን። ከመንግሥት በኩል በስብሰባ እና በተለያዩ ምክንያቶች ለውይይቱ የሚሳተፍ ሰው ማግኘት አልቻልንም።
ሙሉ ውይይቱን ከታኝ የሚገኘውን የድምፅ መጫወቻ በመጫን ያዳምጡ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ

dw.de

ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!!!

 MinilikSalsawiBlogspot.com

       “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ ---- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ---- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ።



ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!) ምን እንደምል ታውቃላችሁ? “የእኔን እድል ይስጣችሁ” (እርግማን እኮ አይደለም!) “እንደእኔ ፕሬዚዳንት ሆናችሁ እዩት” ለማለት ነው። ልክ ነዋ! ኢህአዴግ በፕሬዚዳንትነት የሾመው ሰው ያለው ሥልጣንና ሃላፊነት የቱ ድረስ እንደሆነ ሳያውቁ እኮ ነው ተመቸን ብለው የሚናገሩት። ኢህአዴግ የሾመው ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ ተዓምር እንዲሰራ መጠበቅ “ፌር” አይደለም። (በኢህአዴግ ደግሞ ትግል እንጂ “ተዓምር” መስራት አይፈቀድም!) ከፓርቲው አፈንግጦ ተዓምር ለመስራት የሚወራጭ ካለም የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዓይነት እጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ከቤተመንግስት ወጥቶ ጣራው የሚያፈስ የኪራይ ቤቶች ቤት ውስጥ ይገባል።
ይሄም ታዲያ እጁን ከፖለቲካ ሰብስቦ ከተቀመጠ ብቻ ነው። ነጋሶ ግን እጃቸውን ሰብስበው አልተቀመጡም። በግላቸው በምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ ፓርላማ ገቡ። ራሴ ባረቀቅሁት ህገመንግስት ውስጥ የሰፈረውን ፖለቲካዊ መብቴን ከማስወስድ የሚያፈስ ቤታችሁን ውሰዱልኝ አሉ። (“የነጋሶ መንገድ” በሚለው መፅሃፋቸው እንደነገሩን) በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ “ውጤታማ አልነበሩም” የሚለውን የተቃዋሚዎች ትችት እየተቃወምኩም ሆነ እየደገፍኩኝ አይደለም። (“አይቻልም ወይ መኖር የማንም ሳይሆኑ” ያለችው ድምፃዊት ማን ነበረች?) እኔ ግን ጥያቄ አለኝ - በፕሬዚዳንቱ ላይ በተሰነዘሩት አስተያየቶች ዙሪያ። ፕሬዚዳንቱ ይሄን ሁሉ ዘመን ኖረው ኖረው ከቤተመንግስት ሊወጡ አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው “ውጤታማ ነበሩ? አልነበሩም?” የሚለውን የጦፈ ሙግት ምን አመጣው? ምናልባት ኢህአዴግ አዲስ ለሚሾመው ፕሬዚዳንት ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ለተሰናባቹ እኮ የሚተርፋቸው ፀፀት ብቻ ነው። (The damage is already done! አለ ፈረንጅ) እውነቱን ለመናገር--- ተቃዋሚዎች ስለፕሬዚዳንቱ የሰጡት አስተያየት የድሮ ተረት ከማስታወስ ያለፈ ፋይዳ አለው ብዬ አላስብም (“ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” አሉ) የሚገርመው ደግሞ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መሃል ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ወይም ስኬትና ውድቀታቸው ብሎ ከፋፍሎ ለማየት አንድ እንኳን የሞከረ የለም። ተቃዋሚዎቹ “የማርያም ጠላት” ያደረጓቸውን ያህል በፓርላማ የኢህአዴግ ደጋፊና ብቸኛው የግል ተመራጭ ዶ/ር አሸብርም እንከን የሌለባቸው ፍፁም ፕሬዚዳንት አድርገው ነው ያቀረቧቸው። (“ወልደህ ሳትጨርስ---”የሚለው ተረት ትዝ ብሏቸው ይሆን?) የፕሬዚዳንት ግርማ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ እንኳን የቱንም ያህል መላዕክ ቢያደርጓቸው አይፈረድባቸውም (ሥራቸው ነዋ!) እኔ ተቃዋሚዎችን ብሆን ግን ትችቴን አንድም ኢህአዴግ ላይ አሊያም የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን በገደበው ህገመንግስቱ ላይ ነበር የማነጣጥረው።
(“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” አሉ!) እኔ የምለው ግን--- ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በፕሬዚዳንት ግርማ ላይ የወረደውን የትችት ውርጅብኝ ሰምቶ ይሆን? ከሩጫ በኋላ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት አለኝ ስላለ እኮ ነው! (ፍላጎት ነው ምኞት?) በኋላ ከሚቆጨኝ ለአትሌታችን ምክር ቢጤ ጣል ባደርግለት ደስ ይለኛል። ለፖለቲካ ዲሲፕሊንና ልምምድ ብቻ በቂ አይደሉም። (ሩጫና ፖለቲካ ለየቅል ናቸው!) እንግዲህ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፉት 12 ዓመታት ሰሩም ተባለ አልሰሩ በቅርቡ ከሥልጣናቸው ይሰናበታሉ። ከወር በፊት ይመስለኛል--- ፕሬዚዳንቱ ከ“ሚት ኢቲቪ” አዘጋጅ ተፈራ ገዳሙ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ሲመረጡ የፍርሃት ስሜት አድሮባቸው እንደሆነ ጠይቋቸው፣ በመጀመርያው ጊዜ እንጂ በሁለተኛው ምንም ዓይነት ፍርሃት እንዳልተሰማቸው ገልፀው፣ለሦስተኛ ዙር በፕሬዚዳንትነት መቀጠል አለመቻሉ ትንሽ እንደሚያናድድ ተናግረዋል - በቀልድ መልክ። (ከአንጀታቸውም ሊሆን ይችላል!) ግን አያችሁልኝ--- የኢህአዴግን ምስጢር ወዳድነት። እስካሁን እኮ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ እንኳ አልሰጠንም። (ኢህአዴግ “ሰርፕራይዝ” ማድረግም ነፍሱ ነው አሉ!) እናላችሁ--- ችግር የለም፤ ቀኑ ሲደርስ አዲሱን ፕሬዚዳንት በፓርላማ አቅርቦ ሰርፕራይዝ ይለናል - እንደ ልደት ስጦታ (ስጦታውስ ለኛ ሳይሆን ለተሿሚው ነው!) ባለፈው ሳምንት “ታጋይ ደከመኝ አይልም እንጂ ኢህአዴግ ድክም ብሎታል” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ፅሁፍ ያነበቡ አንድ ደንበኛ ስልክ ደውለው እንዴት እንደወቀሱኝ አልነግራችሁም። ወቀሳው ምን መሰላችሁ? “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ነው። በመቆርቆር ግን አይመስልም፤ “23 ዓመት አንቀጥቅጦ ገዝቶን እንዴት 21 ዓመት ብቻ ትላለህ? ሁለቱን የት ደብቀህለት ነው?” ነበር ያሉኝ።
እኔ እንኳን መደበቄ አልነበረም። ሁለቷ ዓመት የልምምድ ጊዜ ናት ብዬ ነበር የተውኳት (ለካስ ሂሳብ ማወራረድ ተጀምሯል!) እኔ ግን 30 እና 40 ዓመት የመግዛት ራዕይ ላለው ፓርቲ ገና ወገቡ ላይ ሆነን ሂሳብ መተሳሰብ ፋይዳው አልታየኝም። ባይሆን 30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ የሥልጣን ዘመኑን መቆጣጠር እንጀምራለን፤ አሁንማ ምን ተነካና። በነገራችሁ ላይ --- ኢህአዴግ የሥራ ብዛትና ጫና ስላደከመው ከመውደቁ በፊት የአንድ ዓመት እረፍት ይውሰድ በሚል ያቀረብኩትን ሃሳብ አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት ክፉኛ እንደተቃወሙትና እንዳወገዙት ሰምቻለሁ - “ታጋይ አይደክመውም” በማለት። ከዚህ ሃሳቤ የማልታቀብ ከሆነም በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት እንደዛቱብኝ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ ብለውኛል። ከሁሉም የገረመኝ ግን ምን መሰላችሁ? አንዳንድ የኢህአዴግ ካድሬዎች በእኔ ላይ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ገና ካሁኑ መፈክሮች ማዘጋጀት መጀመራቸው ነው። (የሰልፍ ፈቃድ ሳያገኙ?) እስቲ ከመፈክሮቹ ጥቂቶቹን እንያቸው - “ኢህአዴግ ደክሞታል በሚል ማደናገርያ ሥልጣን በአቋራጭ መያዝ የህልም እንጀራ ነው!” “ሥልጣን ለኢህአዴግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” “ኢህአዴግ አረፍ እንዲል የሚፈልጉት የኒዮሊበራል ተላላኪዎች ናቸው!” እኔ ግን እንደነሱ አይደለሁም።
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ቀንደኛ አቀንቃኝ ስለሆንኩ በዛቻውም ሆነ በመፈክሮቻቸው ቅያሜ አላደረብኝም። እንደውም ያለውዝግብ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ካገኙ ከእነሱ ጋር ሰልፍ ለመውጣት ሁሉ አስቤአለሁ - ተቃውሞው በእኔ ላይ ቢሆንም። ከገዢ ፓርቲ ጋር ተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚፈጥር ማወቅ እፈልጋለሁ (ለጠቅላላ እውቀት እኮ ነው!) በዚያ ላይ ተቃዋሚዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚጠሩት በእያንዳንዱ ሰልፍ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍልና ከፖሊስ ጋር የሚጋቡትን እልህና ውዝግብ ሰበብ ለማወቅ እፈልጋለሁ። ኢህአዴግስ ተመሳሳይ ውዝግብና እልህ ውስጥ ይገባል ወይስ ነገሩ አልጋ በአልጋ ይሆንለታል? (የባለቤቱ ልጅ መሆኑ እኮ አልጠፋኝም!) ይሄን ሁሉ የመፈተሽና የማጥናት ፍላጎት አለኝ። ስፖንሰር ተደርጌ እኮ አይደለም። (የሃገሬ ጉዳይ አያገባኝም እንዴ?) ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ቦታው በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንደሆነና “ለልማት ነው ቅድምያ የምንሰጠው” የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልጿል።
በዚሁ ሰበብ ፖሊስ ከቢሮው ንብረቶች እንደወሰደበት እንዲሁም እሁድ እለት ሰልፉን ሊያካሂዱ ሲሉ መንገድ በመዝጋት ሰልፉን እንዳቋረጠባቸው ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። አንድነት ፓርቲም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ሌላ አማራጭ ቦታዎች አቅርብ ከተባለ በኋላ ያቀረበው ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰልፉን ጃንሜዳ አድርግ እንደተባለ አስታውቋል። በዚሁ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መውጣቱን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን ቦታና ጊዜ የሚወስነው መስተዳድሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ “አሁን የቀራቸው የምትቃወሙትንም የምንሰጣችሁ እኛ ነን” ማለት ብቻ ነው ሲሉ ክፉኛ አሽሟጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አዲስ ወጣ በተባለው መመሪያ ተናዶ ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? “እንደዚያ ከሆነማ ለምን ሰልፍ የሚወጣውንም ህዝብ እነሱ አይመድቡልንም?” በአሁኑ ጊዜ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎች ሰልፍ በጣም አስፈርቶታል የሚለው ይሄው የተቃዋሚ ደጋፊ፤ “በመኪና ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ለመበተን፣ ወዘተ--- ለሁሉ ነገር አስፈቅዱኝ እያለ ነው፣ ለምን መፈክሮቹንም እሱ አያዘጋጅልንም” በማለት አዲስ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለገዢው ፓርቲ አበርክቶለታል። “እናም ኢህአዴግ በቅርቡ “ሰላማዊ ሰልፍ እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ አጀንዳዎችን እንቀርፃለን፣ ለሰልፍ የሚወጣ ህዝብ እንመለምላለን፣ በራሪ ወረቀቶችን እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እናደርጋለን ወዘተ-- የሚል ልዩ ማስታወቂያ በኢቴቪ ሲያስተላልፍ ልንሰማ እንችላለን” ብሏል - የተቃዋሚ ደጋፊው። (ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!)        
 MinilikSalsawiBlogspot.com

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ (ተመስገን ደሳለኝ)


ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
እንደ መግቢያ
ድንገቴው የመለስ ህልፈት ህወሓትን ቢከፍለውም፣ ብአዴን ራሱን እንዲያጠናክር መደላድል ፈጥሮለታል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት መለስ ዘመኑን ሙሉ በብአዴን ታማኝነት ላይ ጥርጣሬ ስላልነበረው ቀድሞውንም እንዲዳከም ባለማድረጉ ይመስለኛል፡፡ እርሱ በአይነ ቁራኛ ይጠብቀው የነበረው ህወሓትን ነበር፤ በተለይም በሠራዊቱ እና በደህንነቱ ውስጥ ‹‹ተፅእኖ መፍጠር ይችላሉ›› የሚባሉት አቦይ ስብሃት ነጋ እና የትግራይን መዋቅር በእጁ ያደረገው የቀድሞ የክልሉ አስተዳዳሪ ፀጋዬ በርሄ በጥርጣሬ ዓይን የሚታዩ ሆነው ቆይተዋል፡፡ በምርጫ 2002ቱ ማግስትም ድርጅቱ አቦይን ‹‹በክብር›› እንዲሸኝ ሲደረግ፣ ፀጋዬ በርሄን ደግሞ ‹‹አማካሪ›› በሚል ሽፋን ከመቀሌ ወደ ቤተ-መንግስት (ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ) አዛውሮ በቅርብ እይታ ስር በማዋሉ ሁለቱንም ከጨዋታ ውጪ አድርጓቸዋል፡፡ በግልባጩ አዜብ መስፍንና ‹የመለስ ታማኞች› የሚባሉት እነአባይ ወልዱና ቴዎድሮስ ሀጎስ የፖሊት ቢሮውን ተቀላቅለዋል፡፡ ሁነቱም ከእነአቦይ ጋር በስጋ ዝምድናና በጋብቻ የተሳሰሩ ባለስልጣናትን በማስከፋቱ በድርጅቱ ውስጥ ብቻ የሚታወቅ (አደባባይ ያልወጣ) ልዩነት ፈጥሮ እንደነበረ ይታወሳል (በነገራችን ላይ ኦህዴድ የማዳከሙ ሴራ ሰለባ ነው፡፡ ይህ ሁናቴ ከመለስ ህልፈትም በኋላ ቀጥሏል፤ ለምሳሌ ባለፈው ዓመት የግንባሩ አባል ድርጅቶች፣ የየራሳቸውን ጠቅላላ ጉባኤ ባካሄዱበት ወቅት ብአዴን በ‹ክብር› ካሰናበተው ሁለት ዓመት ያለፈውን መሪውን አዲሱ ለገሰን ወደ ቦታው መልሶ ራሱን ሲያጠናክር፣ በተቃራኒው ኦህዴድ አንጋፋ አመራሮቹን፡- አባዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳና ግርማ ብሩን ከስራ አስፈፃሚነታቸው እንዲያነሳ ተገድዷል፡፡ ይህንን ነው መተካካት የሚሉትም፡፡
ህወሓት
የመለስን ህልፈት ተከትሎ በውስጡ ያደፈጠው ቅራኔ ፈንቅሎ በመውጣቱ ህወሓትን የ‹መቀሌው› እና የ‹አዲስ አበባው› በሚል ለሁለት ከፍሎት ነበር፤ ይህ ግን የመቀሌው-በአዲስ አበባ፤ የአዲስ አበባው-በመቀሌ ደጋፊ አልነበረውም እንደማለት አይደለም (የመቀሌውን አዜብ መስፍን፣ አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሀጎስ… መርተውታል፤ የአዲስ አበባውን ደግሞ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃዬ፣ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ ታጋዮች ዘውረውታል)፡፡ ይህ አጋጣሚም ከእነ አዜብ ቡድን ጋር ትብብር የፈጠረውን ብአዴንን ለጊዜያዊ ድል አብቅቶት ነበር (በ93ቱ ክፍፍልም የብአዴን ድጋፍ መለስ በአሸናፊነት እንዲወጣ ጉልህ ድርሻ ማበርከቱ ይታወሳል)፡፡ አቦይ ስብሃት ነጋ በትግርኛ ቋንቋ በሚታተመው ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ ‹‹ህዝቢ ትግራይ ዘቃልሶ ኣቃሊሱ ዝጠቕሞ ወያናይ ውድብ ይግብኦ›› (የትግራይ ህዝብ የሚያታግለው፣ ታግሎም የሚጠቅመው ወያኔያዊ ድርጅት ይገባዋል) በሚል ርዕስ በፃፉት ፅሁፍ ችግሩን እንዲህ ሲሉ ገልፀውታል፡-
‹‹አባይ ወልዱም ባለፈው የህወሓት ጉባኤ ላይ በተደጋጋሚ ‹ህወሓት ውስጥ ማጠለሻሸትና (የሥልጣን) ሽኩቻ በስፋት እየተስተዋለ ነው› በማለት ሁኔታውን ገልፆታል፡፡ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ ደግሞ የለም፡፡ እንዲህ ያለ በኃይል አሰላለፍ ደረጃ ሊታይ የሚችል የአንድን የፖለቲካ ድርጅት አቅም ከማዳከምና መርሀ-ግብሩን ከማሰናከል አልፎ ተርፎም ድርጅቱን ለአስከፊ ውድቀት ሊጥል ከሚችል አደገኛ ሁኔታ የበለጠ አደጋ ያለ አይመስለኝም፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሐሴ 2005 ዓ.ም)
ከኃይለማርያም ጀርባ
ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንባሩ ሊቀ-መንበር በመሆኑ ጉዳይ ላይ ብአዴንም ሆነ ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ቅሬታ አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እርሱም ሆነ ‹ደቡብን እወክላለሁ› የሚለው ድርጅቱ ለአሸናፊ ኃይል ከማገልገል አልፈው የፖለቲካ አመፅ ሊያስነሱ እንደማይችሉ ይታወቃልና፡፡ ይሁንና በወቅቱ ኃይለማርያም ሰልፉን በ‹መለስ ባርኔጣ› ከሚንቀሳቀሰው ከመቀሌው ህወሓትና ብአዴን ጋር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝበማስተካከሉ የኃይል ሚዛኑ በአንፃራዊነት ወደእነርሱ እንዲያጋድል አድርጓል፡፡ በግልባጩ ለእነ አቦይ እና ደጋፊዎቻቸው የመሸነፍ መገለጫ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ እንግዲህ እስከ ዘጠነኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ድረስ ‹መልከ-ኢህአዴግ› በዚህ መልኩ ነበር የቀጠለው፡፡
‹መፈንቅለ-ህወሓት›
ብአዴኖች፣ ከመቀሌው ህወሓት ጋር የፈጠሩትን ግንባር፣ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ካገኙት ድጋፍ ጋር በማዋሀድ፡- የአዲስ አበባውን ህወሓት የአመራር አባላት ሙሉ በሙሉ፣ የደህንነት ሀላፊው ጌታቸው አሰፋን እና አንጋፋ የህወሓት ታማኝ ጄነራሎችን ከመንግስታዊውም ሆነ ከፓርቲው ኃላፊነታቸው በማንሳት በአሸናፊነት ለመወጣት ስልታዊ እንቅስቃሴ አድርገው እንደነበር ለድርጅቱ ቅርብ ከሆነ ሰው አረጋግጫለሁ፡፡ በባህርዳሩ ጉባኤ ላይም መላኩ ፈንቴ ‹አላሰራ አሉኝ› ብሎ በአደባባይ እንዲያጋልጣቸው ከተደረጉት የንግድ ደርጅቶችና ሀብታም ነጋዴዎች አብዛኞቹ ከአዲስ አበባው ህወሓት ጋር የተሳሰሩ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ኩነቶችም ነው ‹መፈንቅለ-ህወሓት› ለማለት የተገደድኩት፡፡ ሴራው የከሸፈው በሁለት ምክንያቶች ይመስለኛል፤ የመጀመሪያው በሰውየው ህልፈት ማግስት (ተተኪው ጠቅላይ ሚንስትር ገና ባልተመረጠበት) እነአባይ ፀሀዬ ሶስት ሜጀር ጄነራል እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎች (አብዛኞቹ የህወሓት ሰዎች ናቸው) መሾማቸው ኃይላቸውን ሲያጠናክርላቸው፣ በአንፃሩ የመቀሌውን ህወሓትና ብአዴንን በሠራዊቱ ውስጥ የነበራቸውን ተፅእኖ ከማዳከሙም በላይ ኃይል የማሰባሰብ ሩጫቸውንም ገትቶታል፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በደህንነት መስሪያ ቤቱ አቀናባሪነት በ‹ፀረ ሙስና› ሽፋን የተከፈተው ዘመቻ ነው፤ እነበረከትንም ስልታቸውን መልሰው እንዲያጤኑ ያስገደዳቸው ይህ አይነቱ አስደንጋጭ እርምጃ ይመስለኛል፡፡
የህወሓት ‹ቆሌ›
የኢትዮጵያን ልማዳዊ ፖለቲካ ከነሴራው ጠንቅቀው ከተረዱት ጥቂት ሰዎች መሀል አቦይ ስብሃት ነጋ አንዱ መሆናቸው ተደጋግሞ ተነግሯል፡፡ አቦይ ህወሓትን ጠፍጥፎ በመስራቱም ሆነ በስልጣን ለማቆየት የመለስን ያህል (ሊበልጥም ይችላል) ለፍተዋል፡፡ ዛሬም ተፈጥሮ ላመጣባቸው እርጅና እጅ ሳይሰጡ በህወሓት ላይ የሚሴረውን-ለመበጣጠስና ለተቀናቃኞቻቸው-ጉድጓድ ለመቆፈር እንደማይሳናቸው አሳይተዋል፡፡ ይህ ሁኔታም ነው ‹የህወሓት ቆሌ› የሚል ቅጥያ ያሰጣቸው፡፡
ከመለስ ዜናዊ ጋር የነበራቸው ጥብቅ የመተባበር መንፈስም ከጓዳዊነትም በላይ እንደነበር የቅርብ ሰዎቻቸው ይመሰክራሉ፡፡ ግና ይህ የጦፈ ፍቅራቸው ከ2000 ዓ.ም ወዲህ መደብዘዝ ጀምሮ ነበር፤ ልዩነታቸውም ቅስ በቀስ እየሰፋ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ አንዱ መለስ፣ ለአዜብ መስፍን እየሰጠ የነበረውን የፖለቲካ ጉልበት፣ አቦይ ‹ህወሓትን በሴት ቀሚስ እንደማሳደር› አድርገው መውሰዳቸው ነበር፡፡ ሌላው የሴቲቱ ኃይለኝነት የአቦይን የተሰሚነት ክልል ከመፈታተን አልፎ በአደባባይ ክብራቸውን እስከ መዳፈር መድረሱ ይመስለኛል፡፡ ችግሩን ለመፍታትም ከመለስ ጋር ተገናኝተው መነጋገር አልቻሉም፤ ለህወሓት ቅርብ የሆኑ ወዳጄ እንደነገሩኝ መለስ ህይወቱ ሲያልፍ አቦይን ካገኛቸው ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል፤ ምክንያቱ ደግሞ እርሱ ማግኘት ባለመፈለጉ ነበር፤ ይህም ሆኖ አቦይ ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርጉም በልዩ ረዳቱ አማካኝነት ‹አስቸኳይ ጉዳይ ላይ ነው› እያስባለ መልሷቸዋል፤ በስራ አጋጣሚ ከቢሮ ውጪ ሲገናኙም ‹አጣዳፊ ስራ ስለተደራረበብኝ ነው፤ እኔ ራሴ አስጠራሀለሁ› እያለ ለሁለት ዓመት ያህል ሲርቃቸው ከቆየ በኋላ ነበር ድንገት ህይወቱ ያለፈው፡፡
አቦይ ወደ ህወሓት ተመልሰው በንቃት መሳተፍ የጀመሩት የመለስን ጤንነት ሲከታተሉ የነበሩ ሐኪሞች ‹ተስፋ የለውም› ባሉበት ማግስት ነበር፤ እንደምክንያት ያስቀመጡት ህወሓት ከድህረ-መለስ በኋላ፣ የብአዴንን የትከሻ ግፊያ መቋቋም አይችልም የሚል ስጋትን ነው፡፡ የሰውየው መጨረሻ ከታወቀ በኋላም የተፈጠረውን ክፍፍል ተከትሎ የታየው የኃይል ሚዛን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ በወቅቱም አቦይ ‹መፍትሄ› ብለው ያቀረቡት ‹ብአዴንና ከጎኑ የተሰለፉትን የህወሓት የአመራር አባላትን ማሸነፍ ስለማንችል፣ አንጃው (የእነ ስዬ ተወልደ ቡድን) ተመልሶ ያጠናክረን› የሚል ነበር፤ በስማቸውም ‹‹ውራይና›› መፅሄት ላይ በፃፉት (ርዕሱ ከላይ በተጠቀሰው) ፅሁፍ ጉዳዩን እንዲህ በማለት ገልፀውት ነበር፡-
‹‹…ሁላችንም ህወሓት ውስጥ እያለን እኮ አንጃው ድርጅቱን ተቆጣጥሮት በትረ-መንግስቱንም ሊጨብጥ ተቃርቦ ነበር፡፡ በአንጃው የመዋጥ አደጋ ጊዜ ሁላችንም ተኝተን ነበር፡፡ እነዚያ የተሰናበቱት ሰዎች በማዕከላዊ ኮሚቴው ውስጥ ቢቆዩ ኖሮ ይተኙ ነበር ማለት ግን አይደለም፡፡ አሁን ላለው አመራር ይደግፉት ነበር ይሆን ማለቴ ነው እንጂ፡፡ …ከዚህ ቀደምም ሆነ አሁን ከህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የወጣ ሁሉ እንደአዲስ ተደራጅቶ አሁን ላለው ማ/ኮሚቴ እገዛ የሚያደርግበትን መንገድ ማፈላለግ አለበት፡፡…›› (‹ውራይና› ቁጥር 4 ነሀሴ 2005 ዓ.ም)
ሆኖም አባይ ፀሀዬ፣ አርከበ እቁባይ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ ጌታቸው አሰፋን የመሳሰሉት ‹በጭራሽ አይሆንም! የእነርሱ መመለስ ያውከናል› የሚል አቋም በመያዛቸው ሃሳቡ ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
ከዚህ በኋላ የእነ አቦይና አባይ ቡድን ‹ህወሓትን ማዳኛ› ያለውን ሁለት ወሳኝ እርምጃ ወስዷል፤ ከህግ ውጪ ሶስት ሜጀር እና ሰላሳ አራት ብርጋዴር ጄነራሎችን ሲሾም፣ በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበረውን ወ/ስላሴ ወ/ሚካኤልን ከየትኛውም አይነት ‹ኦፕሬሽን› እንዲገለል አደረገው፤ ቀጥሎ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ከሀላፊነቱ አነስቶታል፡፡ በዚህ በኩል ያገኙትን የፖለቲካ ጉልበት በመመንዘር ከህገ-መንግስቱም ሆነ ከተለምዶአዊው አሰራር በማፈንገጥ ተጨማሪ ሁለት ም/ጠቅላይ ሚንስትሮች እንዲሾሙ ጫና ፈጥረው ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ ኃ/ማርያም ደሳለኝን በቅርብ ርቀት እንዲከተል አድርገዋል (በነገራችን ላይ ባለፈው ዓመት አጋማሽ ህወሓት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን በመረጠበት ወቅት ወልደስላሴ ሲጠቆም፣ ጠንካራ ተቃውሞ አቅርቦ እንዳይመርጡት ያነሳሳበት የደህንነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋ ሲሆን፣ በአንፃሩ ጌታቸው የተጠቆመ ጊዜ ወልደስላሴ እና ገብረሃዋድ ተቃውሞውን ቢያስተባብሩም ታናሽ ወንድሙ በላይ አሰፋን ጨምሮ ከመመረጥ ማደናቀፍ አልቻሉም፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወልደስለሴና ገብረሃውድ በሙስና ተጠርጥረው በእስር ላይ ይገኛሉ)፡፡
ሌላኛው የህወሓት ‹ጠባቂ መልአክ› አባይ ፀሀዬ ነው (በ2005 ዓ.ም ወርሃ ጥቅምት በታተመችው ‹አዲስ ታይምስ› መፅሄት ላይ አባይ፣ መለስ ያደረገውን ማድረግ የሚችል /ከንግግር ችሎታ በቀር/ አደገኛ ሰው መሆኑን መግለፄ ይታወሳል) ዘግይቶም ቢሆን ቡድኑን የበላይ ባደረገው የ‹ፖለቲካ ጨዋታ› እርሱም የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስድ ታይቷል፡፡ ደብረፅዮንም ቢሆን ከህወሓት ጋር ባሳለፈው ዘመን ‹ትጉህ ደቀ-መዝሙር› ስለነበር ያካበተው ልምድ ህወሓትን በታደገው ንቅናቄ ላይ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ እነ አባይ ከባህርዳሩ ጉባኤ በኋላ ነው ‹ከመከላከል ወደ ማጥቃት› ተሸጋግረው ብአዴንንና የመቀሌውን ህወሓት በ‹ሙስና› ስም ሰለባ ያደረጉት፡፡ ይህንን እውነታም የሚያጠናክርልን አቦይ ስብሃት ‹‹ውራይና›› መፅሄት ስለ ጉዳዩ ጠይቋቸው የሰጡት ምላሽ ነው፡-
‹‹አሁን በእስር የሚገኙት [እነመላኩ ፈንቴን ማለታቸው ነው] ሙሰኞች ብቻ አልነበሩም፡፡ የፖለቲካዊ ኃይል አሰላለፍንም ሲለውጡ የነበሩ ናቸው፤ ያስፈራሩም ነበር፤ ‹የስልጣን ሹዋሚም ሻሪም እኛ ነን› አስከማለትም ደርሰው ነበር፡፡›› (‹ውራይና› ቁጥር 2 ሠኔ 2005 ዓ.ም)
የብአዴን የአመራር አባል የሆነ አንድ ሚንስትር ለእስር ሲዳረግ፣ ሌላ ሚንስትር ደግሞ ከኃላፊነቱ መነሳቱ ይታወቃል፡፡
አዲሱ ግንባር
ብአዴን የአዲስ አበባው ህወሓት ክንደ-ብርቱ እየሆነ በመምጣቱ፣ የእነ አዜብን ቡድን አውላላ ሜዳ ላይ ትቶ አብሮ ለመስራት ተደራድሯል፡፡ እነ አባይም ‹ከብአዴን ተሻርኮ ሊያስበላን ነበር› ያሉትን የመቀሌውን የህወሓት ኃይል ከሞላ ጎደል ሲያስገብሩት፣ የቡድኑ መሪን አዜብ መስፍንን ደግሞ ከኤፈርት ከማሰናበታቸውም በላይ የፓርላማ ወንበሯን የሰዋችለትን የአዲስ አበባ የከንቲባነት ምኞቷን አጨልመው፣ በመለስ ፋውንዴሽን ገድበዋታል (የመለስ ሙት ዓመት በተከበረበት ወቅት የትግሉን ዘመንና የመለስን ገድል በኢቲቪ ሲተርኩልን የነበሩት የታሪኩ ዋና ተዋንያን አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሀዬ፣ ሳሞራ የኑስ…ሲሆኑ፣ በህልፈቱ ሰሞን ግን መድረኩን ተቆጣጥረውት የነበሩት ብአዴኖች፣ እነኩማ ደመቅሳ እና ትግሉን በመፅሀፍትና በቴሌቪዥን የሚያውቁት እነ ሬድዋን ሁሴን መሆናቸውን ስናስታውስ የእነ አባይ ፀሀዬ ህወሓት ምን ያህል ተገፍቶ እንደነበረ እንረዳለን፡፡)
በአናቱም ብአዴን የበላይነቱን በጨበጠበት ወቅት እንደ ስጋት ቆጥሮት ‹ሊፐውዘው› አስቦ የነበረውን መከላከያም፣ ከድርድሩ በኋላ በሁለቱ ኃይሎች ስምምነት ለአምስት ቀናት ኪራይ ሰብሳቢነትን እና ሙሰናን በተመለከተ ብቻ ተገማግሞ እንዲታለፍ ተደርጓል፡፡ ከኃላፊነታቸው ለማንሳት የታሰቡት ጄነራሎች ጉዳይም ‹ያልታሰበ አደጋ ሊያመጣ ይችላል› በሚል ለጊዜው ተዘሏል፡፡ ይሁንና ኤታማዦር ሹሙን ጄነራል ሳሞራ የኑስን በዚሁ ዓመት መጨረሻ በ‹ክብር› ሸኝቶ፣ ጄነራል አበባው ታደሰን የመተካት ዕቅድ መኖሩን ምንጮች ጠቁመዋል (ከዚህ በኋላ በጡረታ የሚሰናበቱ ጄነራሎች ‹መከላከያ ቴክኖሎጂ› /መቴክ/ በሚመራውና ወደፊት በሚያቋቁማቸው ኢንዱስትሪዎች ውስጥ በስራ-አስኪያጅነት ወይም በቦርድ አባልነት እንደሚመደቡ ቃል ተገብቶላቸዋል)
ከኃ/ማርያም ጀርባ ያደፈጠ-ስውር እጅ
በሁለቱም ቡድን ካሉ ምንጮቼ ‹‹ኃ/ማርያም ስራው ከብዶታል›› የሚል ቅሬታ እንደነበራቸው ሰምቻለሁ፤ ይሁንና መፍትሄ ተደርጎ የተወሰደው በረከት ስምዖንን የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹የፖሊሲና ጥናት ምርምር› አማካሪ በሚል ሹመት በጽ/ቤቱ ማስቀመጥን ነው፤ እርሱሁሉንም ነገር ከጀርባ ሆኖ እንዲያከናውን ወስነዋል፡፡ በረከት የተመረጠው ‹ከመለስ ጋር በቅርብ ስርቷል፣ መለስ ያነበበውን አንባቧል፣ የመለስን የዕለት ተዕለት ሥራ በቅርብ ተከታትሏልና መንገድ ይመራል› በሚል እንደሆነ ምንጮቼ ነግረውኛል (በነገራችን ላይ መለስ ሞት ባይቀድመው ኖሮ የወደፊት ዕቅዱ ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ጀምሮት የነበረውን ግንባታ አጠናቅቆ፣ ከ2007ቱ ምርጫ በኋላ ስልጣኑን፣ ከአሻንጉሊቶቹ ለአንዱ አስረክቦ፣ መኖሪያውንም ወደ አዲሱ ህንፃ አዛውሮ፣ በለቀቀው ቤት ውስጥ የሚያስገባውን ጠቅላይ ሚንስትር ከጀርባ ሆኖ መዘወር ነበር፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ህልፈቱን ተከትሎ ግንባታውም የተቋረጠው፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ግንባታው ሊቀጥል እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ በረከት ስምዖን እንዲገባበት ታስቦ ይሆን? …አባይ ፀሀዬም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ ‹አማክሪ› ሆኖ እንደሚሾም ‹ፎርቹን› ጋዜጣ በ‹ጎሲፕ› አምዱ አትቷል፡፡ መቼም ኃ/ማርያም ‹‹ሰርክ ‹እኔም አንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልለት› እያልኩ እዘምርለታለሁ›› ያለን አምላኩ ካልታደገው በቀር፣ ከእነዚህ ጉልበታም ሰዎች በጤና መውጣቱን እንጃ!)
ህወሓትና ብአዴን ልዩነታቸው መፈታቱን ለማሳየት፣ በረከት ስምዖን ከአዲሱ ሹመት በኋላ በሃያ ሁለት ዓመታት የስልጣን ዘመኑ አድርጎት የማያውቀውን መንግስትን ወክሎ (በግሉ ሄዶ ሊሆን ይችላል) በትግራይ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የስራ ጉብኝት አካሄዷል፡፡ ‹ድምፀ ወያኔ› የተባለው የክልሉ ሬዲዮ ጣቢያም ጉብኝቱን ሳምንት ሙሉ ሳይታክት ደጋግሞ አስተላልፎታል፡፡
ሽራፊ-መረጃ
የአቦይ ስብሃት ነጋ ቡድን በኢህአዴግ ውስጥ ተከስቶ ከነበረው ክፍፍል በአሸናፊነት መውጣቱ ከተረጋገጠ በኋላ አዲስ ወሬ እየተሰማ ነው፡፡ ይኸውም ‹ህወሓት የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን በመልቀቁ፣ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚያስረክቡትን ወንበር አቦይ ስብሃት መያዝ አለባቸው› የሚል ነው፤ ምንም እንኳ ሃሳቡ ተፈፃሚነት ባይኖረውም፣ ምንጮቼ አቦይ ራሳቸው በዘወርዋራ መንገድ ያሰራጩት ወሬ ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ አዜብ መስፍንም ቦታውን የመያዝ ፍላጎት ያላት ይመስለኛል፡፡
ብዙ ሲባልለት የቆየው የድህረ-መለስ ኢህአዴግ ከላይ ለማቅረብ በሞከርኩት መንገድ ግራና ቀኝ ሲዋልል፣ የመከፋፈል ተግዳሮትን ሲሻገርና እንደገና እየተመለሰ ሲሰባሰብ እዚህ ደርሷል፡፡ በዚህ ኮሮንኮቻማ ሂደት ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትሩ ሚና ‹እዚህ ግባ› የምንለው እንዳይመስለን ሆኗል፡፡ ኃይለማርያም መንግስታዊ ብቻ ሳይሆን የፓርቲው ሊቀ-መንበርነትን የመሰለ ጠንካራ ፖለቲካዊ ስልጣን መያዙ ይህ ሰው የሚባለውን ያህል የዳር ተመልካች ሆኖስ ይቆያልን? ለሚለው ጥያቄ ቀጣይ ጊዜያቶች ብቻ መልስ ይኖራቸዋል፡፡ የጠቀስኳቸው የስርዓቱ ጉምቱ ሰዎች በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሱም ቢሆን፣ ይህን የኃይል መገዳደር እያደረጉ ያሉት በስልጣን ሞኖፖሊ ላይ ተቀምጠው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እናም ባቀረብኳቸው ሂደቶች እያለፉም ይሁን አይሁን ለስልጣናቸው የሚያሰጋ ጠንካራ የታቃውሞ ስብስብ አለመኖሩን ማመናቸው ይመስለኛል፣ የኃይል ትንቅንቁን ‹ግዜው አይደለም› ብለው ለማራዘም ሳይጠነቀቁ በግላጭ እርስ በእርስ የተፋለሙት፡፡
የሆነው ሆኖ የፓርቲው የታሪክ ድርሳን እንደሚነግረን ‹ይሆናሉ› የተባሉት ተቀልብሰው፣ ባልተጠበቁ ሁነቶች (የኃይል መገለባበጥ ተከስቶ) ፖለቲካው የሚመራበት አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አያስፈለግም፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ ቢታገትም ፣ የተሳካ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነበር! – ከአንድነት ፓርቲና ከ 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ



አንድነት ፓርቲ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር በመሆን ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለማድረግ ያቀዱት ሰላማዊ ሰልፍ በገዢው ፓርቲ (መንግስት) ክልከላ ሠልፉ ሊደረግበት ወደነበረው መስቀል አደባባይም ሆነ በአማራጭ ነት ያቀረቡት 9 አደባባዮች እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ከአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እስከ ቀበና አደባባይ ባለው አስፋልት ላይ ቁጥሩ ከ80 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ተደርጓል፡፡
ለዚህ ደማቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ ፓርቲዎች አመራሮች አባላትና ደጋፊዎች ያደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና ሕዝቡ የመንግሥትን ፀጥታና የፖሊስ ኃይሎች ማስፈራራት አልፎ የላቀ አዎንታዊ ምላሽ ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲና የ33ቱ አመራር ህዝቡ ለሰጠው አመርቂ ምላሽ ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረቡ፣በቀጣይ ለሚደረገው ወሳኝ ትግል ታላቅ የማበረታቻ እርሾ መሆኑን ያምናል፡፡ ከዚህም ሕዝቡ አመራር ካገኘ ለመብቱና ነፃነቱ ወደ ኋላ የማይል መሆኑንና በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ ፍላጎት መኖሩን ያረጋገጥንበት፣ ትዕይንት ሲሆን በተጨማሪ ሠላማዊ ትግል በጋራ አመራር ከተያዘ ውጤታማ መሆኑን አምነናል፡፡
ሆኖም ከዚህ ሕዝባዊ ንቅናቄ የተማርነው ሌላ ነገር ቢኖር በአገራችን ያለውን የአስተዳደርና የህግ ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ መውደቁንና ገዢው ፓርቲ በየትኛውም ደረጃ በሕዝብ በሚነሱ ጥያቄዎች በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ የወደቀ መሆኑን ነው፡፡
የአዲስ አበባ መስተዳድርና የፌዴራሉ መንግሥት ለሰልፉ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ቢልም የተለያዩ አስተዳደራዊ ደንቃራዎችን በመፍጠርና የማናውቃቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በመፍጠር የቅስቀሳ ሥራችንን በማደናቀፍና ሕዝቡ ወደ ሰልፉ እንዳይወጣ በማድረግ በተግባር ሠልፍ የማይደረግባት አገር ለመፍጠር ሣይታክት ተግቶ ሰርቷል፡፡ ቀስቃሾችና አመራሮችን አስሯል መኪናዎችን አግቷል፡፡ በዚህ ውስጥ ማለፍ የተሣካ ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠራችን ከዚህ በመነሳት አንድነት ፓርቲና 33ቱ በጋራ በተጠናከረ መንገድ በመላው አገሪቱ ቀጣይና ተከታታይ ሕዝባዊ ንቅናቄ የማድረግ አስፈላጊነትን ተምረንበታል፡፡
ስለሆነም በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር የምትገኙ የሠላማዊ ሕዝባዊ ንቅናቄ ደጋፊዎቻችን በሙሉ ለእስከዛሬው በድጋሚ እያመሰገንን ለቀጣዩ የጋራ ሥራችን እንደተለመደው ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
አንድነት ፓርቲና 33ቱ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም1374061_10201496850957121_1380175466_n603944_622133674503606_213601633_n994913_10201496979000322_682846221_n603944_622133674503606_213601633_n1374061_10201496850957121_1380175466_n
1375296_10201496976200252_459019693_n

Saturday, September 28, 2013

የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ?

የህወሓትን ፀረ ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን
ነው። በህወሓት የተፈጸመው እውንተኛ ታሪክና አሰቃቂ ወንጀሎች፣ የህወሓት አመራር በኢትዮጵያ ሃገራችን አሁንም
እየፈፀሙት የሚገኘው ግፍ በግልጽ ተጽፎ የወያኔ ጥቁር ታሪክ ለሕዝብ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። አሁንም እየቀረበ
ነው። ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ለትግል የተሰማራው በየካቲት 11 ቀን 1967 ደደቢት በረሃ እንደመሸገ
ማሀብር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) የተዘጋጀው ፕሮግራም የተረከበው ተሓህት ወይም የዛሬው ስሙ ሀወሓት ነው።
ተሓህት ትግሉን በጀመረበት ወቅት ጥቂት ከነበሩት ታጋዮች ሊመሩን ይችላሉ ብሎ ከመረጣቸው መካከል፤ 1. አረጋዊ
በርሄ፣ ሊቀመንበር 2. ዘርኡ ገሰሰ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ገሰሰው አየለ 5. አባይ ፀሃየ 6. ሥዩም መስፍን 7. አለምሰገድ መንገሻ
8. አስፍሃ ሃጎስ ተመርጠው ተሓህትን መርተዋል። በዚህ ጊዜ ነበር የማገብትን ውርስ ተሓህት ተረከበው ብሎ በጊዜው የነበረ ታጋይ ደስታውን የገለጸው። ውርስ ማለት
ፕሮግራሙ ነው። በጊዜው የነበረ ሁሉም ታጋይ ግን የፕሮግራሙን ይዘትና ምንነትቱን አያውቅም ነበር። ይህ ፕሮግራም ነበር
በ1968 ቀስ በቀስም ተሓህትን ለሁለት የመሰንጠቅ አደጋ የፈጠረበት።< የተሓህት-ህወሓት የመጀመሪያ መሰንጥቅ ተሓህት ገና ከደደቢት በረሃ ሳይወጣ በፊት በሁለት ጎራ የተሰነጠቀበት ወቅት ነው። ይህን መከፋፈል የፈጠረው የፕሮግራሙ
ባለቤት ነን የሚሉ አመራር በድብቅና ከታማኝ ታጋዮች ጋር በመተባበር ወስጥ ለውስጥ ፕሮግራሙ ይዘጋጅ ነበር። ይህን
የማይደግፉና የሚቃወሙ አመራርም ነበሩ።
አክራሪና በአቋማቸው የጸኑ ግን ፕሮግራሙ በትክክል የተዘጋጀ ሃቀኛ የትግራይ ሕዝብ ምኞትና ፍላጎትን በጭብጥ
ያስቀመጠ፤ ትግራይን እና ሕዝቧን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነፃ የሚያወጣ፣ የትጋላችን መርህ ፕሮግራም ነው አሉ። የዚህ
ተሳታፊውች፤ 1. አረጋዊ በርሄ 2፣ አባይ ፀሃየ 3. ሥዩም መስፍን 4. ግደይ ዘራጽዮን 5. ስብሃት ነጋ 6. መለስ ዜናዊ 7. አስፍሃ
ሃጎስ 8. አውአሎም ወልዱ 9. ስየ አብርሃ 10. ሃይሉ መንገሻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አመራር የነበሩና ጥቂቶቹ ደግሞ ከአንድ
ዓመት በኋላ ወደ አመራር የመጡ ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ በተቃውሞ የቆሙትና ፕሮግራሙ በጣም አደገኛ፣ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ፣ ሕዝብ በታኝ፣ ጸረ-
ሕዝብና ጸረ-ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው በማለት የተነሱት ደግሞ 1. ገሰሰው አየለ 2. አግአዚ ገሰሰ 3. አጽብሃ ዳኘው 4. ዶ/ር
አታክልት ቀጸላ ሲሆኑ፣ ከሻእቢያ መጥቶ ተሓህትን የተቀላቀለው መሃሪ (ሙሴ) ተክሌም 5ኛ ሆኖ ከነገሰሰው አየለ ጋር
ተቀላቀለ። እነዚህ ሁሉም የተሓህት አመራር የነበሩ ናቸው።
ማህበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ (ማገብት) ገና ሲፈጠር ጎባጣ፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ሆኖ ነው የተመሰረተው።
ይህንን ውርስ ያስረከበው ለተሓህት በየካቲት ወር 1967 ነው። በደደቢት በረሃ ተጠናክሮ ፕሮግራም ሆነ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ
ፕሮግራሙን በመቃወም የተሰለፉት ያነሱት ነጥብ፤ 1. ተሓህት በጸረ ኢትዮጵያና በሕዝቧ ተቀናጅቶ መፈጠሩ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሃገር መበታተን አለባት የሚለው
በገጽ 8 የተዘጋጀው የባእዳን ሴራና ጸረ ሃገር ነው፣ 2. አማራ የትግራይ ሕዝብ ጨቋኝና ረጋጭ፤ ለድህነት፣ ለሽርሙጥና፣ ለስደት፣ ለመከራ የዳረጋት ጠላት ነው
የሚለው ትንተና ሃቅነት የሌለው የፈጠራ ወሬ ነው። የተጻፈው አማራን ሆን ብሎ ለማጥቃት ነው። ይህም
ከፕሮግራሙ መወገድ አለበት፣ 3. ኤርትራ የአማራው (ኢትዮጵያ) ቅኝ ግዛት ናት የሚለው ቅንጣት ታህል ሃቅነት የሌለው እናንተ አመረር
የፈጠራችሁት የተገንጣይ ዓላማ ነው፣
4. ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት ማለት የአእምሮ ድህነትና ጠባብ ዘረኝነት ነው፣ ስለሆነም መወገዝ አለበት።
5. ተሓህት የኢትዮጵያ ጥንታዊና ታሪካዊ ግዛትዋን እና የባሕር በሯን የሚያስነጥቅ ፕሮግራም ነው። ስለሆነም ጸረ-
ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ነው። ፕሮግራሙ ይለወጥ ወዘተ. የሚሉ ሃሳቦች በማንቀሳቀስ ቀሪው ታጋይም የእነገሰሰው
አየለን ሃሳብ መደገፉን በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች በትክክል ተናግረውታል።
በተጨማሪም አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጨመሩበት ነጥብ ተሓህት በትግራይ ሕዝብ ተቀባይነት ወይም
የውክልና መሰረት የሌለው፣ ፕሮግራሙን በትግራይ ሕዝብ ስም መዘርጋት አግባብነት የሌለው፣ በሕዝብ ስም ማጭበርበር ነው
ብለው በማመን በወቅቱ የነበሩ አነስተኛ ታጋዮች በዚህ ሃሳብ ተስማሙ። በዚህ ጊዜ 1. በስብሃት ነጋ 2. መለስ ዜናዊ
3. አውአሎም ወልዱ 4. ስየ አብርሃ ወዘተ. ተባብረው በአቶ ገሰሰው አየለ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ። በስብሃት ነጋ
እየተመሩ የገሰሰው አየለን ስምና ዝና በጥቁር ቀለም ቀቡት። ሻእቢያም ገሰሰው ከተሓህት ተቀላቅሎ መታገሉን ከመጀመሪያው
ያልተቀበለው ስጋት ወስጥ ስለጣለው ነው። ሻእቢያ ለተሓህት አመራር ያስተላለፈው መልእክት፣ ገሰሰው አየለ በዚህ ከቀጠለ
ተሓህትም ሆነ ሻእቢያ ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ተናግሯል። ገሰሰው አየለ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት የሚለውን
የተህሓት ጥቂት አመራር ሃሳቡን ተቀበሉት።
የእነ ስብሃት ነጋ ቡድን በገሰሰው አየለ ላይ ሲያስፋፉት የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ጥቂቱን እንመልከት፤
1. ድርጅታችን ተሓህት የገሰሰው አየለ ፊውዳል ድርጅት ነው እየተባለ ነው። ይህንን ግለሰብ ከድርጅቱ ማስወገድ
ስላለብን እንተባበር (መለስ ዜናዊ)፣
2. ገሰሰው አየለ ፊውዳል፣ ጸረ-ትግራይ ትግል በመሆኑ በተመቸው ጊዜ ጠብቆ ተሓህትን ከማጣፋት አይመለስም።
የትግራይን ነፃ ሃገርነትና የትግራይን መንግሥት አይቀበልም። ጸረ-ኤርትራ ትግል ነው። የመትከል አገራችን
ሻእቢያም ተማረውበታል። (ስብሃት ነጋ)፣
3. ኤርትራና ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት አይደሉም፣ አልነበሩም። ሁሉም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ግዛትና አካል ናቸው፣
ስለዚህ የተሓህት ፕሮግራም ውድቅ ነው እያለ እንደ ምስጥ ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎከ ከሕዝብ እየነጠለን
ነው (ስብሃት ነጋ)።
በዚህ ጊዜ የነበሩ ታጋዮች እንደሚናገሩት ከሆነ በገሰሰው አየለ ላይ በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የሚመራው ቡድን
የተሰማሩበት የስም ማጥፋት ዘመቻ በየቀኑ ይደርሰው ነበር። በመጨረሻ ተማሮ በህዳር 1968 ከማ/ኮሚቴ ሃላፊነቱ ራሱን
አግልሏል። ይህ በመሆኑ በሃዘን እና በቁጭት የሚናገሩ በወቅቱ የነበሩ ታጋዮች ነበሩ። አክራሪውን አመራር ለመቆጣጠር አቅም
ነበረን ግን ስህተት ፈጸምን ያሉም አልታጡም።
የዲማ ኮንፈረንስ
የዲማ ኮንፈረንስ የተካሄድው በመጋቢት መጀመሪያ በ1968 ነበር። በዚህ ጊዜ አቶ ገሰሰው አየለ በስብሰባው
አልታየም። በወቅቱ በዚህ ጉባኤ የተሳተፉት ታጋዮች ገሰሰው/ስሁል የት ሄደ ብለው ሲጠይቁ የተሰጠው መልስ በሥራ
ምክንያት ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል የሚል እንደነበር ይናገራሉ። ኮንፈረንሱ ከመድረሱ በፊት የስብሃት ነጋ ቡድን በአግአዚ ገሰሰ፣
በጥቂቱም ቢሆን በግደይ ዘርአጽዮን ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል። ነገር ግን ውጤት አልባ ነበር።
በዲማ ኮንፈረንስ የተመረጡት 1. አረጋዊ በርሄ፣ የተሓህት ሊቀመንበር 2. ስብሃት ነጋ 3. ግደይ ዘርአጽዮን 4. ሥዩም
መስፍን 5. አግአዚ ገሰሰ 6. አባይ ፀሃየ 7. ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ ነበሩ። ምርጫው ጸረ-ዲሞክራሲ ስለነበር የነበረው አመራር
ስብሃት ነጋን መርጦ መለስ ዜንዊን ድምጽ ነሳው። በዚሁ ሁሉም ወደየሥራው ሄደ።
ቀደም ብዬ በአርእስቱ ላነሳሁት ጥያቄ መልስ ለመስጠት፣ የተሓህት - ህወሓት ጸረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማን
በመቃወም ለሁለት መሰንጠቁና የሕይወት መስዋእትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው? ለሚለው
ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እነሆ ፎቶግራፋቸውን ከዚህ በማያያዝ አቀርባለሁ።
ገሰሰው አየለ አግአዚ ገሰሰ ሙሴ መሃሪ ተክሌ አጽብሃ ዳኛው ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
አቶ ገሰሰው አየለ የበረሃ ስሙ ስሁል፣ ተወልዶ ያደገው ሽሬ አውራጃ ነው። ገና በወጣትነቱ የሽሬ አውራጃ ማዘጋጃ
ቤት ዋና ሹም በመሆን አገልግሏል። በ1950 አጋማሽ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የኢትዮጵያ ፓርላማ አባል በመሆን
ሠርቷል። ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በማሸነፍ 15 ዓመት ሙሉ የፓርላማ አባል ነበር። በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው አብዮት
እየተጠናከረ ሲመጣ በ1966 የማገብት አባል ሆነ።
አቶ ገሰሰው አየለ የማገብትን አላማ፣ ተግባርና ፕሮግራም በጸረ-ኢትዮጵያነት የተሞላ መሆኑን ትኩረት ሳይሰጥ
በየካቲት 11 ቀን 1967 ለተመሰረተው የትጥቅ ትግል ግንባር ቀደም መስራች በመሆን በአመራር ደረጃ ግንባሩን ሲመራ ነበር።
የተሓህትን ፕቶግራምና ዓላማ ካየ በኋላ ፍጹም ጸረ-ኢትዮጵያ አንድነትና ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብነትን የጨበጠ
ፕሮግራምና በፋሽስት ጣልያን የተዘጋጀ ነው እስከማለት ደረሰ። በህዳር 1968 ከአመራሩ ወረደ።
አቶ ገሰሰው አየለ ያነሳው ተቃውሞ ብዙ ቢሆንም ከተራ ቁጥር 1-4 ያሉትን አንኳር ሃሳቦች አስነስቷል። ታጋዩም
ድጋፍ ሰጠው። ከአመራሩም እንደነ አግአዚ ገሰሰ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክለት ቀጸላና መሃሪ ከጎኑ ተሰለፉ። በተሓህት
ውስጥም ጭንቀትና ሽብር በአመራሩ ወስጥ ተፈጠረ። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድንም ገሰሰው አየለን በዘዴ ለማጥፋት
እቅዱን ዘረጋ።
የገሰሰው አየለ ደብዛ መጥፋት
ከዲማ ኮንፈረንስ በኋላና ክዛም ትንሽ ቀደም ብሎ ገሰሰው አየለ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ ሲሉ የት ገባ የሚሉ ታጋዮችም በዙ።
በዚህ ጊዜ የተሓህት አመራር እርስ በርሱ የሚጋጭ ወሬዎች በድርጅቱ አሰራጨ።
1. በአዲ ነብራኡድ ወስጥ በኢዲዩ ወይም ጠርናፊት ድንገተኛ ጦርነት ከፍተው ጠርናፊት ገደለችው፣
2. እኔ ስለሸመገልኩ አልታገልም ገንዘብ ስጡኝና ሱዳን ሄጄ ልኑር በማለት ገንዘብ ከድርጅቱ ተሰጥቶት በመኪና ተሳፍሮ
ሲሄድ በመኪና ውስጥ የነበሩ የኢዲዩ አባላት ገደሉት የሚል ነበር። ሁሉም ውሸት ነው።
ኢዲዩም ይህንን በተመለከተ ሰፊ መግለጫ በተነ። ገሰሰው አየለን እኛ አልገደልነውም፣ ልንገድለውም አንችልም።
የወንድማቻቾች ደም በከንቱ አናፈስም የሚል ሲሆን፣ የገደለችው ተሓህት ናት አሉ።
በአዲ ነብራኡድ ተገደለ የተባለበት ምክንያት ሕዝቡ ራሱ ምስክርነቱን በሰጠበት በመጋቢት ወር ጦርነት አልነበረም።
የደም መፋሰስ አልታየም አለ። የገደሉት ራሳቸው ወያኔዎች ናቸው ሲል ሕዝቡ ምስክርነቱን ሰጠ። አዲ ነብራኡድ የገሰሰው አየለ
ቤት ነው። ጊዜው የአቶ ገሰሰው አየለ ስሁል አሟሟት እውነቱ ግልጽ ሆኖ የወጣበት ጊዜ ነበር። ገሰሰው በስብሃት ነጋ
የሚመራው የተሓህት አመራር በማይታወቅ ቦታ ደብቀው ወይም እንደ ግዞተኛ አቆይተው በሰኔ 1968 በጥይት ደብደበው
ሽላሎ ቡምበት አካባቢ ተገደለ። በግድያው የተሳተፉትም አውአሎም ወልዱና አሰፋ ማሞ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ግን አልታወቁም።
ይህንን እውነታ ተከታትለው ሃቁን ያገኙት በተሓህት ወስጥ ለትግል የተሰለፉት የገሰሰው አየለ የቅርብ ዘመዶቹ ናቸው።
በጊዜው ሃቁን አስቀምጠው አለፉ። ላደረጉት ጥረት የሚመሰገኑና ባለውለታም ናቸው። ጥቂቶቹ፣ ማለትም እንደነ አዘናው
ገ/ጻዲቅ ታፍነው የት እንደገቡ የማይታወቁም አሉ።
የአቶ ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ያስቀመጠው ነቀፌታና ሃሳቡን የደገፉት ግለሰቦች በከፍተኛ ዲግሪ ከቀ. ኃ.
ሥ. ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ እንደነ እቁባዝጊ በየነ፣ አሰፋ ገብረዋህድ የመሳሰሉ ዘጠኝ ምሁራን የተሓህትን አመራር የውሸት ስም
በመስጠት የሥልጣን ሱሰኞች ተብለው ሽራሮ ውስጥ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። እነዚህም በተሓህት አመራር ቅጥራኛ
ባንዳዎች ተገድለዋል። ይሁን እና መልእክታቸውን አስተላልፈው ከዚች ዓለም በግፍ ተገድለው አልፈዋል። ስማቸው ግን
አልጠፋም፤ ለዘላለም ይኖራል።
2. ዘርኡ ገሰሰ
ዘርኡ ገሰሰ የበረሃ ስሙ አግአዚ ሲሆን፣ በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበር።
ማገብትን ከመሰረቱት አንዱ ነው። በአመራርም እስክ እለተ ሞቱ ተሓህትን ከሚመሩት መካከል ነበር። ዘርኡ ገሰሰና አቶ
ገሰሰው አየለ በተሓህት ፕሮግራም ጠማማነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑ በሁሉም ነጥብ አይለያዩም፣ አንድ
አቋም ነበራቸው።
ዘርኡ ገሰሰ የተሓህትን ፕሮግራም አጥብቆ ያወግዘዋል፣ በታጋዩም ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትና ክብርም ያገኘ አመራር
ነበር። ይህች ግን ለነስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን እና መለስ ዜናዊ አትዋጥላቸውም። አደገኛ መሪ ብለው ፈርጀው
የሚጠበቀው ልክ እንደ ገሰሰው አየለ በዘዴ ማጥፋት ነበር።
ዘርኡ ገሰሰ በተሓህት ፕሮግራም በገጽ 8 ላይ የሰፈረውን እና ሌላውን ፕሮግራም ሁሉ አደገኛ ስለሆነ ፈጽሞ መወገድ
አለበት በማለት ከብዙ አመራሮች ጋር መነጋገሩ የቅርብ ሰዎች የሚሉት ሃቅ ነበር። ነገር ግን ሰሚ አላገኘም። እነ ስብሃት ነጋ
የሚገደልበትን ዘዴ ለማመቻቸት ይሯሯጡ ነበር።
አግአዚ ገሰሰ ከግደይ ዘርአጽዮን እና ከአረጋዊ በርሄ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደነበራቸው የሚያውቁ ታጋዮች በዚሁ ሴራ
ሁለቱ ምንም ዓይነት ተሳታፊነት አልነበረባችውም የሚሉም ብዙ ናቸው። የሴራው አካላት ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ አባይ
ፀሃየ፣ ስዩም መስፍን፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ናቸው በማለት ያረጋግጣሉ።
ይህ በእንዲህ እያለ የተሓህት አመራር ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ሆነው ዘዴውን አቀነባብረው ከጨረሱ፣ አግአዚን
ጨምሮ በአክሱም ከተማ ትልቅ ሥራ እንዳለ አስመስለው ሃሳባቸውን በማቅረብ የሚፈጸመውም በአመራር ደረጃ ስለሆነ
አግአዚ ተዘጋጅ ብለው በትንሽ ቀናት እንደሚገናኙ ተወሰነ። ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጠላት በብዛት የሚገኝበት ለመንቀሳቀስም ሆነ
መንገዱን መጠቀም በማይቻልበት ቦታ ወቅሮ ማራይ መሆኑ በሕዝብ ግንኙነት ጥናት አግኝተዋል። ወቅሮ ማራይ በደርግ
ሚሊሺያ የታጠረ ነው። ቀኑ ደረሰ፣ አግአዚ ገሰሰና ነፃነት ሰንደቅ አብረው ከነስብሃት ጋር ሰመማ በሚባል ቦታ ተገናኙ። ስብሃት
ነጋ ለአግአዚ በየትኛው ቦታ ለመሄድ አስበሃል ሲለው በመደባይ ታብር በኩል ሲለው የመረጥከው መንገድ አደገኛ ነው በማለት
በሕዝብ ግንኙነት አጥንተን ወቅሮ ማራይ ነፃ መሆኑን፣ ሚሊሻም ሆነ የደርግ ሰራዊት የሌለበት ነው ካሉት በኋላ በህሳቡ
ተስማምተው መንገዳቸውን ቀጠሉ። ነፃነት ሰንደቅ አብሮት ስለነበረ ሁሉንም ሰምቶታል። ወቅሮ ማራይ እንደገቡ በሚሊሻ
ተከበው በተተኮሰ ጥይት አግአዚ ገሰሰ ወዲያውኑ ወድቆ ሞተ። ነጻነት ግን አመለጠ። እንደምንም ብሎ ዘና ወረዳ ገባ። እዛ
ላገኛቸው ታጋዮች የደረሰባቸውን ሲነግራቸው፣ ነፃና ጥሩ መንገድ ነው ብለው ስብሃትና አባይ ፀሃየ አግአዚም የተናገሩትን
አምኖ በሚሊሻ ተከበን የጥይት ናዳ ወርዶብን አግአዚን ገደሉት፣ እኔ አመለጥኩ። ስብሃት ነጋና አባይ ፀሃየ ባዘጋጁት የግደያ
ዘዴ የሚቃወማቸውን አግአዚ ገሰሰውን አጠፉት ብሎ የተናገረው በተሓህት ውስጥ ተሰራጨ። ስብሃትና አባይ ተከታትለው
ነፃነትን ለማግኘት የተፈጠረው ነገር ለማንም እንዳይነገር አስጠነቀቁ። ሆኖም ግን ነገሩ ተሰራጭቷል። አመራሩም የአግአዚን
ሁኔታ አንዲት ቀንም ሳያነሳ ቆይቶ በ1ኛው ጉበኤ በጠላት ተገደለ ብለው ተናገሩ። የስብሃት የግድያ ሴራም ሰመረለት።
3. መሃሪ ተክለ
መሃሪ ተክለ የበረሃ ስሙ ሙሴ ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ሲማር የቆየ፤ ከሻእቢያ ጋር የተሰለፈ
የሻእቢያ ታጋይና አመራር የነበረ ሰው ነው። ሻእቢያና ማገብትን በማይበጠስ የብረት ሰንሰለት ያቆራኘው መሃሪ ተክሌ ነው።
ማገብትን የመሰረቱት እነ አረጋዊ በርሄ በጥር 1967 ሳህል ኤርትራ በረሃ ወርደው በሻእቢያ ወታደራዊ ትምህርት ሰልጥነው
ብረት ታጥቀው ደደቢት በረሃ እንዲወርዱ ትልቅ ሚና የተጫወተው መሃሪ ተክሌ ነው። መሃሪ ተክሌ በሻእቢያ ተፈቅዶለት
በተሓህት ውስጥ እንዲታገል ደደቢት በረሃ ከነ አረጋዊ በርሄ ተቀላቅሎ የተሓህት ተዋጊም ሆነ።
የሙሴ ያልተጠበቀ የአቋም ለውጥ
ሙሴ የሁሉንም ታጋይ ባህሪ ጥናት ለመውሰድ ጥቂት ወራቶች ቢወስድበትም የተሓህት ታጋይ ለምንም ለውጥ ዝግጁ
መሆኑን አወቀ። የእነ ገሰሰው አየለ አግአዚ ወዘተ. በተሓህት ፕሮግራም ላይ ያላቸውን አመለካከት አወቀ። ከአስገደ ገ/ሥላሴም
ጋር ጥሩ ግንኙነት መሰረተ። ታጋዩና ሙሴ ውህደት ፈጠሩ፣ ወደዱትም። በዲማ ኮንፈረንስ ለአመራር ብቁ ነው ብሎ ታጋዩ ወደ
ተሓህት መሪነት አደረሰው። ም/ወታደራዊ አዛዥም ሆነ። ይህ በወቅቱ ለነበረው ታጋይ ታላቅ ድል ነበር።
ሙሴ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጸረ-ሻእቢያ አቋም ያዘ። ሻእቢያ ጸረ-ሕዝብ፣ በተለይ ደግሞ ጸረ-ትግራይ ሕዝብ ነው።
ሻእቢያ የኔ ጠላት የትግራይ ሕዝብ ነው የሚል አክራሪ ድርጅት ነው፤ የተሓህት አመራር ደግሞ ሻእቢያን እንደፈጣሪ እየቆጠሩ
ጠዋት ማታ እግሩን ይስማሉ በማለት በተጠናከረ መልኩ ጸረ-ሻእቢያ ቅስቀሳውን በማቀነባበር በስፋት ቀጠለበት፣ ታጋዩም
አብሮት ቆመ።
አመራሩም ሙሴ ከመትክል የትግላችን አጋር ሻእቢያ እየለያየን ነው በማለት ሲናገሩ፣ በእንጻሩ ሙሴ ነፃ ሁኑ፣ አሽከር
አትሁኑ፣ የሻእቢያ አገልጋይና ታዛዥ አትሁኑ ነው የምላችሁ ሲላቸው የተሓህት አመራር ሙሴን ማውገዙን ቢቀጥሉበተም
በታጋዩ ተቀባይነት አላገኘም። ይበልጡኑ የሙሴ ተቀባይነት ከፍ አለ። በዚህ ምክንያት አመራሩ ሙሴ መሃሪ ተክሌ
የሚጠፋበትን መንገድ ማጠንጠን ጀመሩ። የግድያ ሴራ በስብሃት ነጋ የሚመራው የመለስ ዜናዊ፣ አባይ ፀሃየና ሥዩም መስፍን
በመተባባር እቅዱን አወጡ። ተግባር ላይ የሚያውሉት ደግሞ ስየ አብርሃና ጻድቃን ገብረተንሳይ ሲሆኑ ግድያውን የሚፈጸመው
በርሄ ሃጎስ ሆኖ ተመረጠ። በርሄ ሃጎስ አሁን ካናዳ፣ ኦቶዋ በመኖር ላይ ያለ ግለሰብ ነው። በላፈው ግንቦት 2005 አማራው
የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው እያለ አማራውን ኢትዮጵያዊ ሲሰድበውና ሲያንቋሽሸው የነበረ ሰው ነው። በገዘ ተጋሩ ፓል ቶክ።
ስየ አብርሃ በሚመራት ሃይል 41 አመቺ ጊዜ ሲጠብቅበት የነበረው ሙሴ ጻድቃን ገብረተንሳይ በኮሚሳርነት
የሚመራት ጋንታ በርሄ ሃጎስ የነበረባት ጋንታ በመጠባበቅ ላይ የነበሩት ሁለቱ በአጋጣሚ ሓምሌ መጨረሻ 1968 ከሽራሮ ወጣ
ብላ የምትገኘው ቁሽት ጫአ መስከበት ስየ አብርሃ ም/ሃይል መሪ በያዛት ሃይል በኢዲዩ ላይ ጥቃት እንደተጀመረ፣ ሙሴ
ታጋዮቹን እያስተባበረ ጦርነቱን በመምራት ላይ እንዳለ በስተኋላው የነበሩት ጻድቃን ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ውጊያው እየበረታ
ሲሄድ በርሄ ሃጎስ አነጣጥሮ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌን ግራ እጁ ላይ ትከሻውን ጨምሮ ቆርጦ ጣለው። ዞር ሲል ጻድቃን
ገ/ተንሳይና በርሄ ሃጎስ ከኋላ ሆነው እንደመቱት አወቀ። አይን ለአይንም ተገጣጠሙ። በርሄ ሃጎስ ሙሴን የመታበትን ደምመላሽ
ጠመንጃም ለጻድቃን ሲሰጠው አየው። ክፉኛ የቆሰልውን ሙሴን በቃሬዛ ተሸክመውት ሲሄዱ የነበሩትን ታጋዮች ሁሉ
የነገራቸው እኔ በኢዲዩ ጥይት አልተመታሁም፤ የመቱኝና የገደሉኝ ጻድቃን ገብረተንሳይና በርሄ ሃጎስ ናቸው እያለ ሲናገር
እንደነበረና አንድ ሰዓት ተኩል ያህል ቆይቶ ከዚች ዓለም እንደተሰናበተ ይናገራሉ። አዲ ፀጸር ቀሽት ወስጥ ተቀበረ። ወዲያው
በርሄ ሃጎስ ትንሽ ገንዘብ ተቀብሎ ሱዳን ገባ። ሙሴ የተናገረውን ኑዛዜ አውአሎም ወልዱ ሰምቶታል፣ ምስክርነቱን ይስጥበት።
4. አጽብሃ ዳኘው
አጽብሃ ዳኘው፣ የበረሃ ስሙ ሸዊት ነው። በቀ. ኃ. ሥ. ዩኒቨርሲቲ በሂሳብ ትምህርት የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነበር። ማገብት
እንደተመሰረተም ከወራት በኋላ አባል ሆነ። መጋቢት 1967 ከተሓህት ጋረ ተቀላቀለ። ከጊዜ በኋላም በተሓህትን ፕሮግራም
አደገኛነት ሂስ መሰንዘር በመጀመር ፕሮግራሙ ጸረ-ሃገር ሉአላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና በታኝ፣ ሕዝብን እርስ በርሱ
ለግጭት የሚዳርግ በመሆኑ አዲስ ፕሮግራም ማርቀቅ ይጠበቅብናል በማለት ከነ ገሰሰው አየለ - አግአዚ ገሰሰ ጋር በአቋም
ተስማሙ። በሚሰነዝረው ሃሳብ በታጋዩ ተወዳጅ ሆነ፣ በድፍረቱም ምክንያት ስሙ ገነነ። በዚህ መልክ ሲቀጥል፣ ሱዳን፣
ካርቱም ለሥራ ሂዶ በነበረበት ወቅት መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ በአስቸኳይ አስጠርተው ሱዳን ባለህበት ጊዜ ጾታዊ ግንኙነት
ፈጽመሃል በማለት በውሸት ከሰው 06-ሃለዋ ወያነ አስገብተው አሰሩት። አረጋዊ በርሄ ይህን እንደሰማ ከነበረበት ቦታ በቶሎ
ደርሶ ከእሰር አስወጥቶ ሥራውን እንዲቀጥል አደረገ። ሐምሌ 1968 አመራሩ ወደ አምስት ስለወረደ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ
ገሰሰ፣ ሙሴ (መሃሪ) ተክሌ በተሓህት አመራር ስለተገደሉ፤ በአመራር ላይ የቀሩት አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርአጽዮን፣ ስብሃት
ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃየ ብቻ ነበሩ። ከላይ በጠቀስኩት ወርና ዓ.ም. አምስቱ አመራር ተሰብስበው የሚከተሉት ወደ
አመራሩ ገቡ። መለስ ዜናዊ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ አውአሎም ወልዱና ስየ አብርሃ ወደ ተሓህት አመራር ወጡ።
አጽብሃ ዳኘው ለስልጣን እና ሹመት እጁን አልሰጠም። የተሓህት ፕሮግራም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ፣ አውዳሚና
በታኝ ስለሆነ መወገድ አለበት፣ ተሓህት ጠባብና ዘረኛ ስለሆነ ትግላችን ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት። ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት
ናት፣ አማራ ጠላት ነው ማለት ሕገወጥ የፖለቲካ አቋም ነው በማለት ተከራከረ። ክርክሩን እገላ ወረዳ ስብኦ ቁሽት ሲከራከሩ
ስብሃት፣ መለስና አባይ ተናደዱ። ሆያ አዲጨጓር የሚገኘው 06-ሃለዋ ወያነ ሃላፊዎች፣ ሙሉጌታ አለምሰገድና ክንፈ
ገ/መድህንን አስጠርተው ዛሬውኑ አጽብሃ ዳኘውን እና ጓደኛው መኮንን በዛብህን ግደሏቸው። ስብሃት ነጋ ጸረ-ተሓህት ናቸው
የሚል ወረቀት ጽፎና አዘጋጅቶ ሰጣቸው። እነአጽብሃ መኮንን የተሰጣቸውን ወረቀት ይዘው በመሄድ ሆያ ላይ ጉድጓድ ተቆፍሮ
በጥይት ተደብድበው በመገደል ከዚህ ዓለም ተሰናበቱ።
አረጋዊ በርሄ የአጽብሃ ዳኘውና የመኮንን በዛብህን መታሰር ሰምቶ ከነበረበት ተምቤን አካባቢ ሌት ተቀን ተጉዞ
ሕይወታቸውን ለማዳን ያደረገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። ሆያ እንደገባ እነ አጽብሃ ወደኔ አምጡልኝ፣ ተፈትተዋል፣
ጥፋት የለባቸውም ሲል ከሙሉጌታ አለምሰገድ ጋር ያገኘው መልስ፣ ስብሃትና መለስ አባይ ሆያ እንደገቡ ሳይውሉ ሳያድሩ
ይገደሉ ብለው ስላዘዙን ገደልናቸው አለው። የትእዛዝ ወረቀቱም የኸው ብሎ ሰጠው። አረጋዊ በርሄ ይህንን አሳዛኝ ግድያ
ሰምቶ እነስብሃት ነጋ ወደሚገኙበት እገላ ሰብኦ፣ ቁሽት በመሄድ ተገናኛቸው። ነገር ግን ምንም አላደረገም። የተሓህት
ሊቀመንበር እንደመሆኑ ለምን ይሆን በነስብሃት ነጋ፣ መለሰ ዜናዊ ወዘተ. ላይ እርምጃ ሳይወሰድ የቀረው የሚል ጥያቄ ተነስቶ
ነበር። አሁንም እየተነሳ ነው። መልስ መስጠት ያለበትም የወቅቱ የተሓህት ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ ነው።
5. ዶ/ር አታክልት ቀጸላ
ዶ/ር ራስወርቅ ቀፀላ የበርሃ ስሙ ዶ/ር አታክልት ቀፀላ የህክምና ባለሙያ ነው። ቀደም ሲል ከግንባር ገድሊ ሓርነት
ትግራይ (ግገሓት) አባል ሆኖ በረሃ ሲንቀሳቀስ የግገሓት የትግል ስልት አደገኛ ነው በማለት በሰኔ 1967 ከተሓህት ተቀላቀለ።
በተሓህትም ብዙ ስህተቶች እንደሚኖር አልተጠራጠርም ነበር። ነገር ግን ስህተቱን ለማስተካከልና ለማረም ብዙ ታጋዮች
ይኖራሉ የሚለው እምነቱን እንደያዘ ቀስ በቀስ ፕሮግራሙን የማየት እድል ገጠመው። ከነገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ
መሃሪና አጽብሃ ዳኘው ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለፈጠረ፣ እነዚህ ሁሉ የተሓህት ፕሮግራምን የሚቃወሙ ናቸው። አጽብሃ ዳኛው
በነስብሃትና መለስ እንደተገደለም ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በአጽብሃ ፈንታ የተሓህት አመራሩን ጨበጠ። ግን እጁን አልሰጠም።
ዶ/ር አታክለት በፕሮግራሙ መጥፎና አደገኛ፣ ሃገርንና ሕዝብን የሚበታተን ነው ብሎ በማመን ከተለያዩ አመራር ጋር
ሲነጋገርበት እንደነበር ይታወቃል። ከግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ መግባባት እንደነበረውም ራሱ የተናገረው ነው።
ከመለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ከሌሎቹ አመራር ጋር ግን የሻከረ ግንኙነት እንደነበረው ታጋዩ ሁሉ ያውቃል።
ሌላው ቀርቶ ስብሃት ነጋ በየቦታው በሄደበት “የኢትዮጵያ ባንዲራ ራሱ ላይ ጠምጥሞ ዶ/ር አታክለት ቀጸላ በድርጅታችን
ተሓህት ችግር እየፈጠረብን ነው” በማለት በየቦታው መናገሩን እኔ ራሴ አስታውሳለሁ። ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በ1ኛው ጉባኤ
የተሓህት የአመራር ምርጫ በከፍተኛ የድምጽ ቁጥር ተመርጦ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ም/ወታደራዊ አዛዥ ሆነ። የነስብሃት ነጋ
የስም ማጥፋት ዘመቻ አልተሳካም። በነገሩም ተደናግጠው ነበር።
ይህ በየካቲት 5 ቀን 1971 በአዲነብር ኡድ ወረዳ ማይ አባይ በተባለው ቦታ የተካሄደው 1ኛ ጉባኤ፣ የተሓህት ውርስ
ስብሃት ነጋ ሊቀመንበር የሆነበት ጉባኤ ወርሱን የተረከቡት ስብሃት ነጋና ህወሓት ናቸው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀደም ብሎ
የመጣው ፋሽስት ቡድን እውቅና ያገኘበት ጊዜ ነበር።
እነስብሃት ነጋ ዶ/ር አታክልትን ለማጥፋት ብዙ ጥናት በማካሄድ የተመቸ ጊዜ አገኙ። ግንቦት 1971 የውጊያው ዓይነት
ጥቃት በኢትዮጵያ ሰራዊት፣ የውጊያው ቦታ ተምቤን፣ አብይ አዲ ጎንባስ ሞሞና ነበር። የህወሓት ሰራዊትም ይዘጋጅበት ነበር።
ቀኑ ደርሶ ሁሉም የህወሓት ሰራዊት ወደ ውጊያው ቀጠና አመራ። ውጊያው የሚጀምርበት ጠዋት በስተምእራብ በኩል
ከውጊያው ቦታ በግምት በ10 ኪ.ሜ. ርቀት ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና ሳሞራ የኑስ፣ የታጠቀው መሳሪያ ሲሞኖቭ ባለመነጽር
ሆነው ዶ/ር አታክልት ቀጸላን የህወሓት ሊቀመንበር ስብሃት ነጋ ስለጦርነቱ ለመነጋገር ብሎ አስጠራው። እነሱም ለግድያው
በመዘጋጀት በጠሩት መሰረት ደረሰ። ፊታቸውን ወደ ውጊያው ቀጠና ምስራቅ በማዞር ቀስ እያሉ መንገዱን ቀጠሉ። እኔና ዶ/ር
አባዲ መስፍን ከነስብሃት ነጋ ፊት 500 ሜትር ያህል በሚገመት ርቀት ወደ ጦርነቱ ቀጠና እንጓዝ ነበር። ዶ/ር አታክለት ቀጸላ
ስብሃት ነጋ እንዳሰናበተው በፍጥነት እየተጓዘ ሳለ ከ250-300 ሜትር ርቀት ከነሱ መካከል ሳሞራ የኑስ በያዘው ሲሞኖቭ
ባለመነጽር ጠመንጃ አስተካክሎና አነጣጥሮ በመተኮስ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ የጀርባው አከርካሬ ላይ መታው። ‘Special
Column’ ተመትቶ ሲወድቅ አዩት። አባይ ፀሃየ በፍጥነት ሩጦ ወደኛ ተጠግቶ አባዲ፣ አባዲ፣ ብሎ በመጥራት በእጅ ምልክት ኑ
ሲለን ሄደን አገኘነው። ዶ/ር አታክልት ስለሞተ ቅበሩት፣ ነገር ግን ለማንም እንዳትናገሩ ብሎ ተመልሶ ከነስብሃት ነጋ ጋር
ተቀላቀለ። በኋላም ሶስቱም ተያይዘው ሲሄዱ አየናቸው።
ዶ/ር አባዲ መስፍን እና እኔ ጉድጓድ ስንቆፍር እሱ እንደ ባለሙያነቱ ሬሳውን መመርመር ጀምረ። ጀርባው ላይ የመታችን
ጥይት ሰውነቱን ከፍቶ አወጣት። በሲሞኖቭ ጥይት ሳሞራ የኑስ ገደለው ብሎ እምባውን መግታት አቃተው። ጥይቷን በወርቀት
ጠቅልሎ ያዛት። እኔና ዶ/ር አታክልት አፈርና ድንጋይ በመጫን ቀብረን ተሰናብተን ወደ ጦርነቱ ተመለስን። ዶ/ር አታክልት
ሞቶ ይቀበር እንጂ ታሪኩ ህያው ህኖ ይኖራል። እነ ስብሃት ነጋ መለስ ዜናዊ ወዘተ. በንጹሃን ደም መታጠብ የጀመሩት ገና
ከጥዋቱ ነበር። እነዚህ ጀግኖች በሞት ቢለዩንም ድምጻቸውና የተቀደሰ ተቃውማቸው፣ የህወሓት ፕሮግራም ይውደም ያሉት
ድምጻቸው ግን በታጋዩ ዘንድ ተሰራጨ። በዚህም ምክንያት ብዙ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን በማንሳት የተሓህት- ህወሓት
አመራርን አስጨነቁት። አመራሩ ተቃውሞውን አጠፍ በማድረግ በድርጅታችን ሕንፍሽፍሽ ተነሳ ብሎ ብዙ ታጋዮችን እና
ንጹሃንን መጨፍጨፊያ ምክንያት አደረገው። የዲሞክራሲ ጥያቄው ተዋንያኖች፤ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ፣
አጽብሃ ዳኘውና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ ያቀጣጠሉት ነው። የህወሓት ፋሽስትና አምባገነን መሪዎች የመጥፊያቸው ጊዜ እየቀረበ
ነው፣ ተያይዘው በሕዝብ ሃይል ለፍርድ ይቀርባሉ።
ግደይ ዘርአጽዮን
ግደይ ዘርአጽዮን ከአረጋዊ በርሄ ጋር በመሆን የማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡ ህወሓትን
የፈጠሩት ሁለቱ ናቸው። ሌላ የለም። ግደይ የተፈጸሙ ጥፋትም ሆነ ወንጀል ካሉ ከነበሩት አመራር እኩል ተጠያቂ ነኝ በማለት
በግልጽ ተናግሯል። በህወሓት አመራር አስከቆየሁበት በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ነኝ። ነጻ ነኝ ብሎ ራሱን ያላገለለ በመሆኑ
ያስመሰግነዋል።
ግደይ ዘርአጽዮን የተሓህት-ሀወሓት ከፍተኛ አመራር የድርጅቱ ም/ሊቀመንበር በነበረበት ጊዜ አመራሩ የሚፈጽመውን
ግድያና ሽብር አውግዞ ከ1969 መጨራሻ ራሱ ነፃ በመሆን የስንት ታጋይና ሰላማዊ ዜጋ ሕይወት ያዳነ ነው። ግን ብቻውን
በመሆኑ የህወሓትን አመራር ክሚፈጽሙት ወንጀል ሊያቆማቸው አልቻለም። በሰላማዊው ዜጋና በታጋዩ ግን ሰፊ የታማኝነት፣
አጋርነትና ክብር የተሰጠው ግደይ ዘርአይጽዮን ነው። ግደይ የታጋዩ ጥብቅ ጓደኛ ሆነ፣ ተወደደ። ማንኛውም ታጋይ ችግር
ሲገጥመው ለግደይ ያናገራል። ግደይም ችግሩን ይፈታለታል። ግደይ ራሱም የታጋዩን እና የሕዝቡን ፍቅር ጣእሙን ስላወቀው
ሁልጊዜም ደስተኛ ነበር።
መለስ ዜናዊ የሚመራውን ማርክሲስት ሌሊኒስት ሊግ ትግራይ ለማቋቋም የሃላፊነቱ ተሰጠው። በ1ኛው ጉባኤ
በኮሚሽን ደረጃ እንደተቋቋመ በአቋም ልዩነታቸው እነ መለስ ዜናዊ፣ ግደይን እንደጠላት ማየት፣ ግደይ ዘርአጽዮንም በአቋሙ
ስለጸና መፋጠጥ የጀመርንበት ጊዜ ነበር። የነበራቸው ልዩነትም የማይፈታ ሆነ። ሁለቱም በተጻራሪ መንገድ ቀጠሉበት።
በእነ መለስ ዜናዊና አበሮቹ የሚያቀርቡት፤
ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ አብዮት የአብዮቱ መሰረታዊ ሃይሎች ድሃ ገበሬ፤ ላብ አደሩ ሲሆኑ፣ እነዚህን ካሰባሰብን
የአብዮቱ ትግል ዓላማው እና ግቡን ይመታል። ሃብታም ገበሬ ከሁለት ጥንድ በሬዎች በላይ ያሉት ሃብታም ገበሬ
ስለሆነ በማርክስ ሌኒናዊ ሳይንስ ሃብታም ገበሬ የትግላችን ጠላት ነው፣ በማለት አስረግጠው ተናግረዋል።
ሃብታም ገበሬ መደምሰስ መጥፋት አለበት። ለምን የማርክስ ሌኒናዊ ጠላት ሃብታም ገበሬ ነው። መለስ ዜናዊ
ይህንን በወይን መጽሔት እያተመ ታጋዩን ያስተምርበት ነበር።
ግደይ ዘርአጽዮን
ሃብታም ገበሬ የማርክሲዝም ሌኒኒዝም ጠላት አይደለም። አሁንም በህወሓት የሚመሰረተው ማርክሲስት ፓርቲ
ሃብታም ገበሬ ጠላት ሳይሆን የትግል አጋራችን እና ወዳጃችን ነው ተብሎ በትግሉ እንደ ወዳጅ መታወቅ
አለበት። ከሁለት ጥንድ በሬ በላይ ያለው ሃብታም ገበሬ ነው ስለሆነም ጠላት ነው እያላችሁ ምክንያት በመፍጠር
ያምታጠቁት የትግራይ ሕብረተሰብ ፍጹም ጸረ-ሕዝብ ነው። ንብረቱ ሁሉ እየተወረሰ ለህወሓት ገቢ ሲደረግ
ለተገደለው ሕዝብና ለፈረሰው ቤት ተጠያቂ ናቸው። ይህ የሃሳብ ልዩነት በነመለስ ዜናዊ ቡድን እና በግደይ
ዘርአጽዮን መካክል ሰፍቶ በመውጣት ለዓመታት ቀጠለ።
መለስ ዜናዊ
በእኛና በግደይ ዘርአጽዮን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ። አብረን መታገልም አንችልም። ግደይ ዘርአጽዮን ሃብታም
ገበሬ የማርክስ ሌኒናዊ የትግል አጋር ነው፣ ጠላት አይደለም ብሎ ያምናል። ይህ የሚያመለክተው ግደይ
ዘርአጽዮን ጸረ-ማርክስ-ሌሊናዊና በራዥ ነው ሲል በያዘው አቋም የማይነቃነቀው ግደይ፣ አንተና ጓደኞችህ ናችሁ
በራዥና ከላሽ ነህ ስለአለው ንትርኩ ሰማይ ወጣ። ግደይ ዘርአጽዮን አሁንም በዚህ ጉባኤ አቀርበዋለሁ። ሃብታም
ገበሬ የትግላችን አጋርና ወዳጅ መሆኑ ሙሉ እምነቴ ነው። ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ብሎ ማስቀመጥ ጸረ-ሕዝብ
ነው። እነ መለስ ዜናዊ ሃብታም ገበሬ ጠላት ነው ማለታቸው ማንነታቸውን በትክክል ይገልጸዋል።
2. በማለሊት ጉባኤ አመራሩ ዳግም ለሁለት መሰንጠቅ
የማለሊት ጉባኤ በዚህና በሌላውም ጸረ-ዲሞክራሲ ሲካሄድ ሰንብቶ ሐምሌ 21 ቀን 1977 ምርጫው ደረሰ። ይህ ምርጫ
ሕገወጥነትን የተከተለና ሁለት ዋና ዋና ዓላማ የያዘ ነበር።
1. የሥልጣን ሽኩቻ ዋና ዓላማው ነበር፣
2. በዚህ የሥልጣን ሽኩቻ ማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠው በጸረ-ዲሞክራሲና በጸረ-ሕዝብነቱ
አብረው እየመሩት የመጡት አንጋፋ አመራሮች ለማባረር በድርቅ የተጠቃው መከረኛው የትግራይ ሕዝብ እያለቀ
ከአፉ ነጥቀው በነስብሃት ነጋ፣ በስንት ሚሊዮን ብር የተዘጋጀው ማለሊት ስልጣናቸውን ለማደላደል ነበር።
ምርጫው
በሙሉ ድምጽ የመራጭ ብዛት 250 ነበር። ምርጫው በምስጢር ሆኖ በወረቀት የምትፈልገውን መምረጥም ነበር።
ምርጫው ተካሄደ። ድምጹ ተቆጠረ። በዝርዝር ተነገረ። 1ኛ. ግደይ ዘርአጽዮን፣ ያገኘው ድምጽ 247፤ 2ኛ. አረጋዊ በርሄ፣ ያገኘ
ድምጽ 245፤ 3ኛ. ሃየሎም አርአያ፣ ያገኘው ድምጽ፣ 236፤ 4ኛ. ስየ አብርሃ ወዘተ. እያለ የድምጽ ቆጠራው ቀጠለ። ወደ
መጨረሻው ድምጽ ቆጠራ ደረሰ። ይህንን የሚገልጸው ህብሩ ገብረኪዳን ነበር። በጥቁር ሰሌዳ ላይ የተመረጡት ያገኙትን
ድምጽ እየጻፈ ሲገልጽ የሚይዘው የሚጨብጠውን አጣ። የጉባኤው ተሳታፊ ቀጥል ብሎ አፋጠጠው። ላብ ፊቱ ላይ እየወረደ
ቀጠለ። 24ኛ. መለስ ዜናዊ፣ ያገኘው ድምጽ 130፤ 25ኛ. ስብሃት ነጋ፣ ያገኘው ድምጽ 127 በማለት የ25ቱን የማለሊት
ተመራጮች የማለሊት ማ/ኮሚቴ ብሎ በጥቁር ሰሌዳው ላይ በማስቀመጥ ተመልሶ ወደ ቦታው ሄዶ ተቀመጠ። መለስ ዜናዊ
ራሱን ደፋ። ፊቱ የተጠበሰ ስጋ መሰለ። ስብሃት ነጋ ደግሞ አዳራሹን ለቆ ወጣ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የጉባኤው ሊቀመንበር
የነበረው ሥዩም መስፍን ከሰዓት በኋላ በ11 ሰዓት እዚህ እንገናኝ ብሎ ጉባኤተኛውን አሰናበተ። በዚህ ዓይነት ነበር ታጋዩ እነ
መለስ ዜናዊን መሬት ውስጥ የቀበራቸው። ነገር ግን ተመልሰው ታጋዩን አጠቁት። ብዙ ነባር ታጋይ በእነ መለስ፣ ስብሃት ወዘተ.
ተገደለ፣ ከሞት የተረፈውም ሸሸ።
ልክ በ11 ሰዓት ጉባኤው ተሰየመ። በስብሃት ነጋ አመራር የተመረጡት ማ/ኮሚቴ ማለሊት አሰባስቦ ሹመትና ሥልጣን
እየሰጠ እንዲተባበሩት አደረገ። ከአረጋዊ በርሄ ስልጣን አገኛለሁ ብሎ ስየ አብርሃ በከፍተኛ ድምጽ የመረጥነው በግንባር
ቀደምትምነት ክህደት ከነ ስብሃት ጋር ተሰለፈ። በዚሁ ጉባኤ የመጀመሪያው ተናጋሪ መለስ ዜናዊ፤ ቀጥሎ ስብሃት ነጋ፤ ቀጥሎ
ስየ አብርሃ በመተባበር ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ከህወሓት ከማለሊት ተባረዋል ተባለ። ታጋዩ ተደናገጠ፣ አጉረመረመ
አለቀሰ። ከአመራሩ ጻድቃን፣ ሥዩም ገብሩ፣ ወዘተ. በየተራ በሁለት አንጋፋ አመራር አሰነዋሪ የሆነ ስድብ አወረዱባቸው።
የተባረሩትም ክኛ ጋር ተቀላቀሉ። እነ መለስ ዜናዊ ተደላድለው በህወሓት-ማለሊት ኮርቻ ላይ ተቀመጡ። የህወሓት ሁለተኛ
መሰንጠቅ ይህ ነው።
የስየ አብርሃ ክህደት
ስየ አብርሃ ደፋርና ጎበዝ እንደነበረ አውቃለሁ። ከሃዲነቱን ግን አላውቅም ነበር። በ1969 የሕንፍሽፍሽ ዋና ተዋናይ
ነበር ተብሎ በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን እስከ 1977 ድረስ በዓይነ ቁራኛ ሲከታተሉት እንደነበር አውቃለሁ። ከህወሓት
ታጋዮች ደግሞ ለሰየ አብርሃ ጥብቅና እና ድጋፍ አልተለየውም ነበር። ከዚህም የተነሳ ነው በማለሊት ጉባኤ በከፍተኛ ድምጽ
የመረጥነው። ነገር ግን ከሃዲውና እምነተ ቢሱ ስየ አብርሃ የሥልጣን ጥማቱን ለማርካት የህወሓት-ማለሊት ሙሉ ወታደራዊ
አዛዥ ለመሆን ግደይ ዘርአጽዮንን እና አረጋዊ በርሄን በውሸትና በስም ማጥፋት ደበደባቸው። ሲጠብቀውና ሲንከባከበው
የቆየውን ታጋይ ለምን መለስ ዜናዊን እና ስብሃት ነጋን በአነስተኛ ደምጽ መረጣችሁ ብሎ ነባሩን ታጋይ እንደ እባብ እራስ
እራሱን ቀጠቀጠው። በየቦታው እየሄደ አጠፋው።
በህዳር 1980 የህወሓት ታጋይ ባነሳው ተቃውሞ ኤርትራም ሆነ ሌላ ቦታ ሂደን አንዋጋም። ትግራይን ከአማራው ቅኝ
አገዛዝ ነፃ አውጥተን የትግራይን መንግሥት መመስረት ነው እንጂ ከዚህ ውጭ የምናውቀው ነገር የለም። ኤርትራ ሄደው በረሃ
የበላቸውና ያለቁት የትግራይ ወጣት ሴትና ወንድ እስከ አሁን 130,000 ደርሷል። የኛ ድርጅት ህወሓት ከየት ወረዳና ዞን መጡ
የሚል ዝርዝር ስማቸው እንኳን አያውቀውም። እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ከብት እየታፈስን ሂደን ሞተን ቀረን። አሁንም
ትግራይን ነፃ እናወጣለን እንጂ ሌላ ቦታ አንሄድም አለ። በዚህ ጊዜ እነ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ስየ አብርሃን አነጋግረው
በ36,000 ታጋይ ላይ ሞት ፈረዱበት። ይህ ሁሉ ታጋይ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። በዚህ ግድያ የተሰማሩት መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት
ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሃየሎም አርአያ፣ ሳሞራ የኑስ፣ ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ አበበ ተክለሃይማኖት፣ ስየ አብርሃ፣ ክንፈ ገብረመድህን፣
አርከበ እቁባይ፣ ገብሩ አስራት፣ ዓረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ ወዘተ. ነበሩ።
የተግባሩ አፈጻጸም በስየ አብርሃና በክንፈ ገ/መድህን ትእዛዝና አመራር ነበር። ገዳዮቹ፣ ብስራት አማረ፣ ሃሰን ሽፋ፣
ወልደሥላሴ፣ ዘአማኑኤል ለገሰ (ወዲ ሻምበል)፣ ተስፋዬ ጡሩራ (መርሳ)፣ ተስፋዬ አፈርሰው (አጽብሃ) ወዘተ. ነበሩ። ከ200
በላይ የሃለዋ ወያነ (06) ታጋዮችን በማሰለፍ ታጋዩን ገደሉት። የሃውዜን ጥቃትም በደርግ ሚግ 21-23-27 በእጅ አዙር
ያስደበድቡት እነ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ. ከዚህ ተነስተው ነው።
ስየ አብርሃ ይህንን ክህደትና አረመኔያዊ ተግባር ከመፈጸሙ ትንሽ ቀደም ብሎ ከነመለስ፣ ስብሃትና አባይ ፀሃየ ጋር
ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ተጧጡፎ ቀጠለ። ስየ አብርሃ ሁሉንም ያጣ ብቻውን ሆኖ እየተናገረ መሄድ ጀመረ። ታጋዩ ሁሉ
ጠላው፣ ራቀው። የፖሊት ቢሮ አባላት በየወሩ በስብሃት ነጋ የተፈቀደውን የኪስ ገንዘብ ብር 1,000 አልቀበልም አለ። ተወልደ፣
ገብሩ አስራትም እንደዚሁ አንቀበልም ብለዋል። ስየ አብርሃ በፈጸመው ክህደት እስከ ዛሬ በህወሓት ታጋይ እየተወገዘ ነው።
3. የህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ወቅቱ ጥቅምት 1980 ነበር። የህወሓት ማ/ኮሚቴን ጨምሮ የማለሊት ማ/ኮሚቴ በአንድነት የተጠራ ስብሰባ ነበር።
በዚህ ጊዜ የተነሱት ጥያቄዎች የስልጣን ሽኩቻ ሳይሆን የህወሓት-ማለሊት ፖሊት ቢሮ ዱሮ ከነበረውና ከተፈጸሙት ስህተቶች
ያልተማረ፣ ብዙ ስህተት እየፈጸመ ነው። ከዚህ ስህተቱ መማር አለበት ወዘተ. በማለት የቀረበው ጥያቄ አነታራኪ ሆኖ
በመቀመጡ፣ ስብሃት ነጋ በሚመራው ስብሰባ የቀረቡትን ጥያቄዎች በሙሉ ውድቅ አደረጋቸው። መለስ ዜናዊም የስብሃት ነጋን
ሃሳብ ደገፈ። ጥያቄቆቹን ያነሱት በ1975 በ2ኛው ጉባኤ የተመረጡት የህወሓት አመራር ናቸው። እነሱም፤
1. ክብሮም ገ/ማርያም የህወሓት ማ/ኮሚቴና የሰራዊቱ የሎጂስቲክ ዋና ሃላፊ የነበረ፣
2. ኃ/ሥላሴ መስፍን፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴ፣ ጠቅላላ የህወሓት ክፍለ ጦሮች የኮሚሳሮች የበላይ ሃላፊና ተቆጣጣሪ የነበረ፣
3. ሰአረ ገብረጻድቅ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ጠቅላላ የህወሓት ማ/ኮሚቴና ፖሊት ቢሮ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበረ፣
4. ተክሉ ሃዋዝ፣ የህወሓት ማ/ኮሚቴና የቀድሞ የድርጅቱ ዋና የደህንነት ሃላፊ የነበረ ናቸው።
ከላይ የተጠቀሱት አራቱ አመራር ባቀረቡት ሃሳብ አፈንጋጩ የእነ ግደይ ዘርአጽዮን እና አረጋዊ በርሄ ደጋፊዎች ተብለው
ተወነጀሉ። ወንጃዮቹ፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣ አውአሎም ወልዱ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ገብሩ አስራት፣
አርከበ እቁባይ ናቸው፡ እነዚህ የፖሊት ቢሮ አባላት ተሰብሰበው ተወንጃዮቹን በማስጠራት እርማት እንዲያደርጉ ወሰኑ።
በቀረቡበት ጊዜም፣ ያቀረባችሁት ሃሳብ ጸረ-ህወሓት-ማለሊት በመሆኑ፤ ከአመራርና ከሃላፊነታችሁ ተወግዳችሁ በተራ ታጋይነት
ቀጥሉ ተብለው በስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ተሰናበቱ። ይህ ወቅት ህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ የተሰነጠቀበት ወቅት ነበር።
5. የህወሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ይህ የህዋሓት ለአራተኛ ጊዜ መሰንጠቅ በ1993 የተፈጠረው ነው። ዋናው ዓላማ የስልጣን ሽኩቻ ነበር። ሌላው አንዱ
ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ሆኖ ሌላው ደግሞ ጸረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተፈጠረ መበታተን አይደለም። በእነ ስየ አብርሃ የሚመራው
ቡድንም ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ሕዝብ ነው። ሃገራችን ኢትዮጵያን ያፈረሱ፣ የቀይ ባህር የባህር በሯን የሸጡና ያስነጠቁ፣ የዘር
ማጥፋት እልቂት የፈጸሙ፣ ሕዝብን ለድህነት፣ ለችግር፣ ለበሽታና ለስደት የዳረጉ እነ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ ስየ አብርሃ፣
ተወልደ ወ/ማርያም፣ ገብሩ አስራት ወዘተ. ተባብረው በሕዝብና በሃገር ከባድ ወንጀል የፈጸሙ ናቸው። በሁለት የተሰነጠቁበት
ቀንደኛ ምክንያት ደግሞ የስልጣን ሽኩቻ ነው። ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
6. የህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ መሰንጠቅ
ህወሓት ኢትዮጵያን ወሮ በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረ በኋላ መሪው መለስ ዜናዊና የህወሓት አመራር ሁሉም በሃገራችን
ከፍተኛውን የሥልጣን ወንበር ላይ ተደላድለው በመቀመጥ ኢትዮጵያን ለ21 ዓመታት በገዙበት ጊዜ በሕዝብና በሃገር ከፍተኛ
ወንጀል በመፈጸም የኢትዮጵያን ሃብት ዘርፈዋል። ሕዝብን ያደኸየውን ስርዓት የመሰረተው መለስ ዜናዊ ሰኔ 7 ቀን 2004 ከዚህ
ዓለም በሞት ተቀጠፈ። ብስራት አብሳሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ መከታና መመኪያ እንዲሁም ዓይን እና ጆሮ ኢሳት በጥዋቱ
የመለስ ዜናዊን ሞት ነገረን። ለወዳጆቹ ሃዘን ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የእፎይታ ቀን ሆነ። አረመኔው መሪ መለስ ዜናዊ ከዚህ
ዓለም በሞት ተቀጥፎ መኖሪያውን ሲኦል አደረገ። በዚህም ምክያት ህወሓት ለአምስተኛ ጊዜ ተሰነጠቀ። ከላይ እስከ ታች
በቅራኔና በሥልጣን ሽኩቻ እንደ ዱባ ተፍረከረከ።
1. የተህሓት ወግ አጥባቂ 2, ተንኳሽ 3. የመለስ ዜናዊ ውርስ ተረካቢ
(Old guard) (Catalyst) (Legacy)
ሀ. ስብሃት ነጋ ለ. ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሐ. አባይ ወልዱ
ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ጌታቸው አሰፋ ሳሞራ የኑስ
አርከበ እቁባይ ቴዎድሮስ አድሃኖም በየነ ምክሩ
ጸጋይ በርሄ አለም ገ/ዋህድ ቴዎድሮስ ሃጎስ
አባዲ ዘሞ ክንደያ ገ/ሕይወት ብርሃነ ማረት
ትርፉ ኪ/ማርያም ወዘተ.
እነ ስብሃት ነጋ ያላቸው ደጋፊ ጥቂት ሲሆን፤ እነ አባይ ወልዱ የህወሓት ማ/ኮሚቴውን በብዛት ይዘዋል። እነ
ደብረጽዮንም ከነአባይ ወልዱ ድጋፍ አላቸው። አንድ ተረት አለ፣ ‘ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ’ እንደሚባለው ነው።
የህወሓት መንጋ ከአመራሩ ጀምሮ እስከ ተራ አባላቱ በወንጀልና በሰው ልጅ ደም የታጠበ ነው። በዚህ ዓይነት በሳሞራ የኑስ
የሚመራው ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ደህንነቱ፣ የፌደራሉ ሁሉ ወንጀለኞችና ጸረ-ሕዝብ ናቸው። መለስ ዜናዊ በሕይወት በነበረበት
ጊዜ በ1993 የተነሳው የስልጣን ሽኩቻ በሁለት ሲሰነጥቀው፤ አሁንም ተመሳሳይ ዓይነት እጣ የደረሰው ከመለስ ዜናዊ ሞት
በኋላ ነው፤፡ ህወሓትን በሶስት የከፈለው ዋናው የሥስልጣን ሽኩቻ ብቻ ሳይሆን ኢፈርትን ማን ይምራ፣ ማንስ ይቆጣጠር
የሚለው ነበር። በ’ለ’ ስር የተዘረዘሩት የኢፈርት ዋናው የዝርፊያ መሳሪያ ስለሆነ በኛ ይመራ ባዮች ናቸው። በ’ሀ’ ምደብ ስር
ያሉት እነ ስብሃት ነጋ ከላይ እሰክ ታች ኢፈርትን መቆጣጠርና መምራት ያለብን እኛ ነን ብለው ቁመዋል። በተጨማሪም፣
ከሥልጣኑም የሚንስትርነት ቦታ ለኛም ይገባናል ባዮች ናቸው። በተለይ አዜብ መስፍን በሕገወጥ መንገድ ከስብሃት ነጋ
የወሰደችው የኢፈርት መሪነት ለኛ ይመለስልን ሲሉ በ’ለ’ እና በ’ሐ’ የተሰለፉት አልተቀበሉትም። አዜብ መስፍንን ከኢፈርት
አስወግደን በሌላ ሰው እንተካታለን በማለት ተስማምተው ብርሃነ ኪዳነማርያምን በቦታዋ በዳይሬክተርነት አስቀመጡት። እነ
ስብሃት ነጋ ግን ይህንን አልተቀበሉትም። የኢፈርት የበላይ ሃላፊ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ነው። እነ ስብሃት ነጋ በዚህ ግራ
ተጋብተዋል።
በ’ለ’ ምደብ ያሉትን እነ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ትልቁ ጥረታቸው በአባይ ወልዱ የሚመራው በ’ሐ’ ምድብ ስር ያሉት
በ’ሀ’ እና በ’ሐ’ ምድብ ያሉት እንዳይስማሙና በመካከላቸው ሆነው ነገር በመተንኮስ ቅራኔ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋሉ። አዜብ
መስፍንን ካነሳን ዘንድ፤ አንበሳ ባንክን ወዘተ. ተቆጣጠሩ ተብሎ ለነስብሃት ነጋ የተሰጠ ገጸ በረከት ነው። የኤርትራው ተወላጅ
ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ‘ኢትዮ ቴሌኮምን’ የግል ሃብቱ በማድረግ የሃገርና የሕዝብ ሃብት እየበዘበዘ ገንዘቡን በቻይና ባንክ
በማስቀመጥ ኢትዮጵያን እያደማ ይገኛል። በ2007 ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን ፍላጎትም አለው።
ኤርትራዊው ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የሃገር ሃብት እየዘረፈ በማሌዢያና በተለያዩ ሃገራት ባንኮች ሃብቱን እያደለበ
የሚገኝ የህወሓት መሪ ነው። ኢፈርትንም መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ በሃላፊነት የተረከበ ሰው ነው። በ2007 ምርጫም በእነ
ወልዱ ድጋፍ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያገኘ ሰው ነው። እነ አባይ ወልዱ በትግራይ ውስጥ የሚገኙት የኢፈርት
ፋብሪካዎች፣ እንደ አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ፣ መሶብ ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ ወዘተ. ወፍራሙን ድርሻ ያገኛሉ።
በዚሁ መሰረት ኢፈርት ከተመሰረተ ከ1985 ጀምሮ ለመንግሥት ግብር አይከፍልም። ከብሄራዊ ባንክና ከንግድ ባንክ
የሚበደረውን ገንዘብ አይመልስም፣ እንዲያስከፍለው የሚያስገድደው ሕግም የለም። የተለያዩ እቃዎች ሲያስገባና ሲያስወጣ
ቀረጥ ለመንግሥት አይከፍልም። ምክንያቱም ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ስር የያዘው የህወሓት ባለሥልጣናት የግል ንብረታችው
ስለሆነ በማንም ሕግ የማይገዛ ኢፈርት ነው።
መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ በህወሓት ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሯል፣ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ሃይላቸውም
የተበታነ እርስ በርሳቸው አለመተማመን ነግሷል። ሁሉም የህወሓት አመራርና አባሎቹ ደጋፊዎቹ በሙስና የተጨማለቁ በዘር
ማጥፋት ወንጀል በመሰማራት ከ8.9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የገደሉ ናቸው። ከ30 ሚሊዮን በላይም ኢትዮጵያዊ ከተወለደበት
ከሚወዳት ሃገሩ ሠርቶ ከሚበላባት፣ ልጆቹን አስተምሮ፣ አሳድጎ ለቁም ነገር ካበቃበት መሬቱ በማፈናቀል ግማሹ ለስደት ግማሹ
ለሞት፣ ግማሹ ለችግር፣ ለረሃብ፣ መኖሪያ አልባ አድርገውታል። ከዚህ በመነሳት ህወሓቶች በጽኑ አቋም የሚስማሙበት አጀንዳ
አላቸው። ። ከህወሓት የተባባሩ አመራር የነበሩትም በዚህ በጸና አቋም ይስማማሉ።
1. አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሕገመንግሥት የህወሓት ሕገመንግሥት ነው። ይህም ከ1967 እየታገልን ይዘነው የመጣን
የሕይወታችን እና የንብረታችን መድን ነው። ይህ ሕገመንግሥት ከተናደ አሁን ያለነው የተባረሩት አመራርም
ተለቅመን ታሰርን፣ ሃብታችን ተወረሶ እኛም እንገደላለን። ስለሆነም ያለውን ሕግመንግሥት መክላከል የግድ ይሆናል።
ሁሉም በዚህ ይስማማሉ፣
2. ኢፈርት የህወሓት ሃብት ነው። ኢፈርትም በኢትዮጵያ ያሉትን ገዢ ተቋማት በተዘዋዋሪና በቀጥታ የሚቆጣጠር ነው።
ለምሳሌ፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ መአድናት፣ ትራንስፖርት ወዘተ. የሃገሪቱ ንግድም
ከትንሹ እስከ ትልቁ የሚቆጣጠር ነው። ይህ የደም ስራችን ከወደመ በሕዝብ ቁጥጥር ከዋለ ህወሓትና መሪዎቹ ብቻ
ሳይሆኑ የህወሓት መንግሥታዊ ተቋማት ጭምር ይወድማሉ። ስለሆነም ባለን አቅማችን ኢፈርትን መከላከል በበለጠ
ማሳደግ አለብን። በዚህም በማያወላውል መንገድ ይስማማሉ፣
3. የሕዝብ የአመጽ ተቃውሞ ወይም አብዮት ከተነሳ ባለን መከላከያ ሰራዊት ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ልንመልሰው
አንችልም። ሕዝቡ ከአሸነፈ የህወሓት አመራር አባሎችና ደጋፊዎቻችንን በእሳት እንደሚቀቅለን እናውቃለን። ለዚህ
መድሃኒቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በየጎሳ ከፋፍለን አሁን ባለው አይነት ደፍጥጠን ማጥቃት፣ ተቋዋሚ ድርጅቶችን
ማዳከም፣ መግደል ማዋከብ አለብን። የአገዛዛችን መንገድ ሕዝቡን ማስጨነቅ፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ በስደት እንዲጓዙ
ማድረግ እነዚህን በዋናነት እንደ መሳሪያ መጠቀም አለብን። ወጣቱን ዜጋ ደግሞ በሽርሙጥና፣ ሃሺሽ ወዘተ. በብዛት
አስፋፍቶ ከጥቅም ውጭ ማድረግ። በጎሳ ከፋፍለንም ኢትዮጵያዊነት የሚል ስር የሰደደውን እምነት ማጥፋት፣
የአማርኛ ቋንቋን ማጥፋት፣ በየትኛውም ጎሳ የሚገኘውን ስር መሰረቱን ነቅለን እንዳልነበረ ማድረግ። በዚህም ሁሉም
ይስማማሉ።
ኢትዮጵያን አሁን ማን እየመራት ነው?
መለስ ዜናዊ ከሞተ በኋላ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር ተብሎ እንደተሰየመ ሁሉም ኢትዮጵያዊ
ያውቀዋል። ነገር ግን ኃ/ማርያም የእውነት ሳይሆን የውሸት ጠ/ሚኒስቴር ነው። ኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ አሁንም መዋቅሩን
የዘረጋው ህወሓት ነው። ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ኢትዮጵያን የሚመሩትና የሚያስተዳድሩት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ ቴዎድሮስ
አድሃኖምና ንዋይ ገብረአብ ናቸው። ስለዚህ ኢትዮጵያን ማን እየመራት ነው ለሚለው ጥያቄ በትክክል ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ
የህወሓት አመራር ናቸው። የስርዓቱን መዋቅርም በነዚህ ግለሰቦች ይመራል። ኃ/ማርያም ደሳለኝ አድርግ ያሉትን የሚያደርግ
ጉልቻና ቃል አቀባይ ነው።
በ1922 የተወለደው የ83 ዓመቱ ዘራፊና ገዳዩ ሽማግሌ ስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ለባለሥልጣናቱ እንቅፋት
አይሆንባቸውም። መሪዎቹ የሚፈልጉት ዝርፊያ ብቻ ነው። እነ አባይ ወልዱ ከነ ደብረጽዮን ጋር ተስማምተው በትግራይ
ሪፓብሊክ መንግሥት ውስጥ እጃችሁን አታስገቡ። ገንዘብ እንፈልጋለን፣ ከፍተኛ ባጀት መድቡልን፣ እኛም የእናንተ ደጋፊዎች
ነን በማለት ተስማምተዋል።
ለሚቀጥለው የ2007 ምርጫ ህወሓት በአሸናፊነት ወጥቶ ለጠ/ሚኒስቴር፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚሆኑትን
እጩዎቹን አዘጋጅቷል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናል ተብሎ የታጨው ቴዎድሮስ አድሃኖም ሲሆን፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊሆን
የታሰበው ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ነው። “አባይ ማደርያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል” ማለት ይህ ነው። ህወሓት የተዳከመ፣
የበሰበሰ ግንድ ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ ፋሽስታዊ ድርጅት ኢትዮጵያን ረግጦ የመግዛት አቅም የለውም። በኢትዮጵያ ሕዝብ
ሃይል ክንድና አንድነት ይደመሰሳል። ይህንን ድክመታቸውን በመጠቀም ሃገር ቤትም በውጭ ሃገር የምንገኘውን ጨምሮ
አንድነታችንን አጠናክረን በሕዝባዊ አመጽ ወያኔ ህወሓትን የመደምሰስ ጊዜው አሁን ነው።
የመለስ ዜናዊ ራእይ
በዚሁ ጥቂት ጥያቄዎችን በመለስ እደመድማለሁ። መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ማን ነው?
መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ የጠላት ጠላት ደመኛ ጠላት ነው። ከአባቱ፣ ከእናቱና ከአያቶቹ የወረሰው በኢትዮጵያና
በሕዝቧ ላይ የፈጸመው ግፍ፤ የሃገር ማፍረስ ድርጊት በታሪክ የማይረሳ ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የህወሓት አመራርንም
ይጨምራል። የስም ዝርዝራቸውን በተለያዩት ጽሁፎቼና ከዚህ በላይም ስላካተትኳቸው እንሱን መመልከትና ማመሳከር
ይቻላል።
የመለስ ዜናዊ ራእይ በኢትዮጵያ ልማት፣ እድገት፣ ዲሞክራሲ ማለትስ ምን ማለት ነው? በእርሱ አመራር ለ21 ዓመታት
ኢትዮጵያ በልማትና በዲሞክራሲ አብባለች የሚሉት የህወሓት ደጋፊዎችና አጋር ድርጅት ተብለው የሚጠሩት ጸረ-ሕዝብና ጸረ-
ኢትዮጵያ ስብስብ ብቻ ናቸው። ብዙ ለሆዳቸው ያደሩም አሉባቸው። ነገሩ የተጋላቢጦሽ ነው። መለስ ዜናዊ የሚመራው
ህወሓትና አመራሩ በተፈጥሮው ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። ህወሓት አፈጣጠሩ አምባገነን እና ፋሽስት፣ እንዲሁም ጸረ-
ዲሞክራሲ ሆኖ ያደገ ከመቅጽበት የልማት፣ እድገትና ዲሞክራሲ አራማጅ ሊሆን አይችልም። ጎባጣና ጠማማ ሆኖ ያደገ ባህር
ዛፍ ተቃንቶ ለኤሌክትሪክ ምሰሶ ወይም ለቤት መስሪያ ማገር ልታደርገው አትችለም። በምሳር ቆራርጦ ማገዶ ከማድረግ
ውጪ። ህወሓትን በዚህ አይነት ልንመለከተው ይገባል። ስለሆነም የመለስ ዜናዊ ራእይ ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ልማት፣ ጸረ-እድገት፣
ጸረ-ዲሞክራሲ ነው። መለስና ግብረአበሮቹ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማሩ፣ በሙስና የሕዝብና የሃገር ሃብት የዘረፉ፣
የኢትዮጵያን ሕዝብ በፋሽስት መዋቅራቸው ያሰቃዩና የገደሉ ናቸው። እንደዚህ ያለ ጨቋኝና ፋሽስት መንግስት ልማታዊ ሊሆን
አይችልም።
መለስ ዜናዊና ህወሓት ለኢትዮጵያና ሕዝቧ ምን ናቸው? በመለስ ዜናዊና በስብሃት ነጋ የሚመራው ፋሽስት ፓርቲ፣
ኢትዮጵያን ከግንቦት ወር 1983 ጀምሮ ከተቆጣጠሩ ወዲህ ኢትዮጵያና ሕዝቧ በወያኔ ሀውሓት ቅኝ አገዛዝ የወደቀችበት ወቅት
ሆኖ፣ እነሆ ቅኝ ገዢው ህወሓት በሃገራችን አረመኔያዊ ድርጊት እየፈጸመ ይገኛል። በመለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያ
ሉአላዊንት ፈርሷል። ጥንታዊና ታሪካዊ የቀይ ባሕር ወደቦቿን አጥታለች። ሕዝብ በዘሩ እየታየ የዘር ማጥፋት ወንጀል
ተፈጽሟል። ስለዚህ መለስ ዜናዊና ህወሓት እንዲሁም አመራሩ የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላት ናቸው።
መለስ ዜናዊ የወታደራዊ ሳይንስና ስትራተጂ ባለ ራእይ ይባላል። ይህ አነጋገር ደረቅ ውሸት ነው። መለስ ዜናዊን
የሚያውቁና አብረውት በትግሉ የነበሩ ታጋዮች የማይቀበሉት ጉዳይ ነው። የህወሓት መንጋ በምን ዓይነት የውሸት አዘቅት
ውስጥ እንደሰመጠ በግልጽ የሚያሳይ ነው። መለስ ዜናዊ ከትግሉ መጀመሪያ አንስቶ ለብዙ ዓመታት አብረን ተጉዘናል። በጣም
የሚተማመንብን ጓደኞቹ ተክሉ ሃዋዝና እኔ ገ/መድህን አርአያ ነበርን። በሚገባ ስለምናውቀው የወታደራዊ ስታርቴጂስት
አልነበረም። እውቀቱም ችሎታውም ፈጽሞ አልነበረውም። ሃቁ ይህ ነው።
“ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” እንዳለው ዓይነት ነው። መለስ ዜናዊ ከፈሪነቱ የተነሳ በተለያዩ
ጦርነቶች ፈርቶ የሸሸ፣ በህወሓት ታሪክ ውስጥ በፈሪነቱ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ግለሰብ ነው። ከሸሸባቸው ጦርነቶች ለአብነት፤
1. በ1969 ከአድዋ ኦፐሬሽን ጦርነቱ እንደተጀመረ ፈርቶ የሸሸ፣
2. በ1970 ከአዲ ደእሮ ፈርቶ የሸሸ፣
3. በ1971 መጀመሪያ ላይ ከማይቅነጠል ውጊያ ፈርቶ የሸሸ፣
4. በ1971 ህዳር ወር ከፈረስ ማይ ጦርነት ፈርቶ የሸሸ፣
5. ሰኔ ወር 1971 ከሃገረ-ሰላም ውጊያ ታመምኩ ብሎ መሬት ላይ ሲንከባለል በበቅሎ ተጭኖ እንዲምለስ የተደረገው
ናቸው። በምስክርነት የሰራዊቱ የጦር አዛዥ አረጋዊ በርሄ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።
በህወሓት ውስጥ ማንም ታጋይና አመራር የሚያውቀው ሃቅ አለ። ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጂ የነደፈው ጥናት
እያደረገ ወታደረአዊ ስትራተጂ ወታደራዊ ታክቲክ የአሸዋ ገባታ ለረጅም አመታት ጥናት በማካሄድ የጻፈና ያዘጋጀ ብቸኛው
አረጋዊ በርሄ ነው። ለሁሉም ወታደራዊ አመራር ስየ አብርሃ፣ ሃየሎም አርአያ ወዘተ. አስተምሮ ያሳደጋቸው አረጋዊ በርሄ ነው።
ስየ አብርሃ ይሁን ሌላው የሚኩራሩበት ውሸት ነው። ወያኔ ህወሓት እስከ አሁን የሚጠቀሙበት ወታደራዊ ጉዞ በአረጋዊ በርሄ
የተዘጋጀ እንጂ መለስ ዜናዊ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ወታደራዊ ሳይንስ ይሁን ስትራተጂ የጤፍ ቅንጣት የምታክል እውቀት
አልነበረውም። ሁሉም የሚዋሸው ለሆዱ፣ ለጥቅሙና የሙስና ዘርፊያውን በስፋት ለመቀጠል ስለሚፈልግ የሚመታው የውሸት
ነጋሪት ነው።
ግደይ ዘርአጽዮን ከህወሓት ወጥቶ ወደ ስደት ሲሄድ በህቡር ገብረኪዳን መሪነት ተክለወይን አሰፋ፣ ተሻለ
ደብረጽዮንን ጨምሮ ተፈትሾ የያዘውን ሰነዶች ሁሉ፣ ብጣሽ ወረቀት ሳትቀር፣ ጠራርገው በመውሰድ ባዶ እጁን ሱዳን ገባ።
አረጋዊ በርሄ፣ ህቡር ገ/ኪዳን፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ ሁነው ለብዙ ዓመታት ሲያካሂዱት የነበረውን ወታደራዊ
ጥናትና ስትራተጂ የአሸዋ ገበታ፤ በትልልቅ ወረቀቶች ላይ በሰእል መልክ የተዘጋጁ ጠቅላላ ወታደራዊ መጻሕፍት ብጣሽ
ወረቀት ሳትቀር በሁለት የማዳበሪያ ከረጢት ሞልተው የወረሱትን በታጋዮች አሸክመው ለመለስ ዜናዊ አስረከቡት። ‘በሰው
ደንደስ በርበሬ ተወደሰ’ እንደተባለው፣ መለስ ዜናዊ ባልሰራውና በማያውቀው ወታደራዊ ስትራተጂ የአሸዋ ገበታ ንድፈ ሃሳብና
አረጋዊ በርሄ ደክሞ ያዘጋጀው ነው። አሁን ወያኔ የሚጠቀምበት ወታደራዊ አካሄድ የአረጋዊ በርሄ ሥራና ጥናት ነው።
ባልሰራኸው፣ በማታውቀው ጥበብ የራስህ አስመስለህ መጠቀም ያስንቃል፣ ያዋርዳል። ስለዚህ መለስና የህወሓት መንጋ
ውሸታምና በምን ዓይነት ድቅድቅ የውሸት ጨለማ እንደተዘፈቁና ማንነታቸውን እንዲያውቁ ይህንን የጽሑፍ ሰነድ ያንብቡ።
የስብሃት ነጋ መርዶ ነጋሪ
ቀደም ብሎ በተህሓት-ህወሓት የነበረው የኢትዮጵያውያን አመራር ነበር። እነ አቶ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ
(መሃሪ) ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኘው፣ ዶ/ር አታክልት ቀጸላ በምን ምክንያት በምን ዘዴ እንደገደሏቸው በትክክል አስቀምጬዋለሁ።
በየካቲት 1981 በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የነበረው ደርግ ትግራይን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ ወያኔ ህወሓት ካለምንም
ውጊያና ውጣ ውረድ ትግራይን ተቆጣጠረ። ሃቁ ይህ ሆኖ፣ በ1983 በለስ ቀንቷቸው አዲስ አበባ ዘው ብለው ኢትዮጵያን
እነደተቆጣጠሩ፣ ነብሰ ገዳዩ ስብሃት ነጋ በመርዶ ነጋሪነት ተሰማራ። የዶ/ር አታክልት ቀጸላ ወላጅ አባት የሚኖርበት ቤት
በመሄድና እራሱን በማስተዋወቅ የዶ/ር አታክልትን ሞት ነገራቸው። በአረጋዊ በርሄ እንደተገደለ ሲነግራቸው፣ አረጋዊ በርሄ
የማን ልጅ ነው ብለው ሲጠይቁት፣ የቀኛዝማች በርሄ ገብረማርያም ነው ሲላቸው፣ የልጅ በዛብህ ፍላቴ ልጅ? ብለው ጠየቁት፣
አዎን አላቸው። የቅርብ ወንድሙ ለምን ገደለው? ሲሉት፣ በአረጋዊ መገደሉን እንጂ ሌላውን ሳይነግራቸው መርዶውን አሰምቶ
ተሰናበተ። በጅሮንድ ቀጸላም በሚወዱት ልጃቸው መርዶ የተነሳ ታመው ከብዙ ስቃይ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
ስብሃት ነጋ ይህ አልበቃውም። አድዋ አቶ ዳኘው ገ/ሥላሴ ቤት ደረስ በመሄድ የአጽብሃ ዳኘው ወላጅ እናትና ጠቅላላ
ቤተሰቡ ባሉበት፣ በአክብሮት ተቀብለው ቤት ያፈራውን ከጋበዙት በኋላ፣ እናቱ ወ/ሮ ማና ተፈሪ ልጄ ‘ሞላ’ (የቤት ስሙ)
እንባቸውን እያፈሰሱ፣ ልጄ ጠፋብኝ፣ የምታውቀው ነገር አለ ወይ ብለው ሲጠይቁት፣ ስብሃት፣ አጽብሃ፣ ሰዊት ተገድሎ ከሞተ
ብዙ ዓመት ሆኖታል አላቸው። አባትየው ቀበል አድርገው እንዴት ሞተ ሲሉት፣ አረጋዊ በርሄ ገደለው አላቸው። አረጋዊ፣ የቀ/አ
በርሄ ገ/ማርያም ልጅ? ብለው ሲጠይቁት፣ አዎን አላቸው። ያሳደገው ወንድሙ ገደለው? የአጽብሃ ዳኘው እናት በዚህ
ደንግጠው ታመው በሃዘን በሽታ ተሰቃይተው ሞቱ። ሽማግሌው አቶ ዳኘው ገ/ሥላሴ አሁንም በሕይወት አሉ። የዶ/ር
አታክለት ቀጸላ ወላጅ አባትም በመርዶው ምክንያት ታመው፣ ራስ ወርቅ ልጄ እንዳሉ ሞቱ። በ1998 የሁለቱ ቤተውስቦች ስልክ
በቀጥታ ወደ እኔ ደውለውልኝ ተነጋግረናል። በዚህ ሃሳብ ላይ እንዳለን፣ የዶ/ር አታክልት ቀጸላ ወላጅ አባት በጅሮንድ ቀጸላ
ብሩ፣ ወላጅ እናቱና የእኔ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ገ/መድህን አርአያ ወላጅ እናቴ ወ/ሮ አጸደ ገብሩ እናት፣ የሁለቱ እናቶች ታላቅና
ታናሽ የአንድ አባትና እናት ልጆች ናቸው። በዚህ መሰረት ነው የዶ/ር አታክለት ቀጸላ ቤተሰቦች አረጋዊ በርሄ በምን ምክንያት
እንደገደለው የጠየቁኝ። እኔም ስብሃት (ወ/ሥላሴ) ነጋ የነገራችሁ ውሸት ነው። ዶ/ር አታክልትን የገደለው ስብሃት ነጋ ነው፣
በማለት በጽሑፍ እንደገለጽኩት ስነግራቸው አምነውኝ ተለያያን። ያመኑኝ ምክንያት የአታክልት መገደል ለእኔም የሚሰማኝ ልክ
እንደ እነሱ ስለሆን ነው። ለእኔም ለነሱም ወንድማችን ነው።
ቀጥሎ ከትንሽ ወራት በኋላ በ1998 ከአጽብሃ ዳኘው ቤተሰብ ወንድሙ ከእንግሊዝ ሃገር ደወለልኝ። በጽሑፍ
እንዳስቀመጥኩት ገልጬለት አልቅሶና አጽናንቼው ተለያየን። ቀጥሎ ለሁለተኛ ጊዜ በ2000 ወንድሙ ደውሎልኝ፣
ያቀረብኩለትን ሁሉ እንዳለ አምኖ ተቀበለኝ። ሌላው ያቀረበልኝ ጥያቄ ቤተሰቦቼ በአረጋዊ በርሄ ቅሬታ አድሮባቸው ነበር፤
በምን አይነት ይቅርታ ልጠይቀው፣ እባክህ ንገርልኝ ሲለኝ፣ የለም ከሆነ ባንተ ነው መሆን ያለበት ብዬው እንደሚደውልለት
ነግሮኝ ተሰነባበትን። አረጋዊ በርሄ ግምት ያልሰጠው እውነት አለ። የህወሓት ፕሮግራምን ጽፎ ለ12 ዓመት በከፍተኛ አመራር
ላይ ሆኖ ያስተዳደረው ድርጅት ነው። ማንም የማያቀውን የድርጅቱን ወንጀሎች በዝርዝር ያውቃል። ህወሓት በሥልጣን ላይ
ሆኖ ለፈጸመው ግፍ ተጠያቂ እንዳይሆን አረጋዊ በርሄ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ወያኔን ማጋለጥ አለበት።
እነ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ ወዘተ. በትግሉ ጊዜ የተገደሉት ታጋዮች፣ ሰላማዊ ዜጎች በስንት ሺህ የሚቆጠሩ ናቸው።
ከ1982 በዘመቻ መልክ ተነስተው ያስፈጁትን አረጋዊ በርሄ እንደገደላቸው አድርገው ስሙን በክፉ መልክ አጥፍተውታል፣
አሁንም እንደቀጠሉበት ነው። የህወሓት አባላትና ደጋፊዎቹ እስከ አሁን እኛን የፈጀን አረጋዊ በርሄ ነው እያሉ ይገኛሉ። እሱም
ይህንን ነገር በትክክል ያውቃል። አረጋዊ የሚለውና የሚሟገተው፣ ማስረጃችሁን አቅርቡ እያለ ነው። ይህ አባብሉ ግን ትክክል
አይደለም። የፖሊት ቢሮ አባልት ሁሉ በየ06 ሃለዋ ወያነ እየተበተኑ ሕዝብ የጨረሱት አመራሩ ናቸው። በ06 ሃለዋ ወያነ
ሃላፊዎች የምርመራ ሪፖርት ጭፍን ፍርድ ሲሰጥ የነበረው አመራር ነው። በሰነድ ተደግፎ የሚፈጸም ግደሏቸው የሚል ትእዛዝ
በተህሓት-ህወሓት አሰራር አይታወቅም።
እነ ስብሃት ነጋ በአረጋዊ በርሄ ላይ የሚያካሂዱት የስም ማጥፋት እልባት ማግኘት አለበት ከሚል ሃሳብ ተነስቼ
መጋቢት 2 ቀን 2000 በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጆች ማህበር፣ በዶ/ር ግደይ አሰፋ
ሊቀመንበርነት፣ በአቶ ተስፋየ አጽብሃ የሚመራው ቡድን በተጠቀሰው ቀን ተሰበሰበ። ለአረጋዊ በርሄ ያቀረብኩት ሃሳብ በእነ
ስብሃት ነጋና በወያኔ ስርዓት ስምህ እየጠፋ ነው። አንተም በመጀመሪያ ማድረግ ያለብህ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀህ
በህወሓት የተፈጸሙትን ወንጀሎች ለሕዝብ አቅርብ። ያን ስታደርግ የአእምሮ እረፍት ታገኛለህ። በህወሓት በርካታና ከባድ
ወንጀሎች ተፈጽመዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅር ባይ ነው የሚል ሃሳብ አቀረብኩለት። በወቅቱ የነበሩ አመራርና በቴሌ
ኮንፈረንስ የነበሩት የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው። አረጋዊ በርሄ ለምን ደፈርከኝ ብሎ ብዙ ተናገረ። ቁም ነገሩ ቴሌ ኮንፈረንስ
በመሆኑ ነው እንጂ በአካል አጠገቡ ብገኝ ኖሮ ረጋግጦ ያጠፋኝ ነበር። የሁላችንም ግንኙነት ከዚህ ጊዜ በኋላ ተቋረጠ። ጥሩ
ምክር በመለገሴ ጠላት አፈራሁ። የመከራና የችግር ጊዜ ወንድሙን ጠላኝ። ይባስ ብሎ የህወሓት ጠላትና ጽንፈኞች በማለት፣
አስገደ ገ/ሥላሴን እና እኔ ገ/መድህን አርአያን ፈረጀን። ይህን ለማለቱ ብዙ የሰው ምስክሮችት አሉን። የተማረ ሰው ነው።
በህወሓት ውስጥ ያለፈ አመራር ሁሉ፣ ከትግሉ መጀመሪያ አንስቶ፣ ብዙ ወንጀል ፈጽሟል፣ በመፈጸም ላይም ነው። ስለዚህ
ማንም አመራር እኔ ነፃ ነኝ የሚል ካለ ተሳስቷል። ልክ እንደ ግደይ ዘርአጽዮን ጥፋተኛ ነኝ ብሎ ደጋግሞ እንደሚናገረው
ሌላውም ይህንን አርአያነት መከተል አለበት።
ውድ ኢትዮጵያውያን የህወሓት ታሪክና እንወቀው የሚሉት ጽሑፎቼ በዝግጅት ላይ ናቸው። በጥቂት ወራት ውስጥ
ለሕዝብ ይቀርባሉ የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ሶስተኛው ጽሑፌ ደግሞ “ተጠያዊዎቹ እነማን ናቸው” ይሚለውን በማዘጋጀት
ላይ ነኝ። ከማገብት-ተሓህት-ህወሓት የመጡ አመራር አንድ በአንድ ምን ሰሩ፣ በምንስ ይጠየቃሉ የሚለው ሰፊና ግልጽ
መጽሓፍ እየተዘጋጀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ በድህረ ገጽ የማስተላልፋቸውን ጽሁፎች ኢትዮጵያዊ ሁሉ በማተም ሰብስባችሁ “የህወሓት ገበና” በማለት
በማህደር አጠራቅሙት። ጥሩ የሰነድ ማስረጃ ነው። የህወሓት አመራርና ካድሬዎቹ በሕዝብ የሚፈረዱበት ቀን ደርሷል።
ገብረምድህን አርአያ ህወሓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ሃይል ይደመሰሳል!!!
አውስትራሊያ 2006 ዓም የነጻነት ዓመት ናት!!!
መስከረም 6 ቀን 2006

zehabesha