የእርግማን ዘሮች!!!
ካለፈ በኋላ የዓመቱ እኩሌታ ሲቃረብ መባቻው፣
በ2003 ወደመጨረሻው፣
የዓለምን ጥበብ ያደረገች መና፣
ዘመናት የኖረች የልዩዎች ሆና፣
አንድ ልዩ ዕውቀት ዕውቀቴን የናደች፣
ማስተዋልን ልትሰብክ ወደእኔ ተላከች፡፡
ብዙ እንቆቅልሾች ተሰውረው ያሉ፣
ጥበብ መዝግባቸው መጻሕፍት የሞሉ፣
እውነትን/ጥበብን ለማወቅ ባልፈለጉት ሁሉ፣
የዓለም ሞኝ ነገር ተረት የተባሉ፣
ሳልወድ በግዴ አይቼ እንዳምን፣
ሥውሩን የምትገልፅ ያነቃች ግያዝን፣
ከኤልሳዕ ከተማ ወስዳኝ ከዶታይን፣
ይህች አዲስ ዕውቀት ከፈተች አይኖቼን፡፡
ብዙ ጥፋት ጠፍቷል ማስተዋልን አጥተን፣
ሰው ለሰው ጠላቱ መሆኑን ዘንግተን፣
ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው እየተባልን፣
ዘመናት ባክነዋል ከዕውቀት/ከጥበብ ተጋርደን፡፡
በሮሃና አክሱም የቀሩ አሻራዎች፣
የቀደምት ጠቢባን የአእምሮ ጉልበቶች፣
እምን እንደገቡ ምድሪቱን ጠይቄ፣
የእርግማን ዘሮች!
መልስ ስጠባበቅ ሚስጢሩን ናፍቄ፣
ይህች አዲስ ዕውቀት የእንቆቅልሽ መፍቻ፣
ከብልሆች ሰፈር ከጥበብ ዳርቻ፣
መጥታ ሹክ አለችኝ ፍፁም በለሆሳስ፣
የእኩያንን ደባ ለዚች አገር መፍረስ፡፡
ብሩሕ አእምሮዎች ምድሪቱ እንዳታበቅል፣
ድንገት በቅሎም ቢገኝ እንደ አረም ሊነቀል፣
ለካ ጥበበኛው ተበይኖበታል!!
እና ምን ይገርማል ይህች አገር ብትደኸይ፣
ይህች አገር ብትራብ ሰቆቃዋን ብታይ፣
ትጉሀን ልጆቿ ለግዞት ተዳርገው፣
ሟርትና ሟርተኞች ቦታውን ተክተው፣
ቃላቸው ተከብሮ ደብተራና ጠንቋይ፣
ጠለስን ጠላሾች የሚያበሉ ሥራይ፣
ከአባታቸው ሰይጣን አንድነት መሥርተው፣
መታች አስመታቾች ሲሰሩ እንቅልፍ አጥተው'
መልካም ነገር ጠፍቶ ጠቢባን ተኝተው፣
ሰው እየመከነ ዛርውላጅ ተወልዶ፣
አምላክ ተዘንግቶ ለጣዖት ተሰግዶ፣
ጨሌ ቦሮንቲቻ አዳል ሞቲ ጠቋር ፣
አስገባሪ ሆነው ነግሰው በዚች አገር፣
አእምሮአችን ቢነጥፍ ክብራችን ቢዋረድ፣
የእርግማን ዘሮች!
ጥበብ ብትሸሸን ጥላን ብትሰደድ፣
ብንፈዝ ብንባዝን ኑሮ ቢሰናከል፣
ባናስተውል እንጂ እስኪ ምን ይገረማል?!
አዎ እርግማን ነው እጅግ ክፉ እርግማን!፣
እንዳይሆን ፈልገን ያዕቆብ አባታችን፣
ከጣዖት አምላኪው ልጅ ከራሔል ተወልደን፣
የአያታችን ላባ አብራክ ውጤት ሆነን፣
የክፉ ሰው ዘሮች የእርግማን ፅንሰቶች፣
የእናታቸው ገዳይ እኩይ የሙት ልጆች፣
የቢኒዖኒ ደም/ዘር ነጣቂ ተኩላዎች!!!
አቤቱ አምላክ ሆይ ይሄን ዘር አቋርጠው!
መንገዱን ዝጋበት አይኑን አሳውረው!
ከሐናንያ ላከው ሌላ ዓይን ይቀበል!
እርግማኑ ይብቃ አዲስ ትውልድ ይብቀል!!
አሜን!!!
መታሰቢያነቷ የክፉ መናፍስትን ሴራና የልዑል እግዚአብሔርን ኃይል ለማወቅ ለፈለጉት ሁሉ ገሐድ
ላወጡት ለፈላስፋው ለመምህር (መልአከ መንክራት) ግርማ ወንድሙ ይሁንልኝ፡፡
የታላቋ ቀን ልጅ መስከረም 2005 ዓ.ም (Son of the great day, September 2012)
እንደዘበት የምናነባቸውና አልፎ ተርፎም ተረትተረት የሚምመስሉን የመጸሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ዛሬም ማስተዋሉን ባይጋረድብን
የምናያቸው ገሃዳዊ እውነታዎች እንደሆኑ እኔ ሳልወድ በግዴ ምስክር ነኝ!
የእርግማን ዘሮች!
የእርግማን ዘሮች ግጥም ሐሳብ መነሻ፡
ዛሬ ያለንው ብዙ ኢትዮጵያውያንና የያዕቆብ የመጨረሻ ልጅ የቢኒዖን (ብንያም)ነገድ (ሁሉንም ከመምህር
ግርማ ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርቶች እንደተረዳሁት)፡፡
ቢኒዖኒ ማለት የጭንቅ/ሙት ልጅ ማለት ሲሆን እናቱ ራሔል እሱን ስትወልድ በመጨረሻ ጣሯ ያወጣችለት ሥም ነው፡፡
ቢኒዖኒ (ብንያም) እንደ ወንድሙ ዩሴፍ እናቱ በበረከትና በእግዚአበሔር አምልኮት ሳይሆን የፀነሰችው የአባቷን የላባን ጣዖት ሰርቃ
በነበረበት ወቅትና ያዕቆብ ቤተሰቡን ይዞ ከላባ በተለየ ጊዜ ላባ ጣዖቴን ሰረቀሃል ብሎ ሲከተለው ያዕቆብም ከቤተሰቤ ያንተን ጣዖት
የሰረቀ/የምታገኝበተ ሰው እሱ ይሙት (ዘፍጥረት 31፡ 32)ብሎ ከረገመ በኋላ ነው (ሙሉ ታሪኩ ዘፍ 31፡ 22-42)፡፡ እንደ ያዕቆበም
እርግማን ራሔል ቢኒዖኒን (ብንያምን) ስተወልድ በጭንቅ ሞተች!! ምንም እናቱ ቢኒዖኒ (የጭንቀቴ ልጅ) ብትለውም አባቱ ይወደው
ነበርና ብንያም (የቀኝ ክንዴ) ብሎት ነበር (ዘፍ 35፡ 16-21)፡፡ ሆኖም ግን በኋላ ያዕቆብ የልጆቹን መጻኢ ዕድል ለመወቅ እግዚአብሔርን
ሲጠይቅ የብንያም ዕጣፈንታ በጣም የሚያሳዝን እንደሆነ እግዚአብሔር ነግሮት ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው (ዘፍ 49፡ 27) ብሎ ነበር፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ የብንያም ነገድ አሳዛኝ ታሪክ ያለው ነው፡፡ምክነያቱም በዘር የተላለፈ የክፉ መንፈስ (እናቱ ራሔል ያመለከችወ ጣዖት)
እንደሆነ የሀይማኖት ጠባብቶች/ፈላስፋዎች ይናገራሉ፡፡ ይህ የክፉ መንፈስ ዘር ከዘመናት በኋላ የብንያም ነገድ የሆነውን ንጉሱ ሳዖልን
እንዴት እንደጣለው መጽሐፍ (ሳሙ ቀ
ዳማዊ 31፡ 1-13) እንድናሰተውል ይጋብዘናል (ሙሉ ታሪኩ መ.ሳ ቀዳማዊ)፡፡ ኋላም በክርስቶስ ዘመን የብንያም ነገድ የሆነውን ሳዖል
(ኋላ ቅዱስ ጳውሎስ) የቱንም ያህል ለእግዚአብሔር ቀናኢ ቢሆንም ክርስቶስን ለማሳደድ ዳርጎት እንደነበር፣ ልዑል አምላክ ግን ለእሱ
ያለውን ቀናኢነት ስለተመለከተለት ለጥፋት ሲጓዝ መንገድ እንደዘጋብት፣ አይኑን እነዳሳወረው ይድንምና ማድረግ የሚገባውን ያውቅ
ዘንድ ወደ ካህኑ ሐናንያ እንደላከው፣ ከአይኖቹም ቅርፊት እንደተነሳ መጽሐፍ ይናገራል(ሐዋ 9፡ 1-21)፡፡ ይህ ሁሉ ከሆነም በኋላና
ቅዱስ ጳውሎስ በጨርቁ ሳይቀር የሌሎችን ደዌና ርኩስ መንፈስ እያሰወገደ አንኳን ይህ ክፉ መንፈስ እጅግ ሲፈታተነው እንደነበር
መጽሐፍ ይናገራል፡፡ በመጨረሻ ግን ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የክፉ መንፈስ ዘር ለማቋረጥ የቻለ የብንያም ወገን ሆኗል፡፡
በዘር የሚተላለፉ ሚስጥራዊ የጤና ችግሮችና የክፉ መናፍስት ጥቃቶች (Genetically
transferable enigmatic health challenges
vs evil
spirit attacks)☺ ሁላችንም በአፅእኖት ልናስተውለው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ችግሮቻችን ከዘር የተወረሱ ተብለው
በስያሜና በይሁንታ ተሸፋፍነው የክፉ መናፍሰት ሴራዎች ለመሆናቸው ጉዳይ ሳንሰጣቸው ቀርተናል፡፡
· አይናችን ቢፈዝ የዘር ተብለን መነፅር መሰካት፡፡ መነፅሩ ባልኖረበት ዘመን በኖሩ ዘሮቻችን (ወገኖቻችን) የማይታወቀው
የእይታ ችግር (Sight) ዛሬ ብዙዎቻችንን እንዳጠቃን እናስተውል፡፡ መነፅሩ ባይኖር ምን ልንባል ነው? አይነስውር?
· ነርቭ፣ስኳር፣ደምግፊት፣ ኦቲዝም/ዳይሜንሺያ፣ አስም፣አለርጂ፣ ለምፅን ጨምሮ ልዩ ልዩ የቆዳ ችግሮች ወዘተ ሁሉ ከዘር
ጋር እንሚገናኙ ሳይንስ ይናገራል፡፡ ነገሩ ልክ ነው ግን ሳያንስ ችግሩ በዘር በሚመጣ የመንፈስ ጥቃት ሳይሆን በዘር
በሚተላለፍ ደካማ ዘረ-መል (gene) እንደሆነና ለማቋረጥ ምናአልባት ዘረ-መሎቹን ማሰወገድ (gene knock out)
አመራጭ ነው ይለናል፡፡ የስነሕይወቱ ሳይንስ (Biology) ይህን ይበል እንጂ በተግባር ግን ጉዳዩ ውስበስብና
የማይቻልም ነው፡፡
· አንዴ የዘር (genetic) ተብሎ ተፈቅዶለታልና ይህ ክፉ መንፈስ ከኛ በሚመጡት የልጅ ልጆቻችን እንዲቀጥል ፍቃድ
መስጠታችንን አንዘንጋ፡፡ እንደ ጳውሎስ እሰካለቋረጥነው ድረስ እንሚቀጥል ልብ ልንል ይገባል፡፡!
እኔም በአቅሜ በማስተዋል እንድንሔድ እናገራለሁ፡፡ ሊያውም ሳልወድ በግዴ! ለካ እንዲህም አለ! ለልዑል አመላክ ምሰጋና
ይግባውና እኛን ሆኖ ተግልጦ በምድር የተናገረውንና የሠራውን ብዙዎቻችን ሳንወድ በግዳችን ዛሬ አይተን እንድናምን አድርጓል፡፡
ምንም ሳያዩ ያመኑ ብፁዐን ናቸው ቢባልም፡፡ አይተን ላመንውም እግዚአበሔር ይመስገን! አይተውም አናምንም ብለው
የተሰጣቸውን እድል አምቢ ያሉ ብዙዎች ይልቁንም የሚበልጡት ናቸውና፡፡ ማንም ሰው (ከለየላቸው በጣም ጥቂቶች በስተቀር)
በእግዚአበሔር ታምናለህ ቢባል መልሱ አዎ ለመሆኑ አያከራክርም፡፡ እውን ግን አምናለሁ የሚለው ሁሉ ያምናል?! ከጥቂቶች በቀር
አጠያያቂ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ እግዚአበሔርን አምናለሁ ብሎ የሚለው በዙ ሰው ሰይጣን አለ የለም ሲሉት የለም ብሎ የሚያምን
መሆኑ በራሱ የእግዚአበሔርንም ስለሚፈራ ነው እንጂ በትክክለ አንዳለ ስለሚያምን አይደለም አግዚአበሔር አለ የሚለው፡፡
የእግዚአብሔርን ሀልዎት የሚያምን ሰይጣን እንዳለ አሳምሮ ያውቀዋልና! በሌላ መልኩ ስንታይ ደግሞ ከእግዚአበሔር ኃይል ይልቅ
የሰይጣንን እገዛ አብዝተን የምንፈልግ ለመሆኑ በደንብ የምናስተውል ከሆነ ጠንቋይ፣ ቃልቻ፣ ደብተራ ወይም ሌላ አለ በተባለበት
ቦታ የሚጎረፈውን ሕዝብ መመልከት ነው፡፡ በተቃራኒው የልዑል አምላክ ኃይል መገለጫዎች እንደ ኋላ ቀርነት ሞኝነት ሲቆጠሩ
በትልልቅ መንፈሳዊያን በተባሉ ሰዎች ሳይቀር ይታያል፡፡ ነገሩ አይፈረድብንም መተት እንጂ የእግዚአበሔር ሥም ኃይል እንደሚሰራ
መቼ በልባችን እናምናለንና የቱንም ያህል በአፋችን ኃይል የእግዚአበሔር ነው እያልን ብንቀሳፍትም፡፡ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ
የእርግማን ዘሮች!
ያመልከኛል… የሚለው የአምላክ ቃል በትክክልም ለእኛ እንደሆነ እናስተውል፡፡ እኮ ኃይል የእግዚአበሔር እንደሆነ ካመንን
ለሚያምን ሁሉ ይሆንለታል ይላል፡፡ እንኳን ሁሉ ሊሆንልን እንቆጣጠረዋለን የምንለው ሁሉ ሲጠፋብን ነው የሚታየው፡፡ ችግሩ
የእኛ ማመን ነው ወይስ የአምላክ ኃይል አለመኖር????? ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ያመንን የመሰለን ሁሉ ተሸውደን
የምድሩስ የምድር ነው የገሃነም እራት እንዳንሆን፡፡ ዳሩ ገሃንም (የዘላለም እሳት!!!) እንዳለስ ብናምን መች እንዲህ እንሆናለን፡፡
አለማመናችን በእናምናለን ድፍንነታችን መሸፈኑ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው፡፡ አለማመኔን አርዳው (ቃሉ በወንጌል ማርቆስ 9፡ 23-
24 አንድ ሰው ወደ ጌታ ቀርቦ ልጁን እንዲፈውስለት ቢቻልህ እዘንልኝ ባለው ጊዜ ጌታ ብቻልህ ትለኛለህ? ለሚያምን ሁሉ ይቻላል
ባለው ጊዜ ሰውየው ደንግጦ ጌታ ሆይ አለማመኔን እርዳው ያለው ትዝ ስላለኝ ነው) ለማለት አንኳን እድል አላገኘንምና፡፡
አንዳንዶቻችን ራሳችንን መደለላችን እንኳን ሳይታወቀን አይተን እንድናምን የእግዚአበሔር ኃይል ሲገለጥልን እንኳን በምልክት
አናምንም በሚል የራሱ በውስጣችን ያለው የክፉ መንፈስ ስልታዊ ሴራ እንዳናምን ተዳፍኖብን እንቀራለን፡፡ በእግዚአበሔር
ተዓምር ማመን ምኑ ነው ጥፋቱ፡፡ ብዙዎች ጌታን ያመኑት በሚሰራው ተዓምር ነበር እንጂ በሚያስተምረው ትምህርት አነበረም፡፡
በኋላም ሐዋሪያቶቹና ቀጣይ ቅዱሳኖቹ ብዙዎችን ካለማመን ወደ ማመን የቀየሩት በሚሰሩት ተዓምር እንደነበር እንዴት
አናስተውልም፡፡ እስክ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ ውጭ ይናገር ከሆነ አዋቂ ነኝ የሚል የምጣ! አንድ ጥቅስ ከመጽሐፍ እየመዘዙ በምንና
ላምን ምክነያት እንደተነገረ አንኳን በማያስተውሉ ወይም የራሳቸውን ከፉ ሀሳብ ለሰዎች በመንዛት አባል ለማፍራት በሚፈልጉ
ተመርተን ከእግዚአበሔር በሆነ ምልክት አናምንም የምንል እኛ ለመሆኑ ማን ነን?! ምልክትን ሁል ጊዜ ግን መከተል እንደሌለብንና
ከእግዚአበሔር ያልሆኑ ምልክቶች እንዳያሳስቱን ምልክትን በጥንቃቄ እንድናስተውል ተነገረን እንጂ የልዑል አምላክ ኃይል ሲገለጥ
ምልክት ነው እያልን እንድናወግዝ ልባችንንም እንድናደነድን አይደለም፡፡
ሲጀምር እኛ እናምናለን ወይ?! ለሚያምን ሁሉ ይሆናል የሚለው እስኪ በዚህ ዘመን ለማን እየሆነለት ነው ያለው? ግን እኮ
ብዙዎቻችን እናምናለን እያልን ነው? እናምናለንንና ለእኛ አኗኗር ተመችተው ያገኘናቸውን ከመጽሐፍ የተወሰዱ ጥቅሶችን
መደበቂያ አድርገናቸው እየኖርን እንዳለንም ማስተዋል አልቻልንም፡፡ ከእኛ እናምናለን ባዮቹ ወጣ ያሉ በትክክልም የእግዚአብሔር
የእምነት ኃይል የሚታይባቸው በእኛ ዘንድ መተተኞች ይሆናሉ፡፡ እኛ የለመድናቸው ጠንቋይና ደብተራ ግን የተከበሩ አዋቂዎች
ሆነው በክብር በመካከላችን ይኖራሉ፡፡ እንግዲህ እናስተውል ማንን እያመነን እንዳለን፡፡ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ይሰራል ብሎ
ለማመን አቅም እንዳነሰንና ተቦርቡረን እነዳለቅን አላስተዋልንም፡፡ በትክክልም እግዚአበሔር አምላክ ድሮ (እኛን ተረት
እንደሚመስለን ሳይሆን) እንደሚያደርገው ዛሬም ያደርጋል፡፡ በትክክልም እሱን በሚያመለኩት ላይ ኃይሉን ይገልጣል፡፡ በሰዎች
ልጆች ታሪክ ሁሉ ይህ እየሆነ ነበር ወደፊትም ይቀጥላል፡፡ ብዙዎችም የልዑል አምላክ ፀጋ ባለቤቶች የመሆን እድል አግኝተው
ነበር፡፡ ፀጋቸውን ግን የሚያቆዩት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ፀጋው በትክክል ከልዑል አምላክ ቢሆንም የሰዎች ሰውየውን ማድነቅና
(ማክበር ግን አይደለም) ፈተና በመሆን ትመክህት እንዲያድርበት ሆኖ በመጨረሻ እነሱም የተከተሏቸውም በአሰከፊ ሁኔታ
የሚጠፉበት አደጋም አለ፡፡ ትምክህታችውን ለልዑል አምላክ ክብር መገለጫ የሰጡ ግን ምንም አይሆኑም፡፡ ከላይ የጠቀስንውን
የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ ማስተዋል ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ትምክህቱ በልዑል አምላክ እግዚአበሔር ነበርና፡፡ በድፍረትም እኔ ኢየሱስ
ክርስቶስን እንደምመስል እናንተ እኔን ምሰሉ እንዳለም፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ንግግር ከስጋዊ ትመክህት አልነበረም በአምላክ ዘንድ
ያለውን መተማመንና ለእምነቱም ያለውን ቁርጠኝነት ለሌሎችም ለማሳየት እንጂ፡፡
የምንገርመው ግን ከላይ እንደጠቀስኩት የእግዚአበሔር ሲሆን በምልክት አናምንም ያልንው የሰይጣንና አጋንንት ሥራዎች በሆኑት
ምትሃቶች (ማጂክ) ስናምን አለማፈራችን ነው፡፡ ኧረ አንዳንዴም ሳይነሳዊ ትንታኔም ለመስጠት እንሞክራለን! እስኪ በየ
ጋዜጣው/መጽሔቱ ላይ ያሉ የአስትሮሎጂ (የእድል ጥንቆላዎች)፣የኦሾና ራምፓ፣ የመዳፍ መስመር የመሳሰሉትን ስናነብ ምን
እያደረግን እንደሆነ እራሳችንን እንታዘብ፡፡ በየጠንቋዩና ቃልቻው ቤት ለሚደረጉ የሰይጣን ምልክቶችስ፡፡ በአንድ ወቅት ዛሬ
በማረሚያ ቤት ያለው ሰው በጣም ብዙና እጅግ ትልቅ የተባሉ ሳይቀሩ ተከታዮቹ እንደሆኑ ያወቅንው ኋላ ነው፡፡ የሰውም ብዛት
ሲታይ ምን ያህሉ ሰው እውን እግዚአበሔርን እያመለከ እንደሆነ ጥያቄ ውስጥ የጣለ ነው፡፡ አንዳንዶች የሌሎችን ገንዘብ ፍለጋ
(ለመሰለብ) ወይም ሌላውን ለማጥፋት በመቶ ሺዎች ገብረዋል፡፡ የክፉ ሰው ዘሮች! እነዘህ ክፋቶች እንደሚሆኑልን ስለምናምን
በመቶ ሺዎች እንገብራለን፡፡ የእግዚአብሔርን ኃይል ግን ለማስተዋል አእምሮአችን ተዘግቶብናል፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ
አልፈለግንምና፡፡ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው
ይላልና፡፡
አምላክ ሆይ ለማይረባ አእመሮ አሳልፈህ አትስጠን! እናስተውል ዘንድ አቤቱ አእሚሯችንን ክፈት! እርግማናችንንም አስወግድ! አሜን!
የታላቋ ቀን ልጅ (Son of the great day, September 2012)-2005 ዓ.ም (2012 G.C.)__
No comments:
Post a Comment