Friday, September 6, 2013

የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔና ርእስ አስለዋጭ መሳዩ አሳሳቢ ጉዳይ


የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔና ርእስ አስለዋጭ መሳዩ አሳሳቢ ጉዳይ

የቡድን 20 ሃገራት የ 2 ቀናት ጉባዔ፣ ዛሬ በሴንት ፒተርስበርግ ፣ ሩሲያ ተጀምሯል። ጉባዔው፤ በዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት ፣
የቡድን 20 ሃገራት የ 2 ቀናት ጉባዔ፣ ዛሬ በሴንት ፒተርስበርግ ፣ ሩሲያ ተጀምሯል። ጉባዔው፤ በዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመወያየትና በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት ፣ በባንኮቻቸውኪሳራና አጠቃላይ ቀውስ ሳቢያ ኤኮኖሚአቸው ያላንንሠራራላቸውን አገሮች በሚመለከት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ የተነገረ ቢሆንም፣ በጉባዔው ተሳታፊ መንንግሥታት መካከል ያለው ልዩነት የስብሰባውን ሂደትና ውጤት ሳይለውጠው እንደማይቀር ተገምቷል።የዚህ ጉባኤ ዋና የመነጋገርያ ነጥቦች መካከል የቀረጥ ጭማሪን መከላከል፤ የዓለም የፊናንስ ሁኔታን በጥብቅ መቆጣጠር ሲሆን ወቅታዊዉ የሶርያ ወቅታዊ ሁኔታ የመንግስታቱ ዋንኛዉ የመነጋገርያ አጀንዳ መሆኑ ተመልክቶአል። በዚህም የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የአሳድን መንግስት ላይ የተወሰነ ወታደራዊ ጥቃት ለመፈጸም በያዙት እቅዳቸዉ ጸንተዋል። እንድያም ሆኖ በዓለም የበለፀጉ 20 ሀገራት ጉባኤን ከሚካፈሉ መካከል፤ እስካሁን ፈረንሳይ አዉስትራልያ እና ቱርክ ብቻ ናቸዉ፤ በሶርያ መንግስት ላይ ይፈጸም የተባለዉን የቅጣት ዉሳኔ እንደሚደግፉ ያስታወቁት። የሩሲያዉ ፕሪዚደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደቀድሞዉ ሁሉ ፤ በሶርያ ላይ ይወሰድ የተባለዉን የቅጣት እርምጃ በጥብቅ በመቃወም ላይ ናቸዉ። ቭላድሚር ፑቲን የሶርያ መንግስት የኬሚካዊ መሳርያ መጠቀሙ የሚያሳይ ማስረጃ ምዕራባዉያኑን ሀገሮች እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል። ወንጀሉም ከተረጋገጠ ለወታደራዊ ጥቃት ሊቆሙ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
« ከእንዲህ አይነቱ እርምጃ አንወስድም ብዪ አልደመድምም። ነገርግን እዚህ ላይ ወደ ዋንኛዉ ነጥብ እንድታመሩ እፈልጋለሁ። በዓለማቀፍ ህግ መሰረት፤ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ላይ እንዲህ አይነቱን እርምጃ መዉሰድ የሚችለዉ የተ, መ የፀጥታዉ ምክር ቤት ብቻ ነዉ። ከዚህ በተለየ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ላይ የሚደረግ ማንኛዉም አይነት የሃይል እርምጃ ተቀባይነት የሌለዉ እና እንደ ወረራ የሚቆጠር ነዉ»

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ
dw.de

No comments:

Post a Comment