Moresh Wogenie (UK)
መስከረም 16 ቀን 2006 ዓ.ም.
የልማት መጀመሪያው ሰብዓዊ መብትን ማክበር ነው!
አማራ - አቀፍ ልማት ማህበር፦ ዩኬ የሚባል ድርጅት ለንደን በሚገኘው “የኢሕአዴግ”
ኤምባሲ በልማት ስም አባሎቹን ስበሰባ መጥራቱን ደርሰንበታል።
ይህ በብሪታኒያ በበጎ አድራጎት ድርጅትነት ተመዝግቤያለሁ የሚል “የአማራ ልማት
ማህበር” ወያኔ በአምሳሉ ቀርፆ ከፈጠራቸው ተለጣፊዎችና በኢሕአዴግ ስም
ከሚጫወትባቸው አሻንጉሊት ድርጅቶች አንዱ አካል መሆኑን ከመግለጫው ማወቅ
ችለናል።
ማሳወቅ የምንፈልገው ገዥው ፓረቲ ኢሕአዴግ ዛሬ በኢትዮጵያ የአማራውን ዘር
ለማጥፋት በሥውርም ሀነ በግልፅ ቀን ተሌት እየጣረ ባለበት በዚህ ወቅት የአማራ
ልማት ብሎ ተሰብስቦ ቡና መጠጣት ለአማራው ምንም ፋይዳ ያለው ውጤት
እንደማይኖረውና ይልቁንም የዲያስፖራው አማራ ወገኑ ላይ የተጋረጠውን እጅግ
አሳሳቢ ችግር እንዳይገነዘብ የማዘናጋት ሥራ ሆን ተብሎ እየተሠራ መሆኑን ነው።
አማራ ዛሬ በዋነኛነት እየጠየቀ ያለው እንደ ሰብአዊ ፍጡርና እንደማንኛውም ዜጋ
በሀገሩ ላይ በሕይዎት የመኖርና ልጅ ወልዶ የመሳም መብቱ እንዲከበርለት፣
ሃይማኖቱና የእምነት ተቋማቱ እንዳይጠቁበት፣ ለዘመናት የተከበረ፣ አያት ቅድመ
አያቱ የኖሩበት ኢትዮጵያዊ ይዞታውም ሆነ ዳር ድንበሩ እንዲከበሩለትና፤ ያፈራውን
ንብረትና ሃብቱን በፖለቲካ ሹሞች ተነጥቆ ከቅየው መባረር እንዲቀርለት ነው።
በአገሩ በኢትዮጵያ የመኖር መብቱ ተጥሶ፣ ከክልል ወደ ክልል እየተፈናቀለና እየተነዳ፣
ለአገር ውስጥ ኬላ ግብር እየከፈለና የመንደር ዘረኛ ሹሞች አማራውን ሰብዓዊነት
በጎደለው ሁኔታ እንደ ዱር አራዊት በሚያድኑበትና በሕይዎት ወጥቶ የመግባት
ዋስትና ባጣበት በአሁኑ ጊዜ “አማራ ልማት” እያሉ ወረቀት መበተን የሆነው
እንዳልሆነ፣ የተደረገው እንዳልተደረገ፣ አማራው ተደላድሎ የተቀመጠና ልማት ብቻ
የሚጠብቅ ለማስመል ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ፕሮፓጋንዳ ከመሆኑም አልፎ፣ በአማራው
ስም ውጭ አገር ያለውን አማራ ለመዝረፍ የታቀደ ሤራ ነው ብለን እናምናለን።
በመሆኑም በአማራው ስም የምትነግዱ ሃሣዊ መሲህ ስመ - አማሮች፦ በአማራው ላይ
ለሚፈፀመው ግፍና ሰቆቃ ከወያኔ ጋር ተባባሪ በመሆናችሁ ነገ ከታሪክም ሆነ
ከትውልድ ፍርድ እንደማታመልጡ በእርግጠኝነት ልንነግራችሁና ልናስጠነቅቃችሁ
እንወዳለን።
በአንፃሩ ግን፣ ዕውነተኛ አማራ፣ ለአማራው ተቆርቋሪ የሆናችሁና ለአማራው መብት
መከበር የተነሳሳችሁ ወገኖቻችን ሁሉ፣ “አማራ ልማት” በሚል የሀሰት መቀስቀሻ
እንዳትዘናጉ በጥብቅ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። የአማራ ሁለንተናዊ መብት መከበር፣
በተለይም እንደዜጋ በሕይዎት የመኖር ዋስትና እንዲያገኝ፣ መፈናቀሉ እንዲቆም፣
የተፈናቀሉትም መጠለያ እንዲያገኙ፣ አምካኝ መድሃኒት ለአማራው መሰጠቱ ይቁም፣
እያለ አማራው ከወያኔና ከአጋሮቹ ጋር ለሚያደርገው ሰብዓዊ ትግል አጋር ሁኑት፣
ተባበሩት እያልን ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
አማራው በግፍና በዕብሪት የተገፈፈ የዜግነት መብቱን ለማስመለስና እየተፈፀመበት
ያለውን ተነግሮ የማያልቅ ኢሰብዓዊና ሕገ-ወጥ በደል ለማስወገድ በሚያደርገው ትግል
አብሮ መቆም አማራጭ የሌለው፣ የሞትና የሽረት ትግል ስለሆነ፣ ለዚህ ግብ የሚደረግ
እርዳታ ከሁሉም በፊት በቀዳሚነት መሠጠት ያለበት ድጋፍ ነው።
አማራው ጨርሶ ከመጥፋት ለመዳን በሚያደርገው ትግል አብረነው እንቁም!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ሞረሽ ወገኔ (ብሪታኒያ)
zehabesha
No comments:
Post a Comment