የሃበሻ ቤተሰብ-በአሜሪካ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
የሃበሻ ቤተሰብ-በአሜሪካ
አዛሪያስ ይባላል፤ የ19 አመት ወጣት ሲሆን፣ ተወልዶ ያደገው አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነው። አሁን የኮሌጅ ተማሪ
ነው፤ ታላቅ እሕቱ በሕክምና ተመርቃ ጥሩ ደሞዝ እየተከፈላት ትሰራለች። ወላጅ አባታቸው አቶ ዳዊት ይባላል።
አዛሪያስና እህቱ አማርኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ። በጣም የሚደነቀው ስነምግባራቸውና ጨዋነታቸው ነው። ከስንት አንድ
ካልሆነ በቀር እንዲህ በኢትዮጲያዊ ባህልና ስነምግባር ታንፆ የሚያድግ የሃበሻ ልጅ በአሜሪካ ምድር እጅግ ከባድ ነው
ይላሉ በርካታ ወገኖች። ወላጆች ባብዛኛው ልጆቻቸውን ስለኢትዮጲያዊነት ሊያስተምሩ ቀርቶ አማርኛ ቋንቋ እንኳ
አያናግሯቸውም። ራሽያ፣ ሜክሲኮ፣ ህንድ..አገራት ዜጎች ለልጆቻቸው የአገራቸውን ቋንቋ ያስተምራሉ። .. ከወላጅ
አባቱ ጋር አዲስ አበባ ደርሶ ባለፈው ሳምንት የተመለሰ የ6አመት ታዳጊ – ስለአገር ቤት ስጠይቀው « ኢትዮጲያን
ወድጃታለሁ። ሕዝቡ ጥሩ ነው። ግን ቋንቋ አለመቻሌ አዘንኩ» ስሊኝ አባቱን የጎንዮሽ አይቼ አዘንኩ።..
ወደ
አዛሪያስ ቤተሰብ ልመለስ፤ ይህ ቤተሰብ አሁን የሚኖረው በቺካጎ ከተማ ሲሆን፣ አቶ ዳዊት ታውቂ ካፌ አለው። ነጮች
ከጠዋት እስከማታ በዚህ ካፌ በብዛት ይጠቀማሉ። የአገራችን ቡና በጣም ተወዳጅ በመሆኑ ሁሉም ሲጠጣ ይውላል። ከፉል
ጀምሮ የተለያዩ ባህላዊ ቁርሶች አሉ፤ ምሳና እራትም ከክትፎ እስከ ምርጥ ሽሮ በየአይነቱ ይገኛል። አሜሪካኖች
ባህላዊ ምግባችንን (በርበሬውን ) ስለሚወዱት ከካፌው አይጠፉም። ኢትዮጲያን የሚያስተዋውቁ የቡናና የተለያዩ ስእላዊ
ፖስተሮች ዙሪያውን ይታያሉ።..አቶ ዳዊት በአንድ ወቅት ልጆቹን ይዞ አገር ቤት ገብቶ ነበር። ትልቅ
የኢንቨስትመንት ስራ ለመስራት። በግብርናው መስክ በሚሊዮን ዶላር የፈሰሰበት እንቅስቃሴ ጀመሩ። ቢሮክራሲው አላሰራ
አላቸው። ጭራሽ የገዢው ባለስልጥናት “አብረን ካልሰራን ለብቻችሁ አይሆንም” ሲሉ አስቸገሯቸው። ለሟቹ ጠ/ሚ/ር
ቢያሳውቁም መፍትሄ አላገኙም፤ ጭራሽ ጥያቄው ትክክል አለመሆኑን ነገሯቸው። ..መስራት ስላልቻሉ ገንዘባቸውን
አስረክበውና በአደባባይ ተዘርፈው ወደ አሜሪክ ተመለሱ። በአንድ ወቅት ዝርዝሩን አቶ ዳዊት ለኢሳት ቲቪ ገልፀውት
ነበር። …ያላቸውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ ስመለከት ተቆጨሁ፤.. ምክንያቱም ”አገር ቤት ቢሆን የስንት ስራ አጥ ወገኔ
ጉሮሮ ተደፍኖ ባደረ ነበር?..” ብዬ ነበር መቆጨቴ።..አቶ ዳዊት ከተባረከ ቤተሰቡ ጋር ጥሩ ኑሮ ይኖራል። ምንም
የጎደለበት ነገር የለም። ..”ይብላኝልሽ ያልታደልሽ አገሬ”…
(ከአዛሪያስ ጋር ቺካጎን ከመልቀቄ ከአንድ ወር በፊት….)
https://freedom4ethiopian.wordpress.com/
No comments:
Post a Comment