Monday, September 23, 2013

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ተጫዋች ጌታነህ በደቡብ አፍሪካ እየተሳካለት ነው


(ከዳዊት ጋሻው)
የቀደሞው የደቡብ ፖሊስና ደደቢት እንዲሁም የዋሊያዎቹ አጥቂ ጌታነህ ከበደ በደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪሚየር ሊግ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ መጥቷል፡፡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ደቡብ አፍሪካው ቢድቬስት ዊትስ ክለብ የተዛወረው ጌታነህ፣ ክለቡ ባደረገው ወሳኝ የነጥብ ጨዋታ ላይ ከመሸነፍ የተረፈባትን ግብ በ90ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ ነጥብ እንዲጋራ አስችሎታል፡፡ በዚህም ክለቡን ከሽንፈት የታደገ ዕንቁ ተጫዋች መሆኑን አስመስክሯል። getahun kebede SA
ጌታነህ ወደ ደቡብ አፍሪካ ካቀና ወዲህ እስካሁን ሦስት ወሳኝ ግቦችን ማስቆጠር የቻለና የአገሪቱ የስፖርት ቤተሰብ ዓይኑን የጣለበት ተጫዋች መሆን ችሏል። ጌታነህ ስምንት ክለቦች ብቻ በተሳተፉበትና ኤም ቲ ኤን በተባለው የቴሌኮም ኩባንያ በተዘጋጀው ውድድር ላይ ሁለት ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ሁለተኛው ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል፡፡ በዚህም መሰረት በኤም ቲ ኤን ውድድር ላይ ሁለት፣ በአብሳ ፕሪሜር ሊግ ደግሞ አንድ በድምሩ ሦስት ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን የሚያሳየው እንቅስቃሴም አስደሳች መሆኑን የዊትስ ዩኒቨርሲቲ አሰልጣኝ ተናግረዋል፡፡
ጌታነህ ከበደ የሚጫወትበት ዊትስ ክለብ አምስት ጨዋታዎችን በማድረግና 10 ነጥቦችን በመሰብሰብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ ቢድቬስት ዊትስ በሚቀጥለው መስከረም11 ቀን ከሜዳው ውጪ በደቡብ አፍሪካ አብሳ ፕሪሜር ሊግ ደረጃ ሰንጠረዥ አምስተኛ ላይ የተቀመጠውን ሰን ዳውንሰንን ይገጥማል፡፡
የዋልያዎቹ አጥቂ ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ቦትስዋናን 1ለ0፣ ጋቦሮኒ ላይ ኢትዮጵያ ቦትስዋናን 2ለ1 እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድንን 2ለ1 ስታሸንፍ ወሳኝ ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ ሀገሪቱ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ስታደርግ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ከሳላዲን ሰኢድ ቀጥሎ ሁለተኛ ነው፡፡ ሳላዲን በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ አምስት ግቦችን አስቆ ጥሯል፡፡
ጌታነህ ከበደ ከብሔራዊ ቡድን በተጨማሪ በደቡብ ፖሊስ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተሰየመ ሲሆን፤ ለደደቢት እግር ኳስ ክለብ በተጫወተባቸው ጊዜያት ኮከብ ግብ አስቆጣሪና ኮከብ ተጫዋች በመሆን ስኬታማ ጊዜያትን አሳልፏል፡፡
zehabesha

No comments:

Post a Comment