Friday, October 26, 2012

ሐይማኖት ወይስ ኳስ…አንድ ሚያደርገን….



እኔን የሀይማኖት ጉዳይ በጣም እያሳሰበኝ ነው። አመለካከቴንም እየለወጠው ነው  ። ምንም እንኳን አያስፈልጉም ማለት ባልችልም ነገር ግን ሀይማኖት ሰዎችን የሚለያዩና የሚከፋፍል ከሆነ ምን ይሰራሉ ፤አሁን እንደምናየዉ ሰውን አንድ እያደረገ ያለው ኳስ እየሆነ መቷል ስለዚህ ሀይማኖትን ከማስፋፋት ይልቅ ትልልቅ የዕግር ኳስ ሜዳዎችን መገንባት ነው ሚሻለን፤  በቅርቡ እንደተመለከትነው ቢሄራዊ ቡድናችን  ዋልያዎቹ ሲያሸንፉ ያየነው ደስታ በእውነቱ እንዴት እንደገረመኝ አትጠይቁኝ  ማለቴ ያየሁት የኢትዬፒያዊነት ስሜት በእውነቱ አይቸው አላውቅም በጣም ነበር ደስ ያለኝ ።


ታዲያ ሃይማኖት ነው ኳስ ለኛ ሰዎች የሚያፈልገን፤በአሁኑ ሰአት አገራችን ላይ እንኳን በጣም ብዙ ሀይማኖቶች አሉ    የሀይማኖቶች መብዛት ግን ምንም አልጠቀመንም የበለጠ እያጠበበን መጣ እንጂ ………

ሀይማኖቶች ከተቋቋሙበት አላማ ወይም እውነት ወተው የገንዘብ መሰብሰቢያ  የዝሙትና የመዳሪይ ቦታዎች ሆነዋል ፤የፖለቲካ ማራመጃ  ሰውን አንድ ከማድረግ ይልቅ ዘረኝነትን ማስፋፊያ ከመሆን አልፈው ርካሽ ቦትዎች ሆነዋል እውነት አምላክ የትኛው ነው
እስኪ እናንት ሃይማኖተኞች እውነት ማን ነው ፈጣሪ ዘረኛ ፖለቲከኛ ነበር እንዴ ….እንደዚህ እርስ በእርሳችን እየተባላን  ሀይማኖት መሪ ነኝ አያሉ በስከጀርባ ተንኮልን ዘረኝነትን  ዝሙትን የምናስፋፋ ከሆነ ብንሞት ይሻለናል ። አሁን ሀይማኖት አለን ከምንለው ሰዎች
ያ ከሃዲ የተባለው ኦሾ አይሻልም እንዴ   እሱ ቢያንስ ሰዎችን በቆዳ ቀለማቸው አለየም ሰዎችን አንድ አድርጎ ነበር እኮ ። እስኪ የትኛው ሀይማኖት ነው እኛን አንድ እያደረገን ያለው….በፍጹም …..ስለዚህ አንድ ሆነን እንድንቀጥል የሚያደርገን ሀይማኖት ነው  ኳስ….
አሁንስ ደሞ ለማኝን ሀይማኖት እየለየን መርዳት  በመጀመራችን    ለማኞችም አለባበሳቸውን መለዋወጥ ጀምረዋል አሉ  ምክንያቱም ሀይማኖታችን እንደዚህ  እየለያየንና እየበታተነን ነውና….


ሀይማኖተኞች እንዳትቀየሙኝ    እውነቱን ነው  የምነግራችሁ……….

Saturday, July 28, 2012


በአማርኛ የተተረጎሙ የሶፍትዌር ወይም አጠቃላይ የኮምፒውተር አጠቃቀም ቪዲዮ ትምህርቶችን
የእውነት ቲም አዘጋጅቷል ከፈለጉ ይጠይቁን የተለመደውን አድራሻ ይጠቀሙ!!
Ethio3@live.com
በቅርብ ቀን የስልክ አድራሻ እናስቀምጣለን
Ewunet team!





እንደምን ናችሁ የእውነት ተከታታዮች መረጃ ልስጣችሁ ሶፍትዌር ይፈልጋሉ ይጻፉልኝ
ካሉበት ድረስ ይደርስዎታል ሌላም ጥያቆ ካለዎት ይጻፉልን፡፡
Ewunet team

Thursday, July 19, 2012

እውነት/fact




እውነት ምንድን ነው ፡እውነተኛ ነኝ ይላሉ፡ስለእውነትስ ጽፈው ያውቃሉ፡መጻፍስ ይፈልጋሉ፡በእውነት እውነት ምንድን ነው፡ማንስ ነው እውነተኛ፡የሚፈልጉትን እውነትና ያለዎትን እውነት ለእውነት ይጻፍ ፡በደንብ ይሳተፍ፡፡

አንድን የፈለጉትን አስተሳሰብ እውነት ነው ብለው ካሰቡ በቃ ይላኩልን የዎጣልዎታል ፡፡

አንድ ነገር አሰብኩ ስብከትም ፍልስፍናም አይደለም ግን እውነት መሰለኝ  ፡እኛ የምንኖረው መኖር የተፈቀደልንን እንድናስብ የተፈቀደልንን እንድንናገር የተፈቀደልንን እንጂ እኛ የፈለግነውን አይመስለኝም ስለዚህ የተፈቀደላችሁን እውነት ለእውነት ይጻፍ፡፡
እኛ ሰዎች በቃ ሰዎች ነን ፡እኩል ፡ማለቴ ሰው በመሆናችን ብቻ ፡ምንአልባት ጠይም ፡ ጥቁር ፡ ቢጫ ፡ ነጭ  ሌላም ሌላም …
ነገር ግን ሰው ነውና የፈለገውን ነገር ከሰው ውጭ ያልሆነውንና የማይሖነውን ሊሆን አይገባም ፡፡ግን ከሆንን ሰው ማለት ደሞ እውነት ከሆነ ለምን አንዱ በሌላው ላይ ይነሳል ፤አንዱ ለምን የሌላውን ሰውነት ይቃዎማል ፤እንዲህ ስል የተለያየ አመለካከት ፡አስተሳሰብ ፡ ሐይማኖት አይኑረን ማለቴ አይደለም  ፤ምንአልባት የተለያየን ልንሆን እንችላለን ፤ማንም ቢሆን ይህን ሰው የመሆናችንን እውነት ሊቀማን አቅም አለው እንዴ ፤ባይሆን ጥሩ ነው ከሆነ ግን የእውነት ጠላት ነው ማለት ነው፤ እውነት ሰው ነው አልተባባልንም እንዴ 

ወይ ጉድ አንድ ነገር ረስቸ በናታችሁ ፤ሰው  ሰው እንዲሆን ብዙ እውነቶች እንዳሉት ፤ሰው እነዳይሆን ደግሞ መገለጫዎች  አሉት 

፤ማለቴ ውሸት የሚሆንበት ፤ሰው ይህ እውነት ሌሎች እውነቶችን መናቅ አለበት እንዴ ራሡንስ ብቻ መውደድ አለበት እንዴ ;እኔ አይመስለኝም ፤እንዲህ የምለው እኔ የመሰለኝን ነው ፤እናንተ የመሰላችሁን እውነት ለእውነት ይጻፍ፤ በቃ ሁላችንም ያሉንን እውነቶች ለእውነት ካየን  ካወራን ብቻ ነው እውነትን የምናገኘው፤ምክንያቱም ሰው ይህ እውነተኛ እውነት በዙሪያው ብዙ ነገሮች ስላሉ ማንነቱን ማለቴ እውነትነቱን ሊያጣ ይችላልና 

፤እውነቶችን በእውነት ብሎግ እንፈትሸው ምክነያቱም እውነት አንድ ብቻ ነው፡፡

ፖለቲካ ሐይማኖት ከለር ዘር አካባቢ ድንበር ሐገር  ሌላም ሌላም… በፍጹም አይወስነውም ምክንያቱም  እውነት ፡እውነት ብቻ ስለሆነ 

ግን ይህ እውነት ለምንድን ነው ያልሆነውን የሆነው ;አውቃለሁ የማንሆነውን የምንሆነው ያልነበርነውን የነበርነው የሰማነውን ያልሰማነው  ምንም ጥያቄ የለውም ሁሌም ባይሆንም ድህነቱ ወይም የመጣበት እውነት የተሳሳተ እውነት ስነሆነ ይሆናል ፡፡

ይህ እኔ ያሰብኩት ነው ፤እናንተ ደሞ ያሰባችሁትን የምታስቡትን ጻፍትና ይመዘን እውነት ከሆነ  ጥሩ ካልሆነ ደግሞ ድንጋይ ነህ ብለው ይጥሉታል ፡፡

እኛ ውስጥ የሚፈጠሩ በጣም ብዙ እውነቶች አሉ፡፡ለምሳሌ ዲሞክራሲ አምባገነናዊነት ዘፈቀዳዊነት……. ሌለም የሚፈጠሩት እኛ ውስጥ ነው 

ምክንያቱም ውስጣችን የሚኖረው ለኛ ከኛ በኛ ውስጥ ብቻ ነውና    ፤እስኪ ውስጣችን ያለውን እድሜልክ እስራት የተፈረደበትን እውነት ለፍርድ እናቅርበው ፤በእውነት ፍርድ ቤት ማለቴ በኛ ብሎግ በሰዎች ፡፡ምንአልባት እኮ
ሌላ ምድር ሌሎች የተደበቁ እውነቶች ቢኖሩስ ፤ገባችሁ እውነት በቁፈራ ማለቴ በጥረት የምትገኝ ናት ማለት ነው አደል እንዴ፡፡

ግን የምር እስኪ እንነጋገር  ጓደኛሞች አደለን እንዴ  ዝም አንበል ሂትለርም እኮ እውነት ነበረው ግን ያእውነት እሱ ጋር በቻ ነበር  ለዛ እኮ ነው የተሳሳተው እሱን ብጠይቁት አሁን ምን የሚል ይመስላችኋል…

ግን እውነቱን በእውነት ሚዛን መዝኖት ቢሆን ኖሮ ምንአልባት ስሙ በጥሩ ይነሳ ነበር ምክንያቱም መነሻ ምክንያቱ በሱ ውስጥ ያለው እውነት እውነት ነበር፤

ለዚህ ነው ሰዎች የምጨቀጭቃችሁ ለእውነት ጻፍ ተወያዩ በውስጣችሁ በጣም ብዙ እውነት እኮ አለ፡፡

ብዙ ፕላኔቶችን ብዙ አስገራሚ ነገሮችን አዋቅን … አሁንስ ..አሁንም እኮ በጣም ብዙ የተደበቁ እውነቶች አሉ 

በእውነት አደባባይ እውነቶችን  እናውራባቸው ለመዎያየት ሰው ብቻ መሆን በቂ ነው ፤በቃ እውነት በኛ ውስጥ ነች  እላለሁ እናንተስ  በናንተ ውስጥ  ወይስ ሌላ ፡፡ምንድ ነው አውነት ግን እውነት አለ እንዴ እኔ መሰለኝን ጻፍኩ እናንተስ ለሀሳባችሁ አትንገብገቡ አቦአትቋጥሩ፡፡

እኔ በቃኝ  ቻው ይህ ነው የመሰለኝ!!

Use this e-mail address  ethio3@live.com