ወይንሽት ተውልዳ ካደገችበት ሃገርዋ (ኢትዮጵያ) ወደ አርካንሳስ (አሜሪካ) ከመጣች ወደ ዘጠኝ
ዓመት ገደማ ይሆናታል እናቷ በሞት ከተለያቻት ብኋላ ከምትኖርባት ቤት ተባራ አንድ እናት አሰጠግተዋት ሰትኖር ቆይታ
በኋላም ኦርፍነጅ ሆና ይህን እድል አግኝታ ወደ አሜሪካ መታለች ::
ገነት የመሰላት አሜሪካ ገነት አለመሆኑን ደጋግማ የተናገረችው ወይንሽት ኑሮ ቢደላትም የውሰጥ ፍላጎትዋ ሃገርዋ
መመለስ ነበር ይህን ለማድረግም ብዙ ሞክራለች በተለይ ልታሳድጋት ያመጣቻትን እናትዋን በጣም ከመጥላቷ የተነሳ ሌላ
ቤተሰብ እንዲፈለግላት ጠይቃም እንደማይሆን ሲነገራት ፖሊስ በመጥራት እና አልፎ አልፎ ለመታያት(እኔን ከልጆቿ እኩል
አያየኝም የሚል ሰሜት ነበራት) social worker (በዚህ መልክ የመጡትን ለተወሰነ ግዜ የልጆችን ደህንነት
ለመከታተል የሚመደቡ የመንግስት ሠራተኛ ) ለሆኑት ልብስ የለኝም አይገዙልኝም ብላ እሰከመክሰስ ደርሳለች ::እነሱም
ያላትን ልብስ ፎቶ በማንሳት ማሰረጃ አቅርበዋል ይህን ሰታዩ “ወይ ቅብጠት ” ትሉ ይሆናል ነገሩ ግን እንደዛ
አይደልም በአንድ ወቅት በዚህ መልክ የወጣችውን ታሪኳ ለኔ እንደነገረችኝ ከሆነ ” ቲቪ፣መጫወቻው፣ ትልቅ ቤት መኖሩ
እና መዋኛ መኖሩ አይደለም የሚያሰደስተኝ እኔ የምፈልገው ይሀን አይደለም ቤተሰቦቼን፣ ሃገሬን፣ ጓደኞቼን ነው”
ያለችኝን አልረሳውም ይሄንንም ሆኔታ በተለያዩ አጋጣሜዋች አይተናል ሁሉም ነገር ቢሟላላቸው ባዶነት እንደሚሰማቸው
ከተለያዩ ልጆች ይሰማል ይህ ደግሞ ከምንም በላይ የሆነ ነገር የሆነና ምንም አይነት ጥረት ቢደረግም ይሄን ሰሜት
ከውሰጣቸው መፋቅ አይቻልም ከነተረቱ “የሰው ልጅ የሰው ነው ” ይባላል ::
ከዚህ ሁሉ ብኋላ ወይንሽት ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ እድል አግኝታ ከአባቷና ከሁለት እህቶችዋ ጋር ሄደች መመለሷ ግዜያዊ ቢሆንም አላማ ነበራት፣ አላማዋም ቤተሰቦችዋን ማፈለግ ነበር ቀደም ሲል ቤተሰብ እንዳለላት የተነገራት ወይንሽት “አለኝ አጎቶች አሉኝ ” ብላ ሰትከራከር ትሰማ ነበር በዚህ ሁኔታ ግዜ ሳታጠፋ ፍለጋ ገብታ ባጋጣሚ ወንድም እንዳላትና ገጠር እንደሚኖር ሲነገራት እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት ማልቀስ ጀመረች እድሜውን ጠይቃ ታላቋ መሆኑን ስትረዳ ለምን አልፈለገኝም ለምን ተለየኝ የሚል ጥያቄ አቅርባ ገጠር የሚኖሩት አያቷ ውሀ የሚቀዱበት ቦታ እሩቅ በመሆኑ እና እሳቸው መቅዳት ሰላማይችሉ እሱ በዛ መንገድ እንዲረዳ ወደዛ መላኩን አስረድዋት:: የወይንሽት አሳዳጊ ሄደን እናግኘው የሚል ሃሳብ አመጣ ነገር ግን እሷ ፍቃደኛ አልነበረችም ሰለዚህ እሱ ወዳለችበት እንደሚመጣ ተሰማምተው በንጋታው ወንድሟ ተገኝቶ መጣ ተቃቅፈው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ጥያቄውን አዥጎደጎደችለት ይህም ወንድሟ እንደማይማርና የቀን ሰራ እየሰራ እንደሚተዳደር ለማወቅ ችላለች ወንድሟም ማልቀስ ሲጀምር “አይዞህ ከአሁን በኋላ ምንም አትቸገርም አለሁልህ አታስብ እኔ የማለቅሰው ደስ ስላለኝ ነው ” በማለት ልታጽናናው ሞክራለች ::
ወይንሽት አማርኛ መናገር መርሳቷና አለባበስዋ ያስገረማቸውን ጓደኞችዋንና ሰራተኞች ለሚጠይቋት ጥያቄዋች “ከውጪ
ተቀየርኩኝ እንጂ ውስጤ ያው ነኝ ኢትዮጵያዊነቴን አለቀኩም አማርኛም እሰማለሁ መናገር ቢያቅተኝም እሰማለሁኝ ::
የምኖርበትም ቦታ እኔ ብቻ ነኝ ሌላ ኢትዮጲያዊ የለም ” ስትል መልሳለች :: በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ቀለማት
የተሰራውን የእጅ ጌጥ ምን ያደርግልሻል አንቺ ጥለሻት ሄደሻል ብሎ ከእጇ ሊያወልቅ ለሞከረው ወጣት ” እኔ
እፈልገዋለሁ እወደዋለሁ” ብላ መለሰችለት:: በዚህ ያላቆመችው ወይንሽት ለአሳዳጊዋ በግ ገዝታ ሰጦታ ቃክፋይ)
በማበርከት የኢትዮጵያዊነት ባህልዋን እንዳልረሳች በተግባር አሳይታለች::
ወደ ምትወደው ሃገርዋ ለአጭር ግዜ የመጣችው ወይንሽት፣ ግዜው ደረስና ወደ አሜሪካ መመለሱ በጣም እረበሻት
ማልቀሰም ጀመረች ሆኖም መቅረት እንደማትችል ተደጋግሞ ሰለተነገራት ከማልቀስ ሌላ ምንም አላደረገችም:: አሜሪካ
ከገባች በኋላ የሚያሳድጓት ቤተሰቦችዋ እሷ እንደምትፈልገው ኢትዮጵያዊ ባይሆኑም ባይወልዷትም በሚችሉት መንገድ ፍቅር
ሰተው እንዳሳደግዋትና እሷም በፊት ብትጠላቸውና በትፈልጋቸውም አሁን ግን በጣም እንደምትወዳቸው 12 ክፍል
ሰትመረቅ በሰጠችው ንግግር ገልፃለች ::
በመጨረሻም እኔ ይህን ልጽፍ የፈለኩበት ምክንያት ማየት ፈልጋቹ ማየት ላቃታቹ (አልከፈት ላላቹ) ትንሽ ሰለ
ወይንሽት በጥቂቱም ቢሆን እንድታውቁ በማለት ነው :: ይሄን ቪዲዮ አይታችሁ ካላሰለቀሳቹ ግን በቃ ልባችሁ ተመልጧል
ማለት ነው http://worldchannel.org/programs/episode/girl-adopted/
No comments:
Post a Comment