Tuesday, October 22, 2013

ለመወደድም ገደብ ይኑረው!





ለመወደድም ገደብ ይኑረው!
መለየት ግድ ሆኖ እውነት የሆነ ዕለት፣
ሐዘን እንዳይሰብርህ እንዳትወድቅ ድንገት፣
ከሰዎች ተጋርተህ የምትኖረው ሕይወት፣
በመጠኑ ይሁን ገደብ አብጅለት፡፡
ይህን ሳታስተውል ክፉንም ሳታስብ፣
ከሰዎች ተዋደህ ኖረህ ያለገደብ፣
የግድ ያጣህው ዕለት የምትወደውን ሰው፣
ልብህ ይሰበራል ዳግም ላትጠግነው!!
የታላቋ ቀን ልጅ 2001 ዓ.ም (Son of the great day 2009)

No comments:

Post a Comment