Friday, October 11, 2013

እስክንድር ነጋ በአራት ጎብኚዎች ብቻ እንዲጎበኝ ተደረገ


Eskinder Negaታዋቂው የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሚገኝበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በተላለፈ ትዕዛዝ መሰረት የጎብኚዎቹ ቅጥር መወሰኑን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ለፍኖተ ነጻነት ገለጹ፡፡
የመስከረም 19/2006 ሰላማዊ ሰልፍ ብስጭት ከፈጠረባቸው አካላት መካከል አንዱ የሆነው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብስጭቱን አደባባይ ያወጡበትን እርምጃዎች መውሰድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው፡፡ለአንዷለም አራጌ የጎብኚዎቹን ስም እንዲሰጥ ካልሆነ ግን በማንም እንደማይጎበኝ የነገረው አስተዳደሩ የእስክንድርን ጠያቂዎች ቁጥር በአራት መወሰኑ ታውቋል፡፡
ህገ መንግስቱ በግልጽ እስረኞች በወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሊጠይቋቸው በሚፈልጓቸው ሰዎች መጎብኘት እንደሚገባቸው ቢደነግግም የቃሊቲው መንግስት ግን ህገ መንግስታዊውን ድንጋጌ በመጣስ በማን አለብኝነት የእስክንድር ጠያቂዎችን በዝቅተኛ ቁጥር ገድቧል፡፡
የማረሚያ ቤቱ ምንጮች እስረኞች ጥፋት ሲፈጽሙ እንዲህ አይነት ህግ ለተወሰነ ግዜ እንደሚወጣባቸው በማስታወስ በእነ እስክንድር ላይ የተላለፈው ውሳኔ ግን ‹‹ጥፋት መፈጸማቸው ሳይነገራቸው ፣ፈጸሙት ለተባለው ጥፋትም ቀርበው መከራከሪያ ሳያቀርቡ መሆኑ ውሳኔውን ፖለቲካዊ ያደርገዋል››ብለዋል፡፡
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተመሳሳይ መልኩ ከጥቂት ሰዎች ውጪ እንደማትጎበኝ እርሷን ለመጠየቅ የሚፈቀድላቸው ሰዎችም ለአስር ደቂቃ ብቻ እንደሚያገኟት ከዚህ ቀደም መዘገቡ አይዘነጋም፡፡



 zehabesha







No comments:

Post a Comment