Thursday, October 17, 2013

የሃሰት መንገድ ሁሌም መጥፊያ እንጂ መዳኛ ሆኖ አያውቅም!!



ባለፈው ቅዳሜና እሑድ (በ12/10/2013 እና በ13/10/2013) ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን
እና አካባቢውን ያናወጠ የአባ ግርማና ተከታዮቻቸው የሃሰትና የእብሪት ሥራ ውጤት።
ባህረ ሃሰቱን የምንሻገርበት የእውነት መርከብ ማን ይሰጠናል? አትፍራ! እውነት አባትህ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐ. 14:6) እርሱ
መንገድም፤ እውነትም፤ ሕይወትም ነው። መንገድ ነው ትሰማራበታለህ፤ እውነት ነው ትይዘዋለህ፤ ሕይወት ነው ትኖረዋለህ!! ቃሉ
እውነት ነው (ዮሐ.17፡ 17) በቃሉ ስትኖር እውነት አርነት (ነጻነት) ያወጣሃል።
በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የተፈጠረው ችግር አስተዳደራዊ ጉዳይ ብቻ ሆኖ ሳለ ሊፈታም የሚችለው በአስተዳደራዊ መንገድ ብቻ
መሆኑ ፍንትው ብሎ እየታወቀ፤ የመጨረሻው መፍትሔም ሆነ ውሳኔ ሰጪ ደግሞ ሕዝብ (የቤተ ክርስቲያኑ አባላት) መሆናቸው
በቃለ ዓዋዲውም ሆነ በቻሪቲ ሕግ ላይ በግልጽ ተደንግጎ እያለ ለሕዝብ ድምጽና ውሳኔ መገዛትም ሆነ መታዘዝን እንደ ውርደት
የሚቆጥሩት አባ ግርማ ከበደና ደጋፊዎቻቸው ሥጋዊ ዓላማና ምኞታችንን ሊያሳካልን ይችላል ብለው ያመኑት ለጉዳዩ ሃሰታዊ
የሃይማኖት ሽፋን በመስጠት እውነት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በመካድ በሃሰት መንገድ ተጉዘን ሕዝብን አሸንፈን ነግሰን
እንኖራለን አሉ።
በጀመሩት የሃሰት ጎዳና በሃሰት ላይ ሃሰት፤ በተንኮል ላይ ተንኮል፤ በእብሪት ላይ እብረት በመደራረብ በሕዝብ መካከል የሃሰት
ክምርን በመቆለል ሕዝቡ እርስ በእርሱ ተነጋግሮና ተመካክሮ ችግሩን በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ እንዳይፈታ ጋሬጣ ሆኑበት።
የሃሰት ተባባሪና የእከከኝ ልከክልህ አጋር በመፈለግም በአንድ በኩል የወያኔን ሥርዓት በደልና ግፍ ፈርተን ተሰደድን እያሉ በጎን
ደግሞ አሰደደን የሚሉትን ሥርዓት ተነጥፈንለት በላያችን ላይ ይረማመድ ከሚሉ የወያኔ አገዛዝ ደጋፊና አቀንቃኝ “የሰሜን
ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት” እና የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሹማምንቶች ጋር ግንባር በመፍጠር ሌላ የሃሰት ተባባሪና የሥርዓቱ
አፈ ቀላጤ ጳጳሳትን ከኢትዮጵያ አስመጡ።
ከጳጳሳቱ ጋር በመሆንም የቤተ ክርስቲያኗ ዋልታና ማገር የሆኑትን አባላቷን በማግለል በአቋም ልዩነት ምክንያት ከቤተ ክርስቲያኗ
ተገንጥለው የራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ያቋቋሙ አብያተ ክርስቲያናትን አባላት በመሰብሰብ ምእመን የተባለ እንዳለም ሳይቆጠሩ
ተባባሪያቸው የሆኑ ካህናትን ብቻ ሰብስበው የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደርም ሆነ ሃብትና ንብረት በሃገረ ስብከቱ ሲል እንዲውል
የሚል ውል በማስፈረም አጸደቅን አሉ።
ነገር ግን የክርስቶስ መንገድ የሆነውን እውነትን በጽናት ይዘው የሚገኙት የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም
ቤተ ክርስቲያን ቁርጠኛ አባላትና ደጋፊዎች ይህንን ሕዝብን የናቀና ያገለለ አንባ ገነናዊ አሰራር በመቃወም ባደረጉት ትግል
በፈጣሪአቸው ተራዳኢነት በወረቀት ላይ የሰፈረውን የክህደት ፊርማ ከወረቀት ማድመቂያነት አልፎ አንዳችም ፋይዳ እንዳይኖረው
ሊያደርጉት ችለዋል።
ሃሰትና ቅጥፈት የአባ ግርማ ከበደና ደጋፊዎቻቸው፤ ቋሚ ሥራቸውና መታወቂያቸው በመሆኑ እውነት የሞት ያህል
ታስፈራቸዋለችና እውነት ፈጦ በመጣ ቁጥር ተንደፋድፈው በሃሰት ቀለም በመቀባት ለማዳፈን መሞከር የሆሌም ተግባራቸው
በመሆኑ ቻሪቲ ኮሚሽን በ25 June 2013 በተጻፈ ደብዳቤው በቤተ ክርስቲያኗ (ቻሪቲው) ውስጥ የተነሳው ክርክር (Dispute)
በሁለት ወገን የተከፈለ መሆኑን በማመን ለሁለቱም ወገን እውቅናን ከሰጠ በኋላ በአንዱ ወገን ይህ ነው ተብሎ በግልጽ ሊታወቅ
የሚችል Trustees አለመኖርንና በሌላ በኩል ደግሞ አባላት AGM ጠርተው ያካሄዱት የTrustees ምርጫ አብዛኛውን አባላት
አላካተተም በማለት የሁለቱንም ወገን መከራከሪያ ግልጽ ውሳኔ ለመስጠት እንደያስችል አረጋገጠ።
ይህም በመሆኑ ቻሪቲ ኮሚሽን በቻሪቲና በሃገሪቱ ሕግና የአሰራር ደንብ መሠረት ጉዳዩ በውጪ ሽምግልና (Mediator) እንዲታይ
መመሪያ ሲሰጥ አባ ግርማና ደጋፊዎቻቸው በተለመደው ቅጥፈታቸው “ቻሪቲ ኮሚሽን እኛን ተቀበለን” በማለት ቀደም ሲል
ከቻሪቲ ኮሚሽን የተሰጣቸውን website page pass word ተጠቅመው አዲስ የሾሟቸውን አምስት ሰዎች ሥም ዝርዝር በገዛ
ፍቃዳቸው በማስገባት ቻሪቲ ኮሚሽን ስማቸውን ተቀብሎ አጽድቆ እንዳስገባላቸው አድርገው የሃሰት ወሬ በመንዛት
ደጋፊዎቻቸውን ምንም እንደማያውቁ ህጻናት በመቁጠር በሃሰት ጎዳና እንዲነዱ አደረጉ። ከዛም በመቀጠል ወደ Mediator
Service ያልሄዱበትን ምክንያት እስከ 30/08/2013 መልስ እንዲሰጡ በቻሪቲ ኮሚሽን ሲጠየቁ፤ ጠበቃ ስለቀየርን ነው የሚል
ምክንያት በመሥጠት ቀነ ገደቡ እስከ 17/09/2013 እንዲራዘምላቸው ቻሪቲ ኮሚሽንን ጠይቀው አስፈቀዱ፤ ከዛም በመቀጠል ቀነ
ገደቡን በማሳለፍ ሌላ የማይያዝና የማይጨበጥ መረጃ ለቻሪቲ ኮሚሽን በማቅረባቸው በመጨረሻ ቻሪቲ ኮሚሽን ራሱ በጉዳዩ
ውስጥ ገብቶ አስፈላጊውን መፍትሔ ለመስጠት በመወሰን የሁለቱም ወገን ተወካዮች በ21 October 2013 ቻሪቲ ኮሚሽን ዘንድ
ቀርበው ጉዳያቸውን እንዲያስረዱ በ04/10/2013 በጻፈው ደብዳቤ መመሪያ ሰጠ። በዚህ መልክ እውነት የሚወጣበትና እውነት
የምትዳኝበት ቀን ፈጥጦ ሲመጣ አባ ግርማ ከበደና ደጋፊዎቻቸው ከእውነት ጋር ፊትለፊት ላለመተያየት ሲሉ የተለያዩ ሕገወጥና
የሰላም ጠንቅ የሆኑ ተግባራትን በማከናወናቸው ቀጥሎ የተዘረዘሩት ክስተቶች ሊፈጠሩ ችለዋል።፤
1. የቤተ ክርስቲያኑ አባላት የሚጸልዩበት ቦታ የሰዎችን እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ወንጀለኛ አድርጎ ለማቅረብና
ለማስፈራራት በማሰብ ሕጋዊ ፍቃድ (Planning permission) የሚያስፈልገውን መሬት በሕገ ወጥ መንገድ በማስቆፈር
በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከፍተኛ ወጪ የተደረገበት ሕገ ወጥ CCTV አስተከሉ፤
አባ ግርማ በሕገ ወጥ መንገድ ሕዝበ ክረስቲያኑን ለማስፍራረያ ያስተከሉት CCTV ካሜራ
2. ከዚህም በማያያዝ በድጋሜ የሃሰት ተባባሪና የክፉ ሥራ አጋር ይሆኑልናል ያሏቸውን ሁለት ከኢትዮጵያ የመጡ ጳጳሳትን
የሃገረ ስብከት ተብዬው ሊቀ ጳጳስ ጋር በማዳበል የግል ቤታቸው ይመስል በመንፈሳዊ ሳይሆን በሃሰታዊ ኃይል
ተጠቅመው 7 ወር ሙሉ ዘግተው ሕዝቡን ለመከራና ስቃይ የዳረጉበትን ቤተ ክርስቲያን ለእውነተኛ ጸሎትና ቅዳሴ
ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኑን አባላት አሸንፈን ቤተ ክርስቲያኗን የራሳችን አደረግን ለማለት ብቻ ሲሉ በዕለተ ቅዳሜ
12/10/2013 ቤተ ክርስቲያን እንከፍታለን በማለት አዋጅ አሰሙ።
3. ዓርብ ዕለት ምሽት በዋዜማውም የCouncil (የአካባቢ አስተዳደር) ንብረት የሆነውን የቤተ ክርስቲያኑን አጥር ግቢ
መግቢያ ሁለት በሮች በሕገ ወጥ መንገድ በወፍራም ባለሰንሰለት ቁልፍ አስቆለፉ። (ዓላማውም የቤተ ክርስቲያኑ
አባላትን እውጪ ለማስቀረትና አባ ግርማና ተከታዮቻቸውን እንዲሁም ሌሎች ከወያኔ አገዛዝ ሥርዓት ጋር ቁርኝት
ያላቸውን የሥላሴና የጸራጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላትን በኃይል አጠናካሪነት ለይቶ ለማስገባት ታስቦ ነበር።)
በሕዝበ ክረስቲያኑ ላይ የተቆለፈው በር
4. ቅዳሜ 12/10/2013 በጠዋት የደረሱ የመሰላቸው አባ ግርማ ከበደ ፋሲል በቀለ ከተባለው አጃቢና ጋሻ ጃግሬአቸው ጋር
በመሆን እቤተ ክርስቲያኑ አጥር በር ላይ ሲደርሱ ቁርጠኛ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት የአጥሩን በሮች በአንድ አይደለም
በሁለት ጥንድ፤ ጥንድ ተጨማሪ ሰንሰለቶች ሌሊቱን ጥርቅም አድርገው ቆልፈዋቸው ስለነበር አባ ግርማ ከበደ እንደግል
ቤታቸው ቁልፍ እያወዛወዙ ያሰሩበትን ሰንሰለት ቁልፍ ከፍተው እገባለሁ ሲሉ የማይሞከር ነገር ሆነ። በዚህ ክስተት አባ
ግርማ ከበደ የሚገኙበት ሃገር የት እንደሆነና የሰውን መብት መጣስ ደግሞ ምን ያህል አዳጋች እንደሆነ ማወቅና
መረዳት ነበረባቸው።
5. ከአራት ሰዓት ላላነሰ ጊዜ አባ ግርማ ከበደ ከብረት አጥር ጋር ተፋጠው እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ግቢው የሕዝብ
መገልገያ (Public space) በመሆኑ ከካውንስሉ በስተቀር ማንም ሊዘጋውና ሊቆልፈው ስለማይችል በፓሊስ አማካኝነት
በተጠራ ቁልፍ ሰራተኛ (Locksmith) አማካኝነት ሁለቱም የአጥር በሮች ላይ የተቆለፉት በድምሩ 6 ሰንሰለቶች በብረት
መቁረጫ ተቆርጠው በሩ እንዲከፈት ተደርጎ ማንኛውም ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ የመግባት መብቱ
ሊጠበቅለት ችሏል።
6. አባ ግርማና ተከታዮቻቸው ከሃገረ ስብከት ተብዬው፤ ከሥላሴ ቤተ ክርስቲያንና ከኤምባሲ ሹማምንቶች ጋር በመተባበር
ቤተ ክርስቲያኑን እንከፍታለን የሚሉት የአንድን ሃገር ሰውና የአንዲት ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ በሆነው በሕዝብ
መካከል የሃሰት እሾክ አሜኬላ ዘርተውና አብቅለው በመካከሉ መራራቅን በመፍጠር ከቤተ ክርስቲያን ውጪ እንኳ
አብሮ ሆኖ ጸሎት ማድረስ እንዳይችል ካስደረጉት በኋላ፤ ቤተ ክርስቲያን እስከመዘጋት የተደረሰበት ምክንያት አንዳችም
ሰላማዊና ፍትሓዊ እልባት ሳያገኝ 7 ወር ሙሉ ተቆይቶ አሁን ቻሪቲ ኮሚሽን ጉዳዩን በመካከል ሆኖ ለማየት በመወሰኑ
ችግሩን በጠረጴዛ ዙርያ በመነጋገርና ከዛም ካለፈ ሕዝብ እርስ በእርሱ ሳይበጣበጥ ሕግን ተከትሎ ውሳኔ ለማግኘት
በተቃረበበት ወቅት ያንን ፍትሐዊ አካሄድ ለማሰናከል ነበር።
7. እውነትን ፊት ለፊት ከማየት ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተን ሕዝቡን በማበጣበጥና በማጋደል፤ ጥፋቱ የሕዝቡ እንጂ
የኛ አይደለም በማለት ራሳችንን ከደሙ ንጹህ እናደጋለን የሚል ሰይጣናዊ ዓላማ ይዘው የተነሱት አባ ግርማና
ተከታዮቻቸው በዕለቱ ቤተ ክርስቲያኑን እንከፍታለን ያሉበት ሰዓት ሲቃረብ በቤተ ክርስቲያኑ የቪካሬጅ ህንጻ የጓሮ በር
በኩል ከኢትዮጵያ መጡ የተባሉትን ጳጳሳት ሙሉጌታ አሥራትን ጨምሮ በሌሎች የወያኔ አገዛዝ ኤምባሲ ሰዎች
አሳጅበው በሽሽግ ካስገቧቸው በኋላ ሸሽገው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በር ለማምጣት ሲሞክሩ ከቤተ ክርስቲያኑ አባላት ጋር
ከፍተኛ ረብሻ ተፈጠረ።
8. የቤተ ክርስቲያኑ አባላት በአንድ ወገን ሲሆኑ በሌላ በኩል ግን በሹሞቻቸው የሃሰት ስብከት ተታለው ከሥላሴና ከጸራ
ጽዮን አብያተ ክርስቲያናት የመጡ እንዲሁም በአባ ግርማና በተከታዮቻቸው ካህናት የሃሰት ስብከት የተደለሉ ጥቂት
የቤተ ክርስቲያኑ አባላትና ባብዛኛው አባ ግርማና የወያኔ አገዛዝ ወኪሎች (Agents) ያደራጇቸው የቤተ ክርስቲያንን
ደጃፍ ረግጠው የማያውቁ በጎሳ ትስስርና በአሽከርነት አገልግሎት ወያኔ የሌላውን ኢትዮጵያዊ (scholarship) ዕድል
ነጥቆ የላካቸውና በስደት ሰበብ ወደ እንግሊዝ ሃገር የመጡ ወጣት ጋንግስተሮች (የለንደን ወያኔ ፌደራል)ጋር በመሆን
የአባላትን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ ቢሞክሩም እውነቱን ይዘው በጽናት በቆሙ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ቁርጠኛ ትግል
ቤተ ክርስቲያኑን በመክፈት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲመጣ ታስቦ የነበረው ከፍተኛ ብጥብጥና ሁከት በውጪ አልቆ
የቤተ ክርስቲያኑን መከፈት በፓሊስ መመሪያ ሊቀር ችሏል።
9. ቤተ ክርስቲያኑ ለብጥብጥና ለረብሻ ተብሎ አለመከፈቱ ከተረጋገጠ በኋላ በድብቅ የጓሮ በር ገብተው በካህናት መኖሪያ
(Vicarage) ውስጥ እንደተደበቁ የቀሩት ጳጳሳት ደጋፊዎችንን ሳናነጋግር አንመለስም ብለው ለጠሯቸውና ለጋበዟቸው
የአባ ግርማ ተከታዮች ጸሎት እንድናደርስ 10 ደቂቃ ይሰጠን በማለት ለፓሊስ በማመልከታቸው ፓሊስም የማምለክ
መብታቸውን መጋፋት ይሆንብኛል በሚል 10 ደቂቃው እንዲፈቀድላቸው የቤተ ክርስቲያኑን አባላት ስምምነት ጠየቀ።
ሆኖም ግን በቦታ አመዳደብ ላይ ፖሊስ የቤተ ክስቲያኑን አባላት ከተለመደው ቦታቸው ለማራቅ በመሞከሩ የቤተ
ክርስቲያኑ አባላት ከፍተኛ ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንት በማድረግ የተነፈጋቸው መብታቸው ተመልሶላቸው በጳጳሳቱ
የሃሰትና የተንኮል ተባባሪነት የተሰማቸውን ቅሬታ በመፈክር በማሰማትና መንፈሳዊ መዝሙር በመዘመር ጳጳሳቱ
ተደብቀው በገቡበት የጓሮ በር ተመልሰው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል።
እሑድ 13/10/2013
ቤተ ክርስቲያኑን አባ ግርማ ከበደ ዘግተውት ሕዝበ ክርስቲያኑ በውጪ ቁር ላይ መጸለይ ከጀመረ 7 ወራት ያለፉት ሲሆን በነዚህ
ወራት ባሉ እሑዶች ሁሉ አንዳችም ቀን ሳይዘንብ የደጁ ጸሎት ያለምንም ችግር ሲካሄድ ከቆየ በኋላ በዕለቱ ግን መቆሚያ የሌለው
ዘናብ ይወርድ ነበር።
ገና በጠዋቱ ቀድመው የደረሱት የቤተ ክርስቲያኑ አባላት ያዩት ነገር ቢኖር የቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት በብረት ማገጃዎች
(Barriers) መታጠሩንና ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ መግቢያ በሮች በፓሊስ ኃይል በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን ነበር።
ቀጥሎም ከፓሊስ አመራሮች ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት ጳጳሳቱ እስካልመጡ ድረስ እንደተለመደው በግቢው ውስጥ
በሁለት ተከፍሎ የሚደረገው ጸሎት እንዲካሄድ ሕዝቡ እንዲገባ ተደርጎ ሁለት ሰዓት የፈጀ ጸሎትና የወጌል ስብከት ከተካሄደ
በኋላ ሕዝቡ ቅጥር ግቢውን እየለቀቀ በመውጣት ላይ እያለ፡
1. የወያኔ አገዛዝ ሥርዓት ተወካዮችና አባ ግርማ ያደራጇቸው (የለንደን ወያኔ ፊደራሎች) ግለሰቦች ከቤተ ክርስቲያኑ አጥር
ውጪ አንድን ታዋቂ ሃገር ወዳድና ለሃገሩና ለሕዝቡ ገጣሚ ግለሰብ አድፍጠው በመጠበቅ ጥቃት አድርሰውበት ደሙን
ካፈሰሱ በኋላ፤ የእጅ ስልኩን ነጥቀው ወንጀል ሰሪውን ልብስ አስቀይረው ከፓሊስ ለማስመለጥ ሲሞክሩ ከፍተኛ ግርግር
በማስነሳታቸው ከፍተኛ ሁከት በአካባቢው ተነሳ።
2. ከዛም በመቀጠል እነዚሁ ልዩ ተልዕኮ የያዙ ግለሰቦች በተሰጣቸው መመሪያና ሥልጠና መሠረት ታዋቂና የቤተ
ክርስቲያኑ አባላትን፤ ሥራ አመራሮችን፤ አዛውንቶችንና ታዋቂ የወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚ ግለሰቦች ላይ በማተኮር ፓሊስ
በማያይበትና ምስል በማይቀረጽበት ሁኔታ የብረት ከፈፍ ባለው ጫማ አማካኝነት ከበው በእግር በመማታት በሰዎች
አካል ላይ ጉዳት ለማድረስ ጥቃታቸውን በስፋት ለማካሄድ ሲሞክሩ፤ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት በከፍተኛ ደረጃ
የተጋፈጧቸው ከመሆኑም በላይ ወዲያውኑ ፓሊስ ጉዳዩን ደርሶበት ከፓሊስ ጋር ከፍተኛ ግጭት በመፍጠር ጉዳዩ
በፓሊስ ቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።
3. እነዚህ በጥቅም፤ በክፍያና በጎሳ ፓለቲካ ቅስቀሳ አዕምሮሯቸው የተለከፈና የወያኔ አገዛዝ ሥርዓት የጥቃት መሣሪያ
በመሆን በስደተኛው ኢትዮጵያዊ ላይ ጉዳት ለማድረስ የዘመቱ ወጣቶች የቤተ ክርስቲያኑ አካባቢ ረብሻ ካበቃ በኋላ
ወደ ሌላ አካባቢም በመዝመት በአንድ የቤተ ክርስቲያን አባል ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ጉዳት ያደረሱ ሲሆን
ለንደን ውስጥ የሚገኙ ማራቶን እና አዲስ አበባ የተባሉ ሁለት የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች በመሄድ በሰዎች ላይ ጉዳት
ለማደረስ አስፈራርተዋል፤ በንብረትም ላይ ጉዳት አድረሰዋል።
በዕለቱ በቤተ ክርስቲያን አባላት ላይ ወንጀል ከፈጸሙት ከነዚህ ግለሰቦች ውስጥ አምስት ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉ
ሲሆን ከነዚህም ውስጥ:
1. ቲዎድሮስ ገብሩ
2. ዳዊት ግርማይ
3. አማኑእል ኪዳኔ የሚባሉ ይገኙባቸዋል።
ከላይ የተዘረዘረው በሃገረ እንግሊዝ በኢትዮጵያውያን ማህበረ ሰብ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ተግባር ምንጩም ሆነ
ተሞክሮውና ከኋላ ሆኖ የሚያደራጀውና የሚቀነባበረው ማን፤ ለምን፤ እና እንዴት እንደሆን ስደተኛው ኢትዮጵያዊ ለማወቅ
የሚያዳግተው አይሆንም። ይህም በመሆኑ ይህ አይነቱ ድርጊት እንዲቀጥል ዝም ብሎ ከታየ ስደታችን ሳይበቃ በነጻነት ሃገር የወያኔ
ፌደራል ተቋቁሞ ነጻነታችንን በመግፈፍ ትተን የመጣነውን ጭቆና፤ የሰብዓዊ መብት ገፈፋና በስጋትና በጭንቀት መኖርን አሜን
ብሎ መቀበል ስለሆነ ጉዳዩ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ሰበብ ይምጣ እንጂ የወያኔ ዘረኛ አገዛዝን የአፈና ቀንበር በስደተኛው ላይም
ለመጫን የሚደረግ የእብሪት ሙከራ ስለሆነ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ሁሉ ጊዜ ሳይወስድ በመንቀሳቀስ በፍጹም
ቁርጠኝነት ሊዋጋውና ሊያጠፋው ይገባል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

No comments:

Post a Comment