Saturday, October 19, 2013

በመንዝ ከፍተኛ ረሃብ ተከስቷል


(ዘ-ሐበሻ)  በሰሜን ሸዋ ዞን ምንዝና ገራ ምድር ወረዳ ነዋሪዎች ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸውን አስታወቁ፡፡ የወረዳው ነዋሪዎች ከመሃል ሜዳ ረሃብ ከሐምሌ ወር 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የተከሰተ ቢሆንም፤ ከመስከረም 2006 ዓ.ም. ይበልጥ ረሃቡ በመባባሱ ምክንያት ሰዎች ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የክልሉ ባለስልጣናት ለኢህአዴግ አባላት ብቻ እየመረጡ የዕርዳታ እህል እየሰጡ መሆኑንና ተቃዋሚ ናቸው የሚባሉት ከነ መላው ቤተሰቦቻቸው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸው ተጠቁሟል፡፡
ከረሃቡ ጋር በተያያዘ የወረዳውን፣ የዞኑን እና የክልሉ  አመራሮች አመራሮች ምላሽ እንዲሰጡን ብንጠይቅም ምላሽ ማግኘት አልቻልም፡፡ ይሁን እንጂ አማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ንጉሴን ስለሁኔታው ጥያቄ ስናነሳላቸው ካዳመጡ በኋላ መረጃው የለኝም በማለት ስልካቸውን ጆሮአችን ላይ ዘግተዋል፡፡ በተጨማሪም የዝግጅት ክፍሉ የክልሉን ፕሬዘዳንት ወደ ሆኑት አቶ አያሌው ጎበዜ ተንቀሳቃሽ ስልክ ብንደውልም ስልካቸውን ሊያነሱልን አልቻሉም፡፡


zehabesha

No comments:

Post a Comment