Wednesday, October 23, 2013

ህወሓትና ስብሃት! Abraha Desta

አንድ የድሮ የህወሓት ታጋይ ነው። አሁንም መከላከያ (ሰሜን ዕዝ) ነው የሚሰራው። ስለ ህወሓት ወቅታዊ ሁኔታ ሲጀነጅነን ነበር። የህወሓት ‘ጥሩነት’ ይሰብከናል። ስብሃት ነጋ የድሮ ታጋዮች እያሰባሰበ ‘ህወሓት የማዳን ዘመቻ’ መጀመሩ ነገረን።
ስብሃት እንዴት ህወሓትን እንደሚያድናት ብዙ ጥያቄዎች ሰነዘንርለት። በመሃል አቋርጦ … “ኤጭ ስብሃት’ኮ ግን እባብ ነው። በ 70ዓም በሽሬ ገበሬዎች (ገባር ሽረ) ዶሚኔት (dominate) ተደርገናል በሚል ሰበብ ሆን ብሎ ‘ሕንፍሽፍሽ’ (ዉስጣዊ ብጥብጥ) በመፍጠር ህወሓት የግሉ (የቤተሰቡ) ያደረገ ሰው ነው” አለን።
የድሮ ታጋዩ በዉስጡ ሐዘን እንዳለ ከስሜቱ ይነበባል። ይቺ የሽሬ ገበሬዎች የምትለዋን ነገር ራሳቸው ህወሓቶች ባዘጋጁት ። “ሙሴ” የተሰኘ ፊልም በደንብ ይንፀባረቃል። በፊልሙ ገበሬዎቹ ‘የሙሁራን ፎብያ’ እንደነበራቸውና ‘ሙሁራን ዶሚኔት አድርገውናል’ ብለው ማመፃቸው፣ በኋላም መሸነፋቸው ያሳያል።
እውነታው ግን ብጥብጡ (ሕንፍሽፍሹ) ያቀናበሩት እነ ስብሃት ነበሩ። ምክንያታቸውም በሽሬ ገበሬዎች (ገባር ሽረ) ዶሚኔት ተደርገናል የሚል ነበር። እነ ስብሃት ‘እኛ ሙህራን ነን። የፓርቲው አመራር በሙሁራን እጅ መሆን አለበት’ በሚል ሰበብ ፓርቲው ተቆጣጠሩት። በዚህ መንገድ የሽሬ ገበሬዎች ከቁልፍ ቦታዎች ተወገዱ። ገባር ሽሬ በጦርነቶች (ግንባር) እንዲዋጋ ሆነ፤ የነ ስብሃት ነጋ ቤተሰብም ወደ መሪነት መጣ። ሽሬዎች በጦርነቱ አለቁ። ስብሃቶች መሪዎች ሁነው ቤተመንግስቱ ተቆጣጠሩ።
አሁን እስቲ ስብሃት ነጋ ህወሓት ማዳን አለብን ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ይሆን? የሚወገዱስ እነማን ይሆኑ? ግን አትድከሙ በአሁኑ ሰዓት ህወሓትን ማዳን አይቻልም። ግን ህወሓት ተወልዶ እስኪያድግ ድረስ ግዜ የወሰደበትን ያህል ሞቶ እስኪቀበር ድረስም ግዜ ይወስዳል።
(ለማንኛውም በሐየሎም አርአያ የትግል ታሪክ የሚያጠነጥን መፅሐፍ በቅርቡ ይወጣል። ከመፅሓፉ የምናገኘው ነገር ይኖራል ብዬ አስባለሁ።)
It is so!!!Abraha Desta

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/22/521-2/



No comments:

Post a Comment