Wednesday, October 30, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ የአመራር ሽግሽግ አደረገ



በዘሪሁን ሙሉጌታ

ሰማያዊ ፓርቲ በተጓደሉ የፓርቲዎች አመራሮች ምትክና በአሁኑ ወቅት አመራር ላይ የሚገኙ አመራሮች መካከል ሽግሽግ አደረገ።
የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት አባላት ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ሁለት  አዳዲስ የፓርቲው አመራሮች ኃላፊነት እንደተሰጣቸው አዲስ የተሾሙት የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አስታውቀዋል።
አዲሱ የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፀው በፓርቲው ፕሬዝዳንት አቅራቢነት ለብሔራዊ ም/ቤቱ ቀርበው የተሾሙት የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ወጣት ኃይለገብርኤል አያሌው ለስራ ጉዳይ ደቡብ ሱዳን በመሄዳቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በስደት ላይ ባለው በወጣት አርአያ ጌታቸው ምትክ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ እንዲሁም በወጣት ኃይለገብርኤል ምትክ ወጣት ዮናታን ተርሣ መተካታቸውን ሕዝብ ግንኙነቱ ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ወረታው ዋሴ ቀደም ሲል ከነበሩበት የፓርቲው ጥናትና ስትራቴጂ ጉዳይ ኃላፊነት ወደ ፋይናንስ ጉዳይ የተዛወሩ ሲሆን በእሳቸው ምትክ ደግሞ ወጣት ደሳለኝ ነጋ እንዲተካቸው ተደርጓል ብለዋል። ቀደም ሲል ምክትል የሕዝብ ግንኙት ኃላፊ የነበረው ወጣት አሮን በስራ መደራረብ ሳቢያ ወደ ጥናት ምርምር መቀየሩንም አያይዘው ገልፀዋል።
የፖለቲካ ሽግሽጉ ከፖለቲካ ልዩነት ጋር የተያያዘ አለመሆኑንና በቀጣይ ፓርቲውን ይበልጥ ወደፊት ከማራመድ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ኃላፊው ገልፀዋል። በተያያዘም ባለፈው ቅዳሜ “ወጣቶችና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይዞታ” በሚል በአዲስ አበባ የታሪክ መምህር በሆኑት በአቶ ሰለሞን ተሰማ የቀረበው ውይይት በመጪውም ቅዳሜ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።¾  
 
ሰንደቅ.......

No comments:

Post a Comment