Friday, October 11, 2013

የአውራ ጣት ቀለበት



የአውራ ጣት ቀለበት
የማዕረግ ጣቶችሽ ሌጣቸውን ሆነው፣
መዋብ ሲናፍቁ ተራቁተው ታርዘው፣
የጌጥ ያለህ ሲሉ ቀለበት ተርበው፣
ስለእነሱ እያሰብኩ አትኩሬ ባያቸው፣
የትኛው ጌጣችን ውበታችን ማርኮህ፣
ፈዘህ የምታየን እምባ እስኪያቀር አይንህ፣
ይልቅ አውራውን እይ ዘመን ተለውጧል፣
ንግስቶች ተራቁተው ባሪያቸው አጊጧል፣
ብላ ተናገረች የጣቶችሽ ንግስት፣
የኪዳን ሰንደቋ ክብርን የነፈግሻት፡፡
እውንም ከአውራ ጣትሽ አኖቼን ባሳርፍ፣
ቀለበት ባይበት አለኝ እንደመቅፈፍ፣
አርበኛ/አዳኝ እንዳልልሽ ዱሩን አታውቂውም፣
አሮጊት አልልሽ ወዝሽ አልነጠፈም፣
ምን ይሆን መልዕክቱ እኔን አልገባኝም፣
የአውራ ጣት ቀለበት የማድረግሽ ትርጉም፣
አንጃ እኔን ቀፈፈኝ እንዳይሆን የመርገም?!
የታላቋ ቀን ልጅ ነሀሴ  2005 (Son of the great day August 2013)

No comments:

Post a Comment