Friday, October 11, 2013

ዋልያዉ እንዴት ዋለ??የአማካይ ለዉጥ….ሽልማት….ጉዳት..ቤተ ክርስትያን!!



ዛሬ ልምምዱ ዋናዉን ጨዋታ ይመስል ነበር፤እርስ በርስ ጨዋታዉ በዋልያዉ አማካይ ክፍል ላይ ለዉጥ እንደሚኖር ጠቋሚ ሁንዋል፤አዲስ ህንጻ በተጠባባቂ ቡድኑ ዉስጥ ነበር የተጫወተዉ..የዋልያዉ አማካይ ክፍል በአዳነ ግርማና አስራት መገርሳ ጥምረት የሚጫወት እንደሆነም የዛሬዉ የልምምድ ግጥሚያ አሳይትዋል፤የጎል ገደኛዉ በሀይሉ አሰፋ (ቱሳ) የቀኝ አማካይ ክፍሉ ላይ በዋናዉ ቡድን ተጫዉትዋል፤በግራ አማካይ ምንያህል እንዳለ ነዉ፤ከሳላሀዲን ጀርባ ሽመልስ በቀለ ተጫዉትዋል..እናም ትላነት ከነበረዉ ዋና ቡድን የተለወጠዉ የአዲስ መዉጣትና የቱሳ መግባት ነዉ!!
ዋልያዉ ትላንት ምሽት የናይጄሪያና ማላዊን የወዳጅነት ጨዋታ በኢንተር ኮንቲኔንታል ተከታትልዋል፤አሰልጣኞቹና ተጫዋቾቹ በጋራ እየተወያዩ ነዉ ጨዋታዉን ያዩት..
ዛሬ ምሽት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተሰናባቹ ፌዴሬሽን ዳጎስ ያለ ሽልማት ለተጫዋቾቹ አበርክትዋል፤በሴንትራል አፍሪካ ጨዋታ በደርሶ መልሱ በሁለቱም ለተሰለፉት 100ሺ ብር ስጦታ ተበርክትዋል፤ከዛም 65 እያለ አስከ 20ሺ ድረስ ያኔ የነበሩ አሁን የሌሉ ተጫዋቾች ሳይቀሩ በተሰናባቹ ፌዴሬሽን ተሽልመዋል፤በነገራችን ላይ  በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተጫዋቾቹ የቀድሞዉን አመራር ጠርተዉ አመስግነዋል፤በስማቸዉ የተሰራም ኬክ አስቆርሰዋል፤በእናንተ ዘመን ነዉ ያለፍነዉ እናመሰግናለን ነዉ መልእክቱ…
ጌታነህ ከበደ ብቻ በጉዳት ላይ ይገኛል፤የሱን ጉዳይ ለብቻዉ ስለምነግራችሁ አዲስ ነገር ጠብቁ!!የደቡብ አፍሪካዉ ዊትስ ቡድን ሀኪሞች..የዋልያዉ ዶክተሮች…እና ሌሎች እንደማይደርስ አረጋግጠዋል፤እኔ ና ሌሎች 2 ሰዎች ግን ተስፋ አልቆረጥንም!!
የነገ የዋልያዉ ፕሮግራም እንዲህ ነዉ፤3.30 ላይ ትሬኒንግ..ከዛም ምሳ..ጥቂት ቆይቶ መክሰስ..ልክ 12 ሰአት ላይ ደግሞ በጎፋ ገብርኤል ቤተ ክርስትያን ተጫዋቾቹና አሰልጣኞቹ የጸሎት ፕሮግራም ያካሂዳሉ፤በነገራችን ላይ ቄራ ለሁሉም እምነት ተከታዮች የተመቹ ቤተ እምነቶችን ያካተተ ሰፈር መሆኑን ልጠቁማችሁ..ከሜክሲኮ ስትመጡ የቄራ ሰላም መስጊድ..ጎፋን አለፍ እንዳላችሁ ዊነር የፕሮቴስታንት ቸርች…ከዛም ጎፋ ገብርኤል..ካቶሊክም እዛዉ አቅራቢያ አለ..ሰፈሩ የሚታወቅበት ባህላዊ እምነት(የእጅ ስራም)ቢሆን መኖሩን ማንም አይክድም!!
የነገ ሰዉ ይበለንና የዋልያዉን ዉሎ እናያለን!!
 http://www.ethiotube.net

No comments:

Post a Comment