ኤሎሄ! ቅዱስ! ኤልሻዳይ! አዶናይ! ያህዌ! ጸባዖት! ኢየሱስ! ክርስቶስ! አማኑኤል! በአብ
በወልድ በመንፈስቅዱስ ሥም! አሜን! አቤቱ አባት ሆይ እኛን በሥጋ በመዛመድ የወደድከንን ያህል እኛም እንደልጅ የአንተን የአባታችንን
ፍቅር የምናውቅበትን ማስተዋል ትሰጠን ዘንድ ከእኛ ወገን በሆነች
በቅድስት፣ንጺኅትና ዘላለማዊት ድንግል እናትህ ማሪያም ስም እንለምንሀለን!
አሜን!
ብዙዎቻችን ባለማወቃችን ምክነያት፣ ብናውቅም ባለመንጠንቀቃችን ወይም በክፉ ባህሪያችን ምክነያት ብዙ ችግሮች እገጠሙን
እንደሆነ አሁንም አናስተውልም፡፡ ይህ ጽሁፌ እርስ በእርሳችን ተጠራጣሪ እንድንሆን አይደለም፡፡ ግን ማስተዋል ያለብንን እንድናስተውል
ነው፡፡ አንዳንዴ የራሳችን ባህሪ ክፋት የሰይጣንን እገዛ የማያስፈልገው ሊሆን ይችላል፡፡ ከአንዳንድ በተለየ ልምምድ ከራስ በላይ ለሌላው የሚል ለየት ያለ እምነት ካላቸው የአለማችን ጥቂት ሰዎች
በስቀር ሌሎቻችን ሁሌም ለራሳችን እናስቀድማለን፡፡ ከእኛ ውስጥ ደግሞ አሁንም የበዛንው የጓደኛችን ወይም ቅርብ የምንለው ሰው ስኬትና
ደስታ አያስደስተንም ይልቁንም እነመቀኘዋለን/ታለን፡፡ ይህን ክፉ ስሜታችንንም መቃወም ሲገባን ጭራሽ በክፉ ስሜታችን ምሪት የወዳጃችንን
ስኬትና ደስታ ለማጥፋት ስውር ገዳይ መርዝ እናመነጫለን፡፡ በፊትለፊት ግን ለወዳጃችን ከእኛ በላይ "ወዳጀ" የለም!
ገዳይ መርዝነታችን ግን በአኛ፣ በሰይጣንና፣ በእግዚአብሔር ይታወቃል፡፡ እኛ ክፉዎቹና ሰይጣን በእኛ መርዝ ወዳጃችን ሲወድቅ እንደሰታለን
እግዚአብሔር ግን ያዝናል ግን ጊዜ ስላለው ይታገሳል፤ ሰይጣን ኃጥያታችንን በደንብ ያስመዘግባል፣ እግዚአብሔር ክፋታችንን የምንረግምበት (የንስሐ) ሌላ ዕድል ይሰጣል፡፡
እግዚአብሔር ታላቅነታችንን ስለሚያውቅ ታላቅነታችንን
የወደቀውን ወራዳ ሰይጣን ስናሸንፈው ማየትን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን የወደቀ ስለሆነ ደካማነታችንን ኃይል ያደርጋል፡፡ ሰው ግን ከመላዕክትም
ልዩ የሚያደርገው ካጠፋም በኋላ ልጅ ስለሆነ ይቅርታ አለው፡፡ ክፉውንም ደጉንም የመስራት ፍቃድም አለው፡፡ በመላዕክት ዘንድ ያለው
ግን አንድ ብቻ ነው! ወይ ክፉ ወይ መልካም፡፡ እኛ ለክፋታችንም ይሁን ለመልካምነታችን ግን ወሳኙ እግዚአበሔርን ለማወቅ የምናደርገው
ጥረት ነው፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው አንድ አሰፈሪና አደገኛ ነገር አለ፡፡ "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት
መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው" ይላል፡፡ በዚህ አረፍተነገር ውስጥ እግዚአብሔርን ለማውቅ
ያለመውደድ መጠን/ልክ እንዳለው እናስተውላለን፡፡ የማይረባው አእምሮም እንግዲህ ባለመውደዳችን መጠን ነው የሚሰጠን፡፡ አንዳንዶች ብዙ ብናጠፋም የተወሰነችም ብትሆን እግዚአብሔርን ለማወቅ የምናደርጋት
ፍላጎት/ጥረት አንድ ቀን ከወደቅንበት የምታነሳን ልትሆን ትችላለች፡፡ ጥፋታችን ግን ከባሕሪ የተዋሀደ ከሆነ ሰይጣንን ስለምንወክል
ይቅርታ ላይኖረን ይችላል፡፡ የክፋታችንን መጠን በሚከተሉት አራት የሰውን መግደል ወንጀሎች ለማሳየት ወደድሁ፡፡ ሰዎችን በጥይት
ወይም በሌላ በሚታይ ነገር መግደል ይቀርታ ይኖረዋል እውን ከልብ መጸጸቱ ካለ፡፡ በስውር መርዝ በመስጠት የገደለ ይቅርታ ይኖረዋል
ግን ልቡ ለመጸጸት ምን ያህል እድል አለው፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ ውስጥን መዝምዘው የሚገድሉ መርዞችን (carcinogenic) አብልቶ
በቁም ሲሰቃይ እያየ ወዳጁን የገደለ የይቅርታ እድሉ የመነመነ ነው፡፡ ከሁሉ በከፋ ደግሞ በእርኩሳን መናፍስት (መተት) ወዳጁን
የገደለ/የጎዳ ለንስሐ ሊሆን የሚችል ሕሊና ከቶውንም ላይኖረው ይችላል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ አለማዊ ፍርድን የሚያሰጡ
ጥፋቶች ስለሆኑ በምድርም የምንቀጣባቸው ናቸው፡፡ ሦስተኛው በተለየ ምርመራ አለማዊ ፍርድን ሊያሰጠን ይችላል አራተኛው (መተቱ)
ግን የዘላለም ፍርድን ብቻ የሚጠብቅ ነው፡፡ ስለዚህ የሚቀልልን ነገር
የለም! ምነው አለማዊ ፍርድ በተፈረደብን ልክ የዘላለማዊው ፍርድ ሊቀሊልን ይችል ነበርና፡፡
ለብዙዎቻችን የመንግስተ ሰማይና የገሀነም ነገር ተረት ተረት ነው፡፡ አመንም አላመንም ግን እውነታው እውነት ነው፡፡
አለማመናችን የእግዚአበሔርን ቃል እውነትነት ሊሽረው አይችልም፡፡ መንግስተ ሰማያትም ገሀነምም አሉ!! ሊያውም የሁሉ ፈጣሪ ሆኖ
ሳለ በፈጠራት በራሱ የተደነቀች መንግስተሰማይ! በፈጠረው በራሱ አስፈሪነቱ የተነገረለት ገሀነመ እሳት! እንግዲህ እጣችን ከሁለት
በአንዱ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ሳይገባን ቀርቶ ወደ እሳት የምንወድቅበት ጥፋት ብንሰራ በአለማወቃችን ነው የሚል አንደበት ሊኖረን
አይችልም፡፡ ጉዳዩ ማወቅ ባልፈለግንው መጠን የሆነብን አለማወቅ (ለማይረባ አእምሮ መሰጠት) ነውና፡፡ ከእነዚህ ከሁለት ጽንፎች
በአንዱ የሚያበቃንን ሥራ መሥራት እንግዲህ የራሳችን ፍቃድ ነው እንጂ ማንም አያስገድደንም፡፡ ይልቁንም እኛ በባሕሪያችን ክፎ ብንሆን
እንኳን በትንሽ ምህረት ፍለጋችን እግዚአብሔር ለምህረት ብዙ ዕድል እንደሚሰጥ በግልጽ ተናግሯል፡፡ ሲጀምር መንግስተሰማያት የሰዎች
ልጆች የምድር ሥራቸውን ውጤት ሳትሆን በብዙ ክፉ ሥራችንም ጽድቅን በመፈለጋችን መጠን ይችን ብቻ ስላሰብን ልዑል አምላክ ስለቸርነቱ
የሚሰጠን ናት፡፡ እንደዚያ ባይሆን ወንበዴው ስንት አመት ለተዘጋች ገነት ቀዳሚ ባልሆነ፡፡ መጸጸታችንም መሻታችንም ግን እውነተኛ
መሆኑ ነው ቁም ነገሩ፡፡ ተጸጽቻለሁ ብሎ መሸወድ በማይቻልበት ፈራጅ ነው ዳኝነቱ፡፡ ባህሪያችንን ብዙ ክፋቶች ባለማመድንው ቁጥር
ግን ይህንን እወነተኛ መጸጸት ወይም ጽድቅን መሻት አቅም ሊያንሰን ይችላል፡፡ መሸወድንም እውነት እየመሰለን ሊሄድ ይችላል፡፡ ነገሩ
ለማወቅ ባልፈለግንው መጠን ለማይረባ አእምሮ መተላለፍ አለና ነው፡፡ ከላይ እንደምሳሌ ከጠቀስኳቸው ግፎች (ሁሉም ክፋቶች ናቸው
ሊያውም ሰውን መግደል) ሰዎችን በእርኩሳን መናፍስት አጋዥነት ያጠፋ አእምሮው ከልቡ ለመጸጸት እድሉ ከሁሉ የጠበበ ነው፡፡ በአብዛኛውም
መታቾቹና አስመታቾቹ እንደ ልዩ ጥበብ አድርገው የሚመኩበት ሁሌም የገደሉትን ሰው ወዳጅ ሆነው የሚኖሩበት ሌላ የቀረ ወገኑንም በወዳጅነት
የሚገድሉበት፡፡ ጠላት በጠላትነቱ ቢያጠፋ በምክነያት ወይም አልሞት ባይ ተጋዳይ ነው፡፡ በየቧህ ወዳጁ ላይ ክፉን የሚሰራ ግን ለማን
ጥሩ ሊሰራ እድል አለው?
ክፉ መናፍስት ከዘር፣ በልክፍት መልክ፣ በቡዳነትና በመሳሰሉት ሊገቡብን ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ዘመን ግን የክፉ መናፍስት
ዋነኛ ምንጭ መተት እየሆነ መጥቷል፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ አሰመታቾቹ በብዛት የቅርብ ጓደኛ ወዳጅ ሆነው መገኘታቸው አጠፋንው ብለው
በውድቀቱ ከሚደሰቱባት የቧህ ወዳጃቸው ይልቅ በራሳቸው ላይ የከፋ የገሀነም ፍርድ እያቆዩ እንደሆነ ሊገነዘቡ የሚችሉ አይመስልም፡፡
ለማይረባ አእምሮ ተላልፈው ተሰጥተዋልና፡፡ ዛሬ ብዙዎች አንድ ስኬት ላይ ለመድረስ ያዝንው ሲሉ የሚወድቁበት ዋነኛ ምክነያት መተት
በብዛት ደግሞ የጓደኛ መተት ነው፡፡ የወዳጅነት ስጦታዎች በብዛት በገዳይ መርዞች (መተት) የተመረዙ ናቸው፡፡ ወደ ውጭአገር ሰው
ሲሸኝ በወዳጆቹ በሚጎርፉለት የመተት ስጦታዎች ነው፡፡ አዳሜ ያልፍልናል ብለን አገር ለአገር እንከራተታለን ግን መዳረሻችን ሁሉ
ምነው የእኔ እድል እንዲህ የመንከራተት ብቻ ሆነ እያልን ዘመናችንን ጨርሰን ኋላም አይሆኑ ሆነን ወደማይቀረው እንሄዳለን፡፡ በዛም
በእንክርት የጨረስንው ዘመን ዕዳ ሆኖብን ለነፍሳችንም አደጋ ይሆንብናል፡፡ እኛ ችግራችንን መቼ እንዲህ እንደሆነ አወቅን? አንቺ
ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል!! ብዙ በጣም ይቀርቡናል የምንላቸው ሰዎች
ሚስጢር ሲገለጥ ጉዳዩ ብዙ ነው፡፡ እንደ ጠላት በቀጥታ በምናየው ነገር ቢያጠቁን ምን ያህለ ለእነሱም ፍርድ ባልከበደባቸው፡፡ ግን
"ወዳጅነታቸውን" ይፈልጉታል፡፡ ለሌላ ስውር ጥቃት ያመቻቸው ዘንድ፡፡ እነሱ ሰይጣን የሚወዳቸውን ሰው ስላጠፋለቸው
ይደሰታሉ ግን ለእነሱም መልስ ሊሰጠበት የማይችሉትን የመጨረሻ ፍርድ ሰነድ እየመዘገበላቸው እንደሆነ የሚያውቁ አይደሉም፡፡ እነሱ
ሌላውን ለማጥፋት በወደዱት መጠን የዘላላም ፍርድን (ገሃነምን) እየጠበቁ እንደሆንም አያውቁትም፡፡ እርግጥ አንዳንዶቹ ከልምምድ
ብዛት አሁን ሰይጣንን ቀድመውታል፡፡ ግን ለብዙዎች በምድር ዋጋ ቢያስከፍላቸውም የመዳን ዕድል አላቸው፡፡ አዎ ገሀነብም አለ! መንግስተሰማያትም
አለች! ምርጫችን ከየት እንዲሆን በፈለግንው መጠን ከሁለት በአንዱ መጨረሻችን ይሆናል፡፡ ክፉን የምናደርግ የበጎ ነገር ልምምድን
አብዝተን በመሞከር ክፋታችንን እናሸንፈው፡፡
ሌላው እኛ አናውቅህም ያልንው እሱ ግን አሳምሮ የሚያውቀን ከዘር እየተወረሰ የሚመጣ መንፈስ አደጋ ነው፡፡ በሆነ
ጊዜ በእኛ የዘር ግንድ ሲገበር የነበረ ክፉ መንፈስ አብሮ እየተወለደ ከትውልድ ጋር ይቀጥላል፡፡ ዛር፣ ጨሌ፣ ቦረንቲቻ፣ አመቺሳ
ሌሎችም እየተባለ ከቤተሰብ ወደ ልጅ ይተላለፋል፡፡ ዛሬ እኛ ዘመናውያን ሆንና አንገብርም ብለን በማሰባችን ብቻ የቀረልን ይምስለናል፡፡
ግን እውነታው እሱ ግብሩንም በሌላ እኛ በማናውቀው መንገድ እንድንገብረው ያደርጋል፤ በእኛ ላይም በሕወታችን ሁሉ አደጋ ይሆንብናል፡፡
አኛ ግን ዘመናዊዎች ነን ብለን ንቀንዋል፡፡ እሱ አዎ ልክ ናችሁ ይሄ የቀረ ነው እያለ ሥራውን ግን ይሰራል፡፡ አንቺ ታቦኪያለሽ
ውሻ ይደፋብሻል! ትንሽ ለማስተዋል እንዲረዳን በልዩ ልዩ መልክ እየገበርን እንደሆነ ጥቆማ መስጠት እወዳለሁ፡፡ አናስተውል! ለምሳሌ፡
በአሁኑ ዘመን የአመት በዓልም ይሁን ወራዊ በዓል ጊዜ ቤት ጎዝጉዘን ቡና አፍልተን እጣን አጭሰን ካልሆነ ደስ አይለንም፡፡ ልብ
እንበል! ይህ ነገር እነዚያ የዱሮዎቹ በቀጥታ ይህነኑ ስርዓት ለርኩሱ
መንፈስ ከሚያደረጉለት ምን የተለየ አለው? ለምንድነው በትክክልም የዚያኑ የእርኩሱን መንፈስ ግብር ዛሬም ስናደርገው የሚያስደስተን፡፡
ዛሬ ማሪያም ናት ቡና ሳላፈላ፣ ገብርኤል ነው ቡና ሳላፈላ፣ ዛሬ … በጣም አስቂኝ የርኩስ መንፈስ ድራማ እንደሆነ ማስተዋሉን ጋረዶብናል፡፡
እስኪ በየትኛው መስፈርት ነው ቅድስት ድንግል ማርያም በጀበና የምተታሰበው?!! ጉዳዩ ቡና ከመጠጣታችን ጋር አይደለም ከምናደርጋቸው
ሥርዓቶች እንጂ፡፡ ይህን ለማስተዋል አእምሮአችን ተጋርዷል፡፡ ለማወቅ ባልፈለግንው መጠን የሆነብንም እንደሆነ እናስተውል፡፡ ይህ
ጉዳይ ባሕል ተደርጎ ስለተወሰደ የእርኩስ መንፈስ ሴራ እንደሆነ ለማሰብም እድል የለም፡፡ አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! ይልቁንም
የዘመናዊው ዛር የሚካደምበት የጉዝጓዝ ሳር ዋና መገበያያው ደግሞ ቤተክርስቲያን ደጅ አፍ መሆኑ አስደንጋጭ አልሆነብንም፡፡ ሰው
ለበዓል በቤቱ ደስ ያለውን ቢያደርግ ክፋት አለው እያልኩ አይደለም፡፡ የምናደርጋቸው የበዓል ሥርዓቶች በአብዛኛው ከዘር ለመጣ ድብቅ
የእርኩስ መንፈስ ግብር አንዳይሆን እያሳሰብኩ እንጂ፡፡ ቡና መጠጣት ችግር ላይሆን ይችላል ግን ቡና ለመጠጣት ያን ሁሉ ጋጋታ ለምን
እያደረግን እንደሆነ እንድናስተውል ያስፈልጋል፡፡ ሥርዓቱ በትክክልም ከየዛርና ቃልቻው ቤት የተወረሰና ተመሳሳይ መሆኑን እናስተውል፡፡
እኛ ባህል ነው እንላለን ሰይጣን ግን በትክክልም እያስካደመን እንደሆነም አናውቅም፡፡ አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል፡፡
ዘመናውነታችን አይሎም ባሕላዊውን ሥርዓት እንኳን ብንተው በዘር ወይም በልክፍት የገባ ርኩስ መንፈስ በራሳችን ዘመናዊነት
እንድናገለግለው ያደርገናል፡፡ በተለይ ይህ የሚያጠቃው እጅግ መጥቀናል ያሉ ሳይነቲስቶችን፣ በዘፋኝነት ወይም በሌላ ተሰማርተው የተሳካላቸው
ዘመናውያን (celebrities) ነው፡፡ ሳይነቲስቶቹ ሳይንስ የላረጋገጠው የሚል እውርነት ስለሚጋርዳቸው የዚህ ሰለባ ይሆናሉ፡፡
በቀጥታ በራሳቸው እየሆነ ያለውን እንኳን አይገባቸውም፡፡ ሳይንስ ምንም እንደማያውቅ እንኳን እንዴት ማስተዋላቸው እንደጠፋ አይረዱም፡፡
በእነሱ ግንዛቤ እውነት ማለት እነሱ ያረጋገጡት ነው፡፡ ሰማያትን፣ አለም አለማትንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ እንዴት ማወቅ ይቻላል
እያሰቡ ከማድነቅ በቀር፡፡ ግን ለብዙ ሳይንቲስቶች ሰይጣን ማወቅ እንደሚቻል ሰለሚመክራቸው አይገባቸውም፡፡ የሚያሳዝነው ግን ምንም
ሳያውቁ መጨረሻም ሰይጣን እሱ በፈለገው መልኩ ተጠቅሞባቸውና አሰቃይቷቸው ይገድላቸዋል እስከዘለዓለምም የእሱ እንደሆኑ ያረጋግጣል፡፡
ብዙ በአገራችን ሰዎች የሆነውን መጥቀስ ይቻላል ግን በጣም ለግንዛቤ እንዲረዳን የሌላ አገር ሳይንቲስት አንድ እውነታ እንድናስተውል
እጋብዛለሁ፡፡ እንግሊዛዊውን የምልዓተ ዓለማት (Universe) ሳይንቲስተ ስቴፈን ሐውኪንግን እንመልከት፡፡ ይህ ሰው እስከ
21 ዓመት ዕድሜው በእግሩ ቆሞ የሚሄድ ነበር፡፡ ከዚያም እጅ እግሩን የሚያስር "በሽታ" ያዘው ተባለ፡፡ በ27
ዓመቱ ይሞታል ተብሎ እስካሁንም ከ70 ዓመቱም በኋላ እየኖረ ነው፡፡ በዊልቸር ላይ ተሸመድምዶ መናገር እንኳን የማይችል ሰው በአለም ተደናቂ ሳይነቲስት ሊያውም ምልዐተ-አለማት
(ዩኒቨርስ) ተመራማሪ፣ የምርምሩ ውጤት ድምዳሜ ደግሞ ፍጹም እግዚአብሔርን የካደ እና ሳይንስ ያሸንፋል ብሎ የሚያምን አሳዛኝ የምድር
ትል ነው፡፡ አለም አለማትን፣ ሰማያትን በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ አስቡ የእኛ አእምሮ እነዚህን ሁሉ ሊያውቅ ምንድ ነው?፡፡ የዚህን
ሰው ጉዳይ ሳይ ከመጀመሪያውም የበሽታው መንስኤ መዳረሻውም የክፉ መንፈስ አሰራር እንደሆነ አስባለሁ፡፡ እግዚአብሔርን ማሰብ የማይችሉ
ብዙ ዘመናውያን የስኬታቸውም ይሁን የውድቀታቸው ምክነያት ክፉ መንፈስ እንደሆነ የሚጠቁሙ ክስተቶች ብዙ ናቸው፡፡ ይህ ክፉ መንፈስ
ደግሞ በአብዛኛው እነሱ የማያውቁት በዘር የመጣ ጠላት ነው፡፡ እነሱ ግን ስኬታቸውም የራሳቸው ጥረት ውድቀታቸውም መክነያታዊ አጋጣሚ
ይመስላቸዋል፡፡ አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል፡፡
ዛሬ ዛሬ በዙ በዘር የሚታላለፉ ምክነያታቸው በውል ምን እንደሆነ የማይታወቁ በሽታዎች አሉ፡፡ ለመጥቀስ ያህል፤-
የስኳር፣ ደምግፊት፣ አስምና ሌሎች አለርጂዎች፣ ካንሰር ሌሎችም በዘር እንደሚመጡ ይነገርላቸዋል፡፡ በሕክምናው አንዳቸውም የተሳካ
የመዳን ተስፋ የላቸውም፡፡ ጉዳዩ ግን በዘር በሚተላለፍ ዘረ-መል (gene) ሳይሆን በዘር በሚተላለፍ እርኩስ መንፈስ (ጂኒ) እንደተያያዝ
ብዙዎቻችን አላስተዋልንም፡፡ ድሮ ያልነበረ በሽታም አሁን በዝቶ ስናይ ለምን ይሆን ብለን መጠየቅ አልፈለግንም፡፡ ይልቁንም ድሮ
የማይታወቀው ሳይንሱ ስለሌለ ነው ብለን ሽፋን እንሰጣለን፡፡ ቀላል ምሳሌ ዲስክ፣ ነርቭ ምናምን የተባለ ነገር ድሮ አልነበረም፡፡
በእርግጥም የቀደሙት በአልታወቀ ምክነያት ሰው አካሉ ሲዛባ ድሮ ሰይጣን ነው ይሉ ነበር፡፡ አሁን ሕክምናው ምርጥ ምርጥ ስም እየሰጣቸው
በሽታ ተብለው ተከበሩ፡፡ እነዚህ በሽታዎች ምርጥ ስም እንጂ ምርጥ
የተሳካ መድሀኒት ግን የላቸውም፡፡ ሰይጣን የተሰጠውን ስያሜ ከለላ አድርጎ መጫወቻው እንዳደረገን አላስተዋልንም፡፡ አንቺ ታቦኪያለሽ
ውሻ ይደፋብሻል፡፡ አንዳንድ የሰዎች መሠረታዊ ባሕሪ መዛባትን (ከተፈጥሮ ያፈነገጠ) ሳይቀር በዘመናዊው ፍልስፍና መክነያታዊ ትንታኔዎች
ተፈጥሯዊ አናደርጋቸዋለን፡፡ ከእነዚህ አንዱ ማሳያ የሚሆነው በዘመናችን ግብረሶዶማዊነት ተፈጥሯዊ (Biological)እንደሆነ ታስቦ
በሕግ ሳይቀር በአለማችን ብዙ አገራት ድጋፍ እየሰጡት መምጣቱ ነው፡፡ ጉዳዩን ምክነያታዊ በሆነው ከአካባቢ፣ በልምምድ የሚወረስ
ባሕሪ እንኳን እንደሆነ ለማስተዋል አልቻልንም፡፡ የሚያውቀውም የማያውቀውም ተፈጥሯዋዊነቱን አያጸደቀለት ነው! አንድም ሳይንስ ግን ለዚህ ማስረጃ የለውም! ምክነያቱም የሶዶማዊ ዘረ-መል
(gene) የሚባል ነገር የለም ርኩስ መንፈስ (ጂኒ) እንጂ፡፡ ርኩሱ መንፈስ የሰው ዘር እንዳይቀጥል ተመሳሳይ ፆታን አጋብቶ የራሱ
ዘሮች እንዲበዙ እያደረገ መሆኑ አልተገለጠልንም፡፡ ሊያውም የእዚህ እርኩሰት አገልጋዮቹ ከእሱ ጋር ገሀነም እንደሚቀላቀሉት እያረጋገጠ፡፡
አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል፡፡
ሌሎች ብዙ ላነሳቸው የምችላቸው ጉዳዮች አሉ ለዛሬ ግን አንድ የዚህ ሳምንት ገጠመኜን ልንገራችሁና ላብቃ፡፡ አንድ
በጎልማሳነት ያለች ሴት ባለፈው ማክሰኞ ማለት መስከረም 27 2006 ዓ.ም ወደቢሮአችን መጣች እኔ ስልክ እያወራሁ ሰለነበር ምን
እንደፈለገች ሳላውቅ ቁጭ አለች አብራኝ የምተሰራው የሥራ ባልደረባዬ ልታነጋግርህ ትፈልጋለች አለችኝ፡፡ እሺ በዬ የመጣችበትን ጠየቅኳት፣ እሷም ታማ ለሕክምና የሚሆናት ዕርዳታ እንደምትፈልግ
ነገረችኝ፡፡ በሽታዋ ደግሞ ነርቭ ነው፡፡ ግራ እጇ ተቆልሟል፤ እራሴንም ይዞኛል ነው የምትለው፤ አሁን ደግሞ ወደ አይኗ እየመጣ
እንሆነ ነገረችኝ፡፡ ውጭ አገር ሄደሽ ካልታከምሽ ዋጋ የለሽም ተብዬ ነበር ግን አቅም ስለሌላኝ አሁን ኮሪያ ሆስፒታል አፕራሲዎን
ልሞክር ነው አለችኝ፡፡ እኔ አሁን ባለኝ ግንዛቤ ችግሩ ከእርኩስ መንፈስ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ስለገባኝ የመጀመሪያ ጥያቄዬ የነበረው እምነትሽ ምንድ ነው ነበር፡፡ እምነቷን የማወቅ
ጉጉት ኖሮኝ ሳይሆን ቀጥሎ ጸበል ወይም በሌላ የመንፈሳዊ ሀይል ሞክሪ ለማለት እንዲረዳኝ ነው፡፡ በኋላም እሷው ኪዳነምህረት ጸበል
ስትከታተል እንደቆየች ስለነገረችኝና ለውጥ ቢኖረውም ለብዙ ጊዜ ሊለቃት እንዳልቻለ ነገረችኝ፡፡ ከዚያ መ/ር ግርማ የሚባሉ ሰው
ታውቂያለሽ አልኳት፣ አዎ ግን አዛ ልሄድ አሰቤ እሳቸው ጋር የሄዱ ሰዎች አስፈራሩኝ አለችኝ፡፡ ምን ብለው አልኳት፡፡ እዛ ሄደን
ሰውነታችንን የሆነ ነገር ተሰማን እና የሆነ አደገኛ መንፈስ አለ እሳቸው ጋር አሉኝ ልጄም ይህን ሰምታ እናቴ ትሞችብኛለሽ እዛ
አትሂጂ አለችኝ አለች፡፡ እኔም ነገሩ ስለገባኝ በሰዎቹ የማስፈራራት ሂደት ተገርሜ እውነታውን ነገርኳት፡፡ በእርግጥም እነዚያ ያሉሽ
ሰዎች የተሰማቸው ስሜት አለ ግን አደገኛው መንፈስ ራሳቸው ውስጥ እንጂ መ/ር ግርማ ጋር አይደለም ያለው አልኳት፡፡ መ/ር ግርማ
ጋር ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ አነሱ ውስጥ ያለውን ክፉ መንፈስ ስለአስደነገጠው ያ ሊሆን ችሏል፡፡ የሆነላቸው አጋጣሚ ጥሩ እንደሆነ
ሳያውቁ ደንብረው በዛው እንዲጠፉ ያደረጋቸው የውስጣቸው ክፉ መንፈስ እንጂ ራሳቸውም አይደሉም (አንቺ ታቦኪያለሽ…)ብዬ እስከሚገባት
አስረዳኋት፡፡ መጨረሻ አንተ ሁለተኛ ሰው ነህ እዛ ሂጂ ስተለኝ ለሰው ብናገር ስለሚከለክሉኝ ለማንም ሳልናገር ቅዳሜ እሄዳለሁ ብላ
ለራሷ ቃል ገባች፡፡እኔና የሥራ ባልደረቦቼ የምንሰጣትን ጥቂት ገንዘብ እየተቀበለች እያነባች ሀብታም ዘመዶች አሉኝ ግን አሁን አንተ
እንዳነጋገርከኝ እንኳን ሊያነጋግረኝ የሚወድ የለም እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ብላኝ ወጥታ ሄደች፡፡ አስቡት ሰዎች የምንድነበትን ቦታ
ይከክሉናል ግን ስለበሽታችን እኛን ለማነጋገር እነኳን ይጸየፉናል፡፡
አቤቱ እግዚአበሔር አባት ሆይ ባወቅንውም ባለወቅንውም ምክነያት የክፉ መንፈስ አገልጋይ አታድርገን! አሜን!
የታላቋ ቀን ልጅ መስከረም 30 2006 (Son of the great day October 10, 2013)
No comments:
Post a Comment