Friday, October 4, 2013

አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! ክፍል 1 (ቀጣይ አለው)




ቅዱስ፣ እልሻዳይ፣ አዶናይ፣ያህዌ፣ጸባዖት፣ ኢየሱስ፣ክርስቶስ፣ አማኑኤል!  በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሥም! አሜን!!
በአለም ላይ ብዙ ሚስጢራዊ ነገሮች እንዳሉ፣ ሳይንሳዊ ትንታኔዎችም  ብዙዎችን ለማደናገሪያነት እንደሚውሉ፣ አብዛኛው የአለም ሕዝብ በብዥታ እየኖረ መሆኑን ማሰብ የጀመርኩት በጣም ዘግይቼ ነው፡፡ ብዙዎቻችን ብዙ ስኬት የሚያመጡ ምንም እንከን የማይወጣላቸውን እቅዶች አቅደናል፣ ዕቅዶቻችንንም ለመተግበር ሞክረናል፣ መስዋዕትም ከፍለናል፡፡ ይሁን እንጂ ስኬት ያልንውን ልናየው አልቻልንም፡፡ ምንአልባትም እንከን አይወጣለትም ያልንው ዕቅዳችን ለውድቀት ዳርጎን የመጨረሻም ተስፋ መቁረጥን አምጥቶብናል፡፡ ብዙዎቻችንም በአጀማመራችን የት ይደርሳሉ ተብሎ ሲታሰብ ወይ ባለንበት ጫጭተን ቀርተናል ከከፋም ወድቀናል፡፡ ሀብት፣ ንብረት፣ ትዳር ያዝን ስንል የሆነ ጊዜ ይወድማል፣ አልያም ንብረቱ ሲመጣ እኛ የመከራ ሕወት መኖር እንጀምራለን፣ በትምህርት ቤትም ሰዎች እስከሚደንቁ የነበረን ብሩህ አእምሮ የሆነ ቦታ ሲደርስ ፈዞ አናገኘዋለን፡፡ ብዙ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ እንዲህ ያለው ሕወት በአብዛኛው የሚታየው ባልሰለጠኑት አለማት ሲሆን በሰለጠኑት አለማት ተቃራኒ የሚመስል ሂደት አለው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም  እኛም ዜጎቿ ከላይ የተጠቆመው ያልሰለጠኑት አገራት አይነት እጣ እንደገጠመን  ይሰማኛል፤ አሁን አሁን ብዙ የማስተውላቸውም ምልክቶች አሉ፡፡
እንዲህ ያለው የእኛ ጥረትና ችሎታ ተቃራኒ ውጤት ዝም ብሎ የአጋጣሚ ጉዳይ ይመስለኝ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በአይን የማናያቸው እጅግ ክፉ የሆኑ ጥራታችን ወደ ስኬት፣ ኑሮአችን ወደ ሰላም፣ አካላችን ጤነኛ እንዳይሆን የሚዋጉን ጠላቶች በዙሪያችን እንዳሉ ስረዳ የት ነበርኩ እስከዛሬ የሚል ጥያቄ መጣብኝ፡፡ እርግጥ እኔ ብቻ አይደለሁም ብዙ የምድር ነዋሪ ሰዎች የማይገባን ሚስጢር ነው፡፡ ሚስጢር የሆኑት ነገሮች ሁሉ ግን ለዘመናት በገሃድ ሲነገሩን የኖሩ እኛ ካላየን አናምንም ብለን የዘነጋናቸው ወይም ተረት ተረት ያደረግናቸው እንጂ አዲስ አይደሉም፡፡ እነዚህ የማይታዩ ጠላቶቻችን ግን አሳምረው ያዩናል እንድናውቃቸውም አይፈልጉም፡፡ ምክነያቱም ከአወቅናቸው ልንቋቋማቸው እንደምንችል አሳምረው ያውቁታል፡፡ በዘመናችን ብዙዎች የሚያውቁቸው ሰዎች ቢኖሩም ከእነሱ ጋር ወዳጅነት መስርተው እኛ ጅሎቹን በማሰቃየት የሚተባበሩ ይበልጠውንም መሪ በመሆን በስውሮቹ ፍጡራን በመጠቀም የሰዎች የሰቆቃ ኑሮን እርካታ አድርገው የሚኖሩ ናቸው፡፡  እኛ እንለፋለን እነሱ ያወድማሉ፡፡ አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! ነው ነገሩ፡፡ አዎ እርኩሳን መናፍስትና ተባባሪዎቻቸው በእኛው አምሳል የተፈጠሩ ጠላቶቻችን እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ በሌላው ጽንፍ የቅዱሳን መናፍስትና ቅዱሳን ሰዎችም ጥበቃ መኖሩ (እኛ አይገባንም) ነው እንጂ ብዙዎቻችን ድሮ ገና ጠፍተናል፡፡
ወደ እኛ አገር ስንመጣ  ደግሞ ከሌላውም አገር ወሰበሰብ ያለ ነገር አለ፡፡ የብዙዎቹ አገራት የእርኩሳን መናፍስት አሰራር በታወቁ ሰዎች እጋዛ ነው፡፡ በእኛው አገር ግን በግልጽ ከሚታዩት የእርኩሳን መናፍስ አገልጋዮች በተጨማሪ በቅድስና ስም የእርኩሳን መናፍስት አገልጋይ የመኖራቸው ነገር ጉዳዩን አወሳስቦታል፡፡ ብዙዎች በተለይም የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ አገልጋይ ካህናትና መነኩሳት ጭምር የእርኩሳን መናፍስት ጎታችና በሰዎችም ላይ የተለያየ ችግር እንዲፈጥሩ እንደሚልኳቸው በሰፊው ሲነገር እሰማ ነበር፡፡ ግን እንዲህ ያለውን ወሬ እንዴት ሊቀበሉት ይችላሉ? የእግዚአብሔር አገልጋይ የተባሉ በምን ሕሊና ነው የክፉ የሰይጣን ሚስጢራዊ አገልጋይ የሚሆነው! ግን ይህ የማይካድ እውነት ነው! እኛ አባቶች እያልን ጸልዩልን እንላለን እነሱ ግን መቃብራችንን ያዘጋጁልናል! አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! ያሳዝናል! ይህች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን የአምልኮት ሥርዐቷ ቀጥተኛ ሐዋሪያዊ እንደሆነ ቢታመንም ብዙዎች "አገልጋዮቿ" ግን ከሰይጣን ጋር ወዳጅነት የመሠረቱ እንደሆኑ አሁን እንረዳለን፡፡ ቀሪዎቹም የእግዚአበሔርን ኃይል የረሱ ዝም ብለው የሚመላለሱ "አገልጋዮቿ" ሲሆኑ በጣም ጥቂት የተባሉት ብቻ ግን እውንም የልዑል አምላክ እግዚአብሔር አገልጋዮች እንደቀሩ አሁን ለማሰብ ተገደናል፡፡ እንግዲህ እንዲህ ጥቂት አገልጋዮች በቀሩበት ብዙዎቹ የክፉ መንፍስ አገልጋይ ሌሎቹም የልምድ ተጓዥ በሆኑበት ሁኔታ እግዚአብሔር እንዴት በረከቱን ይስጥ? ሌሊቱን በማሕሌት የመላዕክት በሚመስል ሥርዓት ስንዘምር ማደራችን ዋጋው የቱ ጋር ታየ? እግዚኦታችንና ጸሎታችንስ በረከቱ የት አረፈ? እንደነዚህ ዝማሬዎቻችንና ምስጋናችን ሰማይ ተከፍቶ ማየት በቻልን!!  የቀድሞው የግብፅ ኦሮቶዶክስ ፓትሪአርክ የነበሩት አቡነ ሺኖዳ በአንድ ወቅት በአንድ ክብረ በዓል ላይ የሌሊቱን ማሕሌት ሥርዓት አይተው እጂግ በመደመም መዘምራኑን "ለመሆኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስንት ጊዜ ተገለጠችላችሁ" ብለው ሲጠይቁ የዘማሪያኑ መልስ ግን "እመቤታችን ለሰዎች ትገለጣለች እንዴ?" አይነት "አንዴም እንዳላዩዋት ነበር! እሳቸውም በትዝብት እንደው ዝም ብሎ ጩኸት ነበራ በለው አዝነዋል ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ በእርግጥም በግብጻውያን አባቶች የእመቤታችንም ይሁን የሌሎች ቅዱሳን መገለጥ በስፋት ይነገራል፡፡ እሳቸውም ያንን ጠብቀው ይመስላል ጥያቄያቸው፡፡ አሳቸው እዛ አመስጋኝ መስሎ የተሰለፈው ውስጥ ይበልጠው እንክርዳድ (የክፉ አገልጋይ) ወይም ገለባ (የልምድ ብቻ) እንደሆነ መቼ አወቁ! አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል!
ሌላው በሌሎች አገር የእምነቱ ተከታዮች ይኑር አይኑር በአላውቅም በኢትዮጵያውያን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ግን በስፋት የሚስተዋል የመንፈስ-ቅዱስ ስጦታ እየተደረገ የሚታሰብ የልሳን ተናጋሪነትና የመውደቅና የመንፈራገጥ ትዕይንት የተደበቁ የክፉ መናፍስት አሰራር እንደሆነም የታዘብንው አሁን ነው፡፡   ትዕይንቱ ልክ ከሚታወቀው የዛር መንፈስ አሰራር የተለየ አይደለም፡፡ አዳሜ መንፈስቅዱስ ወረደልኝ እልን እንፈራገጣለን ከዘር የወረስንው ዛርና ከባሕር የወጣው ጋኔን በኢየሱስ ሥም እያለ ይጫወትብናል! አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! ሰዎችን ሊየስቆጣ ይችላል ከሚል በየሀይማኖቶቹ የላውን ሌላ ጉድ መጠቆም አልፈቀድኩም፡፡
በግልጽ የእርኩስ መናፍስት አገልጋይ እንደሆኑ በሚታወቁት የጠንቋይና ቃልቻዎች ሳይቀር አሰራራቸው ከእግዚአብሔር እንደሆነ ማስመሰያዎችን ሲጠቀሙ አናያለን፡፡ "የቅዱሳን ሥዕላትን" (ያልተባረከ ስዕል ከስዕልነት ያለፈ ትርጉም የለውም) በቤተአምልኮታቸው መስቀል፡፡ በትላልቅ መንፈሳዊ ክብረ በዓሎች ላይ መታየት፣ ለቅድስና በተባሉ የበረከት ሥራዎች መሳተፍ (ቤተክርስቲያን እስከማሰራት ድረስ) ሌሎችንም ማሰመሰያዎች ይጠቀማሉ! ሕዝብም እንዲህ ያለ አሰራራቸው አጋዥ እየሆነው ቀድሞንም ባለው እነሱን የመከተል ምኞት ይበልጥ እያከበራቸው እየተከተላቸው ይሄዳል፡፡ ብዙዎች ከራሳችንም የባሕሪ ክፋት በትክክልም አውቀን የምንከተላቸው ቢሆንም ጥቂት የማንባል ከእነሱ የሚገኘው ሁሉ ሞት፣ መከራ እንደሆን ሳንረዳ ተከትለናቸዋል! አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል!
ወደሰለጠኑት ዓለማት ስንመጣ የእርኩሳን መናፍስት አሰራር ከእኛው ግደለው፣አፍዘው፣ አውድመው ተቃራኒ ገጽታ ያለው ይመስላል፡፡ እርኩሳን መናፍስትን እንደ ኃይል የሚጠቀሙትም እንደኛዎቹ መሀይም ደብተራዎች (ብዙዎች ሊቅ እንደሆኑ ቢያስቡም እነዚህ ሰዎች ምንም ጥበብ የሌላቸው ማሀይሞች ክፋታቸው ጥበብ የሆነላቸው ናቸው)ና ጠንቋዮች ሳይሆኑ በሕብረተሰቡ ከፍተኛ ቦታ የተሰጣቸው መሪዎች፣ ምሁራኖች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ካለቸውም የዕውቀት የበላይነትና፣ አለም ዓቀፍ እንቅስቃሴዎች አንጻር የእርኩሳን መናፍስትን የሚጠቀሙባቸውም ለረቀቀ ከፍተኛ ጉዳይ እንጂ ተራ ግለሰቦችን ማጥፋት አይደለም፡፡ እነዚህ ሰዎች አለም ዓቀፍ መረብ ያለው አባላት እንዳሏቸውም ይነገራል፡፡ በአላደጉት አገራት (በእኛም አገር) ሳይቀር እነሱ ይመጥናል (ብዙውን ጊዜ ታዋዊና ፈጣን አእምሮ ያለውን) አባለቶቻቸው በሚስጢር አሉ፡፡ በአጠቃላይ ሥያሜያቸው ሚስጢራዊ ማህበረሰብ (Secrete Society) በመባል ይታወቃሉ፡፡ ዓለም አቀፋዊ ዝናን ያተረፉ ትላልቅ የትምህርት ተቋማትም የአባላቶቻቸው ዋነኛ ምንጮች እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ ታዋቂዎቹ የሃርቫርድ፣የካሊፎርኒያ፣ የያለ ዩኒቨረሲቲዎች የመሳሰሉት የሚስጢራዊ ማህበረሰብ መፍለቂያዎች እነደሆኑ ይገመታል፡፡ በአሜሪካ መሪዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የዚህ ማህበረሰብ ተሳታፊ እንደሆኑ ይታማል፡፡ አንደውም የቀድሞው የአሜሪካው መሪ ጆርጅ ቡሽ የዚህ ማህበረሰብ አባል እንደሆኑ በግለታሪካቸው አሰነብበዋል፡፡   አባታቸው ትልቁ ቡሽም አባል እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በእንግሊዝ ቶኒ ብሌየር በስፋት የዚህ ማህበረሰብ አባል እንደሆኑ ከሚነገርላቸው ናቸው፡፡  እነዚህ አንግዲህ በይፋ ከሚነገርላቸው እንጂ ሚስጢራዊም ከመሆኑ አንጻር በብዛት የምዕራባዊው አለም መሬዎችና ትላልቅ ተቋም ባለሙያዎች አባል ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡ በሩቅ ምስራቅ ኤዥያ አገራትም ቢሆን ከጥንትም ጀምሮ መናፍስትን እንደ ኃይል የመጠቀም ልምድ ሰፊ ሥፍራ አለው፡፡ የምዕራባውያኑ ሚስጢራዊ ማህበረሰብና ጥንታውያኑ የምስራቅ ኤዥያ (ሕንድን ጨምሮ) አንድ ሚስጢራዊ ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል መገመት የአገራቱን የሥልጣኔ አካሄድ ለማስተዋል ይረዳል፡፡ ሥልጣኔ የሚመጣበት ከሆነ የሚስጢራዊ ማህበረሰብ ወይም ሌላ የእርኩስ መንፈስ እገዛ ያስፈልገናል እያልኩ አይደለም፡፡ ሁኔታዎችን አስተውለን አኛስ ሁሉንም  ኃይል በሚያሸንፋው በእግዚአበሔር መበልጸግ አንችልም ወይ ከሚል እንጂ? እኛም አገር ቢሆን አኮ አንዳንድ ሙከራዎች በአንዳንደ መሪዎች እንደተደረጉ ይነገራል (ሥም መጥቀስ አልፈለኩም)፡፡ በግልም ደረጃ የሚስጢራዊ ማህበረሰብ አባላት እንዳሉ ይታማል፡፡  
በጥቅሉ ግን አለምን አኛ ጅሎቹ እንደሚመስለን ምክነያታዊው ሳይንስ ብቻ ሳይሆን እያሰለጠናት ያለው ይበልጥ ምተሀታዊ አሰራሮች እንደሆኑ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ ብዙዎች የእኛዎቹ ሳይንቲስቶች ሌሎችን ሲቀላቀሉ ከምዕራባውያኑ ያነሰ ችሎታ አይደለም ያላቸው ይልቁንም በሚያስገርም ሁኔታ የሚበልጥ አእምሮ እንዳላቸው ምዕራባውያኑ ሳይቀሩ ያውቁታል፡፡ ግን ስኬቱ ላይ እኛ የለንበትም፡፡ አንድ የተደበቀ ሚስጢር እንዳለ አልተረዳንም!  የሰለጠኑት አገራት መሪዎችና ጠበብቶች ርኩሳን መናፍስትን ሌሎች አገራትንም ለማጥቃት፣ ዜጎችንም ለማፍዘዝ እንደሚጠቀሙባቸውም ይነገራል፡፡
 አንድ በግሌ የገጠመኝን ነገር ልናገርና ላብቃ፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት አንድ ጓደኛዬ አንድ ትልቅ ሰው መኖሪያ ቤት ይወስደኛል፡፡  የጓደኛዬ ግብዣ ግን ሰውዬውን ቀድሞ በአካል ስለሚያውቃቸውን ፍልስፍናቸውም እጅግ ስላስገረመው ከአንተ ጋር ልትናበቡ ትችላላችሁ የሚያመሳስላችሁ ነገር አለና ከሚል ነው፡፡ ሰውዬውን በዝና ሰምቼ (ብዙዎ ልታውቋቸው የሚችሉ ሰው ናቸው) ስለነበር እኔም ጓደኛዬ እንሂድ ሲለኝ አላመነታሁም፡፡ እውነትም እኔም በዝና እንደሰማሁት ጓደኛዬም እንደነገረኝ ሰውዬው ለየት ያለ ፍልስፍና ነው ያላቸው፡፡ በዚህ ላይ የሌላቸው የመጽሐፍ አይነት የለም! ሚስጢራዊ የተባሉትን ሳይቀር! ጓደኛዬ ታዛቢ ሆኖ እኔና እሳቸው ስንነጋገር (በጣም ከባድ ነበር አንዳንዱን ለመረዳትም) በመሀከል ከተደረደሩት መጽሐፎቻቸው እንዱን ከመደርደሪያው እንዳወርድ አዘዙኝ፡፡ አኔም የጠቆሙኝን መጽሐፍ ሰጠኋቸው፡፡ የመጽሐፉ የሆነ ገጽ ላይ ያለ አንቀጽ እንዳነብ መልሰው ገጹን ከፍተው ሰጡኝ፡፡ አነበብኩት፡፡ በወቅቱ ባነበብኩት ነገር ብገረምም እንደአሁኑ አልገባኝም፡፡  ቃል በቃል ለማስታወስ አልችልም፡፡ ያነበብኩት ግን ሀሳብ "የኢትዮጵያውያንን አእምሮ ማይክሮ ቺፕስ በመጠቀም እናፈዘዋለን ከዚያ አገሪቱንና ሀብቷን መጠቀም እንችላለን" ነው፡፡ መጻሕፉ የተጻፈው በእንግሊዘኛ ነው፡፡ ጸሀፊውም ሚስጢራዊ ከሚባሉት አንዱ ድርጅት ነው፡፡ መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ የተጻፈው ስለ ኢትዮጵያ ይመስላል፡፡ የተሰጠኝን አንቀጽ አንብቤ ስጨርስ ቀና ብዬ "ምን ማለት ነው? " ብዬ ሰውዬውን ስጠይቃቸው "የታቀደልህ ይሄ ነው" አሉኝ፡፡ በዚያን ወቅት ግን ነገሩን የማይሆን እንደሆነ አስቤ ሌላ ጥያቄ አቀረብኩላቸው ይሔንን አይነት ሚስጢራዊ ነገር የያዘ መጽሐፍ ከየት እንዳገኙት እሳቸውም "አንድ ወዳጄ ሰጠኝ"አሉኝ፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስብ ግን ጉዳዩ በትክክልም ሊሆን የሚችል ዕቅድ እንደሆነ አሰብኩ፡፡እኛ እናድጋለን ብለን መከራ እናያለን ግን አእመሮአችን እንደሚሰለብ ታቅዶልናል! አንቺ ታቦኪያለሽ ውሻ ይደፋብሻል! የሰውዬውንም ነገር ሳስብ ከሆነ የሚስጢራዊ አካል ጋር ግንኙነት እንደሚኖራቸው ገመትኩ፡፡ በጣም ሚስጢር የሆኑ ነገሮችን ሳይቀር ያቃሉ፡፡ ስለሚስጢራዊ ማህበረሰብና ቁልፍ አባላቶቻቸውም አሳምረው ያውቃሉ፡፡ የደረደሯቸው መጻሕፍቶች በአብዛኛው ሌላ ቦታ ለመገኘታቸው እጠራጠራለሁ፡፡ ሰውዬው ራሳቸው አባል ይሁኑ ወይም ልዩ ሌላ ኃይል ያላቸው (ተራ የሥጋ ኃይል/ጥበብ ግን ሊሆን አይችልም) ሚስጢራትን የሚያዩ ድምዳሜ ልሰጥ አልፈልግም፡፡ ሌላ ጊዜ ተመልሼ እንዳናግራቸው ጋብዘውኝ ብንለያይም እኔ ተመልሼ አልሄድኩም፡፡ ብዙ ጊዜ አስቤ ነበር አሁንም አንድ ቀን ብሄድና አሁን ባለኝ ግንዛቤዬ ባናግራቸው ደስ ይለኛል፡፡ በአጠቃላይ ዘመናችን በረቀቁ የእርኩሳን መናፍስትና ሥጋ ለባሽ በሆኑ የመናፍስቱ አገልጋዮች እየተመራች እንደሆነ እናስተውል!  
አቤቱ አምላክ ሆይ የአለምን ሁሉ ጥበብ በሚያመክነው ጥበብህ ታንጸን የምንበለጽግበትን አእምሮ ስጠን! ለጠላቶቻችን አሳልፈህ አትስጠን!
አሜን!
የታላቋ ቀን ልጅ (Son of the great day) መስከረም 2006 (September 2013)
ይህ  ጽሑፍ ቀጣይ ይኖረዋል፡፡
  

No comments:

Post a Comment