Friday, October 4, 2013

ክብርሽን አክብሪው!



ክብርሽን አክብሪው!

ትሰሚኝ እንደሆን ልምከርሽ እህቴ፣
ስተሻል መንገዱን የለሽም ከፊቴ፡፡
ከላይ ከተራራው ከፍ ካለው ምድር፣
ክብርሽን አጉልቶ ከሚያሳየው መንደር/ሠፈር፣
ዓዶሎም ተሰደሻል/ሄደሻል ከቁልቁሊቱ አገር፡፡
የክብር ማማዋን ተምናን ረስተሻል፤
ሸለቋማው አገር ቴምናታ ወርደሻል፡፡
ዝቅታውን ናፍቀሽ አዘቅት ለመውረድ፣
ነውርሽን ገልጠሽ ሶምሶንን ለማጥመድ፣
ስትወጠኝ አየሁሽ የደሊናን ዕቅድ፡፡
አሁንም ልምከርሽ እህቴ አሰተውይ፣
ያችን ጥበበኛ ትዕማርን እይ፡፡
ሁሉም በአይኑ ዘግኖሽ የሚያልፍሽ አትሁኝ፣
ገላሽን አታርክሽ አካልሽን ሸፍኝ፡፡
መጎናፀፊያሽን ልበሽና ውጪ፣
በኤናይም ደጃፍ በክበር ተቀመጪ፡፡
እጅሽ መጅ አይንካ ባርነት አትናፍቂ፣
ከነገስታት ነገድ ዘርሽን ደባልቂ፣
ክብርሽን አክብሪው ለራስሽ ዕወቂ፡፡
መንታዎች ፀንሽ ፋሬስን ውለጂ፣
ከዘላለም ንጉስ ከአምላክ ተዛመጂ፡፡
የክብር ዙፋን ነው ያንቺ ልዩ ቦታ፣
ከቶ አመጥንሽም ጋዛና ቴምናታ፡፡
ከንጉሥ ተዋለጅ ዘርሽን ቀድሽው፣
አንች ታላቅ ሴት ነሽ ክብርሽን አክብሪው!!!
የታላቋ ቀን ልጅ 2004 ዓ. ም (Son of the great day 2011)
መነሻ ሐሳብ፡ የአንድ የማውቃት/የማከብራትም ሴት ፎቶ፣በክርስቶስ የዘር ግንድ የገባችው ትዕማር (ዘፍ 38) ደሊላና ሶመሶን፡፡

No comments:

Post a Comment