ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
የአፍሪካ “የዘር አደን”፤ የዘር ካርድ፤ እና የአፍሪካን እጀ ሰቦች/አመጸኞች ማደን?
ሃይለማርያም ደሰለኝ፤ የኢትዮጵያ የስም ብቻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ
የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይ ሲ ሲ) በአፍሪካ አደን ላይ ነው ይላል፡፡ እንደ ቢቢሲ ራድዮ አባባል
ራድዮ በግንቦት (ሜይ) 2013 ሃይለማርያም ሲናገር ‹‹በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከተወነጀሉት መሃል
99% የአፍሪካ መሪዎች ናቸው፡፡ ይህም በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አሰራር ላይ ጉድለት እንዳለ የሚጠቁም በመሀሆኑ
ይህንን እንቃወማለን፡፡ ሂደቱ የዘር አደን ጥቁር አፍሪካኖችን ላይ ሰላቶኮረ ብሉሽነት ይታይበታል::›› ባለፈው
ሳምንት በኢትዮጵያ የገዢው ፓርቲ አፈ(ረ) ቀላ(ው)ጤ: ሲዘላብድ አንዲህ አለ: ‹‹የዓለም አቀፉን የወንጀለኞች
ፍርድ ቤት አሰራር በተለይም አፍሪካያን ገዢዎችንና አመራራቸውን በተመለከተ በሚወስደው እርምጃ ላይ በማንቋሸሽ እና
በማንኳሰስ ላይ በመሆኑ መቼም አድንቀነው አናውቀውም፡፡››
በዚህ ወር መጀመርያ ግድም ሃይለማርያም ደሳለኝ በኬንያው
ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የመሰረተውን ክስ
በስርአት እንዲያነሳ ለአይ ሲ ሲ ሲጽፍ በግልባጩም የተባበሩት መንግሥታት እንዲያውቀው አድረጓል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች
ከሮም አለም አቀፍ ዉል (ዘር ማጥፋትን፤ሰብአዊ መብት ገፈፋን፤የጦር ወንጀልንና ወረራን የሚቀጣ ድንጋጌ )
የመሰረተውን ለቀን እንወጣለን በማለት የማስፈራራት እብደት ተጠናውቷቸዋል፡፡ በዚሁ የወፈፍታ ልክፍት ላይ ለመነጋገር
አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ለማካሄድ በአዲስ አበባው የመሪዎች መሰብሰቢያ ‹‹አማኑኤል›› ለመገናኘት ለአክቶበር 13
2013 ቀጠሮ አድርገዋል፡፡
የዓለም አቀፉ ችሎት አቃቤ ሕግ ጋምቢያዊዋ ዓለም አቀፍ ጠበቃ ፋቱ
ቤንሱዳ፤ በተደጋጋሚ አብዛኛዎቹ በአፍሪካ ላይ የተመሰረቱት ክሶች ከአፍሪካ ሃገራት ጋር በተደረሰ ስምምነት ነው
በማለት አሳስበዋል፡፡ አይ ሲ ሲ አፍሪካውያንን በተለይ በመምረጥ ክስ ሰርቷል የሚለውን የቅዠት አስተሳሰብ ዉድቅ
አርገዉታል፡፡ የአፈሪካውያን ከአይ ሲ ሲ የመውጣት ዋነኛ መንስኤያቸው፤ ‹‹የዘር አደን›› ነው በማለት ነው፡፡ ስለ
ዘር መሳቢያ/ ማታለያ፤ ስለዘርልዩነት፤ስለ ዘር ምልክት፤ ሰምቻለሁ፡፡ ስለ‹‹ዘር ማደን›› ግን ጨርሶ
አልሰማሁም፡፡
ሃይለማርያም በዚህ የትንኮሳ ቴአትራዊ ጥቅሱ አይ ሲ ሲ በአፍሪካ
የአደን ዘመቻ በማድረግ ሰላማዊ አፍሪካውያንን እየወነጀለ ነው ማለቱ ነው? አይ ሲ ሲ ‹‹ተበላሽቶ›› የነጮች
ዘረኝነት ሕገወጥ ግድያን ቡድን ውስጥ በመግባት ሕጋዊውን ኢንስቲቲዩሽን በመጠቀም ለማሳደድ፤ለማሰር፤ከወንጀልና
ከጥፋት ነጻ የሆኑትን የአፍሪካ መሪዎችን ይከሳል ለማለት ነው? ከተወነጀሉት ማሀል 99% የሚሆኑት አፍሪካውያን
በመሆናቸው አይ ሲ ሲ የተቋቋመው አፍሪካውያንን ለመወንጀል ነው ሊለን ነው? የምእራብ ሃገራት አይ ሲ ሲን በመጠቀም
ከምእራቡ ጋር ለመፋለም መጥረቢያ ያነሱትን የአፍሪካን መሪዎች በመነጠል ለመቅጣት አልመዋል ነው የሚለን? ለመሆኑ
እነዚህ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው 99% የዘር አደን የሚካሄድባቸውና ክስ
የተመሰረተባቸው እነማን ናቸው?
ባለፈው ሳምንት ላይ በተንኮል የተሞላው አረመኔ የጦር አበጋዝ
ቻርልስ ቴይለር በተከሰሰበትና በተሰጠው ፍርድ ላይ ያቀረበው የይግባኝ ጥየቄ ከሽፎበታል፡፡ ቴይለር በተከሰሰባቸው
ወንጀሎች፤ (አስገድዶመድፈር፤ ግድያ፤ በሲቪሎች ላይ አካላዊ ጉዳት በማድረስ፤የህጸናት ወታደሮችን በማሰባሰብና
በማሰማራት፤በግብረ ስጋባርነት፤) ከ1995 አጋማሽ ጀምሮ ለ11 ዓመታት በሴራሊዮን ባካሄደው የሽብር ዘመናት ክስ
ተፈርዶበታል፡፡ በተቀሰቀሰው ግጭት 50,000 ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ የቴይለር ችሎት 4 ዓመታት ሲፈጅ ቴይለር
በራሱም ላይ ምስክርነት ስጥቷል፡፡ የቴይለር ችሎት ሂደት 250 ሚሊዮን ዶላር ፈጅቷል፡፡ በተመሳሳይ ወንጀል
በተደራቢ 22 ሰዎችተ ከሰዋል፡፡ 14ቱ ተፈርዶባቸዋል፤ ከነዚህም ዘጠኙ ረጂም የአስር ዘመን እየገፉ ነው፡፡
ተራፊዎቹ ሲሞቱ እንዲሁም መለስተኛ የእስራት ዘመን ጨርሰውም የተለቀቁ አሉ፡፡
በሜይ 2012፡ ቴይለር ላይ ፍርድ በተላለፈበት ወቅት ‹‹ፍትሕ
ለሴራሊዮን፤ ፍትሕ አልባነት ለኢትዮጵያ›› የሚል መጣጥፍ አስነብቤ ነበር:: በጽሁፌም ላይ ያነሳሁት ክርክር፤
በቴይለር ላይ የተላለፈው የፍርድ ውሳኔ በአፍሪካ ውስጥ ያለውን ሳይቀጡ ማለፍና የወንጀል ድርጊት ማብቂያ ከፍተኛ
እመርታ እንደሆነ ነበር ያነሳሁት ፡፡ የአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ መሪዎችና አምባ ገነኖች ምናልባትም ከእንግዲህ አጥፍቶ
ነጻ መስሎ መኮፈስን፤ በማን አለብኝነት ሰላማዊ ሰዎችን ገድሎ እንደልብ መንፈላሰስ መቅረቱን ያስቀር ይሆናል፡፡
የአይ ሲ ሲ ሰራሊኦን ዋናው አቃቤ ሕግ ዴቪድ ክሬን በትክክል እንዳስቀመጠው፤‹‹ይህ በዓለም ላይ የተደወለና
በመደወልም ላይ ያለ ደወል ነው:: የአንድ ሀገረ መሪ ሆነህ የራስህን ሕዝቦች የምትገድል ከሆነ፤ ተከታዩ ለፍርድ
ቀራቢ አንተ ትሆናለህ፡›› የተባበሩት ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን የታይለርን የፍርድ ውሳኔ ‹‹የዓለም የወንጀል ፍርድ
ቤት፤የታላቅ ና ታሪካዊ ወሳኝ ድርጊት ጊዜ ነው›› ብለውታል፡፡
በአይ ሲ ሲ የአደን ሂደት ‹‹አውሬው›› ማን ነው?
በአይ ሲ ሲ እና በተባበሩት መንግሥታት ልዩ ፍርድ ቤት የተዋቀረው
የተጠያቂነት ስርአት አሁን በአፍሪካውያን ፈላጭ ቆራጭ ‹‹ገዢዎች›› አሮጌውን የዘር ካርድ (የቅኝ ገዢዎችና
የኢምፔሪያሊስቶች የነበረውን ካርድ) እየጎተቱ፤ሃላፊነታቸውን ላለመወጣትና ከተጠያቂነታ ለማምለጥ፤ ወንጀል ሰርተው
ጨዋ መስለው መቀመጥን ላለማጣት ሕገ ወጥነትነት እየተገበሩ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ለመቻል እንዲመቻቸው አይ ሲ ሲን
የጥቃት ኢላማቸው እያደረጉት ነው፡፡ ጥያቄው ሃይለማርያም ደሳለኝ በአይ ሲ ሲ ላይ ላነሳው ክስና ወቀሳ፤
የሚያስቆጣና የሚያስደነፋ አባባል መሰረቱ ምን ሆኖ ነው? አይ ሲ ሲ ተበላሽቶ የምእራባዊያን ዘረኛ ዓለም አቀፍ
ድርጅት ነው ለማለት ያበቃው? ወይስ የሃይለማርያም ያዙኝ ልቀቁኝ ድንፋታ በዴቪድ ክሬን የተሰነዘረው ማስጠንቀቂያ
ከንክኖትና አስደንብሮት አለያም መጪውን አመላክቶት ተደነባብሮ ነው? ‹‹የሃገር መሪ ከሆንክና የራስህን ዜጎች
ያለፍርድ የምትገድል ከሆነ ቀጣዩ አንተ ነህ::››
በ2002 ጀምሮ “የሮም ድንጋጌ” በስራ ላይ ከዋለ አንስቶ አይ ሲ
ሲ በሁለት በስልጣን ላይ ባሉ መሪዎች ላይ (የሱዳኑ ፕሬዜዳንት ኦማር አል በሺርና ሟቹ የሊቢያው መሪ ሞአመር
ጋዳፊ) የክስ ማስረጃ አውጥቷል፡፡ ማስረጃው ከቀረበባቸውና ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ ወደ ሥልጣን የወጡት ደግሞ
(የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊየያም ሩቶ)፤ አንድ የቀድሞ ፕሬዜዳንት (የላቤርያው ቻርልስ
ቴይለር) ሌላው ደግሞ በምርጫ ከተሸነፈ በኋላ ስልጣኔን አልለቅም ብሎ ያስቸገረው (የኮት ዲቩዋሩ ላውሬንት
ጋብጎ)፡፡ አይ ሲ ሲ ደርዘኖች በሚሞሉ የአፍሪካ መሪዎችና ተቃዋሚዎች ላይ የክስ ማስረጃ አሰባስቦ ጨርሷል፡፡ አይ ሲ
ሲ ኬንያታን ለፍርድ እንዲቀርብ ማዘዣ ያወጣበት ከ 2008 ምርጫ ጋር በተገናኘ በተፈጠረው ብጥብጥ የተመራጮቹ
የራይላ ኦዲንጋ እና ሙዋይ ኪባኪ ደጋፊዎች ላይ ባስፈጸሙት የሰብአዊ መበት ገፈፋና ግድያ ነው፡፡ እንደተባበሩት
መንግስታት ዘገባ ከ2007 ዲሴምበር እስከ ፌብሪዋሪ 2008 ድረስ በኬንያ 1600 ሰዎች ሲገደሉ፤ ከ600,000
ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው በመገደድ ተፈናቅለዋል፡፡
የሱዳኑ ባሺር በ2003 በዳርፉር ላይ የዘር ማጥፋት ፖሊሲ ዘርግቶ
በተባበሩት ምንግስታት ዘገባ መሰረት 2.5 ሚሊዮን ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል:: በ2009 ባሺር በአይ ሲ ሲ ክስ
ሲመሰረትበት ‹‹ለሁሉም ንገሯቸው፤ ለአይ ሲ ሲ አቃቤ ሕግ፤ ለችሎቱ አባላትና ይሀንን ፍርድ ቤት የሚደገፉ ሁሉ
በእግሬ ጫማ ስር መሆናቸውን አሳውቋቸው›› በማለት አይ ሲ ሲን በማንኳሰስ ተሳለቀ አፌዘ፡፡
የኮት ዲቩዋሩ ጋብጎ በ2010 በተካሄደው ምርጫ በተቀናቃኙ ሲሸነፍ
ቢሮውን አልለቅም ብሎ አሻፈረኝ አለ፡፡ በዚህም ጦስ የተባበሩትመንግስታት በዘገበው መሰረት በቅድመ ምርጫው ወቅት
3000 ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በ2011 በሊቢያ መነሳሳት መጀመርያ ላይ ጋዳፊ አገዛዙን ስርአት የተቃወሙትን
እንዲያዙ፤ እንዲታሰሩና እንደገደሉ አዘዘ፡፡ በአንድ ወቅት ላይ ሕዝቡን ‹‹ትንኮሳ እፈልጋለሁ፡፡ ሕዝቡ ወደ ጎዳና
መውጣት አለበት፡፡ እነዚያን ውሾች ፍጇቸው፤ እናም ‹እናንት ከሃዲዎች እንግሊዞችን ታመጡብናላችሁ በሏቸው› ብሎ
ነበር፡፡
በአይ ሲ ሲ ተጠርጥረው ለፍርድ የቀረቡት ዝርዝር በጣሙን ሰፊ
ነው፡፡ ዝርዝራቸውም የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የተረገሙ እርባና የለሽ ነፍሰ ገዳዮችን ስም ያካትታል፡፡ ዩጋንዳ ውስጥ
‹‹ዘ ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ›› የተባለው የነፍሰ ገዳይ ቡድን ቁንጮ አመራሮችን፤ ለመጥፎነቱ አቻ የማይገኝለትን
ሕጻናትን አስገድዶ እየደፈረ ኋላም አስገድዶ ለጦር የማገዳቸውን ጆሴፍ ኮኒን ጭምር አይ ሲ ሲ ለፍርድ አቅርቧል፡፡
በዴሞክራቲክ ኮንጎም፤ አይ ሲ ሲ የተለያዩ የሚሊሺያ መሪዎችንና አመጸኞችን፤ ጦር የቀሰቀሱትንና በሰው ልጆች ላይ
መብታቸውን በመግፈፍ ወንጀል የፈጸሙባቸውን ቶማስ ሉባንጎን ዲሎን (አይ ሲ ሲ ለፍርድ ያቀረበው የመጀመርያው
ተከሳሽ) ጨምሮ፤ ኮንጓዊያን የጦር አለቆችን፤ ጄርሜን ካታንጋ፤ዣን ፒየር ቤምባ ጎምቦ፤ቦስኮ ናታጋንዳ፤ማቲው
እንጉጆሎ ቺዊ፤ ካሊክቴ አምባራሺማና፤ እና ሲልቨስተር ሙዳኩሙራ በአይ ሲ ሲ ለፍርድ ቀርበዋል፡፡ በሱዳን አህመድ
ሃሩን የሱዳንን ወታደሮችና የጃንጃዊድ ሃይሎችን ከሱዳን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር አብደል ራሂም ሞሃመድ ሁሴን ጋር
በመተባበር በዳርፉር ግጭት በአይ ሲ ሲ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማዘዣ ወጥቶባቸዋል፡፡ ሳለህ ጀርቦ እና አሊ ኩሽያብ
የአፍሪካ ህብረትን የሰላም አስከባሪዎችን በመግደል ክስ ለፍርድ እንዲቀርቡ አድረጓል፡፡
አይ ሲ ሲ የሞአመር ጋዳፊን ልጅ ሰይፍ አል ኢስላምንና የሊቢያን
የመረጃ ሹም አብዱላህ አል ሳኑሲን በሊቢያው የሲቪል ጦርነት ሕዝባዊው ንቅናቄ ወቅት በሕዝብ ላይ ስለተወሰደው
የኃይል እርምጃ ተጠያቂ አድርጎ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡ ሞሃመድ ሁሴን አሊ የኬንያ ፖሊስ ኮሚሽነር፤በአይ ሲ ሲ ክስ
የተመሰረተበት ከካቢኔው ጸሃፊ ከፍራንሲስ ሙታሁራ ጋር፤ ከሬዲዮ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ ጆሽዋ ሳንግ፤ የመንግሥት
ሚኒስትሩ ሄንሪ ኮሲጊ በመሆን በ2007 ምርጫ ወቅት ባደረሱት ሕዝባዊ ግፍና በደል ተከሰዋል፡፡ ሰሎውሬንት ጋብጎ
ባለቤት ሲሞኔ ጋብጎ በሲቪሉ ማሕበረሰብ ላይ ባለቤቷ ስልጣን አልለቅም ባለበት ጊዜ በዘዴ ስለተፈጸመው ጥቃት
በነበራት እኩይ ክስ ተመስርቶባታል፡፡
የአይ ሲ ሲ ክስ ምስረታ ሙሉ በሙሉ የታመነበት ነው ማለት
አይደለም፡፡ በተለያዩ ማስረጃዎች የተነሳ የአይ ሲ ሲ ክስ እንዲሰረዝ፤ ወይም ማረጋገጫ ስይገኝለት እንዲቀር
ሆኗል፡፡ አይ ሲ ሲ ‹‹ክሱ የተቋረጠ›› ያላቸው፤ፍራንሲስ ሙታሁራ፤ ሞሃመድ አሊ፤ ካሊክስቲ እምባሩሺማና እና ባህር
አቡ ጋርዳ ይገኙበታል:: የአይ ሲ ሲ ደወል በአፍሪካ እንዳይደወል ዴቪድ ክሬን ሲያስጠነቅቅ፤ ‹‹የሃገር መሪ
ሆነህ የራስህን ሕዝቦች በግፍ የምትገድል ከሆነ ቀጣዩ አንተ ልትሆን ትችላለህ››:: ይሄ ሁሉ የአፍሪካውያን
‹‹መሪዎች›› የዘር ማታለያ፤ የዘር ማሰርያ፤የሽንገላ ጩኸት፤ምክንያት አልባ ድንፋታ፤ ግትርነት የሚሰማው ያን
የአይ ሲ ሲን የፍትሕና የማስጠንቀቂያ ደወል ድምጽ ለማፈን ሲባል ነው፡፡ እነዚህ የአይ ሲ ሲን ተግባር
የሚያጣጥሉት፤ የሚያንቋሽሹት፤ የዘር ሰበብ የሚጭኑበት፤ የፍትሕ ነበልባል ሙቀቱ ደርሶባቸው የሚያስፈራራቸውና
የሚያስደነግጣቸው፤ ማነህ ባለሳምንት የሚባሉት የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› ናቸው፡፡ እነዚህ ‹‹መሪዎች›› እኮ በሕዝብ
መብት ላይ የቆሙት፤ የገደሉት፤ የመዘበሩት፤ የሰብአዊ መብት የረገጡትን ለፍርድ እንዲቀርቡና እንዲጠየቁ ጨርሶ
አይፈልጉም ምክንያቱም የሰብአዊ መብት ረጋጮቹና ቀደምት ተጠያቂዎቹ እነሱው በመሆናቸው፡፡
እውነቱን ለመናገር በአፍሪካ ያሉ ተጠርጣሪዎችና በመብት ረገጣ፤
ህዝብን በማዋረድ፤የሕዝብን መብት በመግፈፍና ለሕዝብ ጥያቄ መልስ ነው በማለት ሕዝቡን ለግድያ፤ ለአፈና፤ ለእስር፤
ለስደት፤ የዳረጉ የአፍሪካ መሪዎች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ‹‹አሰቃቂ የሆነ ወንጀል በመፈጸማቸው በታላቅ
ሃላፊነት ሊጠየቁ የሚገባቸው ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ይገባል›› በማለት ለአይ ሲ ሲ አቃቤ ሕግ
በ2011 ይፋ ደብዳቤ በመጻፍ የጠየቁት ብቸኛ አፍሪካዊ መሪ የኮት ዲ ቩዋሩ ፕሬዜዳንት አሊሳኒ ኡዋታራ ብቻ
ናቸው፡፡
የአፍሪካ ሕብረት(አሕ) ስለ አይ ሲ ሲ ያለው አመለካከት ግልጽ
ንቀት ነው፡፡ በ2010 የአፍሪካ ሕብረት ‹‹የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገራት በሮም የጸደቀውን የአይ ሲ ሲን ሕግ
አንቀጽ 98 አክብረው የሱዳኑን ፕሬዜዳንት ኦማር አል በሺርን ለፍርድ ለማቅረብ ፈጽሞ አይተባበሩም›› በማለት
ንቀታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት በይፋ የዳርፉሩ ጨፍጫፊና የሰው ልጅ ጸር ለሆነው
በሺር ከለላ ለመስጠት አቋም ያዙ፡፡ በኢትዮጵያስ የአይ ሲ ሲ የክስ ምስረታ የሌለው በምን ምክንያት ነው?
ሃይለማርያም ደሳለኝ እሱና ተባባሪዎቹ በአይ ሲ ሲ ፋይል ላይ ቀጣይ ተከሳሾቹ ስለሆኑ ይሆን ሃሳብ ያናወዘው?
በኢትዮጵያ የገዢው ፓርቲ አባላት አይ ሲ ሲ አንድ ቀን በራቸውን እንደሚያንኳኳና እያንዳንዳቸውን ለፍርድ
እንደሚያቀርብ የሚያረጋግጥ ምክንያት አላቸው ይሆን፡፡ …..ያለበት ዝላይ አይችልም ሆኖባቸው ይሆን? ይህን ማስረጃው
እራሱ ያረጋግጥ፡፡
በሞቱት ጠቅላይ ሚኒስትር መመርያና ትእዛዝ በ2206 ተቋቁሞ
የነበረው አጣሪ ኮሚቴ አጣርቶ ባቀረበው ሰነድ መሰረት፤ የ193 አንዳች መሳርያ ያለነበራቸውን ለሰላማዊ ሰልፍ
የወጡትን ሰላማዊ ንጹሃን ዜግች የግፍ ግድያና 763 ቁስለኞችን እንዲሁም በ2005 የኢትዮጵያ የምርጫ ወቅት ለእስር
መዳረጋቸውን ይፋ አድረጓል፡፡ (እኔም በኢትዮጵያና ብሎም በአፍሪካ ሰብአዊ መብት ጥበቃ ጉዳይ አካል ለመሆን
የበቃሁት በዚያ መነሾ ነው) በኢትዮጵያስ የአይ ሲ ሲ የክስ ምስረታ የሌለው በምን ምክንያት ነው?
መርማሪ ኮሚሽኑ በጁን 8 2005 በአዲስ አበባ ከኖቬምበር 1
እስከ 10 2005 እና ከኖቬምበር 14 እስከ 16 በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የተፈጸመውን ሁከት በተመለከተ ብቻ
እንዲያጣራ ነበር የተሰየመው፡፡ (መርማሪ ኮሚሽኑ በተጠቀሱትና ከዚያም ውጪ በነበሩት ቀናት ከመጠን በላይ በታጠቁ
የመንግስት የደህንነት አባላት የግፍ ግድያ መፈጸሙን በማስገንዘብ ሁሉም ቦታዎች የነበረው ሁኔታ ቢጣራ ግን የሟቾችና
የቁስለኞች ቁጥር ከእጥፍ በላይ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡) በአጣሪ ኮሚሽኑ የተጣሩት ግድያዎች ሁሉ የተፈጸሙት ሟቹ
የገዢው ፓርቲ መሪ በይፋና የሃገሪቱ የደህንነት፤ወታደራዊ፤ መዋቅር በራሱ ቁጥጥር መመርያና ትእዛዝ ስር መሆናቸውን
ከአዋጀ በኋላ ነበር፡፡
ኮሚሽኑ በቀጣይም በኖቬምበር 3 2005 በከንቱው የቃሊቲ ወህኒ
ቤት ተቀሰቀሰ በተባለው ብጥብጥ ወታደሮቹ በአስራ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ ከ1500 ጥይት በላይ በታሳሪዎች ላይ
በማርከፍከፍ 17 ገድለው 53 አቁስለዋል፡፡ይህንና ይህን የመሳሰሉት ዘግናኝ ዘገባዎች ከ16,990 ፋይሎችን
በማገላበጥ፤ 1300 ምስክሮችን በማነጋገር ወራቶች የፈጀ ምርመራ ማከናወኑን በኮሚሽኑ ዘገባ ውስጥ ተካቷል፡፡ በዚህ
የግድያና የተኩስ ተገባር ላይ የተሳተፉ የፖሊስና የደህንነት አባላት ማንነትን የሚገልጽ ማስረጃ የተገኘ ቢሆንና
በማጣሪያው ሰነድ ውስጥ ቢካተትም ስማቸው የተገለጹት በሙሉ ከስራ እንዲሰናበቱ ተደርጎ ከተጠያቂነት ላማዳን ሲበል
በገዢው ፓርቲ ሟች ቁንጮ መሪ ከለላ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በዲሴምበር 2003 በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክፍለሃገር በደህነነት
ታጣቂዎች ሕግ አልባ ግድያ ተካሂዶ 424 ንጹሃን ዜጎች ለሞት ተዳርገዋል፡፡ የሃርቫርዱ ዓለም አቀፋዊው የሰብአዊ
መብት ተሟጋች ክሊኒክ ፕሮግራም ይህን ሕገ ወጥ ግድያ አረጋግጧል፡፡
በ2008 በኢትዮጵያ ክፍለሃገር ኦጋዴን ውስጥ በተካሄደ ብቀላ ‹‹150 ንጹሃን ዜጎች ሲገደሉ ሌሎች 38 ደግሞ 37 ዜጎች በገዢው ታጣቂዎች እንደተገደሉ ሁማን ራያትስ ዎች አረጋግጧል፡፡
በግድያው የተሳተፉም ሆኑ ግድያውን የመሩ አለያም ትእዛዝ የሰጡት
የጦር አባላት ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል፡፡ ከፍተኛ የጦር አለቆችና ሲቪል ባለስልጣናትም ድርጊቱን ያወቁና አውቀውም
ዝም ማለትን የመረጡ የእዝ ሃላፊነት ስላለባቸው እንሱም ከተጠያቂነት አያመልጡም፡፡ ‹‹በሶማልያ መንደሮች ውስጥም
በስፋት የተካሄደው የአስገድዶ መድፈር፤ የግድያ፤ ማሰቃየት፤አስገድዶ ለስደት መዳረግ በኢትዮጵያ ወታደሮች በህዝቦች
ላይ የተፈጸመውን ግፍ ለማረጋገጥ በቂ ማስረጃ ነው፡፡››
በ2010 ሁማን ራይትስ ዎች ለተባበሩት መንግሥታት የጸረ ስቃይ
ኮሚቴ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው ኢሰብአዊ ድርጊት፤ጭካኔ፤ ማሰቃየት፤ አቤቱታውን አሰምቶ ነበር፡፡ ሁማን ራይትስ
ዎች በኢትዮጵያ ፖሊስ አባላትና በጦሩ አባላት በሕዝቡ ላይ ስለሚፈጸመው ግፍና ስቃይ፤ አፈናና ግድያ፤ በተመለከተ
በተቃዋሚ ፓርቲ ላይ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ፤የሌሎችም እንቅስቃሴዎች ሰላማዊ ደጋፊዎች ላይ እና በሽብርተኝነት
ተጠርጥረዋል በሚላቸው ተከሳሾች ላይ የሚደርሰውን ሕገወጥ ድርጊት አስመልክቶ በቂ ማስረጃና አቤቱታ አሰምቷል፡፡
ለሱዳን፤ኬንያ፤ኡጋንዳ፤ እና ለዴሞክራቲክ ኮንጎ ይበቃል ከተባለ
ለኢትዮጵያም ጥሩ ይሆናል፡፡ የተሰባሰበው የሰብአዊ መብት ረገጣና ግድያ ግፍ ማስረጃነቱ ብቃት ያለውና የተረጋገጠ
ነው፡፡ አይ ሲ ሲ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰብአዊ ፍጡራን ላይ ስለተካሄደው ስለተፈጸመውና በመፈጸም ላይ ስላለውም የጦር
ወንጀል ቢያንስ ጥናትና ምርምር የማካሄድ የህግ ሃላፊነትና የሞራል ግዴታ አለበት፡፡ (ወደዚህ ጉዳይ ሌላ ጊዜ
እመለስበታለሁ::)
አይ ሲ ሲ ዘር አደና
በኦክቶበር 13 2013 የአፍሪካ ሕብረት ሲከፈት ወቅቱ አይ ሲ ሲ
ን ለማደን ይሆናል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በዚያ ስብሰባቸው ላይ ቢላዎቻቸውን ስለው ቃላቶቻቸውን አቀናብረውና
አጥንተው፤የአደን ጠመንጃዎቻቸውን አቀባብለው፤በማነጣጠር አይ ሲ ሲን አላማቸው አድርገው ሊተኩሱ ነው፡፡ በተለመደው
አካሄዳቸው ተራ በተራ እየተነሱ ራሳቸውን እርስ በርስ ምስጋናና መካካብ በፈረቃ ሲያዥጎደጉዱት ይውላሉ፡፡ አንዱ
ስለአንዱ ሸብርተኛ መሪ ታላቅነት ይደሰኩራሉ፡፡ የተረሱትን የቅኝ ገዢዎች ተግባር እያነሱ በማውገዝ ይሞሸራሉ፤
የዚያን ቅኝ ገዢ ተግባር በእጅጉ የበለጠ ግፍ መስራታቸውን ለመሰረዝ አንዱ ሌላውን ያሞካሻል፡፡ ይልቁንስ በባሰ
መልኩ ሕዝቦችን ለግፍና ለመከራ በመዳረግ እንደሚገዙ ግን ልቦናቸው ቢያውቅም ከራሳቸውና ከቡችሎቻቸው ደስታ በቀር
ስለሌላው የማያስቡ የአዲሱን ዓለም አካሄድ ለመቀበል ፈቃድ ያጡ ናቸውና አፍሪካንና ሕዝቦቹን በምርኮ ይዘዋል፡፡
በኦክቶበር 13 2013 የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› በአፍሪካ ሕብረት
አዳራሽ ተሰብስበው በአንድነት ሊያናፉ፤ ሊያጉረመርሙና ጭዋታ ፈረሰ ሊሉ ነው፡፡ በዚህም የጨረባ ተዝካር ጩኸታቸው
ተራ በተራ በመፈራረቅ አይ ሲ ሲን ሊኮንኑ፤ ወንጀለኛ፤ ሊያስቀይሙ፤ሊወቅሱ፤አቃቂር ሊያወጡለት፤ ሊረግሙት፤ ዘረኛ
ሊሉት፤የፖለቲካ ክርስትና ስም ሊሰጡት፤ መጥፎ ስም ሊለጥፉበት፤አውሬ ሊያደርጉት፤ በተቻላቸው ሁሉ ሊያጥላሉትና
‹‹ይሉሽን ባላወቅሽ …..››ይሉት አይነት ለማድረግ ነው፡፡ ለዚህ አሉባልታቸው ደግሞ የቀጠሮ ቀናቸውን መጠበቅ
የለብንም ሰምተነዋልና!
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት፤ ባለፈው ወር ባደረገው
ንግግር ላይ ‹‹የምእራቡ ዓለም በአፍሪካ ላይ ያለው ንቀት ማብቃት አለበት›› ብሏል፡፡ ኢምቤኪ እኮ ከ1980 ዓም
ጀምሮ በስልጣን ላይ ያለውን የ89 ዓመቱን ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ የምእራቡ ዓለም ለአፍሪካ ያለውን ንቀት
አሳይቷል፡፡ ኢምቤኪ፤ ‹‹በጣም የሚያስገርመው ነገር በመላው የአፍሪካ አህጉር፤ታማኝና ሕጋዊ ኢንስቲቱሽን መኖሩ
ነው›› ይሄስ የዝምባዌ ሕዝብ ‹‹ስሜት ነው?›› እና አፍሪካውያን ችላ ተብለዋል፡፡ ‹‹በዋሽንግተን፤ ለንደንና
ብራስልስ ‹‹በጭራሽ እናንተ አፍሪካውያን ተሳስታችኋል›› የሚል አማራጭ ድምጽ አለ፡፡ እምቤኪ እኮ ባለፈው
በዚምባብዌ የተካሄደው ምርጫ ሚዛናዊና ነጻ ነው›› ተቀባይነት ያጣበት ሰበብ ግን፤ ‹‹ዋሽንግተን ለንደንና ብራስልስ
ምርጫዊ ሕጋዊ አልነበረም በማለታቸው ነው፡፡ ሕጋዊ ያልሆነበት ብቸኛ መንስኤ ሙጋቢ በምርጫ በማሸነፉ ነው፤ በቃ
ይሄው ነው›› ሲል ተናገረ:: ሙጋቤ ዋሽንግተን፤ ለንደን እና ብራስልስ የሚወዱት፤ ፈላጭ ቆራጭ ቢሆን ኖሮ ምርጫው
በነሱ ቡራኬ ይሰጠው ነበር፡፡ ታዲያ ይሄ ማለት አይ ሲ ሲ በምእራቡ ዓለም የተጠሉትን የአፍሪካን ‹‹መሪዎች››
ይከሳል ማለት ነው? (ይህን ነበር በተደጋጋሚ በማንሳት በተለይም በኤፕሪል መጣጥፌ ትኩረት ስጥቼው የነበረው::)
የአፍሪካ ‹‹መሪዎች››በተደጋጋሚ ‹‹ንቀት›› በማለት
የሚያላዝኑበት ጉዳይ ዋነኛውን ቁም ነገር፤ ሚያካሂዱትን የሰብአዊ መብት ወንጀልን፤የጦር ወንጀለኛነትን፤ የዘር
ጭፍጨፋን፤ የተሰረቁና የተጭበረበሩ ምርጫዎችን ለመሸፋፈን ገለባ የማድረግ ጥረታቸው ነው፡፡ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች››
የምእራቡ ዓለም በአፍሪካ ላይ ያለው ንቀትና አክብሮት ማጣት በማለት እራሳቸው ለሕዝቦቻቸው ያላቸውን ንቀትና
አክብሮት የለሽነት መሰረታዊ የሆነውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ወደ ሌላ ለመለጠፍ የሚያደርጉት ሰሚ የለሽ ባዶ
ጩኸታቸው ነው፡፡
በእውነት የአፍሪካ ‹‹መሪዎች የምእራቡን ዓለም አክብሮት ማግኘት
ከፈለጉ፤ መንገዱ ጩኸት፤ ማጓራት፤ አንዱ የሌላውን ወንጀል ለመደበቅ መሰባሰብ፤ጥረስ ማፏጨት አይደለም፡፡ ትክክለኛው
መንገድ ገንዘባቸውን በጩኸታቸው ቦታ ማድረግና፡ የአይ ሲ ሲ ተመጣጣኝ እንዲያውም ከአይ ሲ ሲ የበለጠ ተደማጭና
ተቀባይነት ያለው ሕጋዊና የሕዝብና ሌላው ዓለም አመኔታ የሚሰጠው ተቋም መገንባት ነው፡፡ አይ ሲ ሲ ን መጥፎ ስም
ከመስጠትና ከማጥላላት አፍሪካውያን ‹‹መሪዎች›› ከመሃላቸው ወንጀለኛውን፤ የሕዝብ አመኔታ ያጣውን፤ ሰብአዊ መብት
የሚደፍረውን፤የጦር ወንጀለኛውን፤ የዘር ጭፍጨፋ የሚያካሂደውን፤ እየመነጠሩ ለፍርድ የማቅረብ ብቃትና ችሎታው
ፈቃደኝነቱ አላቸው በማለት በተግባር ያረጋግጡ፡፡ ‹‹የአፍሪካ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት›› እንዴት ያለ ግሩም ስያሜ
ነው! እንዲህ አይነት ኢንስቲቱሽን በአፍሪካ ምድር ላይ ተመስርቶ ማየት እንዴት የሚያስፈነድቅ ተግባር ነው! ይሄን
ለማየት ግን ተስፋ የለኝም፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ለአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› የመዝናኛ አዳራሽ የመስራት አቅሙ ስለሌለው
200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ምጽዋት ከቻይና ተሰጠው፡፡ ለቻርልስ ቴይለር ችሎት ሂደት አይ ሲ ሲ 250 ሚሊዮን
ዶላር ነው ያወጣው፡፡
ኢምቤኪ በቅርብ ቀን ዲስኩሩ ‹‹የአፍሪካ ምሁራን በአንድ ድምፅ
ምእራቡ ዓለም በአፍሪካ ላይ የሚያሳየውን ‹‹ንቀት›› እንዲያቆም ሊጠይቁና ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባል›› የሚል
ጥሪ አሰምቷል፡፡እኔ ደግሞ በዓለም ዙርያ የሚገኙትን የአፍሪካን ምሁራን የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› ለአፍሪካ ሕዝቦች
የሚያሳዩትን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲያቆሙ በአንድ ድምጽ በአንድነት እንዲጠይቁና ጥያቀውን በሁሉም የዓለም ዙርያ
እንዲያስተጋቡት እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ‹‹ከአይ ሲ ሲ ጎን መቆም ማለት የአፍሪካን ‹‹መሪዎች›› በወንጀል፤ በግድያ፤
በዘረፋ፤ በሰብአዊ መብት ጥሰት፤ በዘር ወንጀለኘነት ለፍርድ ማቅረብ ማለት ነው! አይሲ ሲን የመደገፊያው ወቅት
አሁን ነው!
zehabesha
No comments:
Post a Comment