Sunday, September 22, 2013

የፖሊስ ጭቆናዊ አስተዳደር በተንሰራፋበት ሃገር ውስጥ በተቀቃዋሚነት መቆም እጅጉን አስቸጋሪና አደገኛም ነው፡፡

የሜይ 2005ቱን ምርጫ ተከትሎ ሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፤በርካታ የሲቪክ ማሕበረሰቡ አመራሮች፤የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፤የነጻው ፕሬስ አባላት፤ከያሉበት በመታደን ለሁለት ዓመታት ያህል ወህኒ ተጥለው ነበር፡፡ ላለፈው 6 ዓመታት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ማንኛውንም እንቅስቃሴ ተነፍገውና ታግደው፤በጠበበው የፖለቲካ መድረክ ውስጥ እንዲሹለከለኩ ብቻ ነበር የተፈቀደላቸው፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን ተቃዋሚ የሆኑትን የነጻው ጋዜጣ ባለቤቶችና አባሎቻቸው፤ ሌሊችም የተቃዋሚ ደጋፊዎችና አባላት እየተገፉና ከመስመር እንዲወጡ ጫና እየተደረገባቸው፤ በገዢው ጭቆናዊ አመራር እየተሰቃዩ፤እየታሰሩ፤ ከሕብረተሰቡ ጋር እንዳይገናኙ እየተደረገ፤እነዚህ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተዳክመው፤ ሕዝባዊ ግንኙነታቸው እንዲቋረጥ አድርገውባቸው፤ ከገዢው ፓርቲ ጨቋኝ ስርአት የተለየ እንዳለና ተቃዋሚዎችም ለዚህ የቆሙ መሆናቸውን የሚያሳወቁበት መንገድ ባለመኖሩ ተዳክመዋል፡፡ በሌላም ወገን አንዳንዶቹ ተቃዋሚዎች ተጠያቂነትን በመዘንጋት፤ግልጽነትን በመሸሽ ከአባሎቻቸው ጋር ተቃቅረዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ተቃዋሚ ነን እያሉ በውስጣቸው ግን ዴሞክራሲያዊነትን መቀበልና መተግበርን ስለሚፈሩት አቅቷቸዋል፡፡ ከዚያም አልፎ እራሰቸውን እንደሚቃወሙት ገዢ ፓርቲ ፈላጭ ቆራጭ በማድረግ የራሳቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሲሉ በፓርቲው አባላት መሃል፤ ግጭትንና አለመግባባትን መቃቃርን ፈጥረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያሉትን ተቃዋሚዎች በምንም መልክ ይፈረጁ በምንም ፤በገዢው ፓርቲ አሸናፊ ነኝ አበባል የተጠቀሰው የ99.6 የምርጫ ውጤት ከ2005ቱ የተቃዋሚ ድርጅቶች አሸናፊነት ከተመዘገበው ሃገር አቀፍ ከፍተኛ ድል ጋር ሲተያይ እጅጉን የተለየና የውነትና የሃሰት ድል የታየበት የተቃዋሚዎች ብርታትም የተመሰከረበት ለመሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ካለፈው የ6 ዓመት ሁኔታ የተቃዋሚው ፓርቲ አባላት ሊማሩና ሊያውቁ የሚገበቸው ጉዳይ ቢኖር ዝም ብሎ “መቃወም መቃወም፤ደሞም መቃወም”፤ ለመቃወም ብቻ ሊሆን አይገባም፡፡ የተቃዋሚዎች ሁኔታ ገዢውን ፖርቲና ፖለቲካዊ ዝግመቱንና ያለፈበትነትን መቃወም ብቻ ሳይሆን፤ከዚያም ባሻገር ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ዋናው ዓላማቸው ለሃገራችን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን እስከመዘርጋት ሊጓዝ የግድ ነው፡፡ ዘወትራዊ ተግባራቸው ሳይሰለቹና ሳይደክሙ ሊያከሂዱት የሚገባ ትግላቸው ግልጽነትንና ተጠያቂነትን አበክረው መጠየቅና ለዚያ መታገል ሊሆን ይገባል፡፡ የገዢውን ፓርቲ እለታዊ እንቅስቃሴ በማጤን አግባብነት የሌለውን በመጠየቅ ለመስተካከሉ መቆም፤ መታገል፤ ሂስ ማድረግና መተቸት፤ ያንንም ይፋ ማድረግ ሲኖርባቸው ከገዢው ፓርቲ የተሻለ አመለካከትና መመርያም በማውጣት ለሕዝቡ እያቀረቡ ብቃታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች የገዢውን ፓርቲ ድክመት ብቻ እያነሱ ያንን መኮንን ብቻ ሳይሆን የነሱን የተሻለ ሃሳብም ማሰማት ይገባቸዋል፡፡
ገዢውን ፓርቲና አመራሮቹን በስድብ ክምር ማጥላላትን፤ጥርስን በመንከስ ማንኳሰስ የተቃዋሚውን ፓርቲ አስተሳሰብ ከፍተኛነት ከማቅለሉ ባሻገር ምንም ፋይዳ የለውም:: ተቃዋሚዎች ለተጠያቂነትና ለመልካም አስተዳደር ያላቸውን ሃሳብና ራዕይ ያዛንፍባቸዋል እንጂ የሚየስገኝላቸው ጠቀሜታም ሆነ ትርፍ የለውም፡፡ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በስልጣን ላይ ስላለው ገዢ ሃይል የሚጠቀሙበት ቋንቋ ቁጣ፤ፍርሃት፤የበታችነት ስሜትን የሚያሳይ፤ነው፡፡ ጥቂቶች ብቻ ናቸው እውነትን ይዘው በቆራጥነትና በሎጂክ የሚናገሩትና የሚሟገቱት፡፡ የገዢውን ፖሊሲዎች፤ፕሮግራሞችና ፕሮጄክቶች፤በሰከነ ጥናትና ግምገማ፤ በምርምር አቅርበው የሚናገሩና በምትኩም የተሸለ ጥናት የሚያቀርቡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ገዢው ፓርቲ የሃገሪቱን ለም መሬቶች በሽርፍራፊ ዋጋ ለውጭ ዜጎች መሸጡን ይፋ ያወጡትና ሕዝቡ እንዲያውቅ ያደረጉት ሃገራዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሳይሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ የዉጭ አገር ድርጅቶችና ተመራማሪዎች ናቸው፡፡ በተለያዩ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድቦች ሳቢያ የሚከሰተውን የአካባቢን ችግር በተመለከተም ጉዳዩን ይፋ ያደረጉት የውጭ አገር ተመራማሪዎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን የኤኮኖሚ ፖሊሲውን ግምገማ፤ ምንነትና ድክመቱንም በተመለከተ ይፋ እያወጡ ጥናታቸውን ያቀረቡት የውጪ አበዳሪ አካላት ሲሆን ጥቅምን ከመጠበቅ አኳያ ጥናታቸው አጠያያቂ ነውና እውነታው ይፋ የሚሆነው በታወቁ የሚዲያ አጥኚዎች ነው፡፡ ገዢውን ፓርቲ በተጨባጭና በሃቅ ላይ በተመሰረተ የፖሊስና የፕሮግራም አቀራረጹን መተቸት ባለመቻላቸው ተቃዋሚዎቹ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን ወደማጣቱ ደርሰዋል፡፡ የሚያስፈልገው የቃላት ውግዘት አይደለም፡፡ የሚያስፈልገው ክሪቲካል የሆነ ሚዛን የሚያነሳ ግምገማና የገዢውን ፓርቲ የፕሮግራሙን፤ የፖሊሲውን መክሸፍ በተጨባጭ ማሳየትና ለዚያም ማስረጃዎችንና ጥናቶችን በተገቢው ማቅረብ ነው፡፡ በዚህም ነው ሕብረተሰቡ ከገዢው ፈላጭ ቆርጭ የተሸለና የተለየ ራዕይ ከተቃዋሚዎች ሊጠብቅና ሊያልም የሚችለው፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ውድድር ከመዘጋጀት ባሻገር ብዙ ሊጫወቷቸው የምችሏቸው ሚናዎች አሏቸው፡፡ የአባሎቻችውን የደጋፊዎቻቸውንና የጠቅላላውን ሕብረተሰብ ንቃተ ሕሊና ማዳበርና ለትግሉም ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፖሊሲያቸውን በሚገባ በማዳረስና በማስረዳት ሕብረተሰቡን ማስተማር አለባቸው፡፡ ክርክርና ውይይት በማዘጋጀት፤በአስፈላጊ ርእሶች ላይ በመነጋገርና ሕዝቡንም ተሳታፊ ማድረግ ሁኔታዎችን እያነሱ ችግሮችን በማንሳትና መፍትሔዎችን በመጠቆም የሃገሪቱን የወደፊት ራዕይ መጠቆም አለባቸው፡፡ ሁኔታዎችን በማስተካከል የዴሞክራሲ ባሕል የሚዳብርበትን መንገድ ቀያሽ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስኬታማ መሆን የሚችሉት ለወጣቱና ለሴቶች አስፈላጊውን የአመራር ስልጠና ለመስጠት ማቀድና መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡ የብዙዎቹ ተቃዋሚ ድርጅቶች አመራሮች ሃምሳውን ዓመት የዘለሉ ሲሆኑ በአመራሩ ላይ ያሉትም የሴቶች ቁጥር አናሳ ነው፡፡ ‹‹ዕድሜ ቁጥር እንጂ ሌላ አይደለም›› በወጣቱና በዕድሜ ጠገብ ፖለቲካ መሃል ግልጽ የሆነ ልዩነት አለ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ታላቅ የመነሳሳት ፍላጎት፤ ቅልጥፍና፤ቆራጥነት፤ በዓላማው ላይ መራመድን ይቀይሳል:: ያንንም ተግባራዊ ለማድረግ ፈጣንና ቆራጥ ነው፡፡ ያደርገዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሚዲያውና ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር በመሆን ተቀናጅተው ወደ ሕዝቡ መድረስ አለባቸው፡፡
ከሰብኣዊ

 https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/09/22/97-5/

No comments:

Post a Comment