ዛሬ ዋልያዉ በካላበር ስታድየም ልምመድ ሰርትዋል፤ሜሳዉ በጣም አሸዋማ እንደሂነና ጉልበት እንደሚፈልግ ተጫዋቾቹ
ተናግረዋልጨዋታዉ ነገ በናይጄሪያ 10 ሰአት በኢትዮጲያ 12 ሰአት ይደረጋል፤ዛሬ ዝናብ ዘንብዋል፤ወበቁም
ለመተንፈስ ያስቸግራል፤ከተጫዋቾቹ በፊት አስቀድሞ የመጣዉ የምግብ ባለሙያዉ ተስፋዮ ከካላበር ይልቅ ሌጎስ በጣም
አንደሚሞቅ ነግሮኛል፤ አሰላለፍን በተመለከተ እንደደቡብ አፍሪካዉ የአፍሪካ ዋንጫ ጌታነህ ከበደ የመሀል ክፈሉ ላይ
በስተቀኝ እንደሚሰለፍ ጥርጣሬዎች እዉን እየሆኑ ነዉ፤አስራት አዳነ እና ምንያህል የመሀል አማካዮች..ሳላ እና ሽሜ
አጥቂዎች ይሆናሉ፤ ቡድኑ 30 ሁኖ ነዉ የመጣዉ…7ቱ ተቀናሾችም ታዉቀዋል፤ሁለቱ ፕሮፌሽናሎች ዩሱፍ እና ፉአድ
ከተቀናሾቹ ሁነዋል፤አስገራሚዉ ተቀናሽ የጊዮርጊሱ ሳምሶን ነዉ፤ግብ ጠባቂዉ በሰበታዉ ደረጀ ፣፣በጀማል እና ሲሳይ
ተበልጦ ከ23ቱ ዉጭ ሁንዋል፤በተጫወተባቸዉ ጨዋታዎች ብቃቱ ጥሩ እየሆነ መምጣቱ ቢታይም በአሰልጣኞቹ
አልታመነበትም…ገብረ ሚካኤል ያእቆብና መድሀኔ ታደሰም ከ23ቱ ዉጪ ሁንዋል፤ ነገ ምርጥ 11ዱ ይጠበቃሉ፤ካፍ
ከሰኣታት በፊት የአህጉሪቱን የአመቱ ምርጥ ተጫዋችነት እጩዎች ይፋ ሲያደርግ ጌታነህ ከበደና አዳነ ግርማን አፍሪካ
ዉስጥ ከሚጫወቱ መሀል አካቷቸዋል፤ይንጋና ስሜታቸዉ ምን እንደሆነ እጠይቃቸዋለሁ!!ሳላሀዲን ሰኢድ ደግሞ ከአፍሪካ
ዉጭ በሚጫወቱት ዝርዝር ከነ ዲዲዮ ደሮግባ ጋር በኮከብ እጩነት ቀርብዋል፤ ዛሬ ፕሪ ማች ሚቲንግ
ተደርግዋል፤ናይጄሪያዎቹ አንድ አስገራሚ ጥያቄ ጠይቀዋል፤ከጨዋታዉ በሁዋላ ርችት መተኮስ እንችላለን ወይ
ብለዋል፤ማሸመፋችን እርግጥ ነዉ በሚል መንፈስ ነዉ ይህንን የጠየቁት!!
No comments:
Post a Comment