Friday, November 22, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር/ኢሕአግ/ ምልምል አርበኞችን አሰልጥኖ ማስመረቁን አስታወቀ


mreqa
ከአርበኞች ግንባር ለዘ-ሐበሻ የተላከ ዜና፡ የኢሕአግ የስልጠና ማዕከል ለወራት ያህል ለምልምል አርበኞች ሲሰጥ የነበረው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና በህዳር 12-2006 ዓ/ም አጠናቋል። ስልጠናውን የተካፈሉ ምልምል አርበኞች ከምልምል አርበኝነት ወደ ሙሉ አርበኛ መሸጋገራቸው ደስታ የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸው የድርጅቱ የስልጠና ማዕከል ያሰነቃቸው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና ቀድሞ ከነበራቸው የዕውቀትና የአካል ብቃት አንጻር የተሻለ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸው የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመቀየርና በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ሲንቀሳቀስ ባልታየው አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ላይየአገርና የወገን ችግር ፈች ኢትዮጵያዊ ተልዕኮ ለመወጣት ራሳቸውን በቆራጥነት መንፈስ እንዳዘጋጁ አስታውቀዋል።
mreka
ተመራቂ አርበኞቹ አክለው እንዳብራሩት በተለይ በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወገን እንደሌላቸው ሁሉ ታርደው በየጎዳናው መጣላቸው ሊታገሱት የማይችሉት አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነ አስረግጠው ለዚሁ አጸፋ በእብሪተኛው ወያኔ ቡድን ላይ ጥቃት በመሰንዘር የወገን ደራሽ መሆናችንን እናስመሰክራለን ሲሉ በቁጣ መልክ ገልጸዋል። በህዳር 12-2006 ዓ/ም በተከናወነው የምልምል አርበኞች ምረቃ ስነ-ስርዓት የኢሕ አግ ከፍተኛ አመራር አባላት ተገኝተው እንኳን ለምረቃው ዕለት አደረሳችሁ ካሉ በኋላ በጽናት የኢትዮጵያን ተጠቅሶ የማያልቅ ተግዳሮት መፍትሂ ለመሻትና አንድነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት አገር ለመገንባት በሚደረገው ትግል የሚሰጣቸውን ግዳጅ ለመወጣት ከወዲሁ የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠቁመዋል። በስልጠናው የተሻለ ብቃት ላሳዩ ተመራቂዎችና ሴት ተመራቂዎች ከአመራሩ የማበረታቻ ሽልማት ተቀብለዋል ዝግጅቱም በድርጅታዊ መዝሙር ጀምሮ ሞቅ ደመቅ ባለና የጀግኖችን ተጋድሎ በሚገልጽ መልኩ በድራማ፣ በስነ-ጽሁፍ፣ ቀስቃሽ በሆኑ ዘፈኖች፣ ቀረርቶዎች፣ በውታደራዊ ሰልፍ ትርኢትና በመሳሰሉት ትዕይንቶች ታጅቦ ተከብሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የግንቦት 7 ሕዝባዊ ሃይልም በአቶ አንዳርጋቸው እና በአመራሩ ላይ የወያኔ ተላላኪ የግድያ ሙከራ ለማድረግ አቅዶ ሳይሳካለት ቀረ ባለበት ወቅት ወታደሮችን እንደሚያስመርቅ የገለጸ ቢሆንም ምርቃውን የሚያሳይ ፎቶ እስካሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሳት ፎቶ የለም።

zehabesha

No comments:

Post a Comment