Saturday, November 30, 2013

በሳውዲ አገር የተፈጸመው የኢትዮጵያውያን ውርዴት ያተስተናገደው ማን እንደሆን የማያውቅ ወይም የሚጠራጠር ካለ መልሱ (ተ.ሀ.ሕ.ት.) ነው።


ከጎሹ ገብሩ
Cry-ethiopiaበመጀመርያ የወገናችሁ ሥቃይና መከራ አንገብግቧችሁ ሲያለቅሱ አልቅሳችሁ፣ሲከፉ አብሮ ለምከፋት፣ሲቸገሩ ችግራቸውን አብሮ ለመጋራትና በደላቸው የናንተ በደል መሆኑን ለማሳዬት በዓለም ዙርያ ለምትገኙ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በሙሉ በጣም ኮርቸባችሁ አለሁ። ወሳኙ ሰላም፣ፈቅርና አንድነታችን ማረጋገጥ የምንችለው በጋራ ሥናብር ብቻ ለመሆኑ እሩቅ ሳንሄድ የወያኔው ድራማ በጌቶቻቸው አገር ሽፋንና ከለላ በመጠቀም ያደረጉትን እኩይ የመሃይሞች ድርጊት ውስጡ ለቄስ መሆኑን እርቃኑን በማውጣት ዓይንና ጀሮ ኑሮት ማየትና መስማት ለሚችል ከማስጠንቄቃው ጋር የተላለፈው መልዕክት የመጨረሻው የኢትዮጵያውያን የበቃን ኑዛዜ ነው። ወላጆቻችን አሟሟቴን አሳምርልኝ ብለው ሲፅልዩ ሰንሰማ ለሞት ምን ጌጥ አለውና ብለው ነው እንዲህ የሚሉት እያልን የአባባሉ ትርጉም ሳይረዳን የምናነዉር ወይም የምናሽሟጥጥ ነበርን።
ይሄውና ሲሉት የነበረዉ አባባል ፍልትው ብሎ ለማየት በቅተናል።እነዚህ በሳውዲ አረብያ ሬሳቸው በጎዳና ላይ እንደ በድን ውሻ ሲጎተቱ ፣የሚያምረው ምስላቸው እንደ ከሰል ጠቁሮ ያየነው፣በአረቦች የሰላ ጎራዴ የሰራ አካላታቸው ተዘልዝሎ ያየነው፣እጅና እግሮቻቸው አስረውና አዘቅዝቀው እየተረዳዱ በአኮርማጆ ሲደበደቡ ድምጻቸው ከፍ አድርገው በእግዚያብሄር ሥም ማሩን የሚሉት እህት ወንድሞቻችን ለነጻነትና እንጀራ ፍለጋ የመጡ እንጅ የፈጸሙት በደል ወይም የሚያውቁት ሌላ መንም ነገር እንደለለ የማያውቅ ይኖራል ብየ አልገምትም። ሥለዚህ በማያውቁት አገርና ህዝብ እንደ ረከሰ እንሰሳ ተወርውሮ መቅረትን ስላስጠላቸው ነው ወላጆቻችን ይህን ብለው ሊፅልዩ የቻሉት። ሞት የማይቀር ለሁሉም ፍጡር ግዜው ጠብቆ በቀጠሮው ቀን ከተፍ የሚል አድሎ የማይታይበት  የእግዚአብሄር  ስጦታ ነው።
ስደት ጥንትም የነበረ አሁንም ያለ ለወደፊትም የሚኖር ነው አሁን በኛ  አልተጀመረም። ከ1400 ዓመት በፊት የነብዩ መሐመድ ተከታዮች ከአገራቸው ሸሽተው የኢትዮጵያን አፈር ሲረግጡ  መጠግያ ሰጥተን ያስተናገድን እንግዳ ተቀባዮቹ ኢትዮጵያውያኖች ውለታችን ተዘንግቶ በሳውዲ ቅልብ ወታደሮች አጥንታችን ከስክሰው ደማችን ያፈሰሱት በቅዱስነቱ ከሚታወቀው ከተማ መሃል ላይ ነው።ግን ትእዛዙ የሰጣቸው አካል ከመጋረጃው በኋላ መሆኑ ብንግነዘብም ቅሉ ይህ ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም ያደፋፈሯቸው ሁለት መክንያቶች ጠቅሼ ማለፍ እፈልጋለሁ፦
  1. አንደኛና ዋናው ምክንያት ብየ የምገልጸው በኢትዮጵያውያን መካከል የነበረው መተሳሰር፣ህብረትና ጠንካራው አንድነታችን ለ23 ዓመታት ያህል ለህልውናችን ተፈታታኝ በሆነ መልኩ በመላልቱ ምክንያት በደል እያደረሱብን ያሉት ጠላቶቻችን በቅርብ ሆነው ስላጤኑት አሁን የፈለግነው ብንሰራ ሊያቆመን የሚችል ሃይል  የለምና ትዕቢታቸውን አፈንድተን  የባርነት ቀንበር ልንጭንባቸው የምንችለው ወቅቱ አሁን ነው በማለት ይሄውና በ21ኛው ክፍለዘምን የባርያን ሥራአት አድሰው በኛ ላይ ለመጫን እየተደረገ ያለ የሂልና ጦርነትና ሰጥ ረጭ አድርጎ ለመግዛት የተተበተበ የኋላ ቀሮች ቅዠት ሲሆን።

  1. ሌላው አብይ መክንያት ደግሞ ወገኖቻችንን ማሰቃዬት የለብህም በሎ የሚገላምጥና የሚያፈጥ የኛ የምንለው መንግስት የለለን፣አለ የሚባልለት የተጋድሎ ሀርነት ህዝብ ትግራይ(ተሀህት)መንግስትም በቱጃሮች ሳምባ የሚተነፍስና የሚሽከረከር በጥቅም አይኑ የታወረ ለነሱ የቆመ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን አይሰሩ ግፍ ቢሰራም ደንታ የለለው በመሆኑ የተነሳ የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም በስውዲ መናገሻ እንደ ጎርፍ ሲፈስ እያየ ብዙ ምክንያቶች በመደርደር አድበስብሶ ከማለፍ በቀር የሰራው ምነም ነገር የለም። ከሁሉ በላይ የሚያሳዘነው የተሀህት ተውካይ ተብየው ትእቢት በተሞላው አንደበቱ ሳውዲ የወሰደችው እርምጃ አግባብነት ያለው ነው ብሎ የምስክርነት ቃሉ ሲሰጥ ተሀህት ለማን እንደቆመ ግልጽ አድርጎ የሚያሳይ ማስረጃ ነው።ጥቂት ለወያኔ ያደሩ ግለሰቦች ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል በአፋጣኝ ቢያጓጉዝ ነገር ግን ግምቱ 23000 የሚጠጉት ወገኖቻችን ግን በስቃይ ላይ ለምሆናቸው የምናየው የምንሰማው ሃቅ ነው። መንግስት ያላቸው ሀገሮችማ ዜጎቻቸውን ለማዳን ምክንያት ሲለግቡ አይታዩም።

ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ፦ መንግስት የላትም የምትባለው ሶማሊያ እንኳ በቅርብ ወራታት ውስጥ አንድ የሶማሊ ዜጋ በመገደሉ የተነሳ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት የወገኔን ገዳይ ለፍርድ ካላቀረባችሁ ከናንተ ጋር የሚኖረን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አቋርጣለሁ በማለቷ የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናትም ለጉዳዩ ተኩረት በመስጠት በነገሩ ለመተባበር ተስማምተዋል። ሌላው ከ20ና ከ25 ዓመት በፊት የናይጀርያ ዜጎች በሱዳኗ መናገሻ ከተማ ካርቱም ላይ ችግር ቢከሰትባቸው የናይጀርያው መንግስት ስድስት ስዓት በማይበልጥ ግዜ ዜጎቹን በሙሉ ወደ አገራቸው በማጓጓዝ አደጋውን ሊከላከል ችሏል።አገር ቤት ያለው ወገናችን በወገኖቹ ላይ የተፈጸመውን በደልና ሥቃይ ለመቃወምና ብሶቱን ለሳውዲ መንግስት ለማሰማት በህገ ደንባቸው ያሰፈሩትን መብት ተጠቅሞ ቢወጣ በወያኔው የፌደራል ቅልብ ወታደር የደረሰበት በደል፣ሥቃይና ድብደባ ያላዬ ይኖራል ብዬ አልገምትም።
ይህ በኢትዮጵያውያን ያንዣበበው አደጋ ለመከላከልና ቀርፈን መጣል የምንችለው በኢትዮጵያዊነት ሥም ተባብረን ስንመክት ብቻ ነው። በጎሳ፣በዘር፣በጎጥና በሃይማኖት መለያየቱ ምንኛ እንደጎዳን ለቀባሪ እንደ ማስረዳት ስለሚሆንብኝ መልሱ ለናንተ ልተወው።
ነገር ግን አንድ ተልቅና ብሩህ ተስፋ ሰጭ ሆኖ ያገኘሁትና የታዘብኩት ነገር ቢኖር በተለያዩ ምክንያቶች በየ ማእዘኑ አንገቱን አጎንብሶ የነበርው ኢትዮጵያዊው ወገናችን ከጠርዝ አስከ ጠርዝ ተቆጥቶ በመነሳት ያሳየው ህብረት ለጠላቶቻችን ያርበደበደ ትልቅ የህልውናችን መለያ የሆነውን አንለያይም አንድ ነን ማለቱን ነው።
ወያኔ ባይገፋኝ ከተወለድኩበት
ሰደትን መምረጡ መች ወደድኩት
መብቴ ተረግጦ ነው የተዋረድኩት
እህቶቼም ተደፈሩ ሳይወዱ በግድ
ደሜም አጨቀየው የሳዉዲ አስፓልት
ከባህር ማዶ ላለነው ከአገር ቤት
እረ-ፍርዱ ሰጠን የሰማዩ አባት።
ኦ-ሳውዲ በስመ ገናና
ወራዳ ልበልሽ የድሃ ደመኛ
ህጻናት የሚረሽኑብሽ ከአውላላው ጎዳና።
በቅድሱ ስፍራ በሁሉ የሚከበር
የንጹሃን አካል ተዘልዝሎ ሲመተር
ፍጡርን የሚያሰቃይ በሚዘገንን
ያውም በሰለጠነው በአሁኑ ዘመን
በጣም ያሳፍራል እንዲህ ለመናገር።
ኩላሊቱን ለማዘረፍ የሰራ አካላቱ
ከቶ ለምን ይሆን ወደ አረብ መሰደዱ
እንዲህ ለማይቀረው ተዋርዶ መሞቱ
ተከብሮ ለመቀበር በወገን ዘመዱ
ከባድማችን ላይ ይሻላል መሞቱ።
መሳለቅያ ሆነናል በሞላው ዓለም ላይ
ይብቃን ውርዴት እንግልት ስቃይ
በክብር እንሙት ከአፈራችን ላይ።
በወገኖቻችን ላይ የተፈፅመው በደል
ውጤቱ ይታያል ሳይውል ሳያድር
እንዲህ ያለ ግፍ እንዴት  ይረሳል
በሰፈርይት ቁና መሰፈር አይቀር።
አጼ ተዎድሮስ ቢኖሩ በሕይወት
ምን ይሉ ይሆን በውንት
አብደላ ሳውዲን በኢትዮጵያውያን ደም ሲያጨቀያት።
መስዋእትነት የከፈሉትን ወገኖቻችን መንግስተ ሰማያት ያዋርሳቸው
Ze-Habesha Website may contain advice, opinions, and statements of various information and content providers. The Website neither represents nor endorses the accuracy of information or endorses the contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of the authors.

No comments:

Post a Comment