Thursday, November 21, 2013

በቬጋስ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ

በቬጋስ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ በወገኖቻቸው ላይ የሚፈጸመውን ግፍና የወያኔ አገዛዝ ለዜጎቹ ግዴለሽ በመሆኑ በሰልፍ ተቃወሙ

የአገዛዙ ደጋፊዎች ሳውዲን ብቻ እንቃወም በማለታቸው በሰልፉ ላይ አለመግባባት ተነስቶ ነበር
SONY DSC
SONY DSC
SONY DSC
SONY DSC
SONY DSC
SONY DSC
በቬጋስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ በዜጎቻቸው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና በአገር ቤቱ አገዛዝ ለሚሰቃዩት ወገኖች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ለሳውዲ ያሳየውን ጥብቅና በማንሳት በጋራ ማክሰኞ በከተማዋ ፌደራል ህንጻ ፊት ለፊት በመገናኘት ተቃውሞ አቀረቡ። አንዳንድ የስርዓቱ ደጋፊዎች የመጣነው ሳውዲን ብቻ ለመቃወም ነው በሚል ስርዓቱን ተቃወሙ ያሏቸውን ለመቃወም በመሞከራቸው በሰልፉ ላይ መጠነኛ የቃላት አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር።
በሰልፉ ላይ ቁጥራቸው በመቶ የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥቁር በመልበስ፣ በሳውዲ በወገኖቻቸው ላይ የተፈጸሙ የግፍ እርምጃዎችን የሚያሳዩ ፖስተሮችን እና የሳውዲንና በአገርቤት ያለውን አገዛዝ የሚቃወሙ መፈክሮችን ጭምር በመያዝ ተቃውሙ ላይ ተገኝተዋል።
የሰልፉ ዋነኛ አስተባባሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኮሚኒዩቲ በላስ ቬጋስ ሊቀመንበር አቶ ጌትነት ጸጋዬ ሳውዲ በስፍራው እንደተናገሩት ሳውዲ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመችው ግፍ እንዲቆም ድምጻችንን ከማሰማት ጎን ለጎን መንግስትም በተገቢው ሁኔታ ሀላፊነቱን እየተወጣ ባለመሆኑ ለዜጎቹ ስቃይ ትኩረት እንዲሰጥ እንጠይቃለን ብለዋል።
በሰልፉ ላይ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ከተሰሙት መፈክሮች መካከል <<ሼሞን ሳውዲ!>> <<ሼሞን ወያኔ!>> ከሚሉ መፈክሮች ጀምሮ ተከብረሽ የኖርሽው የሚለውን አገራዊ ዜማ አዚመዋል።
<<ሼሞን ወያኔ!>> ለምን ይባላል የመጣነው ሳውዲን ለመቃወም ነው የሚሉና በተለይ በአገር ቤት በሳውዲ ያ ሁሉ መከራ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ተገቢውን ምላሽ አለመስጠቱ ብቻ ሳይሆን ዜጎች በሳውዲ ላይ ለመቃወም አደባባይ ሲወጡ የሚያስርና የሚደበድብ አገዛዝ ሊጠየቅ ይገባል ከሚሉት ጋር እሰጣ ገባ በሰልፉ ላይ ተነስቷል።
ጉዳዩ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የዜግነት ክብር የሰብዓዊነት ጉዳይ በመሆኑ ዜጎች በዚህ አጋጣሚ እንኳን በጋራ ድምጻቸውን ለማሰማት ወጥተው መንግስትን ላለማስቀየም መሞከራቸው በወቅቱ ቁጣን ቀስቅሷል።
ከተሰሙት መፈክሮች ውስጥ <<ለሳውዲ የወገነውን የወያኔ አገዛዝ እንቃወማለን!>> የሚሉ መፈክሮችም ተጽፈው ተይዘዋል።
በከተማዋ የሚገኙ የክርስትናና የእስልምና ዕምነት ተከታይ መካከል አንድ የሙስሊምና አንድ የክርስትና አባቶች በወገኖቻችን ላይ በሳውዲ የተፈጸመውን ግፍ አውግዘው ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም የወገኖቻቸውን ድም ማሰማታቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል። አምላክ በሕዝቡ ላይ የተፈጸመውን ግፍ ተመልክቶ ፍርድ እንደሚሰጥም ገልጸዋል።በተለይ የሙስሊሙ ተወካይ የሳውዲዎች በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመ ግፍ ከእስልምና ጋር የሚያያዝ ሳይሆን የራሳቸው ጭካኔ ነው በማለት ከቁራን ጠቅሰው አስረድተዋል።
ከሰልፈኛው መካከል ሳውዲን ብቻ ለዛሬ እንቃወምና ለሌላ ጊዜ ሁሉም በየራሱ ሀሳቡን ያንጸባርቅ የሚል ሃሳብ የሰነዘሩ ቢኖሩም ሀሳቡ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። ሰልፈኞቹ ሰልፉን ያካሄዱነት ፌደራል ህንጻ በአሜሪካ ሴኔት የዲሞክራቶች መሪ ሴናተር ሔሪ ሪድ ጽ/ቤት የሚገኝበት ሲሆን የአሜሪካ ሕዝብና መንግስት ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ በማድረግ በሳውዲ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ለማስቆም ድጋፍ ለመጠየቅ ጭምር መሆኑን ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ገልጸዋል።
በሰልፉ ላይ ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆነ ኤርትራውያንም በስፍራው በመገኘት ተቃውሟቸውን በጋራ አቅርበዋል። በሳውዲ ለሞቱት የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በአደባባዩ ላይ ተገልጿል።
በከተማዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ወደ ሎስ አንጀለስ በመጓዝ በዚያ ካሉት ጋር በአንድ ላይ በመሆን በሳውዲ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞ ለማቅረብ ወደዚያው ይጓዛሉ።

zehabesha

No comments:

Post a Comment