Tuesday, November 26, 2013

ጀኔራል ሓየሎምን እንደመጠቀሚያ (አሰገደ ገ/ስላሴ)


ስለ ጀኔራል ሓየሎም ማንነት በትጥቅ ትግል እና ደርግ ከተወገደ በኃላ  ከሞተም በኃላ በተለያዩ አካላት ብዙ ተነግሮለታል፡፡ ጀነራል ሓየሎም በ ፀረ-ደርግ በተደረገዉ ትግል መጀመሪያ 109173594.ux3gpXcs.EthiopiaJan092356በትግራይ  በኃላም ወደ ሰሜን ሸዋ ዘልቆ ከገባ በኃላ ስመ ጥሩና ገናና ነበር።
ሓየሎም በትጥቅ ትግል ጊዜ ወታደራዊ መሪ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካ መሪም ነበር። በመሆኑም ህዝቡ ከህፃን እስከ አዛውንት ፆታና ሃይማኖት ሳይለይ ይወዱት ነበር፡፡ ሌላዉ ቀርቶ የደርግ ምርኮኞችና በደርግ ወታደራዊ መሪዎች የነበሩም ሓየሎምን በመልካም የሰብኣዊ አያያዙና ጀግንነቱ ያደንቁት ነበር። ሃየሎም የኛ ቢሆን ንሮም ይሉት ነበር ከኮነረሬል መንግስቱ ሳይቀሩ ሳይወዱ በግድ ያደንቁት ነበር፡፡
ደርግ ከተወገደ በኃላም  ሓየሎምን በመጥፎ አይን የሚመለከተዉ ሰዉ አልነበረም ። በድንገት በባንዳዎች ከተገደለ በኃላም  መላዉ የኢትዮጵያ  ህዝብ አዝኖለታል። በወቅቱ የመንግስት የህዝብ ብዙሃን መገናኛዎች ተናግረውለታል። በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብና ታጋዮቹ የሓየሎምን ሞት ምፅአተ ምጥ ሆነባቸዉ። ሓየሎም በተንቀሳቀሰበት ቦታ ክልልና ብሄር በማይለይ መሪር ሃዘኑን በእንባ ገለፀ።
ከሞተ በኃላም የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ለተወሰነ ጊዜ በቴሌቪዢን መስኮት ፎቶግራፉን በማገላበጥ ብዙ ተናግረውለታል።
ስለ ሓየሎም ግን አንዳንድ መድረኮች ሲፈጠሩ ለጊዜው ፖለቲካ ፍጆታ ተብለዉ ፎቶ ግራፉን በቴሌቪዢን ስክሪን  በማስቀመጥ የተበጣጠሰ ታሪክ ስለ ሓየሎም መናገር ካልሆነ በስተቀር ስለ ሓየሎም መሰረታዊ የሆነ ታሪክ ተፅፎ ለትውልድ እንዲያልፍ  የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ካድሬዎቻቸዉ እስከ አሁን ሳይቆርጡ ቆዩ። በመከላከያ ሚኒስቴርም የሚገኙ ጋዴዎቹም  ሓየሎም በሚገባ የሚያውቁትም አንዳንድ የመታሰቢያ ወታደራዊ ት/ቤት ቢከፍቱለትም  ፣አነስተኛ ሓወልት ቢሰሩለትም  ስለ ሓየሎም ታሪክ ሊፅፉ አልደፈሩም ።አንዳንድ የሚፅፏቸዉ መፃህፍትም ቢኖሩም አሁን ላሉ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች የሚያሞካሹ ካልሆኑ በስተቀር ስለ ሓየሎምና የሌሎች በህይወት የሌሉ ወታደራዊ ና ፖለቲካዊ መሪዎች የጀግነነት ታሪክ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሳያስፈቅዱና ሳያስባርኩ  ሊፅፉ አይፈልጉም  አንዳንድ  የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችም  በተለያየ አጋጣሚዎች በመድረክ ላይ እየወጡ ሓየሎምን የሕ.ወ.ሃ.ት ፕሮግራም 85% አያውቀዉም ።በተጨማሪም ቀልቃላ ነበር ግን ደግሞ ተዋግቶ ደርግን አሸንፏል በማለት የሓየሎምን ህዝባዊ ፍቅርና ፖለቲከኛነት የሚያጎድፉ ወገኖች ነበሩ እነዚም ለራሳቸዉ ታሪክ የሌላቸዉ ናቸዉ።በተጨማሪም የኮነሬል ሃየሎም ለሃገሩ ሉኣላዊነትና ኣንድነት ጠንክሮ መታገሉ የማያስደስታቸው የነበሩ በመሆናቸው ለምን የሓየሎም መልካም ታሪክ ጎልቶ እንዲወጣ አልፈለጉም ? በኔ እምነት ከጅምሩ ወደ ትግል ሜዳ ሲወጣ የነበረዉን የሀገሩን ሉአላዊነትና አንድነት ፍላጎትና ፍቅር  እጅጉን ቀና ስለነበረ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በ1974 ዓ/ም ሻዕቢያን ለማዳን ሰራዊት መርተህ ወደ ኤርትራ በረሃዎችዝ መት ሲባል እምቢ ለማላምንበት ስትራቴጂና አላማ  አልሄድም ብሎ የቀረ ነበር። ኃላም የሻዕቢያ መንግስት በህዝባችን ላይ ይፈጥረዉ የነበሩ ግፍ ተቃዋሚ ነበር። በየመንና በሻዕቢያ በሓኒሽ  ምክንያት የነበረ ጠብም የኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት ይቃወም እንደነበረ ይታወቃል። የሆነ ሆኖ ሓየሎም በባንዳዎችና በከዳተኞች ተገደለና የሚያውቀዉ ሳይሰንደዉ አለፈ። የሓየሎም መልካም ዝና የማይፈልጉም በውስጣቸዉ ተደሰቱ። ሻዕቢያና  መሰሎቹ በደስታ ፈነጩ።
አሁን የሓየሎም ወርቃማ ታሪክ በሰለሙን ገ/አረጋዊ ታጋይ ነበር ትውልድ ቀዬዉ በአጋሜ አውራጃ በጎሎ መኸዳ ወረዳ በብዘት ቀበሌ የሆነ በ8/03/2006 ዓ/ም የሓየሎምን ታሪክ የሚተነትን መፅሃፍ በመቀሌ ሚላኖ ሆቴል ተበሰረ ።
ፀሃፊ ሰለሞን ገ/አረጋዊ የሓየሎምን ታሪክ ሲፅፍ  ከተወለደበት እስከ ታገለበት ጊዜ ኃላም የትጥቅ ትግል ታሪኩ መረጃ ለመሰብሰብ እጅጉን ብዙ ውጣ ውረድ አጋጥሞታል ። ከትግል  በፊት የነበረ ታሪኩ ለመሰብሰበ ብዙ ችግር አልነበረም የትግል ታሪኩን ግን እራሱና የቅርብ ጓደኞቹ ጥቂት አካል ጉዳተኞች፡ ከጥቂት  ወታደራዊ መሪዎች ፣ ከአርሶ ቸደሮች፣ ምልሻዎች፣ ምርኮኞች መረጃ ለማግኘት ችግር አልነበረዉም ትልቁ ችግር ግን ከሕ.ወ.ሃ.ት  ፅ/ቤት  ከሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ካድሬዎቻቸዉ መረጃ ለማግኘት ፈታኝ እንደነበር ይናገራል። ግን ደግሞ ብዙ ታሪካዊ ሃቆች በራሱ ጥረት አግኝቷል።

መፅሃፉ ተፅፎ ተጠናቀቀ
  ፀሃፊዉ መፅሃፉ አጀጋጅቶ ከጨረሰ በኃላ  የማተሚያ ገንዘብ የማግኘት ጉዳይ ፈተና ተጋረጠበት ፀሃፊዉ የሓየሎም ታሪክ ከፃፍኩ ይቅርና የሓየሎም መፅሃፍ ለማሳተም ብዙ ታሪካዊ ይዘት የሌላቸዉ እና የፓርቲ  መፃሄቶች፣ ጋዜጦች፣ሲታተሙ እንኳን የኢፈርት ካምፓኒዎች የትግራይ እርዳታ ማህበር ፣ የትግራይ ልማት ማህበር፣ የደደቢት ብድርና ቁጠባ  የመንግስት መ/ቤቶች ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የትግራይ  ቱሪዝም  ቢሮ፣  የወረዳ የቀበሌ መስተዳደሮች የግል ካምፓኒዎች  ብዙ ገንዘብ  በመስጠት ታትሟል። በየመ/ቤቱ ካምፓኒዎች፣ ት/ቤቶቸ በህ.ወ.ሓ.ት ባለስልጣኖች ተፅእኖ እየተደረገ እንዲሸጡ ይደረጋል የመንግስት ሰራተኛ የሕ.ወ.ሃ.ት አባላት የኢፈርት ካምፓኒዎች ሰራተኞች የመከላከያ ሚኒስቴር ሰራዊት ከደሞዛቸዉ የሚቆረጥ መፅሃፎቹን እንዲገዙ ይገደዳሉ። ስለ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ የሚተርክ ሰማኒያ ገፅ የያዘ ምፅሄት እንኳን በሚሊዮን የሚቆጠር መፅሄት ታትሞ በ100.00 ብር ተሽጣል በሁሉም ክልሎች  የመንግስት መ/ቤቶች በአስር ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተሽጧል።ሌሎቹም እንደ ወይን ጋዜጣና መፅሄትም በመንግስት ተቃማት  ስፖንሰርነት ይታተማሉ ወይን መፅሄትና ጋዜጣ ግን የ ሕ.ወ.ሃ.ት ልሳን ናቸዉ።
ለሓየሎም ታሪክ የያዘ የተፃፈ መፅሃፍ ግን ለማሳተም ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም የኢፈርት ካምፓኒዎች ፣ለደደቢት ብድርና ቁጠባ ፣ለትግራይ ቱሪዝም ቢሮ፣ ለባህል ትግራይ ፣ለትግራይ ኪነት ማህበር ፣ለትግራይ እርዳታ ድርጅት ለሌሎችም ፀሃፊዉ እርዳታ ጠይቋል። የተጠየቁት ግን  100% አሉታዊ መልስ ሰጡት። ሰውየዉ ማሳተሚያ አጥቶ በአሜሪካ ለሚገኙ የሓየሎም ቤተሰብ  የሓየሎም ወዳጆች የድረሱልኝ ጥሪ አሰማ በጥሪዉ መሰረት ደግሞ የሚከተሉት ወገኖች የማሳተሚያ ገንዘብ ለገሱለት።
  1. አቶ መኮነን ዘለለዉ ከዋሽንግተን                   2. አቶ ኪሮስ አርአያ ገ/ሄር  ከዋሽንግተን
3 . ወ/ሮ ዓወት መኮነን ዘለለዉ USA ዴንቨር ኮሎራዶ      4. አቶ ሙሉአለም ጎይቶኦም አውስትራሊያ
5. ወ/ሮ ፍረ ጎይቶኦም አውስትራሊያ                  6. አቶ ሚኬኤለ ፍቕረ አርአያ ከዋሽንግተን
7. ሄኖክ ሙሉ አለም ገ/ህይወት ዋሽንግተን                           8. አስገደ ገ/ስላሴ ከመቐለ
የምረቃ ዝግጅት
 ፀሃፊዉ መፅሃፉን አሳትሞ ለምረቃ ሲዘጋጅ መፅሃፉን ሊመረቅ ለማሳወቅ ለኢተቪ፣ ለኢዜአ፣ ለድወት እና ኤፍ ኤም ድወት፣ ኤፍ ኤም መቐለ ኤፍ ኤም  ፋና  በሚድያ እንዲያስተላልፉለት ደብዳቤ ፅፎ አስገባ ሁሉም ሚድያዎች ሊያስታልፉለት አልቻሉም በምረቃዉ ቀን ብቻ ኢቲቪ እና ድወት ብቅ ብለዉ ነበር። ግን አልዘገቡም ምክንያቱም አሁን ባሉ  የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቃለ-ቡራኬ ተሰጥቷቸዉ የታተሙና የትግላችንን ጉዞ አዛብቶ የግለዎችና የሕ.ወ.ሃ.ት ቁንጮዎች የሚያሞካሹ  የታጋዮቹን ታሪክ የሚያጎድፉ የሃሰት ታሪክ  የሚደረድሩ መፃህፍቶች የተፃፉ ህዝብና ህዝብን የሚያጋጭ ዘረኝነትን ጠባብነትን የሚቀሰቅሱ መፃህፍት ግን ሁሉም ሚድያዎች በማስተዋወቅ ይጠመዳሉ። የማተሚያ ገንዘብም በሽ ነዉ፡፡ የሚሆንላቸዉ ለመፅሃፍቶች ገበያም አስቀድመዉ ያዘጋጁላቸዋል  የሰማአታት ሃወልት፣ አክሱም ሆቴል አ/አ፣ አክሱም ሆቴል መቐለ፣ ሸራተን አዳራሾች በተፅእኖ ፈጣሪዎችአ ኣዳራሾች በነፃ ይዘጋጅላቸዋል ።
ፀሃፊ ሰለሞን ገ/አረጋዊ ግን ስለ ሓየሎም የፃፈዉ ታሪክ አሁን ባሉ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ቃለ-ቡራኬ (ትእዛዝ )  ስላልተፃፈ  ሁሉም ነገር  ለማግኘት የታደለ አልነበረም ። ሰለሞን የሓየሎም መፅሃፍ ለማስመረቅ ብዙ አዳራሾች ጠይቆ አልተሳካለትም በመቐለ ዘመናዊ ሆቴል  የሚላኖ ሆቴል ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ግን ያዘመናዊ አዳራሻቸዉ ለሓየሎም ያልሆነ ለማን ይሆናል ብለዉ ያ በቀን በብዙ ሺ የሚከራይ አዳራሻቸዉ በነፃ ሰጡት ።






ለ መፅሃፍ ምርቃ ጥሪ
  መጀመሪያ ለመፅሃፉ ምረቃ  የሚያስተባብሩ (የሚያዘጋጁ) 3ት ሰዎች ማለት  ዶ/ር ጌታቸዉ ተፈሪ አቶ አለማየሁ ገዛኸኝ ያሏቸዉ ኮሚቴ ተመሰረተ። የኮመቴዉ ዋና ስራ  ለምረቃ ተሳታፊዎች መጥራት አዳራሽ ማዘጋጀት የምረቃዉ ስብሰባ መምራት መፅሃፉ በምሁራን እንዲገመገም ማድረግ ነበር። ስራቸዉን መበቀጠል መጀመሪያ ከ1300 በላይ የጥሪ ወረቀት አሳትሞ ማሰራጨት የጀኔራል ሓየሎም ፎቶ ያለበት  በተጨማሪም ለምረቃ ተሳታፊ ገደብ ስላልነበረዉ  ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ በዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች ፣የመከላከያ ሚኒስቴር ካምፖች ፣ፖስተሮች ተለጠፉ ።
የጥሪ ወረቀቱ የፀሃፊዉ ስም ስላልነበረዉ የጀኔራል ሓየሎም መፅሃፍ  ስለሚመረቅ ብቻ ነዉ የሚለዉ ሁሉም የትግራይ ክልል መሪዎች አና የህውሓት ማ/ኮሚቴ ከፍተኛ ካድሬዎች የጀኔራል ሓየሎም መፅሃፍ ሊመረቅ ነዉ ተሳተፉ የሚስጥር ድንገት ሆነባቸው እና ያነሱት ጥያቄ ቢኖር ፀሃፊዉ ማነዉ? መፅሃፉስ ምን ይዘት አለዉ? ለመሆኑ ጤናማ መፅሃፍ ነዉ ወይ? ምን ምን ይጠቅሳል ተቃዋሚዎችና ለፖለቲካ መቃወም ብለው የፃፉት እንዳይሆን ?የሚሉ ነበሩ።ሌላ ተራ ታዳሚዎችም መፅሃፉን ማነዉ የፃፈዉ ? የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችስ ያውቁታል ወይ የፖለቲካ ይዘት እንዳይኖረዉ የሚሉ ነበሩ ሌላዉ ቀርቶ አንዳንድ የሓየሎም ቤተሰቦችም እየተፃፈ ያለዉ የሓየሎም መፅሃፍ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ያውቁታል ወይ የሚሉ ጥያቄዎች  ያነሱ ነበሩ።  በመጨረሻም  መጥሪያ ወረቀቱ ለምሁራን ለወጣቶች  በሙሉ ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለነጋዴዎች፣ ለዩኒቨርሲቲዎች ፣ለመከላከያ ሰራዊት፣ ሰሜን እዝ ለኮሌጆች ተሰራጨ ለአቶ አባይ ወልዱ ለትግራይ ክልል አስተዳዳሪም በልዩ የተዘጋጀ የጥሪ ደብዳቤ ተሰጠ የመፅሃፉ ምረቃ ሪቫን እንዲከፍቱም ጭምር ነበር ። የተገለፀላቸው ኣባይ ወልዱ ግን ከመጦፍ ያህል ክብር ኣልሰጡትም ሌሎች ማ/ኮሚቴም ኣልመጡም፡፡
የመፅሃፉ ምረቃ በ8/03/2006 ዓ/ም ዕለተ እሁድ 8:00 ደረሰ የመፅሃፉ ምረቃ ተሳታፊዎች እንደተጠራዉ ብዛት አልመጡም አስቀድመዉ የመጡት ትላልቅ ምሁራኖች ጥቂት ወጣቶች ብቻ መጡ አንዳንድ የሕ.ወ.ሃ.ት ካድሬዎች ወደ አዳራሹ አካባቢ መጥተዉ ይመለሱ ነበር የሚመለሱበት ምክንያት መፅሃፉን የሚመርቁ መሪዎቻቸዉ ያሉ መስሏቸዉ መጥተዉ ግን ደግሞ መሪዎቻቸውን ስላጡ ተመልሰዉ የሄዱ መሆኑ ታውቋል። ከመከላከያ ሚኒስቴርም አልመጡም መፅሃፉን መርቀዉ ይከፍቱታል  የተባሉት አቶ አባይ ወልዱም አልመጡም አንድ የሕ.ወ.ሃ.ት ባለስልጣንም አልመጣም ። ከብዙ ጥበቃ በኃላ በመጨረሻ የክልሉ ም/አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ንግስቲ ወ/ሩፋኤል መጡ። የተሰበሰበ ህዝብ ግን በጀኔራል ሓየሎም አርአያ  የመፅሃፍ ምረቃ  አንድ የሕ.ወ.ሃ.ት መሪና ካድሬ ይቀራል የሚል ግምት አልነበረዉም ተሰብሳቢዉ ጉዳዩን በመመልከት በመድረክ እየወጡ የተበጣጠሰ ንግግር የሓየሎምን ማንነት የሚደሰኩሩት የኖሩት ለጀኔራል ሓየሎም አርአያ አዝነዉ ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ እንደ መጠቀሚያ ነዉ እንዴ ብለዉ  የንዴት ሁኔታ ይታይ ነበር። በተለይ ደግሞ በምርቃኑ ጊዜ የነበሩ ወጣት ምሁራን እጅጉን አዝነዋል።  እንዱሁም  የነበሩ የሓየሎም ቤተሰብም አዝነዋል።
በኔ እምነት የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎች በየመድረኩ  እየወጡ ስለ በትግሉ ወቅት የወደቁ ጀግኖች ሲደሰኩሩ የውሸትና ከአንገት በላይ መሆኑን የማውቅ እንኳን ብሆን የጀኔራል ሓየሎም ታሪክ መፅሃፍ  የሕ.ወ.ሃ.ት መሪዎችና ሎሌዎቻቸዉ ራሳቸውን በማግለላቸዉ ግን የጀግኖች ታሪክ ጎልቶ ሊወጣ የማይፈልጉና ቀናተቾኝ መሆናቸዉ በግልፅ የተጋለጡበት መድረክ ነበር። ይህ ደግሞ ለራሳቸዉ ተጋለጡ እንጂ የሓየሎም ታሪክ መፃፉ ትንሳኤ ሙታን ሆኗል። የሓየሎም ወዳጅ ተደስቷል  ።

የምረቃ ስነ-ስርአት
   መጀመሪያ መፅሃፉ በዶ/ር ጌታቸዉ ተፈሪ  በአራት ደረጃ ከፋፍለዉ ከገመገሙ በኃላ ስለ መፅሃፉ ጠንካራና ደካማ ጎኑ ሳይንሳዊነቱ  ከገመገሙ መፅሃፉ ሓየሎም ከተወለደበት እስከ ወደ ትግል የገባበትና የትጥቅ ትግሉ ጊዜ ታሪክ እስከ ሞተበት  ጊዜ  ብቻ ስለሚተርክ የሓየሎምን አሟሟት ስለማይገልፅ ዶ/ር ጌታቸዉ ግን ‹ ለወደፊት የሓየሎምን አሟሟት የተደበቀ ሚስጥር   ለምን ግልፅ እንዳልሆነ ይህ ሚስጥር  ለወደፊቱ  ምሁራኑ ማጥናት አለባቸዉ ብለዉ ሃሳባቸዉን ትልቅ  የቤት ስራ ለአዲሱ ትውልድ እና ለምሁራኖቹ አስተላለፉ። ከባድ ጥያቄ ነበር፡፡
የዶ/ር ጌታቸዉ ጥያቄ በአዳራሹ ውጥስ የነበረ ምሁር የሁሉም ጥያቄ ነበረ መሰለኝ ሁሉም ለማለት ይቻላል ትክክለኛ ጥያቄ ነዉ የሚል ንግግር ይሰማ ነበር። ከዶ/ር ጌታቸዉ ግምገማ በኃላ የጥቂት ተሳታፊዎች አስተያየት ከተሰማ  መፅሃፉ በወ/ሮ ንግስቲ ወ/ሩፋኤል የትግራይ ክልል ም/ኣፈ ጉባኤ የመፅሃፉ ሪቫን  ተከፈተ፤ ም/ኣፈጉባኤዋ ለሚላኖ ሆቴል ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ላደረጉት አስተዋፅኦ የተዘጋጀ ምስክር ወረቀት ሽልማት ሰጡ።
የ ህ.ወ.ዋ.ሓት መሪዎች የሓየሎም ታሪክ  በመፅሃፍ መልኩ መሰነዱ ለምን ደስ አላላቸዉም ? በኔ እምነት 1ኛ አሁን ያሉ ታጋይ ነበር መሪዎች በ17 አመት የትግል ወቅቱ ጀኔራል ሓየሎምና እንደሱ ያሉ ጀግኖች ሌት ተቀን ታሪክ ሲሰሩ እዚህ ግቡ የማይባሉ ስለነበሩ አመርቂ ታሪክ ስለሌላቸዉ ከቅናት የመነጨ ነዉ 2ኛ አንዳንድ መሪዎችም እንደ ሓየሎም ያለ ወርቃማ ታሪክ እንኳን ባይኖራቸዉ ትንሽ ታሪክ እንኳን ቢሰሩ በተለያዩ መንገድ  ከሓየሎም ጋር በነበረዉ ቂም ምክንያት ጥሩ ግንኙነት ያልነበራቸዉ ናቸዉ።3ኛ ሌሎች የመከላከያ ሰራዊትና የህ.ወ.ሓ.ት ካድሬዎች ወደ መፅሃፉ ምረቃ ያልመጡበት ምክንያት ይዘውት የመጡት የካድሬነት ባሀል ካልተባልክ እንዳትፈፅም ወይ የታገልከውን ብቻ ፈፅም በሚሉት መርህ ባህልና  አድር ባይነታቸዉ የመነጨ ነዉ። 4ኛ የመንግስት ሰራተኛና ነጋዴዎች ምሁራኖች ያልተሳተፉበት ምክንያት አሁንም የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ያልባረኩትና በሚዲያ ያልተነገረለት ስለነበር እንደተለመደዉ ፈርተውና ሰግተዉ ነዉ።ብዙሃን  መገናኛም አስቀድመዉ ማስታወቂያ ያልሰሩበት የሚታዘዙት አሁን ባሉት የህ.ወ.ሓ.ት ማ/ኮሚቴ ስለሆኑ ያለ ትእዛዝ ስለማይሰሩ ነዉ።  5ኛ ከላይ እንደጠቀሰኩት ሓየሎም ከሞተበት ቀን ጀምሮ ለተለያዩ መድረኮች እንደ ፖለቲካ  ፍጆታ መጠቀሚያነት  ለማነሳሳት ሊጠቀሙበት ለጀኔራል ሓየሎም አርአያ ወዳዋቸዉ ሳይሆን ለጊዜዉ ለፖለቲካ ፍጆታ እንደመጠቀሚያ መሆኑን የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች  በዚህ የጀኔራል ሓየሎም ታሪክ የሚተነትነዉ መፅሃፍ ምረቃ ላይ ተጋልጠዋል። ይህ ደግሞ የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ነገሮች ለጊዜያዊ ጥቅም መናገር የተለመደ ባሀሪያቸዉ ነዉ።
ሌላዉ  ቀርቶ እጅጉን የሚያስገርም የሚያሳዝን የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ተፅእኖ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ የሚያስረዳ የጀኔራል ሓየሎም ቤተሰብም በመቐለ ከተማ እያሉ ሳይሳተፉ የቀሩ ኣሉ ።ለዚሁ እንደ ምሳሌ  የጀኔራል ሓየሎም አርአያ እህት ወ/ሮ አልማዝ አርአያ የፌዴራል ፓርላማ  የህዝብ ተወካዮች የሆነች እንዳጋጣሚ ሁኖ የህ.ወ.ሓ.ት የሴቶች ሊግ ጉባኤ መቐለ መጥታ ሰንብታ መፅሃፉ  እሁድ 8:00 ሰአት የሚመረቀዉ  ተሳተፊ ተብላ ተነገሯት ኢትዮጵያ አየር መንገድ  300.00 ብር ስለሚቀጣኝ መሄድ አለብኝ ብላ እሁድ ከሰአት በፊት አ/አ በረረች። ወ/ሮ አልማዝ ደሃ ሁና 300.00 ብር ቅጣት በዝቶባት አይደለም ችግሩ የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች በአባሎቻቸዉ ላይ ምን ያህል ነፃነታቸዉ እንደሚነጥቋቸዉ እና ሽብር እንደሚፈጥሩባቸውና አንዱ እንደማስረጃነት ማረጋገጫ ነዉ።ህ.ወ.ሓ.ት የመጣበትን ጉዞ ልጅ፣ አባት፣ እናት ባልና ሚስት ዘመድ አዝማድ እየለያየ እርስ በርሱ እንዳይጠጋጋ እያደረገ ነበር የመጣዉ። ወ/ሮ አልማዝ አርአያም የወንድማቸዉ ጀኔራል ሓየሎም ወርቃማ ታሪክ የያዘ መፅሃፍ ሲመረቅ ይቅርና በዛች የምረቃ ዕለት በ2:00 ሰአት ልዩነት አ/አ ሊሄዱ ይቅር ከ አ/አ መቐለ የትራንስፖርት ለሆቴል ከፍለዉም በምረቃዉ መገኘት ነበረባቸዉ ግን ለዚች ርካሽ አለምና ለእንጀራቸዉ ሲሉ የጀኔራል ሓየሎም መድረክ ረግጠዉ ሄዱ። መጥፎ ቀን ውለዋል   የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ቢሆኑ ለጀኔራል ሓየሎም አልሆኑም።  ም/ኣፈ ጉባኤዋ የመጣችበት ምክንያት በብዙ ካልኩሌሽን ታስቦበት አሁንም ትንሽ የፖለቲካ ፍጆታ ብናገኝባት ብለዉ ነዉ። ወ/ሮ ኣልማዝ ኣርኣያ መቀሌ ከመምጠጣታ በፊት መጥርያም ደርሳት ነበር ምን ይሁንና…..
በመጨረሻ  በጀኔራለ ሓየሎም ታሪክ ለመፃፍ ብዙ ወጥመዶች  በጣጥሶ  ሃቀኛ ታሪክ ለህዝብ እንዲደርስ ያደረገ ፀሃፊ ሰለሞን ገ/አረጋዊ እጅጉን ምስጋና ይገባዋል። ሰለሞን አሁንም በትግርኛ የተፃፈዉ የጀኔራል ሓየሎም አርአያ ታሪክ ባማርኛ የተተረጎመዉ ቶሎ ብሎ ታተሞ ለመላዉ ኢትዮጵያዊ እንዲደርስ ማድረግ ሳትታክት ተሯሯጥ። ሃቀኛ ታሪክን ሊቀብሩ የሚፈልጉት አይሳካላቸውም ዘመኑ 21ኛ ክፍለ ዘመን ነውና። የጀኔራል ሓየሎም አርአያ ታሪክ መደበቅና ለሁሉም ፀረ-ፋሽስታዊ ደርግ ለተሰዉ አርበኞች ኢትዮጵያውያን  ታሪክ መስረቅና  እንደ መቅበር ይቆጠራል።
በመጨረሻ ኣንድ ኣንድ ወገኖች ፀረ ፋሽሽት ደርግ የተደረገው ጦርነት የእርሰ በርስ ጦርነት ብለው ይተረጉሙታል በኔ እምነት ግን የደርግን ፋሺዝም መዋጋት ከፋሽሽታዊ ጣልያንና ከሌሎች የባእድ ወራሪዎች ከተደረገው ጦርነት እኩል ኣድርጌ ነው የምመለከተው በማናቸውም ፓርቲ ተሰልፈው ከህውሓት ከኢህኣፓ፤ ከግግሓት ከጠራናፊት፤ ከኢዱዩ፤ ከኦብነግ፤ ከኦነግ፤ ከጋንቤላ፤ ከኣፋር፤ ከሱማሌ ፓርቲዎች ተሰልፈው ለደርግ እየተዋጉ የነበሩ ሃይሎች ኣርበኞች ኣድርጌ ነው የምመለከታቸው፡፡ እርሰ በርስ ጦርነት ተብሎ መገለፅ የለበትም ለደርግ ለመቃወም በርሃ ወጥተው በማይረባ ልዩነቶችና ኣለመቻቻል በተፈጠረው እርሰ በርሳቸው ጦርነት የተፋጁት ነው መውቀስ ያለባቸው፡፡ ይህ እርስ  በርስ ጦርነት የምለው ያለሁ ከ 1983ዓ.ም የነበረ ነው፡፡ለሌላ ትርጉም እንዳይሰጠው፡፡

No comments:

Post a Comment